es
Feedback
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

Ir al canal en Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

Mostrar más
2025 año en númerossnowflakes fon
card fon
166 316
Suscriptores
-1724 horas
-227 días
-430 días
Archivo de publicaciones
የማይሸረሸር አለቴ የማይሸረሸር አለቴ የማይናጋ መሰረቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞገሴ አንተህ ነህ የጽድቅ ልብሴ
አዝ
ቀራንዮ ላይ የቆመ በፍቅር የተተለመ ከፊቴ ተነሰነሰ ደምህ ሕይወቴን ወረስ/2/ እፎይ ልበል ልዘምር ሁነኸኛል ጌታ ክብር/2/
አዝ
የሲና ምድር ኅብስቴ የተከተልከኝ አለቴ መርገሜን ሰብሮ አለፈ ሰላምህ ውስጤ ጎረፈ/2/ እፎይ ልበል ልዘምር ሁነኸኛል ጌታ ክብር/2/
አዝ
የማትደፈር ክልሌ የድል አርማዬ አክሊሌ ዓለምን ማሸነፊያዬ አንተ ነህ ክንዴ ጌታዬ/2/ እፎይ ልበል ልዘምር ሁነኸኛል ጌታ ክብር/2/
አዝ
ማዳፎችህን አይቼ በዕንባ ረጠቡ ጉንጮቼ ትዝታዬ ነው ዘወትር መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር/2/ እፎይ ልበል ልዘምር ሁነኸኛል ጌታ ክብር/2/ ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃድቅ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
ዘማሪ_ገብረዮሐንስ_ገብረፃድቅ_=_የማይሸረሸር_ዓለቴ.mp35.14 MB
165🕊 7🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኅዳር ፪/2/
በዚች ቀን ከአባ ጢሞቴዎስ በኋላ የተሾመ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ጴጥሮስ አረፈ። እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ ሰባተኛ ነው ይህንንም ቅዱስ እግዚአብሔር ለሊቀ ጵጵስና ሹመት መርጦ በሐዋርያ ማርቆስ ወንበር ላይ ከአስቀመጠው በኋላ የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አካክዮስ እንዲህ የሚል መልእክትን ጻፈለት እንደ ቅዱሳን ቄርሎስና ዲዮስቆሮስ ሃይማኖት ልዩ ሦስት በሆነ በአንድ አምላክ እናምናለን እናሳምናለን። ይህ አባ ጴጥሮስም እንደ ተቀበላት ገልጦ ስለ ቀናች ሃይማኖት ከራሱም ያለውን ጨምሮ ለመልእክቱ መልስ ጽፎ ከሦስት ምሁራን ኤጲስቆጶሳት ጋር ላካት። አባ አካክዮስም ተቀበላቸው በቅዳሴና በቊርባንም አንድ ሆኑ ያቺንም መልእክት በቃሉ በሚያምኑ ሕዝብ ፊት አነበባት። ከዚህም በኋላ ሌላ መልእክትን ጻፈ በውስጧም ከቅዱሳት መጻሕፍት ብዙ ቃላትን ተርጒሞ ወደ አባ ጴጥሮስ ላካት ። ይህም አባ ጴጥሮስ ኤጲስቆጶሳቱን ሰብስቦ ያቺን መልእክት በፊታቸው አነበባት እነርሱም እጅግ ደስ አላቸው ከቃሏና ከትርጓሜዋም የተነሣ አደነቁ በቀናች ሃይማኖትም ከእርሳቸው ጋር አንድነት ያላቸው መሆኑን ተማመኑ። ይህንን አባት አባ ጴጥሮስንም ከሀድያን ከሆኑ አይሁድ ከአረማውያንም ከመንበረ ሹመቱ እስኪያሳድዱት ድረስ ስለቀናች ሃይማኖት ብዙ መከራ ደረሰበት። ከጥቂት ወራትም በኋላ ወደ ሹመቱ ወንበር ተመለሰ መንጋውንም በቀናች ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ አዘውትሮ ያስተምራቸው ነበር ከእነርሱም ርቆ በስደት በነበረበት ጊዜ ከመናፍቃን እንዲጠበቁና በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ መልእክቶችን ጽፎ ይልክ ነበር በሹመቱ ወንበርም ዐሥር ዓመት ኑሮ በሰላም አረፈ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
