ETHIO-MEREJA®
Ir al canal en Telegram
News & Media Company® USA : Washington Addisababa, Ethiopia🇪🇹 . Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja . ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!! 👉 @ethio_merejabot ✔
Mostrar más2025 año en números

110 282
Suscriptores
-4624 horas
-2877 días
-1 28930 días
Archivo de publicaciones
Photo unavailableShow in Telegram
በነዳጅ ምርቶች ላይ የተጣለዉ አጠቃላይ የ30 በመቶ ግብር በቀጣይ ወር ተግባራዊ እንደሚሆን ተገለፀ
የኢትዮጵያ መንግሥት ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን የነዳጅ ድጎማ ቀስ በቀስ ለማስወገድ ከሚወስዳቸው ሰፋፊ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች አንዱ የሆነው አዲስ የግብር አወቃቀር ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ተግባራዊ ሊሆን ነው።
ይህ አዲስ እርምጃ በነዳጅ ምርቶች ላይ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና 15 በመቶ ኤክሳይዝ ቀረጥን ያካተተ አጠቃላይ 30 በመቶ ታክስ መጣል ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከአንድ ወር በኋላ ታክሱን መሰብሰብ ይጀምራል።
በአዲሱ መመሪያ መሠረት፣ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅቱ የተሰበሰበውን ግብር በሙሉ ለገቢዎች ሚኒስቴር ማስገባት ግዴታው ሲሆን፤ መንግሥት በዚህም እስከ ታኅሣሥ 2018 ዓ.ም ድረስ ለቤንዚንና ናፍጣ መሸጫ ዋጋዎች ሁሉንም ህጋዊ የግብር መጠን ጨምሮ ሙሉ ወጪን የመሸፈን ግብ ላይ ለመድረስ አቅዷል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ከአዲሱ በጀት ዓመት ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች ላይ አጠቃላይ 30 በመቶ ግብር ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሊያደርግ ማቀዱን ከሁለት ወራት በፊት መዘገቡን አስታዉሶ ካፒታል አስነብቧል፡፡
❤ 24😁 8👎 4
Photo unavailableShow in Telegram
የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች እና መከላከያ ዘዴዎች
የማርበርግ ቫይረስ በሽታ (Marburg Virus Disease) በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት የደም መፍሰስና ትኩሳት ህመም ሲሆን በሰዎችም ሆነ በሌሎች እንስሳት ላይ ይከሰታል።
የበሽታው ምልክቶች ለቫይረሱ በተጋለጥን ከ2 እስከ 9 ባሉት ቀናት ውስጥ የሚታዩ ሲሆን፤ ምልክቶቹ:-
👉 ከአፍ፣ ከአፍንጫ ወይም ከቆዳ ስር ደም መፍሰስ፣
👉 ከፍተኛ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት እና ራስ ምታት፣
👉 የጡንቻ እና የጀርባ ህመም፣
👉 ማቅለሽለሽ፣ የሆድ ህመም እና ተቅማጥ፣
👉 ደረት፣ ጀርባ እና ሆድ ላይ በጣም ጎልቶ የሚታይ ሽፍታ ናቸው።
የበሽታው መተላለፊያ መንገዶች
👉 ከበሽተኛ ደም፣ ሽንት፣ እንባ እና ሌሎች ፈሳሾች ጋር የሚፈጠር ቀጥተኛ ንክኪ፣
👉 በታመመ ወይም በሞተ ሰው የሰውነት ፈሳሽ የተበከሉ ቁሶች (እንደ ልብስ፣ አልጋ ልብስ፣ መርፌ እና ሌሎች መገልገያዎች) ጋር በሚኖር ንክኪ፣
👉 በተጨማሪ በበሽታው ከተያዙ የሌሊት ወፎች ወደ ሰዎች ይተላለፋል።
የበሽታው መከላከያ መንገዶች
👉 የተዘረዘሩት ምልክቶች ሲኖሩ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ፣
👉 ከታመመ ሰው ጋር ንክኪ ካለዎት እና ትኩሳት ካለ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መሄድ፣
👉 ሞት በሚከሰትበት ጊዜ አስከሬኑን በባለሙያ ማዘጋጀት እና መቅበር፤ አላስፈላጊ የቀብር ሥነ ሥርዓቶችን ማስቀረት እና ንክኪ ያላቸውን ቁሶች ማስወገድ፣
👉 ከታመመ ሰው ደም እና ፈሳሽ ንክኪ ራስን መጠበቅ፣
👉 ለታመመ ሰው እንክብካቤ በምናደርግበት ጊዜ የመከላከያ ዘዴዎችን ማለትም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እና የእጅ ጓንት መጠቀም፣
👉 እጅን በሳኒታይዘር ወይም በሳሙናና በውሃ በአግባቡ መታጠብ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።
❤ 70👍 11🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ነገ እሁድ ህዳር 7 ቀን 2018 ከሌሊቱ 6:00 እስከ ሌሊቱ 9፡45 ሰዓት ድረስ በሲቢኢ ብር ከሚሰጡ አገልግሎቶች በስተቀር ሁሉም የባንካችን ዲጂታል የክፍያ አገልግሎቶች እንደሚቋረጡ አስታውቋል
****
"ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ነገ እሁድ ህዳር 7 ቀን 2018 ከሌሊቱ 6:00 እስከ ሌሊቱ 9፡45 ሰዓት ድረስ በሲቢኢ ብር ከሚሰጡ አገልግሎቶች በስተቀር ሁሉም የባንካችን ዲጂታል የክፍያ አገልግሎቶች ማለትም በሞባይል ባንኪንግ፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ፣ በኤቲኤም ማሽኖች እንዲሁም በፖስ ማሽኖች እና በኮር ባንኪንግ የሚሰጡ አገልግሎቶች (Core Banking Services) በጊዜያዊነት ይቋረጣሉ።
በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን ይህን አውቃችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳወቅን፣ ለሚፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል ይቅርታ እንጠይቃለን። ብሏል"
❤ 69
ማርበርግ ቫይረስ
1) በሽታው ምንድን ነው?
