2025 año en números

68 961
Suscriptores
Sin datos24 horas
-137 días
-96730 días
Archivo de publicaciones
ልክ እንደ ቡናው!
በአንድ ወቅት አንዲት ወጣት ወደ እናቷ በመሄድ ኑሮ እንደከበዳትና ተስፋ የመቁረጥ ደረጃ ላይ እንዳለች ነገረቻት፡፡ “አንዱ ችግሬ አበሳጭቶኝ ሳልጨርስ ሌላ ይተካል፣ በእርሱኛው ደግሞ ውስጤ ተጎድቶ ገና ሳላገግም ሌላ ይጨመርብኛል” በማለት ከፍቅር ሕይወቷ ጀምሮ እስከ ሌሎች አስቸጋሪ ገጠመኞቿ ስሜታዊ በሆነ መልኩ አንድ በአንድ ገለጠችላት፡፡
በጥበቧ የምትታወቀው እናት፣ ወደ ልጇ ጠጋ በማለት ዳበስ አድርጋት ፍቅሯን ከገለጠችላት በኋላ አሁን ለጊዜው ተረጋግታ ስራ እንድታግዛት ጠየቀቻት፡፡ ልጅ ፈቃደኝነቷን ከገለጸች በኋላ እናት ምንም ጊዜ ሳታባክን አንድን ነገር እነድታደርግ ለልጇ አዘዘቻት፡፡
“ሶሰት ድስቶችን ውኃ በመሙላት በምድጃው ላይ ጣጂ” አለቻት፣ እናት፡፡ ልጅ የተባለችውን ለመፈጸም ወዲህ ወዲያ ማለት ጀመረች፡፡ ያንን ካደረገች በኋላ በመቀጠልም በእያንዳንዳቸው ውስጥ የተለያዩ ነገሮችን እንድትጨምርባቸው ነገረቻት፡፡ “በአንዱ ድስት ውስጥ አንድ ካሮት ጨምሪበት፡፡ በሚቀጥለው ድስት ውስጥም እንደዚሁ አንድ እንቁላል ጨምሪበት፡፡ በሶስተኛው ውስጥ ደግሞ የቡና ዱቄት ጨምረሽ ነይና ንግግራችንን እንቀጥል”፡፡
ልጅ የተነገራትን ካደረገች በኋላ ወደ እናቷ መጥታ ንግግራቸውን ቀጠሉ፡፡ ከተገናኙ ሰንበት ስላሉ ብዙ የሚነጋገሯቸው ነገሮች ነበሩና ሳያስቡት ቆየት አሉ፡፡ ይህንን ሁሉ ስታደርግ እናት ምን ለማድረግ እንደፈለገች በሚገባ ታውቅ ነበር፡፡ ከዚያም እናት በድንገት ከእንቅልፉ እንደባነነ ሰው፣ “የጣድሻቸውን ድስቶች ረሳሻቸው እኮ!” በማለት ልጇን አስታወሰቻት፡፡
ልጅ በፍጥነት ወደድስቶቹ በመሄድ ምድጃውን አጠፋችና ወደ እናቷ ተመለሰች፡፡ እናትም፣ በይ ተመለሺና ያበሰልሻቸውን ሶስቱንም ነገሮች አንድ በአንድ ይዘሽ ነይ አለቻት፡፡ ልጅም ሳህን ካመጣች በኋላ ካሮቱንና እንቁላሉን በጥንቃቄ ከድስቱ ውስጥ በማውጣት አመጣች፡፡ ተመልሳ ቡናውን ለማምጣት ከመሄዷ በፊት እናት ለልጇ በእንቁላሉ እና በካሮቱ ላይ ያየሽውን ለውጥ ንገሪኝ አለቻት፡፡
ልጇም በመጀመሪያ ካሮቱን ከነካካችና ካጤነች በኋላ፣ “ወደ ውኃ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ጠንካራ ነበር አሁን ግን በጣም ለስላሳ ሆኗል” አለቻት፡፡ በመቀጠልም እንቁላሉን ከነካካች በኋላ ቀድሞ እንደነበረ ስላገኘችው፣ “እንቁላሉ ምንም ለውጥ የለውም” አለቻት፡፡ እናት ግን በመመለስ፣ “የእንቁላሉን ላይ ላዩ እንጂ ውስጡን አላየሽውም” አለቻት፡፡ ልጅም እቁላሉን ሰበር ስታደርገው ውስጡ ጠንክሮ አገኘችው፡፡ ስለዚህም፣ “ወደ ውኃ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ውስጡ ፈሳሽ እንደነበረ እርግጠኛ ነኝ፣ አሁን ግን ጠንክሯል” አለቻት፡፡
በመጨረሻም ለልጇ፣ “አሁን የቡናውን ዱቄት ከድስት ውስጥ አውጪና አምጪው” አለቻት፡፡ ልጅ ትንሽ ግር አላት፡፡ “ቡናው ከውኃው ጋር ተዋህዷል፣ እንዴት አመጣዋለሁ?” ብላ አሰበች፡፡ በዚህ ሃሳብ ተመስጣ ወደ ቡናው ስትሄድ፣ መዋሃድ ብቻ አይደለም ቡናው የውኃውን መልክ፣ መዓዛና ጣእም ሙሉ ለሙሉ ለውጦታል፡፡ ከዚያም ቡናውን በሁለት ስኒዎች በመቅዳት ወደ እናቷ ወስዳ እያጣጣሙት መነጋገራቸውን ቀጠሉ፡፡
ልጅ እናቷን፣ “ምን አስበሽ ነው ይህንን ሁሉ ያስደረግሽኝ?” አለቻት፡፡ “አየሽ”፣ አለች እናት፤ “እነዚህ ሶስት ነገሮች አንድ አይነት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለፉት፣ በፈላ ውኃ ውስጥ፡፡ ካሮቱ ካለፈበት ሁኔታ ምንም ነገር መቋቋም እስከማይችል ድረስ እጅግ ለስላሳ ሆነ፡፡ እንቁላሉ ደግሞ ካለፈበት ሁኔታ የተነሳ ውስጡ ጠነከረ፡፡ እነዚህ ሁለት ነገሮች በገቡበት ሁኔታቸው ተጽእኖ ስር በመሆን ባህሪያቸው ተለወጠ፡፡ ቡናው ግን በገባበት ሁኔታ ላይ ተጽእኖ አመጣ፡፡ የገባበትን ቦታ ጣእም፣ ጠረንና እንዲሁም ቀለም እንደለወጠው ተመልክተሻል፡፡”
እናት በመቀጠል እንዲህ አለቻት፣ “አንቺም በምታልፊበት ሁኔታ ያለሽ ምርጫ ከሶስቱ አንዱ ነው፡፡
1. ልክ እንደካሮቱ አጉል ልፍስፍስና በሁሉም ነገር የሚጎዳ አይነት ሰው እንዳትሆኚ ልታስቢበት ይገባል፡፡
2. በተቃራኒው የምታልፊበት ሁኔታ ልክ እንደ እንቁላሉ ውስጥሽን አጉል ጠንካራና ደንዳና እንዳያደርገው ተጠንቀቂ፡፡
3. ከእነዚህ ሁኔታዎች ይልቅ የተሻለው መንገድ በምታልፊበት ሁኔታ ሁሉ በቀላሉ የሚነካና የሚፈርስ ደካማ ወይም ከጉዳት የተነሳ አጉል “ጠንካራ” እና አትንኩኝ ባይ ሳትሆኜ ልክ እንደ ቡናው ሁኔታውን የምትለውጪ የተጽእኖ ሰው ልትሆኚ ይገባል”፡፡
ዶ/ር እዮብ ማሞ
@Human_Intelligence
👍 25❤ 4
በ1237 ዓ.ም አካባቢ ከሦስት መቶ ዘመናት የዛግዌያን አገዛዝ በኋላ ሥልጣን በቤተክርስቲያን ጠንካራ ተጽዕኖ ከዛግዌ ነገሥታት ወደ የዘር ሀረጋቸውን ከሰሎሞን ዘር እንመዛለን ለሚሉ ሰሎሞናዊ ነገሥታት ተዛወረ፡፡ የዛግዌ ነገሥታትን ሥልጣኑን ለሰሎሞናዊው ገዥ ይኩኖአምላክ እንዲያስተላልፉ በመወትወት፣ በመገሰጽ አቡነ ተክለኃይማኖት ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ይነገራል፡፡
በሂደቱም ቤተክርስቲያን እስከ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት ድረስ የዘለቀ የክፍለዘመናት የሢሶ መንግሥትነት ፈላጭ ቆራጭነቷን አጸናች፡፡
ጥቂት ቆይቶ በ330 ዓ.ም አካባቢ የሰሎሞናዊ ስርወመንግሥቱን በትርክት እና በሕግ ለማጽናት ሲባል ‹ክብረነገሥት› የተሰኘው መጽሐፍ የመጻፉ አስፈላጊነት ታመነበት፡፡
መጽሐፉ የኢትዮጵያ ንጉሣዊ ሥልጣን ባለቤቶች የዘር ሀረጋቸውን ከንጉሥ ሶሎሞን እና ከቀዳማዊ ምኒሊክ ዘር የሚመዙ ብቻ መሆናቸውን በማያሻማ ኹኔታ ይደነግጋል፡፡ በዚህም መጽሐፍ የተነሳ ኢትዮጵያን ሀገራቸውን እንደዳግማዊት ኢየሩሳሌም እንዲመለከቷት ተበረታተዋል፡፡ ለዘመናት በክርስትና እምነት መነሻነት በተገነባው በዚህ ትርክት እና በክርስትው ኃይማኖት ምክንያት ከኢትዮጵያ ውጭ በኢትዮጵያዊያን (በሰሜነኛው ክርስቲያን) አዕምሮ የታተመች ሌላ ከተማ (ሀገር) ብትኖር ኢየሩሳሌም ብቻ ናት፡፡ በዚህ ሰበብ ይመስላል ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት ከውጭው ዓለም የመጣውን ሰው በተለይ ክርስቲያኑን ሁሉ የኢየሩሳሌም ሰው እንደሆነ ይቆጥሩ እንደነበር በልዩ ልዩ ተጓዦች ማስታዎች ላይ ተዘግቧል፡፡
በዚህ መልኩ በአስራ አራተኛው መቶ ክፍለዘመን መጀመሪያ የተጻፈው ክብረነገሥት ከፊውዳል ሥርዓቱና ከቤተክህነቱ ጋር ተቀይጦ በኢትዮጵያ የሥነ መንግሥት ታሪክ ሰባት መቶ ዘመናት ድረስ የዘለቀ ገዥ ትርክትን ፈጠረ፡፡ ይህ ትርክት በተለይ ከሞላ ጎደል በአንድ አገዛዝ ሥር የሚያድር፣ ልዩ ልዩ ቋንቋዎችን የሚናገር በአብዛኛው የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነውን ሰሜነኛ ሕዝብ ለሰባት ክፍለዘመናት ያስተዳደረ መሪ ትርክት ሆኖ አሳለፈ፡፡ ዳግማዊ ምንይልክ የተበታተነውን የዳር ሀገር ሕዝብ ሁሉ በአንድ አጠቃለው በዘውዳዊ ሥርዓቱ ሥር ካስገቡትም በኋላ በዚህ ትርክት ሥር እንዲመላለስ ሙከራ አድርገዋል፡፡ ሙሉ ለሙሉ የሰመረ ነበር ባያስብልም ቢያንስ በእሳቸው ዘመን ትርክቱ የአንድነት ስሜት በመፍጠሩ የአድዋ ጦርነትን የመሰለ በተባበረ ከንድ የተገኘ እጅግ አንጻባራቂ ገድል ለመከወን መሣሪያ ሆኗል፡፡
ኢጣሊያኖች ኢትዮጵያን ዳግም የወረሩ ሰሞን በቅኝ ገዥ ሴራ ሕዝቡን ለመከፋፈል አማርኛ ተናጋሪውን ሕዝብ በጅምላ የፊውዳል ሥርዓቱ ተጠቃሚ እና ጨቋኝ ገዥ መደብ እንደሆነ ፈርጀው ትርክታቸውን ማጠንጠን ጀመሩ፡፡ ይህ ትርክት በተለይ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ድፍን ሃያ ሰባት ዓመታት በሕገመንግሥት፣ በመንግሥት በጀት፣ በመንግሥት መገናኛ ብዙሃናት በይፋ እና በስውር እንደ አስፈላጊነቱ ይቀነቀን ነበር፡፡ በበኩሌ ሰሜነኛው ሕዝብ ለፊውዳል ሥርዓቱና ለአገዛዙ በነበረው ጂኦግራፊያዊ ቅርበት ከሌላው ኢትዮጵያዊ ሕዝብ በተለዬ ተጠቃሚ ከመሆን ይልቅ ከሁሉም በላይ በሥርዓቱ ይበደል እንደነበር አስባለሁ፡፡
ከ2010 ዓ.ም በኋላ የመጣው አስተዳደር በመደመር ግራ የገባው ቅኝት እዚያ እና እዚህ እየረገጠ ምንም የትርክት ለውጥ ሳያስፈልገው የጨቋኝ ተጨቋኝ የትርክት ንጥቂያ እና ቁማርን ማስቀጠሉን ለመረዳት ብዙ የፖለቲካ ብስለት የሚጠይቅ አይመስለኝም፡፡
እኛ ግን ለመላው ጥቁር ሕዝብ ትርክት ቀማሪነት የታጨን ሆነን ሳለን የራሳችን የቤት ሥራ እንኳን ሰርተን ያልጨረስን መሳቂያ የመሆናችን ነገር ያሳዝናል፡፡ ታላቁ ጥቁር የተሰኘ በንጉሴ አየለ ተካ የተጻፈ መጽሐፍ ያነበበ ሰው ሁሉ ንጉሠ ነገሥቱ አጼ ኃይለሥላሴ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ስር ለነበሩ ጥቁር ሕዝቦች ሁሉ እንደምን ይታገሉ እንደነበር መታዘብ ይችላል፡፡
ታሪካችንን አላወቅነውም፡፡ መናናቂያ አድርግነዋል፡፡ በታሪክ አጋጣሚ ያገኘነውን በሰው ዘርን ሁሉ ፊት በግርማ ሊያስጠራን የሚችል ዕድል እንደዘበት አምልጦናል፡፡ እናስ ያቆሙን መሰረቶች ምን ያህል ጽኑዓን ነበሩ? እንደ ኅብረተሰብ የአቋራጩ፣ ልክፍተኞች ሆነን ለመገኘታችን ምክንያቱ ምንድን ነው? የምንዋቀሰው፣ የምንናናቀው በድንቁርናችን ልክ አይደለምን? ለፍጥረት ሁሉ ከሚተርፍ በረከት፣ ኅሊና እና ርህራሄ ጋር ተፈጥረን ሳለን ዘመኑን ስላለመዋጀታችን በሰንደቅ ዓላማ ለሚያስለምን ችጋር ራሳችንን አላጨንምን?
