es
Feedback
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

Ir al canal en Telegram

Journalist-at-large

Mostrar más
2025 año en númerossnowflakes fon
card fon
133 748
Suscriptores
-4624 horas
-1437 días
-61730 días
Archivo de publicaciones
Photo unavailableShow in Telegram
"አገር ከፖለቲካ ፓርቲዎች በላይ ናት" አቶ ቡልቻ ደመቅሳን ለዜና ግብዐትነት በርካታ ግዜ የማነጋገር እድል ገጥሞኝ ነበር። ግልፅ እና ለቆሙለት አላማ የቻሉትን ያህል የሚሞግቱ ሰው ሰው የሚሸቱ ፖለቲከኛ ነበሩ። በአንድ ወቅት ፓላማ ላይ "... እንዴት ኢትዮጵያ ይህን ያህል አደገች ይባላል?" ብለው ሲሞግቱ እንደተለመደው የፓርላማ አባሎች ግርርር ብለው ሲስቁ ብዙዎቻችን አይተናል። እውነታው ግን እሳቸው እኛ የማናውቀውን አውቀው ስለነበር ነው ብዬ አስባለሁ፣ መረጃ በመንግስታት እንደሚቀነባበር ስለሚገባቸው። የአለም ባንክ የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ሆነው እ.አ.አ ከ1970- 1974 እንደሰሩ ልብ ይሏል። ነፍስ ይማር! Photo: Dagu @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 623😢 166 120🙏 53🕊 19😁 5
Photo unavailableShow in Telegram
በአዋሽ ፈንታሌ እና ሌሎች አካባቢዎች የሚገኙትን ወገኖች በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት ሊከሰት ከሚችለው አደጋ ለማዳን በሚካሄደው እንቅስቃሴ ላይ የመከላከያ ተሽከርካሪዎች በስፋት እየተሳተፉ እንደሆነ ታውቋል 🙏🏽 @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 821 104🙏 83😁 46🕊 11🤔 7😱 5
Photo unavailableShow in Telegram
የከሰም ስኳር ፋብሪካ በሚታየው መልኩ በመሬት መንቀጥቀጡ ተጎድቷል፣ ከ400 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውሀ የያዘው እና ለስኳር ፋብሪካው ግብአት የሚሆነውን የሸንኮራ አገዳ ለማልማት የተሰራው ግዙፉ የከሰም ግድብ ያለበት ሁኔታ ግልፅ አይደለም የዛሬ ሶስት ወር ገደማ የፃፍኩትን መልሼ ላጋራው ⬇️ ከሰሞኑ ከሚያባንኑኝ ጉዳዮች አንዱ በቅርብ ቀናት አዋሽ አካባቢ የተከሰተው ርዕደ መሬት እና አያድርስ እና ከፍ ያለ መጠን ያለው መንቀጥቀጥ ቢከሰት በአካባቢው ያሉ ግድቦች ላይ መደርመስ አስከትሎ ዜጎች ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ነው። በአካባቢው ያለው ግዙፉ የከሰም ግድብ ላይ ጉዳት ቢደርስ ሊለቀው የሚችለው ግዙፍ የውሀ መጠን በታችኛው ተፋሰስ ላይ ያሉ ዜጎችን ሊውጥ ይችላል። "ግድቡ በክረምቱ ወቅት ግዙፍ የውሀ መጠን ይዞ ይገኛል፣ አደጋ ቢከሰት ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለማሰብ ይከብዳል" ያሉኝ አንድ ባለሙያ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም ለአደጋው ተጋልጠው ይገኛሉ ብለዋል። አደጋ ከደረሰ በኋላ "ብዬ ነበር" ማለት ወይም ከንፈር መምጠጥ ዋጋ የለውም፣ ስለዚህ ሌላው አለም ላይ እንደሚደረገው ቢያንስ ሁኔታው በደንብ እስኪጠና ተጋላጭ ወገኖችን ወደ ሌላ ቦታ ማስፈር ቢቻል እጅግ መልካም ነው።  እባካችሁ የሚመለከታችሁ አካላት ትኩረት፣ ትኩረት፣ ትኩረት! Photo: Tamiru Huliso @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 443 49🙏 17😢 16🕊 11😱 9
Photo unavailableShow in Telegram
የዚህ የመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል፣ ዛሬ ለሊት በሬክተር ስኬል የተመዘገበው 5.8 ደርሷል መንግስት አሁን ላይ ከምንም በላይ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፣ ሚድያው እና የሚመለከታቸው አካላት በአደጋ ወቅት ሊወሰዱ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች እና ዝግጅቶች ሊያስቡበት ይገባል። ለረጅም ሳምንታት እየተከሰተ ስለቆየ ህዝቡ የተላመደው ይመስላል፣ ይህ አደገኛ ነው። ጥንቃቄ፣ ጥንቃቄ፣ ጥንቃቄ በዚህ ዙርያ መሠረት ሚድያ ከአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አንድ ባለሙያ ጋር ቃለመጠይቅ አድርጎ ያቀርባል።። ፈጣሪ ሀገራችንን እና ህዝባችንን ይጠብቅ! @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 760🙏 242 81😢 47🤔 7🕊 3😁 2😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
