es
Feedback
ግጥም ብቻ 📘

ግጥም ብቻ 📘

Ir al canal en Telegram

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch @shiyach_bicha@zefenbicha @leul_mekonnen1

Mostrar más
2025 año en númerossnowflakes fon
card fon
65 745
Suscriptores
-924 horas
-597 días
-32030 días
Archivo de publicaciones
.......... ላመልክህ አልኩና ስምክን እየጠራሁ፤በእንባ ላመሰግን ይታየኛል ደሞ ጸሎቴ በሙሉ፤ደሮሶ ጉም ሲዘግን እኔ አንተን አይደለው በመከራ መጽናት፤ከቶ አላውቅበትም ለሚገርፈኝ ሁሉ ይቅር በለው እያልኩ፤አልጸልይለትም ላመልክህ እልና ምስጋናዬን ትቸው እየኝ ስብሰለሰል ሁለት ስለት መሆን ይቃጣኛል መሰል በስምህ መጽውቶ ስምህን ተጣርቶ እራፊ ለሚያጣ አንበጣ ብትልክ መአት ብታመጣ ይህ አይደል ተአምር ይህ አይደል አምልኮት እሳት ላዘነበ ውሀ ነኝ መለኮት ታድን እነደሆነ እሲቲ አሁን አድነኝ፤ቀናት አይቀጠር ጋንን ለደገፈ፤ይከብደዋል ጠጠር ..... ...... ላመልክህ እልና .... ...... ደሞ እተወዋለው መካድ እንዳይመስል ክህደቴም ሀቅ አለው ... ..... By @Mad12titan @getem @getem @getem
Mostrar todo...
👍 43 9😢 6😱 5👎 3🔥 2
ቤት እማ ጨዋ ነሽ፣ እንኳን ሌላ ሌላ እኔንም አታይም፣ ግን እድሜ ለሱሱ፣ ወተሽ ወዳጅ ካየሽ አታልፊም አትተይም። የሸመገለን ወንድ፣ በሰለቸ ዐይንሽ ዕያየሽ ወጠምሻ፣ የሱን መድሃኒት፣ አርገሽ ለቀን ያዝሽው የኔን ማስታገሻ By @tafachgitm @getem @getem @getem
Mostrar todo...
👍 19 3
................ ዛሬም እንደትናትና ናፈቅሺኝ ከንደገና ተገዝ የበዛበት የቀናው ጎዳና ውብ መልክሽን ሳለ ከመንገዱ መሀል ላመል የበቀለው ዘንባባና ጥዱ ሳቅሽን የመሰለው ፈገግታሽን ኳለ! የለማኝ የተሽከርካሪው የማቲው ጫጫታ እራቀኝ ከመንገድ መሀል ገትሮ በህላዌ አመጠቀኝ አካልሽ ከኔ ባያርፍም፤ጥላሽን ዳብሼ ጸናሁ ዳናሽ ከከተበበት፤በጽናት ልቤን መራሁ ደረስኩብሽ ስል ስትርቂኝ ቀሚሽን ያዝኩ ስል ስትነጥቂኝ ማፍቀር ሲያደናቅፈኝ ተስፈ ሆኖኝ እንቅፋት በበቀል እንዲሽርልኝ የነፍሴን ስብር እጥፈት ትናንት እንዳልነበረ መዳፍሽ እንዳልዳበሰው አላውቅም በሚል ቃል ክጄ ፍቅርሽን እንዳላረክሰው ትዝታሽ መግል ሆነብኝ ናፍቆትሽ የጊዜ ቁስል ጎዳናው ይፈካልኛል ጫጫታው መልክሽን ሲስል መከተል መሄድ መጓዝ ነው ጥላዋን ያፈቀረ ሰው መንገዱ የቀናለትን ልመና እንዳይመልሰው ቃላት አይከጅሉትም ገላ ያልበቃውን ሰው ጠልቼሽ እንደዲድንልኝ የፍቅርሽ የነፍሴ ቁስል ሸሽቼሽ እንዲሰምርልኝ ህይወቴ ህልም እንዲመስል ሀሞቴን አምርሬ ሀጥያትሽን ደርድሬ እረሳሁሽ ብዬ መንፈሴን ሳጽናና ትናፍቂኝ ጀመር ዛሬም እንደገና By @mad12titan @getem @getem @getem
Mostrar todo...
