es
Feedback
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

Ir al canal en Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

Mostrar más
2025 año en númerossnowflakes fon
card fon
166 293
Suscriptores
-1724 horas
-227 días
-430 días
Archivo de publicaciones
​​​ሕዳር ሚካኤል ! እንኳን ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሲመት በሠላም አደረሰን ! በዓለ ሲመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል (አንብባችሁ ስትጨርሱ ለሌሎችም ታሪኩን እንዲያዉቁ #SHARE ብታደርጉ ብዙ አተረፋችሁ፡፡) ቤተ ክርስቲያን ልጆቹዋ የመላእክትን ተራዳኢነት አውቀው እንዲጠቀሙና የመንግሥቱ ወራሾች ለመሆን እንዲበቁ ስትል ለቅዱሳን መላእክት የመታሰቢያ ቀን በመስጠት በእነርሱ የምናገኛቸውን እርዳታዎች እንዲታወሱ ታደርጋለች፡፡ በዚህም መሠረት በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል። ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በተሰኘው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ ዲያብሎስ ይዋጋው፣ በጸሎትም ይራዳቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ኃጢአት ሠርተው ሲያገኛቸው ለእግዚአብሔር አድልቶ ኃጢአተኞችን ስለሚቀጣ እግዚአብሔር ሕዝቡን “በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት” (ዘጸ.23፡21) ብሎ አስጠንቅቋቸው ነበር፡፡ ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን ያስረዳናል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች ሕዝበ እስራኤልን ይራዳቸው የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ አያረጋግጥም የሚል ካለ “መልአክ” የተባለው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ነቢዩ ዳንኤል በተላከ ጊዜ ገልጦልን እናገኛለን፡- ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ስለመሾሙ ሲመሰክር “በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም የለም”(ዳን.10፡21) ብሎአል፡፡ ስለዚህም ለኢያሱ የተገለጠውና እስራኤላውያንንም የመራው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን፡፡ #ይቀጥላል ....... 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
224🕊 14
ውእቱ ሚካኤል.mp33.86 MB
130🥰 3
ውእቱ (2).mp33.47 MB
97🥰 14
እግዚኡ ረሰዮ.mp32.16 MB
104🥰 11
አንተኑ ሚካኤል.mp32.33 MB
115😍 10
ንግረኒ.mp32.11 MB
96🥰 11
ተወከፍ.mp33.24 MB
87🥰 9
ባሕረ ግርምተ.mp32.90 MB
88🥰 10
በገዳም.mp32.10 MB
89🥰 9
ረደኤ ምንዱባን.mp31.96 MB
86🥰 9
ሰፊሖ ክነፊሁ.mp33.28 MB
91🥰 7🔥 1
የኅዳር ቅዱስ ሚካኤል ማኅሌት ++++ ሰላም ለጒርዔክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ፤ ብዑላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ ፤ እመትትኃየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ፤ ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ሥጋየ ጌሠ ፤ ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ ። ዚቅ አመ ይፈጥራ እግዚአብሔር ለምድር፤ ኢዜነዎ ለሰማይ፤ ወኢተማከረ ምስለ መላእክቲሁ፤ ወተከለ ፫ተ ዕፀ ሕይወት በዲበ ምድር ። ነግሥ ጎሥዓ ልብየ ጥበበ ወልቡና፤ ለውዳሴከ ጥዑመ ዜና፤ ቅዱስ ሚካኤል ልማድከ ግብረ ትኅትና፤ አንተኑ ዘመራኅኮሙ ፍና፤ ወአንተኑ ለእስራኤል ዘአውረድከ መና ። ወረብ አንተኑ ሚካኤል መና መና ዘአውረድከ፤ ወአንተኑ ለእስራኤል መና ዘአውረድከ። ዚቅ አዝነመ ሎሙ መና ይብልዑ፤ ፀዓዳ ከመ በረድ፤ ወርእየቱ ከመ ተቅዳ፤ ኅብስተ እምሰማይ ወሀቦሙ፤ አውኃዘ ሎሙ ማየ ህይወት፤ ዘትረ ኮኲሕ ፈልፈለ ነቅዕ ዘኢይነጽፍ፤ ኅብስተ እምሰማይ ወሀቦሙ። ፫. ነግሥ / ዘመንክር ጣዕሙ / ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ። ዚቅ፦ ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ቃልኪ አዳም ይጥዕመኒ እምአስካለ ወይን፤ አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናገሮ በዓምደ ደመና፤ እሞሙ ይእቲ ለሰማዕት እኅቶሙ ለመላእክት፤ አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናገሮ በዓምደ ደመና ። ለዝክረ ስምከ / መልክአ ሚካኤል / ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ፤ ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ፤ ሶበ እጼውዕ ስመከ ከሢትየ አፈ፤ ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ፤ ለረዲኦትየ ነዓ ሰፊሐከ ክንፈ። ወረብ ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል ረዳኤ ምንዱባን፤ በከመ ከመ ታለምድ ዘልፈ። ዚቅ ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይል፤ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤ ይስአል ለነ ረዳኤ ይኲነነ አመ ምንዳቤነ፤ ሰፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ ። ወረብ ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይል ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤ ይስአል ለነ አመ ምንዳቤነ ይስአል ሰፊሆ ክነፊሁ። ለልሳንከ / መልክአ ሚካኤል / ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተሀበለ፤ በእንተ ሥጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበሀለ፤ ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ፤ ቀዊምየ ቅድመ ሥዕልከ ሶበ አወትር ስኢለ፤ በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ። ወረብ ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስኢለ፤ በብሂለ ኦሆ በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ። ዚቅ ረሰዮ እግዚኡ ለውእቱ ሚካኤል፤ እምኲሎሙ መላእክት ይትለዓል መንበሩ፤ ስዩም በኀበ እግዚኡ ምእመን። ወረብ እግዚኡ ረሰዮ ለውእቱ ሚካኤል፤ እምኲሎሙ መላእክት መላእክት ይትለዓል መንበሩ። ለኅንብርትከ / መልክአ ሚካኤል / ሰላም ለኅንብርትከ ኅንብርተ መንፈስ ረቂቅ፤ ዘቱሣሔሁ መብረቅ፤ ነግሀ ነግህ አንተ በአዝንሞ መና ምውቅ፤ በገዳም ዘሴሰይኮሙ ለነገደ ኅሬ ደቂቅ፤ ሴስየኒ ሚካኤል ሕገከ በጽድቅ። ወረብ በገዳም በገዳም በገዳም ዘሴሰይኮሙ፤ ለነገደ ለነገደ ኅሬ ደቂቅ። ዚቅ ባሕረ ግርምተ ገብረ ዓረፍተ፤ ወበውስቴታ አርዓየ ፍኖተ፤ በእደ መልአኩ አቀቦሙ በገዳም ለሕዝቡ አርብዓ ዓመተ፤ ወሴሰዮሙ መና ሕብስተ፤ ኪነ ጥበቡ ዘአልቦ መሥፈርተ። ወረብ ባሕረ ግርምተ ዓረፍተ ገብር አርአየ ፍኖተ እግዚአብሔር በእደ መልአኩ አቀቦሙ ለእስራኤል አርብዓ ዓመተ ለሕዝቡ በገዳም/፪/ አምኃ ሰላም / መልክአ ሚካኤል / አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክእከ ኲሉ፤ ለለአሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ፤ ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ፤ ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኀ ሰማያት ዘላዕሉ፤ ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ። ዚቅ ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኃ ሰማይ፤ ወስእለተነ ከመ መዓዛ ሠናይ፤ ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኃ ሰማይ። ወረብ ተወከፍ ጸሎተነ ጸሎተነ ውስተ ኑኀ ሰማይ፤ ወስእለተነ ከመ መዓዛ ሠናይ ሊቀ መላእክት። አንገርጋሪ + ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይል፤ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤ ይስአል ለነ ረዳኤ ይኲነነ አመ ምንዳቤነ፤ ሰፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ። እስመ ለዓለም ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ አስተምህር ለነ ሰአልናከ በ፲ ወ፬ ትንብልናከ፤ ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ ዓይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ፤ ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ ይሰግድ በብረኪሁ እስከ ይመጽእ ሥርየት ለኃጥአን፤ ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ መኑ ከማከ ክቡር። አቡን (በ፮) ዝስኩሰ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ይስአል ለክሙ ኀበ ንጉሠ ስብሐት ስዮም በኀበ እግዚኡ ምእመን፤ ረሰዮ እግዚኡ ለውእቱ ሚካኤል እምኲሎሙ መላእክት ይትለዓል መንበሩ፤ ስዮም በኀበ እግዚኡ ምእመን፤ በጽሑ መላእክት ወቦሙ መዘምራን ማእከለ ደናግል ዘባጥያተ ከበሮ ስዮም በኀበ እግዚኡ ምእመን። ዓራራይ ሐመልማለ ወርቅ ልብሱ ዘመብረቅ፤ ሚካኤል ሊቅ ሐመልማለ ወርቅ ክነፊሁ ዘእሳት፤ አድኅን እግዚኦ ዛተ ሀገረ ወካልዓተኒ አህጉረ በሐውርተ፤ በኃይለ መላእክቲከ እለ እምዓለም አሥመሩከ ረዳእየ አንሰ ኪያከ ተወከልኩ። ቅንዋት ሚካኤል ብሂል ዕፁብ ነገር መልአከ ኪዳኑ ለእግዚአብሔር፤ ገብርኤል ብሂል ወልደ እግዚአብሔር፤ ወዲበ ርእሱኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል። ሰላም መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዐቢይ። +++ ወረቦቹ የመምህር ዕንቈ ባሕርይ ተከስተ ናቸው
Mostrar todo...
138🥰 4🔥 1
ኢየሱስ ጥዑም ስምከ ኢየሱስ ጥዑም ስምከ ማዳንህ የተሰበከ መውደድህ ስንቱን ማረከ አኮቴት ስብሐት ለከ ምስጋና ለአንተ/2/ ስብሐት ለከ
አዝ
ኢየሱስ የማትታሰር ለትውልድ የምትነገር ቀዳሴ ነፍስና ሥጋ ለሊቱን የምታነጋ
አዝ
ከሌዊ የተወለደ ሰረጸ እምቤተ ይሁዳ ተረፈ ዓለም በሙሉ ማዳኑን ስለተረዳ
አዝ
ጨለማ የታል ጨለማ የኢየሱስ ሞገስ ሲሰማ ይሰግዳል ጉልበት በፊቱ ያቀልጣል ግርማዊነቱ
አዝ
ዮሐንስ አይኑን ሲያነሳ ሲበራ ከመ ጸሐይ ወደቀ እንደሞተ ሰው መቅረዝ ፊት ግርማውን ሲያይ
አዝ
አይኖቹ እንደነበልባል ይጠራል ይመረምራል እግሮቹ የጋለ ናስ የጠፋን የሚመልስ ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
6082726593_1 (12).mp34.60 MB
133🔥 3🥰 3😍 2