ይሄ በመንግስት የተወሰደ እርምጃ ትክክለኛ እና ወቅቱን የጠበቀ ነው ቡሩንዲ ወታደራቿን ልታስወጣ ስለሆነ የኢትዮጵያ ሀይልን ከአፍሪካ ህብረት የተልእኮ ጦር ጋር ቀላቅሎ በሶማልያ ለማቆየት መልካም አጋጣሚ ነው። የዛሬ አመት በዚህ ሳምንት የተፈፀመው የዲፕሎማሲ ስብራትን ለመጠገን የተወሰደ ጥሩ አካሄድ ነው።  በሌላ በኩል የፑንትላንድ አስተዳደር ከኢትዮጵያ ወደ ግዛቲቱ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ምንም ታክስ እንዳይከፍሉ እና ታርጋ ሳይቀይሩ እንዲንቀሳቀሱ ፈቅዷል፣ ይህም ራሱን የቻለ ጥቅም አለው ተብሎ ይታሰባል። @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 622 75😁 56🤔 17😱 9😢 3
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ፕ/ር አታላይ አየለ ከሰሞኑ ህዝቡን እየረበሸ እና እያሳሰበ በሚገኘው የመሬት መንቀጥቀጥ ዙርያ ለቲክቫህ ሚድያ በሰጡት አስተያየት "መሬት በራሷ ጉዞ እየሄደች የምታስተነፍሰው ሃይል ነው ምንም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም ቦታውም፣ በምን ያህል ርቀት ላይ እንደሆነ ይታወቃል በተለይ አዲስ አበባ ያለ ሰው ምንም ሊደነግጥ አይገባም" የሚል አስገራሚ ምላሽ ሰጥተው ተመለከትኩ። - የመሬት መንቀጥቀጡ በአዋሽ አካባቢ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እያፈናቀለ በሚገኝበት ወቅት - በርካታ ህንፃዎች፣ የመኖርያ ቤቶች እና መንገድ ጭምር እየተሰነጣጠቀ ባለበት ግዜ፣ እንዲሁም - ይህ ሁሉ የመሬት መንቀጥቀጥ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ እየተከሰተ ባለበት ሀገር ውስጥ በአደጋ ወቅት ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ይህ ነው የሚባል ስራ ባልተሰራበት ሁኔታ እንዲህ አይነት 'አታስቡ' እና 'አትደንግጡ' አይነት አስተያየት ፍፁም ተገቢ ያልሆነ እና ህዝብን ይበልጥ ለአደጋ ሊዳርግ የሚችል ሆኖ ተሰምቶኛል። @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 1 242😁 125 71🙏 57🤔 40😢 28😱 12🕊 4
በትናንትናው እለት በ100 አመታቸው ያረፉት የቀድሞው የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር የኢትዮጵያ ወዳጅ ነበሩ የካርተር ማዕከል (The Carter Center) እንደ ትራኮማ፣ የጊኒ ትል በሽታ፣ ወባ እና ወዘተ ያሉ በሽታዎችን ከመከላከል እስከ የምግብ ምርት ማሳደግ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም ከምርጫ ታዛቢነት እስከ እርቅ ማፈላለግ ባሉ ስራዎች ላይ በሀገራችን በስፋት ተሳትፋል። አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ምናልባትም የጂሚ ካርተር ተቋም በአለም ዙርያ ካሉት ስራዎቹ ሁሉ ትልቁን ያከናወነው በኢትዮጵያ ነው፣ በዚህም በአብዛኛው የሀገራችን የገጠራማ አካባቢዎች ነዋሪ ተጠቃሚ ሆኗል። ብዙዎች የካርተር ማዕከልን የሚያስታውሱት ምርጫ 97'ን ተከትሎ የተገደሉ ንፁሁንን በማውገዙ እና ምርጫው ላይ የታዩ ጉድለቶችን በግልፅ በማሳወቁ ነበር። ደርግ ሊወድቅ ሰሞን ደግሞ በኮሎኔል መንግስቱ እና በህወሓት እንዲሁም የኤርትራ ሀይሎች መሀል የሰላም ንግግር ናይሮቢ ላይ አስጀምረው ነበር። የአሜሪካ ተንታኞች ጂሚ ካርተርን ከቀደሙት መሪዎች ሁሉ ከስልጣን ከወረዱ በሗላ ከፍተኛ ተፅእኖ የፈጠሩት ናቸው ይሏቸዋል፣ ሀገራችንም አንዷ ተጠቃሚ ነበረች። እናመሰግናለን፣ ነፍስ ይማር! @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 596🙏 128 74😁 32😢 19🤔 12🕊 12😱 7
Photo unavailableShow in Telegram
በሲዳማ ክልል በቦና ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችን ቁጥር 71 መድረሱ ታውቋል እጅግ ያሳዝናል፣ ነፍስ ይማር! @EliasMeseret
Mostrar todo...