258🕊 5🥰 3
ኦ እንዳንተ ያለ ወዳጅ ኦ እንዳንተ ያለ ወዳጅ አላገኘሁም እኔ ኦ ውለታህን ሳስበው በእንባ ይመላል አይኔ/2/
አዝ
ከእናቴም ልጆች በላይ አንተ ውድ ነህ ለኔ ወዳጅ እና ዘመዴ ጌታ የክፉ ቀኔ ምን አለኝ እና ልስጥህ የሚነገር የሚወራ እኔስ ተሸንፌያለሁ በእንባ ስምህን ልጥራ
አዝ
ተሰድጄ ብወጣ ወተሃል ከኔ ጋራ ትናንትናን አለፍኩት ጠላቴን እያራራ ደግሞ የነገውን ቀን አንተ ታውቃለህ ጌታ ወጥመዴን ስበር እና አፌን ሙላው በእልልታ
አዝ
በእስረኞች መሃል ሆኜ ሰንሰለት ለብሻለሁ አለም እውነት የላትም ፍትህ ካንተ እሻለሁ መቼ ታጽናናኛለህ ወዳጅ እና ዘመዴ አውጣኝ አውጣኝ ለሚልህ አንተ አታጣም ዘዴ
አዝ
መመላለስ አይደክምህ እኔን ማስታመም አንተ ደክመህ አልፈህልኛል እጆቼን አበርትተህ ሁሌ በሬ ላይ ቆመህ ደጃፌን የምትመታ ግባ የክብር ንጉስ ብያለሁ ማራናታ ብያለሁ ማራናታ/4/ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
ኦ_እንዳንተ_ያለ_ወዳጅ_ዘማሪት_ምርትነሽ_ጥላሁን_Official_Audio1.m4a4.38 MB
star reaction 2 151🥰 7🔥 5😍 1
ኃይሌም ዝማሬዬም ኃይሌም ዝማሬየ እርሱ ነው ዘላለም ከብሮ ያስከበረኝ እንደ እግዚአብሔር የለም እንደ እግዚአብሔር የለም ክብር ለሱ ይሁን ታላቅ ነው ዘላለም
አዝ
አቤቱ ጉልበቴ ሆይ አቤቱ መጽናናቴ ታትመሀል በውስጤ ተስለሀል ከፊቴ አያውህ አሻግሬ በተራሮች ከፍታ ጨለማየን ስትገፈው ሰንሰለቴን ስትፈታ     
አዝ
ዶኪሜ ነህ ኢየሱስ ዶኪሜ ነህ ጌታየ እግሮቼ ላይ ይፈሳል የማይቆመው እንባየ ናፈቀችህ መንፈሴ እንደ ዋላ ተጠማሁ ስምህን አውጄበት ይሸበራል ከተማው     
አዝ
ዲዳው አፉን ከፈተ ምርኮኛው ነጻ ወጣ ምድር ባንተ አረፈች ለተገፉት ቀን ወጣ የእንባየ ምትክ ሆኖ ጽድቅህ መንደሬን መላ የረዳኝ የሚረዳኝ ማን አለ ካንተ ሌላ       
አዝ
አቁሞኛል ግሳፄህ አቁሞኛል ፍቅርህ ወዳጅ አበዛህልኝ ወዳጄ እያልኩህ ጸጋ ሞልቶ ፈሰሰ የዝማሬ ማእበል ደጅህ በመንጋ ሞላ ጌታየ ሆይ ምን ልበል ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
6082726593_1 (2).mp35.32 MB
199🕊 6🔥 5🥰 4
ኅዳር ፩ /1/
‎ ‎ በዚች ቀን ከአፍራቅያ የሆኑ ቅዱሳን መክሲሞስ፣ ማንፍዮስ፣ ፊቅጦርና፣ ፊልጶስ በከሀዲው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘመን በሰማዕትነት አረፉ ። ‎ ‎በዚህም ከሀዲ ንጉሥ ዘመን ሰባቱ ደቂቅ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት አንቀላፍተው የነቁ ከእርሱ በሸሹ ጊዜ ነው ። እሊህም ቅዱሳን መስተጋድላን ክብር ይግባውና ክርስቶስን ክዶ ክርስቲያኖችን ሲአሠቃይ በአዩት ጊዜ ሃይማኖታቸውን ግልጥ ያደርጉ ዘንድ በአንድ ምክር ተስማምተው በአንድነት ተሰብስበው ወደ ከሀዲው ንጉሥ ቀረቡ እኛ በእግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግልጥ የምናምን ክርስቲያኖች ነን ለእርሱም እንሰግዳለን እናመልከዋለንም ብለው ጮኹ ። ‎ ‎ይህ ከሀዲ ዳኬዎስም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ እንዲገርፉአቸው አዘዘ አንድ ጊዜም ሁለት ጊዜም ታላቅ ግርፋትን ገረፏቸው በእሳት በአጋሉትም ከብረት በተሠሩ በትሮች ደበደቧቸው ። ‎ ‎ከዚህም በኋላ በበርኖስ እላቂ ጨርቅ ከመጻጻና ከጨው ነክረው ቊስላቸውን አሹአቸው የንጉሡንም ትእዛዝ ባልሰሙ ጊዜ ሥቃዩንም ፈርተው ከበጎ ምክራቸው ባልተመለሱ ጊዜ ቁጣን በማብዛት ጽኑዕ ሥቃይን ‎ ‎እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው ። ከዚያ የነበሩ ብዙ ሕዝብም ትዕግሥታቸውን በአዩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ሞቱ በዚያንም ጊዜ ንጉሥ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጧቸው አዘዘ እንደዚህም የምስክርነታቸውን ተጋድሎ ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
183🥰 12🕊 11🔥 5😍 3
በዕፀ መስቀሉ በዕፀ  መስቀሉ የተከፈለልኝ የኢየሱስ ፍቅር  ምንኛ ማረከኝ ከፍቅርም በላይ ሆነና መሠጠኝ ከመስቀል ሥር ሁኜ ፊቱን እያየሁኝ
አዝ
ዓለምን በፍቅሩ ያሸነፈ ጌታ የጸብን ማዕበል በፍቅሩ የገታ ሕይወቴን ጸጥ አድርጎ ይምራት በምልሐቱ እኔ ምን አለፍኝ አልደክምም በከንቱ
አዝ
ደሙ ከወዙ ጋር ተዋሕዶ ሲወርድ በእኔ በደል ጌታዬ ቀረብልኝ ለፍርድ ሀጥያቴን በጫንቃዉ ተሸክሞልኛል በደሌን ደምሥሶ ንፁሕ አድርጎኛል
አዝ
የቀራንዮ ግፍ በአንተ ላይ የሆነዉ ሰይጣንን ጠርቆ ከመንገድ አወጣዉ እሾሕ አሜኬላዉ ተደምስሶልናል የንጹሕ በግ ደም አዳምን ታድጓል
አዝ
ይኽንን ሥጋዬን ብሉ ይላችሁዋል ይኽንን ደሜንም ጠጡ ይላችሁዋል ከመስቀል ሥር ሆነን ደሙን እንቀበል ሥጋዉን እንብላ ሠዉ ሆይ ችላ አንበል   ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
ZEthiopia_በዕፀ_መስቀሉ,_በሊቅ_መዘምር_ይልማ_16k.m4a6.83 KB
108🥰 5
ትኩረት ❗️❗️❗️ በስመመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::   ''ወደ ተራሮች ውጡ እንጨትንም አምጡ ቤቴንም ስሩ እኔም በእርሱ      ደስ ይለኛል እኔም አመሰግናለሁ ይላል እግዚአብሔር ''                         ትንቢተ ሀጌ ፦ 1÷7-9 ውድ ኦርቶዶክሳዊያን ከሀገር ውስጥም ውጭም የተቻላሁን እንድታደርግልን ስል የደብሩ ሀገረ ስብከቱና ደብሩ በእግዚአብሔር ስም ይጠይቃል ። ይህ ቤተ - ክርስቲያን ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል በወለጋ በሆሮ ጉዱሩ ሻምቡ ከተማ ይገኛል። ከዚህ ቀደም በአካባቢው የነበረው የሠላምና ውስጣዊ ችግሮች የነበረ ሲሆን አሁን ግን ያ ተስተካክሎ ሠላም ሲሆን በአካባቢው ያለው ምዕመን ቁጥር አነሰተኛ በመሆኑ እንዲሁም የበጀት ችግር በመኖሩና ምንም አይነት የገቢ ምንጭ ስለ ሌለው የእድሳት ስራው የተቋረጠ ደብር ነው ።    የህንፃ ቤተ ክርስቲያን እድሳት አካውንት አዋሽ ባንክ                     013521525869400                     013521525869400
Mostrar todo...
