Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
Ir al canal en Telegram
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Mostrar más2025 año en números

228 851
Suscriptores
-13024 horas
-9947 días
-4 55830 días
Archivo de publicaciones
👆②✍✍✍ "…ትግሬዎቹ የራቡን ምክንያት ከአቢይ አሕመድ እና ከወያኔ ትከሻ ላይ አውርደው በተዘዋዋሪ ዐማራ ነው ያፈናቀለን እያሉ ኮተቱን ሁሉ ዐማራ ትከሻና ጫንቃ ላይ አራግፈው ሲጥሉ ነው የሚታዩት። እንዲህ ሲደረግ ዐማሮቹ እንዴት እንደማይነቁ ነው የሚገርመኝ። የትግሬ አክቲቪስትና የትግሬ ቲክታከሮች ወንጀሉን ከአቢይ አሕመድና ከደብረ ጽዮን ትከሻ ላይ አውርደው ዐማራን የሚከስ የክስ ዶሴ ሲያቀርቡ ዐማራ ተብዬው የቲክቶክ ሰፈር ሰገጤ ግን አራዳ አራዳ እየተጫወተ ከከሳሾቹ ጋር አብሮ ራሱን ሲከስስ ውሎ ያድራል። ተራቡ የተባሉት ከወልቃይት ጠገዴ፣ ከሁመራ የተፈናቀሉ ናቸው እያሏቸው ይሄንን እንኳ አያስተውሉም። መቼ? እንዴት? ከየት ብሎም አይመረምርም። እንደው ኧረ ኤድያ የዐማራ አክቲቪስትና ቲክቶከርስ ነገር ቢቀር ይሻላል። ማርያምን ቢቸግር እኮ ናቸው። ከተንኮለኛ ጠላቶቻቸው እኩል ሲሰድቡኝ ነው የሚውሉት። ከምር በጣም ነው የሚያሳዝኑኝ።
"…በትግራይ ሺዎች ተፈናቅለዋል። አብዛኞቹ የተፈናቀሉት ግን እዚያው ትግራይ ውስጥ ነው። ያፈናቀላቸው ወያኔና የፌደራል መንግሥቱ ነው። የተፈናቀሉት ደግሞ ከትግራይ እንደጉድ ተዝቆ ወደ ዱባይ ለሚጋዘው ለወርቅ መዓድኑ ሲባል ነው። በትግራይ ወንዞች ለወርቅ ማውጫው ኬሚካል ሲባል በሚለቀቁ መርዞች ተበክለዋል። በትግራይ ከዚህ የተነሣ ከብቶች፣ የዱር እንስሳት ሳይቀሩ እንደ ቅጠል እየረገፉ ነው። በትግራይ ነዋሪዎች አየሩም፣ አፈሩም፣ ወንዙም በኬሚካል እየተበከለ ስለሆነ ከቀዬአቸው እየተፈናቀሉ በድንኳን ለመኖር ተገደዋል። ይሄን የሚናገር የለም። የሚተነፍስ የለም። ሁሉም ተፈናቃይ ከወልቃይት፣ ከጠገዴና ከጠለምት የተፈናቀሉ ነው የሚመስላቸው። ከዚያ የተፈናቀሉ የሉም ማለት ሳይሆን አሉ ነገር ግን ትግሬ እየተፈናቀለው ለወርቁ ሲባል መሆኑን አይተነፍሷትም።
"…ራቡ በትግራይ እውነት ነው፡፡ ሽሬን ጨምሮ በብዙ አካባቢዎች ራብ ገብቷል። የሚገርመው ነገር ከሽሬ የወርቅ ማምረቻ ብቻ ሰሞኑን ዳግማዊ ግራኝ አሕመድ 32 ኩንታል 3,200 ኪሎ ወርቅ ነው ጭኖ የወሰደው። በምትኩም የተባበሩት አረብ ኤምሬትና ኢራን ቦንብና ድሮን እያሸከሙት ነው። በድሬደዋ፣ በደብረ ዘይትና በባህርዳር የጦር መሳሪያዎቹ እየተራገፉም ነው። ይሄ ለዜጎቹ መጨፍጨፊያ ነው። ወርቁ የተጋዘበት፣ የተወሰደበት የትግሬ ሕዝብ ግን ለማኝ፣ በላስቲክ ውስጥ የሚኖር ነው የሆነው። ሕወሓትም በወርቁ ጉዳይ እየተከሰሰች ነው። በኤርትራ በኩል በኮንትሮባንድ እየቸበቸበችው ነው። በምትኩ ለታጣቂዎቿ መሳሪያ እየሸመተችበት ነው። በራብ እየተጠቁ ነው ተብሎ አሁን አታሞ የሚመታባቸውን ምስኪኖች እንዴት አንደሚያፈናቅሏቸው ከዚህ በታች የማስቀምጥላችሁን ቪድዮዎች በጥንቃቄ ትመለከቱ ዘንድ ልጋብዛችሁ።
"…Who's Profiting from Tigray's Gold? ከትግራይ ወርቅ ማነው ትርፍ እያገኘ ያለው? የሚለውን ተመልከቱ።
• https://youtu.be/4yIT30EuT2Y?si=nSQ8OiI10AsPsi-U
"…ይህ አስደንጋጭ እውነታ ነው። በየወሩ በብዙ ሺ ቶን የሚገመት ወርቅ ከትግራይ በገፍ ይወጣል። ነገር ግን የተሸጠውን የወርቁን ሽያጭ ቼኩን የሚወስደው፣ የሚቀበለው ማነው? በዚህ ሁለት ደቂቃ በሚፈጅ አጭር ቪድዮ በትግራይ ሕገወጥ የወርቅ ማዕድን ማውጣትን በተመለከተ ዓይናችሁን ይከፍታል። መርዛማ ሳይናይድ እና የሜርኩሪ ብክለት በሕዝቡና በእንስሶች ላይ እያደረሰ የሚገኘውን አደጋ ቁልጭ አድርጋችሁ ታዩበታላችሁ። ወርቁ በኮንትሮባንድ መንገድ ወደ ሱዳንና ወደ ሌሎች ስፍራዎች እንዴት እንደሚጋዝ፣ በኮንትሮባንድ ተግባሩ ላይ ወታደራዊ መኮንኖች እንዴት እንደሚሳተፉ ሁላ ነው የሚጠቁመው። ከዚህ የተነሣ የሚነሱ ክሶች፣ አውዳሚና ገዳይ ግጭቶች እንዲሁም የአካባቢ ማኅበረሰቦች ያጋጠሟቸውን ኢኮኖሚያዊ ኪሳራዎች ትመለከቱበታላችሁ። አጭሯ ቪድዮ ዋቢ ያደረገችው ከአዲስ ስታንዳርድ፣ ከቪኦኤ፣ ከቻተም ሃውስ እና ከሌሎች ዘገባዎች በመነሳት፣ የተረጋገጡ እውነታዎችን ከሐሰት መገለጫዎች (ስለ ቻርሎት ቱዋቲ የሚቀርቡ ክሶችን ጨምሮ) ነው ለይቶ የሚያሳየው። ቪድዮው አጭር፣ በሚገባ የተመረመረ እና ወቅታዊ - ለጋዜጠኞች፣ ለተመራማሪዎች እና በአፍሪካ ቀንድ ሙስናን እና የአካባቢ ውድመትን ለሚከተሉ ሁሉ ተስማሚ የምርመራ መነሻ የሚሆን ቪድዮ ነው። ትግሬ እየወደመ ያለው በራሱ በትግሬ ነው። ነገር ግን ባልዋለበት ዐማራን መክሰስ ያረካዋል። ይሄ እርግማን ነው።
• Illegal gold mining – the death of all our animals: Adiabo! June 8, 2025 ~ ሕገወጥ የወርቅ ማዕድን ማውጣት እና የሁሉም እንስሶቻችን ሞት፡ አዲያቦ! ሰኔ 8፣ 2025
https://youtu.be/qJK4nvOk2lo?si=MHeFLJOUutH5K4d1
"…ይሄ ደግሞ በራሳቸው በትግሬዎቹ የተዘጋጀ ዶክመንተሪ ፊልም ነው። አዲያቦ የመስቀል ዕለት በአውሮጵላን የተደበደበው ትዝ ይላችኋል አይደል? በተባበሩት መንግሥታት እነ ካናዳ ትግራይ ትግራይ የሚሉት ለምንድነው ካላችሁ መልሱ ወርቅ ነው። ትግሬን ከሌላው ኢትዮጵያዊ በተለየ መልኩ የሚወዱበት ምንም ምክንያት የላቸውም። እናስ ይሄ እርሻውን የተነጠቀ፣ ከብቶቹ ያለቀበት ሕዝብ ከመሰደድ፣ ከመራብ፣ ከመጠማት፣ ከመሞት ውጪ ሌላ አማራጭ እንዴት ይኖረዋል? አይደለም ወልቃይት አሜሪካ ብታሰፍረው ምን ይፈይዳል? ምን ይጠቅመዋል። ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ። ከምር እኔ የሚያናድደኝ እውነታውን እያወቁ ግግም ብለው ሐሰት ላይ ተዘርፍጠው ራሳቸው ዝገው ሌላውን የሚያዝጉቱ ናቸው። ወልቃይት ወልቃይት እያሉ ሕዝብን ማደንዘዝ ምንም ትርፍ የለውም። ለወርቅ ብለህ እርሻውን በአዲያቦ ነጥቀህ ለማኝ ያደረግከውን ወልቃይት መሬቱ ተነጥቆ ነው ብለህ ብትጮህ ፈጣሪስ መች ይሰማሃል እንኳን ጎንደሬ።
• Tigray Flagship Firms: Ribirth after war and the future of business.
