es
Feedback
YeneTube

YeneTube

Ir al canal en Telegram

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Mostrar más
2025 año en númerossnowflakes fon
card fon
107 362
Suscriptores
-5724 horas
-4017 días
-2 12730 días
Archivo de publicaciones
Photo unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
Mostrar todo...
4👎 1
የውድቀት አዋጅ! በድሉ ዋቅጅራ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮጵያውያን ለደህንነታቸው የቆመ፣ ሀላፊነት የሚሰማው አስተዳዳሪ የሚያገኙት መቼ ነው?! (በድሉ ዋቅጅራ) በመጀመሪያ ከአርባ በላይ በሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ተምረውም/ሳይማሩም ተመርቀው፣ወይም ትምህርታቸውን 12ኛ ላይ አቁመው፣ እዚህ ግባ የሚባል የስራ እድል በሌለባት ሀገር የሚበተኑ ወጣቶች፣ ማህበራዊ ሚዲያን እንደስራ ፈጠራ/እድል በመጠቀም እራሳቸውን በገቢ ለመደጎም የሚያደርጉትን ጥረት በጅምላ አልቃወምም፡፡ ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆኑኝ በቁጥር ጥቂት የማይባሉት፣ ለይዘት ፈጠራ ያጠራቸውን እውቀትና የህይወት ልምድ ድንቁር፣ የአእምሮና የስነልቦና ችግር በወለደው ድፍረትና ንቀት ተክተው ‹‹የደደቡትና የሰገጡት›› ናቸው፡፡ እንደሰመረ ባሪያው አሌክስ አብረሀም ወዘተ. ያሉ ሰዎች በቲክቶ በሚሰሩት ጠቃሚ ይዘት ስማቸው እንኳን ሳይጠራ፣ አለመለወጥን፣ አእምሮን ያለመጠቀምን አርማ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ወጣቶችን መኪና የሚሸልሙ፣ በሚሊየን የሚቆጠር ተከታዮች እንዲያገኙ የሚያግዙ ተቋማትን መመልከት እጅግ በጣም ይሸማቅቃል፤ በሀገርና በማህበረሰብ ላይ ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ ይሁን እንጂ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም፣ ‹‹በሀገር እና በማህበረሰብ ላይ ተስፋ መቁረጥ፣ ሀገርን ለደንቆሮዎች፣ ለደፋሮችና ለአንባገነኖች አሳልፎ መስጠት ነው፡፡›› ይሉ እንደነበረው፣ ይህን ‹‹እንዳሻው›› ብሎ ማለፍ ያዳግታል፡፡ ምን አይነት ተቋማት ናቸው ይህን የሽልማት ፕሮግራም የሚያዘጋጁትና በገንዘብ የሚደግፉት? ለነዚህ ተቋማት ሀገርና ማህበረሰብ ከሸቀጣቸው ማራገፊያነት የዘለለ ትርጉም የላቸውም ማለት ነው? በነገራችን ላይ የከሳቴ ብርሀን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት፣ ‹ሰገጠ› የሚለውን ቃል፣ ‹‹ክፉ ሰው፤ ሞገደኛ፤ የሰውን ነገር የማይቀበል፤ . . .