#የቫይረሱ አይነት: ማርበርግ ቫይረስ የፋይሎቫይረስ (Filoviridae) ቤተሰብ አባል ሲሆን ይህም ኢቦላ ቫይረስ የሚገኝበት ቤተሰብ ነው። ለዚህም ነው ሁለቱም በሽታዎች ተመሳሳይ የሕመም ምልክቶች እና የሞት መጠን ያላቸው።
#ክብደት: በሽታው ከባድ እና ከፍተኛ የሞት መጠን ያለው ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ በተከሰቱ ወረርሽኞች በበሽታው ከተያዙት ውስጥ እስከ 88% የሚደርስ ሰዎች ሞተዋል (እንደ ወረርሽኙ ሁኔታ ሊለያይ ይችላል)።
#ታሪክ: በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ በ1967 ዓ.ም በጀርመን ማርበርግ እና በፍራንክፈርት እንዲሁም በሰርቢያ ቤልግሬድ ከተሞች ተከስቷል። ቫይረሱ የመጣው ከዩጋንዳ በመጡ የላብራቶሪ ምርምር ዝንጀሮዎች አማካኝነት ነው ይባላል።
2) ስርጭት (በሽታው እንዴት ይተላለፋል?)
+++ ዋናው #ምንጭ: የማርበርግ ቫይረስ ተሸካሚዎች ፍራፍሬ ላይ የሚያዘወትሩ የሌሊት ወፎች (Rousettus bats) ናቸው። ሰዎች በቫይረሱ ሊያዙ የሚችሉት በእነዚህ የሌሊት ወፎች ባሉበት ዋሻዎች ወይም ማዕድናት ውስጥ በመገኘት ነው።
+++ ከሰው ወደ ሰው የሚኖረው #ስርጭት: ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በበሽታው የተያዘ ሰው ወይም እንስሳት በሚወጡ ፈሳሾች (ደም፣ ምራቅ፣ ማስታወክ፣ ሰገራ፣ ሽንት፣ የዘር ፈሳሽ እና ሌሎች) ጋር በቀጥታ በመገናኘት ነው።
3) #ምልክቶች
የበሽታው ምልክቶች በአብዛኛው ከ2 እስከ 21 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ይታያሉ።
የሚከተሉትን እንመልከት
#የመጀመሪያ ደረጃ ላይ : ከፍተኛ ትኩሳት፣ ከባድ ራስ ምታት፣ ከባድ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ህመም፣ ድካም ስሜት።
#ሁለተኛ ደረጃ (ከጥቂት ቀናት በኋላ): ከባድ ተቅማጥ፣ የሆድ ቁርጠት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ የደረት እና የጉሮሮ ህመም።
#የከፋ ደረጃ (ከ5-7 ቀናት በኋላ) ከባድ የደም መፍሰስ (ከአፍንጫ፣ ከድድ፣ ከዓይን እና የቆዳ ስር)፣ የጉበት እና የኩላሊት ድካም፣ የንቃተ ህሊና መሳት፣ የብዝሃ-አካል ስራ መቆም (Multi-organ failure) እና ሞት። ከዚህ በተጨማሪ የዓይን መቅላት፣ የቆዳ ሽፍታ (በተለይ በደረት፣ ጀርባና ሆድ አካባቢ)።
4)የሚሰጠው ህክምና እና መከላከያ መንገዶች
#ፈውስ: ለጊዜው ቫይረሱን የሚያጠፋ የተረጋገጠ መድኃኒት ወይም ክትባት የለም።
#ህክምና: የሚሰጠው ህክምና ምልክቶችን ለማስታገስ (Supportive Care) ነው።
#ፈሳሽ መተካት (IV fluids): በከፍተኛ ተቅማጥ እና ማስታወክ የጠፋውን ፈሳሽ መሙላት ነው።
#የደም መፍሰስ ቁጥጥር: የደም ግፊትን ማረጋጋት እና የደም መርጋት መከላከል/ማከም።
#የተጎዱትን የአካል ክፍሎች (ኩላሊት፣ ጉበት) ድጋፍ መስጠት።
በጣም #አስፈላጊው ነጥብ
-) የግል መከላከያ ቁሳቁስ (PPE): የጤና ባለሙያዎች የታመሙ ሰዎችን ሲያክሙ ጓንት፣ ጋውን፣ ጭንብል እና የዓይን መከላከያ የግድ መጠቀም አለባቸው።
_) ንጽህና: እጅን በአግባቡ በሳሙና መታጠብ፣ በተለይ የታመመ ሰው የነካን ወይም የጎበኘን ከሆነ።
የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ
1) የዓለም ጤና ድርጅት (World Health Organization - WHO): Marburg Virus Disease (MVD)
2) የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከላት (Centers for Disease Control and Prevention - CDC : Marburg Hemorrhagic Fever (Marburg HF)