👍 27 17🔥 1😢 1
............ በስሜት ተናንቀን በስጋ ተዋውቀን ገላሽን ስሞቀው ወዝሽን ስጠምቀው ጠረንሽ ሰንፍጦኝ ጥፍርሽ ላመል ልጦኝ የስሜት ጣረ ሞት ውስጥሽን አፍሞት ፍቅርን ስንሰራ ..... ........ ............ ውል ከሌለው ስፍራ ደከም ስትይ አርፈሽ ክንዴን ተደግፈሽ ፍቅርን ስታወጊኝ በአሽሙር ስትወጊኝ በህጻን ፈገግታ ያዋቂ ጨዋታ ብ........ዙ ስናወጋ .... ...... ......... እንደ ድንገት ነጋ አይኔን አጨፍግጌ ገላሽን ፈልጌ ላቅፈው ብንጠራራ ላወራሽ ብጠራ ህልም ነው የለሽም ያወጋሁሽ ሁሉ ያደረግነው ሁሉ ፍሬው አልደረሰሽም ? By @Mad12titan @getem @getem @getem
Mostrar todo...
31👍 25😢 11😁 1
ተይው (kerim) ተይው አላገግም መዳን አልፍልግም ስለ አንቺ መታመም መዳኔ ነው እና አንቺን በማፍቀር ውስጥ እኔ ልጣ ጤና ተይው........ By @poem2513 @getem @getem @paappii
Mostrar todo...
40👍 21🔥 9👎 1
የእግዜር አፍቃሪ (የሞገሤ ልጅ) እጅሽ ድብቅ የለው፣ ያለውን ሳይሰስት መዘርጋት ይወዳል፣ እንጀራው በመሶብ፣ ጠላው በእንስራ ጥጋብን ያደምቃል። ጨለማም ይያዘው፣ አቶም ቤትሽ ይግባ የእግዜር እንግዳ፣ መቀበል አትሰንፊም፣ ቀድሞም ቤትሽ ለሠው ስለተሰናዳ። እኔን ግን ያልገባኝ፣ የእግዜር እንግዳን መቀበል ሳትፈሪ፣ የከበደሽ ነገር፣ ክብድ ያለሽ ነገር የእግዜር አፍቃሪ። By @eyadermoges1 @getem @getem @paappii
Mostrar todo...
👍 25 13🔥 6😱 1
............. እንቆቅልህ ትለኛለች ምን አውቅልሽ ሳለ መልሴ ሀገር ስጠኝ ትለኛለች አይሰስትም ለሷ ነፍሴ ትውስድ ሀገር ምን አታበት ተጠይቆ በሷ አንድበት ማን ወንድ አለ የመለሰ ? ሀገር ስጠኝ ባለች ቅፅበት ሀገር ሰቷት ተመለሰ By @mad12titan @getem @getem @getem
Mostrar todo...
47👍 24🔥 7🤩 4🎉 1
ሌሎችም ውስጥ... (ሳሙኤል አለሙ) መች ኑር ብለሽኝ... አልኖርም አልኩ፤ መች ሙት ብለሽኝ... አልሞትም አልኩ፤ በክቡራን'ና ክቡራት አልታይሽም እየተቀደምኩ። እንደው... ታክቶሽ እንጂ ለምስጋናው ዝለሽ እንጂ ለፍለጋው፤ አታጭኝም ነበር... ሌሎችም ውስጥ እየተጠጋጋው። ሳሙኤል አለሙ @Samuelalemuu @getem @getem @getem
Mostrar todo...
22👍 13🔥 4🤩 4
............. ትንሽ ትንሽ የቆጠብናትን ሳቅ ነይ አብረን እንሳቅ የእንባ ላቦት ፊቱን አጥቦት የኑሮ አለት ከሚጋፋ በለቅሶ ጉም የሚጠፋ የህመም ሲቃ የቋጠረ ያንገቱ ክር የከረረ አንቆ እስትንፋስ ለሚነጥቀው እያላላ ከሚስቀው የሰው መንጋ ሳንጠጋ ገሽሽ ላርግሽ ካለምኩበት ልመሽግሽ የፎረፍናት ከፈጣሪ የደበቅነው ከአሳዳሪ አለኝ ቦታ ድረሽ ላፍታ እዚህ ጋራ ባልልሽም የማልመው አይጠፈሽም ተገኚልኝ ከቀጠርኩሽ ንገሺልኝ ከሰየምኩሽ ካነገትነው የቀን ቀንበር ከወረስነው የቂም መንበር እሽቅድድም ከበዛበት የደበቅናት አንዲት ዕለት ለደም ቁርባን የበግ መባን ከለመደው ከሚወደው የሸሸግናት የቀለስናት አለች ቦታ ድረሽ ላፍታ የህይወት ምሰሶ ቁልቁል ተደርምሶ ጨፍልቆ እስኪገለን ላፍታ ገሸሽ ብለን ትንሽ ትንሽ የቆጠብናትን ሳቅ ነይ አብረን እንሳቅ By @mad12titan @getem @getem @paappii
Mostrar todo...