›› ሲል ይፈታዋል፡፡ የሽልማቱ ሲገርመን፣‹‹ሰግጥ - ፈምስ›› የሚባል ሀገራዊ ጉዞ፣ አዶናይን ይዞ፣ ድንቁርናን ተመርኩዞ፣ ሊዘጋጅ ስለመሆኑ ጋዜጣዊ መግለጫ መሰጠቱን ተመለከትኩ፡፡ ‹‹በኤ.አይ የተሰራ ነው በሉኝ›› ብዬ፣ ሰዎች ጋ ደወልኩ፡፡ የተመኘሁት ሳይሆን ቀርቶ እውነት ነው፡፡ ልጆችና ወጣቶች በተለያየ ምክንያት የነዚህ ቲክቶከሮች ተከታይ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እኔን እንቅልፍ የነሳኝ ፈጽሞ በማልጠብቀው ሁኔታ፣ የጋዜጣዊ መግለጫው ተናጋሪ ወይዘሮና የሰራዊት ፍቅሬ ጉዳይ ነው፡፡ ይህች ሴት ለልጆችዋ፣ ‹ደድቡ፣ ሰግጡ› ትላለች ማለት ነው? በአፍለኛው የሬዲዮ ድራማ አሀዱ ብሎ፣ ብዙ ውጣውረዶችን አልፎ፣ እዚህ የደረሰው ሰራዊት ፍቅሬ፣ የመጣበት የሙያ ትግል ጉዞ ላይ ውሀ ከልሶ፣ ‹ሰግጥ - ፈምስ› የሚል ሀገራዊ ዘመቻ ፊታውራሪ ለመሆን የተነሳው ምን አስልቶ ነው? ለመሆኑ ሰራዊት የዚህ አካል መሆኑ ለልጆቻችን የሚያስተላልፈው መልእክት፣ ‹እዚህ የደረስኩት፣ ‹ደድቤ - ሰግጬ ነው› የሚል እንደሆነ ያውቃል? የትምህርት ስረአታችን ማጥ ውስጥ ነው! በሙስና ተጨማልቀናል! የሀይማኖት ተቋሞቻችን ረክሰው አለማዊ መድረኮችን እየመሰሉ ነው! . . . ይህ ሁሉ አልቆረቆራቸውም፤ ለዘመቻ አላነሳሳቸውም፡፡ ‹‹ወርቅ በወርቅ›› ብሎ ፊልም የሰራበት፣ ሀገራችን የምትታወቅበት አትሌቲክስ ተዋርዶ፣ ከአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ያለ ወርቅ መመለሳችን እንኳን ሰራዊት ፍቅሬን በቁጭት ለተግባር አላነሳሳውም፡፡ ሰራዊትን ለሀገራዊ ዘመቻ ያነሳሳው የሀገሪቱ የደደቦች፣ የሰገጤዎች ማነስ ነው፡፡ በመጨረሻ ይህ ጉዞ የሀገራዊና ማህበረሰባዊ ውድቀታችን ይፋዊ አዋጅ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገርና ህዝብ አስተዳድራለሁ የሚል መንግስት፤ ባህል ሚንስቴር፣ ትምህርትት ሚኒስቴር፣ በወጣቶች፣ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ሚንስቴሮች፣ ካሉ (አሉ ብዬ አምናለሁ) ይህ ጉዞ መታገድ አለበት፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሀይማኖት ስም፣ በአነቃቂ ንግግር ስም፣ በይፋ ማህበረሰባዊ እሴቶቻችንን የሚቃረኑና የዘቀጡ፣ ለማጭበርበር የቀረቡ ይዘቶች በማቅረብ፣ በህዝብ በተለይ ባልተማረው ማህበረሰብ ስነልቦና ላይ የሚጫወቱ የማህበራዊ ሚድያ ይዘት አቅራቢዎች ላይ ህጋዊና ተገቢ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል።
Mostrar todo...
138👍 56🔥 6😁 6
Photo unavailableShow in Telegram
#ትግራይ ኃይሎች ከምክትል ፕሬዝዳንቱ ጋር ንግግር ቢያደርጉም የፕሬዚዳንት ጽ/ቤትን ለቀው ለመውጣት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተገለፀ #መቀሌ፡ የትግራይ ኃይሎች ዛሬ ሐሙስ ጠዋት በመቀለ የሚገኘውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ዙሪያ ለአጭር ጊዜ ከበባ አድርገው በቅጥር ግቢው ዙሪያ እንቅስቃሴና ትራንስፖርት ተስተጓጎለ። አዲስ ስታንዳርድ እንዳረጋገጠው፣ ኃይሎቹ ወደ ጽህፈት ቤቱ የሚወስደውን መንገድ በመዝጋት ጽ/ቤቱን ከበዋል። በዚህም የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት እና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሰራተኞች እንዳይገቡ ከልክለው ውጪ እንዲቆዩ አስገድደዋል። የአዲስ ስታንዳርድ ምንጮች እንደጠቆሙት፣ ወደ 70 የሚጠጉ የአርሚ 31 ወታደሮች በክስተቱ ውስጥ ተሳትፈዋል። በስፍራው የሚገኝ የአዲስ ስታንዳርድ ዘጋቢ እንዳረጋገጠው፣ ኃይሎቹ በኋላ ላይ የከበቡትን አካባቢ መንገዶች ለቀው በመውጣታቸው ትራፊክ እና መደበኛ እንቅስቃሴ እንዲቀጥል የተደረገ ሲሆን ከፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት መግቢያ በር ግን ለወው አልወጡም። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዝዳንት አማኑኤል አሰፋ ከኃይሎቹ ጋር መነጋገራቸው የተገለፀ ቢሆንም፤ ኃይሎቹ ከፕሬዝዳንቱ ጋር ስብሰባ ለማድረግ ካልተፈቀደላቸው በስተቀር ለመልቀቅ ፍቃደኛ አልሆኑም ሲሉ ምንጮች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል፡፡ @Yentube @Fikerassefa
Mostrar todo...
36👍 6😁 3👎 1😭 1
Photo unavailableShow in Telegram
መደበኛ ሎተሪ 1752ኛ ዛሬ ህዳር  25 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በእድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል። @Yenetube @Fikerassefa
Mostrar todo...
9👍 4🔥 1
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተፈረመ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተፈርሟል፡፡ ስምምነቱን የክልሉ ርዕሰ መሰተዳድር አረጋ ከበደ እና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን በመወከል ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ተፈራርመዋል። በአፍሪካ ህብረት እና በኢጋድ አደራዳሪነት ወይይት እና ድርድር ሲካሄድ መቆየቱ የተገለጸ ሲሆን፥ በዚሁ መሰረት የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተፈርሟል፡፡ ርዕሰ መሰተዳድሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ ዛሬ ለክልላችን ህዝብ የመጀመሪያው ትልቅ የሰላም ኩነት የተካሄደበት ቀን ነው ብለዋል። ከግጭት አሸናፊም ተሸናፊም የለም፥ ከሰላም ሁሉም ያተርፋል፥ ስምምነቱ ለሰላም ወዳድ ህዝባችን ትልቅ እፎይታን ይሰጣል ነው ያሉት፡፡ የህዝብና የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ለመጡ ወንድሞቻችን እንደ መንግስት አድናቆትና ክብር አለኝ ብለዋል፡፡ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን (አፋሕድ) በመወከል ስምምነቱን የተፈራረሙት ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ባደረጉት ንግግር፥ ማንኛውም ግጭት መጨረሻው ውይይትና ድርድር ነው ብለዋል። ችግሮችና የሀሳብ ልዩነትን በንግግር መፍታት ፖለቲካዊ ሽንፈት ሳይሆን ጥበብና ብልጠት መሆኑን ገልጸው፥ ችግሮችን ለመፍታት ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ማበር ተገቢ አለመሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊካ አዳዲ በበኩላቸው፥ ስምምነቱ የሀገሪቱን ቀጣይ መዳረሻ የሚያቃና ነው ብለዋል። @Yenetube @Fikerassefa
Mostrar todo...