ባምላኩ አበባው
ፕሮፌሽናል ነርስ እና የማህበረሰብ ጤና ባለሞያ
ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከል
❤ 89👍 3😱 2
የጤና ሚኒስቴር ተከናዉኗል ባለዉ የዘረመል ምርመራ፣ ቀደም ሲል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጅንካ ከተማ መከሰቱ የተገለጸው የሄሞራጅክ ፊቨር በሽታ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን ማረጋገጡን አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ተደርጓል ባለዉ ምርመራ ከቀናት በፊት በበሽታዉ መጠርጣራቸዉን ካሳወቀዉ 8 ሰዎች ዉጪ አዲስ በበሽታው የተጠረጠረ አለመገኘቱን ገልጿል።
ቫይረሱን የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎችን ለማጠናከር የተለያዩ የሙያ ስብጥር ያካተተ ከፍተኛ ፈጣን ምላሽ ሰጭ ቡድን ወደ ክልሉ መላኩን ጠቁሟል።
በምርመራው መሰረት፣ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኘው የቫይረስ ዝርያ ከዚህ በፊት በሌሎች ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ላይ ከተከሰቱት ጋር ተመሳሳይ ዝርያ ያለው መሆኑ ታውቋል።
ይህን ተከትሎ በሃገር አቀፍ እንዲሁም በክልል ደረጃ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች የክስተት አስተዳደር ስርዓት (IMS) ተቋቁሞ የምላሽ ስራዎች እየተስተባበሩ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል።
በ ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም የሚመራዉ የአለም ጤና ድርጅት በጂንካ አካባቢ የተከሰተውን ወረርሽኝ ለመከላከል 300 ሺህ ዶላር ከድርጅቱ አስቸኳይ ፈንድ በኩል መልቀቃቸውን መግለፃቸው ይታወሳል።
❤ 56🥰 3👎 2👏 2
የቴሌቪዥን ስርጭት መቋረጥ!!
የሳተላይት አቅራቢ ድርጅት በሆነው SES የቴሌ ፖርት ላይ እስራኤል አካባቢ ባጋጠመው ከፍተኛ የአየር ፀባይ ለውጥ ምክንያት የኃይል መቋረጥ ተፈጥሯል፡፡
በዚሁ ምክንያት የአብዛኛዎቹ የሀገራችን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ስርጭት ተቋርጧል፡፡
አገልግሎቱን ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ጣቢያዎቹ ገልፀዋል፡፡
❤ 28😁 6🙏 5👏 1
#Hemorrhagic_Fever ምንድን ነው?
ይህ በሽታ በቫይረስ የሚከሰት ከባድ የበሽታ ቡድን ነው ። በሽታው በመሰረቱ የደም መፍሰስን ወይም የደም መርጋትን በሰውነት ውስጥ የሚያመጣ ነው ። በርካታ የሰውነት አካላትን በማጥቃት እና በሰውነት ውስጥ ያሉ የደም ሥሮችን የሚጎዳ ፣ በተለያዩ ቫይረሶች የሚመጣ በሽታ ነው።
#የበሺታው_መንስኤ እና የቫይረስ ዓይነት
. Ebola and ,Rift Valley Fever (RVF) & Yellow Fever ተብሎ የሚከፈል ሲሆን እንደ #ኢቦላቫይረስ ፣#ደንጉ እና #የለውፊቨር የተባሉ ቫይርሶች የበሺታው መንስኤ ሲሆኑ #በትንኝ ንክሻም የሚመጡ ናቸው ።
በሽታው ስሙ እንደሚያመለክተው በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ደም እንዲፈስ በማድረግ ለሞት የሚዳርግ ህክምና አልባ አደገኛ በሺታ ነው።
በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ደም መድማት እና መፍስሥ ከተከሰተ የበሽታው ከባድ ደረጃ ምልክት ነው።
በሽታው እንዴት ይተላለፋል?
