Addis Ababa Education Bureau
Ir al canal en Telegram
ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡
Mostrar más2025 año en números

150 232
Suscriptores
Sin datos24 horas
+677 días
+34630 días
Archivo de publicaciones
Photo unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ የቲያትር ጥበብ ውስጥ ጉልህ አሻራ ባሳረፈው አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለፅን ፤ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን እንመኛለን።
ፈጣሪ ነብስህን በአጸደ ገነት ያኑር።
(11/12/2017 ዓ.ም)
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
😭 150❤ 74💔 22👍 14😁 8🙈 7🏆 5🥱 3🖕 3🔥 2🙏 1
9,536 ጎልማሶች በክረምት ወቅት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ።
(9/12/2017 ዓ.ም) ትምህርቱ ቢሮው የ90 ቀን የንቅናቄ እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባቱን ተከትሎ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በተዘጋጁ የመማሪያ ጣቢያዎች በመሰጠት ላይ መሆኑን ከልዩ ፍላጎትና የጎልማሶች መሰረተ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ቢሮው በ2017ዓ.ም የክረምት ወቅት የ90 ቀን የንቅናቄ እቅድ አዘጋጅቶ እያከናወናቸው ከሚገኙ ተግባራት መካከል አንዱ ጎልማሶች በበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የትምህርት አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል መሆኑን ገልጸው ቢሮው ትምህርቱ በወጣለት መርሀግብር መሰረት በአግባቡ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን በጣቢያዎቹ በሚያደርገው ድጋፍና ክትትል ማረጋገጡን በመጥቀስ ትምህርቱን እየሰጡ ለሚገኙ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ምስጋና አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎትና የጎልማሶች መሰረተ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ፍቃዱ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ 11,000 ጎልማሶችን በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ታቅዶ 9,536 ያህሉ በመማር ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው ጎልማሶቹ ትምህርቱን ሲያጠናቅቁ የብርሀን ምዘና ወስደው እንደፍላጎታቸው 3ኛ ክፍል ገብተው መደበኛ ትምህርት የሚማሩበት ወይም በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ገብተው በሚመርጡት ሙያ የአጭር ጊዜ ስልጠና ወስደው ህይወታቸውን የሚመሩበት አማራጭ መዘጋጀቱን አመላክተዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 134😱 5👎 4🏆 3🥰 2👏 1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባዉን አካሄዷል።
ካቢኔዉ በዛሬዉ ዉሎዉ በቀረቡት 4 የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ የተለያዩ ዉሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡
በዚህም መሰረት ፡-
1ኛ ራስን ችሎ የሚለማ ቦታ ዝቅተኛው ስፋትና የፊት ለፊት ገፅታ ርዝመት ( set back) አተገባበር ጥናት ላይ ተወያይቶ የከተማዋን እድገት ታሳቢ ያደረገ እና የአተገባበር ምቹነት ታሳቢ ባደረገ የቀረበዉ ጥናት ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
2ኛ በኮሪደር ልማት የለሙ ልዩልዩ መሰረተ ልማቶች እና የወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለስልጣን ለማቋቋም የቀረበዉ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ የማስተዳደር ፣ አገልግሎት የመስጠት፣የመጠበቅ ፣የማስተባበር እና የማቀናጀት ኃላፊነት እንዲኖረው ሆኖ እንዲቋቋም ውሳኔ አሳልፏል፡፡
3ኛ የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ አስተዳደር አግባብነት ያለዉ አካል ሳይፈቅድ ፤ የተያዙ ይዞታዎች አገልግሎት የመስጠት ጊዜን ለማራዘም በቀረበ የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
4ኛ. አገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች እና የኢንዱስትሪ ልማት ተቋማት ላይ ለመሳተፍ የቀረበ የመሬት ጥያቄ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
❤ 79👎 12
Photo unavailableShow in Telegram
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ተማሪዎችና ወላጆች የዩኒቨርስቲ መረጃ ሳምንት አዘጋጀ::
(8/12/2017 ዓ.ም) አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲደራጅ በመንግስት ተወስኖ የራሱን የተማሪዎች ቅበላ ፖሊሲ ማውጣቱ ይታወቃል:: በዚሁ መነሻ በ2017 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያዎቹን ተማሪዎች ባዘጋጀው መስፈርትና ፈተና ሰጥቶ መቀበሉ ይታወሳል::
