ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
Ir al canal en Telegram
The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man
Mostrar más2025 año en números

44 133
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
-22730 días
Archivo de publicaciones
በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን ልጆች አባታችን በህይወት ይኑር ይሙት አናዉቅም አሉ
በፓኪስታን በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን ልጆች ከሶስት ሳምንታት በላይ በህይወት ስለመኖራቸዉ ምንም ማስረጃ እንዳላገኙ ባለስልጣናቱ ስለሁኔታው እየደበቁ ነው ብለው እንደሚፈሩ ተናግረዋል፡፡በፍርድ ቤት የተፈቀደ የእስር ቤት ጉብኝቶች ሲታገዱ እና የእስር ቤት ዝውውሮች ሊደረጉ ይችላሉ በሚል ዉዝግብ ዉስጥ መግባታቸዉን ገልጸዋል፡፡
የኢምራሃን ካን ልጅ ቃሲም ካን ለሮይተርስ እንደተናገረው ለሳምንታዊ መገናኘትን የፍርድ ትእዛዝ ቢሰጥም ቤተሰቡ ከካን ጋር ቀጥተኛ ወይም የተረጋገጠ ግንኙነት አልነበረውም ብሏል።አባቴ ደህና ይሁን ቆስሎ ወይም በህይወት እንዳለ አለማወቅ የስነ ልቦና ጉዳት ነው" ሲል በማከል ለሁለት ወራት ያህል የተረጋገጠ ግንኙነት አልነበረንም ሲል ተናግሯል።
ዛሬ ስለ ህመሙ ምንም የተረጋገጠ መረጃ የለንም። ትልቁ ፍርሃታችን የማይቀለበስ ነገር እየተደበቀብን መሆኑን ነው።ቤተሰቡ ከአንድ አመት በላይ የካን የግል ሀኪም እንዲገናኙ ደጋግሞ ጠይቋል ሲሉ አክለዋል።የፓኪስታን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተያየት እንዲሰጥ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የእስር ቤቱ ባለስልጣን ለሮይተርስ እንደተናገሩት ካን በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዉ ወደ ከፍተኛ የጸጥታ ተቋም ለማዘዋወር ምንም አይነት እቅድ እንደሌለ ገልጸዋል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
😭 22❤ 9🤔 1😢 1
ኃላፊነታቸውን በመጠቀም ከዝግ አካውንት ላይ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ያደረጉት የባንክ ሰራተኞች በእስራት ተቀጡ
የቦረና ዞን ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል መግለጫ እንዳመለከተው1ኛ ገልገሎ ቀንጨሮ፣ 2ኛ አብዲሳ ከበደ፣3ኛ ጉቱ ንጋቱ ፣4ኛ ገመዴ ሚኤሶ 5ኛ ካሳ ግርማ ፣6ኛ በሺ ሞቱማ፣ 7ኛ መክብብ ቡልቡላ ሙያቸውን በመጠቀም የማጭበርበር ወንጀል መፈጸማቸው ተገልጿል። ሰባቱ ግለሰቦች በቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ ያያ ቀበሌ የሚገኝ አንድ ባንክ ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ባለሞያዎች ናቸው።
ሰራተኞች የተሰጣቸውን እምነት እና ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው የስራ ሃላፊነት እና ሞያ በመጠቀም ለያቤሎ ከተማ ለሚሰራ ትምህርት ቤት ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የተመደበ እና ፕሮጀክቱን በሚያንቀሳቅሰው ኮንትራክተር ስም በየሶስት ወሩ የሚታደስ የዝግ ባንክ አካውንት ውስጥ ያለ 1 ሚሊየን 93 ሺህ 6መቶ ብር የደንበኞች አገልግሎት እና ሽያጭ ክፍል ኦፊሰር በሆነው በሶስተኛ ተከሳሽ ጉቱ ንጋቱ ትዕዛዝ የተዘጋው የሂሳብ አካውንት እንዲንቀሳቀስ ተደርጓል።