👍 51❤ 11
ከየንጉሥ ዳግማዊ ቴዎድሮስ መቃተት ይሄው ነበርና፡፡ ከእንግሊዟ ንግሥት ቪክቶሪያ ጋር ከመቃቃራቸው በፊት በጻፉላቸው አንድ ደብዳቤ ‹‹የኢትዮጵያ ሰዎች ታውረናልና ዓይናችን ያብሩልነ›› የሚል ተመጽኖ አሰምተዋል፡፡
ሥልጣኔ ግን፣ በቁጭት፣ በትጋት፣ በፈጠራ እንጅ በልመና በምጽዋት የሚሆን አይደለም፡፡ ጥበቡን ትሰርቀዋለህ ወይ ትኮርጀዋለህ እንጅ ማንም በችሮታ ሊያድልህ አይችልም፡፡ አጼ ቴዎድሮስ ቁጭቱ ነበራቸው፡፡ ሀገሪቱ የራሷ መርከብ እንዲኖራት ተመኝተዋል፡፡ መርከብ በመስራት እንጂ መርከብ በመግዛት ልዕልና እንደሌለ ገብቷቸዋል፡፡ ጣና ሐይቅ ላይ መርከብ ለመስራት ተፍጨርጭረዋል፡፡ በየጊዜው በገንዘባቸው እየገዙ ነጻ የሚያወጧቸውን ባሮች ጥበብን ይማሩ፣ ረዳት ሆነው እንዲያገለግሉ ዘንድ ወደ ደብረታቦር የኢንደስትሪ መንደራቸው ይልኩ ነበር፡፡
ቴዎድሮስ መድፍ መግዛት ቢፈልጉ እንግሊዞች በገፍ ሊያቀርቡላቸው ይችሉ ይሆናል፡፡ እሳቸው ግን ዓሳውን ከመቀበል ዓሳው ማጥመድ መማርን መረጡ፡፡ ልክም ነበሩ፡፡ ነገርግን ቁጭቱ እንጂ ብልሃቱ ብልጭም አላለላቸው፡፡በኮፍያ ማውለቅ ማጥለቅ ሰበብ ሳይቀር ከነጮቹ ጋር እንደተነታረኩ እንዲችው ሲትከነከኑ አለፉ፡፡
እናስ ሊውጠን ያሰፈሰፈውን የዓለም ቅኝት ለመመከት ዝግጁነት እንደማጣታችን ቅኝ ያልተገዛነውስ ከአያቶቻችን ጦረኝነት እኩል የሀገሪቱ ጅኦግራፊያዊ አቀማመጥ አስቸጋሪነት እና ለውጭ ኃይሎች የሚስብ የንግድ እና የምርት አማላይ ከባቢ አለመፍጠራችን መሆኑን ማመን አያሻግረንምን?
ጦርኝነታችን ሳይረሳ ነው ታዲያ... ኢትዮጵያን አምርሮ የሚጠላው ሮማን ችካዝሮብስካ ራሱ ‹‹ኢትዮጵያዊያን በተፈጥሯቸው ጀግኖችና ጦር ወዳዶች ናቸው፡፡›› ሲል መስክሯል፡፡ ነገርግን ግብፆች ከጥንት ጀምሮ ለቁጥር ለሚታክት ጊዜ ቅኝ ለመገዛታቸው ዋነኛዎቹ ምክንያቶች የተፈጥሯዊ አቀማመጣቸው ለወራሪ አመችነትና የአካባቢው የንግድ እንቅስቃሴ አማላይነት መሆናቸውን መገንዘብ አያዳግትም፡፡ የግሪኮች፣ የሕንዳዊያን፣ የሮማዊያንና የእስራኤላዊያንም እውነት ከዚህ የተለየ አይመስለኝም፡፡
የአክሱም ሥልጣኔ ግን አንድ ሥልጣኔ ሊኖረው የሚገባው ቅንጣቶች ሁሉ ነበሩት፡፡ የተደራጀ ሥነ መንግስት፣ የጽሕፈት ቋንቋ፣ ኃይማኖት፣ ባህል፣ ዕደ ጥበብ፣ የንግድ ግንኙነት፣ ፈጠራ፣ ከተሞች... ከሞላ ጎደል ሁሉም ነበሩት፡፡ በእኔ ዕምነት አክሱም - ላሊበላ - ፋሲል (ጀጎል)፣ አድዋ፣ የግዕዝ ፊደል እና ያሬዳዊ ዜማ የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ስድስት ማዕዘናት ናቸው፡፡ እንግዲህ ከእነዚህ ስድስቱ ሦስቱ ግዑዛን ሐውልቶች ወይ ሕንጻዎች (monolithic monuments) ሆኑ፡፡
ነገርግን አክሱምን፣ ላሊበላን፣ ፋሲልና ጀጎልን የጠረቡ እጆች ስለምን ለሺህ ዘመናት በደሳሳ ጎጆዎች ውስጥ እንደተቸነከሩ ማሰብ ሕመምን ይፈጥራል፡፡ ፊደል ነበረን፤ እንደ ሕዝብ ከመጻፍ ይልቅ መስማትን እንመርጣለን፡፡ ይበልጡኑ መሀይማን ነበርን፡፡ በኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አማካኝነት ሙዚቃን በኖታ በመጻፍ የመጀመሪያዎቹ ብንሆንም እዚሁ አበርክቶ ላይ ጥቂት ሀሳብ ለመጨመር የተክሌ አቋቋም, እስኪቀመር አንድ ሺህ ሦስት መቶ ዓመታት መጠበቅ ነበረብን፡፡
👍 8❤ 2
አክሱም ላይ አንቀላፍቶ
ማይጨው ላይ መንቃት
የእኛ ስልጣኔ የጎደለው ነገር ምን ነበር?
የአክሱም ሥልጣኔ ለዓለማቀፍ ግብይት የወርቅ፣ ለሀገር ውስጥ ግብይት ከኒኬል እና ከብር የተቀረፁ የግዕዝ እና የግሪክ ፊደላት እንዲሁም ያስቀረጸውን ንጉሥ ምስል የታተመባቸው ሣንቲሞች ነበሩት፡፡ ሥልጣኔው ሙዚቃን በኖታ ለመጻፍ እስከመቻል ድረስ የባህል መራቀቅን ተቀዳጅቷል፡፡ ነገሥታት ለመቃበሮቻቸው ክብር ከግብጽ ፒራሚዶች የማይተናነሱ ጌጠኛ አንድ ወጥ ሐውልቶችን (monolithic statue) ያስቀርፁ ነበር።
ቅድመ አክሱም ዳማት፣ ፑንት እና የአክሱም ሥልጣኔዎች ከግብፅ፣ ሮም፣ የመንና የአረቢያ ምድር እስከ ሕንድና ቻይና ድረስ የባህል፣ የንግድ መስተጋብሮችን ይከውኑ ነበር፡፡ የአክሱም ሥልጣኔ ከፍተኛ ደረጃ በደረሰበት በ6ኛው መቶ ክፍለዘመን መጀመሪያ አክሱም በኤሮፓ ስሙ ገናና ነበር፡፡ በኤሮፓ ነገስታት ለጦር እርዳታ ተለምኖ ወደ የመን ዘምቷል፡፡ የአክሱም ሥልጣኔ ዛሬም ድረስ በዓለም ላይ ከሚያገለግሉ ጥቂት እጅግ የሰለጠኑ የጽሕፈት ቋንቋዎች አንዱ የግዕዙ ሳባዊ የተራቀቀ ፊደል ገበታ የመጨረሻውን ልህቀቱን አቀዳጅቶ ለግልጋሎት አብቅቶታል፡፡ ሌላው ቀርቶ የግብጽ ሥልጣኔ ይህ ልህቀት አልነበረውም፡፡ ግብፆች መጀመሪያ በምልክቶች በኋላ በተዋሷቸው የግሪክና የአረብኛ ቋንቋዎች ይጠቀሙ ነበር፡፡
ሥልጣኔው ከሌሎች አቻ ሥልጣኔዎች የባህል፣ የንግድ፣ የሃይማኖት እና መሰል መስተጋብሮችን ማድረግ መቻሉ ለዛ፣ ቀጣይነት፣ ቅናትና ፈጠራ እንዲኖረው አስችሎታል፡፡ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት እንደመሰከሩት አክሱም በዘመኗ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የተነሳ ቅይጥ የሚያድግ ባህል አስተሳሰብና ማኅበረሰባዊ ስሪት ነበራት፡፡ ፔሪፕለስ ኦፍ ኤሪትሪያን ሲ የተሰኘው ጥንታዊ የታሪከ መጽሐፍ ደራሲ እንደሚለው የአዶሊሱ ንጉሥ ዞስካለስ ከሀገሩ ቋንቋዎች በተጨማሪ ግሪክኛን አቀላጥፎ ከመናገር አልፎ በግሪክኛ የሚጻፉ መጻሕፍትን ያነብ ነበር፡፡ ፕሮፌሰር ታደሰ ቅድመ አክሱሟ ንግሥት ማክዳ ንግድ የምታሳልጥባቸው እስከ አምስት መቶ የሚደርሱ መርከቦች እንደነበሯት ጽፏል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንደመሰከረው በዘመኑ ለንጉሥ ሶሎሞን ከቀረቡት ሥጦታዎች ሁሉ የንግሥተ ሳባን የሚወዳደር አልነበረም፡፡
ሥልጣኔ በንግድ፣ በግጭት እና በአሰሳ ይስፋፋል፡፡ ግጭቱን እንደኛ የተካነው ባይኖርም ከግጭት ከድቀት ውጭ ምንም ያላተረፍን ሕዝቦች ብንኖር እኛ ብቻ ሳንሆን እንቀርም፡፡ ሲቆይ ኢትጵያዊያን ‹‹ከተራራው ጀርባ ስላለው ዓለም ግድ የሌላቸው›› ተብለን የሚዘበትብን ሕዝቦች ሆንን፡፡ የአዶሊስ እና ዘይላ ወደብ በአረቦች እጅ ከወደቁ ጀምሮ ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም ተነጠለች፡፡ ለአንድ ሺህ አምስት መቶ ዘመናት በውስጧ የሚያልፍ አንድ ድንበር ተሻጋሪ የንግድ መስመር አልነበረም፡፡
ከሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ ኢትዮጵያ የባህር በሮቿን አጣች፡፡ ከዓለም ተነጠለች፡፡ ኤድዋርድ ጊበን እንዳለው ‹‹ዓለምን ረስታ ዓለምም ረስቷት ለሺህ ዓመታት አንቀላፋች፡፡» በውስጥ ቁርቁሷ ላይ አተኮረች፡፡ ከዚያ በፊት ያልነበሩት የእርስበርስ ጦርነቶች እንደ አሸን ፈሉ፡፡ ቄስ ሪካርዶ አልባሬዥም በጉዞ ማስታወሻቸው እንደታዘቡት የፊውዳል የመሬት ሥሪቱ የገበሬውን የምርት ባለቤትነት የሚገድብና ጭሰኛ የሚያደርግ መሆኑ ገበሬው ለራሱ የሚበቃውን ያህል ብቻ እንዲያመርት አስገድዶታል፡፡ ትርፍ ምርት በጎተራው ማከማቸት፣ ሰንጋ፣ ጠጅ መጣል ሁሉ ለገበሬው ያልተፈቀዱ ነበሩ፡፡ ይሄም ለዘመናት ሀገሪቱን ከአምራችነት የገደባት ይመስላል፡፡
