አዲስ ነገር መረጃ
Ir al canal en Telegram
#አዲስ_ነገር_መረጃ #መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ Addis Ababa , Ethiopia Buy Ads : https://telega.io/?r=UbutLo2z #ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot
Mostrar más2025 año en números

103 347
Suscriptores
-9224 horas
-3717 días
+21730 días
Archivo de publicaciones
Photo unavailableShow in Telegram
የትራምፕ አስተዳደር አንጋፋ ዲፕሎማቶችን ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ አዘዘ
የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በዓለም ዙሪያ በተለያዩ ሀገራት በአምባሳደርነትና በከፍተኛ የዲፕሎማሲ እርከን ላይ የሚገኙ 30 የሚጠጉ አንጋፋ ዲፕሎማቶችን በአስቸኳይ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።
ከእነዚህ ዲፕሎማቶች መካከል ግማሽ ያህሉ (15ቱ) በአፍሪካ ሀገራት ተመድበው የሚሰሩ መሆናቸው ውሳኔው በአህጉሪቱ ላይ ያለውን ትኩረት አጉልቶታል።
የውሳኔው ዓላማ የፕሬዝዳንት ትራምፕን "አሜሪካ ትቅደም" (America First) ፖሊሲ በተግባር ለመተርጎም የታለመ ሲሆን፤ ነባር ዲፕሎማቶችን በአዲስና ከአስተዳደሩ ርዕዮተ ዓለም ጋር በሚጣጣሙ ግለሰቦች ለመተካት የታቀደ ነው።
አስተዳደሩ የሀገሪቱን የውጭ ጉዳይ ተልዕኮ በአዲስ መልክ ለመቅረጽ መወሰኑን ገልጿል።
ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ የተጠሩት ባለሙያዎች በዘርፉ ለረጅም ዓመታት ያገለገሉና ሰፊ ልምድ ያላቸው መሆናቸው ይታወቃል።
ይህም በአሜሪካ እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ባለው የቆየ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ላይ ምን ዓይነት ለውጥ ሊያመጣ ይችላል የሚለው ጉዳይ በዓለም አቀፍ ተንታኞች ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል እንደ ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘገባ።
ልዑል ወልዴ
@Addis_News
@Addis_News
❤ 11🤔 5💯 2
01:08
Video unavailableShow in Telegram
👉 ከ8 በላይ ሳይቶችን ገንብቶ ያስረከበው
ቴምር ፕሮፐርቲ
አሁንም በድጋሜ አዳዲስ ሳይቶችን
ለሽያጭ አቅርቧል ።
📍 ሳር ቤት
#በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ)
👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 5.7ሚ
👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚ
👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚ
👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 11.4ሚ
#በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን)
👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚ
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን)
👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚ
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን)
📍 አዋሬ
#በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ)
👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 145ካሬ = 10.3ሚሊዮን
#በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 78ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.7ሚሊዮን)
👉 135ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 14.8ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.9ሚሊዮን)
👉 157ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.4ሚሊዮን)
⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ ;- 0940464607
0994003949
25.16 MB
❤ 8
Photo unavailableShow in Telegram
የሌሊትና የማለዳ ቅዝቃዜ እስከ ታህሳስ መጨረሻ ይቀጥላል
የሌሊትና የማለዳው ቅዝቃዜ እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ ድረስ በተለይም በደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታዉቋል፡፡
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት መረጃ እንዳመለከተው፤ ከሳይቤሪያ የሚነፍሰው ከፍተኛ የአየር ግፊት ወደ ኢትዮጵያ የሚዘልቅ በመሆኑ ደረቅ፣ ጸሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ይስተዋላል።