😢 873😱 43👍 24🙏 24 12
Photo unavailableShow in Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ ዳር አበባ እና ሳር ለማጠጣት የሚውለው የመጠጥ ውሀ በመሆኑ ህዝቡ መቸገሩ ታወቀ (መሠረት ሚድያ)- በአዲስ አበባ ከተማ በተለይ በቅርብ ግዜያት ከተሰሩ የኮሪደር ልማቶች ጋር ተያይዞ ለተተከሉ የመንገድ ዳር አትክልትና ሳር ለማጠጣት የሚውለው ውሀ ለነዋሪዎች መጠጥ ከሚያገለግል የውሀ መስመር በመሆኑ ህዝቡ ውሀ መቸገሩ ታወቀ። ተጨማሪ ያንብቡ: https://t.me/meseretmedia/736 Via @MeseretMedia @EliasMeseret
Mostrar todo...
😱 371😢 313👍 196😁 74🤔 49 27
Photo unavailableShow in Telegram
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ መንግስት ራሱ በምንጭነት የሚጠቅሳቸው ተቋማት ደግሞ ከ120 ሚልዮን ህዝባችን ውስጥ 86 ሚልዮኑ በድህነት ውስጥ እንደሚገኝ እየነገሩን ነው የህዝቡን ምሬት፣ እሮሮ እና ስቃይ ደግሞ እለት ከእለት በግልፅ እያየነው ነው። ኢኮኖሚያችንን ፕላን የሚያረጉልን ደግሞ ስሌታቸው ስክሪንሾቱ ላይ ያለውን እያሳያቸው ነው። ችግር ሲያጋጥም ጭንቅላትን ብቻ ለይቶ አሸዋ ውስጥ መቅበር ማለት ይህ ነው።  @EliasMeseret
Mostrar todo...
😢 807👍 301😁 81 54🤔 30😱 3
Journalism is not just about speaking to those in power; it is about speaking truth to power ✊️ #Journalism @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 1 823 292🙏 79🕊 31😁 28🤔 20😢 2
Thank you, America! የእነዛ በርሀብ የተጎዱ ምስኪን ህፃናት ምስል ከአእምሮ አይጠፋም። https://t.me/meseretmedia/731
Mostrar todo...
👍 839🙏 268 71😢 48🕊 13🤔 12
"ጠንካራ ዲፕሎማሲ... " ብሎ ለኮመተ ክፍያ ተጀመረ እንዴ? አንዳንዴ እኮ አንሰማም፣ የሰማችሁ አሳውቁን። #የሚድያሰራዊት Via Inbox @EliasMeseret
Mostrar todo...
😁 1 848👍 139🤔 39🙏 28😢 22😱 13 12
#መልካምዜና ሚያንማር ውስጥ እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለማውጣት እንቅስቃሴ ተጀምሯል በቅርቡ ያጋራሁትን ይህን ከታች የሚታይ ካርታ መነሻ በማድረግ ምርመራ እንደተደረገ እና በቻይና ጋንግ ቡድን ታግተው የሚገኙትን 1,300 ገደማ ዜጎች ለማውጣት የውጭ ጉዳይ አንድ ቡድን ወደ ስፍራው እንደሚጓዝ ታውቋል። ይሁንና እኔ ካጋራሁት ቦታ በተጨማሪ ሌሎች ስፍራዎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ። በእነሱ ዙርያ ምንም እንቅስቃሴ እንዳልተጀመረ አሳውቀውኛል ስለዚህ ለክትትል እንዲመች ቦታዎቹን ከታች አስቀምጣቸዋለሁ። @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 632🙏 112 51😁 16😱 11😢 9🤔 5🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
"ጡጦ የምልበት አቅም የለኝም። ጡቴን ብቻ ነው ሳጠባቸው የከረምኩት። የጡት ወተት አሁን አነሳቸው፤ እንዴት ይድረሳቸው?. . . የተገኘው ምግብም አልሆናቸው አለ፤ አልስማማቸው አለ።" ይህ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ ዛሬ ላይ ያለው ሁኔታ ነው... መቸስ አይናችን እያየ ከሚረግፉ ህዝብ ያለውን አሰባስቦ ቢረዳስ? በዚህ ዙርያ ለማስተባበር የምትችሉ እንነጋገር፣ ይህም ስም ካልተሰጠው እና ካልተከለከለ ማለት ነው። Quote via BBC Amharic @EliasMeseret
Mostrar todo...
