fa
Feedback
"زاد المعاد" ዛዱልመዓድ- የነገው ስንቅ

"زاد المعاد" ዛዱልመዓድ- የነገው ስንቅ

رفتن به کانال در Telegram

በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም የሚዘጋጁ ተከታታይ ትምህርቶች፣ ፈትዋዎች፣ ኹጥባዎች: ሙሓደራዎችና አጫጭር ምክሮች የሚቀርቡበት ቻናል القناة التعليمية الرسمية لأبي عبد الله أحمد بن آدم الشراري دروس في القرآن والعقيدة والفقه وفتاوى وخُطب ومقالات متنوعة باللغة الأمهرية http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

نمایش بیشتر
2025 سال در اعدادsnowflakes fon
card fon
71 484
مشترکین
+724 ساعت
+1597 روز
+33330 روز
آرشیو پست ها
📝 ዛዱል መዓድ የፅሁፍ ፈታዋ           ቁ/01       ዕለተ ረቡዕ 26/6/1447 ዓ.ሂ ✍ በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ጥያቄ 1⃣ ፡- ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን ትምህርት እንዲከታተሉ መስጂድ ማስገባት ይቻላልን? መልስ 1⃣ ፡- ሙስሊም ያልሆነን ሰው የተከበረውን የመካህ መስጂድ (መስጂደል-ሐራም እና የሐረም ክልል) ማስገባት በጥብቅ ይከለከላል። ይህም በአሏህ በተከበረው ቃል በአት-ተውባህ ምዕራፍ አንቀጽ 28 ላይ ሰፍሯል፤ ምክንያቱንም ከላይ ገልጸናል።  ከመካህ ታላቁ መስጂድና ከሐረም ክልል ውጪ ወዳሉ ሌሎች መስጂዶች ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን መግባት በተመለከተ ከሊቃውንት አስተያየቶች ውስጥ ሚዛን የሚደፋው መግባታቸው አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘና ሸሪዓህ የሚደግፈውና የሚፈቅደው በቂ ምክንያት እስካለ ድረስ ለምሳሌ ሙስሊም ያልሆነ ሰው ወደ ኢስላም እንዲገባ የሚያነሳሳውን ኢስላማዊ ትምህርት ለመከታተል፣ የጁምዓ (አርብ ቀን) ሳምንታዊ ስግደት ላይ የሚተላለፈውን መልዕክት ወይም ኹጥባህ ለመስማት፣ ከሐይማኖቱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ጥያቄዎችን መልስ ለማግኘት ወይም ውኋ ጠምቶት መስጂድ ውስጥ እንጂ ሌላ ቦታ ላይ የማያገኝ ከሆነ ለመጠጣት ወዘተ መሰል ምክንያቶች የመስጂድን ክብርና ስርዓት በጠበቀ መልኩ ጥበቃና መሰል ሌሎችን ስፍራው ላይ የሚገኙ ሰዎችን አስፈቅዶ መግባት ይችላል የሚለው አስተያየት ነው። ነቢዩ ሙሐመድ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም “ሠቂፍ” የሚባሉ የዐረብ ጎሳዎችን ልኡካን እና “ነጅራን” ከሚባል አካባቢ የመጡ ክርስቲያኖችን ሙስሊሞች ካለመሆናቸው ጋር መስጂድ ውስጥ ተቀብለው ማስተናገዳቸው ይታወቃል:: ይህንንም ያደረጉት ከተለያዩ ምክንያቶች አንጻር ሲሆን የሚከተሉት ሁለት ነገሮች እንደ ዋና ምክንያት ይጠቀሳሉ፥ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚያደርጓቸውን ኹጥባዎች (ድስኩሮች) እና ምክሮችን ይሰሙ ዘንድ፣ ሙስሊሞች ለጌታቸው ሲሰግዱ ያዩና ቁርኣንም ይሰሙ ዘንድ ነው። መስጂድ እንዲያርፉ ያደረጉበት ምክንያት ይህ ብቻ ሳይሆን ሌላም ሙስሊሞች ጋር በመቀራርባቸውና መስጂድ በመቆየታቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ስለነበሩ ነው ። ነገር ግን ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች መስጂድ መግባታቸው ከላይ ከተጠቀሱት ጥቅሞች በተቃራኒ መስጂዶች ወይም ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ወይም ጉዳት ያደርሳሉ ተብሎ እስካልተሰጋ ድረስ ብቻ ነው። እንዲህ ዓይነት ስጋት ካለ ወይም ለጸብ የሚዳርግ ከሆነ መግባቱ የተከለከለ ይሆናል። ጥያቄ 2⃣ ፡- አንዳንዴ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች ቤት ውስጥ እያለን የሰላት ወቅት ይደርሳል፤ እዛው መስገጃ አንጥፈን ብንሰግድ ሰላታችን ትክክል ይሆናልን? መልስ 2⃣ ፡- አዎን መስገድ ይቻላል። ነገር ግን በአቅራቢያ መስጂድ ካለ ወንዶች መስጂድ ሄደው ከሙስሊሞች ጋር በጋራ መስገድ ግዴታ ይሆንባቸዋል። ሴቶችም ካልተቸገሩና የሚያሰጋ ነገር ከሌለ ኢስላማዊ አደብን በጠበቀ መልኩ መስጂድ ሄደው መስገድ ይችላሉ። ነገር ግን እንደ ወንዶች ግዴታ አይሆንባቸውም። ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች ቤት ውስጥ በሚሰገድበት ጊዜ በቂብላ (በሰላት አቅጣጫ) በኩል የተሰቀለ ፎቶና ስዕል ነገሮች መኖር የለባቸውም፤ በተለይም የሚመለኩ ምስሎች ከሆኑ መነሳት ይህም ካልተቻለ መሸፈን አለባቸው። ይህ ካልሆነ ግን ሌላ ቦታ ላይ ሄዶ መስገድ ይገባል። ጥያቄ 3⃣ ፡- ሙስሊም ያልነበረ ሰው ከመስለሙ በፊት የሰራቸው መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ ይመዘገቡለታልን? መልስ 3⃣ ፡- አቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ የተባሉት የነቢዩ ﷺ ባልደረባ እንዳስተላለፉት ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል፥ “አንድ ሰው የሰለመና እስልምናውም ያማረ እንደሆነ ከዛ በፊት የሰራቸው መልካም ስራዎችን በሙሉ አላህ የመልካም ሥራ መዝገቡ ላይ ያሰፍርለታል። የሰራቸው ሐጢኣቶችንም ይቅር ይለዋል። ከዛ በኋላ እንደ ስራው ይመነዳዋል። አንድ መልካም ስራ ከሰራ በ10 እና እስከ 700 እጥፍና ከዛም በላይ ሊደርስ በሚችል ምንዳ ሲመነዳው፤ አንዲትን ሐጢኣት ከሰራ ደግሞ በሰራው ሐጢኣት ልክ ብቻ ይመነዳል፤ ይህም አላህ ይቅር ካላለው ነው” ብለዋል። በዚህም መሰረት አንድ ሙስሊም ያልነበረ ሰው ከመስለሙ በፊት እንደ ምጽዋት መስጠትና ዝምድናን መቀጠል ያሉ መሰል መልካም ስራዎችን ይሰራ ከነበረና ከዛም ኢስላምን ተቀብሎ በዛው ጸንቶ ከሞተ የነዚህን መልካም ተግባራት ምንዳ አላህ ዘንድ ያገኘዋል። ነቢዩ ሙሐመድ ሰለለሁ ዐለይሂ ወሰለም በርሳቸው ዘመን ኢስላምን ለተቀበለ ሐኪም ኢብኑ ሒዛም ለሚባል አንድ ባልደረባቸው "አስቀድመህ ከሰራሃቸው መልካም ሰራዎችህ ጋር አብረህ ነው የሰለምከው" ብለውታል። ይህ ንግግራቸው ለሐኪም ኢብኑ ሒዛም ብቻ ሳይሆን ተመሳሳይ ሁኔታ ላላቸው ሰዎች በሙሉ ያገለግላል። ጥያቄ 4⃣ ፡- ሰውነቱ ላይ ንቅሳት ያለበት ሰው ምን ማድረግ ይጠበቅበታል? መልስ 4⃣ ፡- ንቅሳት በኢስላም ለወንድም ይሁን ለሴት የተከለከለ ነው። በልጅነቱ ቤተሰቦቹ የነቀሱት ሰው እሱ ምንም አይጠየቅም፤ ተጠያቂዎቹ ቤተሰቦቹ ናቸው። እራሱ የተነቀሰ ወይም ያስነቀሰ ሰው አላህ ዘንድ ይጠየቃል። ነገር ግን ሙስሊም ያልነበረ ሰው ኢስላምን ሲቀበል ሁሉም ያለፉ ወንጀሎቹ ይሰረዙለታል። ሆኖም ግን ማንኛውም ሰውነቱ ላይ ንቅሳት ያለበት ሰው የጤና ባለሞያዎችን አማክሮ ንቅሳቱን ማጥፋት ይጠበቅበታል። በምንም መልኩ ማጥፋቱ ካልተቻለ ከአቅም በላይ በሆነ ነገር አላህ አይጠይቅም። ነገር ግን በተቻለ ያክል ንቅሳቱን ሰዎች እንዳያዩት ለማድረግ መሞከር ይገባል።     🔹🔸🔹🔸🔹🔸 💥 በተጨማሪም የተለያዩ ፔጆቻችንን ለመቀላቀልና ዌብሳይታችንን ለማግኘት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ 🌐 https://zadulmead.org ✔️ https://telegram.me/ahmedadem ✔️https://facebook.com/yenegew ✔️https://youtube.com/@Zadul-Mead ✔️ https://x.com/zadul__mead ✔️https://instagram.com/zadulmead አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:- 🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ "ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197
نمایش همه...
