es
Feedback
Tikvah-University

Tikvah-University

Ir al canal en Telegram
2025 año en númerossnowflakes fon
card fon
352 855
Suscriptores
-4824 horas
+967 días
+1 45930 días
Archivo de publicaciones
Photo unavailableShow in Telegram
#ExitExam በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ያድርጉ! የተፈታኞች የምዝገባ ጊዜ፦ ከታህሳስ 06-13/2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን የምትፈተኑ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባችሁን በተጠቀሱት ቀናት ማድረግ ይጠበቅባችኋል። @tikvahuniversity
Mostrar todo...
👍 223 125👎 23😢 14🥰 11👏 5😱 4🙏 3
Photo unavailableShow in Telegram
#AAU በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተከፈተው የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ዛሬ ይጠናቀቃል። የህጻናት መጻሕፍት፣ የታሪክ መጻሕፍት፣ ልብወለዶች፣ የፍልስፍና መጻሕፍት እና ሌሎችም በተመጣጣኝ ዋጋ በአውደ ርዕዩ ያገኛሉ። በዋናው ግቢ (6ኪሎ) የባህል ማዕከል የተከፈተው አውደ ርዕይ፤ ዛሬ ታህሳስ 05/2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል። ይጎብኙ፣ ይሸምቱ! 🕙 እስከ ከሰዓት 11:00 ሰዓት @tikvahuniversity
Mostrar todo...
48👏 1🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
🎓 ለተማሪዎች እና ለሥራ ፈላጊዎች! የእርስዎ የሥራ ፍለጋ ጉዞ ከእኛ ጋር ቀላል፣ ፈጣን እና ተስፋ የተሞላበት ይሆናል! የኛን አገልግሎት ተጠቅመው ከሚያገኙዋቸው ጥቅሞች፦ ⚡የሙያ ብቃት፣ ልምድ እና የግል መረጃዎችን ያካተተ ፕሮፌሽናል የሥራ መግለጫ (Profile) መፍጠር፣ ⚡በሚመርጡት የሥራ ዘርፍ አዲስ ማስታወቂያ ሲወጣ ፈጣን የቅፅበት ማሳወቂያዎች (Notifications) ይደርስዎታል፣ ⚡የቅጥር ሂደትን መከታተል የሚያስችልዎ፣ ⚡በሰው ሰራሽ ክህሎት (AI) የተፈጠሩ መልዕክቶችን መፃፍ፣ ⚡ሥራዎችን በቦታ፣ በሙያ ብቃት እና በሥራው ዓይነት መሠረት መፈለግና ማጥራት (Filter) ማድረግ፣ ⚡በቦቱ በኩል ከአሠሪዎች ጋር በቀጥታ መገናኘት! ⚡የትርፍ ጊዜ (Part-time)፣ የሙሉ ጊዜ (Full-time)፣ የልምምድ (Internship) እና የርቀት ሥራ (Remote) አማራጮች የሚያገኙባቸው፣ 👇🏾 ይህን ሊንክ በመጫን AfroJobLink ን ይቀላቀሉ! ፈጣን የሥራ ቅጥር ያድርጉ! 🌐  https://t.me/afrojoblink ለበለጠ መረጃ፦ 0911745927 / 0911632184
Mostrar todo...
62👍 4👏 2😱 1🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#MoE በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድራችሁ ያለፋችሁና በየትምህርት ቤቶቹ የተመደባችሁ የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 11 እና 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ወደ ትምህርት ቤታችሁ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ለ9ኛ ክፍል የሚያስፈልጉ የመማሪያ ቁሳቁሶች (ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ ቦርሳ፣ የስፖርት ትጥቅ፣ ወዘተ) ➫ የመኝታ አልባሳት (አንሶላ እና ብርድ ልብስ) ➫ ስትማሩ ከነበረበት ትምህርት ቤት መሸኛ እና የትምህርት ውጤት ዩኒፎርም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውል ከያዘበት አቅራቢ ድርጅት በራሳችሁ ወጪ የሚሸፈን መሆኑ ተመላክቷል። ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞ ወይም ዘግይቶ ወደ ትምህርት ቤቶቹ መሔድ እንደማይቻል ተገልጿል። @tikvahuniversity
Mostrar todo...