• https://youtu.be/zs33I4D8BS4?si=yAdG7uSCT_zTaMuS
"…በደጉ ዘመን በዘመነ ወያኔ የኢትዮጵያን ቢዝነስ እና ኢንዱስትሪዎች በአናታቸው ላይ ቆሞ የነበረው እና በትግራይ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚገኙት ሁለት ቁልፍ ኩባንያዎች ማለትም ኢዛና ማይኒንግ እና መስፍን ብረታ ብረትን ያነሣና ሁለቱም ከአውዳሚው የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ የጀመሩትን ታላቅ ዳግም የመነቃቃት ሁኔታ ነው የሚያሳየው። ይህ ቪዲዮ ውስብስብ የሆነውን የፖለቲካ ገጽታ እንደገና ለመገንባት፣ ለማዘመን እና ለማሰስ ያደረጉትን ጥረት ለማሳየት ይጥራል። ጦርነቱ በኢዛና ማይኒንግ እና በመስፍን ሜታልስ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ፣ የገንዘብ ኪሳራዎችን እና የአሠራር ተግዳሮቶችን፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንን ሽርክናዎችን ጨምሮ ሥራዎችን እንደገና ለማስጀመር የተጠቀሙባቸውን ስልቶች ያዩበታል። ትግራይ ከርሰ ምድሯ ተገልብጦ ከማኅጸኗ ወርቅ ሲዛቅም ይመለከቱበታል። ከዚያ ወያኔና ኦሮሙማ ተጠቃቅሰው ትግራይ ተፈናቀለ፣ ምዕራብ ትግራይ ዋይ ዋይ እያሉ ሀገር ምድሩን ያደነቁሩታል። በትግራይ ለወርቅ ተብሎ የተፈናቀለው የሀገሬው ሰው ወንዞቹ ተበክለውበት፣ ልጆቹ ወደ የመን፣ እሱ ወደ ድንኳን ተሰድዷል። ይሄንን ግን የሚተነፍስ የለም።…👇②✍✍✍
"ርእሰ አንቀጽ"
• ተፈናቃዮችን እንደ ሽፋን፣ እንደ ጋሻ፣
የተፈናቃዮች ቦለጢቃ…!
"…የቲክቶክ አዋርድ የሚባል አንድ ሰገጤ የሆነ የደነዘዘ ፕሮግራምን አንድ ነፈዝ ምስኪን ኦሮሞን የአዋርዱ ባለቤትና ዋና አዘጋጅ አድርገው የሽልማት መርሀ ግብር በኢትዮጵያ ዋና ከተማ በአዲስ አበባ ያዘጋጃሉ። ዕጩዎቹም የቲክቶክ አስደናቂ የማኅበረሰብ ችግርን የፈቱ በቲክቶክ አዲስ ግኝት ፈጣሪዎችን የሚሸልም ነው የተባለው። ውድድሩ ሄዶ ሄዶ ያው እንደተለመደው ለመጨረሻ ለሽልማቱም ዕጩ ሆነው ሁለት ቲክታከሮች መቅረባቸው ተነገረ። አንደኛው በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ካናዳዊው የሰግጥ፣ ደድብ፣ ፈምስ ባለቤት ትግሬው አዶኒ ሲሆን ሁለተኛዋ ደግሞ ሁሌ ወንድ መሆን የሚያምራት ከቤዋ የኦሮሞ እስላም ዩቲ ናስ የተባለችዋ ሴት ናቸው ለፍጻሜ መቅረባቸው ተነገረ። በመሃል ሰይፉ ፋንታሁን ኦሮሞዋን በሚዲያው ላይ አቅርቦ ቃለ መጠይቅ በማድረጉ በትግሬዎች ዘንድ አዋራ እና ሁከት አስነሳ። ሰይፉም ተወገዘ፣ ተዛተበትም። ትግሬዎቹ ነገሩን አጦዙት። የትግሬ ጋዜጠኞች፣ መንበረ ሰላማ ሳይቀር መግለጫ የሚመስል ሓሳብ ማንፀባረቅ ጀመሩ። ምስኪን ዐማራ ከዳር ሆኖ አንዴ ለአዶኒ፣ አንዴ ለዩቲናስ እያጨበጨበ ይመለከት ጀመር።
"…ነገርየው እየከረረ መጣ። ግማሽ ኤርትራዊቷ የቴዲ አፍሮ ሚስት ወሮ አምለሰት ሙጬም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ አረገፈችበት። በአንደኛው ሥጋዋ ሥቧት ትግሬውን አዶኒን በዩቲዩቧ ላይ አቅርባ ጥንተ ጠላቷን ሰይፉ ፋንታሁንን ቀን ጠብቃ ቀልጥማ ጣለችው። በዚያው ድንጋይ አዶኒን አቅርባ የቴዲ ሚስት በመሆኗ ያላገኘችውን የሰብስክራይበር ብዛት ሸመተችበት። የኦሮሙማ ደኅንነቶች ነገርየው መክረሩን አዩና መከሩ። መከሩና የሽልማት ድርጅቱን አዘጋጅ ባለቤትና ኮሚቴውን በኦሮሚኛ ኮቱ ብለው ጠሩ። ጠሩናም አነጋገሩአቸው። በድምፅ ማን እየመራ ነውም ብለው ጠየቁ? እስላሟ ኦሮምቲቲ ዩቲ ናስ ጋሽ ከቤ ብለው መለሱ። በቃ እንዲህ አድርጉ። ሽልማቱን ለትግሬው አዶኒ ስጡት። ልጅቷ ብታሸንፍም ኦሮሞ እንዲህና እንዲያ አደረገ ብለው ፖለቲካ ይሠሩብናል። ከልጅቷም ጋር ተነጋግረናል። በቀጣይ ብዙ ነገር እንድታሸንፍ እናደርጋታለን። የአሁኑን ግን ለትግሬው ወጣት ስጡት እና ግርግሩን አብርዱልን በማለት ተወያይተው ተስማሙ። ደግሞስ መኪናውን ያቀረበው ያው የታወቀ የእነ አዶኒ ሰው አይደል? ራሳቸው ይውሰዱት ብለው አስገደዱ። እንደ መከሩትም ሆነ። ካናዳዊው የትግሬ ወጣት የኢትዮጵያን የቲክቶክ አዋርድን ጥርግርግ አድርጎ በላው። ለዐማሮቹ ለእነ ታኩር የቀረላቸው አልነበረም።
"…መሸ ነጋ በስንተኛው ቀን አገዛዙ ለባህል ተቆርቋሪ ሆኖ ከች አለ። ከች አለና በአዋርዱ ላይ ተዋርደው የታዩትን፣ በሙታንታ ያለጡት መያዣ በዝግጁቱ ላይ የተገኙትን፣ እንደሴት ቀሚስ ለብሰው የመጡትን የትግሬ የተሸለሙትን ጭምር ሰብስቦ ዘብጥያ አወረደ። ከዚያ እነ ቢቢሲ፣ እነ አሲሲ፣ እነ ዲሲሲ፣ እነ ቲሲሲ፣ እነ ኤልሲሲ፣ እነ ኤልሲ የትግሬ ቲክታከሮች ታሠሩ፣ ዘብጥያም ወረዱ ብለው እሪሪ ቋቀምበጭ ብለው ቀወጡት። ወዲያው ብዙም ሳይቆይ የታሠሩት በሙሉ ከእስር ተፈቱ። የትግሬ ታሳሪዎች በሙሉ ከእስር እንደተፈቱ በቀጥታ ተዘጋጅቶ በጠበቃቸው አጀንዳ ላይ በኃይለኛው ተጥደው መረባረብ ጀመሩ። እነ ጉማ ሰቀታ ሳይቀር ነጠላ ዘቅዝቀው ማልቀስ ጀመሩ። ፍጥነታቸው፣ ኅበረታቸው፣ ጩኸታቸው ገራሚ ነበር። ህፃፅ፣ ህፃፅ የሚል የተጠና ነጠላ ዜማ ለቀቁ። ለቀቁና ወዲያው ብር ማሰባሰብ ጀመሩ።