በተለይም በሰሜን፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛውና በደቡብ ደጋማ አካባቢዎች የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ከአምስት ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ሊመዘገብ እንደሚችል ተጠቁሟል።
ይህ ቅዝቃዜ እስከ ወሩ ማጠናቀቂያ ድረስ የሚዘልቅ በመሆኑ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍 7❤ 4
Photo unavailableShow in Telegram
ኢራን የሚሳኤል መርኀግብሯ መከላከያ እና የሚቃጣባትን ጥቃት ለማስቆም የተነደፈ መሆኑን አሳሰበች።
የጦር መሣሪያዎቿም ለድርድር አይቀርቡም ብላለች።
እስራኤል የኢራንን ባለስቲክ ሚሳኤሎችና የኒኩሊየር መርኀግብሮቿን በማሳየት በቅርቡ ለ12 ቀናት በተካሄደው ጦርነት ወቅት ለማውደም የሞከረቻቸው ስጋቶች ማለቷ ተዘግቧል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢስማኢል ባቃይ በበኩላቸው «የኢራን ሚሳኤል መርኀግብር የኢራንን ግዛት ለመከላከል የተዘጋጀ በመሆኑ ለድርድር አይቀርብም ማለታቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል።
አክለውም የኢራን የመከላከያ አቅሟ ከወራሪዎች የሚደርስባትን ጥቃት ለመከላከል ያለመ በመሆኑም ለውይይት የሚቀርብ አይደለም ሲሉን አጽንኦት ሰጥተዋል።
የኢራን የባለስቲክ ሚሳኤሎች የመወንጨፍ አቅም እስራኤልን እንደሚያሰጋ ነው የተገለጸው።
ባለፈው ዓመት ሰኔ ድንገት እስራኤል ለሰነዘርችው ጥቃት ኢራን የእስራኤልን የተለያዩ ከተሞች ኢላማ ያደረገ የሚሳኤሎችና የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ማድረሷ ይታወሳል።
@Addis_News
@Addis_News
❤ 31👍 7🤣 3💯 1
Photo unavailableShow in Telegram
🌟🌟ታላቅ የበዓል ቅናሽ በካሬ 78,000 ብር
✅እንዲሁም ሙሉ ክፍያ ለሚከፊል በካሬ 54,800
🔷 በ10 % ቅድመ ክፍያ
🔷 50 % የባንክ ብድር የተመቻቸለት
📍Location እንግሊዝ ኢንባሲ አጠገብ ውብ እይታ (Top View) ያላቸው ቤቶች በሽያጭ ላይ እንገኛለን
👉ከባለ 2 መኝታ- ባለ4 መኝታ
✅ ህንፃው ላይ ያሉ ተጨማሪ አገልግሎትች
👉5 ሰፋፊ ሊፍት /elevator
👉የቆሻሻ መጣያ/garbage chute
👉አውቶማቲክ ጀኔረተር/ automatic generator
👉ሰገነት/terrace
👉የመኪና ማቆምያ/car parking
👉 ጂም , እስፖ
👉 የዋና ገንዳ
👉 የልጆች መጫወታ
✨ባለ 2 መኝታ
138 ካሬ
157.3 ካሬ
163.6 ካሬ
✨ባለ 3 መኝታ
152.4 ካሬ
158.1 ካሬ
187.6 ካሬ
211.5 ካሬ
✨ባለ 4 መኝታ
240.7 ካሬ
258.4 ካሬ
📞 ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
0973559591
0919489575
Telegram -@Homef17
❤ 1👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የገቢዎች ሚኒስቴር በልብስ ስፌት አገልግሎት ላይ የሚጣለውን የኤክሳይዝ ታክስ አከፋፈል በተመለከተ አዲስ ማብራሪያ ሰጥቷል።
ሚኒስቴሩ፣ የልብስ ስፌት ፋብሪካዎች "የአገልግሎት ሰጪ ነን" በሚል ምክንያት ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ መሆን እንደማይችሉ ባወጣው ሰርኩላር ደብዳቤ ላይ አመልክቷልተ
ከዚህ ቀደም የገንዘብ ሚኒስቴር በሰጠው ማብራሪያ፣ አምራቾች ከደንበኞች የሚቀርብላቸውን ጨርቅ የመስፋት አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት የኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፍሉ አይጠየቁም ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ይህ አሰራር የታክስ ገቢ እንዲታጣ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።
በመሆኑም በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 (እንደተሻሻለው) መሠረት፣ በHS Code 50.07 እስከ 63.04 የተመደቡ የጨርቃ ጨርቅና የተሰፉ ልብሶች ምርቶች የኤክሳይዝ ታክስ የሚጣልባቸው በመሆኑ፣ የልብስ ስፌት ፋብሪካዎች ግዴታቸውን እንዲወጡ መታዘዙን ካፒታል ጋዜጣ ለመረዳት ችሏል።
የገንዘብ ሚኒስቴር በቁጥር ታ/ክ/4/5/952 በቀን 01/04/2018 በሰጠው አዲስ ማብራሪያ መሠረት፦ የኢንቨስትመንትና የንግድ ፈቃድ ያላቸው የልብስ ስፌት ፋብሪካዎች ለኤክሳይዝ ታክስ ዓላማ የመመዝገብ ግዴታ አለባቸው።
በተጨማሪም "የልብስ ስፌት አገልግሎት ሰጪ ነን" በሚል ሰበብ ከታክስ ነፃ መሆን አይችሉም የተባለ ሲሆን አምራች ፋብሪካዎችና የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ይህንን አውቀው ተገቢውን ክትትል እንዲያደርጉ የገንዘብ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
በታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በገቢዎች ሚኒስትር የተላለፈዉ ይህ ውሳኔ በዘርፉ ሊሰበሰብ የሚገባውን የታክስ ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብና አሰራሩን ግልፅ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 5😢 4👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
🥚የእንቁላል 7 አስገራሚ የጤና በረከቶች
1. ለአእምሮ ጤንነት አስፈላጊ ነው!
እንቁላል ክሎሪንን ለአእምሮ በመመገብ ጤንነቱን ይጠብቃል፡፡
ክሎሪን መልዕክት አስተላላፊ በመሆን ያገለግላል፡፡ አስኳል ውስጥ የሚገኝው ፎሌት ንጥረ ነገር የነርቭ ሴሎችን በመጠበቅ አእምሮ ተግባሩን በትክክል እንዲወጣ ያደርገዋል፡፡
2. ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል!
እንቁላል የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅምን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል፡፡ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በሳምንት ቢያንስ 6እንቁላል መመገብ በጡት ካንሰር የመጋለጥ እድላችንን በ44% ይቀንሳል፡፡
3. ለአይን ጤንነት ይጠቅማል!
2 ካሮቲኖይድ፣ ሉቲይንና ዜክሳንቲን የጠራ እይታ እንዲኖረን እና አይናችን ጤናማ እንዲሆን ይረዱናል፡፡ እንቁላል ተመጋቢ ከሆኑ ከካታራክትና ከፀሃይ ጐጂ ጨረር ከመጋለጥ ይከላከልልዎታል፡፡
4. የፀጉር እና ጥፍር ጤንነትን ለመጠበቅ!
በሰልፈር የበለፀገ አሚኖ አሲድ በእንቁላል ውስጥ ይገኛል፡፡ የጥፍር ጤንነትና ጥራትን ይጨምራል፡፡ ሌሎች እንደ ብረት፣ ዚንክና ሴሊኒየም ለፀጉር ጤንነት የበኩላቸውን ድርሻ ይወጣሉ፡፡
5. የሰውነት ክብደትን ያመጣጥናል!
በፕሮቲን የበለፀገ ስለሆነ የሰውነት ክብደትን ለመጨመር ተመራጭ ነው፡፡
እንቁላል ስንጠቀም ከመጠን በላይ እንዳንመገብ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
6. አጥንታችን ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል!
እንቁላል ከፍተኛ የቫይታሚን ዲ፣ ፎስፈረስና ካልሲየም መጠን አለው እነዚህ በአንድነት በመሆን የአጥንት ችግርን ይከላከላል፡፡
7. ከድንገተኛ የልብ ህመም፣ የደም መርጋትና ድንገተኛ ከሆነ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስን ይከላከላል፡፡
@seledadotio
@seledadotio
❤ 28🔥 8
መረጃ‼️
የኢትዮጵያ የግል ድብልቅ የትራንስፖርት ወይም መልቲ ሞዳል አገልግሎት ሠጪ ኩባንያዎች ጅቡቲ ወደብ ላይ ደረሠኝ እንዳይቆርጡ የወደቡ ባለስልጣናት በድንገት ማገዳቸው በግል ኩባንያዎቹ የሎጅስቲክ ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ከባድ ችግር መፍጠሩን ፎርቹን ዘግቧል።
የጅቡቲ የወደብ አስተዳደር፣ ከእንግዲህ በወደቡ ላይ ደረሠኝ መቁረጥ የሚችሉት የንግድ መርከብ ባለቤቶች የሆኑ የትራንስፖርት አገልግሎት ሠጪ ኩባንያዎች ብቻ ናቸው ማለቱን ዘገባው ጠቅሷል።
በዚህ አዲስ መመሪያ ሳቢያ፣ የግል ትራንስፖርት ኩባንያዎች የካርጎ ጭነቶችን ከወደብ ማውጣት እንዳልቻሉ ዘገባው አመልክቷል።
በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ መካከል ቀደም ሲል የተፈረመው የወደብ አጠቃቀም ስምምነት የጊዜ ገደቡ ያለፈ ሲኾን፣ ስምምነቱን በድጋሚ ለማደስ ንግግ እየተደረገ ይገኛል ተብሏል።
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የመሩት ልዑካን ቡድን፣ ባለፈው ሳምንት ወደ ጅቡቲ ተጉዞ ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር መነጋገሩ አይዘነጋም።
መንግሥት ለግል የድብልቅ ትራንስፖርት አገልግሎት ሠጪ ኩባንያዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቃድ የሠጠው ከአንድ ዓመት በፊት ሲሆን፣ ቀደም ሲል ዘርፉን በብቸኝነት ተቆጣጥሮት የቆየው መንግሥታዊው የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ድርጅት ነበር።
Via : ዋዜማ
@Addis_News
@Addis_News
❤ 16🤪 3
Photo unavailableShow in Telegram
የይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸው ይዞታዎች ታክስ እንዲከፈልባቸው የሚያስገድድ ሕግ ተዘጋጀ
የይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸው ነገር ግን በይዞታው ጥቅም የሚያገኙ፣ የንብረት ታክስ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ሞዴል ረቂቅ የንብረት ታክስ አዋጅመዘጋጀቱ ተነገረ።
ረቂቅ አዋጁን የገንዘብ ሚኒስቴር ከገቢዎች፣ ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር ማዘጋጀቱ ተገልጿል።
ለሁሉም ክልሎችና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተላከው ሞዴክ የንብረት ታክስ ህጉ በሊዝ ይዞታ ስሪትም ሆነ ከይዞታ ስሪት ውጪ በሚተዳደር ማንኛውም የቦታ መጠቀሚያ የሚጣልና የሚሰበሰብ መሆኑ ተገልጿል።
ሆኖም የተመዘገበ የባለቤትነት መብት በሌለበት ጊዜ ታክስ መክፈሉ ብቻ ባለይዞታ እንዳማያደርግና በሌሎች ህጎች የሚወሰዱ እርምጃዎችን እንደማያስቀር ተገልጿል።
በከተማው ቦታ መጠቀሚያ መብት ላይ የሚጣለው ታክስ ምጣኔ ታክስ የሚከፈልበት ዋጋ ላይ 0 ነጥብ 2 በመቶ በታችና ከአንድ በመቶ በታች በማይበልጥ ሁኔታ ተግባራዊ እንደሚደረግ፣ ከተሞች አግባብነት ያላቸውን ህጎች መሰረት በማድረግ በባዶ ቦታ ላይ ከፍተኛ የታክስ ተመን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ሰፍሯል።
በሌላ በኩል ዝቅተኛ ገቢ ላለው አንድ ቤተሰብ በመኖሪያነት የሚያገለግል የከተማ ቦታ፣ ህንጻና የቦታ ማሻሻያ ከንብረት ታክስ ነጻ መደረጉ ተገልጿል።
በተመሳሳይ የሀይማኖት ተቋማት ለአምልኮና ለመካነ መቃብር አገልግሎት የሚጠቀሙባቸው ንብረቶች ፣ ለህብረተሰቡ ነጻ ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ለአገልግሎቱ የሚጠቀሙባቸው ንብረቶች ከታክስ ነጻ ናቸው ተብሏል።
@seledadotio
@seledadotio
❤ 18🤣 7😨 3
“ትግስታችን አልቋል”ህወሓት‼️
በምርጫ ቦርድ የተሰረዘው ህወሓት ሳምንታዊ መልዕክት በሚል ባወጣው መግለጫ፣ ትዕግሴት አልቋል ብሏል፡፡ የፌደራል መንግሥቱን የወነጀለው ህወሓት፣ በተደጋጋሚ ያቀረበው ጥሪ ምላሽ አለማግኘቱን ገልጿል፡፡
በፕሪቶሪያ የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ በተደጋጋሚ ጥሪ ባቀርብም ምላሽ እያገኘ አይለም ያለው ህወሓት፣ ከዚህ በኋላ አልታገስም ብሏል። ቡድኑ በመግለጫው ለዘላቂ ሰላም መስፍን ቁርጠንነት ቢኖረኝም፣ የትግራይ ህዝብን ለማጥፋት የሚደረጉ ሴራዎችን አልታገስም ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት “የትግራይ ህዝብን በተለያዩ መንገዶች የዘር ማጥፋት ዘመቻውን ቀጥሏል” በማለት የወነጀለው ህወሓት፣ ትግራይ ያለው የሰብአዊ ቀውስ መባባሱን ጠቁሟል። ለዚህም አስታኮ ማስጠንቀቂያ አዘል መግለጫ ያወጣበትን የህጻጽ ተፈናቃዮ ረሃብ ያነሳ ሲሆን፣ የፕሪቶሪያው ስምምነት ባለመተግበሩ ትግራይ ተደራራቢ ቀውስ እያስተናገደች ነው ብሏል፡፡
ይሁን እንጂ ትግራይ ለገጠማት ቀውስ የፌደራል መንግሥቱን ተጠያቂ የሚያደርገው ራሱ ህወሓት ተፈናቃዮች የፖለቲካ መያዛ በማድረግ ይወነጀላል፡፡ ከህወሓት በተቃራኒ የቆሙ በርካታ የትግራይ ፖለቲካ ኃይሎች ተፈናቃዮች ለችግር የተጋለጡት ሰብዓዊነት እና ፖለቲካ በመቀላቀሉ ነው ይላሉ፡፡
ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በትግራይ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ነው ያለውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል ለመከላከል ጥረት እያደረገ አለመሆኑን አመልክቷል። ህወሓት በመግለጫው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተገቢውን ዕርምጃ መውሰድ አለበት ያለ ሲሆን፣ ትዕግስትም ልክ አለው በማለት አሳስቧል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 32🤣 10😢 3