ስድስቱ የሙስሊም መብትና ግዴታዎች.mp314.71 MB
📢  ሙሓደራ 🫟 ድስቱ የሙስሊም መብትና ግዴታዎች 🔊 በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም የዕለተ እሁድ 23/6/1447 ዓ.ሂ ትምህርት      ዳውንሎድ ሊንኩን ለማግኘት   ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️       https://is.gd/6haqsofmuslim                 ዛዱል መዓድ 🔹🔸🔹🔸🔹🔸 🌐 https://zadulmead.org ✔️ https://telegram.me/ahmedadem ✔️https://facebook.com/yenegew ✔️https://youtube.com/@Zadul-Mead ✔️ https://x.com/zadul__mead ✔️https://instagram.com/zadulmead አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:- 🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ "ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197
نمایش همه...
#የዚህ ሳምንት ከመግሪብ እስከ ዒሻእ ደርስ አይኖርም በአላህ ፈቃድ ቀጣይ ሳምንት ይቀጥላል።
نمایش همه...
4_5895638677358386427.mp313.35 MB
🌳የቁርኣን ተፍሲር🌳           ክ/304 🔹تفسير سورة ص 🔮 የሱረቱ ሷድ ተፍሲር ቁ/5 (ከ34-40)       የዕለተ ጁሙዓ 21/6/1447 ዓ.ሂ. የቁርኣን ትምህርት 🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም     የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ          ⬇ ⬇ ⬇ ⬇ 🔎 https://is.gd/eIgBEZ 🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸 💥 በተጨማሪም የተለያዩ ፔጆቻችንን ለመቀላቀልና ዌብሳይታችንን ለማግኘት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ 🌐 https://zadulmead.org ✔️ https://telegram.me/ahmedadem ✔️https://facebook.com/yenegew ✔️https://www.youtube.com/@Zadul-Mead ✔️ https://x.com/zadul__mead ✔️https://instagram.com/zadulmead 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ
نمایش همه...
(304) የዛዱል መዓድ ፈታዋ.mp38.29 MB
የዛዱል መዓድ ፈታዋ 🌾 فتاوى زاد المعاد           ቁ/304         ረቡዕ 19/6/1447 ዓ.ሂ 🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም         የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ        🔽🔽🔽🔽🔽🔽      🔗 https://is.gd/fetawa_303   🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹 ▪️1/ እድሜያቸው የገፋ ሴቶች ወይም ብዙ ከሆኑ ያለ መህረም ሀጅ ማድረግ ይቻላል የሚል ፈትዋ እየሰሙ ሴት እህቶቻችን በዚህ መልኩ እየሄዱ ነው በዚህ ጉዳይ ምክር ቢሰጠን በነፃ ቪዛ አገኘን በሚል በተሣሣተ ፈትዋ ለመሄድ የተነሱ እህቶች ስላሉ ቢነገራቸው። ▪️2/ ክርስቲያን አጎቴ ላይ መሸፈን አለብኝ? ▪️3/ የወሊድ መከላከያ የምትጠቀም ሴት ሀይድ አይታ ከጨረሰች በሗላ የሚፈስ ፈሳሽ ፆሟን እና ሰላቷን ያበላሻል? በዚህ መልኩ የሰገደችውና የፆመችው ቀዷ ማውጣት አለባት? ▪️4/ አንድ ሰው ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ቤት ቢኖረውና ለሙስሊሞች መኖሪያ ምቹ ካልሆነ ለቤተ ክርስቲያን መሸጥ ይቻላል ወይ? ▪️5/ ኢማሙ ሩኩዕ ላይ እያለ የደረሰ ሰው ፋቲሀን ሳይቀራ ሩኩዕ ቢያደርግ ሰላቱ ሙሉ ይሆናል ወይ? ▪️6/ ሙሳን ያናገረው ኸድር ነብይ ነው ወይስ አይደለም? ▪️7/ ብዙ ግዜ ቤት ስገባ መግቢያ አከባቢ ኻዲሞች ካሉ አሰላሙ አለይኩም ብዬ እገባለሁ ባለቤቴ ግን ጥሩ አይደለም አትበላቸው ትለኛለች እኔ ግን ሙስሊም እስከሆኑ ከኛም እኩል ናቸው እያልኩኝ ነው እኔ ከተሳሳትኩ ልመለስ ወይም እሷ ከተሳሳተች እሷ ትመለስ ለዚህ ማብራሪያ ስጡን። ▪️8/ አንድ ሙስሊም እህታችን ናት ሙተነቂብ ናት በጅልባብ ውስጥ ቁምጣ ትለብሳለች ከለበስሽም ሰፊ ሱሪ ልበሺ ስንላት ዲናችን ገር ነው አይቻልም የሚል ማስረጃ አምጡልኝ አለች አሁን ይባስ ብላ ለካፊር ሴቶች እያሣየች ነው እስልምና ገር ነው እያለች ያብራሩልን። ▪️9/ ባለቤቴ ከሌላ ሴት ጋር የሀራም ግንኙነት ጀምሯል አብረን አልጋ ከተጋራን 4 አመት ሆኗል የሀራም ግኑኝነት እንደጀመረ ከማወቄም ጋር ለትዳሬ ብዬ ዝምታን መርጬያለሁ ይህ ዝምታዬ ከሸሪአ አንፃር እንዴት ይታያል? ፍቺስ መጠየቅ እችላለሁ?