"…በአንድ ቀን ምድሪቷን ቀውጢ አደረጓት። ኦሮማራዋ ገንገበት፣ ረኸጧ ማማር አለባቸውም ጨዋታው ሳይገባት እወደድ ብላ ማስታወቆያ ትሠራላቸው ጀመር። ኦሮምቲቲዋ ቤታዮ፣ ሌሎችም ግራ ቀኝ ሳያጣሩ አብረው መጮህ ጀመሩ። በዚህ ዓይነት ሁሉም ቲክቶከር በተቀደደለት ቦይ ሊፈስ ነው እንዴ ብዬ አዘንኩ። ወዲያውም ይሄ የብር አሰባሰብ እንዴት ነው? እንዴት በግለሰቦች ባንክ ብሩ ይሰበሰባል? ምን ማለት ነው? ደግሞስ ለሽሬ አውሮጵላን ማረፊያ የሚቀርብ ቦታ ላይ ላሉ ተፈናቃዮች ተመርጦ ተራቡ፣ ሞቱ ብሎ ማጯጯህ ለምን ተፈለገ? ተራቡ የተባሉት በመላ ትግራይ ያሉ አይደሉም ወይ? ህፃፅ፣ ህፃፅ፣ ህፃፅ ብሎ ነጥሎ መጮህ ለምን አስፈለገ? ከረዳስ ራብተኛ ዜጎቹን መርዳት ያለበት ራሱ የሀገሪቱ መንግሥት አይደለም ወይ? ለራብተኞቹ የሚያስፈልገውን እርዳታ ቲክታከሮቹ ጭነው የተራቡት ምን መብላት እንዳለባቸው አውቀው ነው? ነገርየው ልክ አይደለም። የተራቡ አሉ አዎ አሉ። በምንና ለምን ተራቡ የሚለው ሳይገለፅ እንዲሁ እያወዛገቡ መጮህ፣ ልክ አይደለም። ነገር ግን ርዳታ አሰባሰቡ ሕጋዊ መንገድን የተከተለ አይደለም በማለት ጓ አልኩኝ።
"…በነገራችን ላይ እነዚህ የትግሬ ቲክታከሮች በምንም መንገድ ለሌላው ኢትዮጵያዊ ድምፅ ሆነው አያውቁም። ጆን ዳንኤል የሚባለው ከዩቲናስና ከኤርሚያስ ጋር ጌም እየተጫወተ የሌለ ግምኛ ቀልድ ሲቀልድ ኤርሚ የሚባለው ልጅ በሀገሪቱ ላይ ሰው እየተገደለ፣ እየሞተ አንተ እንዴት እንዲህ ትላለህ ብሎ ሲጠይቀው፣ አንድም የሞተ ሰው የለም፣ እንዲህ ብለህ የሌለ ነገር በመናገርህ በወንጀል ያስከስስሃል ብሎ የተሟገተ ጋለሞታ፣ ሴት አውል ቲክቶከር ነው እንግዲህ አንደኛ አዛኝ ሆኖ ከእስር ቤት እንደተፈታ በማግስቱ በተሰጠው ገፀ ባህሪ መሠረት መንገድ የሚጠርጉ እናቶችን ቱታ ለብሶ ሲጠርግ ቆይቶ፣ ማታውኑ መቶ ሃምሳ ሚልዮን ብር በቲክቶክ አንበሳ ሲወርድለት አምሽቶ፣ በማግስቱ ብሩንና ቲሙን ይዞ ሽሬ ገብቶ ጥቁር ለብሶ ዱቄት ተሸክሞ የታየው። ዱቄቱ መቼ እና እንዴት እንደተገዛ? ለ16 ሺ ተፈናቃይ እንዴት እንደሚዳረስ ፈጣሪ ይወቅ።
"…ትግሬዎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ በደል የተፈፀመው በ2 ዓመቱ የጁንታውና የኦሮሙማው ጦርነት ወቅት ብቻ የሚመስላቸው ነገር ነው የሚገርመው። ችግር በእነሱ ላይ የተፈጸመ ብቻ አስመስለው የሚያላዝኑትን ሳይ ድንቅ ነው የሚሉኝ። ትግሬዎቹ ከ1983 ዓም ጀምሮ እስከ 2018 ዓም ድረስ በወያኔና አሁን ደግሞ ባለፉት 8 ዓመታት በኦሮሞ ብልፅግና አንድ ሊያረገን በሚገባን የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነትና አማኞች ላይ የሚፈፀም ጥቃትን እንኳን እያዩ ዝምታን ነው የመረጡት። በዐማራ ክልል፣ በኦሮሚያና በደቡብ በመጠለያ ካምፕ ለሚማቅቁት ቅንጣት ታህል ርህራሄ ያላሳዩ ጉዶች ለራስ ሲሆን ግን ሰማይ ምድሩን ነው የሚያደበላልቁት። ያውም በሚጠሉት፣ በሚፀየፉት በአማርኛ ቋንቋ ነው ልመናውን የሚያጧጧፉት።
"…ይሄ ገንገበት በቲክቶኳ ቡቶክሳም በእነ ማማር አለባቸውና በጋሽ ቤታዮ የሚመራው ዐማራ መሳይ የአሞራ መንጋ ደግሞ ግራቀኝ ሳያይ ያጎረሱትን ሁሉ ነገር ሳያላምጥ እየወጣ በነገር ቁንጣን ሲሰቃይ ይኖራል። የዐማራ ቲክቶከር እወደድ ባይ ሆኖ ከነጎደው ጋር አብሮ ሲነጉድ ብታዩት ለጉድ ነው። ጠዋት ለጆን ዳንኤል አንበሳ ሲያወርድ ያረፍድ እና ከሰዓት ላይ ሲባንን የጨጓራ መድኃኒት ሲቅም ያመሻል። የዐማራ ሴቶች ምን እንደነካቸው ፈጣሪ ይወቅ። ከጥቂቶች በቀር ለሌላ መጫወቻ ይሆኑ ዘንድ የተፈጠሩ ነው የሚመስሉት። ጥቂት ልባም፣ ጀግና፣ ፅኑ የሆኑ ሴቶችን እያየሁ ቢሆንም መንጋው ግን እንደነዱት ነው የሚነዳው። የስድባቸው ክርፋት ደግሞ አያድርስ ነው። …👇①✍✍✍
መልካም…
"…ዛሬ ምሽት ቀሲስ ሳሙኤል ግዛው እረፍት ስለሆነ ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ላይ ከበድ ያለ መርሀ ግብር ይኖረናል። ከዚያ በፊት ግን ለትናንት የቀጠርኳችሁን የተፈናቃዮች ጉዳይ በግልብ መነዳት ሳይሆን በጥልቀት መርምረን ለተፈናቃዮቹ እና በራብና በጥም፣ በችጋርም ለሚሰቃዩት ወሀኖች ትክክለኛ እና ዘላቂ መፍትሄ ይመጣ ዘንድ የሚወተውተውን ርእሰ አንቀጼን ከወዲሁ ልለጥፍላችሁ ወደድኩ። ከዚያም ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ መርሀ ግብራችን እስኪደርስ ድረስ በጉዳዩ ላይ ብንወያይ ብዬም አሰብኩ።
"…ደግሞም ደግሞም ትናንት በቲክታከር ታኩር ተደከልለው በራብተኞች ስም ደብረ ብርሃን ከትመው ከሕዝብ ገንዘብ ሊሰብስቡ ቋምጠው የነበሩትን ፀረ ዐማሮቹን የወሎ ኅብረቶች ሸንቆጥ በማድረግ ልመጣባችሁ ነኝ ብዬ ቀጠሮ መያዜን ሲሰሙ ዛሬ ጠዋት እኔም ሳልዘበዝብባቸው በፊት ማገዶም ሳያስፈጁኝ አቶ ወርቁ አይተነው የተበሉት ባለሀብት እርዳታ መርዳታቸውን ተከትሎ እሱን ሰበብ አድርገው፣ ወርቁ አይተነው በመርዳቱ አገዛዙን እናስከፋዋለን በማለት ለራብተኞቹ ብለው ይሰበስቡ የነበረውን ገንዘብ ከመሰብሰብ ታቅበዋል። በቀጣይ እስከአሁን የሰበሰቡትን ሰይፍና ገጀራ ነው ወይስ ዱቄት የገዙበት? የተሰበሰበውስ ገንዘብ የት አደረሱት፣ ምን ያህልስ ብር ነው የተሰበሰበው የሚለውን በጥልቀት እንሄድበታለን። አሄሄ መች እንላቀቅና!! ሌባ ሁላ።
• እህሳ ርእሰ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ?