የጭካኔ ጥግ!!!! በአዲስ አበባ ሰሚት ጠፍቶ ሲፈለግ የነበረው የ7 አመቱ ህፃን ተገድሎ የካ ጫካ ውስጥ ተገኘ
ቀብሩ ዛሬ ተፈፅሟል።
ቤተሰቦቹ የ7 ዓመቱ ህፃን ሀበን ካሱ ከአዲስ አበባ፣ ሰሚት እሁድ ታህሳስ 5/2018 ዓም ከቤት እንደወጣ አለመመለሱን በመግለፅ በእግር በፈረስ፣በፖሊስ በማህበራዊ ሚዲያም በመንገር ትንሹን ልጅ አስፈለጉ።
ይገኛል የሚለው ተስፋ ይዘው ፣በሌላ በኩልም ተገድሎ ይሆን ፣አውሬ በልቶት ይሆን ፣ ሰው ሰውሮት ይሆን? ሌላም ሌላም በውስጣቸው እየዞረ ከሳምንት ጭንቀት በኋላ የትንሹ ልጅ ሬሳ በሰው ተገድሎ ክብር እንዴለለው ፍጡር ጫካ ውስጥ ተጥሎ ተገኘ።
ፖሊስ የህጻኑን መገደል ዛሬ ጠዋት ለቤተሰቦቹ ያረዳ ሲሆን ቤተሰቦቹም ለአስክሬን ምርመራ በሆስፒታል ይገኝ የነበረውን አስክሬን በመረከብ ስርአተ ቀብሩን ፈጽመዋል።
ስርአተ ቀብሩ በዛሬው ዕለት 8:30 ሰሚት በሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
ተጠርጣሪው ህጻኑን ቀደም ብሎ ገድሎት ለቤተሰቦቹ በመደወል በገንዘብ ሲደራደር ነበር ተብሏል።
ይህ ተጠርጣሪ በፖሊስ ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት ነው።
😢 63❤ 20💔 13🙏 4👍 2
በንብረት ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት ወንድማቸውን በጩቤ ወግተው የገደሉት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
የእናት እና አባታችንን ንብረት ብቻህን ለምን ታስተዳደራለህ በማለት ወንድማቸውን የገደሉት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ።
በምስራቅ ባሌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አሻግሬ ጥላሁን እንደገለጹት ጥበቡ ድሪባ፣ መብራቱ ዲሪባ እና ሀብታሙ ዲሪባ የተባሉት ሶስት ወንድማማቾች ከአንድ አባትና እናት የተወለዱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በምስራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ወረዳ አቃሸት ቀበሌ ሲሆን እንደማንኛውም ልጅ ሶስቱ ወንድማማቾች፣ በልጅነታቸው አንዱ ለአንዱ በመተጋገዝ የወጣትነት እድሜ ክልል ውስጥ ገብተው እያሉ ታላቅ ወንድም ቀድሞ ትዳር ይመሰርታል። በዚህም አባት እናት ታላቅ ወንድምን ለንብረታቸው ተቆጣጣሪ በማድረግ ሁለት ታናሽ ወንድሞች ለታላቅ ታዘው እንዲያድጉ ያደርጋሉ። የወንድማማቾቹ አባት በተፈጥሮ ህመም በሞት ይለያሉ።
የቤተሰብ ሙሉ ንብረትን ሃላፊነት ለታላቅ ወንድማቸው መሰጠት ያላስደሰታቸው ሁለቱ ወንድማማቾች እናታቸውን እኛስ ምንም አይነት ሃላፊነት የለንም በማለት እናታቸውን ማስቸገር እንደጀመሩ ነው የተገለፀው።
የሁለቱ ልጆቻቸው ከታላቁ ጋር የገቡትን ቅራኔ ለመፍታት እናት ታላቅየው ከሚያስተዳድረው መሬት የተወሰነው እንዲሰጣቸው ተስማምተው ጥበቡ ለሁለቱ ወንድሞቹ ያለውን መሬት ከፍሎ ይሰጣቸዋል።
ይሁን እና በዚህ ደስተኛ እንዳልሆኑ እና አብላጫውን የወሰደው እሱነው በማለት ቂም ቋጥረው ይቆያሉ። በዚህም መስከረም 17 ቀን 2018 ዓም የመስቀል በዓል እለት መጠጥ የጠጡት ወንድማማቾች ምሽት 12:30 ላይ ታላቅ ወንድማቸውን ወላጅ እናታቸው ጋር ቆይቶ ወደ ቤቱ ሲመለስ ጠብቀው ፀብ በማንሳት በያዙት ስለታም ጩቤ ሆድ እቃውን በመውጋት ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ሕይወቱ እንዲያልፍ ያደርጋሉ።
የአካባቢው ሰዎች ወዲያው ለፖሊስ ጉዳዩን ይጠቁማሉ ። ፖሊስም የሟችን አስክሬን በማንሳት ለአስክሬን ምርመራ ወደ ሆስፒታል በመላክ የድርጊት ፈፃሚዎች ሁለቱ ወንድማማቾች መሆናቸው ባገኘው ተጨባጭ መረጃ ተከታትሎ በቁጥጥር ስር ያውላቸዋል።
የምርመራ መዝገባቸውንም በአስክሬን እና በሌሎች ማስረጃዎች በማጠናከር ለአቃቢ ሕግ ይልካል። ዓቃቢ ህግም ከፖሊስ የተላከውን መዝገብ ተመልክቶ በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ ይመሰርታል።