4.09 MB
141🥰 12🔥 8🕊 6
ትኩረት ❗️❗️❗️ በስመመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::   ''ወደ ተራሮች ውጡ እንጨትንም አምጡ ቤቴንም ስሩ እኔም በእርሱ      ደስ ይለኛል እኔም አመሰግናለሁ ይላል እግዚአብሔር ''                         ትንቢተ ሀጌ ፦ 1÷7-9 ውድ ኦርቶዶክሳዊያን ከሀገር ውስጥም ውጭም የተቻላሁን እንድታደርግልን ስል የደብሩ ሀገረ ስብከቱና ደብሩ በእግዚአብሔር ስም ይጠይቃል ። ይህ ቤተ - ክርስቲያን ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል በወለጋ በሆሮ ጉዱሩ ሻምቡ ከተማ ይገኛል። ከዚህ ቀደም በአካባቢው የነበረው የሠላምና ውስጣዊ ችግሮች የነበረ ሲሆን አሁን ግን ያ ተስተካክሎ ሠላም ሲሆን በአካባቢው ያለው ምዕመን ቁጥር አነሰተኛ በመሆኑ እንዲሁም የበጀት ችግር በመኖሩና ምንም አይነት የገቢ ምንጭ ስለ ሌለው የእድሳት ስራው የተቋረጠ ደብር ነው ።    የህንፃ ቤተ ክርስቲያን እድሳት አካውንት አዋሽ ባንክ                     013521525869400                     013521525869400
Mostrar todo...
4.09 MB
1
Repost from TgId: 2131344856
Photo unavailableShow in Telegram
« እንዴት ልመናችሁ ? » የብዙዎቻቹ ጥያቄ ነው ። ይሄው አጭር መልስ ለአንድ ሳምንት በ300 ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ 3 ኮርሶችን ወስዳቹ ውሳኔ ላይ ትደርሳላቹ በ3 ኮርስ ደግሞ አይደለም ዕምነት ሙያውን በራሱ አጋመሳቹት አይደለም ወይ 😄 ደስ ካላቹ ሙሉ ክፍያ ከፍላቹ መቀጠል ወይም 300 ብር ተመልሶላቹ ማቋረጥ በሚገባ ትችላላችሁ ፣ አሁኑኑ ተመዝገቡ ፣ በማትጠብቁት ፍጥነት ባለሙያ ሁኑ @Greenbirdtechnology @greenbirdtechs @greenbirdtechs የለውጥዎ ክንፍ 🔑 🐥
Mostrar todo...