በሁለተኛ ተከሳሽ አብዲሳ ከበደ አማካይነት እንዲፀድቅ ተደርጎ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ወደ ሶስተኛ ተከሳሽ ጉቱ ንጋቱ አካውንት ገቢ መደረጉን የቦረና ዞን ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል መግለጫ አመላክቷል፡፡በተጨማሪም የፕሮጀክቱን ተቀማጭ ሂሳብ በየሶስት ወሩ በሚታደስ ፍቃድ እንዲያንቀሳቀስ ፈቃድ ከተሰጠው ኮንትራክተር የግል አካውንትም 400 ሺህ ብር ወደ ስድስተኛ ተከሳሽ በሺ ሞቱማ ገቢ እንዲደረግ በሰባተኛ ተከሳሽ መክብብ ቡልቡላ ኦዲት ተደርጎ የጸደቀ በማስመሰል ከፍተኛ የሆነ ምዝበራ መከናወኑን በምርመራ እና የኦዲት ግኝት ተረጋግጧል ።
በዚህ መሰረት አንደኛ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ተከሳሾች ከመመሪያ እና ከአሰራር ደንብ ውጭ ተቀማጭ ገንዘብ እንዲቀሳቀስ በማድረግ አራተኛ ፣አምስተኛ ፣ስድስተኛ እና ሰባተኛ ተከሳሾች ደግሞ የተንቀሳቀሰው ሂሳብ ወደ ግል አካውንቶች እንዲገቡ በመፍቀድ ፣ በማፅደቅ እና ከመመሪያ ውጭ የተሰራን አሰራር ሪፖርት ባለማድረግ ወንጀል በፖሊስ እና በአቃቢ ህግ ጉዳያቸው ተጣርቶ በማስረጃ ተረጋግጦ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደቡብ ቅርጫፍ ተልኳል።
ሰባቱ የባንክ ሰራተኞች ላይ በስልጣን እና ሞያ በመገልገል የምዝበራ ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል። ክሱን ሲከታተል የነበረው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደቡብ ምድብ ችሎት፣ ሰሞኑን በዋለው ችሎት 1ኛ ተከሳሽ በዘጠኝ ዓመት ከስምንት ወር ፣ 2ኛ ተከሳሽ በስምንት ዓመት ከሁለት ወር እስራት፣ 3ኛ ተከሳሽ በስድስት ዓመት ከስምንት ወር እስራት፣ 4ኛ ተከሳሽ በስድስት አመት ከአራት ወር እስራት፣5ኛ ተከሳሽ በ3 ዓመት ከዘጠኝ ወር እስራት 6ኛ ተከሳሽ በአንድ አመት ከሶስት ወር እስራት ፣ 7ኛ ተከሳሽ በአንድ አመት ከሁለት ወር እስራት እንዲቀጡ የወሰነባቸው ሲሆን ሰባቱም ተከሳሾች በተጨማሪ ሶስት ሶስት ሺህ ብር የተወሰነባቸው መሆኑን የምርመራ ክፍሉ ለብስራት የላከው መግለጫ አመላክቷል።
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 26😁 6🤔 3👍 2👎 1💔 1
Photo unavailableShow in Telegram
የስዊዘርላንድ ቢሊየነር በሀብታሞች ላይ ከፍተኛ ግብር እንዲጣል ጠየቁ
አንድ ታዋቂ የስዊዘርላንድ ቢሊየነር ሀገራቸው ከ50 ሚሊዮን የስዊስ ፍራንክ ወይም 62 ሚሊዮን ዶላር እና ከዚያ በላይ በውርስ ሀብት ላይ 50 በመቶ ታክስ እንዲከፈል የቀረበዉን ሀሳብ ውድቅ በማድረግ የሀብታሞች ቀረጥ እንዲጨምር ጠይቀዋል።የግሉ ፍትሃዊነት ድርጅት ተባባሪ መስራች የሆኑት አልፍሬድ ጋንትነር የሀብት ክምችት መጨመር አለም አቀፋዊ ችግር መሆኑን ከስዊዘርላንድ ጋዜጣ ታገስ-አንዘይገር ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡
ጋንትነር "በዚህች ሀገር ውስጥ ያሉ ጥቂት ሰዎች ትልቅ ሀብት አላቸው እናም ሌሎች የጤና መድን እና የቤት ኪራይ እንዴት እንደሚከፍሉ የማያውቁ ሊሆኑ አይገባም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ችግሩን ለመቅረፍ ምንም ካልተደረገ፣ “ኤሎን ማስክ፣ ማርክ ዙከርበርግ እና ፍሬዲ ጋንትነርስ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ተጨማሪ ገንዘብ ይሰበስባሉ” ሲሉ ጋንትነር ተናግረዋል።
