2025 año en números

127 433
Suscriptores
-6624 horas
-2667 días
-76830 días
Archivo de publicaciones
Photo unavailableShow in Telegram
#AmboUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አምቦ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 29 እና 30/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፦
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ካምፓስ
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሃጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
" በአስቸኳይ የተማሪዎቻችሁን መረጃ በተገቢው መንገድ ስጡ " - ቢሮው
በትግራይ ክልል በ52 የግል ኮሌጆች ላይ ስረዛና የእግድ ቅጣት ተጣለ።
43 ኮሌጆች ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዙ ሲወስን 9 ኮሌጆች የተጠየቁት እስኪያሟሉ የእግድ ቅጣት ተላልፎባቸዋል።
የትግራይ የቴክኒክ የሙያና የስራ ፈጠራ ቢሮ በግል ኮሌጆች ላይ የስረዛና የእግድ ቅጣት መጣሉን ይህም ባለፉት ሁለት ዓመት በትምህርት ባለሞያዎች የተደረገ ጥናት መሰረት አድርጎ መሆኑን ገልጿል።
ከመንግስት ፍቃድ የተሰጣቸው ኮልጆቹ ከትግራይ ጦርነት በኃላ የሚገኙበት ሁኔታ ለማወቅ ተከታታይ ጥናትና ድጋፍ ማድረጉን አሳውቋል።
የስረዛ ቅጣት የተሰጣቸው 46 ኮሌጆች የተማሪዎቻቸው መረጃ በተገቢው መንገድ እንዲሰጡ አሳስቧል።
የእግድ ቅጣት የተጣለባቸው 9 ኮሌጆች ደግሞ ሊያሟሉት የተጠየቁት አሟልተው ሲገኙ እግዳቸው ይነሳል ብሏል።
ስርዝና እገዳው በማህበራዊ የትስስር ገፅ በተሰራጨ ደብዳቤ መስማታቸው እንዳበሳጨው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ-መቐለ አስተያየት የሰጡት የግል ኮሌጆች ማህበር አመራሮች " የኮሌጆቻችንና የተማሪዎቻችን ክብር የሚነካ ተግባር ነው " የተፈፀመው ብለዋል።
" ኮሌጆቹ በትግራዩ ደም አፋሳሽ ጦርነት ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰባቸው የክልሉ የሚመለከተው አካልና የኢፌዲሪ የትምህርት ሚንስትር ያወቃሉ በእንደዚህ ሁኔታ ያለፉ የትምህርት ተቋማት መደገፍ እንጂ ማገድና መሰረዝ አይገባም " ሲሉ ገልጸዋል።
(የተሰረዙ እና የታገዱ የትምህርት ተቋማት ዝርዝር ከላይ ተያይዟል) #ቲክቫ
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Repost from TgId: 1401419976
Photo unavailableShow in Telegram
One of the essential skills for any penetration tester, blue teamer, or red teamer is knowing how to find and exploit weaknesses in Active Directory.
Register And Learn Now: https://course.geezsecurity.com/course/gtcrt
ለበለጠ መረጃ👇👇
Contact Us
✅ @geezsecsupport
📞 +251953537820
📬 info@geezsecurity.com
#GTCRT @geeztechgroup
Photo unavailableShow in Telegram
#AAU
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዩቤልዩ በዓሉን ለማክበር ዝግጅት አጠናቋል።
ክብረ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 75 ዓመታት ያበረከተውን አስተዋፅኦ በመጽሐፍ ተሰንዶ ይፋ የሚደረግ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
ዘጋቢ ፊልም፣ የአካዳሚክ ሴሚናሮች፣ የፓናል ውይይቶች እና የበጎ ፈቃድ ሳምንት መርሐግብሮች እንደሚካሔዱም ጠቅሰዋል፡፡
በሌላ በኩል የዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ የመሆን ሒደት እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር የሚያግዘውን ከ2024 እስከ 2028 ዓ.ም የሚመራበትን የአምስት ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ አዘጋጅቷል፡፡
የተለያዩ መመሪያዎች፣ ሰነዶች እና ፖሊሲዎች ፀድቀው ወደ ሥራ ገብተዋል የተባለ ሲሆን፤ ከ500 በላይ የነበሩት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ወደ 418 እንዲሸጋሸጉ መደረጋቸው ተገልጿል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
በረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት ይስጡ!
የትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ መሪ ስራ አስፈጻሚ ቡድን ባዘጋቸው ሁለት ረቂቅ ደንቦች ላይ የትምህርት ማኅበረሰቡ እና ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጡ ጠይቋል፡፡
1. በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣ ረቂቅ ደንብ፦ https://forms.gle/HisAZoyTpmo1ZFCA6
2. የተማሪዎች የሥነ-ምግባር መመሪያ (የመጀመሪያ ረቂቅ)፦
https://forms.gle/R72ai6EiMnzZtGsC6
ሊንኮቹን በመጫን ከዛ በመቀጠልም ማስፈንጠሪያ (Link) የሚለውን በመጫን ሰነዶቹን ማግኘት ይችላሉ፡፡ ሁለቱንም ሰነዶች ካነበባችሁ በኋላ የተጠየቁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን ሞልታችሁ (Submit) የሚለውን በመጫን አስተያየትዎን መላክ እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Repost from TgId: 1401419976
01:12
Video unavailableShow in Telegram
What is Red Team Engagement ❤️?
Register Now: https://course.geezsecurity.com/course/gtcrt
ለበለጠ መረጃ👇👇
Contact Us
✅ @geezsecsupport
📞 +251953537820
📬 info@geezsecurity.com
#GTCRT @geeztechgroup
8.38 MB
Photo unavailableShow in Telegram
#MekdelaAmbaUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፦
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ የሪሚዲያል ተማሪዎች በዋናው ካምፓስ (ጊምባ)
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ የሪሚዲያል ተማሪዎች በመካነ-ሰላም ካምፓስ
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣
➫ የሌሊት አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#MattuUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር መቱ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ታህሳስ 01 እና 02/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ትምህርት ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡
የምዝገባ ቦታ፦ በበዴሌ እና በመቱ ካምፓሶች
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)
➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)
➫ ብርድ ልብስ፣ እንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#ArbaMinchUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ትምህርት ሰኞ ህዳር 29/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡
አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች https://smis.amu.edu.et/pages/check_campus_placement ሊንክን በመጫንና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መለያ ቁጥር በማስገባት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ማወቅ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።
የምዝገባ ቦታ፦
➫ አባያ እና ጫሞ ካምፓሶች የተመደባችሁ ተማሪዎች አርባ ምንጭ ከተማ በሚገኙት አባያ እና ጫሞ ካምፓሶች
➫ ሳውላ ካምፓስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ አራት ፓስፖርት መጠን የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ እንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
የግል ትምህርት ቤቶችን ፈቃድ የመስጠት፣ እውቅና የማግኘት እና የመመዝገብ ሙሉ ሥልጣን ለክልል ትምህርት ቢሮዎች ተላለፈ።
ውሳኔው ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው አዲስ መንግሥታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት ረቂቅ ደንብ መሠረት መሆኑ ተገልጿል።
ውሳኔው በመላ አገሪቱ የሚገኙ የግል ትምህርት ተቋማትን አሠራር ለማካለል እና የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።
አዲሱ ረቂቅ ደንብ በጠቅላላ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1368/2017 ላይ የተመሰረተ ሲሆን፤ የክልል ትምህርት ቢሮዎች የግል ትምህርት ቤቶች፣ በሲቪል ማኅበራት የሚተዳደሩ ተቋማት እና የኃይማኖት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የሁሉም መንግሥታዊ ያልሆኑ ትምህርት ቤቶች ፈቃድና ምዝገባ ጉዳዮችን እንዲያከናውኑ ስልጣን ሰጥቷቸዋል።
ምንም እንኳን በረቂቅ ደንብ አብዛኛው ሥልጣን ለክልሎች የተላለፈ ቢሆንም፣ የትምህርት ሚኒስቴር በዋናነት በአለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች (International Schools) እና በማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች (Community Schools) ላይ ያለውን ብቸኛ የፈቃድና የቁጥጥር ስልጣን እንደያዘ ይቆያል።
ከሥልጣን ክፍፍሉ በተጨማሪ ረቂቅ ደንቡ ሁሉንም የግል ትምህርት ቤቶች ዳግም ምዝገባ እንዲያደርጉ ያስገድዳል እንዲሁም የመመዝገቢያ፣ የገንዘብ አስተዳደር እና የተቋማዊ አመራር ጥብቅ ደረጃዎችን አስቀምጧል።