1· ከተያዙ እንስሳት ጋር በመነካካት፡ በእንስሳት (ለምሳሌ አይጥ) ፣ ሽንት፣ ምራቅ ፣ ወይም ሌሎች ከሰውነት የሚለቀቁ ፈሳሾች በሚነካኩበት ጊዜ።
2· በነፍሳት ንክሻ፡
3· ከሰው ወደ ሰው፡ ከተያዘ ሰው የሚገኘው ደም፣ ምራቅ፣ የሰውነት ፈሳሾች ወይም ሌሎች ክምችቶች በቀጥታ በሚነካኩበት ጊዜ። ይህ ለበሽታው ከባዱ እና ዋነኛው ዓይነት የመተላለፊያ መንገድ ነው።
#የበሽታው_ምልክቶች
ምልክቶቹ በድንገት ሊታዩ እና በፍጥነት ሊባባሱ ይችላሉ። አንድ ሰው በቫይረሱ በተጠቃ ከ 2-21 ቀናት ውስጥ ምልክቶቹ መታየት ይጀምራሉ
መጀመሪያ ላይ የሚታዩ ምልክቶች
ምልክቶቹን በሁለት ከፍሎ ማየት የሚቻል ሲሆን
የመጀመሪው ቀለል ያሉ ምልክቶች እና የመጨረሻው አደገኛ //አስጊ ደረጃ ላይ ሲደርስ የሚታዩ ናቸው
#የመጀመሪያ_ምልክቶች
· ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት (ትኩሳት)
· ድካም እና የመዛል ስሜት
· የጡንቻ፣ የአጥንት ህመም እና ቁርጥማት
· ራስ ምታት
· የጉሮሮ ህመም
#ከባድ_ምልክቶች (በሽታው እየተባባሰ ሲሄድ)፡
· በቆዳ ስር ደም መውጣት
. ከአፍ፣ አፍንጫ፣ ከዓይን ወይም ከጆሮ ደም መፍሰስ።
· የጭንቅላት አዕምሮ መናጋት ፣ መደንገጥ፣
. ራስን መሳት ኮማ ውስጥ መግባት)
· የኩላሊት እና የጉበት መጎዳት እና ስራ ማቆም
· ከፍተኛ ድካም እና ሾክ/Shock
· የበርካታ አካላት አለመሥራት
እንዴት መከላከል ይቻላል ?
በሽታው በትንኝ ንክሻ አማካኝነት የሚተላለፍ በመሆኑ #የአልጋ_አጎበርን ነፍሶን ከሞት መታደግ ስለሆነ በአግባቡ ይጠቀሙት ። ከታማሚ ሰው ጋር ያልዎትን ንክክ መከላከል እና
አፋጣኝ አስፈላጊ የህክምና እርዳታ ማግኘት አስፈላጉ ሆኖ ፣በሺታውን ሙሉበሙሉ ማዳን የሚችል ህክምና የለም ፣
መከላከል ብቸኛው ቁልፍ መንገድ ነው !
የሚከተሉትን ማድረግ ያስፈልግዎታል !!
1. እጆችዎን በንፅህና ይታጠቡ፡ በሳሙና እና በንጹህ ውሃ ዘወትር ማጠብ አስፈላጊ ነው።
2. ከሌሎች ሰዎች (ክምችቶች) ራስዎን ይጠብቁ፡ ከሰዎች ደም፣ ምራቅ ወይም ሌሎች ከሰውነት የሚለቀቁ ፈሳሾች ንክኪዎች ራስዎን ይጠብቁ። ይህ ለቤተሰብ አባላት እና በተለይም ለህክምና ባለሙያዎች እጂግ አስፈላጊ ነው።
ብዙ የህክምና/ጤ ና ባለሙያዎች ህይወታቸውን የሚያጡበት ወረርሺኝ ነው።
3. ከእንስሳት ይራቁ፣ አይጦችን እና ሌሎች እንስሳት ከቤትዎ አርቀው ያቆዩ። የሚታወቁ የእንስሳት ክምችቶች ባሉበት ስፍራ ጥንቃቄ አይለይዎት
4.ከ ነፍሳት ይጠበቁ ፣ አጎበር መጠቀም፡ ነፍሳት እና ወረርሽኙ ወደተከሰተበት ቦታ ፈጽሞ አይሂዱ ፣
❤ 47👍 6😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ልዑካን ቡድን፤ የኢትዮጵያ የተራዘመ የብድር አቅርቦት (ECF) አራተኛ ዙር ግምገማ፤ በባለሙያዎች ደረጃ ከስምምነት ለመድረስ የሚያስችል “አዎንታዊ እርምጃ” ማሳየቱን አስታወቀ።
በአራተኛው ዙር ግምገማ ላይ የሚደረገው ውይይት በመጪዎቹ ሳምንታት እንደሚቀጥል የልዑካን ቡድኑ መሪ አልቫሮ ፒሪስ ገልጸዋል።
የአይ ኤም ኤፍ ልዑካን ቡድን ይህን የገለጸው፤ ከጥቅምት 20 እስከ ዛሬ ሐሙስ ህዳር 4፤ 2018 በአዲስ አበባ ጉብኝት ካደረገ በኋላ ባወጣው አጭር መግለጫ ነው። የልዑካን ቡድኑ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ጨምሮ ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር “ውጤታማ ውይይቶች” ማድረጉን አስታውቋል።