ቤተክህነት በዚህ ጊዜ በ3ኛው መቶ ክፍለዘመን አጋማሽ ከቤተመንግስት እስከ ቤተሰብ በእያንዳንዱ ጉዳይ አድራጊ ፈጣሪ ሢሶ መንግስትነት ሚናዋን በሚገባ መከወን ጀምራለች፡፡ በአክሱም ውድቀት ምክንያት የክርስትና ባህል ከተቀረው ዓለም ሙሉ ለሙሉ በመነጠሉም የማያቋርጥ ዕድገቱ ተገትቶ ወደ የሆነ አንድ ዓይነት የጠጠረ የባህል ቅኝት (sedentary cultural scheme) የተገፋ ይመስላል፡፡ ማኅበረሰቡ የሕዝብ፣ የንግድ እና የባህል ንቅናቄ ማጣቱ ለሺህ ዓመታት ያንከባለልነውን የሆነ ዓይነት የማይሸራረፍ ጠጣር የባህል ቅኝት እንደፈጠረ አስባለሁ፡፡
የተፈጠረው አንድ ዓይነት የማይሸራረፍ፣ የማያድግ፣ የተቸነከረ፣ የማይሻሻል ባህል ለኅብረተሰቡ አቆርቋዥ ነበር፡፡ ጥበቡን፣ አስተሳሰቡን፣ አምልኮውን፣ አገዛዙን፣ ሁለንተናውን ለሺህ ዓመታት የፊጥኝ አስሮ በተመሳሳይ ቅኝት ነድቶታል፡፡ ከኃይማኖታዊ ቅኝቱ ውልፊት የሚል እና ዓለማዊነት የሚዳዳው ፈጠራ እንደ ወንጀል ይቆጠር ነበር።
ንቅናቄ ግን ሕይወት ነው! የወንዝ ውኃ ከኩሬ በምን ይበልጣል ቢሉ በእንቅስቃሴው አይደለምን? ንቅናቄ ውኃን ብቻ ሳይሆን መላውን ሥነ ፍጥረት ያበለጽጋል፡፡ እንቀስቃሴው፣ ንቅናቄው የሕዝብ የግለሰብ ሲሆን ደግሞ አስተሳሰብን ይሞርዳል፤ አድማስን ያሰፋል፤ ንቅናቄ ያላገኘው ሕዝብ ተነሳሽነት የማጣት አደጋ ውስጥ ይገባል፡፡ ባህሉ፣ ልማዱ፣ የመታደስ፣ የመሞረድ ዕድሉ ይጠባል፡፡
ይህ አንድ ዓይነት የጠጠረ የባህል ቅኝት (sedentary cultural scheme) ከሰሜን እስከ ደቡብ በአራቱም አቅጣጫ የተሰለፈው ኢትዮጵያዊ ልዩ ልዩ ነገድ ሁሉ መገለጫ ነበር፡፡ ኮንሶው፣ ከንባታው፣ ሀዲያው፣ ጋሞው፣ ዶርዜው የደንባትን የሆነች አንዲት ዓይነት ማኅበረሰባዊ ቅጥ ብቻ እንደጉንዳን አሎሎ እያሽከረከረ ያለምንም ፈቅታ ሲፍገመገም አሳልፏል፡፡ እንግሊዛዊው የታሪክ ሊቅ ኤድዋርድ ጊበን በ770ዎቹ ‹The History of the Decline and Fall of the Roman Empire› በተሰኘ ርዕስ በጻፋቸው ተከታታይ መጻሕፍት ስለአክሱም ሥልጣኔ መዳከም ሲተነትን የሚከተለውን የሚያትከነክን ሀሳብ ሰንዝሯል፡፡
‹‹ኢትዮጵያዊያን፣ በኃይማኖት ጠላቶቻቸው ተከበው፣ ዓለምን ረስተው ዓለምም ረስቷቸው ለአንድ ሺህ ዓመታት አንቀላፉ፡፡ እንደገና የባነኑት በፖርቹጋሎች ጉብኝት ነበር፡፡ ፖርቹጋሎቹም በመጀመሪያ ከሆነ የሩቅ ፕላኔት ከሰማይ እንደወረዱ ዓይነት ሆነውባቸዋል፡፡ [...] በብቸኝነት ዘመናቸው አቢሲኒያዊያን እንደገና ወደ ድንቁርና ሊመለሱ ምንም አልቀራቸውም ነበር፡፡ ከዘመናት በፊት እስከ [ሲሪላንካ] ደሴቶች በውቅያኖሶች ላይ ለንግድ የሚቀዝፉ መርከቦች እንዳልነበራቸው ሁሉ ኢትዮጵያዊያን የአፍሪካን ወንዞች እንኳን ማቋረጥ ተሳናቸው፡፡ የአክሱም ስልጣኔ ቅሪቶች ተረስተው ምድረበዳ ወረሳቸው፡፡ ሀገሪቱ ህብር አጥታ ወደ ተነጣጠሉ መንደሮች ወረደች፡፡"
ነገሥታቶቻቸው እስከ አስፈሪ ሞገሳም ስማቸው በሰላሙም በትርምሱም መሀል ረክተው የዘላን (ተንቀሳቃሽ- ቋሚ መኖሪያ የሌለው) አኗኗራቸውን ገፉበት፡፡»
👍 19❤ 1
አምስቱ የአስጊ ሁኔታ እውታዎች
1ኛ እውነታ፡- ማደግን እስካላቆምኩ ድረስ ፍርሃት ሊሄድ አይችልም፡፡
2ኛ እውነታ፡- አንድን ነገር የማድረግን ፍርሃት የማስወገጃው ብቸኛ መንገድ ወጥቶ ያንን የምንፈራውን ነገር ማድረግ ነው፡፡
3ኛ እውነታ፡- በራሴ ላይ ባለኝ አመለካከት ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ የማድረጊያው ብቸኛ መንገድ መውጣት … ማድረግ ነው፡፡
4ኛ እውነታ፡- ከዚህ በፊት ወደማላውቀው ክልል ውስጥ ስገባ ፍርሃት የሚሰማኝ እኔ ብቻ አይደለሁም፤ ይህ ሁሉም ሰው የሚጋራው ስሜት ነው፡፡
5ኛ እውነታ፡- ስጋቴን ተጋፍጬ ለመሄድ አቅም እንዳጠረኝና እንዳቃተኝ ሲሰማኝ በዚያ ፍርሃት ውስጥ ከመኖር ይልቅ ስጋቴን ተጋፍጬ በማለፍ የሚመጣው ፍርሃት እጅግ የተሻለና አናሳ ነው ፡፡
የየእለት ኑሮህ ከምንም አይነት አስጊ ሁኔታ (Risk) ነጻ ሊሆን እንደሚገባው ካሰብክ ከሁሉም ነገር ተጠንቅቀህ እንድትኖር ሊያነሳሳህ ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ምንም አይነት ስጋት እንዳይደርስብህ ስትል የተለመደውን ጎዳና ይዘህ ዘመንህን በፍርሃት እንድታባክን የማድረግ ተጽእኖ አለው፡፡
ለላቀ ውጤት ሲባል አዳዲስና ያልተለመዱ ነገሮችን ከማድረግ ጋር የሚመጣን ስጋት በጥንቃቄ በማጤንና ትክክለኛውን ስሌት በመስራት ወደ አዲስ ነገር ለመዝለቅ ያልወሰነ ሰው ከለውጥና ከመሻሻል የራቀ ሰው ከመሆኑም ባሻገር ሕይወት የአሰልቺ ድግግሞሾች መስክ ትሆንበታለች፡፡
በዚህ እውነታ ላይ የተለቀቀውን ቪዲዮ ከአንድ ሰአት በኋላ ስለማጋራችሁ ከተመለከታችሁ በኋላ ወደ አዲስ ነገር ለመግባት ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡
ዶ/ር እዮብ ማሞ
👍 56❤ 3👏 1
አምስቱ የአስጊ ሁኔታ እውታዎች
1ኛ እውነታ፡- ማደግን እስካላቆምኩ ድረስ ፍርሃት ሊሄድ አይችልም፡፡
2ኛ እውነታ፡- አንድን ነገር የማድረግን ፍርሃት የማስወገጃው ብቸኛ መንገድ ወጥቶ ያንን የምንፈራውን ነገር ማድረግ ነው፡፡
3ኛ እውነታ፡- በራሴ ላይ ባለኝ አመለካከት ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ የማድረጊያው ብቸኛ መንገድ መውጣት … ማድረግ ነው፡፡
4ኛ እውነታ፡- ከዚህ በፊት ወደማላውቀው ክልል ውስጥ ስገባ ፍርሃት የሚሰማኝ እኔ ብቻ አይደለሁም፤ ይህ ሁሉም ሰው የሚጋራው ስሜት ነው፡፡
5ኛ እውነታ፡- ስጋቴን ተጋፍጬ ለመሄድ አቅም እንዳጠረኝና እንዳቃተኝ ሲሰማኝ በዚያ ፍርሃት ውስጥ ከመኖር ይልቅ ስጋቴን ተጋፍጬ በማለፍ የሚመጣው ፍርሃት እጅግ የተሻለና አናሳ ነው ፡፡
የየእለት ኑሮህ ከምንም አይነት አስጊ ሁኔታ (Risk) ነጻ ሊሆን እንደሚገባው ካሰብክ ከሁሉም ነገር ተጠንቅቀህ እንድትኖር ሊያነሳሳህ ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ምንም አይነት ስጋት እንዳይደርስብህ ስትል የተለመደውን ጎዳና ይዘህ ዘመንህን በፍርሃት እንድታባክን የማድረግ ተጽእኖ አለው፡፡
ለላቀ ውጤት ሲባል አዳዲስና ያልተለመዱ ነገሮችን ከማድረግ ጋር የሚመጣን ስጋት በጥንቃቄ በማጤንና ትክክለኛውን ስሌት በመስራት ወደ አዲስ ነገር ለመዝለቅ ያልወሰነ ሰው ከለውጥና ከመሻሻል የራቀ ሰው ከመሆኑም ባሻገር ሕይወት የአሰልቺ ድግግሞሾች መስክ ትሆንበታለች፡፡
በዚህ እውነታ ላይ የተለቀቀውን ቪዲዮ ከአንድ ሰአት በኋላ ስለማጋራችሁ ከተመለከታችሁ በኋላ ወደ አዲስ ነገር ለመግባት ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡
ዶ/ር እዮብ ማሞ
የልማድ ምስጢር!