በረቂቁ መሠረት ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤት ኮሚቴ እንዲያቋቁሙና በገንዘብ አስተዳደራቸው ሙሉ በሙሉ ገለልተኛና ግልፅ እንዲሆኑ ይጠበቅባቸዋል። #Capital
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#JimmaUniversity
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ገቢ የውጭ ሀገራት ተማሪዎች አቀባበል አድርጓል፡፡
ተማሪዎቹ ከጎረቤት ሀገራት ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ የመጡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በተማሪዎች አገልግሎት፣ በዩኒቨርሲቲው ደንብና መመሪያዎች እንዲሁም በአጠቃላይ የትምህርት እና የካምፓስ ደህንነት ጉዳዮች ላይ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
መንግሥት የትምህርት ዲፕሎማሲን በማጠናከር፣ ለጎረቤት ሀገራት ነጻ የትምህርት ዕድል በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት በመስጠት ላይ ይገኛል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Repost from TgId: 1401419976
Photo unavailableShow in Telegram
🧑💻 #GTCRT v1 – Intermediate Cyber RED TEAM Training 📣
⚡️ የመካከለኛ ደረጃ የ Red Teaming ኮርስ – ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ☄️
⚡️ Course Highlights
🩷 Duration: 3 Months
🩷 Difficulty: Intermediate to Advanced
✅ Key Modules You'll Master:
✅ External Reconnaissance (Passive & Active)
✅ Initial Access (Phishing, Weaponization, Delivery)
✅ Pivoting and Tunneling
✅ Privilege Escalation (Windows & Linux)
✅ Lateral Movement & Persistence
✅ AD Exploitation & Domain Dominance
✅ OpSec & Evasion Techniques
✅ Full-Scope Attack Path Simulation within AWS LAB
👑 Ideal for:
✔️Aspiring Penetration Testers
✔️SOC Analysts moving to Offensive Security
✔️System/Network Admins hardening their environments
✔️Anyone ready to Think Like an Adversary
Register Now: https://course.geezsecurity.com/course/gtcrt
ለበለጠ መረጃ👇👇
Contact Us
✅ @geezsecsupport
📞 +251953537820
📬 info@geezsecurity.com
#GTCRT @geeztechgroup
Photo unavailableShow in Telegram
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።
ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥራት ምክንያት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ገልፀዋል።
የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች የአንድ ዓመት የማስተማር ዘዴ (Pedagogy) ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በዚህም የመምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ይቻላል ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህነነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም ገልፀዋል።
ባለፈው ዓመት ከቅድመ-መዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል በሀገሪቱ አጠቃላይ የመምህራን ቁጥር 625,000 የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ቁጥሩን ወደ 700,000 ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል። #Fortune
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
#MoE
የክብር ዶክትሬት የተሠጣቸውን ግለሰቦች “ዶክተር ወይም የክብር ዶክተር“ በማለት በመጠሪያነት መጠቀም አይቻልም፡፡ - የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)
ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የተቋማቸውን የ1ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ትናንት ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡
በከፍተኛ ትምህር ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥ ችግር የነበረበት መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ወጥ አሰራር ለመከተል በማስፈለጉ የክብር ዶክትሬት አሰጣጥ ሀገራዊ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።
ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ማድረግ አለባቸው ያሉት ብርሃኑ (ፕ/ር)፤ የክብር ዶክትሬት ማዕረግ የሚያገኙ ሰዎችን 'ዶክተር' ወይም 'የክብር ዶክተር' በሚል መጠሪያ መጠቀም እንደማይቻል አሳስበዋል።
የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ለመስጠት ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባቸው በመመሪያው ተገልጿል፡፡