25👍 21😁 6🤩 2
ቀኝ ጉንጬን ቢመታኝ ግራ አቀረብኩለት ያንገቴን ቢነጥቀኝ የእጄን ደገምኩለት ተማምኜው ነበር መዳኔን በፍትህ ዱላው ሲጠነክር አልዞር አለኝ ፊትህ የወለዱትን ልጅ ነጥቆ እንደማስታቀፍ ያቆሰለን ስቆ በእመነት እንደማቀፍ ምን አለ የከበደ ? ያልጸነሰ ሆዷ ቢያምጥ ምን ወለደ ከደረቀ ጡቷ ምን አስጎነጨችው የያዕቆብ ዘር ብላ ልጄን ነጠቀችው በስምህ ነው አሉ በደሉ በሙሉ ነጻነቴን ነጥቆ ክቡሩን እያሻረ ምነውሳ አብርሀም ቃልኪዳኑን ሻረ ለመከነ መሀጸን ፍሬ ላላደለው ከእቅፌ ነጠቁኝ የያዕቆብ ዘር ብለው በስምህ ነው አሉ ገራፊው በሙሉ ቀኝ ጉንጬን ቢመታኝ ግራ ደገምኩለት ግራዬን ቢደግመኝ ምኔን ላቅርብለት ትግስትም ጡር አለው ለማመንም ገደብ ከገራፊዋች አፍ ወንጌልህ ሲነበብ ቃልህ አያጽናናም ፍቅርህ አያጸናም ሜቼም የናት አንጀት ለወለደው እንጂ ላመለከው አይደላም የእንባ ማድጋህን በንሰፍረው አይሞላም ህግጋት አላቅም ቅኖናና ዶግማ ትፈርድልኝ እንደው መበደሌን ስማ በስምህ ነው አሉ በዳዩ በሙሉ ስለት ያበዛብን ጭነት የጣለብን ጋን ላቆመ ጠጠር ጠብታ የመቆንጠር ያህል ለወደደኝ በክብሩ የማገደኝ ሴትነቴን ንቆ ጭኖቼን ፈልቅቆ ሲደፍረኝ የዋለ ለስምህ ነው አለ! The Handmaids Tale : Nolite te bastardes carborundorum By mad12titan @getem @getem @getem
Mostrar todo...
👍 21 12😢 4👎 1
ሆድ ለባሰው አንጀት        እንባ እንደው አይገድም ፍቅርንና ናፍቆት መለየት ያቃተው         ለማፍቀር አይሄድም ድም       ድም             ድም                   ድም   ማሰብ ማሰላሰል    አስታወስኳት መሰል ነጋሪት ቢጎሰም መለከት ቢነፋ ከ'ሷ ዘንድ አድርሶ ከ'ኔው ዘንድ ሚመልስ አንድ ዜማ ጠፋ ሁሉም ወሳጅ ሆነ አድርሶ የሚያስቀር ታድያ የናፍቆት ነው እንጂ እንዲህ ሆነ ማፍቀር? እንጃ እንጃ እንጃ ከራስ ጋር ፍጥጫ በምሰማው ዜማ እሷን ሚያስታውሰኝ         አንድ ነገር አላት      ቆይ እሷ ምንድን ናት ብናፍቅ ሳልከጅል እባላለው ወይ ጅል? ብተክዝ ብፈዝም በሃሳብ ነበልባል ናፈቃት ነው አፈቀራት ምባል? አይ.....አይ አይ ናፈኳትም አልናፈኳትም ብቻ አላፈቀርኳትም። ዮኒ       ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
Mostrar todo...
👍 31 8🤩 4🎉 1
ልኬ እንደቆጨችኝ ፡ ቴክስት ሜሴጄ እኔም ከተሸኘሁ ፡ላልመለስ ሄጄ አታቻኩለኝ እግሬ፡ አታጣድፈኝ እጄ ቀናት ከማፋሰስ ፡የማይለቀሙ ቃላት ከማፋለስ ፡ለትርጉም አዝግሙ ያኖሩትን ማንበብ ፡ የኖሩትን ማሰብ፡ እየደጋገሙ። ልፃፍ ጊዜ ስጡኝ ልረፍ ብዕር ስጡኝ ፊደላት አድምጡኝ፡ አካላቴም ስሙ... መንገዱን ላትዘልቁ፡ ልቤን አታድክሙት የደረስኩበትን፡ ልድረስና ልሙት። By red-8 @getem @getem @paappii
Mostrar todo...