“ደጋግመን የምናደርገውን ነገር ነን፡፡ ስለሆነም፣ ልቀትና ምርጥነት የአንድ ጊዜ ተግባር ጉዳይ ሳይሆን የልማድ ጉዳይ ነው” - Aristotle
“እኔ የአንተ የዘወትር አጋርህ ነኝ፡፡ ታላቅ የሆንኩ ረዳትህ ነኝ ወይም ደግሞ ከባድ የምባል ሸክምህ፡፡ ወደ ስኬት ልገፋህ እችላለሁ፣ ወይም ደግሞ ወደ ውድቀት ልጎትትህ ብቃት አለኝ፡፡ ሁል ጊዜ እንዳዘዝከኝ ለመሆን ዝግጁ ነኝ፡፡ በየእለቱ ከምታደርጋቸው ነገሮች ገሚሶቹን ለእኔ አሳልፈህ ብትሰጠኝ ባፋጣኝና በትክክለኛው መንገድ አከናውናቸዋለሁ፡፡ ጠንከርና ጨከን ካልክብኝ፣ በቀላሉ ልትገራኝና ልታስተዳደረኝ ትችላለሀ፡፡ አንድ ነገር በምን መልኩ መደረግ እንዳለበት አሳየኝና ትንሽ ካለማመድከኝ በኋላ በፈለከው ጊዜ ሁሉ በፍጥነት አከናውንልሃለሁ፡፡ ታላላቅ የተሰኙ ሰዎች አገልጋይ ነኝ፤ ሆኖም የውድቀትና ያለመሳካትም ምክንያት እኔው ነኝ፡፡ ታላላቅ የሆኑን ሰዎች ታላቅ ወደ መሆን ያመጣኋቸው፤ የወደቁና ያልተሳካላቸውንም ሰዎች ለዚያ ያበቃኋቸው እኔ ነኝ፡፡ ማሽን አይደለሁም፤ ነገር ግን ልክ እንደ ማሽን የተሰጠኝን ሁሉ ሳላዛባ፣ ልክ እንደሰው ደግሞ በብልህነት እሰራለሁ፡፡ ከፈለክ ለትርፍ ተጠቀምብኝ ካለዚያም ለክስረት ተጠቀምብኝ፣ በእኔ በኩል እንደሆነ ምንም ልዩነት አያመጣም፡፡ ውሰደኝ፣ የራስህ አድርገኝ፣ አሰልጥነኝ፣ ጠንከርና ጨከን በልብኝ እኔም በተራየ አለምን አስገዛልሃለሁ፡፡ ቀለል በልልኝና ችላ በለኝ፣ አጠፋሃለሁ፡፡ ማን ነኝ? እኔ ልማድ እባላለሁ!” – Anonymous
ልማድ ማለት በአንድ ነገር አቅጣጫ ራሳችንን ከማስለመዳችን የተነሳ ያንን ነገር በቀላሉ ማድረግ ስንጀምርና እንደውም ማቆም ሲሳነን ማለት ነው፡፡ ይህ እውነታ ደግሞ ለጤናማውም ሆነ ለጤና ቢሱ ልማድ የሚሰራ እውነታ ነው፡፡ ልማድ ማለት ካለምንም የውጭ ግፊትና ጉትጎታ ማድረግ የጀመርነውና “የማንነታችን” ክፍል ወደ መሆን የመጣ ጉዳይ ነው፡፡ ከመልካም ልማድ ውጪ ማንም ሰው ምንም ነገር ማድረግ አይችልም፡፡ በሌላ አባባል ወደ ልማድ ባልመጣ መልካም ነገር ወደ ስኬት መምጣት አንችልም፡፡
ብቃትና ጥራት ማለት የተለመደን ነገር ባልተለመደ መልኩ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ይህ እንዲሆን ደግሞ መልካምን ልማድ ማዳበር የግድ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ በአንድ ስፖርት ኦሎምፒክ ላይ የሚወዳደሩ ሰዎች በአማካኝ ካለማቋረጥ ለስድስት ዓመታት ሙሉ በአመት ለ310 ቀናት፣ በየቀኑ ለአራት ሰዓታት ልምምድ ያደርጋሉ፡፡ ሌሎች ሰዎች ቀኑን ሙሉ የማይሰሩትን ስራ እነዚህ ስፖርተኞች ጠዋት አንድ ሰዓት ከመሆኑ በፊት ሰርተው ይጨርሳሉ፡፡
አሁን ምንም አይነት የላቀ ደረጃ ላይ የደረሰን ሰው ተመልከትና ጀርባውን አጥና፤ ለረጅም ጊዜ ደጋግሞ ያደረገውንና የገነባውን አንድ ነገር ታገኛለህ፡፡ በሌላ አባባል፣ አሁን የደረሰበት የላቀ ደረጃ የደረሰው በአጋጣሚ ሳይሆን አንድን መልካም ልማድ አዳብሮና በዚያ ልማድ ዙሪያ ደጋግሞ በመስራትና በመሻሻል ነው፡፡
የንጽህና ልማድ ቤትን፣ አካባቢንና አገርን በንጽህና ልቀው እንዲገኙ ያደርጋቸዋል፡፡ የስራ ልማድ በብልጽግና ልቀን እንድንገኝ ያደርገናል፡፡ የጥናት ልማድ በእውቀት እንድንልቅ መንገዱን ይጠርጋል፡፡ ከማንኛውም ውብ ነገር ጀርባ መልካም ልማድ አለ፡፡ በእኔና በአንተም ኑሮ ስሌቱ ያው ነው፡፡
አንድ ቀን ከእንቅልፋችን ስንነሳ በአንድ ነገር ልቀን አንገኝም፡፡ ከአንድ ግብ አንጻር በየእለቱ የገነባናቸው ልማዶቻችን ናቸው የነገን ልቀታችንን የሚወስኑት፡፡ ልማድ የሕወታችንን አብዛኞዎቹን (ምናልባት ሁሉንም) ነገሮች አቅጣጫ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ ጤንነታችንን፣ ኢኮኖሚያችንን፣ ወዳጅነታችንን የኑሮአችንን ጥራትና ሌሎችም ዋና ዋና ነገሮችን ስለሚወስን፤ ልማድ ሲጨመቅ ማንነት ይሆናል፡፡
ዶ/ር እዮብ ማሞ
@Human_Intelligence
👍 47❤ 9👏 5🙏 4😢 1
የልማድ ምስጢር!
“ደጋግመን የምናደርገውን ነገር ነን፡፡ ስለሆነም፣ ልቀትና ምርጥነት የአንድ ጊዜ ተግባር ጉዳይ ሳይሆን የልማድ ጉዳይ ነው” - Aristotle
“እኔ የአንተ የዘወትር አጋርህ ነኝ፡፡ ታላቅ የሆንኩ ረዳትህ ነኝ ወይም ደግሞ ከባድ የምባል ሸክምህ፡፡ ወደ ስኬት ልገፋህ እችላለሁ፣ ወይም ደግሞ ወደ ውድቀት ልጎትትህ ብቃት አለኝ፡፡ ሁል ጊዜ እንዳዘዝከኝ ለመሆን ዝግጁ ነኝ፡፡ በየእለቱ ከምታደርጋቸው ነገሮች ገሚሶቹን ለእኔ አሳልፈህ ብትሰጠኝ ባፋጣኝና በትክክለኛው መንገድ አከናውናቸዋለሁ፡፡ ጠንከርና ጨከን ካልክብኝ፣ በቀላሉ ልትገራኝና ልታስተዳደረኝ ትችላለሀ፡፡ አንድ ነገር በምን መልኩ መደረግ እንዳለበት አሳየኝና ትንሽ ካለማመድከኝ በኋላ በፈለከው ጊዜ ሁሉ በፍጥነት አከናውንልሃለሁ፡፡ ታላላቅ የተሰኙ ሰዎች አገልጋይ ነኝ፤ ሆኖም የውድቀትና ያለመሳካትም ምክንያት እኔው ነኝ፡፡ ታላላቅ የሆኑን ሰዎች ታላቅ ወደ መሆን ያመጣኋቸው፤ የወደቁና ያልተሳካላቸውንም ሰዎች ለዚያ ያበቃኋቸው እኔ ነኝ፡፡ ማሽን አይደለሁም፤ ነገር ግን ልክ እንደ ማሽን የተሰጠኝን ሁሉ ሳላዛባ፣ ልክ እንደሰው ደግሞ በብልህነት እሰራለሁ፡፡ ከፈለክ ለትርፍ ተጠቀምብኝ ካለዚያም ለክስረት ተጠቀምብኝ፣ በእኔ በኩል እንደሆነ ምንም ልዩነት አያመጣም፡፡ ውሰደኝ፣ የራስህ አድርገኝ፣ አሰልጥነኝ፣ ጠንከርና ጨከን በልብኝ እኔም በተራየ አለምን አስገዛልሃለሁ፡፡ ቀለል በልልኝና ችላ በለኝ፣ አጠፋሃለሁ፡፡ ማን ነኝ? እኔ ልማድ እባላለሁ!” – Anonymous
ልማድ ማለት በአንድ ነገር አቅጣጫ ራሳችንን ከማስለመዳችን የተነሳ ያንን ነገር በቀላሉ ማድረግ ስንጀምርና እንደውም ማቆም ሲሳነን ማለት ነው፡፡ ይህ እውነታ ደግሞ ለጤናማውም ሆነ ለጤና ቢሱ ልማድ የሚሰራ እውነታ ነው፡፡ ልማድ ማለት ካለምንም የውጭ ግፊትና ጉትጎታ ማድረግ የጀመርነውና “የማንነታችን” ክፍል ወደ መሆን የመጣ ጉዳይ ነው፡፡ ከመልካም ልማድ ውጪ ማንም ሰው ምንም ነገር ማድረግ አይችልም፡፡ በሌላ አባባል ወደ ልማድ ባልመጣ መልካም ነገር ወደ ስኬት መምጣት አንችልም፡፡
ብቃትና ጥራት ማለት የተለመደን ነገር ባልተለመደ መልኩ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ይህ እንዲሆን ደግሞ መልካምን ልማድ ማዳበር የግድ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ በአንድ ስፖርት ኦሎምፒክ ላይ የሚወዳደሩ ሰዎች በአማካኝ ካለማቋረጥ ለስድስት ዓመታት ሙሉ በአመት ለ310 ቀናት፣ በየቀኑ ለአራት ሰዓታት ልምምድ ያደርጋሉ፡፡ ሌሎች ሰዎች ቀኑን ሙሉ የማይሰሩትን ስራ እነዚህ ስፖርተኞች ጠዋት አንድ ሰዓት ከመሆኑ በፊት ሰርተው ይጨርሳሉ፡፡
አሁን ምንም አይነት የላቀ ደረጃ ላይ የደረሰን ሰው ተመልከትና ጀርባውን አጥና፤ ለረጅም ጊዜ ደጋግሞ ያደረገውንና የገነባውን አንድ ነገር ታገኛለህ፡፡ በሌላ አባባል፣ አሁን የደረሰበት የላቀ ደረጃ የደረሰው በአጋጣሚ ሳይሆን አንድን መልካም ልማድ አዳብሮና በዚያ ልማድ ዙሪያ ደጋግሞ በመስራትና በመሻሻል ነው፡፡
የንጽህና ልማድ ቤትን፣ አካባቢንና አገርን በንጽህና ልቀው እንዲገኙ ያደርጋቸዋል፡፡ የስራ ልማድ በብልጽግና ልቀን እንድንገኝ ያደርገናል፡፡ የጥናት ልማድ በእውቀት እንድንልቅ መንገዱን ይጠርጋል፡፡ ከማንኛውም ውብ ነገር ጀርባ መልካም ልማድ አለ፡፡ በእኔና በአንተም ኑሮ ስሌቱ ያው ነው፡፡
አንድ ቀን ከእንቅልፋችን ስንነሳ በአንድ ነገር ልቀን አንገኝም፡፡ ከአንድ ግብ አንጻር በየእለቱ የገነባናቸው ልማዶቻችን ናቸው የነገን ልቀታችንን የሚወስኑት፡፡ ልማድ የሕወታችንን አብዛኞዎቹን (ምናልባት ሁሉንም) ነገሮች አቅጣጫ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ ጤንነታችንን፣ ኢኮኖሚያችንን፣ ወዳጅነታችንን የኑሮአችንን ጥራትና ሌሎችም ዋና ዋና ነገሮችን ስለሚወስን፤ ልማድ ሲጨመቅ ማንነት ይሆናል፡፡
@Human_Intelligence
አያ ጅቦ አለህ ? አለሁ ምን እየሰራህ ነው?....