በሙያው የተለየ ሥራ ያበረከተ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላ ዜጋ በመመሪያው የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ማግኘት እንደሚችል ጠቅሰዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን የተመለከተ መመሪያ (Guideline for the Bestowal of Honorary Doctorate Degrees in Ethiopian Higher Education Institutions) አዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው አካላት ሐምሌ 2017 ዓ.ም መላኩ ይታወቃል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#DireDawaUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3×4 መጠን የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) FAN No.፣
➫ ከአካባቢው የአየር ሁኔታ ጋር የሚስማማ እንሶላ እና ትራስ ልብስ፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#OdaBultumUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፦
በዩኒቨርሲቲው አዲሱ ካምፓስ
ትምህርት የሚጀምረው ህዳር 29/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ፓስፖርት መጠን የሆነ ስምንት ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#JinkaUniversity
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ለተመደቡ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ከጥቂት ቀናት በፊት ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ የምዝገባው ጥሪ ላልተወሰን ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
በመሆኑም በቀጣይ በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እስከሚደረግላቹ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#DillaUniversity
በዲላ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው ፕሮግራም የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ለመማር አመልክታችሁ ተቀባይነት ያገኛችሁ አመልካቾች ምዝገባ የሚካሔደው ህዳር 09 እና 10/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
የምዝገባ ቦታ
➫ በህክምናና ጤና ሳይንስ ዘርፍ ያለፋችሁ፦ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ (ሆስፒታል ግቢ) ሬጅስትራር ፅ/ቤት
➫ በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ያለፋችሁ፦ በኦዳያኣ ግቢ ዋና ሬጅስትራር ህንፃ ቁጥር 609
➫ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ያለፋችሁ፦ ነባሩ ግቢ ሬጅስትራር ፅ/ቤት
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒውን፣
➫ የቅርብ ጊዜ ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ Official Transcript ለዲላ ዩኒቨርሲቲ በፖ.ሳ.ቁ. 419 ወይም በኢ-ሜይል አድራሻ registrar@du.edu.et ማስላክ፣
➫ በመንግሥት ስፖንሰር የተደረጉ ከሆነ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርብዎታል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
#DebarkUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም እንዲሁም በቅጣት ህዳር 29/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ትምህርት የሚጀምረው ህዳር 29/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3×4 የሆነ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Photo unavailableShow in Telegram
ትምህርት ሚኒስቴር በዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤታማነት ላይ ጥናት እያካሔደ ነው፡፡
ጥናቱ በሦስት ወራት ውስጥ ተጠናቆ ይፋ እንደሚደረግ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
መንግሥት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በመጀመሪያ ዲግሪ ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከሰኔ 2015 ዓ.ም ጀምሮ እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል።
እስከ 250 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች በዓመት ሁለት ጊዜ የሚሰጠውን ፈተና እየወሰዱ መሆኑን የገለፁት መሪ ስራ አስፈጻሚው፤ ፈተናው ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት መቅሰም የሚጠበቅባቸውን ክህሎት እና እውቀት ለመፈተሽ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።
የመውጫ ፈተናውን ውጤታማነት በመገምገምና በቀጣይ መሰራት ያለበትን ሥራ በመለየት የአፈጻጸም ወጥነትን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ጥናት በቀጣይ ሦስት ወራት ተጠናቆ ይፋ ይደረጋል ብለዋል። #ኢዜአ
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