"…ትግሬዎቹን ተፈናቃዮች፣ ማን አፈናቀላቸው? ማን አስራባቸው? መሬታቸውንስ ማን ነጠቃቸው? ከየት ነው የተፈናቀሉት? የትግሬ ቲክታከሮቹን እንዲህ እንደ ግሪሳ ማን አሰማራቸው? …ራሳቸው የትግሬ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተፈናቃይ የተባሉትን በራብ እየረገፉ ነው ተብሎ እንዲጯጯህ እየተደረገ ያለውን ጉዳይ በተመለከተ ምን አሉ? …ከምር እኒህ ተፈናቃዮች ከወልቃይት የተፈናቀሉ ናቸውን? ጦማሬ ብዙዎቹን የሚያስቆጣ ቢሆንም መራር ሃቁን ከምስጋናው በኋላ በቪድዮ አስደግፌ ይዤላችሁ እቀርባለሁ።
• ለማንኛውም…
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
9.08 KB
1.13 MB
1.19 MB
2.77 MB
"…ትግሬዎቹን ተፈናቃዮች፣ ማን አፈናቀላቸው? ማን አስራባቸው? መሬታቸውንስ ማን ነጠቃቸው? ከየት ነው የተፈናቀሉት? የትግሬ ቲክታከሮቹን እንዲህ እንደ ግሪሳ ማን አሰማራቸው? …ራሳቸው የትግሬ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተፈናቃይ የተባሉትን በራብ እየረገፉ ነው ተብሎ እንዲጯጯህ እየተደረገ ያለውን ጉዳይ በተመለከተ ምን አሉ? …ከምር እኒህ ተፈናቃዮች ከወልቃይት የተፈናቀሉ ናቸውን? ጦማሬ ብዙዎቹን የሚያስቆጣ ቢሆንም መራር ሃቁን ከምስጋናው በኋላ በቪድዮ አስደግፌ ይዤላችሁ እቀርባለሁ።
• ለማንኛውም…
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
9.07 KB
2.77 MB
9.61 KB
1.19 MB
በውስጥ መስመር አታለቃቅስብኝ።
"…ትግሬዎቹና የወሎ ኅብረቶቹ ተጠቃቅሰው ነው በአንድ ጊዜ በተራቡ ዜጎች ስም እርዳታ የጀመሩት። ትግሬ ያፈናቀለኝ ዐማራ ነው የሚለው። አቢይ አሕመድን አይከስስም። የወሎ የወሀቢያ እስላምም ተፈናቃዮቹ ከየት እንደተፈናቀሉ አይነግርህም። አፈናቃዩን እያገለገለ፣ ለአፈናቃዩ እየተገረደ በተፈናቃዮች ስም ለመሸቀጥ፣ ገንዘብ ለመሰብሰብ ይላላጣል።
"…ይሄ ከታኩር ጋር ንግግር የሚያደርገው ድልብ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ዐማራ ፋኖ አህመድ ኢብራሂም መሃመድ ይባላል። በደሴ የወሀቢያ እስላም ሰብሳቢ ነው። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመውረስ፣ ደሴ መድኃኔዓለምን ወደ መስጊድነት ለመቀየር እየሰለጠነ ያለው ፀረ ኦርቶዶክስ፣ ፀረ ዐማራ አሸባሪ ቡድንም ቀንደኛ ሰው ነው።
"…ለትግሬዎቹ ግርግር ዛሬ የደነገጠው ኦሮሙማ መልስ ሰጥቷል። ለእነዚህ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኢትዮጵያ ቡድኖች ግን መልስ አይሰጥም። ምክንያቱም እነዚህ ለአገዛዙ የድጋፍ መሠረቶቹ ናቸውና ነው።
"…ፋኖን ለመዋጋት በመንግሥት ድጋፍ እየሰለጠነ ያለን የእነ ሙጂብ አሚኖን ቡድን በገንዘብ የሚደግፍ ዐማራ ካለ በራሱ ላይ እንደፈረደ፣ ለመታረጃው ካራ መግዣ እንዳዋጣ ነው የምቆጥረው። ወሎ የፈሰሱትን ተፈናቃዮች ዘልሎ መጥቶ ደብረ ብርሃን ላይ ከትሞ መቀፈል ልክ አይመጣም።
"…30 እና 40 ሺ ተፈናቃዮች የሚረዱት በመንግሥትና በዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንጂ በአጭቤ የወሀቢያ እስላሞች ስብስብ አይደለም። ልክም አይደለም። ተረጂዎች የሚረዱም ከሆነ በራሳቸው ኮሚቴ፣ ልክ እንደ ጎንደሮቹ የቀበሮ ሜዳ ተፈናቃዮች እንጂ በማንም አጭቤ ገፋፊ መንገደኛ ማጅራት መቺ ሁላ አይደለም። ይሄ ልክ አይደለም። ትግሬዎቹ ልክ አይደሉም ካልን የዐማራ የወሃቢያ እስላም ልክ የሚሆኑበት ምክንያት የለም።
• ፋንዳ፣ ጧ በል አልኩህ።
1.40 MB
መልካም …
"…ዝርዝሩን ነገ በሰፊው እመለስበታለሁ። በትግራይ ወያኔ፣ በወሎ የወሎ ኅብረት በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት በተራቡ ትግሬዎችና ዐማሮች ስም ከኢትዮጵያውያን በሕገወጥ መንገድ ገንዘብ ለመሰብሰብ ማሰፍሰፋቸውን ነው እኔ እያየሁ ያለሁት።
"…አግማስ ኢትዮጵያ የሚባል የለየለት ፀረ ዐማራ ወሎን ክልል አደርጋለሁ ባይና በእነ ሙባረክ ሰይድ የሚመራ የእስልምና ቡድን ቲክቶከር ታኩርን ይዞ ለሽቀላ ወጥቷል። ሌባ ሁላ። ፀረ ዐማሮች በዐማራ ስም ገንዘብ ሊሰበስቡም አይገባም። የራሳችንን ክልል እንመሠረታለን ባዮቹ፣ ዐማራ አይደለንም ባዮቹ ደብረ ብርሃን ላይ ምነው ጆፌ ጣሉ?
"…የነገ ሰው ይበለን። አመስጋኙ 1ሺ ሰው እንደሞላ በሰፊው እመለስበታለሁ። ልክ እንደ ትግሬዎቹ እነዚህንም ያሰፈሰፉ ፀረ ዐማራ የወሃቢ እስላሞች ቅስማቸውንና ጅስማቸውን ነው ሰብሬ፣ ሰብሬ የምለቀው። አሄሄ ደግሞ ወሃቢያ ሊያታልለኝ። እግርህን ብላ።
• ስደተኞቹ፣ ተፈናቃዮቹ የግድ ይረዳሉ። መረዳትም አለባቸው። ነገር ግን በሕግ በሥርዓት፣ የደብረ ብርሃን ዐማራ ባለበት ኮሚቴ ውስጥ እንጂ ፀረ ዐማራ አክራሪ ነፍሰ ገዳይ የወሃቢያ እስላም በሚሰበስበው ብር አይደለም።
• አለቀ። ፈንዳ፣ ጧ በል።
Photo unavailableShow in Telegram
• አንዱ ነው እንዲህ አድርጎ የሳለኝ…!
"…ስለ ውሻነቴ፣ ውሻ ስለመሆኔ ምንም ጥርጥር የለውም። ያውም ማንም የሌለው ከሩቅ የሚያሸት አፍንጫ፣ ከሩቅ የሚሰማ ጆሮ፣ የተደበቀን፣ የተሰወረን የሚያይ ዓይን ያለው፣ ለሀገሬ ኢትዮጵያና ለሃይማኖቴ ተዋሕዶ ታማኝ፣ ቅን፣ ንቁ፣ በምንም ጉዳይ ከአቋሙ፣ ከዘበኛነቱ፣ ነቅነቅ ሸርተት የማይል፣ ሌባና ወንበዴ ላይ 24/7 የሚጮህ ንቁ ውሻ ነኝ።
"…ውሻ ስልህ ደግሞ ምርጥ ሥጋና አጥንት የሚቀርብለት፣ የግል ሀኪምና ፓስፖርት ጭምር ያለው የተመጣጠነ ምግብ የሚቀርብለት፣ ከአሳዳሪዎቹ ጋር አልጋ፣ የሻወር ገንዳ የሚጋራ የፈረንጅ ውሻ እንጀራ በውኃ የሚወረወርለት፣ በባለቤቶቹ ምስጋና እንዳልመስልህ፣ እኔ የሀበሻ ውሻ ነኝ። ሌባ መጣ ብዬ ስለጮህኩ ምንአባህ ከሞቀ እንቅልፌ ትቀሰቅሰኛለህ ብሎ አዳሜና ሔዋኔ፣ ወጪ ወራጁ አፉን የሚከፍትብኝ፣ ያገኘውን አንስቶ ድንጋይ የሚወረውብኝ የሀበሻ ውሻ ነኝ። እንዲያ መደረጌ የማያቆመኝ፣ የማያሳዝነኝ፣ የማያሳፍረኝም ምርጥና ታማኝ ውሻ ነኝ። በፍጹም አላፍርበትም።
"…በተነሣው የውሻነቴ አጀንዳ ጉዳይ ሌላ ጊዜ በሰፊው ተመልሼ አብራራለሁ። ለዛሬ ግን ያው መባሌ ካልቀረ ደግሞ አንድ አጭበርባሪ አዲስ ሾተላይ ሴረኛ ላይ ዉዉዉዉ በማለት ልጮህ ነኝ። ደግሞ ጫጫታ ይበዛብኛል የራሱ ጉዳይ።
• ልጀምር ነኝ።
"…ተሰብስቦ በካሽ ወደ ባንካቸው የገባው 6 ሚልዮን አንድ መቶ ሺ ብር ነው አሉኝ። ቃል የተገባ 6 ሚልዮን ብር ደግሞ አየር ላይ አለ። ቃል የተገባው ብር ሊገባም ላይገባም ይችላል። መድረኩ ላይ ቃል የሚገቡት ጴንጤዎች፣ እስላሞችና ጓደኞቻቸው ናቸው እና ላይገባ ይችላል። ስለዚህ ቃል የተገባውን እርሱት። እምጷ ቀሊጦ።