😢 1 019👍 208🙏 46 34😱 13🤔 8🕊 5
Photo unavailableShow in Telegram
1. "30 አመት ውጪ ሀገር ታክሲ እየሰራህ እዚህ መጮህ አይቻልም..." 2. "ዛሬ የአሜሪካንን ድሪም ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር ችለናል..." ... አለ አፍሪካን የሚወክል ሚድያ አዲስ አበባ ላይ ላቋቁም ነው ብሎ ከመንግስት በተሰጠው ሁለት ሰፋፊ ቦታ ከባድ ጆካ የተጫወተው ወንድማችን... አሜሪካን ሀገር Seattle ከተማ ላይ ደግሞ የገዛውን ጭውቴ እናውቃለን። #የዛሬይቱኢትዮጵያ  በሰፊው እመለስበታለሁ... @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 1 088😁 403 56🤔 32😢 31🙏 17😱 16🕊 12
Photo unavailableShow in Telegram
የቀድሞው ምክትል ጠ/ሚር አቶ ደመቀ መኮንን አፍሪካ ውስጥ ያሉ ህፃናትን መቀንጨር የሚከላከል ድርጅት እንዳቋቋሙ ዛሬ ሰማን ድርጅታቸው ለግዜው አፍሪካን ትቶ እሳቸው የወጡበት የአማራ ክልል ውስጥ እንዲህ በርሀብ እየተጎዱ ያሉ ህፃናት ላይ ትኩረት ቢያደርግ እላለሁ። ይህ የ1977 ድርቅ ሳይሆን አሁን ላይ የኢትዮጵያ ህፃናት ምንም በማያውቁት እያለፉበት ያለ ስቃይ ነው፣ አንዳንዱ ህዝባችን ደግሞ "ጦርነት አቁሙ በሏቸው፣ ወይም ርሀቡ ይቀጥላል" እያለ በህፃናቱ መሳለቅ ይዟል። እንደ ህዝብ መጨረሻችን ይህ መሆኑ ያሳዝናል። Photo: Belay Manaye @EliasMeseret
Mostrar todo...
😢 1 170👍 283 47😁 35🤔 18😱 9🕊 9🙏 4
Mostrar todo...
👍 182😢 31 13🤔 10😁 6
#MyOpinion በዚህ ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ የዛሬ 11 ወር ገደማ ከሶማሊላንድ ጋር የፈረመችው ስምምነት ከዚህ በኋላ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው መረዳት ይቻላል። በሌላ በኩል "የሶማሊላንዱ ስምምነት በስም ተጠቅሶ ተሰርዟል ካልተባለ ለስምምነት አንቀመጥም" ሲሉ የነበሩት የሶማልያ መሪዎች የፈለጉትን ሳያገኙ ቀርተዋል። በዋናነት ግን ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ የባህር በር የማግኘት አካሄዷን በሞቃዲሾ በኩል ለማድረግ መስማማቷ ሶማሌዎችን ዋናው የስምምነቱ ተጠቃሚ አድርጓቸዋል። ሲቀጥል ስምምነቱ የግብፅ ጦር ከሶማልያ እንዲወጣ የሚል ነጥብ አልተካተተበትም።  ለዲፕሎማሲያችን ትልቅ፣ ትልቅ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ክስተት ሆኖ ማለፉ ግልፅ ነው... ግን ቢያንስ ጦርነት ማስቀረት መቻሉ ትልቁ ትርፍ ነው። "ይሄ አካሄድ ግን ያስኬዳል?" ብለን በወቅቱ የጠየቅን የተለያየ ስም ሲሰጠን ነበር። የሆነው ይሁን... ከዚህ ክስተት መማር ከቻልን መልካም፣ ካልሆነ ግን የሀገርን ዲፕሎማሲ ብቻ ሳይሆን ታሪክ እና ጥቅም በእጅጉ የሚጎዳ መሆኑ ግልፅ ነው። @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 1 005 88😁 74🙏 36🤔 27😱 4🕊 3😢 2
Photo unavailableShow in Telegram
አስታራቂ አይጥፋ! Peace is what we need. @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 484😁 163 71🕊 42🙏 16😱 11🤔 8😢 5