25👍 19🎉 2🔥 1
ስንብት ----------------- ተሰነባብተንም አይቆሮጥልኝ ፍቅርህ በኔ ላይ ካስቻለህ ያው መንገዱ ይቅናህ ። ሁሌ ማወዛገብ ሁሌ ማስፈራራት ሁልጊዜ መታመም ሁሌ መሰቃየት ለኔ ካሰብክልኝ እስኪ ልቤን ያዛት ። ጭንቀትህን ንገረኝ ህመምህን ልታመም ልሞት ነው አትበለኝ .......... ፍቀድልኝ እና እንይ ይቺን አለም። እጅህን ልያዛት ከሞትንም አብረን ነው አይተን ያለም ግዛት። እየተሰናበትክ ነፍሴን አስጨነካት የኔ ፍቅር ፍቀድልኝ እና ነፍስህን ልያዛት ። by Bline asefa @getem @getem @paappii
Mostrar todo...
49👍 20👎 10🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
📌 Free entry Short movie Comedy Music ( full band ) Poem Magic Live painting & other .. 0935697143 for previous show, Check our channel 👇 https://youtube.com/channel/UC9ItbVvxXMLV7QIT-rCJyTg?si=Mj5GlhjsE1ZvBtjM @getem
Mostrar todo...
👍 18 1🔥 1
📌 Free entry Short movie Comedy Music ( full band ) Poem Magic Live painting & other .. 0935697143 for previous show, Check our channel 👇 https://youtube.com/channel/UC9ItbVvxXMLV7QIT-rCJyTg?si=Mj5GlhjsE1ZvBtjM
Mostrar todo...
REVUE 5.jpg7.16 KB
ማጉያ ያንዳንዷ ቆንጆ ሴት: ውበት የሚጎላው: በምታስከትላት: አስጠሊታ ሴት ነው:: By yisimak worku @getem @getem @paappii
Mostrar todo...
😁 71👍 33 19👎 8🔥 4😱 4🤩 3
አካል ቡጢን ፈርቶ በምላሴ ሸጥኳት እህቴ ናት ብዬ እኔው ሚስቴን ዳርኳት ዮኒ      ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
Mostrar todo...
😁 43👍 25😢 10 8
* ስትፈጥን አትቸኩል * አበው የተረቱት ቃላቶችን መርጠው ከመናገር አልፈን ውስጥ ውስጡን ብናየው የቃላት መረጣ የአስተሳሰብ ርቀት የምሳሌ አይነታ ይንግግር ምጥቀት ”የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል” የሚለውን ስናይ ውስጡን ስንመረምር ከቃላት ዉስጥ መርጠን ትርጉም ስንበረብር የተጠቀሙት ቃል ስህተቱን መግለጫ ጥፋት ሁኖ አገኘን የ ችኩል መቋጫ እዚጋር ልብ አድርግ ላዩ ግልጽ ቢመስልህ ሃሳቡ እንደ ጀንበር ትርጉሙ ረቂቅ ነው እንደ ወርቅ ሚቆፈር የጅቡ ጥፋቱ የጅቡ ስህተቱ አይደለም ፍጥነቱ ... ፍጥነት መሄጃ ነው የጊዜ መለኪያ የማስተዋል ስራ የሰአት ማትረፊያ ፍጥነት ግዜያችን ነው ቶሎ መገስገሻ መሪያችንን ሳንለቅ በሰአት መድረሻ ችኩልነት ግን የማስተዋል እጥረት የዉሳኔ ችግር የቅንብር ድክመት በጎን የሰሩትን በሌላው ጎን ማፍረስ ሲለቅሙ የዋሉትን ከመሬት ላይ ማፍሰስ ወደ ግራ ወደ ቀኝ ከፊት ወደ ኋላ ዙርያን ሳያጤኑ እንዲያው በችኮላ መራመድ ግብ አድርጎ ወደ ፊት መገስገስ መድረሻ እያሰቡ እዛው መንከላወስ... ዛሬን እያሰበ ነገውን ዘንግቶ ነገን እያሰበ ዛሬዉን ረስቶ እንደ ችኩሉ ጅብ መያዙን አስቦ ቦታዉን የሳተ ዛሬን እያሰበ ነገን ያልገመተ ከአደኑ በላይ ሌላ ስራ ፈጥሮ በአደነው እንስሳ ቀንድ ተቸንክሮ አለያም ... መብላቱን አስቦ ረሀብ ጠንቶበት ጠኔዉን ሊያስታግስ ሆዱን ሊያጠግብበት ነገን እያሰበ ዛሬዉን ረስቶ ቦታ ስቶ ቢነክስ ማስትዋል ዘንግቶ ፍጹም ከገመተው ነገር ተዟዙሮ እራሱን አገኘው በደሙ ተነክሮ እናም አደብ ግዛ ማስተዋሉን ይስጥህ ፍጥነትን ስታስብ ችሎታው ይኑርህ የመወሰን ብቃት መሪው አይለይህ የአበውን ተረት በጥልቀት ስናየው አትፍጠን ሳይሆን ... ስትፈጥን አትቸኩል ሁኖ አገኘነው። By ዘይድ ሁሴን ቅዳሜ ፣ ጥር 24 ፣ 2017 ዓ.ም @getem @getem @getem
Mostrar todo...