ባለሙያዎቹ ከባንኮች እና የግል ኩባንያዎች ጋር ጭምር መገናኘታቸው በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል። ውይይቶቹ የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት 3.4 ቢሊዮን ዶላር የሚበደርበት ስምምነት አፈጻጸምን የተመለከቱ ናቸው።
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ይህንን የተራዘመ የብድር አቅርቦት ያጸደቀው በሐምሌ 2016 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ ከዚህ ቀደም በባለሙያዎች ያደረጋቸው ሶስት ግምገማዎችን መሰረት በማድረግ፤ 851.7 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለኢትዮጵያ መንግስት ለቅቋል።
❤ 35👎 4🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
በጂንካ ከተማ በሄሞሬጅክ ፊቨር በሽታ እስካሁን የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል
#Ethiopia | በጂንካ ከተማ በሄሞሬጅክ ፊቨር በሽታ በግምት ከ20 ቀናት በፊት በጠና ታሞ የሞተን አንድ ግለሰብን ጨምሮ 6 ወንዶች ህይወታቸዉ ማለፉን የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቢንያም አስራት ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
ህይወታቸዉ ካለፈ ሰዎች መካከል ከ20 ቀናት በፊት በጠና ታሞ የነበረዉን ግለሰብ ሲያስታምሙ የነበሩ ዶክተር እና ነርስ እንደሚገኙበት ዶክተር ቢንያም አክለዋል ።
ከግለሰቡ ጋር ግንኙነት የነበራቸዉ አራት ሰዎች በሳምንት ጊዜ ዉስጥ ራስ ምታት ፣ትኩሳት ፣ማስመለስ ፣ድካም እና የማስቀመጥ ምልክት አሳይተዉ በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ክትትል ሲደረገላቸዉ የቆየ ሲሆን የተደረገላቸዉ የኩላሊት ምርመራ ዉጤት ከፍ ያለ ነበር ያሉት ዳይሬክተሩ በአንድና ሁለት ቀን ልዩነት የጤና ሁኔታቸዉ ተባብሶ ህይወታቸዉ ማለፉን ገልፀዋል ።
ከአራቱ አንዱ ወደ ሀዋሳ ሪፈር ተደርጎ ክትትል እየተደረገለት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የተሻለ ሁኔታ ላይ መሆኑ ተገልጿል ። እስካሁን ባለዉ ስምንት ሰዎች በበሽታዉ ተጠርጥረዋል ።
ምልክት ከታየበት ማንኛውም ሰው ጋር ንክኪ በሚኖርበት ጊዜ ራስን የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም ፣ሁልጊዜ እጅን በሳኒታይዘር ወይም በውሃና በሳሙና በመታጠብ ማጽዳት ያስፈልጋል ተብሏል።
የጤና ሚኒሰቴር ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተመዘገበውን ይህንን የበሽታ መንስኤ ለማወቅ እና ተጨማሪ ስርጭትን ለመግታት እንዲሁም ለመቆጣጠር ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን ወደቦታው መላኩን ተገልጿል፡፡
❤ 67😢 17🙏 1
ጥር 30/ 2016 ዓ.ም ቀን በደላንታ ወረዳ በ021 ቀበሌ የኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ የነበሩ ወጣቶች ጉድጓዱ በመደርመሱ ምክኒያት ተዳፍነው የቀሩት በርካታ ወጣቶች አፅም መገኘቱ ተሰማ!