በ2018 ትምህርት ዘመን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባሉት ሰባት ኮሌጆችና በህግ ትምህርት ቤት ስር በሚገኙ 353 የድህረ ምረቃና 66 የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ተማርዎችን ተቀብሎ ለስኬት ለማብቃት በመዘጋጀት ላይ ይገኛል::
እጩ ተማሪዎችና ወላጆች ስለ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአጠቃላይና ስላሉት ኮሌጆች ፣ ትምህርት ፕሮግራሞች ፣ ትምህርት ክፍሎችና የተማሪዎች አገልግሎት መስጫዎቹ መረጃ የሚሰጥበት መረጃ ሳምንት ከነሃሴ 05 ጀምሮ ተዘጋጅቷል::
ይምጡ አንጋፋውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይጎብኙ፤
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይማሩ ፤ ህልሞን ያሳኩ ፤
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 72🏆 5👏 4😁 2
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ በበኩላቸው ሁለቱ ዳይሬክቶሬቶች በጋራ ከሚያከናውኗቸው ተግባራት መካከል የመምህራን ቅጥርን እና ዝውውርን ጨምሮ አጠቃላይ መረጃዎችን ወደ ኢ-ስኩል ሲስተም ማስገባት አንዱ መሆኑን ገልጸው የመምህራኑ መረጃ ወደ ሲስተም መግባቱ የሚያስተምሩት የትምህርት አይነት እና የተመደቡበትን ሴክሽን በሲስተሙ አማካይነት በቀላሉ ለማወቅ እንደሚያግዝ አስረድተዋል።
መረጃው ወደ ኢ-ስኩል ሲስተም ያልገባ መምህር በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት ሴክሽን የማይመደብ ከመሆኑ ባሻገር የተማሪ አቴንዳንስና ውጤት መሙላት ስለማይችል የመምህራኑን መረጃ ከወዲሁ ወደ ሲስተም ማስገባት እንዲቻል ስልጠናው ሲስተሙን ባለማው ትሪያ ትሬዲንግ አማካይነት መሰጠቱን የቢሮው ሲስተም አስተዳደር ቡድን መሪ ወይዘሮ ሰላማዊት ተስፋዬ ገልጸዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 81👍 13😁 6🥰 1👏 1
የመምህራንን መረጃ ወደ ኢ-ስኩል ሲስተም በማስገባት የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።
(8/12/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራን እና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ከቢሮው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋት ዳይሬክቶሬት ጋር በመሆን የመምህራንን አጠቃላይ መረጃ ወደ ኢ-ስኩል ሲስተም በማስገባት የመማር ማስተማር ስራው ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችል ስልጠና ለክፍለ ከተማ የመምህራን ልማት ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም ለአይ ሲቲ እና መረጃ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ሰቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራ እና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበራ ስልጠናው በዋናነት በኢ-ስኩል ሲስተም አማካይነት የመምህራንን ቅጥር፣ዝውውር እና ሌሎች መረጃዎችን በመሙላት የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ ለማድረግ እንዲቻል ታስቦ መዘጋጀቱን ጠቁመው ቢሮው በቅርቡ የሰራው የመምህራን የውስጥ ዝውውር እና ሽግሽግን ሲስተሙን መሰረት አድርጎ መረጃ የመምህራኑ ወደ ተመደቡበት ክፍለ ከተማ መላኩን በመግለጽ መረጃው ወደ ኢ-ስኩል ሲስተም ያልገባ መምህር ዝውውርን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት ስለማይችል በቀጣይ ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የመምህራኑን መረጃ ወደ ሲስተም ማስገባት እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።
❤ 68😁 3🏆 2👍 1
"ለ2018 የትምህርት ዘመን በምገባ ፣ በዩኒፎርም ፣ በደብተር አቅርቦት በሁሉም ረገድ ያሉብንን የቤት ስራዎች እያጠናቀቅን እንገኛለን ... ምክንያቱም ብልፅግና ያለ ትውልድ ግንባታ አይሆንምና" ፡- ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ
(7/12/2017 ዓ.ም)
https://youtu.be/RP9ED_bVhpk
❤ 72👍 31😁 16🏆 6🖕 6
Photo unavailableShow in Telegram
ለልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የመምህራን ቅጥር ምዝገባ
(7/12/2017 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ባስገነባቸው ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2018 የትምህርት ዘመን ሥራ ለማስጀመር መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
በመሆኑም ከላይ የተገለፁ መስፈርቶችን የምታሟሉ መምህራን ከዛሬ ነሐሴ 07/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በhttps://sbs.moe.gov.et/profile/teacher ላይ በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
➫ ተፈላጊ መምህራን ብዛት፦ 42
➫ ቅጥር፦ በቋሚነት
➫ የጽሁፍ እና የቃል ፈተና ይሰጣል
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 185👍 63🥰 10👎 7👏 3😁 3😈 3🦄 2🖕 1