23
Repost from TgId: 1904326773
😍 ይሄን መልዕክት እንደምትወዱት አልጠራጠርም    
ተማሪ ሆናቹ ስለ Alpha የማታውቁ በነፃ ገብቶ ማየት እንደሚቻል ያልሰማቹ ብቻ ይሄ ፅሁፍ ለእናንተ ነው
      🙋 ማጥናት እየፈለጋቹ አልገባ ላላቹ     🤵‍♂ አጥንታቹ እየረሳቹ ለተቸገራቹ     🤯 ብዙ ሰዐት አጥንታቹ ትንሽ ብቻ cover ለምታደርጉ    
እነሆ መፍትሄ👇👇👇
📨 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙ ተማሪዎች Telegramምን እንደ ጥናት ረዳታቸው እየተጠቀሙ ይገኛሉ።        ይሄ ግን ከሁሉም ይለያል        Alpha referance note ይሰኛል ✅ Alpha referance note በሚያሰገርም መልኩ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በሚያስብል ደረጃ የHigh school መፅሐፍን በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ በተብራራ note በውስጡ ✅ solved problemኦቸ ✅ እኛጋ ብቻ በሚገኙ የአስተማሪውን ጭንቅላት ያነበቡ በሚመስሉ Teacher's mind ጥያቄዎች ✅  ያጠኑትን በማያስረሱ Alpha trickኦች እና በብዙ explanatory image ኦች እና አማርኛ እንግሊዘጋ ገለፃዎቹ ታጅቦ ቀርቦላቹሀል።     ማየት ማመን ነው በነፃ አዎ በነፃ ገብታች ማየት ትችላላቹ።👇   📭  Grade 9. https://t.me/+TVC58hn3fmBiMGE0 📭  Grade 10. https://t.me/+4qJ4_ThRMOM0NDk0 📭  Grade 11. https://t.me/+aQ0B91PaNbFmMWE8 📭  Grade 12. https://t.me/+3KlluyhOmltjN2E8 📭  Remedial.(Gamma) https://t.me/+x_eY8u9jno84ZDk0
Alphaን አንብቤ ቀለለ ሀሳቤ!
Mostrar todo...
30🥰 4
ማርቆስ ወንጌላዊ ማርቆስ ወንጌላዊ ሐዋርያ/2/    ለግብፅ ለግብፅ ወኢትዮጲያ ማርቆስ ወንጌላዊ ሐዋርያ
አዝ
ግብፅን አቀናሃት ወንጌል ዘራህባት የክርስቲያን ሃገር መንበር አደረግሃት ተሰምቷል ገድልህ ዝናህ በአህጉር በምድረ ኢትዮጵያም ከዳር እስከዳር   
አዝ
እንደ ወንጌል ልጅህ እንደ እስክንድርያ አባቷ ነህና ማርቆስ ለኢትዮጵያ ከነጣቂ ተኩላ ሕዝቧን ጠብቅላት እንዳሳፈርካቸው የግብዕን ጣዖታት   
አዝ
ጴጥሮስ በክታቡ ልጄ ማርቆስ ያለህ ለመልእክት መብቃትክን ጳውሎስ ያመነብህ ከሐዋርያት ጋር ረዳት ሆነህ ቃለ ክርስቶስን ዞረህ ያስተማርህ   
አዝ
ባላመኑት ፊት ስሙን መሰከርህ የኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዕቱ ሆነህ ወንጌልን የሰበክህ መከራን ሳትፈራ አንበሳው ማርቆስ ኢትዮጵያን አደራ     ዘማሪ ብዙአየሁ ተመስገን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
6082726593_1 (3).mp36.25 MB
134🥰 5🔥 1
ኃይሌም ዝማሬዬም ኃይሌም ዝማሬየ እርሱ ነው ዘላለም ከብሮ ያስከበረኝ እንደ እግዚአብሔር የለም እንደ እግዚአብሔር የለም ክብር ለሱ ይሁን ታላቅ ነው ዘላለም
አዝ
አቤቱ ጉልበቴ ሆይ አቤቱ መጽናናቴ ታትመሀል በውስጤ ተስለሀል ከፊቴ አያውህ አሻግሬ በተራሮች ከፍታ ጨለማየን ስትገፈው ሰንሰለቴን ስትፈታ     
አዝ
ዶኪሜ ነህ ኢየሱስ ዶኪሜ ነህ ጌታየ እግሮቼ ላይ ይፈሳል የማይቆመው እንባየ ናፈቀችህ መንፈሴ እንደ ዋላ ተጠማሁ ስምህን አውጄበት ይሸበራል ከተማው     