​​ኅዳር ፲፩ /11/ ‎ ‎በዚች ዕለት አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቷ የሆነች የተመሰገነች የቅድስት ሐና የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው ። ‎ ‎ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት ። ለማጣትም ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ያገለገለቻት ናት ። ‎ ‎ሶፍያም ለባል ተድራ ለመጥመቁ ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደቻት ። ይችንም ቅድስት ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙ ኢያቄም ለሚባል አጋቧትና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት እሊህም ሰሎሜና ኤልሳቤጥ ለቅድስት ሐና የእኅትማማች ልጆች ናቸው ። ‎ ‎የዚችንም የቅድስት ሐናን በሥውር የምትሠራውን ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳናስታውሰው አናውቀውም ግን ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እናውቃለን እንረዳለን እርሷ አምላክን በሥጋ ለወለደችው ወላጅዋ ትሆን ዘንድ የተገባት ሁናለችና ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥና የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ታላቅ ጸጋ ባልተገባት ነበር ። ‎ ‎ይህችም ጻድቅት ሐና መካን በመሆንዋ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔርዘወትር በጸሎት ትማልድ ነበር እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችና የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት ። ‎ ‎ስለዚህም ይህን ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት የበዓሏን መታሰቢያ በደስታ ልናከብርይገባናል ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከእኛ ጋርይሁን ለዘላለሙ አሜን ። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
273🕊 22🥰 5
ከደጅህ ስደርስ ከደጅህ ስደርስ ልቤ ይመታል ወደ ማደሪያህ ልቤ ተነስቷል ኦ ጌታዬ ሆይ /3/ ልቤ አንተን ይመኛል
አዝ
ሕይወቴን ለአንተ ልሰጥ መጣሁኝ ለኃጢያቴ ይቅርታ ከአንተ እሻለሁኝ ኦ ጌታዬ ሆይ /3/ መንገድን አሳየኝ
አዝ
የአንተ መንገድ እጅግ ይከብዳል የጽድቅ ፈተና ማለፍ ይጠይቃል ኦ ጌታዬ ሆይ /3/ ጥበቃህ ይደንቃል
አዝ
ደካማ ብሆን በእራሴ ባልችለው አንተ በእኔ ካለህ ድል አደርገዋለው ኦ ጌታዬ ሆይ /3/ አሸንፈዋለው
አዝ
ከደጅህ ስደርስ ልቤ ይመታል ወደ ማደሪያህ ልቤ ተነስቷል ኦ ጌታዬ ሆይ /3/ ልቤ አንተን ይመኛል ዘማሪት ትዕግስት ኃይሌ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
ይህን_ዝማሬ_ስትሰሙ_ማን_ትዝ_ይልዎታል_ከደጅህ_ስደርስ_ዘማሪት_ትዕግስት_ኃይሌ_Ke_Dejeh_S.m4a4.84 MB
95🥰 4🔥 3🕊 2
Repost from TgId: 2150339683
Photo unavailableShow in Telegram
🏵 ሰላም፡ለኵልክሙ። እነሆ ግእዝን በአንድ ወር ልዩ ግእዝን የምንማርበት ዝግጅታችን ተመልሰናል። በግእዝ ቋንቋን ትውልዱ በሚቀለውና ዘመኑን በዋጀ መልኩ በርቀት ትምህርት ለመስጠት ቅድመ ዝግጅታችንን አጠናቀናል። ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመመዝገብ ጥንታዊና ውዱ ቋንቋችንን ዕንወቅ። 📖 ትምህርቱን ከ10 ዓመት ዕድሜ በላይ ለሆኑ ፤  ስልክ ወይም ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ በመጠቀም ሁሉም ሰው መማር ይቻላል
✅ ምዝገባውን ለማካሄድ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በዚህ በመላክ ነው ✅ @Geez180 @Geez180 @Geez180 👈
                 ⛳️ ለበለጠ መረጃ በምዝገባ ቦታ ወይም በአድራሻዎቻችን አግኙን። መማር ለሚፈልጉ ሌሎችም ኦርቶዶክሳውያን ሼር በማድረግ እንጋብዛቸው። ሠናይ፡ጊዜ። @MerfaqeGeez 🏵 ም ር ፋ ቀ ፡ ግ እ ዝ 🏵 0975760575
Mostrar todo...