ስዊዘርላንድ ከዓለማችን ከፍተኛ የሀብት አስተዳደር ማዕከላት አንዷ ስትሆን በሀገሪቱ ውስጥ ወደ 2,500 የሚጠጉ ግብር ከፋዮች ከ50 ሚሊየን ፍራንክ በላይ የሚያወጡ ንብረቶች እንዳሏቸው የስዊዘርላንድ የግብር ባለስልጣናት አስታውል።እሁድ እለት በተደረገዉ ህዝበ ውሳኔ ከ 78 በመቶ በላይ የሚሆኑት የስዊስ መራጮች የታቀደውን የውርስ ታክስ ውድቅ አድርገውታል፡፡
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 19
በሀላባ ዞን ከደንብ እና መመሪያ ውጭ አገልግሎት ሲሰጡ በነበሩት የግል ጤና ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ
በሀላባ ዞን ጤና መምሪያ በጤናና ጤና ነክ አገልግሎትች ግብአት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በተደረገ የግል ጤና ተቋማት የቁጥጥር ስራ ከደንብ እና መመሪያ ውጭ አገልግሎት ሲሰጡ በነበሩት ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል።
የግል ጤና ተቋማቶች በየተቋሙ የተቀጡሩትን የባለሙያዎችን መረጃ በተሟላ መልኩ አደራጅተው ማሳወቅ እንደሚገባቸው መመሪያው ገልጿል።
በመሆኑም በዌራ ዲጆ ወረዳ ፍቃድ የተሰጣቸው የግል ጤና ተቋማት የተሟላ የባለሙያ መረጃ ከማሳወቅ አንፃር በተደጋጋሚ ቢነገርም ሊፈፅሙ ባልቻሉት በ4 በግል ጤና ተቋማት ላይ የዞኑ ጤና መምሪያ ከወረዳው ጋር በመሆን የማሸግ እርምጃ ወስደዋል።
እርምጃ የተወሰደባቸው ጤና ተቋማት በሚቶ ዲጆ መካከለኛ ክሊንክ ፣ኤርሚያስ መካከለኛ ክሊንክ ፣አባቆርቾ መካከለኛ ክሊንክ እና ከቤ መድሀኒት መደብር ሲሆኑ ከባለሙያ መረጃ አደረጃጀት በተጨማሪ ባለፈቃዱ በስራ ላይ ያለመገኘት፤ ወርሃዊ ሪፖርቶችን አሟልቶ ያለመላክ የሚሉት ይገኙበታል መባሉን ብስራት ከሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ያገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 18👍 8
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ስለ ሀገራችን 'ከእውነት የራቁ መግለጫዎችን' ሰጥተዋል ሲሉ ከሰሱ
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ሀገራችን "ከእውነት የራቁ መግለጫዎችን" መናገራቸውን ቀጥለዋል ሲሉ ከሰዋል።ራማፎሳ ለህዝቡ ባደረጉት ንግግር ትራምፕ ከቀናት በፊት ደቡብ አፍሪካን በፍሎሪዳ በሚካሄደው የቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ ላይ እንደማይጋብዟት መናገራቸዉን ተችተዉ አንስተዋል፡፡
"በአፍሪካነርስ ላይ የተካሄደውን የዘር ማጥፋት እና በአገራችን በነጮች ላይ የተፈፀመውን መሬት ስለመቀማት ከእውነት የራቁ መግለጫዎችን ደጋግመዉ ትራም ተናግረዋል" ሲሉ ራማፎሳ አክለዋል፡፡ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ደቡብ አፍሪካ በ2026 በአሜሪካ በሚካሄደው የቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ ላይ እንደማትቀርብ አስታውቀው፣ ሀገሪቱ የቡድን 20ን ፕሬዝዳንት ለአሜሪካ ኤምባሲ ተወካይ ለማስረከብ ፈቃደኛ መሆኗን ጠቅሰዋል።
"በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ተገቢውን የዲፕሎማሲ ፕሮቶኮሎችን በመመልከት የቡድን 20 ፕሬዚዳንቱን ለ 2026 በይፋ ለአሜሪካ አስረክበናል" ሲሉ ራማፎሳ ገልጸዋል።ትራምፕ በዚህ ወር በጆሃንስበርግ በተካሄደው የቡድን 20 ስብሰባ ላይ ደቡብ አፍሪካውያን ነጮች ያለ ልዩነት እየተገደሉ እና መሬታቸው እየተነጠቀ ነው ሲሉ ቢናገሩም የደቡብ አፍሪካ መንግስት መሰረተ ቢስ ክስ ሲል ደጋግሞ ሲያጣጥለው ቆይቷል።