👍 55 35🎉 8🔥 4😢 1🤩 1
ፍቅር በቃኝ እኔ ልበ ስንኩል ማፍቀር የተሳነኝ የወደድኩትን ውድ ጨርሼ ማልገኝ መውደድን ለመውደድ ኃይል ያጠረኝ ካቅሜ አንጠፍጥፌ ልጠቀለል ባንድ ሰው ሥር አረፍ ልል ብጥር ብጥር ለጨዋታ ሆኗል አሉ የፍቅር ነገር  እውነት ቀርቶ በትብብር እንደውም ሰዶ ማሳደዱም ደክሞኛል ሰጥቶ መቀበሉም እንዲሁ የገባው ሰው እስኪመጣ የራሱ የፍቅር ትርጉሙ መፅሐፉ ላይ የተፃፈው እንደዚህ ነው የተባልነው  እርሱ ሰው ተገኝቶ እስከሚያሳርፈኝ ፍቅር በቃኝ By yodan @getem @getem @getem
Mostrar todo...
31👍 24🔥 5👎 2
በእናትህ እቀፈኝ ለልጅህ እጅ ዘርጋልኝ ማደፌን አይተህ ላታልፈኝ፣ ጌታ ሆይ አምላኬ ባክህ በእናትህ አግዜር እቀፈኝ። በእናትህ እቀፈኝ ... ከክንድህ አፈንግጫለሁ በተግባር ከቤትህ 'ርቄ፣ በሀጥያት ተጎሳቁዬ ቆሽሼ በአለም ወድቄ፣ አትሁን ያልከኝን ስሆን አትስራ ላልከኝ ስተጋ፣ ጎንህን እንደ ለንጊኖስ አድፌ አንተን ስወጋ፣ መቅደስህ ውብ ሰውነቴን በእርኩሰት እቆሽሻለሁ፣ በእናትህ እቀፈኝ ጌታ ካቀፍከኝ እመለሳለሁ። ለበደልኩህ በደል ላደረስኩብህ ግፍ፣ በምህረት ካልመጣሁ ከላይ መቅሰፍት አርግፍ፣ አንደበቴን ዝጋው ቅስሜንም ሰባብረው፣ ሃሳቤን አጨልም እውቀቴን ቅበረው። መዝለሌን ግታልኝ ለሀጥያት ምርኮ፣ አቅሜን አንበርክከው ለክርብርህ አምልኮ፣ የአለም ጉልበቴን በሽንፈቴ ተካ፣ አለምን ልናቃት በስምህ ልመካ፣ ሰው አርገኝ ጌታዬ ልጅህን አትርፈኝ፣ አምላኬ በድንግል በእናትህ እቀፈኝ፣ ማወቄ አልጠቀመኝም ማደጌ እያደር ጎዳኝ፣ መናገር ከንቱ ልፋት ነው ለነፍሴ አንድም አልረዳኝ፣ ባውቀውም ምን እንደማደርግ በሀጥያት እንደተመራሁ፣ መመለስ ባለመቻሌ ለነፍሴ አሁንስ ፈራሁ፣ ፍርሀቴን ተቀበልና ለቤትህ ለንስሀ አብቃኝ፣ በእናትህ ጌታዬ እቀፈኝ ከእቅፍህ መራቈ በቃኝ። በእናትህ እቀፈኝ ... Join(@gitimtm) ✍ ይቴ (@gtmwustie) @getem @getem @gitimtm
Mostrar todo...
👍 44 35