😁 40 35👍 8😭 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
4🔥 1
ማስታገሻ በሚል ማንኛውም መድኃኒት ከሃኪም ትዕዛዝ ውጪ ከመውሰድ ህብረተሰቡ ሊጠነቀቅ እንደሚገባ ተነገረ መድሃኃኒቶችን ያለ ሀኪም ትዕዛዝ መጠቀም እንዲሁም ከታዘዘው መጠን በላይ መውሰድ ለጸረ ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድ እንደሚያስከትል በወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የላብራቶሪ ዳይሬክተር እና የጸረ ተህዋሲያን መላመድ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ  የሆኑት ባህረዲን ዳሪ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድ ምክንያት ታማሚዎች ታክመው መሄድ ከሚገባቸው በላይ በጤና ተቋማት እንዲቆዩ ላልተፈለገ ወጪ እንዲሁም ለከፋ የጤና ችግር ተጋላጭ እንደሚያደርጉ  እና በሽታ የመከላከል አቅም እንደሚቀንሱ   ተጠቁሟል ። የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች ከህክምና ባለሙያ  ትዕዛዝ ውጪ መውሰድ የጎንዮሽ  ጉዳቶች እንደሚያስከትል ተጠቁሟል።  ሰዎች ለራስ ምታት እና ለተለያዩ ህመሞች ከፓራስታሞል ጀምሮ ዳይክሎፌን እያሉ የሚወስዷቸው መድሃኒቶች  ደረጃቸው ከፍ እያለ በሄደ ቁጥር የሚያስከትለው ችግርም እንደሚጨምር ተጠቁሟል።በተጨማሪም በንጽህና ጉድለት የጸረህዋሲን ጀርሞች መላመድ  ከታማሚ ወደ ታማሚ ስለሚተላለፉ ንጸህናን መጠበቅ እንደሚገባ ተነግሯል። በአለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ በሰዎች ፣በአካባቢ እንዲሁም በእንስሳት ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳትን የሚያስከትል ሲሆን ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር እንዲሁም ሌሎች ጉዳቶችንም ለመቆጣጠር  የሚመለከተው አካል ሁሉ በትኩረት ለለሰራበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑ ተጠቁሟል።ማንኛውም ሰው ህመም ስለተሰማው ብቻ ማስታገሻ በሚል ማንኛውንም አይነት መድሃኒቶች  መውሰድ እንደሌለበት እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሃገራት ላይ ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት  እንደሚያደርስ  በወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የላብራቶሪ ዳይሬክተር  የጸረ ተህዋሲያን መላመድ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ  የሆኑት ባህረዲን ዳሪ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በወራቤ ሆስፒታል በሽታወን የመከላከል ስራ በትኩረት በኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። @Yenetube @Fikerassefa
Mostrar todo...
16
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
Mostrar todo...
4🔥 3
Photo unavailableShow in Telegram
ተጨማሪ መረጃ ከመቀሌ የትግራይ የጸጥታ ኃይሎች አባላት የጊዜያዊ አስተዳደሩን ቢሮ መክበባቸውን ለቢቢሲ ትግርኛ ገልፀዋል። የትግራይ የጸጥታ ኃይሎች አባላት “የደመወዝ ክፍያ ዘገየ” በሚል ቅሬታቸውን መሳሪያዎቻቸውን ይዘው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ህንፃን ከበውታል። የአርሚ 31 ጦር 71 አባላት ትናንት ረቡዕ ምሽት ከአራጉሬ (እንደርታ) አካባቢ ወደ መቀሌ መጥተው አመፅ እንዳስነሱ ታውቋል። ዛሬ ጠዋት የአስተዳደር ህንፃውን ከበውታል። ከዚህ በተጨማሪ የ “አርሚ 31 ኮር 312 ክፍለ ጦር ረመፅ የሚባለው ዛሬ ህዳር 25/2018 ዓ.ም 5:05 የመሳሪያ ማስቀመጫ መጋዘን በመስበር ትጥቃቸውን በመታጠቅ ከነሩበት ቦታ ወደ መቀሌ በመገስገስ ላይ መሆናቸውን ምንጮች ጠቁመዋል። የፌደራል መንግሥቱ በጀት በወቅቱ ባለመልቀቁ በትግራይ ክልል ደመወዝ በወቅቱ መክፈል እንዳልተቻለ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲሁም ህወሃት በተናጠል ለፌደራል መንግስቱ ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል። @Yenetube @Fikerassefa
Mostrar todo...