ራማፎሳ ዩናይትድ ስቴትስ በጉባኤው ላይ ላለመሳተፍ ያቀረበችበት ምክንያት ደቡብ አፍሪካ አፍሪካነርስ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመች ነው በሚል መሠረተ ቢስ እና የውሸት ውንጀላ መሆኑ አሳዛኝ ነው ብለዋል። ይህ ስለ አገራችን ግልጽ የሆነ የተሳሳተ መረጃ ነው ሲሉ አክለዋል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 22😁 1
መናገርና እና መስማት የተሳናትን ታዳጊ አስገድደው የደፈሩ ሁለት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመዉ በኣሪ ዞን በደቡብ ኣሪ ወረዳ ሸካመር ቀበሌ ልዩ ስሙ ጃካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።ተከሳሾች በቁጥር ሁለት ሲሆኑ ስንታየሁ ወንድማገኝ እና አብነት ታጋይ የተባሉ ናቸው፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት ሁለቱ ተከሳሾች የግል ተበዳይ የሆነችዉን ነፃነት ደጄኔ የተባለችዉን የ15 ዓመት ታዳጊ በተፈጥሮ መናገርና እና መስማት የተሳናት ስትሆን በሰዓቱ ደጅ እንጀራ እየጋገረች ዕቃ ለመውሰድ ወደ ቤት ውስጥ ስትገባ ተከሳሾች ተከታትለዋት በመግባት በኃይል አንቀዋት በመያዝ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ከፈፀሙ በኋላ ከአከባቢው መሰወራቸው ገልጸዋል።
የግል ተበዳይ አሳዳጊ የሆኑት አጎቷ ጉዳዩን ለሚመለከተው የህግ አካል ካሳወቁ በኋላ ይህንን ድርጊት በማስመልከት ጥቆማ የደረሰው የወረዳው ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል መርማሪ ፖሊስ ወንጀሉን ስለመፈፀማቸው የሚገልጽ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማደራጀት ምርመራውን አጣርቶ መዝገቡን ለወረዳው ዐቃቤ ህግ ይልካል።የወረዳው ዐቃቤ ህግም ከፖሊስ የቀረበለትን የምርመራ መዝገብ ተቀብሎ ተከሳሾች በኢ.ፈ.ዲ.ሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና 620(2) (ሀ) ሥር ክስ መስርቶ ለደቡብ ኣሪ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀርባል ።
ፍርድ ቤቱም የቀረበለትን የክስ መዝገብ በሰው እባ በህክምና ማስረጃ በማጣራት እያንዳንዳቸው በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቿል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
🤬 28❤ 20💔 9👎 2😱 2
በኢንዶኔዥያ፣ ሲሪላንካና ታይላንድ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ1 ሺ በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ
ባለፉት ቀናት በተከሰቱት አውሎ ነፋስ በኢንዶኔዥያ፣ ስሪላንካ እና ታይላንድ በደረሰ የጎርፍ አደጋ እና የመሬት መንሸራተት ቢያንስ ከ1 ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን በአስከፊ የአየር ሁኔታ የተጎዱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመርዳት እየተሰራ ይገኛል። ሰኞ እለት ወደ ሰሜን ሱማትራ ያቀኑት የኢንዶኔዥያ ፕሬዝዳንት ፕራቦዎ ሱቢያንቶ መንግስት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ "አስፈላጊውን እርዳታ እንዴት ወዲያውኑ መላክ እንደሚቻል" ነው ብለዋል ።
“ፈጣሪ ቢፈቅድ ልንደርስባቸው የሚገቡ በርካታ ሩቅ መንደሮች አሉ” ያሉት ፕራቦዎ፣ መንግስት የእርዳታ ጥረቱን ለማገዝ ሄሊኮፕተሮችን እና አውሮፕላኖችን እያሰማራ መሆኑን ተናግረዋል።ፕራቦዎ ቢያንስ በኢንዶኔዥያ 442 ሰዎችን ለገደለው እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የደረሱበት አልታወቀም ለተባለዉ ከባድ የጎርፍ አደጋ እና የመሬት መንሸራተት ምላሽ ብሄራዊ ድንገተኛ ሁኔታ አዋጅ እንዲያውጁ ከፍተኛ ጫና በአስተዳደራቸዉ ላይ እየተደረገ ይገኛል፡፡
