TIKVAH-MAGAZINE
Ir al canal en Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524
Mostrar más2025 año en números

194 405
Suscriptores
-5824 horas
-1527 días
-79430 días
Archivo de publicaciones
Photo unavailableShow in Telegram
#Update
የአፍሪካ ልማት ባንክና ኢትዮጵያ የ184 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ተፈራረሙ።
ስምምነቱ ኢትዮጵያን፣ ጁቡቲንና ደቡብ ሱዳንን የሚያስተሳስረው መንገድ ፕሮጀክትን ለመገንባት የተፈፀመ ነው።
ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴና የባንኩ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር አሌክስ ሙቢሩ ፈርመዋል።
ከአፍሪካ ልማት ባንክ የተገኘው ገንዘብ የአዲስ አበባ ጂቡቲ ኮሪደር አካል የሆነውን የመልካ ጂሎ- አዋሽ የ67 ኪሎሜትር የፈጣን መንገድ ለመስራት ይውላል።
ይህ መንገድ የአዳማ- አዋሽ የፈጣን መንገድ የሁለተኛ ዙር አካል ሲሆን 90% የባህር ንግዷን በጂቡቲ በኩል ለምታደርገው ኢትዮጵያ ቁልፍ መስመር ነው።
በተጨማሪ ሶስቱን ሃገራት የሚያስተሳስረው ኮሪደርም አካል ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 20👍 7👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
📱ብድር ለመውሰድ ቀላል መንገድ ይፈልጋሉ?
Digaf MFI ብለው ከፕላይ ስቶር /playstore/ በማውረድ ብድር ማመልከት ይችላሉ፡፡
በስልክዎ ብቻ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ይመዝገቡ እና የብድር ሂደትዎን ቀላል አድርጉ!
👉 አሁን ይዉሰዱ | ቀላል | ፈጣን | ተደራሽ
📥 መተግበሪያውን አሁን ይጫኑ እና ብድር ሂደትዎን ቀላል አድርጉ!
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.digaf.digafselfapp
ለበለጠ መረጃ ደሞ 6575 ላይ ይደውሉ!
ድጋፍ አነስተኛ ብድር አቅራቢ አ/ማ
👍 9❤ 7
Photo unavailableShow in Telegram
አባይ ሆምስ
ስመ ጥሩ እና ገናናው አባይ ቴክ ለረጅም ዓመታት የመኪና መገጣጠሚያ እንዲሁም ሌግዠሪ ዶፕሌክስ ቤቶችን በ ፍላሚንጎ ሰርቶ እንዳስረከበ ይታወቃል አሁን ደግሞ በመሃል ሜክሲኮ አፓርትመንት እና የንግድ ሱቅዎችን ለሽያጭ አውጥተናል።
ለመኖሪያ አልያም አትርፈው ለመሸጥ የሚመርጡት
👉 የሳይት አድራሻ :- በመሃል ሜክሲኮ አፍሪካ ህብረት አጠገብ
👉 ቅድመ ክፍያ 10%
👉 ባለ 1 መኝታ
👉 ባለ 2 መኝታ
👉 ባለ 3 መኝታ
👉 እንዲሁም የንግድ ሱቆች በ10, 14, 33.6, 50.4 ካሬ ጀምሮ
በተጨማሪም እንደ አከፋፈሎ ከ 10-20 % ቅናሽ ይደረግሎታል
📍ሜክሲኮ
ለበለጠ መረጃ በ 09-38-95-23-23
❤ 13👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የሶማሊያ የአደጋ ኤጀንሲ የሃገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ክምችት ውስጥ ምንም ምግብ እንደሌለ አስታወቀ።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር መሃሙድ አብዱሌ የሶማሊያ መንግስት ህዝቡን መርዳት የማይችልበት ደረጃ መድረሱን ገልፀው "ሶማሊዎች ሊረዳቸው የሚችለው አላህ ብቻ ነው" ብለዋል።
ዳይሬክተሩ የሃይማኖት አባቶች ድጋፍ እንዲደረግ ማህበረሰቡን እንዲያሰባስቡ ጠይቀዋል።
ቻይና በዚህ ሳምንት ሶማሊያ ድርቅን እንድትቋቋም የ1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ የሰጠች ሲሆን በርካታ ሃገራትም ድጋፍ እያደረጉ ነው።
የአለም አቀፍ እርዳታ ባለበት ሁኔታ የምግብ ክምችት አለመኖሩ ወትሮውንም በሶማሊያ በሙስና እና በጎሳ ይሰራል ተብሎ በሚታማው ኤጀንሲ ላይ ጥያቄ ፈጥሯል።
ዘገባው የሶማሊ ጋርዲያን ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
😢 58❤ 30👍 6🙏 6👎 2🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
Lafto Partners is looking to hire a Senior Creative English Writer.