በአቃቢ ህግ የተመሰረተውን ክስ የተመለከተው የምስራቅ ባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሕዳር 23 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት ተከሳሾቹ ጥፋተኛ መሆናቸው በሙሉ ማስረጃ በመረጋገጡ አንደኛ ተከሳሽ መብራቱ ዲሪባ በእድሜ ልክ እስራት ሁለተኛ ተከሳሽ ሃብታሙ ዲሪባ በሃያ አምስት አመት እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ማስተላለፉን ዋና ኢንስፔክተር አሻግሬ ጥላሑን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
Dagu
@Addis_News
@Addis_News
❤ 15😢 7
ነገደ መናብርት የሚባሉትን መላእክት የሚመራቸው አለቃ ነው
አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ በሰዓታቱ “ጽርሐ አርያም አዳራሹ፤ የትጉሃን መኖሪያ ቦታው የሚኾን እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ተብሎ በአንድነት በሦስትነት ይመሰገናል፤ ካህናተ ሰማይ በዙሪያው ይቆማሉ፤ በዙፋኑ ፊት እየሰገዱ አክሊሎቻቸውን ያወርዳሉ፤ እሳትነቱ በሚበርቅ፣ ጊዜ እንዳይመታቸው ይንቀጠቀጣሉ” ይላል፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በመጽሐፈ አክሲማሮስ “በራማ ሰማይ የሚገኘውን ሁለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በሁለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ከሚመራው ከዚኽ ነገድ 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡” ይለናል፡፡ በ720 ዓ.ዓ ዐሥሩ ነገደ እስራኤል ሲማረኩ ጦቢት የተባለ ጻድቅ ሰው ዐብሮ ተማርኳል፡፡
ቅዱስ ሩፋኤል ይህን ጦቢትን የተራዳ መልአክም ነው፡፡ በመጽሐፈ ጦቢት 2÷14 እንደተጻፈው ሰውን በመርዳት በደግነቱ የታወቀው ጦቢት ከመንገድ ወድቆ የተገኘ በድን ቀብሮ፤ በዚያው ሌሊት ከቅጥሩ አጠገብ ፊቱን ተገልጦ ተኝቶ ሳለ አዕዋፍ ትኩስ ኩስ ዐይኑ ላይ ጥለውበት እንደ ብልዝ ያለ ወጥቶበት ዐይኑ ጠፋ፤ ሚስቱም ባለማስተዋል “በጐነትህ ምጽዋትህ ያዳነህ ወዴት ነው?” በማለት ስትናገረው ዐዝኖ ሞትን ተመኘ፡፡ ቅዱስ ሩፋኤልም አይኑን ሲፈውሰው፣ በላይዋ ላይ ያደረ ጋኔን ባሏን ይገድልባት ቤተሰቦቿን ያንቋሽሿት የነበረችውን የራጉኤል ልጅ ሳራን ያደረባትን ርኩስ መንፈስ አስወጥቶ የጦቢት ልጅ ጦብያ እንዲያገባት አድርጓል፡፡ የመላዕክት ተራዳኢነት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ትልቅ ስፍራ አለው፡፡
ቅዱስ ሩፋኤልም ከዚህ በኋላ ወደ ጦቢት በመኼድ ረዥም ዘመን የታወረ ዐይኑን አብርቶለት ከሰብዐቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሩፋኤል እኔ ነኝ ብሏቸው ተሰውሯል፡፡ ጦቢት 12÷15፡፡ ፈታሔ ማኀፀን ወሰፋድል። መወለድ መንፈሳዊ። ወሐኪም ሰማያዊ ይባላል። የወላድ ማኀፀን እንዲፈታ በእግዚአብሔር ስለተሾመ አዋላጅ ብትኖርም ባትኖርም ቅዱስ ሩፋኤል በዚያ አይታጣም፡፡
በተለይ በባላገር ያሉ ሴቶች በምጥ ጊዜ ሁሉ መልክአ ሩፋኤል በአንገታቸው ያነግታሉ፣ ይጸልያሉ፣ የተጸለየበትንም ጸበል ይጠጣሉ፤ በፍጥነትም ይወልዳሉ። ቅዱስ ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን፤ “ሩፋ” ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፡፡ በመጽሐፈ ሄኖክ 6÷3 ላይም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ተብሏል፡፡
ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስም “በፊቱ የሚቆሙ የመላእክት ሰራዊትም ኹሉ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ የመላእክት አለቆችም ለማይታይ ለባለዚህ ስም ዘንበል ብለው ይሰግዳሉ፤ ዙፋኑን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ ዕጣንን የተመሉ የወርቅ ማዕጠንት በእጆቻቸው ያለ ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ይኸውም የቅዱሳን ጸሎት ነው እስከ ዘላለሙ ሕያው በሆነው ፊት የሚቀበለው መሥዋዕት አድርገው ወደ ላይ ያሳርጋሉ” በማለት አስተምሯል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ነገደ መናብርት የሚባሉትን ራማ በሚባለው ሰማይ የሚኖሩትን ነገደ መላእክት የሚመራቸው ናቸው፡፡ ዓመታዊ በዓሉ ጳጉሜ 3 ሲሆን በየወሩ በ13ኛው ቀን ደግሞ መታሰቢያ በዓሉ ይከበራል፡፡ ገዳማውያንም ይህን ተራዳኢነቱን በመታመን ዘወትር በጸሎታቸው ይጠሩታል፡፡
እኛንም የቅዱስ ሩፋኤል በረከትና ረድኤቱ አይለየን፤ ምልጃው ይጠብቀን፡፡ ገዳማቸውን በመደገፍና በዓታቸውን በማጽናት የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
❤ 41🤪 3
Photo unavailableShow in Telegram
🚨ውፍረት መጨመር ይፈልጋሉ❓❓
+251964593642
✔ ከአንድ ወር እስከ 45 ቀን ዉስጥ
ክብደት መጨመር የሚረዳ
✔ የምግብ ፍላጎት መጨመር የሚያስችል
✔ የቆዳን ጥራት እና ልስላሴ ለመጨመር
የሚረዳ
✔ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት የሌለዉ ፤
ለቀጭን ሰዎች የሚመከር
✔ ለሴቶችም የተስተካከለ አቋም
እንዲጎናፀፉ የሚያግዝ
✔ ለወንዶችም ለሴቶችም የሚሆን አለን ፤
🚴♂ያሉበት እናደርሳለን
------------------------------------
ለበለጠ መረጃ ☎️ +251964593642
+251906495051
+251907495051
Telegram: 📥 t.me/AM_CS
t.me/AM_CS1
t.me/AM_CS2
------------------------------------
❤ 6🤪 6💯 1
በረሃብ አለንጋ እየረገፉ ያሉ ወገኖች ከሕፃፅ የተሰማ ሰቆቃ‼️
በትግራይ ክልል ህፃፅ ከተማ የሚታየው ትዕይንት እጅግ አሳዛኝ ነው። የረሃብ ፅልመት በየቤቱ ገብቶ ህፃናትንና አረጋውያንን እየቀጠፈ ይገኛል። እናቶች ልጆቻቸውን የሚያበሉት አጥተው፣ ልጆችም የደረቀ ጡት እየመጠጡ ለሞት ሲፋጠጡ ማየት ሰብአዊነትን የሚፈትን ሆኗል።
ይህን ርሃብ ተከትሎ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ምላሽ ለመስጠት ኮሚቴ ማቋቋሙን ምንጮቻችን ገልጸዋል።
@Addis_News
@Addis_News
😢 78❤ 19💔 3😨 1
04:30
Video unavailableShow in Telegram
ሰዎች viral የሆነው በ view የሚከፍለውን አፕፕ እኛም እንስራው
በመጀመሪያ ከታች ያለውን ትነኩትና አፑን download ታደርጉታላችሁ በመቀጠል create account የሚለውን ከነካችሁ ቡሃላ
1 በዚህ ሊንክ ግቡ ና Appun playstoreን or appstoreእን ምረጡ
https://app.buzzerfan.com/referral-invite/rsdf3de6aff03447bab57010ece7626afe
👉 Gmail
👉 የማረሱትን password
👉 ከዛ otp code ይላክላችሁአል ያንን paste ታደርጉታላችሁ
👉ከዛም ምትፈልጉትን sports ትመራጣላችሁ, ስም, username እና እድሜ ታስገባላችሁ
👉በመጨረሻም referral code ይጠይቃችሁአል ከስር ያለውን copy ታደርጉትና አስገብታችሁ
🕹️ Referral code ይህንን ተጠቀሙ
👉6AF-10 Ereferral code የሚል ሲመጣላችሁ bonus point ለማግኘት ይህን ኮድ አስገቡ 👉 6AF10E
ከዛ የመጀመርያችሁን 100 point ይሰጣችቹአል ✌️
ከዛም ከ tiktok ላይ ፅድት ያሉ የ sports edits ያለ watermark download እያደረጋችሁ post በ ማድረግና invite በማድረግ ሸቅሉ አሰራሩ ካልገባችሁ ከላይ ቪዲኦ ተያይዟል ተመልከቱና ስሩ👆💲💰💰
31.85 MB
❤ 5👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
አዋሽ ወይን፣ አራዳ ቢራን ሊገዛ ተቃርቧል!