ከስሪላንካ አቻቸው አኑራ ኩማራ ዲሳናያኬ በተለየ መልኩ ፕራቦዎ እስካሁን ድረስ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ እርዳታ እንዲሰጣቸዉ በይፋ ከመጠየቅ ተቆጥበዋል።የኢንዶኔዥያ መንግስት ሁለት የሆስፒታል መርከቦችን እና ሶስት የጦር መርከቦችን እርዳታ የጫኑ ድጋፎችን በጣም አስከፊ ወደሆኑ አካባቢዎች ልኳል፡፡የስሪላንካ መንግስት አለም አቀፍ ዕርዳታን በመጠየቅ በአደጋዉ ለታገቱ ሰዎች ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮችን እየተጠቀመ ይገኛል፡፡ቢያንስ 334 ሰዎች መሞታቸውን የሲሪላንካ የአደጋ ኤጀንሲ ያስታወቀ ሲሆን በርካቶች አሁንም ጠፍተዋል።
የታይላንድ ባለስልጣናት በበኩላቸዉ በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል በቀጠለው የጎርፍ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 176 ደርሷል ብለዋል።መንግስት የእርዳታ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ቢገልጽም በጎርፉ ምላሽ አሰጣጥ ላይ ህዝባዊ ትችት እየጨመረ ይገኛል፡፡ ሁለት የአካባቢው ባለስልጣናት በደካማ ምላሽ አሰጣጣቸዉ የተነሳ ከስራ ታግደዋል ሲል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 12😭 9😱 8
የአፋር ክልል የልጅነት እርግዝና በስፋት ከሚስተዋልባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ቀዳሚ መሆኑ ተጠቆመ
በኢትዮጵያ የልጅነት እርግዝና ቀድሞ ከነበረበት እየቀነሰ መምጣቱ ቢነገርም ጉዳዮ ሙሉ ለሙሉ መፍትሄ እንዲያገኝ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በሚኒስቴሩ የስነተዋልዶ ቤተሰብ እቅድ የአፍላወጣቶችና ወጣቶች ባለሙያ አቶ ሞቱማ በቀለ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ሁኔታው በኢትዮጵያ የተለያዪ ቦታዎች የሚስተዋል አሳሳቢ ጉዳይ ነው።
የልጅነት ጋብቻ ጎልቶ በሚታይባቸው አካባቢዎች ችግሩ በይበልጥ እንደሚታይ የተናገሩ ሲሆን እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ሴት ህፃናት የችግሩ ሰለባ መሆናቸውን ጠቁመዋል ።እንዲህ ያለው ጉዳይ መዘዙ ብዙ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን በዚህ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች በወሊድ ጊዜ በማህፀናቸው ላይ በሚከሰት ችግር ለሞት እና ለፊስቱላ የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ።
በ2016 በተደረገው የዳሰሳ ጥናት የልጅነት እርግዝና በአፋር ክልል 66 ነጥብ 7 በመቶ መድረሱን የተናገሩት አቶ ሞቱማ ይህም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አካባቢዎች በቀዳሚነት አስቀምጦታል ብለዋል።እንደዚሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የልጅነት እርግዝና 50 በመቶ መድረሱ የተገለፀ ሲሆን የሶማሌ ክልል ደግሞ 49.4 በመቶ ድርሻን በመያዝ የሁለተኛና የሶስተኛ ደረጃን መያዛቸውን የዳሰሳ ጥናቱ ይፋ አድርጓል።ለጉዳዮ መፍትሄ ለማምጣት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራን እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ተይዘው የነበሩ ወንድም እና እህት ከበሽታው አገግመው ከማዕከል ወጡ