"…በካሽ ከተሰበሰበው 6 ሚልዮን ብር ውስጥ 6 ሚልዮኑን የወልቃይት ትግሬው የኢቨንቱ አዘጋጅ እና አርቲስቶቹ፣ ገተት የተራቡ ፋርሴ ቡላ አበል እንጀራቸው የሆኑት ሆዳም ዘማሪዎቻችን፣ ቲክታከሮቹ እና ከተጠመቁ ገና ሳምንት ያልሞላቸው፣ የተጠመቁበት ውኃ ያልደረቀላቸው ፓስተሮች በውላቸው መሠረት ለሥራው የተፈራረሙበት ነውና ጥርግርግ አድርገው ወስደው ሄዱ አሉ። አሁን ቤተ ክርስቲያኑ ያን ሁሉ ሚልዮን ብር ወጪ አድርጎ ሲያበቃ በእጁ የቀረው 1መቶ ሺ ብር ብቻ። 🙏🙏😭😭😁😁😡😡
"…ይህንን ሴራ ደፍሬ ሳጋልጥ ግን ጭምብላቸው ተገፈፈ። እንጀራቸውን አመድ ላይ ጣልኩት። ማንቁርታቸውን አንቅኩት። የበግ ለምዳቸው የተገፈፈባቸው ተኩላዎች ጠበል እንደነካው አጋንንት በየቦታው ይለፈልፍ ጀመረ። ኦሮሞ ነኝ፣ ብልፅግና ነኝ። መንግሥቴ ነው። እሪሪ ቋቀምበጭ። ያዙኝ ልቀቁኝ። ሌባ ሁላ።
• ለዚህ ዘረፋ መጀመር በር ከፋቹ ኮሜዲያን እሸቱ መለስ ሆይ እና ሊቀጳጳሱ ሆይ፣ ቀዩአን ያየ አጫውታችሁ በወሮ ትእግስት ፈረደ የ1ሚልዮን ዶላር ብድርን እንደ ስጦታ ዐውጃችሁ በኮሚሽን ነፃውን የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት፣ በዶላርና በፓውንድ ያስጀመራችሁ፣ በሀገሪቱ እሾህ የተከላችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ይፍረድባችሁ። ሌላ ምንም አልል።
"…የእኔ ሥራ የእኔ ተግባር እንደ ታማኝ ውሻ እናንተ ተኝታችሁ ሳለ የሚመጣባችሁን ሌባ፣ ዘራፊ፣ ቀማኛ አይቼ፣ ሰምቼ፣ አሽትቼ በጩኸት መቀስቀስ ነው። ድምጼ ላያምር ይችላል። ሊረብሻችሁም ይችላል። ግን ደግሞ የቤተ ክርስቲያኔና የሀገሬ ውሻ አድርጎ ነው የፈጠረኝ። ኢትዮጵያዊ ውሻ ስለሆንኩ ደግሞ ክብርን ከእናንተ አልጠብቅም። ኢትዮጵያዊ ውሻ እንደ ፈረንጅ ውሻ መች ክብር አለውና ነው ክብርን የምፈልገው። ኧረ አላበድኩም። ደሞዜም አይደል ስድቡ።
"…ግን ግን የረቀቀውን ሌብነቱን፣ ዘራፊነቱን፣ ግልሙትናውን ስለምገልጥበት ሌባው ይስደበኝ። ዘራፊ ወንበዴው ይስደበኝ። መናፍቁ፣ ሜንጤው፣ የወሃቢይ እስላሙ፣ ስኳዱ፣ ሸንጎው፣ ወያኔና ኦነጉ፣ ብልፅግናውም ይስደበኝ። እነሱ እሼ እንቅፋት ስለሆንኩባቸው ይስደቡኝ። የሚገርመኝ የቀጠሩኝ፣ የራሴ የምላቸው ቤተሰቦቼ ባለማዕተብ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ልጅ ነኝ የሚሉት ቤተሰቦቼ የምላቸው ሲሰድቡኝ ነው የምደነቀው። ሰው እንዴት ሌባ፣ ዘራፊ፣ ወሮበላ፣ ወንበዴ መጣብህ ብዬ ከጥልቅ እንቅልፉ ስለቀሰቀስኩት ከሌባው እኩል ሲሰድበኝ ይውላል። እኔ ግን ስድብ ደሞዜ ነውና ኬረዳሽ። ለማንኛውም ገና አስለፈልፋቸዋለሁ። አስቀባጥራቸዋለሁም። ደግሞ ለሜንጤ…
• ለማንኛውም…
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
10.67 MB
3.30 MB
4.01 MB
4.61 MB
Photo unavailableShow in Telegram
መልካም…
"…ከርእሰ አንቀጹ ንባብ በኋላ በቀጥታ የምንገባው ወደ እናንተ አስተያየቶች ነው። እስከ እኩለ።ሌሊት ድረስ በርእሰ አንቀጹ ላይ፣ በትግራዩም ራብ ላይ፣ በዘራፊ ወንበዴ ተመላሽ የካቶሊክ እና አጭቤ የኦሮሞ ጴንጤ ዘራፊ የወልቃይቴው ሎዛ ኢቨንት ጉዳይ ላይ ሓሳባችሁን መስጠት ትችላላችሁ።
• ጀምሩ…✍✍✍
👆③✍✍✍ …ለእያንዳንዳቸው ተሰጥቷቸው የተመለሱ ናቸው። 70 ሺ ጎርሰው ማለት ነው። 70 ጎራሽ ሁላ።
• የሕዝቡ መልስ እና አስተያየት።
ሀ፦ እየተደረገ ያለውን በሚገባ አውቀናል። ሰምተናልም እኛ ገበሬወች ነን። ነገርግን ቅርሱን የመጠበቅ ግዴታም ሓላፊነትም አለብን። ቤተመቅደስ ገብተን ቅርሱን አንድ ሁለት ብለን ቆጥረን ባናውቅም እንዳይወጣ ማድረግ ግን አያቅተንም እናንተ ካህናት ብትሆኑ የኛው ሰው ስለሆናቹሁ ጎደለ የተባ ነገር ብንሰማ ከእናንተ ራስ አንወርድም።
ሁ፦ ካህናቶች ደግሞ ቅርሱን የመጠበቅም ለሕዝብም የማሳወቅ ግዴታ አለባችሁ። ይህን ባታደርጉ ውርድ ከራሳቹሁ። ቅርስን ለትውልድ ያሻግሩታል እንጂ እንዴት ቅርስን ያዘርፉታል? ይሄ የሞት ሞት ነው።
ሁ፦ እኛ ታቦታችን በአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ተጭኖ የመጣ፣ በሌላው ቤተክርስትያን እንደሚገኝው ዓይነት ሳይሆን የተለየና ዕፁብ ድንቅ እንደሆነም አባቶቻችን ነግረውናል። ሌላውን ቅርስ ግን አገልጋይ ካህናት ታውቁታላቹህ።
• ከሕዝብ ጎን የቆሙት ካህናት ቀጠሉ…
ሀ፦ ቅርሱን መጠገኑ ባልከፋ ነበር ቅርሰን የማመናመን እና ዘረፋ ማካሄድ የሚመስል አዝማሚያን ግን ምን አመጣው?
ሁ፦ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ሦሶት መቅደሶች አንድ ማኅሌት እንዳለ ሁላችንም እናውቃለን አንደኛው መቅደስ በቅርስ ብቻ የተሞላ ነው። ያለውንም እኛም እናንተም ታውቁታላቹህ። ይህ ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱ ብቻ ሳይሆን የሕዝብም ሀብት ነው። ስለዚህ ከሕዝቡ ጋር በመሆ ኮሚቴ ተዋቅሮ ከመቋሚያ ጀምሮ ያለው ንብረት መቁጠር መመዝገብ ሕዝብ ማወቅ አለበት።
ሂ፦ እንደተባለው ቅርሳችን ይታደስ ቢባል እንኳ ቅርሳችንን ለእድሳት ዝግጁ የምናደርገው በቅዱስ ላልይበላ ያለውን ጩህት እየሰማን ስለሆነ መጀመርያ በቅዱስ ላልይበላ ላይ እድሳት መሥራታቸውን እና በምን ሁኔታ ሠርተው እንደጨረሱ ካወቅን በኋላ ከህዝብ ጋር ተወያይተን የምንወስነውን ነው የሚሆነው። በማለት በዚህ መልኩ ከሕዝቡ ጋር ተወያይተው ስብሰባው ያለ ውሳኔ ተቋጭቶ ሕዝቡ ወደ ቤቱ ሄዷል። ነገር ግን ሕዝቡን ከበተኑ በኋላ ከወረዳ ቤተክህነቱ እና ከቱሪዝም የመጡት አወያዮች የቤተክርስትያኑን ካህናት በድጋሚ በመሰብሰብ ለማወያየት ሞክረዋል።
• ውይይቱም አወያዮቹ እንዲህ በማለት ጠየቁ።
ሀ፦ ይህን ሁሉ መረጃ ለሕዝቡ ማን ነገረው ?
ሁ፦ እናንተስ ከሁለት ተከፍላቹሁ ግማሾቻችሁ ከሕዝብ ጎን ሌሎቻቹሁ ደግሞ ከእኛ ጎን በመሆን ቅርሱ እንዳይታደስ የምታደርጉት ለምንድን ነው? በሚል ነበር የጦፈ ክርክር ተንሥቶ ክርክር የተጀመረው።
• እኒያ ከእነ ዳንኤል ክብረት ሥልጠና ወስደው ተልኮ ተሰጥቷቸው የመጡት ካህናት እንዲህ ማለት ጀመሩ።
• እኛን ያልሆነ ስም ለሕዝቡ በመንዛት እና በመስጠት እንደዘራፊ አስቆጥረውናል እኛ ቅርስ ይጠገን ባልን ስለዚህ ሹመት እና ሥልጣን የሚፈልጉ ከሆነ ይውሰዱ ከሕዝብ ጋር አያጣሉን ይህን ቤተ ክህነቱም ይወቅልን
* ከህዝብ ጎን የበሩት ደግሞ መለሱ
• እኛ ሕዝቡን እልነገርነውም አልቀሰቀስነውምም፣ ሕዝቡ በራሱ መንገድ ነው የሰማው። እኛም የሕዝቡ አንድ አካል ስለሆን አብረን ነው ወሬውን የሰማን። ነገርግን ካህን ስለሆን እየተሠ ራ ያለውን ሁኔታ ቆም ብለን እንድንመረም ሁነናል። ልዩነታችንም የፈጠረው ይሄው ነው። አሁንም ቢሆን አቋማችን ያው ነው። ከሕዝብ አንወጣም ከወንበዴም ጋር አንተባበርም ነው ያልነው እንጂ ስልጣን ስጡን ሹሙን አላልንም ሓሳባችን ይሄው ነው በማለት ሁላቸውም ሓሳባቸውን በነፃነት አንፀባርቀው፣ ከቤተ ክህነቱና ከቱሪዝም የመጡትነ ካህናቱ ሳይስማሙ ተለያይተዋል።