135👍 17👎 14🙏 5
Photo unavailableShow in Telegram
የፋይዳ መታወቂያ ያውጡ! ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ማውጣት እንዳለባቸው ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች የሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ተማሪዎቻቸው በሙሉ የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) እንዲያወጡ እያደረጉ ነው፡፡ ብሔራዊ መታወቂያው ለምዝገባ፣ ለፈተና እንዲሁም ለተለያዩ የግቢ ውስጥ አግልጋሎቶች ግዴታ እንደሚሆንም እየተገለፀ ነው፡፡ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ለመውሰድ፣ ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ለመፈተን፣ የብቃት ምዘና ፈተና (Licensing Exam) ለመውሰድ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና (ESSLCE) ለመውሰድ ብሔራዊ መታወቂያ ማውጣት የግድ እንደሆነ በመንግሥት መገለፁ ይታወቃል፡፡ @tikvahuniversity
Mostrar todo...
96👎 77👍 18😱 3
Photo unavailableShow in Telegram
የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በመጪው ዓመት የማሪታይም ስልጠና መስጠት ሊጀምር ነው፡፡ ኢንስቲትዩቱ በአሁኑ ወቅት የስርዓተ ትምህርት ቀረጻ እያካሔደ ሲሆን፤ ስልጠናውን በቀጣይ ዓመት ለማስጀመር አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡ የሀገሪቱን የገበያ ፍላጎት በማጥናት ከደረጃ ስድስት እስከ ደረጃ ስምንት (ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ፒኤችዲ) ደረጃ የሆኑ አዳዲስ ስልጠናዎች በኢንስቲትዩቱ እየተሰጡ እንደሚገኙ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡ አዲስ ከተጀመሩ የስልጠና መስኮች መካከል የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI)፣ የኒው ኢነርጂ ቬሂክል፣ ባዮ-ሜዲካል ቴክኖሎጂስ እና ሳይበር ሴኪውሪቲ እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል። #ኢፕድ @tikvahuniversity
Mostrar todo...
27🙏 5👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ያኔት_ኮሌጅ 🔔 በምዝገባ ላይ ነን! BSc Fields of Study: → BSc in Medical Laboratory Science → BSc in Pharmacy → BSc in Nursing TVET Programs: → Nursing → Medical Laboratory → Pharmacy → Accounting and Finance → Hardware & Networking Service → Radiography የCPD ማዕከል አገልግሎት ☎️ 0929969696 / 0996828282 አድራሻ፦ 📍 መሳለሚያ ሰፈረ ሰላም ንጉሴ ቱሩፊ ህንፃ 📍 6 ኪሎ ካምፓስ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት አጠገብ Telegram: @Yanet6kiloc
Mostrar todo...
16👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የሞዴሊንግ (Modeling Art) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! 👉 ከሞዴሊንግ ቴክኒኮች ጀምሮ የተለያዩ የሞዴሊንግ ዓይነቶችን በተግባር በአንድ ላይ አካቶ የሚሰጥ ስልጠና 👉 በተቋማችን አዳራሽ የሞዴሊንግ ዝግጅቶችን በማቅረብ ራስዎን በበለጠ የሚያስተዋውቁበት 👉 በሞዴሊንግ ዝግጅቶች ላይ የሚያሳትፍዎትን ዕድል የሚያገኙበት ስልጠና ☎️   0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/ Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Mostrar todo...
30🥰 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#DillaUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ ➫ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ አዳያኣ ግቢ፣ ➫ በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ ሀሴደላ ግቢ። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3x4 የሆነ አራት ፎቶግራፍ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ። @tikvahuniversity
Mostrar todo...
142😢 20👏 11🙏 9🥰 6👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
#WolaitaSodoUniversity ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ትምህርት ወደ ተቋሙ ለተመደቡ ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል። የሪሚዲያል ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም እና በቦዲቲ ካምፓስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ጥር 01/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ ➫ ስማችሁ ከ A-B የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቦዲቲ ካምፓስ፣ ቦዲቲ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ C-R የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዋናው ግቢ፣ ወላይታ ሶዶ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ S-Z የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ፣ ታርጫ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ A-B የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቦዲቲ ካምፓስ፣ ቦዲቲ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ C-S የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዋናው ግቢ፣ ወላይታ ሶዶ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ T-Z የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ፣ ታርጫ ከተማ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ @tikvahuniversity
Mostrar todo...