በደላንታ ወረዳ በ021 ቀበሌ ልዮ ቦታው ቆቅ ውሃ ተብሎ በሚጠራው የኦፓል ማውጫ ቦታ ላይ ጥር 30/ 2016 ዓ.ም ሃሙሰ ቀን ከሌሊቱ 6:00 የኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ የነበሩ ወጣቶች ጉድጓዱ በመደርመሱ ምክኒያት በርካታ ወጣቶች ተዳፍነው የቀሩ መሆኑ ይታውቃል። የወጣቶቹን ህይዎት በህይዎት ለመታደግ መንግስት የተለያዩ ጥረቶችን ቢያደርግም ወጣቶቹን ከተዳፈኑበት ማውጣት አልተቻለም ነገር ግን በዛሬው እለት ከዓመታት ቆይታ ብኋላ ማዕድን በማውጣት ላይ የነበሩ ወጣቶች አፅማቸውን ያገኙ መሆኑን መረጃው ደረሶናል ሲል ወረዳው አስታውቋል።
በመሆኑም የወረዳው መንግስት በተገኘው መረጃ መሰረት አፅሙን ለማውጣት የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹን እየሰራ ይገኛል ብሏል።
ህዳር 4/2018 ዓ.ም
ደላንታ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
❤ 42😢 38👎 1🤯 1
Photo unavailableShow in Telegram
የውጭ ትምህርት ቤቶች 30% ከሀገራቸው መንግሥት ድጋፍ ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ የሚያስገድድ ረቂቅ ደንብ ይፋ አደረገ
ትምህርት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት የሚመሩበትን አዲስ ረቂቅ ደንብ ማዘጋጀቱን ያስታወቀ ሲሆን፣ ረቂቁ በተለይ በውጭ ሀገር ማኅበረሰቦች ለሚቋቋሙ ትምህርት ቤቶች አስገዳጅ መስፈርቶችን አኑሯል።
ካፒታል የተመለከተዉ ረቂቅ ደንቡ እንደሚያስገድደው፣ በውጭ ሀገር ማኅበረሰብ የተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች ከጠቅላላ በጀታቸው ውስጥ 30% (ሰላሳ በመቶ) የሚሆነው ከሀገራቸው መንግሥት ድጋፍ ማግኘታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ቀሪውን 70% ደግሞ ራሳቸው መሸፈን የሚችሉ መሆናቸውን የሚያሳይ ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ ግዴታ ተጥሏል።
ይህ የፋይናንስ ማረጋገጫ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና አግባብ ባለው የሰነዶች ማረጋገጫ ባለሥልጣን ተረጋግጦ መቅረብ እንዳለበት ደንቡ ያመለክታል።
በዚህ ለትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት አስተያየት ክፍት በተደረገዉ አዱሱ ረቂቅ ደንብ፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት የአገሪቱን የትምህርት ሕግ፣ የመምህራን ብቃት፣ የተማሪዎች መብት እና የትምህርት ደረጃን ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ ሕጎችን ማክበር ይጠበቅባቸዋል።
በዚህ ደንብ ላይ እንደተገለፀዉ ፤ተቋማቱ የራሳቸው የሆነ የገንዘብ ምንጭ (ከተማሪዎች ክፍያ፣ ከስጦታ ወይም ከኢንቨስትመንት ትርፍ) እና ነጻ አስተዳደር ያለው ድርጅታዊ አወቃቀር ሊኖራቸው ይገባል።
ረቂቅ ደንብ ላይ ሚኒስቴሩ ተቋማት ሊያስከፍሉት የሚችሉትን የትምህርትና ሌሎች አገልግሎት ክፍያዎችን ጣሪያ በተመለከተ መመሪያ እንደሚያወጣና በየሦስት ዓመቱ እንደሚስተካከል ደንግጓል። የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ ከ3 ወራት በፊት ተጠቃሚዎችን ማወያየት እንደሚኖርባቸው ያስገድዳል።
❤ 38🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴምርፕሮፐርቲስ #እነሆ_አዲስሳይት
📍 ሳር ቤት
#በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ)
👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን
👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 11.4ሚሊዮን
#በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን)
👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን)
📍 አዋሬ
#በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ)
👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 145ካሬ = 10.3ሚሊዮን
#በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 78ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.7ሚሊዮን)
👉135 ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 14.8ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.9ሚሊዮን)
⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን!
+251964439488
+251907232222
Telegram: https://t.me/OusmanTemer
WhatsApp: https://wa.me/251964439488
❤ 18👍 2😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
የቀድሞው ሰላም ዴኤታ ሚኒስቴር አቶ ታዬ ደንደአ ዛሬ በዋለው ችሎት በሁለቱ ክሶች ነጻ ተባሉ
በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ጸረ ሽብር ችሎት በዛራ ውሎው፤ "ከጠላት ጋር መተባበር" በሚል በአንቀፅ 251(ሐ)፣ መገፋፋትና ግዙፋዊ መሰናዳት አንቀፅ 257(ሰ) እንዲሁም፤ የፀና ፍቃድ ሳይኖር የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት በሚል ሦስት ተደራራቢ ወንጀሎች ተከሰው በክርክር ሂደት ላይ እንደነበሩ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ፤ የቀድሞ የሰላም ሚንስቴር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአን መዝገብ ሲመረምር የነበረው 1ኛ የፀረ-ሽብር እና ሕገመንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ዛሬ ሕዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ባስተላለፈው ውሳኔ 'ተከሳሹ ከተጠረጠሩበት ወንጀል ነጻ ናቸው' ብሏል።
ጠበቃቸው አበራ ንጉሥ በሁለቱም የመጀመሪያ ክሶች ባቀረቡት የሰው፣ የሰነድ እና የቪዲዮ ማስረጃዎች በበቂ ሁኔታ ተከላክለዋል በማለት በአብላጫ ድምፅ በነፃ እንዲሰናበቱ ፍርድ መሰጠቱን የገለጹ ሲሆን፤ በ3ኛ ደረጃ ለቀረበባቸው የፀና ፍቃድ ሳይኖር የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ግን 'ባቀረቧቸው ማስረጃዎች በበቂ ሁኔታ ማስተባበል አልቻሉም' በማለት የጥፋተኝነት ፍርድ በሙሉ ድምፅ ሰጥቷል ብሏል።
እንዲሁም ጥፋተኛ በተባሉት አንድ ክስ የቅጣት አስተያየት ለመስማት ለሕዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል ሲሉ ጠበቃቸው አበራ ንጉስ ተናግረዋል።
❤ 66😁 17🤔 2👍 1😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
#የተፈቀደላቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችን አገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
❤ 26
ኢትዮጵያ በ2027 COP32 ጉባዔን እንድታስተናግድ ተሳታፊ ሀገራት ተስማሙ
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2027 የሚካሄደውን የዓለም የአየር ንብረት ጉባዔን (COP32) በአዲስ አበባ እንድታስተናግድ የጉባዔው አባል ሀገራት በመርሕ ደረጃ መስማማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የዘንድሮው የCOP30 ጉባዔ ፕሬዚዳንት አንድሬ ኮሪያ ለሮይተርስ እንደተናገሩት፥ ኢትዮጵያ ዛሬ ምሽቱን የ2027 አስተናጋጅ ሆና ይፋ እንድትደረግ ሀገራት በመርሕ ደረጃ ተስማምተዋል።
ኢትዮጵያ ባሳለፍነው መስከረም ወር ጉባዔውን የማስተናገድ ፍላጎቷን ይፋ ያደረገች ሲሆን፤ የአፍሪካ ሀገራትም ኢትዮጵያ በ2027 የሚካሄደውን የዓለም የአየር ንብረት ጉባዔ (COP32) እንድታስተናግድ በሙሉ ድምጽ መስማማታቸውም ነው የተዘገበው።
የቀጣዩ ዓመት የዓለም የአየር ንብረት ጉባዔ (COP31) አስተናጋጅ ሀገር ማንነት አሁንም ያልተለየ ሲሆን፤ አውስትራሊያ እና ቱርክ ጉባዔውን ለማስተናገድ ጥያቄ አቅርበዋል።
አውስትራሊያ የCOP31 ጉባዔን ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ ከሆኑ ቦታዎች መካከል ቀዳሚ ከሚባሉት የፓሲፊክ ደሴቶች ጋር በመተባበር ለማዘጋጀት ማለሟን አስታውቃለች።
❤ 67😁 3👍 2👎 2🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴምርፕሮፐርቲስ #እነሆ_አዲስሳይት
📍 ሳር ቤት
#በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ)
👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን
👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 11.4ሚሊዮን
#በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን)
👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን)
📍 አዋሬ
#በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ)
👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 145ካሬ = 10.3ሚሊዮን
#በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 78ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.7ሚሊዮን)
👉135 ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 14.8ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.9ሚሊዮን)
⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን!
+251964439488
+251907232222
Telegram: https://t.me/OusmanTemer
WhatsApp: https://wa.me/251964439488
❤ 17😱 4👍 1🥰 1
ጌትነት እንየው አምስት ሚሊዮን ብር እና BYD መኪና ተሸለመ።
የሁለገቡ ከያኒ ጌትነት እንየው የ68ኛ አመት የልደት በአልና የ43 ዓመታት የሙያ አገልግሎት የምስጋና መርሐ-ግብር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ተከብሯል።
ተስፋ የኪነጥበብ ኢንተርፕራይዝ ባዘጋጀው እና በርካታ የጥበብ ቤተሰበች በተገኙበት ልዩ የምስጋና መርሐ-ግብር ላይ አቢሲኒያ ባንክ ለከያኒ ጌትነት እንየው የ5 ሚሊዮን ብር ስጦታ አበርክቶለታል። ከዚህ በተጨማሪም ሌላኛው ተቋም ሀበሻ ቢራ አ.ማ የ2025 አዲስ BYD መኪና በስጦታ አበርክቶለታል።
ለአርባ ሶስት አመታት የሰራበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ካባ ያለበሰው ሲሆን አቢሲኒያ ባንክ በቅርቡ በ ባህርዳር ከተማ የሚከፍተውን ቅርንጫፍ ባንክም በጌትነት እንየው ስም መሰየሙን ይፋ አድርጓል። በዚህ ታላቅ መርሐ-ግብር ላይ ከያኒውን የሚዘክሩ ዝግጅቶች እና ምስክርነቶች ቀርበዋል።