27👀 3
Photo unavailableShow in Telegram
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተወያዩ! የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ "የአፍሪካ ቀንድ ሰላም" እና "ቀጣናዊ መረጋጋትን" በተመለከተ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የዋሽንግተን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስታወቀ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው አጭር መገለጫ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይት የተደረገው ረቡዕ ኅዳር 24/2018 ዓ.ም. መሆኑን አመልክቷል። ይህ የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ውይይት በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደ ነው። በውይይቱ ላይ ሁለቱ ባለሥልጣናት፤ ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ መረጋጋት ያላቸውን ቁርጠኝነት እና ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም መሠረት በመጣል ዙሪያ መነጋገራቸውን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መግለጫ አሳውቋል። የኢትዮጵያን ውስጣዊ ጉዳዮች በተመለከተ ንግግር ስለማድረጋቸው በመግለጫው ላይ አልተጠቀሰም። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩቢዮ መካከል የተደረገውን ውይይት በተመለከተ በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ምክትል ቃል አቀባይ በኩል የተላለፈው መልዕክት በአንድ አረፍተ ነገር የተጠቃለለ እና ዝርዝር ጉዳዮችን ያልያዘ ነው። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር የተደረገውን ንግግር በተመለከተ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጽሕፈት ቤት በኩል እስካሁን በይፋ የተገለጸ ነገር የለም።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩቢዮ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ቀጣናዊ የሰላም ጉዳዮችን በተመለከተ ውይይት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። https://www.bbc.com/amharic/articles/c14vk5nplrdo @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
20👍 5👎 3😭 3
Photo unavailableShow in Telegram
ሰበር ዜና ባሁኑ ሰአት በመቀሌ የጀነራል ታደሰ ወረደ ቢሮ በአርሚ 31 ታጣቂዎች መከበቡ ተሰምቷል። በትናንትናው ዕለት አንዳፍታ ሚዲያ ጀነራሉ ጫና ውስጥ መግባታቸውን ዘግቦ ነበር። @Yenetube @Fikerassefa
Mostrar todo...
32😭 11👀 11
ከአየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጠ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) በእስራት እንዲቀጡ ወስኖ የታሰሩት በቂ ስለሆነ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጠ። የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል)፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን፣ ኤልያስ ድሪባ እና ይዲድያ ነጻነት ላይ በነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 3፡30 ሰዓት ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ መቐለ ከተማ ለመጓዝ አውሮፕላኑ ለበረራ ዝግጁ ቢሆንም የአየር ሁኔታ ለበረራ አዳጋች በመሆኑ በረራው ቢደረግ የሚያደርሰውን ከባድ አደጋ ለመከላከል ጉዞው ተሰርዞ መንገደኞች ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ሲነገራቸው በረራው በግድ መደረግ አለበት አንወርድም በማለት ቀሪ ተሳፋሪዎችም እንዳይወርዱ በመክልከል አሳድመዋል በሚል በዝርዝር ጠቅሶ ክስ አቅርቦባቸው ነበር። በተጨማሪም ዐቃቤ ሕግ 1ኛ ተከሳሽ ጆን ዳንኤል ላይ በ3ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀጽ 13 ንዑስ ቁጥር 3 ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ክስተቱን ቲክቶክ በተባለ ማህበራዊ ሚዲያ በተንቀሳቃሽ ምስል ቀርጾ በቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ የሚል ክስ አቅርቦበት ነበር። ተከሳሾቹ በተከሰሱበት የህግ አንቀፅ ጥፋተኛ የተባሉ ሲሆን ችሎቱ በዛሬው ዕለት የዐቃቤ ሕግን የቅጣት ማክበጃ እና የተከሳሾችን የቅጣት ማቅለያ መርምሮ ውሳኔ አሳልፏል። በዚህም ተከሶሾቹ የተከሱበት የህግ አንቀፅ ቀላል እስራትን የሚያስከትል በመሆኑ 1ኛ ተከሳሽ በአንድ አመት ከአራት ወር፤ 2ኛ፣ 3ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች በስምንት ወር እንዲሁም 4ኛ ተከሳሽ በ10 ወር እስራት እንዲቀጡ ወስኗል። በመሆኑም ተከሳሾቹ በእስር ላይ የቆዩበት ጊዜ ተሰልቶ ተከሳሾቹ እንዲፈቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ውሳኔ አሳልፏል። @Yenetube @Fikerassefa
Mostrar todo...