-አዋሽ ወይን ኮማሪን ለመጠቅለል ከስምምነት ሲደርስ፣ የሀይነከን እቅድ በምንዛሬ ለውጥ ምክንያት ተሰርዟል
የዓለም አቀፉ ግዙፍ የቢራ ኩባንያ ሀይነከን፣ የኮማሪ መጠጥ ኩባንያን ለመጠቅለል የነበረው እቅድ መክሸፉ ተሰማ።
ይህን ተከትሎ አንጋፋው አዋሽ ወይን አክሲዮን ማህበር፣ ይፋዊ የግዢ ስምምነት ውስጥ በመግባት የኮማሪን ብራንድ ለመረከብ መቃረቡ ተገልጿል።
ካፒታል ጋዜጣ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ በሀገሪቱ አንጋፋውና ስኬታማው የመጠጥ አምራች አዋሽ ወይን፣ በአራዳ መጠጥ ምርቱ የሚታወቀውን ኮማሪ መጠጥ ኩባንያን ለመግዛት ከስምምነት ደርሷል።
በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ተጠናቆ የነበረው የሀይነከን እና ኮማሪ ስምምነት ሊፈርስ የቻለው በኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጥ ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል። ምንጮች እንደገለጹት፣ በውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ የተደረገው ማስተካከያና የብር የመግዛት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ፣ የኩባንያውን ዋጋ የመወሰንና የክፍያ ስርአቱን ውስብስብ በማድረጉ ስምምነቱ እንዲቋረጥ ምክንያት ሆኗል ሲል ካፒታል ዘግቧል፡፡
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 13
Photo unavailableShow in Telegram
ከጥር 23 ጀምሮ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀምና ማምረት በህግ ያስቀጣል
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶች ላይ የተጣለው እገዳ ከጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ እንደሚሆንና እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር አስታወቀ።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
📌 የእገዳው ገደብ፦ የ6 ወራት የሽግግር ጊዜው ጥር 23 ያበቃል። ከዚህ ቀን በኋላ ስስ ፕላስቲኮችን ማምረት፣ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትና መጠቀም በህግ ያስጠይቃል።
📌 አማራጭ አቅርቦቶች፦ የወረቀትና ሌሎች ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ከረጢቶችን ለሚያመርቱ አካላት የማሽነሪ ከቀረጥ ነፃ መብትና የብድር አቅርቦት እንዲመቻች እየተሰራ ነው።
📌 የክትትል ስራ፦ ባለስልጣኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በገበያ ውስጥ የሚታዩ ህገወጥ የፕላስቲክ ስርጭቶችን ለመቆጣጠር ዝግጅቱን አጠናቋል።
🚨 ማሳሰቢያ፦ ማንኛውም ነጋዴም ሆነ አምራች እስከ ጥር 23 ድረስ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ወደ አማራጭ ምርቶች እንዲሸጋገር ጥሪ ቀርቧል።
@seledadotio
@seledadotio
🤣 17❤ 10👍 5
የእርሻ ማሳ ውስጥ የገባ ዝሆን የ76 ዓመቱን አዛውንት ሕይወት ሲያጠፋ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት አደረሰ
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሀረማያ ወረዳ እርሻ ማሳ ውስጥ የገባው ዝሆን የአንድ ሰው ሕይወት ሲያጠፋ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት ማድረሱን ፖሊስ አስታውቅቋል።የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮምንኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፍ ምክትል ኢንስፔክተር ካሲዬ አበበ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በዞኑ ሐረማያ ወረዳ በሊና ቀበሌ ውስጥ ድርጊቱ ተፈፅሟል።
የእርሻ ማሳ ውስጥ የገባው ዝሆን አቶ መሐመድ አሕመድ ቱሌ የተባሉትን የስምንት ልጆች አባት በኩንቢው ጠልፎ የጣላቸው ከእርሻ ማሳቸው ውስጥ ዝሆኑን ለማውጣት ባደረጉት ጥረት እንደሆነ ገልፀዋል። በኩቢው አዛውንቱን ጠቅልሎ ከጣላቸው በኃላ በእግሩ ሲረጋግጣቸው የተመለከተው የሀያ አመት ወጣት አዛውንቱን ከዝሆኑ ጥቃት ለመታደግ ጥረት ሲያደርግ ዝሆኑ ጉዳት አድርሶበት እንደ ሄደ ገልፀዋል።
የአካባቢ ሰዎች ዝሆኑ ስፍራውን ለቆ ከሄደ በኋላ ሲደርሱ የአዛውንቱ ሕይወት ያለፈ ሲሆን ጉዳት የደረሰበትን ወጣት ደግሞ በሕይወት ያለ በመሆኑ ወዲያው ወደ ሀረማያ ሆስፒታል በማድረስ የሕክምና እርዳታ አግኝቶ በጤንነት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ዝሆኖች አንዳንዴ ከባብሌ ፖርክ በመውጣት በሰብል ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሲሆን ይህንኑ ለመከላከል በሚደረግ ሙከራም በሰው ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱ ምክትል ኢኒስፔክተር ካሲዪ አበበ ጨምረው ገልፀዋል።dagu
@seledadotio
@seledadotio
❤ 30😢 20