አዝ
ዲዳው አፉን ከፈተ ምርኮኛው ነጻ ወጣ ምድር ባንተ አረፈች ለተገፉት ቀን ወጣ የእንባየ ምትክ ሆኖ ጽድቅህ መንደሬን መላ የረዳኝ የሚረዳኝ ማን አለ ካንተ ሌላ       
አዝ
አቁሞኛል ግሳፄህ አቁሞኛል ፍቅርህ ወዳጅ አበዛህልኝ ወዳጄ እያልኩህ ጸጋ ሞልቶ ፈሰሰ የዝማሬ ማእበል ደጅህ በመንጋ ሞላ ጌታየ ሆይ ምን ልበል ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
6082726593_1 (2).mp35.32 MB
1
እንባችን ደረቀ እንባችን ደረቀ ለካስ ያልቃል እንባ ሃይል አጣን ለሀዘን ኧረ ወዴት እንግባ ኤርምያስን እንጥራው ቢያስተምረን ሰቆቃ 'መቼ ነው ሚቆመው የምዕመናን ሴቃ/2/
አዝ
አሐዱ አብ ቅዱስ ብሎ የቀደሰው የካህኑ ደም ነው በግፍ የፈሰሰው ማን ማንን ያፅናና በሁሉም ቤት ለቅሶ መቼ ነው ምናየው ዕንባችን ታብሶ
አዝ
ለምን ትተኛለህ ጌታችን ሆይ ንቃ መገፋት ስቃዩን አልቻልነውም ይብቃ የሰማዕታት ደም እንደ ጎርፍ ፈሰሰ የሰማነው ሁሉ በኛ ላይ ደረሰ
አዝ
ኃጥያት በአንድ በኩል ከውስጥ ይወጋናል ጠላትም ከውጪ ቀስት ያነሳብናል ከማዕተባችን ጋር በፍቅርህ እሰረን ከፈተና አታግባን ቢመጣም አስችለን
አዝ
እኛን ከሞት ይልቅ መካድ ያስፈራናል ከፈተናም ይልቅ መውደቅ ያሰጋናል የሠለስቱ ደቂቅ የአርባዕ ሐራ ጌታ አሁን ድረስልን በአለም አንረታ
አዝ
ቅዱሳን ሰማዕታት ኢትዮጵያን ክበቡ በእምነታችን አፅኑን ሳይሰጥም መርከቡ ጊዮርጊስ ሆይ ድረስ ዛሬም እንደ ጥንቱ ያንተን ፀሎት አምነን አንቀርም በከንቱ ዘማሪ ዲያቆን ቀዳሚፀጋ ዮሐንስ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
እንባችን ደረቀ (1).mp32.63 MB
233🕊 17🥰 10
ጥቅምት ፳፱ /29/
በዚችም ቀን የተመሰገነና የከበረ የደብረዘኸኝ መምህር ጸቃውዐ ድንግል አረፈ። የዚህም ቅዱስ አባቱ ካህን ነው በጥበብ እና በበጎ ተግሣጽም አሳደገው መለኮታዊ ትምህርትን ሁሉ አስተማረው አድጎ አርባ ዓመትም በሆነው ጊዜ አባቱ ከአንድ ገዳም ውስጥ መነኰሰ  ለመምህርነትም ተመርጦ በአባ ገብረ ማርያም ወንበር ላይ ተሾመ። በዚያንም ጊዜ አባቱ ለልጁ የምንኵስና  ልብስ አለበሰው ስሙንም  ጸቃውዐ ድንግል ብሎ ሰየመው። ከዚያችም ጊዜ ጀምሮ ያለ ማቋረጥ በጾም እና በጸሎት ብዙ በመስገድም ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። ከዚህም ዓለም የሚለይበት ሰዓትበደረሰ ጊዜ ጥቂት ታሞ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ በረከቱም  ከእኛ ጋር ትኑር አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
197🕊 13😍 3
​​አትንኩን አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል/2/ የቅዱስ ጊዮርጊስ የጳውሎስ ልጆች ነን/2/
አዝ
ጥቂቶች ሆነን ተነስተን ነው እንዲሁ ምድርን የመላነው ልጣል ከውሃ ከእሳት ጽኑ ነው የያዝነው እምነት አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል/2/ የተክለሃይማኖት የጴጥሮስ ልጆች ነን/2/
አዝ
ድሆች ስንባል ባለጸጋ ሁሉን የያዘ ነው ከእኛ ጋ ብርቱውን ጎልያድ የጣለ በወንጭፋችን ጠጠር አለ አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል/2/ የክርስቶስ ሰምራ የአርሴማ ልጆች ነን/2/