Job Description
We are seeking an exceptional English Writer & Editor with a passion for reading, storytelling, and deep engagement with both Ethiopian and global contexts.
We’re looking for a professional who thinks critically, writes creatively, and brings stories to life with clarity and insight.
Key Responsibilities
- Write and edit high-quality stories, articles, and digital content.
- Develop creative concepts and proposals for communication and media projects.
-Collaborate with creative teams to deliver authentic, impactful narratives.
**Requirements*"
-Proven professional experience in writing, editing, communications, or journalism.
-Exceptional command of English with advanced writing and editing skills.
-Deep curiosity, extensive reading habit, and strong understanding of Ethiopian society and global issues.
-Excellent organizational and interpersonal skills.
-Knowledge of additional Ethiopian languages is an added advantage.
About the job
-Full time engagement
- Location: Addis Ababa - Megenagna
- Net Salary 30-40k
How to Apply
Send your CV, cover letter, and two or more writing samples to info@lafto.partners
Email Subject: Editor Job – [Your First Name]
@TikvahethMagazine
❤ 21🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
"ጊፋታ" በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት ተመዘገበ።
ጊፋታ የወላይታ ህዝብ የአዲስ ዓመት ፌስቲቫል በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት በተባበሩት መንግስታት ትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት(ዩኔስኮ) መመዝገቡ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን እንዳስታወቀው "ጊፋታ" በህንድ፣ በኒው ዴሊ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 2ዐኛው የኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርስ ጥበቃ የመንግስታት ኮሚቴ ስብሰባ ነው በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት መመዝገቡ የተገለጸው።
ጊፋታ ዩኔስኮ ቅርስን በሰው ልጆች ወካይ ኢንታንጀብል ቅርስነት ለመመዝገብ ያስቀመጣቸውን አምስት መመዘኛዎች አሟልቶ ተገኝቷል ተብሏል።
- በዓሉ እድሜ፣ ፆታ፣ ሀይማኖትና ማህበራዊ ደረጃን ሳይለይ የሚያሳትፍ መሆኑ፣
