Addis Ababa Education Bureau
Ir al canal en Telegram
ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡
Mostrar más2025 año en números

150 232
Suscriptores
Sin datos24 horas
+677 días
+34630 días
Archivo de publicaciones
መስታወቂያ! Beeksisa!
(ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም)
https://docs.google.com/forms/d/1BRr8H83V95gkNAU22tAODTgdz15yUK6x4LFywpnz1mc/preview
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 39🤔 2
ፕሮግራሙን በንግግር ያስጀመሩት የክ/ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሌሊስቱ ተስፋዬ ትምህርት ጽ/ቤት ከሚመለከታቸው የትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ በትምህርት ዘርፉ ላይ ማነቆ የሆኑ ችግሮችን እየፈታ አዳዲስ ጥናቶችንና የማስተማር ስነ_ዘደዎችን እየተገበረ በጉልህ የሚታይ ለውጥ እያስመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል።
ወ/ሮ ለሊስቱ አክለውም ትምህርት ቤቶችን በእውቀትና በክህሎት የበቃ ትውልድ መገንቢያ ማዕከል ለማድረግ ሁሉም ሰው ያለእረፍት መስራት ይኖርበታል ያሉት ኃላፊዋ በቀጣይ ጊዚያት ጉባኤው የተሻለ ተቋም ለመገንባት አስፈላጊውን ሁሉ ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅበት ፤ የልዩ ፍላጎት ትምህርት አሰጣጡን የበለጠ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና የተማሪዎችን የ6ኛ ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሀገራዊና ክልላዊ ፈተና ውጤት የበለጠ ለማሻሻል ፣የተማሪዎችን የክፍል ውስጥ ጥምርታ ከፍ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸው ክ/ከተማው ላለፉት 5 ዓመታት በ1ኛ ደረጃ የሚታወቅበትን የሳይንስ ፈጠራ ውድድርም የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በመጨረሻም በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተናዎች ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና የተሻለ የተማሪ ቁጥር በፈተና ላሳለፉ ትምህርት ቤቶች የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 21👍 4👏 3
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት "በእውቀትና በክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን!" በሚል መሪ ቃል 32ኛ መደበኛ የትምህርት ጉባኤውን አካሂዷል።
(ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም) በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ሌማንቾ ዛሬ ጉባኤያችንን ያደረግነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በተጠናቀቀበት ቀን በመሆኑ ጉባኤያችንን ልዩ ያደርገዋል በማለት ሀገራችን እያንሰራራችና በልዩ ልዩ ዘርፎች ሁለንተናዊ ለውጥ እያስመዘገብን ያገኘነውን ድል በትምህርት ቤቶቻችንም ደግመነዋል እንዲሁም በትምህርት ቤቶች አካባቢ ምቹ ሁኔታና የተሻለ የመማሪያ ስፍራ እንዲመቻች ትልቅ መስዋዕትነት ተከፍሏል ብለዋል።
አቶ ፋንታሁን አክለውም ትውልድ ላይ ሰርተን ትውልድን ይዘን የማንሻገረው ችግር የለም ይህ ወደፊትም ለትምህርቱ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተን መስራታችንን እንቀጥላለን ብለዋል።
❤ 29
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
(ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም)
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
🖕 10❤ 7
Photo unavailableShow in Telegram
የነገው ቀን
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ
ትናንትን በመጠቀምና በማረም፣ ዛሬ ላይ ተግተን በመሥራት፣ ነገን እጅግ የተሻለ ለማድረግ ተነሥተናል፡፡ በአናሎግ ዘመን የነበሩ ችግሮች በዲጂታል ዘመን አይደገሙም፡፡ ነገ “ዲጂታል ኢትዮጵያ” ፕሮጀክት ከመሆን አልፎ ባህል ይሆናል፡፡ ንግድ እና አገልግሎታችንን በማቀላጠፍ፣ መረጃዎቻችንን ተደራሽ በማድረግ፣ አንድ ሰው አንድ እንዲሆን በማስቻል፣ የፋይናንስ ሥርዓታችንን ይበልጥ ተደራሽ ቀልጣፋ እንዲሆን በማድረግ፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶችን በየአቅጣጫው በማስፋፋት፣ ዲጂታል ኢትዮጵያ እንዲሳካ የሁላችንን ጥረትና ትኩረት ይፈልጋል፡፡
Guyyaa Borii
Dijitaal Itoophiyaa Dhugoomsuu
Kaleessatti fayyadamuufi sirreessuudhaan, har'a jabaannee hojjechuudhaan, isa borii kan baay'ee fooyya'e gochuuf kaaneerra. Rakkoowwan bara anaaloogii turan bara dijitaalaatti irra hin deebi'amani. Bor "Dijitaal Itoophiyaa" n piroojektii ta'uunsaa hafee aadaa ni ta'a. Daldalaafi tajaajila keenya si'oomsuudhaan, namni tokko namuma tokko akka ta'u dandeessisuudhaan, sirna maallaqaa keenya caalaatti qaqqabamaafi si'ataa akka ta'u gochuudhaan, tajaajiloota barnootaafi fayyaa kallattii hundaan babal'isuudhaan Dijitaal Itoophiyaan akka milkaa'u tattaaffiifi xiyyeeffannoo hunda keenyaa barbaada.