123👍 91👎 28😢 11😱 8🙏 7🥰 3
Photo unavailableShow in Telegram
#MizanTepiUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ ➫ በማኅበራዊ ሳይንስ መስክ የተመደባችሁ ሚዛን አማን ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ፣ ➫ በተፈጥሮ ሳይንስ መስክ የተመደባችሁ ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 3 ኮፒ፣ ➫ መጠኑ 3x4 የሆነ የቅርብ ጊዜ ዘጠኝ ፎቶግራፍ፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ፡፡ @tikvahuniversity
Mostrar todo...
69😢 12👍 11🙏 9👎 8🥰 3😱 3
#ETA የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ፈቃድ ባገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሩና በ2018 ዓ.ም አጋማሽ #የመውጫ_ፈተና ለሚፈተኑ ተማሪዎች የማጣርያ መስፈርቶችን ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልኳል፡፡ ብቁ እጩ ተፈታኝ ሆኖ ለፈተናው ለመቅረብ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፦ ➫ የተማሩብት ተቋም የተሰጠውን የፈቃድ ጊዜ፣ የትምህርት መስክ እና ካምፓስ ማረጋገጥ፣ ➫ የተፈታኝ ሙሉ ስም እስከ አያት መኖሩን ማረጋገጥ፣ ➫ ወደ ተቋሙ በዝውውር የመጡ ተማሪዎች ካሉ የዝውውር ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ ➫ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በቀረቡት የመውጫ ፈተና ተፈታኞች መረጃ፣ በትምህርት መስኮች እና በካምፓሶች የስነ-ስርዓት ጥሰት የሌላቸው መሆኑ ማረጋገጥ፣ በትምህርት ላይ ቆይታቸው አራት፣ አምስት እና ስድስት ዓመት ለሚጠናቀቅ የትምህርት መስኮች በየመርሐግብሮቹ ሊረጋገጡ የሚገባ የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከላይ ከተያያዙት ምስሎች ይመልከቱ። @tikvahuniversity
Mostrar todo...
63🙏 7😢 4
Photo unavailableShow in Telegram
ዕድልዎን በ በሽ ይሞክሩ! ዛሬውኑ በሽ ይግዙ እና እስከ 1ሚሊየን ብር የማሸነፍ እድልዎን ከፍ ያድርጉ! *777*0# ላይ አሁኑኑ ይደውሉ! ዛሬውኑ የበሽ ጥቅሎችን እየገዙ በሽልማት ይንበሽበሹ! የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፦ https://onelink.to/ewsb22 የቴሌግራም ቦታችን 👇 https://t.me/official_safaricomet_bot #SafaricomEthiopia #MPESAsafaricom #furtheraheadtogetherether #besh
Mostrar todo...
23👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ScholarshipTip የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ኮሌጅ በኖርዌይ የልማትና ትብብር ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ ባስጀመራቸው በስነ ትምህርት የሁለተኛ ዲግሪ በሒሳብ ስነ ማስተማር (MED in Educational Sciences: Teaching of Mathematics) እና በስነ ትምህርት የሁለተኛ ዲግሪ በሳይንስ ስነ ማስተማር (MED in Educational Sciences: Teaching of Science Subjects) ፕሮግራሞች ከየካቲት 2018 ዓ.ም ጀምሮ #ነፃ የትምህርት ዕድል አመልካቾችን ተቀብሎ ለማስተማር ይፈልጋል። አመልካቾች ልታሟሏቸው የሚገቡ፦ ➫ የ2ኛ ዲግሪ ለመማር በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ ይኖርባችኋል፡፡ ➫ በባዮሎጅ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ እና ሂሳብ ትምህርት መስኮች የመጀመሪያ ዲግሪ ሊኖራችሁ ይገባል፡፡ ➫ ከላይ በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች የ2ኛ ዲግሪ ያላችሁ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡ ➫ የማስተማር ልምድ ያላችሁ አመልካቾች ቅድሚያ ይሰጣችኋል፡፡ ➫ በፕሮግራሞቹ ተቀባይነት ለሚያገኙ አመልካቾች ነፃ የትምህርት ዕድሉ በዋናነት የሚሸፍነው ለዩኒቨርሲቲው የሚከፈለውን የትምህርት ክፍያ (Tuition Fee) እና የምርምር ገንዘብ ሲሆን፤ መጠነኛ ወርሃዊ የኪስ ገንዘብም ይታሰብላችኋል፡፡ 🔔 አመልካቾች ዩኒቨርሲቲው ለ2018 ዓ.ም ሁለተኛ ሴሚስተር በሚያወጣው ማስታወቂያ የማመልከቻ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማመልከቻችሁን ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ለበለጠ መረጃ፦ 0929402311 / 0918766232 @tikvahuniversity
Mostrar todo...