66👍 9👎 3😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኦፌኮ ከምዝገባ ላለመሰረዝ ሲል 10 እጮዎችን ብቻ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እንደሚያሳትፍ አስታወቀ! የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከምዝገባ ላለመሰረዝ ሲል ”ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አስር እጩዎችን ብቻ ማስመዝገቡን ማስመዝገቡን አስታወቀ።የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕ/ር መራራ ጉዲና ፓርቲያቸው ሕጋዊ ግዴታውን ለመወጣት ብቻ 10 የእጩዎች ስም ዝርዝር ማስገባቱን ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል። የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ትላንት ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ፣ ማዕከላዊ ኮሚቴው ቅዳሜ ኅዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ፣ በ7ኛ ዙር የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ ላይ በአዲስ አበባ ውስጥና በአንዳንድ ጥቂት አከባቢዎች ብቻ ሊሳተፍ መወሰኑን አስታውቋል። ይሁን እንጂ ፓርቲው እስከምርጫዉ ጊዜ ድረስ ሁኔታዎች ተስፋ ሰጪና መሠረታዊ በሆነ መንገድ ከተለወጡ ዉሳኔዉን እንደገና እንደሚያጤን ማዕከላዊ ኮሚቴዉ ወስኗል ሲልም አክሏል፡፡ ይህን ተሳተፎ “ምሳሌያዊና ስልታዊ” ሲል የገለጸው ፓርቲው፣ ውሳኔው የተላለፈው፣ በመላ አገሪቱ ነጻ፣ ፍትሐዊና ሰላማዊ ምርጫ ለማካሄድ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ “አስቻይ ሁኔታ እንደሌለ” በመረጋገጡ ነው ብሏል፡፡ በኦሮሚያ፣ በአማራና በሌሎችም ክልሎች በግልጽ በሚታዩ ወታደራዊ ግጭቶች ምክንያት በስፋት መፈናቀልና በአሰቃቂ የህይወት መጥፋት መኖሩ የተወሰነ ተሳትፎ ብቻ ለማድረድ ላሳለፈው ውሳኔ ዋና ምክንያት ነው ሲል ኦፌኮ ገልጿል። ተጨማሪ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=10048 @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
10👎 5
Photo unavailableShow in Telegram
"ከ4 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ማስመዝገብ ተችሏል" -የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በባለሃብቶች ይነሱ ለነበሩ ጥያቄዎች ተግባራዊ ምላሽ በመሰጠቱ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ እንዲጨምር ማስቻሉን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል።በሂደት ከተመለሱ ጥያቄዎች መካከል 14 ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች መቀየር መቻሉ አንዱ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ተናግረዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ይነሱ ለነበሩ ጥያቄዎች ተግባራዊ ምላሽ መሆኑን ሌላ ተጠቃሽ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡እንዲሁም ከውጭ ምንዛሪ ጋር ተያይዘው ይነሱ ለነበሩ ጥያቄዎች በኢኮኖሚ ማሻሻያው መሠረት ለውጦች መገኘታቸውን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻዎችን ማስፋቱ ድርጅቶች በቀላሉ ምርታቸውን ወደ ተለያዩ ሀገራት መላክ እንዲችሉ በማድረግ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ ላይ የጎላ ሚና አበርክቷል ብለዋል።በኮሚሽኑ የሚሰጠው የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ፈጣን፣ ግልጽና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት መስጠት ማስቻሉን አመላክተዋል። እንደ ኢዜአ ዘገባ በአጠቃላይ በዘርፉ በተደረጉ የማሻሻያ ሥራዎች በእ.ኤ.አ 2024/2025 ከ4 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ማስመዝገብ ተችሏለል። [ቅዳሜገበያ] @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
6😁 6
Photo unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
Mostrar todo...