- የቅርሱ ተስተላልፎ ጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ
፤ በትምህርት ቤቶችና በሚዲያዎች ለትውልድ በመሸጋገር ላይ የሚገኝ መሆኑ፤
- በዓሉ ሰላምን፣ አንድነትን እና አብሮነትን የሚያበረታታ መሆኑ፣
- ለዘላቂ ልማት፣ የምግብ ዋስትናን ከፍ በማድረግና አካባቢን ከመጠበቅ አንፃር ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ መሆኑ፤
- ኖሚኔሽን ፋይሉ በቅርሱ ባለቤቶች ነፃና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ተሳትፎ የተከናወነ መሆኑ እና
- ቅርሱ በሀገሪቱ ብሔራዊ ምዝገባ ውስጥ የተካተተ መሆኑ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
😀 | @tikvahethmagazine
👍 63❤ 56🤔 2🕊 2👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
🔥በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ
🎄🎄መጪውን በአል ምክንያት በማድረግ 30% የነበረው ቅናሽ ለውስን ቤቶች ብቻ 🎄35% የተደረገ ሲሆን እርሶም ይሄን ቅናሽ በመጠቀም መሀል ፒያሳ ላይ የቤት ባለቤት የመሆን ሀሳብ ካሎት ፈጥነው ይመዝገቡ🎄🎄
🏡ባለ ሁለት እና ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ
ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት
💎ባለ 2 መኝታ በ 840,000 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 1,207,500 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ
🔥እንዲሁም የቤቱን 65% ሲከፍሉ 35% በድርጅቱ የሚሸፈን ይሆናል (35% ቅናሽ)
💎 ባለ ሁለት መኝታ ሙሉ ክፍያ 5,460,000 ብር ሙሉ ክፍያ
💎 ባለ ሶስት መኝታ ሙሉ ክፍያ 7,848,750 ብር ሙሉ ክፍያ
- በግንባታ ላይ የሚገኙ
ይደውሉልን፤ የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelMERITRealtor)
❤ 25
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ በአማካይ በአየር ትራንስፖርት መንገደኛ ላይ የምትጥለው ታክስ 0.03 ዶላር ብቻ ነው።
የአየር ትራንስፖርት መንገደኞች በ2024 ብቻ ከ60 ቢሊየን ዶላር በላይ ታክስ ከፍለዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር ያለው የአለም አቀፉ የሲቪል አቪየሽን ተቋም(ICAO) በ2024 በአየር ትራንስፖርት ከሚጓዙ መንገደኞች በትኬታቸው ላይ ተጨምሮ ከሚከፍሉት ታክስ ተሰበሰበ ያለውን የገንዘብ መጠን ይፋ አድርጓል።
በአየር ትራንስፖርት ትኬት ላይ ለአየር መንገዱ ከሚከፈለው ክፍያ በተጨማሪ የተለያየ አይነት ታክስና ክፍያ የሚጨመር ሲሆን በአንድ የጉዞ ትኬት ላይ የሚጣል ታክስና ክፍያ ከጥቂት ዶላሮች ተነስቶ እስከ 200 ዶላር ይደርሳል።
በመንገደኞች ላይ በዚህ መልኩ ከተጣለ ታክስም በአለም አቀፍ ደረጃ 60.4 ቢሊየን ዶላር መሰብሰቡን ተቋሙ ይፋ ሲያደርግ በአንድ የጉዞ ትኬት ላይ በአማካይ 12.6 ዶላር ይጣላል።
በ2024 የአየር ትራንስፖርት ዘርፉ 32.4 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ትርፍ ያገኘ ሲሆን ይህም በመንገደኞች ላይ ተጥሎ ከተገኘው ገቢ በግማሽ ያነሰ ነው።