እናንተን ልበላ
እናቴ የአምስተኛ እና የስድስተኛ ክፍል ጂኦግራፊ አስተማሪ ነበረች፤ ጡረታ ከመውጣቷ በፊት፡፡ የምታስተምርበት ትምህርት ቤት ብማርም እሷ የምታስተምርበት ክፍል አልተማርኩም። ልጆች ስለምትወድ፣ እንደ ልጆቿ ስለምትቀርባቸው እንደሚወዷት በርካታ ጊዜ ምስክርነት ሰምቻለሁ፡፡ አሁን እንኳን ጡረታ ወጥታ መንገድ ላይ ያስተማረቻቸው ተማሪዎች ፍቅር እና አክብሮታቸውን ሲገልጹላት ብዙ ጊዜ አይቻለሁ።
እናቴ የላላ፣ የተቆጠበ ማኅበራዊ ግንኙነት ያላት፣ ረጋ ያለች፣ ፈገግታ የማይለያት ደርባባ ሴት ናት። ሙሉ ጸጉሯ ሃጫ በረዶ መስሎ ጥቁር ነበረው ቢባል ለማመን ይቸግራል። ብቻዋን ነው ያሳደገችኝ፡፡
ልጅ ሳለሁ እቴቴ አባቴ የት ነው ያለው? እላታለሁ፡፡
“ይመጣል ሰላም ለማስፈን ነው የሄደው” ትለኝ ነበር!! በስንት ተረት ሰላም ምን ማለት እንደሆነ ከገባኝ በኋላ ሁከት እና ግርግር ሳይ አባቴ አልደረሰም ማለት ነው እያልኩ፣ ሲደርስ አባቴ ሁሉን ያስተካክላል እያልኩ አደግሁ።
ሲደርስ ሰላም ይሆናል።
"ትንሽ ነፍስ ሳውቅ አባቴ ጦርነት እንደሄደ፣ እናት ሀገሬ ብሎ ሸልሎ ወጥቶ አድሮ ወጥቶ መቅረቱ ተገለጸልኝ። አባቴ እንዴት ነበር? እለዋለሁ ከእኔ በዕድሜ በልጦ ተወልዶ በጥቂትም ቢሆን አባቴን የሚያውቀው ወንድሜን።
“አባታችን ተጫዋች፣ እናታችንን የሚንከባከብ፣ ደ'ሞ ደ'ሞ ከሥራ ማታ ሲመጣ ሁሌም በፌስታል ለእኛ አንድ ነገር ሳይዝ የማይመጣ፤ ከሥራ ደክሞት እንኳን መጥቶ ሳያጫውተን የማያድር ነበር” እያለ ይተርክልኛል።
በትንሹም በትልቁም አባቴ ቢኖር እላለሁ፤ ጉድለቱ ሲሰማኝ... አባት እና ልጅ ሲሄዱ የልጁ ዕድለኝነት ሲታየኝ የአባት ፍቅር ጉድለት ስሜት እየጠዘጠዘኝ፣ እኔም እንደ ማደግ ወንድሜም ለአቅመ አዳም ደረሰ።
ወንድሜ ሥልጣን ላይ ያሉትን የአባቴን ገዳዮች ለመታገል ፖለቲካን ማደሪያው አደረገ። ተቃዋሚ ነን ካሉት ጋር ሁሉ ቀድሞ ይሰለፋል፡፡ ሁሌም የተቃዋሚዎች ባንዲራ ያዥ እሱ ነው፡፡ ደፋር ነው ይሉታል።
አንድ ቀን ማታ እናቴ “ወንድሜ ቤት አላደረም” ብላ ሀገር ይያዝ አለች... ፈለገች፣ አስፈለገች... እሱን የበላ ጅብ አልጮህ አለ። ከጥቂት ቀን በኋላ ግን መታሰሩን ሰማን... እናቴ አነባች፣ ተንገበገበች! ያኔ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍቶኝ ስቅስቅ ብዬ ያለቀስኩት። ንፍጤን እና እንባዬን እየጠረግኩ አይመጣም እኮ እሱም እንደ አባዬ አይመጣም በኋላ ማንም የሚያግዝልኝ፣ ወንድሜ አይመጣም
የሚያስጠናኝ አይኖርም... እያልኩ አለቀስኩ!
በወንድሜ መታሰር ድብርት ይሆን ብቸኝነት የሆነ ውሉ የማላውቀው መንፈስ ወረረኝ። ደፋር እኮ ነው እያሉ ከፊት ሲያሰልፉት የነበሩት ሰዎች አንድ ቀን እንኳን ለመጠየቅ አልደፈሩም፡፡ የታሰረበትን የሚነግረን አጥተን ስንከራተት ያውቁ እንደሆን ስንጠይቃቸው እሱን ራሱ አናውቀውም አሉን፡፡
እናቴ የተነሳውን ርእስ ወደ ወንድሜ ስባ አምጥታ “አሄሄሄሄ ያልታደልኩ” ትላለች። በሰልኩ መሰለኝ ድሮ ስለ አባቴ እያወራችኝ ስታለቅስ፣ ሕመሟ ስለማይገባኝ ጀመራት የምል የነበርኩ ልጅ ዛሬ እኔ አለሁልሽ እያልኩ አጽናናት ጀመር።
ወንድሜ በታሰረ በሁለተኛ ወሩ እስር ቤት ውስጥ በተፈጠረ ጠብ መሞቱን ፖሊሶች ቤታችን መጥተው ሦስት መሥመር በማትሞላ ደብዳቤ አረዱን። እርማችንን ተንሰቅስቀን፣ ተንቀጥቅጠን አወጣን።
አባቴ እና ወንድሜ ሞቱ። ነገር ግን ለሞታቸው መታሰብያ የሞቱለት ጨለማን የማውደምም ሆነ ብርሃን የማፈንጠቅ ሂደት አልተከናወነም።
የቤታችን ሁለት የሙቀት ምስሶዎች ተገንድሰው ያለ ሙቀት፣ ያለ ምሰሶ እንኖራለን!
እኔ ስሜ ብርሃኑ ቢሆንም እናቴ ብርሃኔ ነው የምትለኝ፡፡ “ብርሃኔ” ስትለኝ 'ኔ' ን እርግጥ ጫን አድርጋ ስለምትጠራኝ የሆነ ማያዬ፣ እይኔ፣ ጧሪዬ የምትለኝ ነው የሚመስለኝ።
እንደ መርፌ ቀዳዳ አንድ ሆኜባት የኑሮ ፍልስፍናዋ በእኔ እና በኔ ዙሪያ ያጠነጥናል። ትንሽ ካመሸሁ ሰቀቀኗ ልክ የለውም። ሁሉም ነገር በሷ ሐሳብ ልክ ብቻ መሆን አለበት። አስራ ሁለት ሰዓት ቤት መግባት አለብኝ። አንድ ደቂቃ ካለፈ ስልኬ ይጮሃል። ቤት ገብቼ የማወራቸው ወሬዎች ከሀገር፣ ከመንግሥት፣ ከፖለቲካ የራቁ መሆን አለባቸው። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለፖለቲካ ቀረበ፣ ለሀገር መቆርቆር ስሜት ያለው ወሬ ማውራት አልችልም።
“ብርሃኔ አደራህን አታምሽ፣ በማያገባህ አትግባ፣ በፖለቲካም ቢሆን፤ ደ'ሞ ደ'ሞ ፖለቲካ ሽንፍላ ነው አይጸዳም፤ የራስ ወዳዶች መጠቀሚያ ቃታ ነው፤ የግል ችግሩን እኛ እያለ እየቸረቸረ ዝና እና ፍራንክ የሚለቅም ብቻ ነው ያለው፡፡"
ሐሳብ ከሐሳብ አይፋጭም። እኔ ልብላው፣ እኔ ካልበላሁት በሚል ይናጫሉ እንጂ ትግሉ የሐሳብ፣ ለሕዝብ ጥቅም የቆመ አይደለም፡፡ ሕዝብ ሕዝብ የሚሉት ለቲፎዞ ነው። አየህ ልጄ በፖለቲካ ጥሩ የደደበው ያሸንፍና ሥልጣን ይይዛል። ትዕቢት የወጠረው ደግሞ ይወድቃል፤ እኔ የማውቀው እና ያየሁት ፖለቲካችን ይሄ ነው፤ እንዳትበላብኝ አበባዬ።
ይሄውልህ ብርሃኔ ብሔር፣ ጎሳ፣ ዝምድና የፖለቲካችን መሠረት ነው። በእሱ ትሰባሰባለህ፣ ሴራ፣ ውሸት፣ ሆድ፣ ክሕደት፣ ድድብና አለው፡፡ ዓለሜ የታላቅነት እውነተኛ ሕልም፣ እውቀትህ ያስበላሃል። እውነተኛ ከሆንከ ያሴሩብሃል፣ ያድሙብሃል፣ ስምህን ያጠለሹታል። የማያውቅህ ወታደር ጥንካሬውን ይፈትሽብሃል ወይ ደግሞ እንዳባትህ እና ወንድምህ ግንባርህን ይልሃል።”
"ፖለቲካችን ሞት አለው፤ ካልጨከንክ፣ ካልደደብክ መከራ ይጥልብሃል፣ ያሻህን ተናግረህ አትኖርም፣ አትወጣም፣ አትገባም፣ ሚስትህን ባል አልባ፣ ልጅህን አባት ታስናፍቀዋለህ። ቂመኛ ነው ቀን ይጠብቅልሃል። እንደኔ ባል እና ልጅ እንዳንተ አባት እና ወንድም ደቼ ትበላለህ።
ብርሃኔ እኔ ልሙት እልሃለሁ ፖለቲካችን ውስብስብ አይደለም። ለመጉላት ደደብ እና ራስ ወዳድ መሆን መስፈርቱ ነው። የሚወደድ ነገር የለውም፡፡
አበባዬ የሚፈልጉትን የሚያጎሉት እና የሚያፈዙት እነርሱ ራሳቸው ናቸው። ይሄውልህ ብርሃኔ በዚህ ጸድቶ በማይጸዳ ፖለቲካ ብትሞትብኝ ለአንድ ሳምንት ብሶቴ፣ እንባዬ፣ ለቅሶዬ በየሰፈሩ በየካሜራው ይንከባለላል። ከዛ... ይረሳል፤ ሐዘኑ እና ስብራቱ እኔ ጋ ብቻ ይቀራል።
ብርሃኔ የተበላሸ ሂደት ውስጥ ትክክል መሆን ስሕትት ነው!!
ልጄ የዚህ ሀገር ፖለቲካ ይቅርብህ፤ ትበላብኛለህ። አንዲት ጣት ማጣት ለማይገባው ዓላማ ባል እና ልጄን ገብሬያለሁ። ይበቃኛል።
ዜናው፣ ትግሉ፣ ፕሮፖጋንዳው፣ ጽንፈኝነቱ ከሰውነት ማማ ላይ ያወርዳል።
አደራህን ዓለሜ ግርግር ስታይ ለማጣራትም ብለህ ቢሆን እንኳን አትገተር። አትቀላቀል፤ ፖለቲከኞች ለግል ጥቅም ነው ተናጭተው የሚያናጩት። ሕዝብ ጥቅም ማግኛ ቃታቸው ነው። ችግሩ ወደ አንተ ካልመጣ አንተ ወደ ችግሩ አትሂድ።”
ከእናቴ የተለየ ሐሳብ ባይኖረኝም ያጣችውንም ስለማውቅ ስትናገር ጣልቃ ሳልገባ እሰማታለሁ፡፡
ዛሬም አባቴን እና ወንድሜን የበሉት ጅቦች ይጮኻሉ። ፕሮፖጋንዳቸውን ይነዛሉ። አንዱ ጎራ “ተነስ ከእኔ ጋ ብርሃን፣ ሰላም፣ ብልጽግናን በጋራ እናምጣ” ሲል አንዱ ጎራ “ሁሉም ሰላም ነው ተኛ! ዋ!” ይለኛል። ሁለቱም ጎራ እያንዳንዱን ክስተት ሥልጣን ማቆያ እና ሥልጣን መጨበጫ እንድትሆን አድርገው ይቀነብቧታል። ለሁሉም ና ከእኛ ጋ ሁን ጥሪዎቻቸው መልሴ ግን አንድ ነው፡፡
ወንድሜን እና አባቴን መልሱልኝ እና!!!
መፅሀፍ- አዎ እሱጋ ያመኛል
ደራሲ - አድሀኖም ምትኩ
share& Join
@Human_Intelligence
👍 82❤ 6🙏 5🔥 1😢 1
ከእዳ ወደ የምን እዳ?
(በእውቀቱ ስዩም)
ጋሻው አዳል የተባለ የምወደው የቆየ ዘፋኝ እንዲህ የምትል ዝነኛ ዘፈን አለችው፥
“ማለዳ ማለዳ
ማለዳ መጥተሽ
አይ ! እህህ
ማለዳ መጥተሽ
እኔን ሳታገኝ ትመለሻለሽ?”
ዘፈኑን በሰማሁ ቁጥር ጋሻውን እንዲህ እለዋለሁ” አባ! በማለዳ የት ሄደህ ነው የማታገኝህ? ውስጥህ የበቀለውን ችግኝ ስታጠጣ አምሽተህ በዛው መንገድ ላይ የመሰረት ድንጋይ ተንተርሰህ አድረህ ነው?”
ሳስበው፥ ጋሻው ይህንን ዘፈን የዘፈነው ለፍቅረኛው ሳይሆን ለአበዳሪው ይመስለኛል፤ ብድር ስር ምን ትዝ አለኝ !ኢትዮጵያ ብድር መመለስ ከተሳናቸው አገሮች አንዷ ሆና እንደተመደበች ሰማችሁ አይደል? እምደንቅ እኮ ነው!
ባለፈው ያሜሪካው ያውሮፓ አበዳሪዎች ከኢትዮጵያ ግምጃ ቤት ሀላፊ ጋር ተገናኝተው በጠረጴዛ ዙርያ እና በጠረጴዛ ስር ተወያይተው ነበር;
በቦታው ተገኝቼ እንደታዘብኩት ውይይቱ ይህንን ይመስላል፥
ያሜሪካው - እዳችንን መች ነው ምትከፍሉን?
የኢትዮጵያው- የምን እዳ?🤔
ያውሮፓው- በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ እንዳበደርናችሁ ረሳችሁት እንዴ?
የኢትዮጵያው - ስራ ስለሚበዛ እንረሳለን!
የአሜሪካው - እስቲ መፎጋገሩን ትተን በግልጽ እናውራ፤ በኢኮኖሚ ደረጃ የት ላይ ነው የምትገኙት?
የኢትዮጵያው፤- ማለት?
የአውሮፓው ፤- እርሙን የበላ ድሀ ናችሁ ? ወይስ ቀን የሚወጣለት ድሀ ናችሁ?