Via: በፍቃዱ አባይ
❤ 110👍 20🤔 10👎 3👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ በዩኔስኮ የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል ሀገር ሆና ተመረጠች
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል ሀገር ሆና ተመርጣለች።
ኢትዮጵያ በሳማርካንድ፣ ኡዝበኪስታን እየተካሄደ በሚገኘው 43ኛው የዩኔስኮ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል ሀገር ሆና የተመረጠችው፡፡
የሥራ አስፈፃሚ ቦርዱ ከጠቅላላ ጉባኤው እና ሴክሬታሪያት በተጨማሪ በዩኔስኮ ከሦስቱ መሠረታዊ አካላት አንዱ ሲሆን፣ በጠቅላላ ጉባኤው ይመረጣል።
በጠቅላላ ጉባኤው ሥልጣን ስር የሚሰራው ቦርዱ ለተቋሙ የሥራ መርሐ-ግብር እና በዋና ዳይሬክተር የቀረበለትን ተጓዳኝ የበጀት ግምት በመመርመር ከውሳኔዎቹ ጋር ለጠቅላላ ጉባኤ እንደሚያቀርብ ተጠቁሟል።
ቦርዱ እያንዳንዳቸው የአራት ዓመት የሥራ ዘመን ያላቸው 58 አባል ሀገራትን ያቀፈ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም እስከ ጎርጎሮሳውያኑ 2029 በቦርድ አባልነቷ ከሌሎች ሀገራት ጋር በቅንጅትና በአብሮነት ለጋራ ውጤት እንደምትሰራ ተመላክቷል።
ኢትዮጵያ በቦርድ አባልነት መመረጧ እንደ ሀገር ብሎም እንደ አህጉር የኢትዮጵያንና የመላው አፍሪካን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና ከዩኔስኮ ዓላማና ተልዕኮ አንፃር በባለብዙ መድረኮች ድምጿን ለማሰማት መልካም አጋጣሚን እንደሚፈጥር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
❤ 96😁 15👏 6👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የኢትዮጵያ መንግሥት የድሮን ጥቃት በመፈጸም በትግራይ ኃይሎች አባላት ላይ ጉዳት ማድረሱን ገለጸ።
ህወሓት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ የትግራይ ክልል ከአፋር ጋር በሚዋሰንበት አካባቢ አርብ ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም. ስለተፈጸመው የድሮን ጥቃት ዝርዝሩን ባይገልጽም ጉዳት መድረሱን አመልክቷል።
ይህ የድሮን ጥቃት በአካባቢው በነበሩ የትግራይ ሠራዊት አባላት እና ነዋሪዎች ላይ ጉዳት አድርሷል ያለው መግለጫው፣ ይህ የድሮን ድብደባ ፕሪቶሪያ ስምምነትን ሙሉ በሙሉ የጣሰ እና የከፋ አደጋ ውስጥ የከተተ ነው ብሏል።አንድ ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ የህወሓት ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንደተናገሩት በሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃቱ የተፈጸመው ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ነው።
ባለሥልጣኑ ጥቃቱ የተፈፀመው በትግራይ እና አፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢ በሚገኝ ሚልካ በሚባል ወታደራዊ ካምፕ ላይ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል።
ህወሓት በመግለጫው በኃይሎቹ ላይ ጉዳት መድረሱን ብቻ የጠቀሰ ሲሆን፣ ወታደራዊ ባለሥልጣኑ ግን "አነስተኛ" ያሉት ጉዳት መድረሱን ለቢቢሲ ተናግረዋል።ቢቢሲ ጥቃቱን በተመለከተ ከኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት እንዲሁም ከፌደራል መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት በስልክ እና በጽሁፍ መልዕክት አስተያየት ለማግኘት ቢሞክርም ምላሽ አላገኘም።
ህወሓት ባወጣው መግለጫ "በትግራይ ሕዝብ ሞት እና ስቃይ የሚረካው የኢትዮጵያ መንግሥት የፕሪቶሪያ ስምምነትን ወደ መጣስ ተሸጋግሯል'' በማለት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተጨማሪ ደም መፋሰስ እንዳይመጣ የበኩሉን ይወጣ ሲል ጠይቋል።(bbc)
❤ 69👎 24👍 7😢 4😁 2👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ የታሪፍ ቅነሳ የሚደረግላቸውን 24 የአፍሪካ ሀገራት ይፋ አደረገች
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስር የታሪፍ ቅነሳ የሚደረግላቸው ሀገራትን ዝርዝር ይፋ አደረገች፡፡
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ግብፅን ጨምሮ በቀጣናዊ የገበያ ትስስሩ ለታሪፍ ቅናሹ ብቁ የሆኑ 24 የአፍሪካ ሀገራት ይፋዊ ዝርዝር ለሁሉም የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችና ለጉምሩክ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና አስተዳደር ማዕከል አሳውቋል ተብሏል፡፡
ከፀደቁት አባል ሀገራት በሚመጡ እቃዎች ላይ ውሳኔ የተደረሰበትን የታሪፍ ቅናሽ ተግባራዊ ማድረግ እንዲጀመርም መመሪያ ሰጥቷል።
በዚህ መሰረት የታሪፍ ቅናሽ የሚደረግላቸው ከምስራቅ አፍሪካ ሰባት ሀገራት፣ ከደቡብ አፍሪካ ስምንት ሀገራት፣ ከሰሜን አፍሪካ አራት ሀገራት፣ ከምዕራብ አፍሪካ ሦስት ሀገራት፣ እንዲሁም ከመካከለኛው አፍሪካ ካሜሩን ይገኙበታል ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ስር መስከረም 29 ቀን 2018 በይፋ ግብይት መጀመሯ የሚታወስ ነው፡፡#Ethio fm
❤ 60👍 8🤔 3👎 2😱 1😢 1