Repost from YeneTube
Photo unavailableShow in Telegram
Summer realstate በካሬ 73,318 ብር ብቻ 10% ቅድመ  ክፍያ 50% ባንክ የተመቻቸላቸው Location እንግሊዝ ኢምባሲ አጠገብ ✅ አፓርትመንቶች ቤቶች  እንግሊዝ  ኢምባሲ  ደስ እሚል እይታ ያላቸው ቤቶች በሺያጭ ላይ ነን ከባለ 2 መኝታ - ባለ 4 መኝታ ደረስ ☑️ እስታንድ ባይ ጀኔኔትር ☑️5ሊፍት ያለው ☑️የዋና ገንዳ ☑️ፓርኪንግ ☑️ጅም, እስፓ ,ሚኒ ማርኬት, ☑️ቴራስ   ✅  ባለ 2 መኝታ 134.6 ካሬ 137.6  ካሬ 155.6  ካሬ ✅  ባለ 3 መኝታ 183.8 ካሬ 156.9 ካሬ 197.8 ካሬ ✅ ባለ 4 መኝታ 260 ካሬ ለበለጠ መረጃዎች 📞  0912355631
Mostrar todo...
4
Repost from YeneTube
Photo unavailableShow in Telegram
አዲሱ #Kiwiday መተግበሪያ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው እና በአይነቱ ብቸኛው የሆነ ትምህርታዊመተግበሪያ ነው። ለ1ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ሁሉንም ነገር  ያለዉ መተግበሪያ ነው። በአዲስ ሥርዓተ ትምህርት ላይ የተመሠረተ እና በአግባቡ ጥቅም ላይ ከዋለ የተማሪዎችን ውጤት ከ 75% በላይ እንደሚቀይር ባለሙያዎቻችን ይተነብያሉ። ✅ ለኦሮሚያ፣ ለአዲስ አበባ፣ ለአማራ እና ለሁሉንም ክልል ተማሪዎች  ✅ ለወላጆች እና ለተማሪዎች የኪዊ አፈጻጸም ክትትል (KPT) ✅ ያለ ኢንተርኔት ለአንድ ሙሉ ዓመት ይሰራል ✅ አማርኛ / አፋን ኦሮሞ / እንግሊዝኛ ይጠቀማል ✅ ያልተገደበ የኪዊዴይ ፈተና (KQ) በየቀኑ ✅ የተደራጁ የኪዊ ማስታወሻዎች ፣ሁሉም  የመማሪያ መጽሐፍት እና ማጣቀሻዎች ✅ አንድ መተግበሪያ = አንድ ተማሪ የሚያስፈልገውን ሁሉ የያዘ ✅ ቀላል፣ ፈጣን እና ተማሪዎች ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ያግዛል ✅ አስጠኚን ሊተካ የሚችል ✅ Free: 0 ብር ለ አንድ ዐመት ✅ Basic: 200 ብር ለ አንድ ዐመት ✅ Premium: 1000ብር ለአንድ ዐመት ከGoogle Play  ለማዉረድ ▶️https://play.google.com/store/apps/details?id=com.KiwiEducation.learningApplication ⚠️ለመጠቀም ከመጀመርዎ በፊት ወይም የሚፈልጓቸውን ነገሮች ካላገኙ፡ ‹የትምህርት ይዘቶችን› ን ተጭነው ያውርዱ። ቻናላችንን ይቀላቀሉ  በእነዚህ ያግኙን Phone number: 0981333522 Telegram: https://t.me/Kiwidayapp Website: www.kiwielearning.com Tiktok: https://www.tiktok.com/@kiwidayapp Youtube: https://www.youtube.com/@Kiwidayapp #Education #Ethiopia
Mostrar todo...