ኃላፊው አያይዘውም ቢሮው የ2018 ዓ.ም ትምህርት ከመጀመሩ በፊት የተማሪዎች ደንብ ልብስ ዝግጁ እንዲሆን የ90 ቀን እቅድ አዘጋጅቶ በትኩረት በመስራቱ የደንብ ልብሶቹ ወደ ትምህርት ቤቶች በመሰራጨት ላይ እንደሚገኙ በዛሬው ምልከታ ማረጋገጣቸውን ገልጸው የደንብ ልብስ ለማቅረብ ውል የገቡ አምራች ድርጅቶች በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ መሰረት በጥቂት ቀናት ውስጥ ቀሪ ስራዎችን አጠናቀው የደንብ ልብሶቹን ለትምህርት ተቋማት ተደራሽ እንዲያደርጉ አቅጣጫ መቀመጡንም አመላክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የግዢ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ መንግስቱ አጥናፉ በበኩላቸው ለ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት የተማሪዎች ደንብ ልብስ ለማቅረብ ከተወዳደሩ 50 ድርጅቶች መካከል 21 አምራቾች ጨረታውን አሸንፈው ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቅሰው ኤጀንሲው ድርጅቶቹ በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ መሰረት ጥራቱን የጠበቀ ምርት በማቅረብ ላይ መሆናቸውን እየተከታተለ የሚገኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 68👍 19🏆 14🥰 2
የ2018 ዓ.ም ትምህርት ከመጀመሩ በፊት የተማሪዎች ደንብ ልብስን ጨምሮ ሌሎች የመማሪያ ግብአቶች ዝግጁ መደረጋቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ አስታወቁ።
(6/12/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ሳምሶን መለሰ እና ከአዲስ አበባ ከተማ የግዢ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አመራሮች ጋር በመሆን የተማሪዎች ደንብ ልብስ አምርተው በማሰራጨት ላይ ከሚገኙ አምራች ድርጅቶች መካከል ኤልቴክስ ጋርመንት ማምረቻ እና ሌጀንድ ኢንዱስትሪ ተገኝተው ሂደቱን ተመልክተዋል።
ከተማ አስተዳደሩ በልዩ ሁኔታ ትኩረት በመስጠት እና ከፍተኛ በጀት በመመደብ የተማሪዎች ደንብ ልብስን ጨምሮ የመማሪያ ደብተር፣መጽሐፍ እንዲሁም ለቅድመ አንደኛ ፣አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ጠቁመው የግብአት አቅርቦቱ የተማሪዎች ውጤት እና ስነምግባር እንዲሻሻል እያበረከተ የሚገኘው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል።
❤ 56👏 4🤔 3
ስኬት ባንክ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእንኳን ደስ አላችሁ ስጦታ አበረከተ፡፡
(6/12/2017 ዓ.ም) ስኬት ባንክ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 የትምህርት ዘመን ቢሮ ለነበረው ስኬታማ ስራ ከከተማ አስተዳደሩ መሸለሙን አስመልከቶ የእንኳን ደስ አላችሁ ስጦታ አበርክቷል፡፡
የስኬት ባንክ አመራሮች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በመገኘት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 የትምህርት ዘመን ለነበረው ውጤታማ ስራና ከከተማ አስተዳደሩ ባገኘው ሽልማት መደሰታቸውን ገልጸው የእንኳን ደስ አላችሁ ስጦታ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ አበርክተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ስኬት ባንክ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 የትምህርት ዘመን ለነበረው ስኬታማ ጉዞ ስኬታችሁ ስኬታችን ነው በማለት ደስታዉን በዚህ መልኩ መግለጹ ያስደሰታቸዉ መሆኑን ገልጸው ባንኩ ላበረከተው የእንኳን ደስ አላችሁ ስጦታ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 76👍 30👎 2
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት 4 የመማሪያ ክፍሎችን መልሶ ግንባታ በዋሊያ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስጀመረ፡፡
(6/12/2017 ዓ.ም) የመማሪያ ክፍሎቹ ግንባታ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አማካኝነት የሚገነቡ ሲሆን ከ4.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ እንደሚደረግባቸው የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ሰማኝ አስታጥቄ ገልፀዋል።
በቂርቆስ ወረዳ 11 የሚገኘው የዋሊያ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያለበትን የመማሪያ ክፍሎች ጥበት ለመቅረፍ ታስቦ ግንባታው የሚከናወን መሆኑ ተገልጻል።
የማስፋፊያ ግንባታው የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ በዶክተር ምስክር ነጋሽ እንዲሁም በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚና በአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል በወይዘሮ የሺእመቤት ነጋሽ አማካኝነት ተጀምሯል።
4 የመማሪያ ክፍሎች ለ2018 የትምህርት ዘመን አገልግሎት እንዲሰጡ በፍጥነትና በጥራት ተገንብተው የሚጠናቀቁ መሆኑ በመርሀ ግብሩ ላይ ተመላክቷል፡፡
በእለቱ ከግንባታው በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ለ218 ተማሪዎች በ5 መቶ ሺህ ብር ወጭ ሙሉ የትምህርት ግብዓት መለገሱም ተገልጿል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 67🤩 2👎 1🔥 1🤬 1