አዝ
በሕይወት በቃል አስተማረን አምላካችን ነው የነገረን የዚህ ዓለም ጨው ተብለናል አልጫውንም አጣፍጠናል አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል/2/ የቅዱስ መርቆሬዎስ የማርቆስ ልጆች ነን/2/
አዝ
እንደ ደመና የከበቡን የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩን ስላሉን ብዙ ምስክሮች ደካሞች ሲሉን ነን ኃይለኞች አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል/2/ የቅዱስ ጊዮርጊስ የጳውሎስ ልጆች ነን የተክለሃይማኖት የጴጥሮስ ልጆች ነን ቤተክርቲያን እማማ ዝናሽ በዓለም ይሰማ እስካረጅም እስክሸመግልም ድረስ ለሚመጣ ትውልድም ሁሉ ክንድህን ኃይልህንም ጽድቅህንም እስክነግር ድረስ አቤቱ አትተወኝ ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
406245552.mp32.42 MB
244😍 7🕊 5🥰 4🔥 3
Photo unavailableShow in Telegram
ጥቅምት ፳፰/28/
በዚች ቀን ቅዱስ መርትያኖስና መርቆሬዎስ በሰማዕትነት አረፉ። እኒህም ለቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱ ነበሩ:: አርዮሳዊ የሆነው ሁለተኛው ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ አባ ጳውሎስን በአርማንያ በሥውር እሥር ቤት ውስጥ አንቀው እንዲገድሉት ካደረገ ቡኃላ እኒህ ቅዱሳን መርትያኖስና መርቆሬዎስ የዕረፍቱን ቀን ገድሉንም ጻፉ::አርዮሳዊውንም ንጉሥ ረገሙት:: ንጉሡም እንደረገሙት በሰማ ጊዜ ወታደሮች ልኮ ወደ እርሱ አስቀረባቸው በሰይፍም ገደሏቸው:: በዚያም በገደሏቸው ቦታ ቀበሩአቸው እስከ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘመንም በዚያ ቦታ ኖሩ እርሱም ዜናቸውን በሰማ ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ሥጋቸውን ወደ ቍስጥንጥንያ በክብር አስመጣ ያማረች ቤተክርስቲያንንም ሠርቶላቸው ሥጋቸውን በውስጧ አኖረ በዚችም ቀን በዓልን አደረገላቸው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
248🕊 10😍 1
ይቅር በል እንጂ አትፍረድ ይቅር በል እንጂ አትፍረድ የባህሪህ ነው ሰውን መውደድ የቀድሞን በደል አታስብብን ይቅርታህ ፈጥኖ ይደረግልን /2/
አዝ
ዕለት ዕለት እኛ ስንበድል አንተ ደግሞ ትላለህ ይቅር በማይቆጠር በበዛ ምህረት ዓለማቱን ይዟል ቸርነትህ አልመጣህም ፃድቃንን ልትጠራ ተገልጠሃል ለሃጣን ልትራራ ጨምርልን የንሰሃ ዘመን እንመለስ ወዳንተ መልሰን
አዝ
ቸር ሰው ወዳጅ የፍጥረቱ ጌታ ለኃጥያታችን አድርግልን ይቅርታ ባርከን አክብረን ነፃም አድርገን ቅዱስ ፈቃድህን ለመስራት አብቃን አልመጣህም ፃድቃንን ልትጠራ ተገልጠሃል ለሃጣን ልትራራ ጨምርልን የንሰሃ ዘመን እንመለስ ወዳንተ መልሰን
አዝ
የሰውን ድካም አንተ ታውቃዋለህ ለእጆችህ ስራ ዘወትር ትራራለህ የበደላችን ማሰሪያ ይፈታ በፍቅር እየን ጠዋት እና ማታ አልመጣህም ፃድቃንን ልትጠራ ተገልጠሃል ለሃጣን ልትራራ ጨምርልን የንሰሃ ዘመን እንመለስ ወዳንተ መልሰን
አዝ
ዕለት ዕለት እኛ ስንበድል አንተ ደግሞ ትላለህ ይቅር በማይቆጠር በበዛ ምህረት ዓለማቱን ይዟል ቸርነትህ አልመጣህም ፃድቃንን ልትጠራ ተገልጠሃል ለሃጣን ልትራራ ጨምርልን የንሰሃ ዘመን እንመለስ ወዳንተ መልሰን