እነዚህ ተጨማሪ ታክሶች ከሃገር ውስጥ በረራ አንፃር በአለም አቀፍ በረራዎች በ108% ሲጨምሩ በአለም አቀፍ በረራ የተጣሉ ታክሶች ገቢ ከአጠቃላዩ ገቢ 38 ቢሊየን ዶላሩን ይይዛል።
በአህጉር ደረጃ ሰሜን አሜሪካ ከተጣሉ ታክሶች 34.1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ያገኘች ሲሆን ይህም በአለም አቀፍ ደረጃ ከተገኘው ገቢ 57% ይሸፍናል።
አህጉራችን አፍሪካ በዚህ አይነት መልኩ ከተጣሉ ታክሶች 2 ቢሊየን ዶላር ስታገኝ ከጠቅላላው 3% ብቻ ነው።
አርጀንቲና ከፍተኛ ታክስ የምትጥል ሃገር ስትባል ከሃገሯ በሚወጡ መንገደኞች ላይ በአንድ በረራ በአማካይ 138 ዶላር ትጥላለች።
በአፍሪካ ግብፅ በ2024 ከመንገደኞች ታክስ 689 ሚሊየን ዶላር በማግኘት ቀዳሚ ስትሆን በመንገደኛ በአማካይ 28.3 ዶላር ታስከፍላለች። ግብፅ ከመንግስት በጀቷ አንፃርም የሰበሰበችው ታክስ 1.1% ነው።
ሞሪሺየስ በአማካይ በመንገደኛ 63.8 ዶላር ታክስ በአማካይ በማስከፈል በአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን ከመንግስት በጀት አንፃርም 3.6% ነው።
ኢትዮጵያ በዚህ አይነት ታክስ በ2024 የሰበሰበችው 300,000 ዶላር ብቻ ሲሆን በአማካይ በመንገደኛ 0.03 ዶላር በማስከፈል ከኮሎምቢያ በመቀጠል ዝቅተኛውን ታክስ በአማካይ ታስከፍላለች።
ሙሉ ሪፖርቱን ከዚህ ማግኘት ትችላላችሁ ።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 95👍 29🤔 12👎 7🤣 6🔥 1🙏 1🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
አባይ ሆምስ
ስመ ጥሩ እና ገናናው አባይ ቴክ ለረጅም ዓመታት የመኪና መገጣጠሚያ እንዲሁም ሌግዠሪ ዶፕሌክስ ቤቶችን በ ፍላሚንጎ ሰርቶ እንዳስረከበ ይታወቃል አሁን ደግሞ በመሃል ሜክሲኮ አፓርትመንት እና የንግድ ሱቅዎችን ለሽያጭ አውጥተናል።
ለመኖሪያ አልያም አትርፈው ለመሸጥ የሚመርጡት
👉 የሳይት አድራሻ :- በመሃል ሜክሲኮ አፍሪካ ህብረት አጠገብ
👉 ቅድመ ክፍያ 10%
👉 ባለ 1 መኝታ
👉 ባለ 2 መኝታ
👉 ባለ 3 መኝታ
👉 እንዲሁም የንግድ ሱቆች በ10, 14, 33.6, 50.4 ካሬ ጀምሮ
በተጨማሪም እንደ አከፋፈሎ ከ 10-20 % ቅናሽ ይደረግሎታል
📍ሜክሲኮ
ለበለጠ መረጃ በ 09-38-95-23-23
❤ 16
Photo unavailableShow in Telegram
#update
አለም አቀፉ የጦር ወንጀሎች ፍርድ ቤት በዳርፉር በነበረው ጥሰት በተሳተፉት አሊ መሃመድ አብድአልራህማን ላይ የ20 አመት እስር ወሰነ።
አሊ ኩሻይብ በሚል ቅፅል ስም የሚታወቀውና ከ20 አመታት በፊት በዳርፉር ጭፍጨፋ ወቅት ጃንጃዊድ የተባለው ታጣቂ መሪ የነበረው ግለሰብ ባለፈው ጥቅምት በፈፀማቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ መባሉ ይታወሳል።
ኩሻይብ በግድያ፣ በአስገድዶ መድፈር፣ ህዝብን በአስገዳጅ መልኩ ከቦታው ማዘዋወር እና ንፁሃንን ማጥቃትን ጨምሮ በ31 ክሶች ጥፋተኛ ተብሏል።
መርማሪዎች የአለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በወንጀለኛው ላይ የእድሜ ልክ እስራት ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ የ20 አመት እስር ወስኗል።
ግለሰቡ በተደጋሚ አሊ ኩሻይብ እኔ አይደለሁም ብሎ መካዱ ሲታወስ ጠበቆቹ የ7 አመት እስር ብቻ እንዲፈረድበት ጠይቀው ነበር።