102🙏 19😱 3
Photo unavailableShow in Telegram
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ የመምህራን የሥራ ቦታ ዝውውር ሊያስጀምር ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት በክልሉ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የመምህራን እና ትምህርት ቤት አመራሮች ዝውውር በዚህ ዓመት ሊጀመር መሆኑን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ደምስ እንድሪስ ገልፀዋል። የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር መመሪያ መሻሻሉን የገለፁት ኃላፊው፤ ዝውውር ለማድረግ ገዳቢ የነበሩ ችግሮች በተሻሻለው መመሪያ ምላሽ ማግኘታቸውን አስረድተዋል፡፡ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የታጠፉ የትምህርት ዓይነቶች ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራን አዲስ በተመደቡበት የትምህርት ዓይነት ዝውውራቸው የሚፈፀም መሆኑ ተመላክቷል፡፡ በዘርፉ የሚታየውን የሰው ሃይል ስምሪት ምጥጥን ለማረጋገጥም ያስችላል ተብሏል፡፡ ዝውውሩ ገቢራዊ ከመሆኑ በፊት በተሻሻለው መመሪያ ላይ በዘርፉ ለሚገኙ ባለሙያዎች ስልጠና የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል፡፡ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ከታህሳስ 30/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 10/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት የዝውውር ፎርም እንደሚሞሉ ተገልጿል። #አክትቢ @tikvahuniversity
Mostrar todo...
36👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የኮምፒውተር፣ የቢሮ ዕቃዎች እና የሞባይል ጥገና እና ኔትዎርኪንግ (Computer, Office Machine and Mobile Maintenance and Networking) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! 👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና 👉 የሶፍትዌር ላይ ጥገናን አካቶ የሚሰጥ ☎️ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Mostrar todo...
27👏 2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ArsiUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት አርሲ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3x4 የሆነ 4 ፎቶግራፍ፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ @tikvahuniversity
Mostrar todo...
130😢 23👎 15😱 11👍 9
Photo unavailableShow in Telegram
የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ይመዝገቡ! ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ17 የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በታህሳስ 2018 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡ በመሆኑም አዲስ እንዲሁም ነባር የመንግሥት እና የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hpe.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ አሳስቧል፡፡ የኦንላይን ምዝገባ ጊዜ፦ ከታህሳስ 02-12/2018 ዓ.ም ከተጠቀሰው የምዝገባ ጊዜ በኋላ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ Print አድርጋችሁ መያዝ እንዳለባችሁ ገልጿል፡፡ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ ተመዛኞች ምዝገባውን ለማካሔድ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ግዴታ በመሆኑ፣ የፋይዳ መለያ ልዩ ቁጥር (FIN) በትክክል እንድታስገቡ አሳስቧል፡፡ @tikvahuniversity
Mostrar todo...
66👍 10👎 5👏 1😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ይመዝገቡ! ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ17 የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በታህሳስ 2018 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡ በመሆኑም አዲስ እንዲሁም ነባር የመንግሥት እና የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hpe.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ አሳስቧል፡፡ የኦንላይን ምዝገባ ጊዜ፦ ከታህሳስ 02-12/2018 ዓ.ም ከተጠቀሰው የምዝገባ ጊዜ በኋላ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ Print አድርጋችሁ መያዝ እንዳለባችሁ ገልጿል፡፡ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ ተመዛኞች ምዝገባውን ለማካሔድ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ግዴታ በመሆኑ፣ የፋይዳ መለያ ልዩ ቁጥር (FIN) በትክክል እንድታስገቡ አሳስቧል፡፡ @tikvahuniversity
Mostrar todo...
😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ያኔት_ኮሌጅ 🔔 በምዝገባ ላይ ነን! BSc Fields of Study: → BSc in Medical Laboratory Science → BSc in Pharmacy → BSc in Nursing TVET Programs: → Nursing → Medical Laboratory → Pharmacy → Accounting and Finance → Hardware & Networking Service → Radiography የCPD ማዕከል አገልግሎት ☎️ 0929969696 / 0996828282 አድራሻ፦ 📍 መሳለሚያ ሰፈረ ሰላም ንጉሴ ቱሩፊ ህንፃ 📍 6 ኪሎ ካምፓስ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት አጠገብ Telegram: @Yanet6kiloc
Mostrar todo...
22👍 4