❤ 49👍 6👏 2🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ መስከረም 5/2018 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን ገለፀ።
(ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን ትምህርት ከመስከረም 5/2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚጀመር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ገልጸዋል።
በትምህርት ካሌንደሩ መሠረት ከመስከረም 5/2018 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ የሚጀምሩ መሆኑን የገለጹት የቢሮ ሀላፊው እስከዛ ድረስ በትምህርት መዋቅሩ ስር የሚገኙ አካላት በሙሉ አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ ሀላፊው አክለዉም ትምህርት ቤቶች ከትምህርት ማህበረሰቡ ጋር ውይይት በማድረግና ከመግባባት ላይ በመድረስ ብሎም ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን በደማቅ ሁኔታ ለመቀበል በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በ2018 የትምህርት ዘመን ሁሉም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናትና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ወላጆች ፣ መምህራንና የዘርፉ ባለድርሻዎች የጀመሩትን የንቅናቄ ተግባር አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባና የትምህርት ቤት ምዝገባም እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 111👎 19👍 14🤮 6🤬 3🥰 2
Mostrar todo...
❤ 15
የቦሌ ክፍለከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን ታደሰ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር በተከናወኑ ተግባራት በተማሪዎች ውጤት እና ስነምግባር ላይ ከፍተኛ መሻሻል መስተዋሉን ገልጸው በቀጣይ የጉባኤው ተሳታፊዎች የክፍለከተማውን የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም በመገምገም በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል በሚያስቀምጡት አቅጣጫ መሰረት ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ አመላክተዋል።
በመርሀግብሩ ማጠቃለያ በጉባኤተኛው የተዘጋጀ ባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ ለታዳሚው የቀረበ ሲሆን በ2017ዓ.ም በክፍለ ከተማው የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና የትምህርት ተቋማት ዕውቅና ተሰቷል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 25👍 2
የቦሌ ክፍለከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የ2017 ዓ.ም የትምህርት ጉባኤውን በዕውቀት እና ክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን በሚል መሪ ቃል የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አካሄደ።
(ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም) የቦሌ ክፍለከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የ2017 ዓ.ም የትምህርት ጉባኤውን በዕውቀት እና ክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን በሚል መሪ ቃል የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አካሄደ።
በጉባኤው የጽህፈት ቤቱ የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም እቅድ እንዲሁም በክፍለ ከተማው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በ2017 ዓ.ም የተመዘገበው የተማሪ ውጤት ትንተና በጽህፈት ቤቱ የስራ አስተባባሪ በሆኑት ወይዘሮ መአዛ ተስፉ እና አቶ ስለሺ ሶሪ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ እና የጉባኤው የክብር እንግዳ አቶ መስፍን ሀይሌ በጉባኤው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ጉባኤው በ2017 ዓ.ም የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸምን እና የ2018 ዓ.ም የትኩረት መስኮችን መሰረት አድርጎ የሚካሄድ እንደመሆኑ የክፍለ ከተማው አስተዳደር የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል በጉባኤ የሚቀመጡ ቀጣይ አቅጣጫዎችን መሰረት በማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመው በበጀት አመቱ በክፍለከተማው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራው ውጤታማ እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
❤ 24👍 4👎 1👏 1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ በተቋሙ አካባቢ ለሚኖሩ አቅመ ደካማ ለሆኑ ነዋሪዎችና ለቢሮ ሰራተኞች የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር አካሔደ።
(ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም) የ2018 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በተቋሙ አካባቢ ለሚኖሩ አቅመ ደካማ ለሆኑ ነዋሪዎችና ለቢሮ ሰራተኞች የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር አካሄዳል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ማዕድ ባጋሩበት ወቅት ባስተላለፍት መልዕክት እለቱ የማንሰራራት ቀን እና የህዳሴ ግድቡ የተመረቀበት ዕለት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ ብለዋል፡፡ መርሀ ግብሩ በየአመቱ የሚከናወን የአብሮነት ፣ የወንድማማችነትና የመደጋገፍ መግለጫ መሆኑን ጠቅሰው ቢሮ ከትምህርት ልማት ስራዉ ጎን ለጎን በተቋሙ አካበቢ ለሚኖሩ አቅመ ደካማዎችና ለቢሮ ሰራተኞች በበአላት ዋዜማ ሁልጊዜ የሚያካሂደውን ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 41👍 2
የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የ15 ቀናት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገመገሙ ::
(ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አጠቃላይ ካውንስል አባላት የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በ 15 ቀናት ውስጥ ያከናወናቸውን ተግባራት ገምግመዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወ /ሮ አበበች ነጋሽ የቀረበው ሪፖርት ሥራ ክፍሉ በዝግጅት ምዕራፍ ተአማኒነት ያለው መረጃ ከማግኘት አንፃር
ተግባርና ኃላፊነቱን ለመወጣት የተሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል ::
በሥራ ክፍሉ ሰራተኞችን ለማብቃት እየተሰጡ ያሉ ስልጠናዎችም ያላቸው ፋይዳ ትልቅ መሆኑን የገለፁት አማካሪዋ በቀጣይ የአቻ ፎረም አደረጃጀቶችና በውይይቱ የተፈቱ ችግሮች በጉልህ እንዲቀርቡ አሳስበዋል::
የቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በበኩላቸው በተለያየ ጊዜ የሚቀርቡ የ15 ቀናት ሥራ አፈፃፀም ሪፖርቶች ያሉ ክፍተቶችን አፋጣኝ የሆነ ማስተካከያ በመውሰድ ሥራን በጥራት ለማከናወን የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል::
የአጠቃላይ ካውንስል አባላቱም የስራ አፈፃፀሞች ላይ የሚሰጡት ገንቢ አስተያየቶች ሥራዎች በስኬት እንዲሰሩ አቅም የሚፈጥሩ በመሆኑ የስራ ክፍሎች እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል ::
በግምገማው የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ታዬ ወልደኪዳን ዳይሬክቶሬቱ በ15 ቀናት ውስጥ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት ተደርጎበታል ::
ሪፖርቱ ሲቀርብ የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ እና አቶ አሊ ከማል የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወ /ሮ አበበች ነጋሽ ፣ የፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ እንዲሁም የሁሉም ሥራ ክፍሎች ዳይሬክተሮች ተሳትፈዋል ::
❤ 56👍 4🥰 2
ህዳሴ
የደም
የላብ
የእንባና የዉሃ ጠብታ !
የመሆኑ ማሳያ ሀውልት በግድቡ ዙሪያ ተመርቋል
(ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም)
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 42👏 6👍 3😁 2
ተመረቀ!
(ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም)
እንኳን ደስ አላችሁ፣
እንኳን ደስ አለን፤
ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 44👏 9
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታዬ ወልደኪዳን ስልጠናው በዋናነት በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚገኙ የመረጃ እና አይ ሲቲ ባለሙያዎችን ጨምሮ የወረዳ የመረጃ ባለሙያዎች በአጠቃላይ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ሲስተም ዲጂታላይዜሽን ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ፈጥረው በየተቋማቸው የተማሪ፣የመምህር ፣እንዲሁም የትምህርት ተቋማቸውን አጠቃላይ የትምህርት መረጃዎች ወደ emis.moe.gov.et ሲስተም በአግባቡ ማስገባት እንዲችሉ በክፍለ ከተማ የመረጃና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪዎች አማካይነት በአስራ አንዱ ክፍለ ከተሞች በተዘጋጁ አስራ አንድ የስልጠና ጣቢያዎች መሰጠቱን አስታውቀዋል።
ዳይሬክተሩ አያይዘውም ቢሮው በቀጣይ በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ የግል ትምህርት ተቋማት ተመሳሳይ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን አመላክተዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 22👍 5👎 1
የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለመንግስት 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመረጃ እና አይ ሲቲ ባለሙያዎች እንዲሁም ለወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት የመረጃ ባለሙያዎች ትላንትናና ዛሬን ጨምሮ በተግባር የተደገፈ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ።
(ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም) ስልጠናው በዋናነት በአጠቃላይ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ሲስተም ዲጂታላይዜሽን አተገባበር እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና ወስደው በየትምህርት ቤቶቻቸው የተማሪ፣ የመምህር ፣ የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ አጠቃላይ የትምህርት መረጃዎችን ወደ emis.moe.gov.et ሲስተም እንዲያስገቡ ለማስቻል ለሁለት ቀን መሰጠቱን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ሳምሶን መለሰ የስልጠናው ተሳታፊዎች በወሰዱት በተግባር የተደገፈ ስልጠና መሰረት መረጃዎቹን በአግባቡ ወደ ሲስተሙ በማስገባት ላይ መሆናቸውን ቢሮው በየትምህርት ተቋማቱ በሚያደርገው ድጋፍ እና ክትትል የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቁመው ሰልጣኞቹ የወሰዱትን ስልጠና መሰረት በማድረግ መረጃዎቹን ወደሲስተሙ በማስገባት ጥራቱ የተጠበቀ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የትምህርት መረጃ ለሚመለከተው አካል በአግባቡ ተደራሽ እንዲሆን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲውጡ ጥሪ አስተላልፈዋል።
❤ 22👍 5🥰 1