ከ2003-2004 በነበረው የዳርፉር ጭፍጨፋ ከ300,000 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከ2.5 ሚሊየን በላይ ሰዎችም ተፈናቅለዋል።
የአለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በዳርፉር ጉዳይ የተሰጠ የመጀመሪያው ውሳኔም ሆኗል።
በ2020 ለአለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት የመንግስት አካላት ይገድሉኛል በሚል ራሱን አሳልፎ የሰጠው አሊ ኩሻይብ ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በእስር ቤት ያሳለፈው ጊዜ ከውሳኔው ላይ ይቀነስለታል።
ዘገባው የአልጄዚራ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 43👎 6👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
#Sudan
የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ደቡብ ሱዳን ነዳጅ የምትልክበትን ዋነኛ የነዳጅ መስመር መያዙን አስታወቀ።
ደቡብ ሱዳን የምታመርተውን ነዳጅ በሱዳን በኩል ለአለም ገበያ ስታቀርብ ዋነኘው መስመር ሄግሊግ ሲሆን ይህንን መስመር የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መቆጣጠሩንና ደህንነቱን እንደሚጠብቅ ገልጿል።
ሰራተኞች ቦታውን ለቀው መውጣታቸውና ስራም መቆሙ ሲዘገብ የደቡብ ሱዳን ዋነኛ የገቢ ምንጭ የሆነውን የነዳጅ ምርት የመላክ ስራ ላይ ስጋት ፈጥሯል።
ሄግሊግ በሁለቱ ሃገራት ድንበር አቅራቢያ ሲገኝ ወሳኝ የነዳጅ መሸጋገሪያም ነው።
ባለፉት 3 ወራት ደቡብ ሱዳን በጎረቤቷ ሱዳን በኩል 165,000 በርሜል ነዳጅ በቀን ለአለም ገበያ እያቀረበች ነበር።
ዘገባው የብሉምበርግ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 57👍 8😢 5
Photo unavailableShow in Telegram
#Update
በናይጄሪያ ታግተው ከተወሰዱ ተማሪዎች መካከል 100 ያህሉ ተለቀቁ።
ከሳምንታት በፊት በናይጀሪያ ከሚገኝ ትምህርት ቤት 303 ተማሪዎችና 12 መምህራን ታግተው መወሰዳቸው ሲታወስ 100 ህፃናቱ ተለቀው ወደ ዋና ከተማዋ አቡጃ መድረሳቸው ተዘግቧል።
በወቅቱ ከታገቱ ተማሪዎች ውስጥ 50 ያህሉ ከአጋቾች ማምለጣቸው ሲታወስ በአሁኑ ጊዜ በአጋቾች የታገቱት 153 ተማሪዎችና 12 መምህራን ናቸው።
የተለቀቁ ህፃናት የህክምና ክትትል የተደረገላቸው ሲሆን በቀጣይ ቤተሰቦቻቸውን ይቀላቀላሉ።
ከ2014 ወዲህ በናይጄሪያ በአጠቃላይ ከ1400 በላይ ተማሪዎች መታገታቸው ተዘግቧል።
ዘገባው የአልጄዚራ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 29🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
#Update
በናይጄሪያ ታግተው ከተወሰዱ ተማሪዎች መካከል 100 ያህሉ ተለቀቁ።
ከሳምንታት በፊት በናይጀሪያ ከሚገኝ ትምህርት ቤት 303 ተማሪዎችና 12 መምህራን ታግተው መወሰዳቸው ሲታወስ 100 ህፃናቱ ተለቀው ወደ ዋና ከተማዋ አቡጃ መድረሳቸው ተዘግቧል።
በወቅቱ ከታገቱ ተማሪዎች ውስጥ 50 ያህሉ ከአጋቾች ማምለጣቸው ሲታወስ በአሁኑ ጊዜ በአጋቾች የታገቱት 153 ተማሪዎችና 12 መምህራን ናቸው።
የተለቀቁ ህፃናት የህክምና ክትትል የተደረገላቸው ሲሆን በቀጣይ ቤተሰቦቻቸውን ይቀላቀላሉ።
ከ2014 ወዲህ በናይጄሪያ በአጠቃላይ ከ1400 በላይ ተማሪዎች መታገታቸው ተዘግቧል።