ፍቺ ጠይቄ ብፈታ ዒዳ መቁጠር ይጠበቅብኛል? 4 አመት ሙሉ ግንኙነት ስላላደረግን። ይሄ የሚሆነው በዝሙት ላይ ስለወደቀ ነው።     🔹🔸🔹🔸🔹🔸 💥 በተጨማሪም የተለያዩ ፔጆቻችንን ለመቀላቀልና ዌብሳይታችንን ለማግኘት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ 🌐 https://zadulmead.org ✔️ https://telegram.me/ahmedadem ✔️https://facebook.com/yenegew ✔️https://youtube.com/@Zadul-Mead ✔️ https://x.com/zadul__mead ✔️https://instagram.com/zadulmead አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:- 🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ "ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197
نمایش همه...
የዛሬው ደርስ የሚጀምረው ሱረቱል አል-ሙእሚኑን አንቀፅ 57 ነው
نمایش همه...
(341) የወቅፍ ምንነትና ትሩፋት.mp36.25 MB
🌾የጁሙዓ ኹጥባ ቁ/341 🌾 🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም           የወቅፍ ምንነትና ትሩፋት           እሁድ 16/6/1447 ዓ.ሂ                 ዛዱል መዓድ           የዳውንሎድ ሊንኩን ለማግኘት              🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽    🔗 https://is.gd/khutuba_341         🔸🔹🔸🔹🔸🔹 💥 በተጨማሪም የተለያዩ ፔጆቻችንን ለመቀላቀልና ዌብሳይታችንን ለማግኘት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ 🌐 https://zadulmead.org/ ✔️ https://telegram.me/ahmedadem ✔️https://facebook.com/yenegew ✔️https://youtube.com/@Zadul-Mead ✔️ https://x.com/zadul__mead ✔️https://instagram.com/zadulmead 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ
نمایش همه...
ከጥቂት የተፍሲር ፕሮግራም በቀጥታ ይተላለፈል ሱረቱል ሙዕሚኑን አንቀፅ 45 - 56
نمایش همه...
تفسير سورة ص 4 mnk.mp312.52 MB
🌳የቁርኣን ተፍሲር🌳           ክ/303 🔹تفسير سورة ص 🔮 የሱረቱ ሷድ ተፍሲር ቁ/4 (ከ26-33)       የዕለተ ጁሙዓ 14/6/1447 ዓ.ሂ. የቁርኣን ትምህርት 🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም     የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ          ⬇ ⬇ ⬇ ⬇ 🔎 https://is.gd/B8qcsk 🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸 💥 በተጨማሪም የተለያዩ ፔጆቻችንን ለመቀላቀልና ዌብሳይታችንን ለማግኘት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ 🌐 https://zadulmead.org ✔️ https://telegram.me/ahmedadem ✔️https://facebook.com/yenegew ✔️https://www.youtube.com/@Zadul-Mead ✔️ https://x.com/zadul__mead ✔️https://instagram.com/zadulmead 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ
نمایش همه...