34🔥 1🥰 1
በልቤ ከተማ በልቤ ከተማ ተመላለስበት ይረጋል ህይወቴ አንተ ስታርፍበት ወደ እልፍኜ ግባ እረፍ በምንጣፌ እንዳመልክህ ጌታ እንባዬን አርግፌ
አዝ
ባለፀጋ ስትሆን ድሆች ከበውሃል ለንግስና ዙፋን አህያን መርጠሃል አጀብ አትፈልግም አውቅሃለሁ ጌታ ብቻህን ነበረ ደጄን ስትመታ ለጠላት አሰራር ዋሻ የሆንኩትን ስራኝ እንደገና ቤተመቅደስህን
አዝ
ድንግዝግዝ ኑሮዬ በምራቅህ ይብራ ጨለማ አይዝህም አንተ ስትሰራ ማረኝ ያሉት እጆች ሲያጨበጭቡልህ ሰምቼ አልቀረሁም በብር አየሁህ ለጠላት አሰራር ዋሻ የሆንኩትን ስራኝ እንደገና ቤተመቅደስህን
አዝ
ማዕበል ህይወቴ ግራ ቀኝ የሚለው እንደምን ይረካል ጌታዬ ሳታዘው ተራመድ በልቤ በሞገስ በግርማ ኢየሱስ ነህ አንተ የምስኪኑ ማማ ለጠላት አሰራር ዋሻ የሆንኩትን ስራኝ እንደገና ቤተመቅደስህን
አዝ
ከያዕቆብ ጉድጓድ ብቀዳም አብዝቼ ዛሬም በጥማት ነኝ ከቶ መች ረክቼ የህይወት ውሃ ምንጭ ነፍስን የምትመልስ በበረሃው ልቤ ለዘላለም ፍሰስ ለጠላት አሰራር ዋሻ የሆንኩትን ስራኝ እንደገና ቤተመቅደስህን ዘማሪ ዕዝራ ኃይለሚካኤል 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
Belibe Ezira Hailemichel.m4a6.13 MB
204🥰 17🕊 13
Repost from TgId: 2150339683
Photo unavailableShow in Telegram
🏵 ሰላም፡ለኵልክሙ። እነሆ ግእዝን በአንድ ወር ልዩ ግእዝን የምንማርበት ዝግጅታችን ተመልሰናል። በግእዝ ቋንቋን ትውልዱ በሚቀለውና ዘመኑን በዋጀ መልኩ በርቀት ትምህርት ለመስጠት ቅድመ ዝግጅታችንን አጠናቀናል። ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመመዝገብ ጥንታዊና ውዱ ቋንቋችንን ዕንወቅ። 📖 ትምህርቱን ከ10 ዓመት ዕድሜ በላይ ለሆኑ ፤  ስልክ ወይም ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ በመጠቀም ሁሉም ሰው መማር ይቻላል
✅ ምዝገባውን ለማካሄድ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በዚህ በመላክ ነው ✅ @Geez180 @Geez180 @Geez180 👈
                 ⛳️ ለበለጠ መረጃ በምዝገባ ቦታ ወይም በአድራሻዎቻችን አግኙን። መማር ለሚፈልጉ ሌሎችም ኦርቶዶክሳውያን ሼር በማድረግ እንጋብዛቸው። ሠናይ፡ጊዜ። @MerfaqeGeez 🏵 ም ር ፋ ቀ ፡ ግ እ ዝ 🏵 0975760575
Mostrar todo...
28🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
‎ኅዳር ፲ /10/
‎ ‎በዚች ቀን ቅዱሳት ንጹሐት መነኰሳይያት ደናግል እናታቸው ሶፍያም በሰማዕትነት አረፉ። እኚህም ቅዱሳት ከተለያዩ አገሮችና ቦታዎች ሲሆኑ መለኮታዊ ፍቅርበአንድነት ሰበሰባቸው የምንኲስናንም ልብስ ለበሱ ይኸውም የመላእክት ልብስ ነው። በሮሜ አገር ከአሉ ገዳማትም በአንዱ የሚኖሩ ሆኑ ቅድስት ሶፍያም በእነርሱ ላይ እመ ምኔት ሆነች። ‎ ‎እርሷም ጸጋንና ዕውቀትን የተመላች ናት የቅዱሳን መነኰሳትን ገድል በማንበብ እየጾሙ እየጸለዩ በምድር ላይ እንደ መላእክት እስከ ሆኑ ድረስ መንፈሳዊ ዕድገትን አሳደገቻቸው ከእነርሱም በአንድ ገዳም ውስጥ ሰባ ዓመት ያህል የኖሩ አሉ ከውስጣቸውም ልጅ እግሮች የሆኑ አሉ። ‎ ‎ከሀዲ ንጉሥ ዑልያኖስም ከፋርስ ንጉሥ ከሳቦር ጋር ሊዋጋ በሮሀ ሀገር በኩል በሚያልፍ ጊዜ እርሱ ሳቦር ሊወጋው ወደርሱ እንደሚመጣ ሰምቷልና አልፎ ሲሔድም በውስጡ እሊህ ደናግል ያሉበትን ገዳም አይቶ ይህ ምንድን ነው ብሎ ጠየቀ ሰዎችም ይህ የደናግሎች ገዳም ነው አሉት። ‎ ‎በዚያንም ጊዜ ወደዚያ ገዳም ገብተው ደናግሎችን እንዲገድሏቸው በገዳሙ ውስጥም ያለ ገንዘባቸውን ሁሉ እንዲዘርፉ ወታደሮቹን አዘዘ ወታደሮችም ገብተው እሊያን ደናግል በሰይፍ ገደሏቸው ገዳሙንም አጠፉ የገዳሙን ገንዘብ ሁሉንም ዘረፉ። ‎ ‎ከሀዲውን ንጉሥ ግን ስለ መንጋዎቹ በቀል እግዚአብሔር ተበቀለው ይህም እንዲህ ነው ያጠፋው ዘንድ ሰማዕት መርቆሬዎስን አዘዘው መርቆሬዎስም በአካለ ነፍስ ሒዶ በጦር ወጋውና በክፉ አሟሟት ሙቶ ወደ ዘላለም ሥቃይ ሔደ። እሊህ ቅዱሳት ደናግል ግን ወደ ዘላለም ተድላ ደስታ ገቡ። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
185🕊 17
ዛሬም አለሽ በልቤ ዛሬም አለሽ በልቤ/3/ ድንግል ሆይ ወለታሽ አይጠፋም ከሀሰቤ
አዝ
እንደ ሀጥያቴ ብዛት እንዴ በደሌማ የጥልቁ ሰንሰለት ሲይንሰኝ ነው ጨለማ ግን ያንች ሆንኩኝና ሁሉንም አለፈኩኝ ያንን የሞት ባህር በምልጃሽ ቀዝፈኩኝ
ዝ አርፏል ልቤ በአንቺ በአዛኝቷ ማርያም ውስጤ እያፈሰሰ ፍቅርና ሠለም ህመሜም ቢያስረሳኝ የወዳሴሽ ቃና እመቤቴ እላለሁ ዛሬም እንደገና
አዝ
እናታችን ፅዮን ሰው ሁሉ ይልሻል ዳዊት በበገና ያመሰግንሻል የአሴቦን ነግሥታት ለክብርሽ ዘማሩ የማትፈርሽ መቅደስ የእግዚአብሔር ሀገሩ
አዝ
እጅግ ብዙ ነገር አድርገሽልኛል ይቅር ባይ ልጅሽ በፍቅር አይቶኛል እኔስ እኖራሉሁ ድንግል በአንች ጥላ ጨለማን አላይም ከእንግድህ በኃላ ዘማሪ ልዑልሰገድ ጌታቸው 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
file_18564.mp34.92 MB
176😍 11🕊 6🥰 5🔥 2