ዘገባው የአልጄዚራ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
Photo unavailableShow in Telegram
🔥በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ
🎄🎄መጪውን በአል ምክንያት በማድረግ 30% የነበረው ቅናሽ ለውስን ቤቶች ብቻ 🎄35% የተደረገ ሲሆን እርሶም ይሄን ቅናሽ በመጠቀም መሀል ፒያሳ ላይ የቤት ባለቤት የመሆን ሀሳብ ካሎት ፈጥነው ይመዝገቡ🎄🎄
🏡ባለ ሁለት እና ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ
ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት
💎ባለ 2 መኝታ በ 840,000 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 1,207,500 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ
🔥እንዲሁም የቤቱን 65% ሲከፍሉ 35% በድርጅቱ የሚሸፈን ይሆናል (35% ቅናሽ)
💎 ባለ ሁለት መኝታ ሙሉ ክፍያ 5,460,000 ብር ሙሉ ክፍያ
💎 ባለ ሶስት መኝታ ሙሉ ክፍያ 7,848,750 ብር ሙሉ ክፍያ
- በግንባታ ላይ የሚገኙ
ይደውሉልን፤ የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelMERITRealtor)
❤ 12👍 1👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
#Sudan
በሱዳን ደቡብ ኮርዶፋን ግዛት በተፈፀመ የአየር ጥቃት 63 ሕፃናትን ጨምሮ 114 ሰዎች ሞተዋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
ባለፈው ሳምንት በተፈጸመው በዚህ የድሮን ጥቃት ቢያንስ ሶስት ጊዜ በመዋዕለ ሕፃናት እና በአቅራቢያው ባለው የገጠር ሆስፒታል ላይ ጉዳት ማድረሱ ነው የተገለጸው።
የሱዳን ዶክተርስ ኔትወርክ እና የአደጋ ጊዜ ጠበቆች፣ በሱዳን በሲቪሎች ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት የሚከታተሉ ቡድኖች፣ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን (RSF) ተጠያቂ አድርገዋል።
😀 | @tikvahethmagazine
😢 86❤ 22💔 11👍 6🕊 6👎 4🤯 2🤬 2
Photo unavailableShow in Telegram
ቲክቶክ በናይጄሪያ የምሽት የቀጥታ ስርጭቶች እንዳይደረጉ አገደ።
የቻይናው የማህበራዊ ሚዲያ ተቋም ቲክቶክ በናይጄሪያ በምሽት የሚደረጉ የቀጥታ ስርጭቶችን በጊዜያዊነት ማገዱን ገልጿል።
ቲክቶክ በናይጀሪያ ከምሽቱ 5 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት የሚደረጉ የቀጥታ ስርጭቶችን ማቆሙን ይፋ ያደረገው ወሲባዊ ይዘት ያላቸው ስርጭቶች መብዛታቸውን ተከትሎ ነው።
ይህ የወሲብ ይዘት በብዛት ይሰራጭበታል በተባለው በዚህ ሰዓትም በናይጄሪያ የቀጥታ ስርጭቶችን ማሰናዳት ወይም መመልከት አይቻልም።
"የይዘት ደህንነትና ተጠቃሚዎቼን እጠብቃለሁ" ያለው ቲክቶክ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ምክንያት ከ49,000 በላይ የቀጥታ ውይይቶችን ከናይጄሪያ አጥፍቷል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቲክቶክ እውቅና እና ትኩረት ለማግኘት በሚል ወሲባዊ ይዘት ያላቸውን ነገሮች ማሰራጨት እየተለመደ ሲሆን ቲክቶክ በተደጋጋሚ ቁጥጥር እንዲያደርግ በተለያዩ አካላት ሲጠየቅ ቆይቷል።
ቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት እገዳው ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ያሳወቀው ነገር የለም።
መረጃው የDW ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 115👏 45👍 18🤣 11
"ህብረተሰቡ መመዝገብ ሲገባቸው ያልተመዘገቡ አክስዮኖችን እንዳይገበያይ" - የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን
አስቀድመው በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ባለቤቶች የተያዙ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን የማስመዝገቢያ ቀነ ገደቡም ህዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡
አክስዮኖቻቸውን ያላስመዘገቡ አክስዮን ማኅበራት ምንም አይነት አዲስም ሆነ ነባር አክስዮን ሽያጭ እና ግብይት ጋር የተያያዘ እንቅስቃሴ እንዳያከናውኑና እና አክስዮን የሚያገበያዩ ቢሮዎች ያሏቸው ኩባንያዎችም የማገበያየት ስራ እንዲያቆሙ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስጠንቅቋል።
ይህንን በማያደርጉ አክስዮን ማኅበራት ላይ ሽያጭ መሰረዝ እና ገንዘብ ቅጣት፤ ከዚህም ባለፈ የሥራ ሃላፊዎችን እና የቦርድ አባላትን እስከማገድ፤ በጥቁር መዝገብ እንዲሰፍሩ እስከማድረግ የሚደርስ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል። የህግ ተጠያቂነትም ያስከትላል ተብሏል።
ከዚህ በኋላ ያልተመዘገቡ ሰነደ ሙአለ ንዋዮችን ለግብይት ማቅረብ እና መገበያየት በካፒታል ገበያ አዋጁ ከ7 እስከ 15 አመት ጽኑ እስራት እንዲሁም ከ150,000 እስከ 300,000 በሚደርስ መቀጮ ያስቀጣል ሲል አስታውቋል።
ህብረተሰቡ መመዝገብ ሲገባቸው ያልተመዘገቡ አክስዮኖችን እንዳይገበያይ እና አክስዮኖችን ከመገበያየቱ በፊት መመዝገባቸውን አሊያም ከምዝገባ ነጻ የተደረጉ መሆናቸውን እንዲያረጋግጥ አሳስቧል።
አክሎም፥ በባለስልጣኑ ፈቃድ ባልተሰጣቸው ደላሎች እና አሻሻጭች አማካኝነት እና ፈቃድ ከተሰጠው ሰነደ ሙአለ ንዋይ ገበያ ወይም ያልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያ ውጭ አክስዮኖችን እንዳይገበያይም ነው አጥብቆ የገለጸው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 63👍 7😢 1🙏 1
"ህብረተሰቡ መመዝገብ ሲገባቸው ያልተመዘገቡ አክስዮኖችን እንዳይገበያይ" - የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን
አክስዮኖቻቸውን ያላስመዘገቡ አክስዮን ማኅበራት ምንም አይነት አዲስም ሆነ ነባር አክስዮን ሽያጭ እና ግብይት ጋር የተያያዘ እንቅስቃሴ እንዳያከናውኑና እና አክስዮን የሚያገበያዩ ቢሮዎች ያሏቸው ኩባንያዎችም የማገበያየት ስራ እንዲያቆሙ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስጠንቅቋል።
ይህንን በማያደርጉ አክስዮን ማኅበራት ላይ ሽያጭ መሰረዝ እና ገንዘብ ቅጣት፤ ከዚህም ባለፈ የሥራ ሃላፊዎችን እና የቦርድ አባላትን እስከማገድ፤ በጥቁር መዝገብ እንዲሰፍሩ እስከማድረግ የሚደርስ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል። የህግ ተጠያቂነትም ያስከትላል ተብሏል።