"…መሽቶ ሲነጋ ትናንት ታሕሳስ 13/2018 ዓም ደግሞ በድጋሚ የቀንቀኒት ሚካኤል ካህናት የላስታ ቤተክህነት በተገኘበት ተሰብስበው ውይይት አድርገው ውለዋል። ካህናቱም በአንድ ድምፅ የሰበካ ጉባኤ ሰብሳቢውን ቅርሱ አደጋ ላይ እንዲወድቅ ያደረገው የመጀመርያው ግንባር ቀደሙ እሱ ስለሆነ ከዛሬ ጀምሮ ከሓላፊነቱ እንዲነሳልን የሚል ጥያቄ የጠየቁ ሲሆን በምላሹ የሓ ግን ከሓላፊነት ቦታየ አልለቅም። እንድለቅ ከፈለጋቹሁ ፍርድቤት ክሰሱ የሚል ምላሽ ይመልስላቸዋል። በዚህም የተበሳጩት ሌሎች ካህናት ከአዲስአበባ 70ሽህ ብር ተቀብለህ የመጠህው ቅርስ ለማውደም ከሆነ እናያለን። አንተን የሾመህ የዚህ ቤተክርስትያን ካህን እና ምእመን እንጂ መንግሥት አይደለም የሾመህ። በፍርድ ቤት አንተን የምን ከሰው ምን ይሁን ብለን ነው? እንደ ሾምንህ ውረድ ስትባል አልወርድም ያልክበት የተለየ ተልኮ ቢኖርህ ነው በማለት የተካረረ ዱላ ቀረሽ ፀብ ውስጥ ገብተዋል። ቤተክህነቱም ነገሩ ካቅሙበላይ ሲሆንበት እንምከርበት በማለት ጉዳዩን በይደር አቆይቶ ስብሰባው ተበትኗል።
"…ይህንና ይህን የመሳሰሉ ውጥረቶች ባሉበት ሁኔታ አቡነ ኤርሚያስ ነገሮችን የሚያጋግል፣ የደብረ ሮሀ ሊቃውንትን የሚያስቆጣ ድርጊት መፈጸማቸው ነው የሚነገረው። ከዚሁ ጉዳይ ጋር ተያይዞ አቡነ ኤርሚያስ በጋሸና የደብረ ሮሃን ክብር የሚገፍ ነው የተባለ የመሰረት ድንጋይ መጣል ጋር ተያይዞ ከሁለት ተከፍለው የነበሩትን የላልይበላ ካህናት በራሳቸው በአቡነ ኤርምያስ አማካኝነት እና በሀገር ሽማግሌዎችም። በኩል የተደረገው የእርቅ ጉዳይ ሙሉ ለሙሉ አለመቋጨቱ ነው የተሰማወረ። ምክንያቱም በባህሉ መሠረት በልደት በዓል ዋዜማ ከየሃገሩ ለመጡ ዲያቆናት ይሰጥ የነበረው የድቁና ማዕረግ ለመቀበል ወደ ላልይበላ ይመጡ የነበሩት ተማሪዎች በደብረ ሮሀ ክህነት መስጠት አቁመው ወደ ጋሸና በማዞራቸው ምክንያት ሊቃውንቱና ሕዝቡ ለምን ድቁና የሚሰጡበት ቦታና ጊዜ፣ ወራትም ጭምር ተቀይሮ ጋሸና ሆነ የሚል ጥያቄ ስለተነሳ ይሄ ጉዳይም ማኅበረሰቡን ጭምር ያሳዘነ በመሆኑ ነው ድብልቅልቁ እየወጣ ያለው። ለቤተ ክርስቲያን ፈተናው እንደ ሀገር ቢሆንም የቅዱስ ላሊበላው ግን የከፋና አደገኛ ነው። ውጊያው መንፈሳዊ ነው። ጠላታችን ደግሞ ከሩቅ ሳይሆን ከውስጣችን ነው። ውጊያውን በድል እንደምንወጣው ከኋላ ታሪካችን ጀምሮ የታወቀ ቢሆንም ውጊያው በጊዜ በድል ይጠናቀቅ ዘንድ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በያለንበት እንጸለይ፣ እንበርታ በርቱ።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ ከራየን ወንዝ ማዶ።
👆②✍✍✍ "…በስውር የተደራጀውን ቡድን በመጠቀም ልደትን ተንተርሶ ግቡን ለመምታት ያሰባችሁትን እና በየቤተክርስቲያኑ ለመግጠም ያሰባችሁትን ካሜራ በፍጥነት አቁሙ። አቢይም፣ አባ ኤርምያስም፣ የደብሩ ሰራተኞችም ያልጠበቃችሁት ነው የሚሆነው። የደብሩ ሠራተኞች ሆይ፣ አባ ኤርምያስ የሚኖሩት ወልድያ አቢይ አህመድ ደግሞ አዲስ አበባ ነው። የችግሩ ገፈት ቀማሾች እናንተ ናችሁ። የእስካሁን ግፋችሁ ጽዋው የሞላ ይመስላል። ከሕዝብ አታመልጡም። ከዚህ በኋላ አንድም ቁፋሮ ማየት አንፈልግም። ማን አስቆፍሩ አላችሁ? በላሊበላ ዙሪያ የምታካሂዱትን ቁፋሮ በአፋጣኝ አቁሙ። ከሕዝቡ ጋር ደም ከመቃባታችሁ በፊት ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ጀርባ ልታካሂዱት ያሰባችሁትን ቁፋሮ አስቁሙ። ለሕንጻው የምታስቡ ከሆነ እስኪ በዩኔስኮ ሕግ መሠረት መድፉን፣ ዙ23ቱን አስቁሙ፤ መድፉን ከአምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ውጭ አስጠምዱ።
"…የስውር ቡድኑ አባል ሆናችሁ የተመለመላችሁ የላሊበላ ነዋሪዎች ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ እንመክራለን። በተለይ የግል ትምህርት ቤት ያላችሁ ተጠንቀቁ። ከዳንኤል ክብረት ጋር ምን እንደምትሠሩ የተሰወረ አይደለም። በፕላንና በተራድኦ ድርጅት፣ በዓለም አቀፍ ድርጅት ስም ተሰማርታችሁ የስውር ቡድኑ አባል ሆናችሁ እንደተመረጣችሁና ለእነ ዳንኤል የመረጃ ግብዓት እንደሆናችሁ እያወቅን ዝም ብለናል። ከዚህ እኩይ ዓላማ ካልታቀባችሁ በመረጃና በስማችሁ እንመጣለን። "መጻሕፍቱ አርጅተዋል፤ እስካን ይደረጉ" ስትሉ ሕዝቡ "አይሆንም" ስላላችሁ በአዲስ ስልት መጥታችሁ "በብራና ይጻፉ፤ ይለበጡ" በማለት ለማውጣት እና ብራና ጸሐፊዎችን በመመልመል ልታደርጓት ያሰባችኋትን እናውቃታለን። በአስቸኳይ አቁሟት። አንድም ብራና ከቤተ መቅደሱና ከጥንቱ ሙዚየም ብትወጣ ወዮላችሁ። ለግለሰብ በትናችሁ እሳካን ልታደርጉ?! ያለ እናንተ ብልጥ የለም። ከዚህ በፊት አፍሮ አይገባውን መስቀል "ሕመምተኛ እንሽበት" ብላችሁ እንደሸጣችሁት የምንረሳ መሰላችሁ፤ እረፉ። ብራና እንጽፋለን ብላችሁ የተመለመላችሁም አውቃችሁ ግቡበት።
"…በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላችሁ ስለ ቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያን ጉዳይ ይገደናል የምትሉ፣ በዲፕሎማሲው ዘርፍ የተሠማራችሁ፣ የሚድያ ባለሞያዎች፣ በውጭ አለም የምትኖሩ ክርስቲያኖች፣ እውነተኛ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ሰልፍ በመውጣት እንድትደግፉን፣ ጥሪያችንን በእንግሊዝኛ ለሚመለከተው ሁሉ እንድታሰሙልን፣ አቡነ ኤርምያስ ቅዱስ ላሊበላ ላይ ምን እያካሔዱ እንደሆነ እንድታጋልጡልን፤ ከቻላችሁ ለዩኔስኮ መሥሪያ ቤት እንድትጮሁና ደብዳቤ እንድታስገቡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። እኛ ማድረግ የምንችለው ማጋለጥ እና ሰማዕት መሆን ብቻ ነው። ሌላው የእናንተ ድርሻ ነው። ቤተክርስቲያን ያለችው ውድመት ላይ ነው፤ ድረሱላት። አባ ጽጌ ሥላሴ እና ቀሲስ ዶ/ር መንግሥቱ ጎበዜ የተፈራረሙበትን ሰነድ ይዘው እንዲያቀርቡልን እና በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ በሚድያ የተሰማራችሁ በምርመራ ጋዜጠኝነት ዓውድ ጠይቁልን፤ ምን እንደተፈራረሙ ውሉን ማየት አለብን ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