👉 የወጣቶቹ አባት በቫይረሱ ህይወታቸው አልፏል
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በማርበርግ በሽታ ቫይረስ ተይዘው ህይወታቸው ካለፈ አባታቸው ጋር ንክኪ የነበራቸው ወጣቶች ማገገማቸው ተሰምቷል። ወጣቶቹ ምልክት አሳይተው የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ቫይረሱ ስለመኖሩ ተረጋግጦ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ህክምና ተደርጎላቸው ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጦ ከህክምና ማዕከል እንዲወጡ ተደርጓል ።
የበሽታው ተጠቂ ወጣት ኢዩኤል ኤቃል 19 ዓመቱ ሲሆን ታዳጊ እህቱ የእርሱ ሥራ ኤቃል 16 ዓመቷ ነው። በተደረገላቸው የህክምና ድጋፍ ከማርበርግ ቫይረስ በሽታ ነፃ በመሆናቸው እጅግ በጣም መደሰታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።
አቶ እንዳሻው አክለውም ከእነዚህ ወጣቶች በተገኘ ልምድ ማንኛውም የበሽታ ምልክት የሚታይባቸው ግለሰቦች ፈጥነው ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የሚሰጠውን ህክምና ክትትል ማድረግ ከበሽታው የመዳን ዕድል እንደሚያሳድግ ገልፀው፤ ህብረተሰቡ ከመዘናጋት ወጥተው የቫይረሱ ምልክት እንደ ታየ ወደ ጤና ተቋም ሊመጡ ይገባል ብለዋል፡፡
የቢሮ ሀላፊው የጤና ባለሙያዎችን፣ በተግባሩ የተሳተፉትን አመራሮችን ጨምሮ ጤና ሚኒስቴር፣ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትንና አጋር ድርጅቶችን አመስግነዋል፡፡አገግመው ከማዕከሉ የወጡት ወጣቶች ልዩ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀው ፈጣሪን በማመስገን ስለተደረገላቸው ህክምናና ክትትል ባለሙያዎችንና በተግባሩ የተሳተፉ ሁሉንም አካላት አመስግነዋል።
በትግስት ላቀው
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 32😢 6😁 4🙏 4🤬 1
Photo unavailableShow in Telegram
በሆንዱራስ ምርጫ በትራምፕ የሚደገፉት ፖለቲከኛ እየመሩ መሆኑ ተሰማ
በሆንዱራስ አጠቃላይ ምርጫ ቀደምት የምርጫ ውጤቶች እንደሚያሳዩት የቀኝ ክንፍ ብሄራዊ ፓርቲ መሪ ናስሪ አስፉራ በጠባብ የነጥብ ልዩነት እየመሩ ይገኛል፡፡የምርጫው ምክር ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በድምጽ ዉጤቱ ላይ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀዉ ወግ አጥባቂው እጩ ከቀድሞው የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ እና ምክትል ፕሬዝዳንት ሳልቫዶር ናስራላ በጠባብ የድምጽ ልዩነት እየመሩ ይገኛል፡፡ ከመራጮች ድምጽ መካከል ከአንድ ሦስተኛዉ በላይ ተቆጥሯል።
የቀኝ ክንፍ ፖለቲከኛ አስፉራ በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሚደገፉ ሲሆን እኚሁ እጩ በምርጫዉ ከተሸነፉ ትራምፕ ለመካከለኛው አሜሪካ ሀገር የሚሰጡትን የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያቋርጡ ዝተዋል። የምርጫዉ ውጤቶቹ የመጀመሪያ እና ከፊል መሆናቸውን አጽንኦት የሰጡት የኤጀንሲው ኃላፊው ውድድሩ በሁለቱ ወግ አጥባቂ እጩዎች መካከል የስለት ጠርዝ ላይ የሚደረግ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።