የኢትዮጵያው - የሰው ሀብት አለን ! መቶ አምሳ ሚሊዮን ደርሰናል ! ጠባይ ካላችሁ አምሳ ሚሊዮኑን ህዝብ ልንለግሳችሁ እንችላለን !
የአሜሪካው - እያወራን ያለነው ስለገንዘብ ነው !
የኢትዮጵያው - እንዳታባክኑት እኛው ጋ ይቀመጥላችሁ ብለን ነው እንጂ ገንዘቡም ቢሆን አለ!
የአውሮፓው- ሌላው ቢቀር ወለዱን ክፈሉን
የኢትዮጵያው- ለጊዜው አይርወለድ እንጂ ወለድ አላዘጋጅንም!
የአሜሪካው-- ሌላ ምን መፍትሄ ይኖራል?
የኢትዮጵያው-- ጥቂት የእፎይታ ጊዜ ስጡን!
ያውሮፓው --ምን ያህል ጊዜ?
የኢትዮጵያው- ትንሽ አምሳ አመት ብትታገሱን
ያውሮፓው- በአምሳ አመት ጊዜ ውስጥ ብድሩን የምትከፍሉበት የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ትደርሳላችሁ?
የኢትዮጵያው--አይ እናንተ ብድሩን የማትፈልጉበት ደረጃ ትደርሳላችሁ’
የአሜሪካው -- ከዛሬ ጀምሮ ከዛምቢያ እና ከጋና ቀጥሎ መበደር ከማይችሉ አገሮች ጎን ተመድባችሁዋል!
የኢትዮጵያው- ይህንን ጨካኝ ርምጃ ዝም ብለን አናየውም 🙁🙁
የአውሮፓው- ምን ልታደርጉ ትችላላችሁ?
የኢትዮጵያው---ብድር የተነፈጉ አገሮች ማህበር መስርተን እንታገላለን !
የአሜሪካው- እናያለን !
እዚህ ላይ፥ የኢትዮጵያው በንዴት ተሰናብቶ ከሄደ በሁዋላ እንደገና ተመልሶ መጣና ፥
“አንድ የመጨረሻ ጥያቄ ነበረኝ ! “ አለ፤
ሁለቱ ሀያላን - ምንድነው?
የኢትዮጵያው፤-
“ዛምቢያን አስይዘን መበደር አንችልም?”
***
በዕውቀቱ ሥዩም
@Human_Intelligence
🤣 56👍 42😢 8❤ 6🙏 4
የምሽቱ ወሳኝ ጥያቄዎች!
አንድ እውነታ ጋር የመድረሻው ትክክለኛው፣ አቋራጩና ፈጣኑ መንገድ ትክክለኛውን ጥያቄ መጠየቅ ነው፡፡
ከዛሬ በመጀመር ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ራሳችሁን ልትጠይቁ የሚገባችሁ ወሳኝ ነገሮች . . .
• በፍጹም እንደማያስኬደኝ የገባኝና ማቋረጥ ያለብኝ ተግባር ምንድን ነው?
• በፍጹም ማቆም ሳይገባኝ ያቆምኩትና እንደገና መጀመር ያለብኝ ተግባር ምንድን ነው?
• በፍጹም እንደማያዛልቀኝ የተረዳሁትና ማቆም ያለብኝ ግንኙነት የትኛው ነው?
• በፍጹም ላቋርጠው ሳይገባኝ በስሜታዊነት ያቋረጥኩትና እንደገና በይቅርታ ማስተካከል ያለብኝ ግንኙነት የትኛው ነው?
• በፍጹም ትኩረቴን ልጥልበት የማይገባኝና የትኩረት ለውጥ ላደርግበት የሚገባኝ አእምሮዬን የተቆጣጠረው ሃሳብ ምንድን ነው?
ዛሬ ማታ እነዚህን ጥያቄዎች በመጠየቅ መልስን ሳታገኙ ወደ መኝታችሁ ላለመሄድ ሞክሩ፡፡
ጥያቄዎቻችሁ ሰፋ ካሉና ጊዜን ከጠየቁ የተወሰኑትን ከመለሳችሁ በኋላ ከራሳችሁ ጋር ለነገ ቀጠሮን በማድረግ ነገ ቀጥሉት፡፡
ከላይ የተጠቀሱትንና መሰል ጥያቄዎችን መጠየቅና እውነታው ጋር መድረስ የመጀመሪያው የቆራትነት እርምጃ ሲሆን፣ ከዚያ አለፍ ያለው ቆራጥነት ደግሞ የደረስንበትን እውነታ ለመቀበልና ለውጥን ለማምጣት የመወሰን ቆራጥነት ነው፡፡
መልካም አዳር!
@Human_Intelligence
ጎሰሳችን ከሽፎ እንጂ
ጥዑም ጊዜ ላይ ነበርን፡፡ ወይን እየተጎነጨን፣ እየተሳሳምን፣ ድንገት ሳላቅድ፣ ሳልቀምር፣ ሳላስብበት ከአንደበቴ የውስጤ እውነት አመለጠኝ።
ትክ ብዬ ሳያት ፈገግ ብላ “እችን የመሰለች ልጅ ጠበስክ አ?” አለችኝ ወደ ራሷ እያመለከተች፤ በትንሹ ፈገግ አልኩ፡፡ ፈገግታዬን እንደ መስማማት ቆጥራ በሚያምር ፈገግታዋ እያየችኝ “እናትህማ መርቀውሃል” ስትለኝ ይሄኔ ነበር የልቤ እውነት ያመለጠኝ፡፡
ታውቂያለሽ ግን አንቺ ሕልሜ እንዳልሆንሽ፤ የመጣሽበት መንገድ፣ ዕቅድሽ፣ መርሕሽ ከእኔ ጋ መች ይሄዳል? አልኳት።
ሽማግሌ ከላክሁኝ በኋላ፣ በጋራ ስለምንወልዳቸው ልጆቻችን ስናወራ ከርመን እንዴት እንዲህ ይባላል? ሁሉ እውነት እንዴት ይወራል? የልብ እውነት ሁሉ ይዘረዘራል?! ትበሳጫለች ብዬ ነበር ግን ደግሞ የጠበኩትን የፊት መለዋወጥ አላየሁም። ረጋ እንዳለች፣ ፊቷ ሳይለዋወጥ ትክ ብላ አየችኝ፤ ቅፍፍፍ የሚል ስሜት ዋጠኝ፤ ምን አለ አስማተኛ በሆንኩ እና እንዳልሰማች ማድረግ አልያም እንዳልተናገርኩ መሆን ብችል።
ቃላቱን እርግጥ አድርጋ
“ትክክል!! ጊዜው አሳዝኖን ነው አብረን የሆነው፤ አብረን ሆነን በስሱ ሌላ የፍለጋ ሙከራ ስላልተሳካልን ነው የምንጋባው። አንዲት ቀን Messenger'ህን ከፍቼ አይቻለሁ፡፡ የምታወራቸውን እንስቶች ቀልብ ለመግዛት የምትሄድባቸውን መንገዶች፣ መሻፈዶች፣ ላጤ ነኝ ጨዋታዎች፣ ብልግናዎች ተመልክቻለሁ፤ ሁሉም ከእኔ ጋ አንድ ዓይነት ነበሩ። የማደርገውን ነበር የምታደርገው፤ ከፍቶኝ ነበር እንዳላኮርፍ፣ እንዳልጨቀጭቅህ፣ እንዳልጣላህ ካንተ አለመሻሌ አሸማቀቀኝ። የብዙ ሰዎች ትዳር እንዲህ እንደሆነ አይቻለሁ፤ ከገቡ በኋላ በልጆቻቸው ይጽናናሉ፤ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሚስትና እና ባላቸውን እየከሰሱ ኑሮን ይገፉታል።
ለዛ ነው እንከን የለሽ ትዳር የሚያስሱት ቆመው የሚቀሩት!
በቆዩ ቁጥር መለኪያቸውን እየቀየሩ ካጣጣሉት፣ ከተጠየፉት የኑሮ ቀንበር ላይ ራሳቸውን ያገኙታል። ለዛ ነው እንደሚታረድ በግ ሁሉን እያወቅኩ ሽማግሌ ስትልክ፣ ቀለበት ስታጠልቅልኝ፣ የልቤን እውነት አፍኜ የምከተልህ፡፡”
ሲዘበራረቅብኝ ይታወቅኛል። ግራ ገባኝ፤ የሕይወት አጋርን በዚህ ደረጃ አለማወቅ ምን ይባላል? እችን ልጅ ነገሮች በዚህ ደረጃ ይገባታል ብዬ አላሰብኩም። ሴት ልጅ ትታለልልሃለች እንጂ አታታልላትም፤ እኔ እንዲህ እንደሚሰማኝ እንጂ እሷ እንደዚህ እንደሚሰማት አላውቅም ነበር።
ለምን ታድያ አብረን እንሆናለን ሁለታችንም እንዲህ ከተሰማን?
“እኔንጃ”
ምን አልባት ጊዜያችን፤
ምን አልባት ዕድሜያችን አሳዝኖን?
ምን አልባትም በዙሪያችን ያለ ውትወታ?
ምን አልባት ዘራችንን ለመተካት ካለን ፍላጎት?
ምን አልባት መላመዳችን እንዳንለያይ አግቶን ይሆን?
ምን አልባት አንዳችን ለአንዳችን ካለን ውስጣዊ ስሜት ይሆን?
ምን አልባት በዙሪያችን ካሉት ሰዎች የበለጠ ስለምንዋደድ??
ምን አልባት በስሱ ሌላ ለማግኘት ያሰስነው ኀሰሳ ስላልተሳካ??”
ሰው የልቡን ሁሉ አለማውጣቱ ይሆን ቁርኝታችንን ያላሳደፈው? ባለጋራችንን አለማወቅ ጠቀሜታ ይኖረው ይሆን? አንዳንድ ዕውቀት ምቾት አይሰጥም፡፡ ዕውቀት ትካዜን ታበዛለች እንዲል መጽሐፉ፤ አንዳንድ ውይይቶች ሽንቁር ያበጃሉ፡፡ የጀመርኩትን ወይኔን በአንድ ትንፋሽ ወደ ጉሮሮዬ አንቆረቆርኩት፡፡
እንደዚህ ዓይነት ሎጂክ ተዘባዝቦ ግንኙነት፣ ትዳር መመሥረት ይቻል ይሆን? እንዳለችው ፍርሀት ነው? እጦት ነው? መላመድ ነው? ምንድን ይሆን በትክክል ያጋመደን?
ምን አስቸኮለን? ምን አሸበረን? ይሄን እውነታ ከተዘራዘሩ በኋላ እንዴት ጎጆ ይቀለሳል? ልጅ ሳይመጣ፣ ንብረት ሳናፈራ፣ ኑሮ ሳይንጠን የግንኙነታችንን መዓዘን መገምገም እንዳለብን ነው የገባኝ። አሁን የምጎዳት ነገ ከምሰብራት አይበልጥም፤ ዛሬ የሚሰማኝ ሕመም ነገ ከሚጋረጥብኝ መከራ አይበልጥም፡፡
ማሬዋ ሰው ውድ ፍጠር ነው። ችኮላችን፣ ብልጣብልጥነታችን፣ በራሳችን ማስተዋል ላይ መንጠልጠላችን የእኛ የራሳችን የሆኑት ሰዎች ጋ አንድንሸዋወድ ያደርገናል። ጊዜ እንውሰድ፣ ተነጣጥለን ዙሪያችንን፣ መንገዳችንን እንመርምር፤ ብልግናችንን ይቅር እንበለው። የቆምንባቸውን ስፍራዎች እንቃኛቸው፣ ከፈጸምናቸው ጥፋቶች ጋ እንፋጠጥ፣ እናርማቸው፣ እናበጃጃቸው፡፡ ብቸኝነት አባብቶን፣ አቻ ግፊት ወትውቶን፣ መላመድ አሳስሮን፣ የቤተሰብ ግፊት ገፈታትሮን ኑሮ አይመሠረትም። የሁሉም ጓዳ እንዲህ ነው ተብሎ አዲስ ጎጆ አይበጅም፤ ሁሉም ሄዷል ተብሎ እንኳን በስሕተት መንገድ በትክክለኛ መንገድ መሄድ ተገቢ አይደለም።
ከመጣንበት መንገድ የምንሄድበት ሩቅ ነው። ራሳችንን ከእርስ በእርሳችን ነጣጥለን እናጢነው። የአሰተውሎት መንገድ ደግሞ አሜን ካልነው ባሻገር ያለውን እውነታ መጋፈጥን ይጨምራል።
ያኔ የውስጣችን እውነት ፍንትው ብሎ ይታየናል፤ ለውሳኔም ይረዳናል። ስሕተታችንን ለማረም የመጀመሪያው እርምጃ ነው።
ከዚህ ሁሉ መንገድ ከፍርሀት ጋ መጋፈጥ
በኋላ መመለስ እንዳስፈራት ታስታውቃለች፡፡ እኔም የወጠንኩትን፣ የለመድኩትን፣ የወሰንኩትን ዳግም ለመመርመር እና ለመከለስ ሳስብ ደስስ የማይል የሚቀረዝዝ ስሜት ሲወረኝ እየተሰማኝ ነው።
መፅሀፍ- አዎ እሱጋ ያመኛል
ደራሲ - አድሀኖም ምትኩ
share
Join: @Human_Intelligence
👍 42🤔 5
እያንዳንዱን ችግር እንደ መሰላል ከተወጣጣህበት ከስኬት ጫፍ ትደርሳለህ!!
በአንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጉድ ወስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች፡፡ በጣም መጮህ ጀመረች፡፡ ባለቤቱም እሷን ለማውጣት ብርቱ ሙከራ አደረገ አልተሳካለትም ፤ አህያዋ አርጅታለችና ጉድጓድ ውስጥ ሊቀብራት አሰበ።
ጎረቤቶቹንም ጠራና ጉድጓዱን በአፈር መሙላት ጀመረ፡፡ አህያዋ ይህንን ስተመለከት እየቀበራት መሆኑን ተረዳችና እጅጉን አዘነች፡፡
ይሁን እንጂ አፈር በተደፋባት ቁጥር አህያዋ አንድ ነገር ታደርግ ነበር። አፈሩን እያራገፈች ከአፈሩ ውስጥ ብቅ ትል ነበር። በተደጋጋሚ ከዚያም በተደፋው አፈር ላይ መቆም ትጀምራለች። በሒደት ውስጥ በአፈሩ ላይ በቆመች ቁጥር ከነበረችበት ጉድጓድ ከፍ እያለች በመጨረሻም ከጉድጓዱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መውጣት ቻለች፡፡ በሚገርም ሁኔታ አህያዋን ሊቀብሯት የሞከሩት ስዎች ሁሉ በአህያዋ አወጣጥ በእጅጉ ተደነቁ፡፡
ውድ አንባቢያን እንደሚታወቀው የአህያዋ ታሪክ ሁላችንንም ይመለከተናል። የሚጫንብን አፈር ደግሞ በየጊዜው የሚያጋጥሙንና ዝም ብንላቸው በመጨረሻ ሊቀብሩን የሚችሉ ችግሮች ወይም መሠናክሎች ናቸው፡፡ አፈሩን የሚጭኑት ሰዎች በዙሪያችን ያሉ ሰዎች፣ ነገሮች፣ በህይወታችን ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩብን አዳዲስ ለውጦች እንዲሁም የራሳችን አፍራሽ ስሜቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ጉድጓዱ ደግሞ አሁን ያለንበት ግራ የተጋባንበት! ተስፋ ቢስ የሆንበት፡ መላ ያጣንበት ህይወት ወይም ገጠመኝ ሊሆን ይችላል፡፡
በእርግጥም እኛ ሰዎች በጤናችን! በኢኮኖሚ ህይወታችን፤ በትዳርና ፍቅር ህይወታችን በተለያየ አጋጣሚ ልክ እንደ አህያዋ ጉድጓድ ውስጥ የመግባት ዕድላችን ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ጠንካሮች እንደ ጠንካራዋ አህያ ከገቡበት ጉድጓድ ውስጥ መውጣት ሲችሉ አንዳንዶቹ በዚያው ተቀብረው ቀርተዋል፡፡
ውድ አንባቢያን በህይወታችን ውስጥ ያለው አማራጭ! ወደ ላይ መውጣት አልያም ደግሞ ወደ ታች ወርዶ ከጥልቅ ጉዳጓድ ውስጥ ተቀብሮ መቅረት ብቻ ነው! በየጊዜው ሊገጥመን የሚችለውን ችግር ልክ እንደ አህያዋ የሚጫንባትን አፈር እየረገጠች ወደ ላይ ከፍ እንዳለችው ሁሉ አንተም/አንቺም በየጊዜው የሚገጥማችሁን ችግሮች እንደ ድጋፍ እየተጠቀማችሁ በጥንካሬ ወደ ላይ መነሳት ያስፈልጋል፡፡ ከጥልቁ ጉድጓድ ውስጥ ለመውጣት የምንችለው ለመውጣት የምናደርገውን ጥረት ባለማቆም ብቻ ነው።
በመሆኑም ምንጊዜም በጠንካራ ውስጣዊ ቁርጠኝነትና እምነት ችግሮችን እንደ መወጣጫ ደረጃ በመጠቀም ከታች ወደ ላይ ተጓዙ ለማለት እወዳለሁ።
#share
Join: @Human_Intelligence
👍 80❤ 18😢 6👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#አደይ_አበባዋ_እና_ስስት
የአደይ አበባ እንደ ጉድ በተሰጣበት ሰፊ የአበባ ማሳ ላይ የበቀልኩ አንዲት ሚጢጢ እድለቢስ አደይ ነኝ" ስትል አሰበች የከፋት አበባ። "የቱንም ያህል የውበት ጌጥ ቢደፋብኝ፣ እንዴትም ሆኜ ባምር ብቆነጃጅ ከዚህ ሁሉ እልፍ ውበት መሀል የእኔን ነቁጥ ታህል ቁንጅና ልብ የሚል ከቶ ማንም የለም::"
ይህን ስትል አንድ መልዓክ ሰማት፡፡
ዝም አላለም፡፡
"ግን እኮ ቆንጅዬ ነሽ!"
"እሱማ አዎ፡፡ ግን እኔ የምሻው ከዚህም በላይ ነው፡፡ ብቸኛዋ ውብ አበባ መሆን እፈልጋለሁ:: አቻ ባይኖረኝ ደስ ይለኛል::"
ከዚህ በላይ ምሬቷን መስማት የተሳነው መልዓክ አፈፍ አድርጎ ተሸከማትና ወደ ከተማው ትልቁ አደባባይ ወሰዳት፡፡
ከጥቂት ቀናት በኋላ የከተማዋ ከንቲባ አትክልተኛውን አስከትለው ወደ አደባባዩ በመሄድ አንዳንድ ለውጦች ለማድረግ ወሰኑ
"እዚህ ምንም የሚረባ ነገር የለም:: ሁሉም ረብ የለሽ ጉድ ነው። ''ከንቲባው ለአትክልተኛው ትዕዛዝ ሰጡ:: "መሬቱን በሙሉ በደንብ አድርገህ ቆፍርልኝና ጠቃሚ ነገር ትከልበት፡፡''
''ቆይ! ቆይ! አንዴ ቆይ!" አደይ አበባዋ ተማጸነች፡፡ "እንደዚያ ካደረጋችሁ ትገድሉኛላችሁ! ጩኸቷን ሰምተው ከንቲባው ቆም አሉ። ቢሆንም እንዲህ መለሱላት-
"አንቺን የመሰሉ ሌሎችም በርካታ ውብ አደይ አበቦች ቢኖሩ ኖሮ ለአደባባያችን ጌጥ ትሆኑ ነበር፡፡ አንቺ ግን ብቻሽን ነሽ፡፡ ሌላ የአደይ አበባ ምንም የለም:: ብቻሽን ደግሞ የአትክልት ስፍራ ልትሆኚ አትችይም::"
ወዲያውም አበባዋን ከስሯ መንግለው ጣሏት::
ከፓውሎ ኮሆልዮ
❤ 28👍 22
የመኖር ጥበብ!!
💚የመኖርን ጥበብ በእጅጉ የሚሻ አንድ ሰው ወደ አንድ ታላቅ ጠቢብ ዘንድ ይሄዳል። ግራ መጋባት የሚታይበት ይህ ሰው ጠቢቡ ጋር እንደ ደረሰ የጥያቄ መዕት ያወርድበታል። ጠቢቡም ሰው ሁሉንም ጥያቄ በጥሞና ይሰማ ነበር። " የመኖርን ጥበብ አውቅ ዘንድ ካንተ ዘንድ መጣው። ቢቻልህስ ንገረኝ።" አለው።
💛ጠቢቡም ሰው እንዲ ሲል መለሰለት። "በ አንድ ወቅት ሰው ሁሉ የሚገረምበት አንድ ትልቅ ከመስታወት የተሰራ ትልቅ ቤት ነበር። ሁሉም ጥበብን የሚሻ የሚሄድበትና ጥበብን የሚማርበት። እናልህ ሁለት ሰዎች ይሄን ሰምተው ወደዛ ቤት ይሄዳሉ። ሁለቱም እጅግ የተለያዩ ናቸው። አንዱ ደስተኛ ተጫዋች ቅለል ያለ ህይወት የሚመራ ሲሆን ሁለተኛው በአንፃሩ ንዴታምና ብስጩ፥ ህይወትንም መክበድ የሌለባትን ያህል አክብዶ የሚያይ ነበር።
❤️ወደ መስታወት ቤት ሲደርሱ ደስተኛው ሰው ቀድሞ ገባ። ወደ ቤቱም ሲገባ በጣም ተማረከበት። ፊታቸው እጅግ የበራ፥ ህይወትን በእጅጉ የሚያጣጥሙ አይላፍ ህዝብ ተመለከተ። ከበፊቱም በላይ እጅግ ተደስቶም ከመስታዎት ቤቱ ወጣ። ውጪ ቆሞ ላለው ለሌለኛው ሰውም ያየውን ነገረው።
💚እጅግ ብስጪ ንዴታሙ ሰውም ወደ መስታዎት ቤቱ ገባ። ያጋጠመውም ነገር ከበፊቱ እጅግ የተለየ ነበር። አእላፍ ደስታ የራቃቸውንም ሰዎች ተመለከተ። ቤቱን ከመውደድ ይልቅ ጥላቻ ሞላበት። እጅግ በተበሳጨ ቁጥር ቤቱ ውስጥ ያሉትም አእላፍ ሰዎች ብስጭታቸው ይጨምር ነበር። እሱ የሚያደርገው እያንዳንዱን ነገር እነርሱ በእጥፍ ይመልሱለት ነበር።" አለ ጠቢቡ ሰው።
💛ቀጥሎም "አየህ ሁለቱ ሰዎች ያዩት ነገር ሌላ ነገር ሳይሆን የራሳቸውን ምስል ነው። መስታወቱ የራሳቸውን ምስል መልሶ እያሳያቸው ነበር። እዚም ምድር ላይ የተለየ የመኖር ጥበብ የለም። አንተ የሆንከውን አከባቢህ ይሆንልሀል። ደስታን ከሰጠኸው እጥፍ አርጎ ይመልስልሃል። ፍቅር ከሰጠኸው አትርፍርፎ ላንተም ይሰጥሀል። ጥበቃ ካረክለት እርሱም መልሶ ይንከባከብሃል። ደግ ስትሆንለት ደግነት ታገኛለህ።
❤️ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደሚባለው ሰው በ አሉታዊ ሀሳብ ተብትቦ ደግ ነገርን ከሰው ይጠብቃል። እየገደለ መኖርን ይፈልጋል። እያደማ መዳንን ይሽል። እየሱስ ይሄን ባንድ አርፍተ ነገር " የዘራኸውን ታጭዳለህ። " በማለት ገልፆታል። "ሊደረግልህ የምትፈልገውን አንተ ለሰው አድርግ ይላል።" ደግሞም እንዲህ ይባላል " አለም ላይ ማየት የምትፈልገውን ነገር አንተ ደግሞ እርሱን አርግ።"
💚አዎ ሰው ነገሮችን ሁለት ጎን እንዳላቸው ሳያቅ ይኖርና በመጨረሻም ይጎዳል። አሸናፊነትን እንጂ በሌላ ጎን ያለውን ሽንፈትን አይረዳውም። ህይወትና ሞት ፥ ደስታና ሀዘን ፤ መግደልና መሞት ፥ መውደድና ጥላቻ...... ወዘት የአንድ ነገር ሁለት ጎኖች ናቸው። አንዱን ብቻ ስንረዳ የእውነትን ግማሽ ተረዳን ማለት ነው። ሁለቱንም ስንረዳ ግን ሁሉም ይገባናል። ሀዘንን ለመሸሽ በሌሎች ሀዘንን አናመጣም። መውደድን ለማቆየት ሌሎችን አንጠላም።
💛ነገር ግን ተቃራኒ የሌለው አንድ ነገር አለ። እርሱም በ እ/ር ተመስሏል። ይህ ተቃራኒ የሌለው አቻም ያልተገኘለት ነገር ፍቅር ነው። ፍቅር ጊዜን ጠብቆ የማይከዳ የተፈጥሮ ሀብት ነው። ገፅ በረከት ስጣታም ነው። ፍቅር ስንሰጥ ሁሉንም በሁሉ ውስጥ እናገኛለን።
❤️ለዚህ የመኖር ጥበብ በጥቅሉ ያለ ቅድመ ሁኔታ ማፍቀር ነው። የሰው ልጅ ደጋግሞ ከመስማቱ ያልተገበረው ነገር ግን የሰለቸው ቃል። ሰው ተቃራኒ ያለውን ፍቅር ይዞ ይጎዳል። ፍቅር ይበለው እንጂ ይሄ በፍቅር ስም የሚነግድ ሌላ አይነት ስሜት ነው። ግዜን ጠብቆ ወደ ጥላቻ የሚሄድ ፍቅር ፍፁም ፍቅር አይባልም ። ፍፁሙን ፍቅር እሻ"!!!