"…ሸልተሩ እንዲነሳ ከተፈለገ መጀመሪያ አገር ሰላም ይሁን። ኮማንድ ፖስቱ ይነሳ። እውነተኛ ሕዝቡ ያመነባቸው ካህናትና የደብሩ ተወላጆች ይወከሉ። ፈረንሳይ ሳትሆን ዩኔስኮ እንደጫነው ራሱ ዩኔስኮ ያንሳው። በሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ላይ አደጋ ቢደርስ ዋና ተጠያቂው ዩኔስኮ ነው። አቢይ ከሕንጻው ላይ መድፍ ጠምዶ ሲያነቃንቀው ስለ ቅርስ ይመለከተኛል የሚለው የዩኔስኮ ዝምታ ምንድን ነው? ፈረንሳይ ከብራናዎቹና ከቁፋሮው ምን ያህል ብታተርፍ ነው በዚህ ልክ ዙሪያ ጥምጥም የምትዞረው? መስሏት ነው እንጂ ቤተ ክርስቲያንን የሲኦል ደጆች አይችሏትም። የኢትዮጵያ አምላክ አይተኛም፣ አያንቀላፋም። ኢትዮጵያን ትላንት ጣሊያን አልቻለቻትም፤ ዛሬም በፈረንሳይ አይሳካም። በደምና አጥንታችን ላይ ካልሆነ በቀር ቆመን አይሆንም። በፍጹም!! ይኸው ነው።
[ካድሬውም፣ የጨረቃ ጳጳሱም፣ ራሱ አቢይ ሳይቀር ዘመዴ ምን መረጃ አግኝቶ ይሆን ብለው ከዘመዴ ቴሌግራም ላይ ነው ተጥደው የሚውሉት። የተነሳው አቧራ አቧራ አይመሰልህ አክሊለ ገብርኤል። ብዙ መረጃ አለን አስፈላጊ በሆነ ጊዜ እናወጣዋለን። ይህንን አጀንዳ ሌሎች ሚድያዎችም መወያያ እንዲያደርጉት አድርግና እናክሽፈው። ሥራህ ጥሩ ውጤት እያመጣ ነው ልጃችን። በርታ። እግዚአብሔር ይጠብቅህ።] የሚል ምክር ለእኔም ለእናንተም በመስጠት ጭምርም ነው የተለያየነው።
"…ይህ በእንዲህ እንዳለ የአቡነ ኤርሚያስ፣ የአቢይ አሕመድና የፈረንሳይ ጦር ፊቱን ያዞረው ወደ ቀንቀኒት ሚካኤል ውቅር ቤተ ክርስቲያን ነው። ቀንቀኒት ከቅዱስ ላሊበላ ገዳም ራቅ ብሎ የሚገኝ፣ የላሊበላ ሕዝብ የሚጠጣው ውኃ ሁላ ከዚያ እንደሚመጣ የሚነገርለት ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ነው። ቀደም ብሎ በሊቃውንተ ኢትዮጵያ አማካኝነት በዚሁ በዘመዴ የቴሌግራም ገፅ ላይ ቅዱስ ላሊበላን በተመለከተ በርእሰ አንቀጽ መልክ ጠንካራ መልእክት ከተላለፈ በኋላ የላስታ ተወላጆች ቤተ ዐምሓራዎች በሙሉ በጥቅሻ ነው ተሰባስበው መምከር የጀመሩት። እናም ለታሕሳስ 12/2018 ዓም በቀንቀኒት ሚካኤል በተጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ሁሉም ከያለበት ነው የተሰባሰበው።
• እሁድ ታህሳስ 12/2018 ዓም
ላስታ ቀንቀኒት ሚካኤል
"…ጠዋት ከሥርዓተ ቅዳሴ በኋላ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ምእመናን፣ የላስታ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ተወካዮች እንዲሁም የላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት ተወካዮች በተገኙበት ነበር ተጠባቂው ውይይት የተጀመረው። ውይይቱን የመሩት ደግሞ ከቤተ ክህነቱና ከባህልና ቱሪዝም ተወክለው የመጡት ሰዎች ነበሩ።
• ውይይቱ ተጀመረ።
• በአወያዮቹ በኩል የቀረቡ ሓሳቦች
ሀ፥ የ 1,600 ዓመት ቅርሶችን የያዘው ቤተክርስቲያናችን እድሳት ያስፈልገዋል፣ ጥገና ያስፈልገዋል፣ ተጎድቶብናል እና የመሳሰሉ…
ሁ፦ ላልይበላ ከተማ የሚኖሩ ያካባቢው ተወላጆች ቅርሳችን ባግባቡ እድሳት እንዳይደረግለት እንቅፋት እየሆኑ ነው ይህንም ወዳጅ ዘመድ የሆናችሁ ሃይ ልትሏቸው ይገባል።
ሂ፦ ከቀንቀኒት ሚካኤል እስከ ጨርቆስ ድረስ ውስጥ ለውስጥ የዋሻ መንገድ እንዳለ እናውቃለን። እናም ይህንም ባግባቡ ቅርሱን ለመጠበቅ ሲባል ውጫዊ መንገድ እንሠራለን።
ሃ፦ በላልይበላ የቅርስ እድሳ ላይ የተሰማሩ የቀን ሠራተኞች የሚከፈላቼው 500 ብር ነው። እኛ ደግሞ እዚህ ለምናደርገው ማንኛውም ሥራ ለቀን ሠራተኛ ልጆቻችሁ 1,000 ብር እናደርጋለን። ሥራውም ረዘም ያለጊዜ ሊወስድ ስለሚችል ቅድሚያ ለእናንተና ለልጆቻቹሁ የሥራ ዕድሉን እንሰጣለን ሓሳብ በማንሳት ውይይቱ ተጀመረ።
"…ሕዝቡ ወጥ አቋም ይዞ፣ ካህናቱ ለሁለት ተከፍለው ነው ውይይቱ የተጀመረው። አራት ቀሳውስት እና ሦስት ዳቆናት ሊቀ ገበዙን ጨምሮ ከመንግሥት እና ከቤተ ክህነቱ ልዑካን ጎን ሆነው።
ማስታወሻ፦ እነዚህ ከመንግሥትና ከቤተ ክህነቱ ወኪሎች ጋር የቆሞት ካህናት ከሁለት ሳምንት በፊት የሌላውን ለጊዜው ባይታወቅም በሰሜን ወሎ ውስጥ በማንኛውም አብያተክርስቲያናት እና አድባራት የሚገኙ የተመረጡ የሰበካ ጉባኤ አባላት ቀጥተኛ በሆነ በዳንኤል ክብረት እና በብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ትእዛዝ ላለፉት ሁለት ሳምንታት አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር እና ወልዲያ ሢልጠና ሲሰጣቸው እና ውይይት ሲያደርጉ ቆይተው ተልእኮ ተሰጥቷቸው አበልም ካልጋ፣ ከምግብ እና ከትራንስፓርት ውጭ ለሁሉም ተሳታፊ የኪስ ገንዘብ የሚሆን 70,000 ሽህ ብር…👇②✍✍✍
"ርእሰ አንቀጽ"
• የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያን የቅርስ ዘረፋ ፕሮጀክት - የዘረፋ ቅየሳ (...ከባለፈው የቀጠለ...)
"…የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያንን የቅርስ ዘረፋን ጉድ ካጋለጥን በኋላ ፈረንሳይም፣ አቢይ አህመድም፣ አቡነ ኤርምያስም በንዴት እየተንጨረጨሩ ነው። የሚይዙትን የሚጨብጡትንም ማጣታቸውን፣ ደግሞም ሌላ ሴራም መጠንሰሳቸው የተሰማው። አቡነ ኤርምያስ በኅቡዕ የሚሠራ የራሳቸውን ቡድን እንዳቋቋሙ፣ አቢይ አሕመደም ስውር ቡድን እንዳቋቋመ፣ ፈረንሳይም የራሷን ስውር ቡድን ልዩ ተልእኮ ሰጥታ እየተንቀሳቀሰች እንደሆነ ነው የሚሰማው። ሦስቱም ቡድኖች በቅርስ ምርምር ልምድ ያላቸው፣ በከርሰ ምድር ቁፋሮና በጥንታውያን ቅርሶች ላይ የዳባረ እውቀት ያከማቹ፣ በስለላና ቅርስ በመመዝበር የታወቁ፣ በቀላሉ ሰውን እንዴት ማታለል እንዳለባቸው የተካኑ ባለሙያዎች የተሰባሰቡበትን ቡድን አቋቁመዋል ነው የሚባለው።
"…ዋና ግባቸው ጥናት የተካሔደባቸውንና ለቁፋሮ የተመረጡትን ቦታዎች በቀላሉ መቆፈርና መዝረፍ የሚቻልበትን ዘዴ በመዘየድ ለመንገድ፣ ለተፋሰስ፣ ለዓውደ ምሕረት ግንባታ በሚል ሰበብ ቁፋሮውን ሳይደናቀፍ ማስቀጠል ነው። ለዚህ ተመልምለው ቁፋሮ እየቆፈሩ የሚገኙት የጉልበት ሠራተኞች እውቀቱም ግንዛቤውም የሌላቸው፣ የዕለት እንጀራቸውን ብቻ የሚያስቡ፣ ከገጠር ለእንጀራ ብለው የፈለሱ፣ ምንም ዓይነት ጥያቄም ሆነ አስተያየት የማይሰጡ፣ ከሰጡም ከሥራው እንደሚባረሩ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ናቸው። እነሱም ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ እንዳይቀየሩ፣ ሌላው ሕዝብ ከቁፋሮው ቦታ እንዳይገኝ፣ የቁፋሮው ቦታም በኮማንዶ ጦር እንዲታጠር ተወስኗል። ቁፋሮው የሚካሔደው ለጥናትና ምርምር መሆኑ እንዳይታወቅ ዓውደ ምሕረት ሊሠራ ነው፣ ድልድይ ሊገነባ ነው፣ ተፋሰሱን ለመጥረግ ሸልተሩ ከመነሳቱ በፊት ይህ ያስፈልጋል፣ ቤተ ክርስቲያኑ የሚጠገነው እነዚህ ሲመቻቹ ነው ተብሎ ነው ለሕዝቡ የተነገረው። ውስጡ ግን ሌላ ነው።