አስፉራ 40.6 በመቶ ድምጽ በማግኘት ቀዳሚ ሲሆኑ የቅርብ ተፎካካሪያቸዉ ናስራላ 38.8 በመቶ ድምጽ አግኝተዋል፡፡በሶስተኛ ደረጃ የገዥው ግራዊንግ ሊብሬ ፓርቲ እጩ ሪክሲ ሞንካዳ ይገኛሉ፡፡አምስት ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች ለምርጫዉ ቢቀርቡም በዋናነት የሶስትዮሽ ውድድር ተደርጎ እየታየ ነዉ።አሁንም ገና ያልተቆጠረ ድምጽ የቀረ በመሆኑ ዉጤቱ በቀላ ሊለዋወጥ ይችላል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 11
''ውብ አዲስ ፩''
በአንድ ዓመት ውስጥ ሦስት የግል ሥዕል ትርዒት (Three solo -art shows) ለማዘጋጀት የተሰናዳው ሠዓሊ -ሀሮን የመጀመሪያውን ''ውብ አዲስ ፩'' በጎላ ጋለሪ እያሳየ ይገኛል። የሥዕል ትርዒቱም እስከ ህዳር 28/2018 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
የሥነጥበብ አድናቂዎችና፣ወዳጆች በነፃ መታደም ትችላላችሁ።
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 15
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የዋጋ ጥናት የተካሄደባቸው ምርቶችን ብዛት ወደ 100 ሺህ ለማድረስ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የቦርድ አመራሮችና ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ የነጋዴ ተወካይ ማህበራት አመራሮች ጋር ተቀራርቦ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይቱም የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ከገቢዎች ቢሮ ከአገልግሎት አሰጣጥና የግብር ከፋይ መስተንግዶ፣ ከደረሰኝ ባለሙያዎች ቁጥጥርና ስነ ምግባር ፣ ከቀን ገቢ ግምት ፣ ከተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ አተገባበር ጋር ያሉ ችግሮችን አንስተዋል። በተጨማሪም ከክሪላንስ አገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍና መስተንግዶ ጋር በተያያዘ ይስተዋላሉ ያሏቸው ችግሮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
የቢሮው የኮሙኒኬሽን ቢሮ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ከአገልግሎት አሰጣጥና ከመስተንግዶ፣ ከክሊራንስ አገልግሎት፣ ከሲስተም መቆራረጥ፣ ከባለሙያዎች ስነ ምግባር ጉድለት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ቅሬታዎች የተጠያቂነት አሰራርን በማጠናከር ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የምርቶች የገበያ ዋጋ ጥናት ተጠቃሚ የሚያደርገው በዋናነት ህጋዊ ግብር ከፋዩን ነው ። ከዋጋ ጥናቱ ጥራት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመቅረፍም ከግብር ከፋዮች የሚቀርብን ቅሬታ መነሻ በማድረግ ቢሮው በትኩረት የጥናት ስራውን በመስራት እየፈታ ይገኛል ብለዋል፡፡
ባለፈው ዓመት በ2 ሺህ ምርቶች የዋጋ ጥናት የተካሄዱ ሲሆን በየጊዜው ቁጥሩን በማሳደግ በአሁኑ ወቅት ወደ 16 ሺህ ምርቶች ለማድረስ መቻሉን ገልፀዋል። በዚህም የሚስተዋል የጥራት ጉድለት ለማረምና በቀጣይም የዋጋ ጥናት የተካሄደባቸው ምርቶች ብዛት ወደ 100ሺህ በማድረስ ይበልጥ ጥራቱን ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አቶ ሰውነት አየለ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
በምህረት ታደሰ
#ዳጉ_ጆርናል
👎 18❤ 5😁 1