4👍 1
ለትግራይ ክልል ከፌደራል መንግስት በየወሩ ይላክ የነበረው በጀት፣ ከጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት ሁለት ወራት ሙሉ በሙሉ መቆሙን የክልሉ ፕላን ኮሚሽን ኃላፊ ወ/ሮ ሃንሳ ተኽላይ ለቢቢሲ ገለጹ። ይህ የሆነው በማዕከላዊ መንግስት እና በህወሓት መካከል ያለው የፖለቲካ ውጥረት "የፕሪቶሪያውን ስምምነት ለአደጋ እያጋለጠው ነው" በተባለበት ወቅት መሆኑ የጉዳዩን አሳሳቢነት ጨምሮታል። ኃላፊዋ እንዳሉት ከቆመው በጀት መካከል፣ ከጦርነቱ በኋላ በየወሩ ይከፈል የነበረው 844 ሚሊዮን ብር "የካፒታል በጀት" (በፌደራል መንግስት በኩል በክልሉ የሚተዳደር) ይገኝበታል። ለ2018 ዓ.ም. ለትግራይ ክልል ከተመደበው 18.8 ቢሊዮን ብር ውስጥ፣ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ምንም አይነት ክፍያ እንዳልተፈጸመ ወ/ሮ ሃንሳ ተናግረዋል። በተጨማሪም፣ ለአዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ ተብሎ ለመስከረም ወር የተላከው 481 ሚሊዮን ብር "በነበረው ሰፊ ልዩነት" ምክንያት ሳይከፈል መተላለፉን ገልጸዋል። አሁን ግን "የጥቅምትም ሆነ የኅዳር በጀት አልመጣም" ብለዋል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጄነራል ታደሰ ወረደ በበኩላቸው፣ በሕዳር ጽዮን በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በጀት ባለመምጣቱ አስተዳደሩ "ወርኃዊ ደመወዝ'ኳ መክፈል ለማንችልበት ደረጃ ደርሰናል" ሲሉ መናገራቸውን በዘ-ሐበሻ ዜና መዘገባችን ይታወቃል። በጀቱ በመቋረጡ ምክንያት፣ በተለይም በገጠር ወረዳዎች የመንግስት አገልግሎት መቋረጥ መጀመሩን የገለጹት ወ/ሮ ሃንሳ፣ ክልሉ የራሱን ገቢ ለመሰብሰብ እንኳን በጀት እንደሚያስፈልገው ጠቁመው "በከባድ ችግር ውስጥ ነን" ብለዋል። ስለ በጀት መቋረጡ ምክንያት ከፌደራል መንግስት (ገንዘብ ሚኒስቴር) ለማብራሪያ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ሲል ቢቢሲ ዘግቧል። ሌሎች የአራት ኪሎ ቤተ መንግስት ምንጮች ግን ለትግራይ ሕዝብ የሚላከውን በጀት የክልሉ መሪዎች ለታቂዎቻቸው ደሞዝ እየከፈሉበት የሚል ግምገማ መኖሩንና አሁን በጀቱ ቆመ የተባለው ከዚህ ጋር በተያየዘ ነው ሲሉ ይናገራሉ። @Yenetube @Fikerassefa
Mostrar todo...
49👎 4👍 3😁 1
በኮንጎ 43 ሰዎች በኢቦላ ሕይወታቸው ማለፉ ተነገረ።
የኢቦላ ቫይረስ በኢትዮጵያ ከተከሰተው ማርበርግ ቫይረስ ጋር ተመሳሳይ ባህሪ ያለው በሽታ ነው።
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል። የሀገሪቱ ጤና ሚኒስትር ሮገር ካምባ 53 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ፣ 43 የሚሆኑት ህይወታቸው አልፏል ብለዋል። ወረርሽኙ እንዳይስፋፋ ለመከላከል ከ27,000 በላይ ለሚደርሱ ዜጎች ክትባት ተሰጥቷል ተብሏል። @Yenetube @Fikerassefa
Mostrar todo...
8😭 2👍 1