"…ለምሳሌ ቤተ ገብርኤል ተራራው ላይ የመጀመሪያው ቁፋሮ ሲካሔድ በርካታ ዘመን ያስቆጠረ አንድ አስከሬን ተገኝቷል። መስቀሉን እንደጨበጠ፣ ዳዊቱን እንዳነገተ ነበር የተገኘው። ያ አስከሬን ግን የት እንደገባ ማንም አያውቅም። ለምርምር ወደ ፈረንሳይ ሄዷል የሚሉም አሉ። የተገኘውን አጽም በተመለከተ እስካሁን ዝም ያልነው ከቅርስ ዘረፋው ጋር ስለሚገናኝና ጊዜው ገና ስለነበር ነው። ውድ የሆኑ ብራናዎች፣ መስቀሎች፣ እና ጽላቶችም ተገኝተዋል። የት እንደገቡ ግን አይታወቅም። ይህንን የሚያውቀው የፕሮጀክቱ ዋና ኃላፊ ኪዳኔ ወልደ ጊዮርጊስ ነው። ካህናቱና ምእመኑን የሚያስደርሰው የለም። ኪዳኔ ወልደ ጊዮርጊስ ሚስቱ ፈረንሳዊት መሆኗን አስምሩበት። ከኢትዮጵያ ይልቅ የሚስቱ ሀገር ፈረንሳይ በልጣበት በጥፋቱ የቀጠለ ሰው ነው። ነገር ግን በዚሁ ጥፋቱ ከቀጠለ የመውጊያውን ብረት ተቃውሞአልና ለእሱ ይብስበታል።
"…የቅዱስ ላሊበላ አድባራት ሕዝበ ክርስቲያን መጀመሪያ የጠየቁት "ዩኔስኮ ቤተ ክርስቲያኑ ላይ የከመረውን ሸልተር ያንሳ!" ነበር። 'ቁፋሮ ይካሔድ፣ ቅርስ ይዘረፍ፣ እስካን ይሁንልን' ብሎ የጠየቀ የለም። ዩኔስኮ በጉዳዩ መልስ ሳይሰጥ ፈረንሳይ ዘው ብላ ገባች። ለሕዝቡ ሸልተሩ ይነሳል ተባለ። ዩኔስኮ ላሊበላ ላይ የከመረው ሸልተር ግቡ የዘረፋ መሆኑ የገባን አሁን ነው። ሸልተሩ ሲሠራ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ያለው ታቦት፣ ቅርስና መጻሕፍት መውጣት አላስፈለጋቸውም ነበር። አብያተ ክርስቲያናቱ አገልግሎታቸው ሳይቋረጥ ነው መጠለያው የተሠራው። ዛሬ ሸልተሩ ሲነሳ ለምን ቅርሱ በሙሉ ይውጣ ተባለ?! ጥያቄ ነው።
"…የቅዱስ ላሊበላ ሰበካ ጉባኤ አንዳንድ የቢሮ ሠራተኞች ቅዱስ ሚካኤል ግቢ ከጥንቱ ሙዚየም ጀርባ በመድረክ ግንባታ ሥራ ስም ቁፋሮ ለመጀመር ማሰባቸውም ታውቋል። አይጠቅማችሁም እና አቁሙት። ምክራችን ነው። እናንተ ፀረ ክርስቶስ፣ ለሆዳችሁ ያደራችሁ፣ ይሁዳ እንደሆናችሁ እናውቃለን። በአስቸኳይ አቁሟት። እኮ እናንተ ስለ ዓውደ ምሕረት ጨንቋችሁ?! አዛኝ ቅቤ አንጓች። አቡነ ኤርምያስ መጪውን ልደት ተንተርሰው ከአቢይ አህመድ ጋር ተመሳጥረው ስውር ቡድን አቋቁመው ሊሠሯት ያሰቧትን እናውቃለን። እርምጃችሁ የተሰወረው ከሰው ነው እንጂ ከእግዚአብሔር፣ ከቅዱሱ ከላሊበላ፣ ከሊቃውንተ ኢትዮጵያ የተሰወረ አይደለም። እኛ በየዓውደ ምሕረቱ መልስ እንዳንሰጥ ታሳስሩናላችሁ፣ ታስገድሉናላችሁ፣ የመተንፈሻ ቦታ መድረክ ወይም ሚድያ የለንም። ያለን አማራጭ በዘመዴ በኩል ብቻ ለዓለሙ ሁሉ ማቅረብ ነው።
"…ሊቃውንቱ ይቀጥሉና አባ ኤርምያስ ሆይ ታሪክ አያበላሹ። በቅዱስ ላሊበላ ደብር ላይ ደም ባያፋስሱ መልካም ነው። የሚሄዱበትን ርቀት ካልገቱት ደም መፍሰሱ አይቀርም። ልደትን ተንተርሰው የውስጥ ቅርስ ቆጠራ እንዲካሔድ እና በረቀቁ ካሜራዎችና ባለሞያዎች የብራና መጻሕፍትን፣ ቅርሶችንና ንዋያተ ቅድሳትን እስካን ለማድረግ እንዳሰባችሁ አውቀናል። ያወቅንበት መንገድ አያገባችሁም። ለዚህ የስውር ቡድን አቀነባባሪ፣ ተባባሪ፣ ሠሪ ተላላኪ የሆነ ነጭም ይሁን ጥቁር፣ አውሮፓዊም ይሁን አፍሪካዊ ዝም ብለን ዓናይም በክብር ሰማዕትነትን እንቀበላለን። ያለ ምክንያት እየሞትን አይደል? በክብር መሞት ጌጥ ነው። ይህ ከመሆኑ በፊት ፈረንሳይም፣ አቢይም፣ አባ ኤርምያስም፣ የደብሩ ሠራተኞችም ቁፋሮውን የእስካኑን ጉዳይ ብትረሱት ይሻላል። የማይሆን ከሆነ ግን ሞተን የዓለም አጀንዳ እናደርገዋለን። በዚያውም የአቡነ ኤርምያስ እምነተቸው፣ ማንነታቸው፣ አስተዳደጋቸው ሁሉ እንዲጠናልን እንፈልጋለን። ይህን ያክል አረመኔነት ከምን የመነጨ ነው? አቡኑ ማናቸው? ወደ ጵጵስና የመጡበት መንገድ እንዴት ነው? እንዲመረመር እንፈልጋለን። አንድ ጳጳስ ክርስትና እንዲወድም በዚህ ልክ ያለ እረፍት ሲሠራ ዓይተን አናውቅም። እባክህ አክሊለ ገብርኤል ማንነታቸውን አጣራልን። መልካቸው ነው እንጂ ሥራቸው ኢትዮጵያዊ አይመስለንም። ከአሁን በኋላ ሁሉም ነገር ግልጽ ሆኖ ስላየነው ማንንም አንሰማም። ብቻችንን አንታሰርም፣ ብቻችንን አንሞትም። ማንን ይዘን እንደምንሞት እናውቃለን ይላሉ ሊቃውንተ ኢትዮጵያ በምሬት። እኔ በበኩሌ የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና የከሚሴ ልዩ የኦሮሚያ ዞን ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ወሎዬ ነው የሚመስሉኝ። ሌላ ማንነት እንዳላቸውም አላውቅም። የሚያውቅ ካለ ግን ለመስማት ዝግጁ ነኝ።
"…ሊቃውንተ ኢትዮጵያ ይቀጥላሉ። ዘመዴ ሰሞኑን አቡነ ኤርምያስን ላሊበላ ከተማ ውስጥ ለስብሰባ ሲንቀሳቀሱ ስታይ አቢይን የምታይ ነው የሚመስልህ። በኮማንዶ ጦር ታጅበው፣ ከተማው በድሽቃ ታጥሮ ነው የሚጓዙት። የላሊበላ ሕዝብ ጉድ ነው ያየው። እንዴት አንድ ጳጳስ በዚህ ልክ ይታጀባል? መንግሥትን ምን ያህል ቢጠቅሙት ነው? የላሊበላ ምእመን ይህንን እወቅ፤ አቡነ ኤርምያስ ወደጠሩት ስብሰባ፣ እነ መንግሥቴ ወርቁ ወደሚመሩት ስብሰባ አትሒድ። ከሄድክም በንቃት ተከታተል። ባገኘኸው አጋጣሚ ቁፋሮውን አስቁም። እውነተኛ ካህናት ገበዞችን ጠብቅ። ከዛሬ ጀምሮ አንድ ካህን ወይም አንድ መሪጌታ አሊያም አንድ ምእመን ቢታሰር ቢገደል ሙሉ ሓላፊነቱን አቡነ ኤርምያስ ይወስዳሉ።👇①✍✍✍
መልካም…
"…አመስጋኙ 1ሺ አልፏል። አሁን በቀጥታ ወደ ተጠባቂው ርእሰ አንቀጻችን እናመራለን። ምሽቱን እስ እኩለ ሌሊት ድረስ በርእሰ አንቀጻችን ላይ ስንወያይ እናመሻለን።
• በትግራይ ተከሰተ የተባለውን ራብ በተመለከተም ባሰፈርኩት ሓሳብ ላይ አስተያየት መስጠት መብታችሁ ነው።
• ሌላው ምድረ ወሮ በላ መንገደኛ ዱርዬ ሁላ ቀፎውን ስለነካሁበት ተሸፋፍኖ የነበረው በሙሉ ተገላልጦ መለፍለፍ ጀምሯል። ቤተ ክርስቲያን የከሰሩ ዘራፊ ፓስተሮች መራጊፊያ ወደብ አትሆንም። አዳሜና ሔዋኔ የእኔ ሥራ ጠቅ ማድረግ ነው። ከዚያ ወጥተህ መለፍለፍ የአንተ ሥራ ነው። አለቀ። ጀመርኩህ እንጂ መች ነካሁህ አባቴ። ፓስተሪቶችና ፓስተሩ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ላይ ጠብቁኝ። ኦሮሞ ነኝ አልክ፣ ብልፅግና ከወልቃይቴው ሎዛ ኢቨንት ጋር ቤተ ክርስቲያንን መጋጥ ብሎ ነገር የለም። ፓስተርዬ ጧ በል አልኩህ። ኦሮሞነት፣ ዐማራነት፣ ትግሬነት ወዘተ የሌባ መደበቂያ አይደለም። ጥፋ ከዚህ አጭቤ ሌባ ሁላ። 😂
"…ዛሬ የምናነበው ከሊቃውንተ ኢትዮጵያ ጋር የጀመርነውን ክፍል ሁለት የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትና የቀንቀኒት ሚካኤል የእሁድ ስብሰባን በተመለከተ ነው።
• አላችሁ አይደል…?
1.82 MB
14.20 MB