#share
Join: @Human_Intelligence
👍 67❤ 16🙏 1
Repost from TgId: 1163708603
የጠፋውን የሰው ልጅ ፍለጋ (Search for the lost human soul)
ዘመኑ 1950ዎቹ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ... ከሁለቱ የዓለም ጦርነቶች ስካር የባነነው ዓለም ለሌላ ዓይነት ባርነት ራሱን ሲያዘጋጅ ተገኘ፡፡ ሥልጣኔውም አገዘው፡፡ የሥልጣኔ ቀዳሚው ተልዕኮ የሰውን ልጅ እንሰሳዊ ደመነፍስ ማላመድ (taming human animalistic aggresion) ቢመስልም ውጤቱ ግን የተገላቢጦሽ ሆነ፡፡ ለኤሮፓዊ ፋውስታዊ የዛገ መዳዳቱ ስምረት ቴከኖሎጂው ረዳት ሆነለት፡፡
ዘመኑ ሰው ወደ አሻንጉሊትነት የሚያደርገውን የመምዘግዘግ ጉዞ አሀዱ ያለበት ሆነ፡፡ በአዲሱ ፈጠራ ቴሌቪዥን በመታገዝ "ፖፕ ከልቸር" ሰለጠነ፡፡ ሁሉም አብረቅራቂው ዘመን አመጣሽ ሳጥን ጋር ፍቅር ወድቆ ለአዲሱ ጊዜ ባርነት ራሱን አዘጋጀ፡፡ ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ ቴክኖሎጂው በቀኝም በግራም እኩል ይመነደጋል፡፡ ቫይረሱ እና አንቲቫይረሱ፣ ሚሳኤሉና ጸረሚሳኤሉ እኩል ይበለጽጋሉ፡፡
ዛሬ ከሰባ ዓመታት በኋላ በዓለምአቀፍ ደረጃ ወደ ሁለት ቢሊዮን የሚጠጉ የቴሌቪዥኖች ዝግጅቶች ፣ ከ5 ቢሊዮን በላይ የሞባይል ስልኮች በሰው ልጆች እጆች ላይ ይገኛሉ። በአንጻሩ በሰው ልጆች የንባብ አትሮኖሶች ላይ እንደተዘረጉ የሚገመቱት መጻሕፍት ዓይነት ከ150 ሚሊዮን አይበልጥም፡፡
እነሆ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሞታችን ረክሶ ‹ላይቭ ስናየው ስንኳ ማስደንገጡ ቀንሷል፡፡ እንበላለን፤ ግን አናጣጥምም፡፡ እንዋሰባለን፤ ግን ፍቅርን ረስተናል፡፡ አብረን ሆነን ለብቻችንን ነን፡፡ አብረን እየኖረን አንዳችን ለሌላችን በዓድ፣ ሩቅ ነን፡፡ ወዳጅነት፣ ሣቅ፣ ፈገግታ፣ መታመን፣ ፍቅር፣ ፍትወት... ሸቀጥ ሆነው በገበያ ዋጋ ይቸበቸባሉ፡፡
ሰብዓዊት የማይቀለበስበት አስፈሪ ውጥንቅጥ ውስጥ ገብቷል፡፡ አንዳንዶች ይህ አረዳድ ጭፍንነት ሊመስላቸው ይችላል፡፡ አንዳንዶች ሀዘኑ ቤታቸው እስኪገባ ድረስ የመቃብር ደወሉ በየዕለቱ ለእነርሱ እንደሚደወል ይረሱታል፡፡
እናስ ኤሪክ ፍሮም እንዳስጠነቀቀው የሚቀጥለው ዘመን ሮቦቶች ለመሆን ምን ያክል ይቀረናል? በዚያ ዘመን (በ195oዎቹ አጋማሽ) የተነሱት እንደ ኤሪክ ፍሮም ዓይነት የሰው ልጅ ዕጣ ያስጨነቃቸው አሰላሳዮች ሰው ስለመዳረሻው እንዲጠነቀቅ አብዝተው ቢወተውቱም ሁሉም ከአጥበርባሪ ሳጥኗ ጋር ሲወዛወዝ ሰሚ አልነበራቸውም፡፡ ኤሪክ ፈሮም በ1955 እ.ኤአ በታተመ The Sane Society› በተሰኘ መጽሐፉ ላይ እንዲህ አለ፡፡
‹የ19ኛው ክፍለዘመን ጥያቄ፣ ትርክት ‹‹እግዚአብሔር ሞቷል›› ነበር፡፡ የሀያኛው ክፍለዘመን ፈተና ግን የሰው ልጅ ሞቷል› ሆነ፡፡ በ19ኛው ክፍለዘመን ኢ-ሰብዓዊነት ማለት ጭካኔ ነበር፡፡ በ20ኛው ክፍለዘመን ግን ኢሰብዓዊነት ማለት መደንዘዝ፣ ስሜት ማጣትና መነጠል ሆነ፡፡ የትናንት ስጋታችን የሰውን ልጅ ወደ ባርነት እንዳይገባ ነበር፡፡ የነገ ስጋታችን ግን የሰውን ልጅ ከሮቦትነት የመታደግ ሆኗል፡፡››
‹‹ሁላችንም በዘመናዊው የምዕራብ ዓለም የምንኖር ሰዎች እብደት ውስጥ ነን፡፡ ራሳችን እያታለልን ላለመሆናችን ምን ዋስትና አለን?››
ዓለም መልክ የሌለው መገማሸር ውስጥ ገብታለች፡፡ ልክ አንደ ሁልጊዜው!... በዚህ ሂደት ሰው የመሆናችን ቀለም አጥተናል፡፡ ሰው የመሆናችን ውሉ በምን ይረጋገጥ? ከቅድመ አያቶቻችን የሚያስተሳስረን ፈትለነገር ከተቋረጠ ሺህ ዘመናት አልፈዋል፡፡ በሕንጻ ሰንሰለቶች መካከል እየተመላለስን ስንኳ ሕልማችን የተራራ፣ የሸንተረር፣ የአደን፣ የለቀማ ነው፤ እንደ ግዞተኛ ነን፤ ፊሊፒናዊ፣ ቼካዊ፣ ቱርካዊ... መሆናችን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ፣ የቅዱስ ቁርዓን፣ ወይም የማናቸውም ቅኝት ሥሪት መሆናችን እውነታውን አይቀይረውም፡፡
እኔ ግን የዓይኑ ቀለም ያላማራቸውን በጅምላ ኮንነው ሰልፊ እየተነሱ ዘቅዝቀው የሚሰቅሉ ሕዝቦች ሀገር ዜጋ ነኝ፡፡ ያ ሁሉ የሺህ ዘመናት ወንጌል፣ ሥነምግባር፣ ሀፊዝ፣ ሥርዓት፣ ትምህርት፣ ግብረገብነት በቅፅበት ውኃ በልቶት መቅላት፣ እስከነፍስ ማቃጠል፣ መደፍጠጥ፣ ማሳደድ... ሁሉም በሚያስደነግጥ ፍጥነት ሲከናወን አቅመቢስ ስዱድ፣ ዲዳ ሆኘ ተመልከቻለሁ፡፡ ታምሜያለሁ፡፡ ብዙ ኢፍትሃዊነት ባለበት ምንም ማድረግ ካለመቻል በላይ የሚያም ምንስ ነገር ይኖራል?
ለነገሩ በየትኛውም የዓለም ክፍል በሰብዓዊነት፣ በአጠቃላይ በስነፍጥረት ላይ የሚቃጣ በደል ካላመመኝ የስካሩ አካል ሆኛለሁ ማለትም አይደል? አንዳንዶች ለዚህ መድኃኒቱ ዜግነትን ማስረጽ፣ ሕገመንግስት መቀየር... ዓይነት _ ጨዋ ሐሳቦችን ሲሰነዝሩ እሰማለሁ፡፡ ምንኛ የዋሆች ሆነዋል ጃል! የታመመው በአጠቃላይ የሰው ልጅ (ሰብዓዊነት) መሆኑን ማየትስ እንዴት ይሳናቸዋል? ይህ የሰብዓዊነት ማሽቆልቆል፣ ስርዓት በመቀየር፣ ደንደሳም ዴሞክራሲ በማስረጽ፣ በአዋጅ በማስነገር፣ ኢትዮጵያን እንደ አሜሪካ በማበልጸግ ብቻ ሊሻሻል አይችልም፡፡ እንዲውም ሁላችንም ከጫፍ እስከ ጫፍ እንደ ሰው ካላሰብን አንተርፍም፡፡
ዘመናዊው የሰው ልጅ ከቅድመ አያቶቻችን አንጻር የሁሉም ነገር ውስጥ መትረፍረፍ ውስጥ ነው፡፡ ዛሬ የአንድ አሜሪካዊ ቤተሰብ አማካይ የመገልገያ ቁሳቁሶች ብዛት እስከ 300,000 ይገመታል፡፡ ከመቶ ዓመታት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር 5000% እጥፍ ተመንድጓል፡፡ ዘመኑ በሁሉም ነገር የመትረፍረፍ (Abundance) ቅዠት ውስጥ የሚዳክር ይመስላል፡፡ ነገርግን መትረፍረፍ መቅሰፍት ሆኖብን ምኞታችን፣ እውነታችን፣ የሕይወት ትርጉማችን አሳክሮብናል፡፡ ምንም የማይፈይድልን የመረጃ ናዳ ያጥለቀልቀናል፡፡ በተሳከረ የመረጃ ቱማታ ተዋክበን እውነታችን ራሱ ዋጋ አጥቷል፡፡
ዘመኑ እንደየትኛውም ግልብ ዘመን ነበርና ኤሪክ ፍሮምና መሰሎቻቸው አድማጭ አላገኙም፡፡ እንደየትኛውም ዘመን... ዛሬ ለስሙ እንሰዋለን የሚሉ ቢሊዮናት ተከታዮች ያሉት መሲሁ በቁርጡ ቀን ከመስቀሉ ፊት ለፊት ለብቻው እንደነበረበት ዘመን፡፡ የሚያሳዝነው ዘመን ልብ መግዛት ሲጀምር ዕድሎች ቁጭት ሆነው ከተፍ ማለታቸው እኮ ነው፡፡
የሰው ልጅ የለየለት ዕብደት ውስጥ ገብቷል፡፡ ነጠል ብሎ ለሚታዘብ ተመልካች የሚታየው የሚሰማው ሁሉ አጃኢብ ነው፡፡ ሥልጣኔው ሁሉ በየዕለቱ የሚያስመዘግበው መካን፣ መራቀቅ የአውዳሚነት መሆኑ ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ ከጦር መሣሪያ ጋር ያልተነካካው ቴክኖሎጂያዊ ፈጠራ ስንኳ በየዕለቱ ሰብዓዊነትን የሚያኮሰምን የመሆኑ ነገር ያስደነግጣል፡፡
ተመራማሪዎች በቅርቡ ሰው በማይደርስባቸው አስፈሪ የአርክቲክ አካባቢዎች ሳይቀር ብዙ ሺህ ቶን የሚመዝን የማይበሰብስ ቆሻሻ አግኝተዋል፡፡ የሰው ልጅ አሁን በተያያዘው ግዴለሽ ጎዳና ከቀጠለ ሩቅ በማይባል ዘመን ሕይወት ከውቅያኖሶችና ባህራት ተጠቃልሎ ሊጠፋ ይችላል፡፡
በፍም እሳት መቃመስ
ያዕቆብ ብርሀኑ
ይቀጥላል
@Zephilosophy
👍 66
❤ቢታነፅ ቢወቀር!
(በእውቀቱ ስዩም)
እኔም አንድ ሰሞን
ልክ እንደ ሰለሞን
"ሁሉም ከንቱ ከንቱ ንፋስን መከተል
ላይጥሉ መታገል: ላይከብሩ መባተል"
እያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ: እፈላሰፍ ነበር!
ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጓሮ በር በኩል: ሰለሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ንፋስ አሳድጄ እንደ ቆቅ አጠመድሁ
ከፀሀይዋ በታች: ግልገል ፀሀይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ: ብርሀን አበደርሁ
ማቅ የነበረው ጨርቅ: ሸማ ሆኖ ቆየኝ
"ከንቱ የነበረው: "አንቱ" ሆኖ ታየኝ!
ለካስ...
ጠቢብ ቢያስተምረው
መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ: ቢታነፅ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም: ካልወደደ በቀር!
#share
Join: @Human_Intelligence
❤ 46👍 34🥰 4