ከዚህ በኋላ ያልተመዘገቡ ሰነደ ሙአለ ንዋዮችን ለግብይት ማቅረብ እና መገበያየት በካፒታል ገበያ አዋጁ ከ7 እስከ 15 አመት ጽኑ እስራት እንዲሁም ከ150,000 እስከ 300,000 በሚደርስ መቀጮ ያስቀጣል ሲል አስታውቋል።
ህብረተሰቡ መመዝገብ ሲገባቸው ያልተመዘገቡ አክስዮኖችን እንዳይገበያይ እና አክስዮኖችን ከመገበያየቱ በፊት መመዝገባቸውን አሊያም ከምዝገባ ነጻ የተደረጉ መሆናቸውን እንዲያረጋግጥ አሳስቧል።
አክሎም፥ በባለስልጣኑ ፈቃድ ባልተሰጣቸው ደላሎች እና አሻሻጭች አማካኝነት እና ፈቃድ ከተሰጠው ሰነደ ሙአለ ንዋይ ገበያ ወይም ያልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያ ውጭ አክስዮኖችን እንዳይገበያይም ነው አጥብቆ የገለጸው።
😀 | @tikvahethmagazine
Photo unavailableShow in Telegram
ስዊድን ለዩክሬን ድጋፍ ለመስጠት ስትል ለ5 ሃገራት የምትሰጠውን ድጋፍ ልታቋርጥ ነው።
ስዊድን ለዩክሬን የምትሰጠውን ድጋፍ ለመጨመር ለዚምባቡዌ፣ ታንዛኒያ፣ ሞዛምቢክ፣ ላይቤሪያና ቦሊቪያ የምትሰጠውን ድጋፍ በሚቀጥሉት አመታት እንደምታቆም አስታውቃለች።
ስዊድን ዩክሬን በጣም አስፈላጊዋ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲዋና ቀዳሚ የእርዳታ ፖሊሲዬ ነች ስትል ለዩክሬን የምትሰጠውን እርዳታም በ2026 ወደ 10 ቢሊየን ክራውንስ ወይም 1.06 ቢሊየን ዶላር እንደምታደርስ ገልፃለች።
ስዊድን ከአምስቱ ሃገራት እርዳታ ማቆሟ በሚቀጥሉት 2 አመታት 2 ቢሊየን ክራውንስ ያድናል ብላ ይኸው ገንዘብ ወደ ዩክሬን እንደሚላክ አስታውቃለች።
ስዊድን ባለፉት 3 አመታት በአመት 56 ቢሊየን ክራውንስ በመመደብ እርዳታ ስትሰጥ የቆየች ሲሆን በሚቀጥሉት ሁለት አመታት ይህንን መጠን ወደ 53 ቢሊየን ክራውንስ ዝቅ ለማድረግ ስታቅድ የተወሰነውን ገንዘብ ለኢምግሬሽን ወጪና ስደተኞችን ከሃገሯ ለማባረር እንደምትጠቀም ገልፃለች።
በስዊድን በ2022 አዲስ መንግስት ከመጣ ወዲህ ለ10 ሃገራት የሚሰጠውን ድጋፍ አቋርጧል።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
👎 61❤ 40👍 6🤣 5🤬 2
Photo unavailableShow in Telegram
🔥በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ
🎄🎄መጪውን በአል ምክንያት በማድረግ 30% የነበረው ቅናሽ ለውስን ቤቶች ብቻ 🎄35% የተደረገ ሲሆን እርሶም ይሄን ቅናሽ በመጠቀም መሀል ፒያሳ ላይ የቤት ባለቤት የመሆን ሀሳብ ካሎት ፈጥነው ይመዝገቡ🎄🎄
🏡ባለ ሁለት እና ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ
ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት
💎ባለ 2 መኝታ በ 840,000 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 1,207,500 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ
🔥እንዲሁም የቤቱን 65% ሲከፍሉ 35% በድርጅቱ የሚሸፈን ይሆናል (35% ቅናሽ)
💎 ባለ ሁለት መኝታ ሙሉ ክፍያ 5,460,000 ብር ሙሉ ክፍያ
💎 ባለ ሶስት መኝታ ሙሉ ክፍያ 7,848,750 ብር ሙሉ ክፍያ
- በግንባታ ላይ የሚገኙ
ይደውሉልን፤ የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelMERITRealtor)
❤ 14🤔 1