አዝ
ቸር ሰው ወዳጅ የፍጥረቱ ጌታ ለኃጥያታችን አድርግልን ይቅርታ ባርከን አክብረን ነፃም አድርገን ቅዱስ ፈቃድህን ለመስራት አብቃን አልመጣህም ፃድቃንን ልትጠራ ተገልጠሃል ለሃጣን ልትራራ ጨምርልን የንሰሃ ዘመን እንመለስ ወዳንተ መልሰን ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃድቅ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
6082726593_1 (1).mp311.02 MB
230🥰 9🕊 8😍 8
Photo unavailableShow in Telegram
ጥቅምት ፳፯/ 27/
በዚች ቀን ቅዱስ አባት የሀገረ ቃው ኤጲስቆጶስ አባ መቃርስ አረፈ:: ይህ አባት በወንበር ተቀምጦ ሕዝቡን በሚያስተምራቸው ጊዜ የወገኖቼን ኃጢአታ ቸውን፤የከፋች ሥራቸውንም እያየ ዘወትር ያለቅስ ነበር። ለዚህም ቅዱስ  የዝንጉዎችን ምክር ተከትሎ  ያልሔደ  በኃጢአተኞችም ጐዳና ያልተጓዘ  በዘባቾችም መቀመጫ ያልተ ቀመጠ  የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ፈቃዱ የሆነ እንጂ ሕጉንም በቀንና  በሌሊት የሚያነብ የሚያስተምር ብፁዕ ነው የሚለው የነቢይ ዳዊት ቃል ተፈጽሞለታል። የንጉሡም  መልክተኛ  አባ  መቃርስ በንጉሥ ሃይማኖት እንደማያምን በአወቀ ጊዜ ተቆጥቶ ከኵላሊቱ ላይ ረገጠው ያን ጊዜም ሙቶ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ  ሥጋውንም ምእመናን ወስደው ከነቢይ ኤልሳዕና ከመጥምቁ ዮሐንስ ሥጋ ጋር በአንድነት አኖሩት ወደ ከወደደው ክርስቶስም  የመንግሥት ዘውድን ተቀዳጅቶ ሔደ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም  በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
271🥰 17🕊 13😍 1
ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ተዋሕዶ ሃይማኖቴ የጥንት ነሽ የእናት እና አባቴ ማዕተቤን አልበጥስም ትኖራለች ለዘለዓለም
አዝ
የግብጽን ከተሞች በደም ገንብተናል በመግደል ጽድቅ የለም ሞተን ግን ኖረናል ማዕተብሽን ፍቺ በጥሺው ቢሉኝ እኔስ ከነ አንገቴ ውሰዱት አልኩኝ
አዝ
ጴጥሮስ ተሰቀለ ጳውሎስ ተሰየፈ ተዋሕዶ እያለ አረ ስንቱ አለፈ ሌሎችም በእሳት በስቃይ አልፈዋል ዘመን የማይሽረው ታሪክን ጽፈዋል
አዝ
ፊተኛ ነንና አንዳንሆን ኋለኛ ሕዝቤ ተነቃቃ ተነሥ አትተኛ ጅብ ከሄደ ውሻ እንዳይሆን ጩኸቱ የተዋሕዶ ልጆች አሁን ነው ሰዓቱ
አዝ
ዓይተን እንዳላየን ስንት አሳልፈናል የእርሱ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም ብለናል አሁን ግን ይበቃል ዝምታው ይሰበር ይገለጥ ይታወጅ የተዋሕዶ ምሥጢር በዘማሪት አዜብ ከበደ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Mostrar todo...
ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ሀይማኖቴ_ተዋህዶ_ሀይማኖቴ_የጥንት.m4a9.46 KB
166
ጥያቄ❓ከመመለስዎ በፊት የእለቱን ስንክሳር ይመልከቱ። ለምትሳተፉ ለሁላችሁ ቃለ ሕይወት ያሰማልን። ቅዱስ ሐዋርያ ጢሞና ከሰባቱ ዲያቅናት ውስጥ አንዱ ነው።Anonymous voting
  • ‎ሀ. እውነት‎
  • ለ. ሐሰት
0 votes
93🥰 11🔥 2🕊 1