fa
Feedback
YeneTube

YeneTube

رفتن به کانال در Telegram

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

نمایش بیشتر
2025 سال در اعدادsnowflakes fon
card fon
107 485
مشترکین
-5524 ساعت
-4277 روز
-2 16930 روز
آرشیو پست ها
#የአፍሪካ_ህብረት#ሶማሊላንድን እውቅና ውድቅ አደረገ፤ ለሶማሊያ “የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት” ያለውን "ጽኑ ቁርጠኝነት" አረጋገጠ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ሶማሊላንድን እንደ ገለልተኛ ሀገር እውቅና ለመስጠት የሚደረገውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ ውድቅ ማድረጋቸውንና ህብረቱ ለሶማሊያ "አንድነት እና ሉዓላዊነት ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት" በድጋሚ አረጋግጠዋል። "ከሶማሊላንድ ጋር በተያያዙ የቅርብ ጊዜ ክስተቶች" ላይ በሰጡት መግለጫ፤ ዩሱፍ እንደተናገሩት የአፍሪካ ህብረት በውህደት ስምምነቱ (Constitutive Act) መርሆዎች ላይ የተመሰረተውን "ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ እና ወጥ የሆነ አቋሙን በማያሻማ ሁኔታ በድጋሚ ያረጋግጣል" ብለዋል። ሊቀመንበሩ አክለውም የህብረቱ አቋም በተለይም የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁኑ አፍሪካ ህብረት) እ.ኤ.አ በ1964 ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት "ከነፃነት በኋላ የተወረሱ ድንበሮች የማይደፈሩ መሆናቸውን በማክበር" ላይ የተመሰረተ መሆኑን አሳስበዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር "ሶማሊላንድን እንደ ገለልተኛ አካል እውቅና ለመስጠት ያለመ ማንኛውንም ተነሳሽነት ወይም እርምጃ በፅኑ ውድቅ ያደርጋሉ" ያለው መግለጫው፤ "ሶማሊላንድ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ አካል ሆና ትቀጥላለች" ሲል አክሏል። ሊቀመንበሩ "የሶማሊያን አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማዳከም የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ ከአፍሪካ ህብረት መሰረታዊ መርሆች ጋር ይቃረናል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በተጨማሪም እንዲህ ያሉ እርምጃዎች "በአህጉሪቱ ሰላምና መረጋጋት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድር አደገኛ አርአያነት የመፍጠር አደጋ አላቸው" ብለዋል። AS. @Yenetube @Fikerassefa
نمایش همه...
እስራኤል ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና በይፋ መስጠቷን አስታወቀች የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አገራቸው የሶማሊላንድ ሪፐብሊክን እንደ ነጻ እና ሉዓላዊት ሀገር በይፋ መቀበሉን አስታወቁ። ይህም በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ለውጥ መሆኑ ተገልጿል። ኔታንያሁ ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ዕውቅናው የተረጋገጠው ከእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር እና ከሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ ጋር በጋራ በተፈረመ "የሁለትዮሽ ስምምነት" አማካኝነት ነው። ጠ/ሚሩ በመግለጫቸው ቀደም ሲል በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አነሳሽነት የተፈረመውን "የአብርሃም ስምምነት" መንፈስን የተከተለ መሆኑን ገልፀዋል። ነታንያሁ ፕሬዝዳንት አብዲራህማንን "ታሪካዊ መግለጫ" ባሉት በዚህ ስምምነት ላይ እንኳን ደስ ያለዎት ያሏቸው ሲሆን፤ ለሰላም እና ለመረጋጋት ላሳዩት ቁርጠኝነትና አመራር ምስጋና አቅርበውላቸዋል። በተጨማሪም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት በእስራኤል ይፋዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ ግብዣ አቅርበውላቸዋል። እንደ ኔታንያሁ ገለጻ፣ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን በወሰዱት እርምጃ ደስታቸውን ገልጸው፤ እስራኤል ሽብርተኝነትን በመዋጋትና ቀጣናዊ ሰላምን በማስፈን ረገድ ለምትጫወተው ሚና ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ ሂደት መሳካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ሳር፣ የሞሳድ ዳይሬክተር ዴቪድ ባርኒያ እና የእስራኤል የደህንነት ተቋማት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ሰጥተዋል። ነታንያሁ እንደገለጹት፤ እስራኤል በግብርና፣ በጤና፣ በቴክኖሎጂ እና በኢኮኖሚ ዘርፎች በሚደረጉ ሰፊ ትብብሮች አማካኝነት ከሶማሊላንድ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማስፋፋት አቅዳለች። Via አዲስ ስታንዳርድ @Yenetube @Fikerassefa
نمایش همه...
46🔥 7👎 2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ የጸጥታ ግምገማ እንዲቀርብለት ጠየቀ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  በትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩን ለመወሰን፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ይፋዊ የጸጥታ ሁኔታ ግምገማ እየጠበቀ መሆኑን አስታወቀ። ምርጫ ቦርድ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጸው፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ የምርጫ ወረዳዎችን በጸጥታ ሁኔታቸው ላይ በመመስረት በአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀጠናዎች በሚል በመለየት ሪፖርት እንዲያቀርብ በይፋ ጠይቋል። ቦርዱ ይህ መረጃ ሳይደርሰው በትግራይ ክልል ምርጫ ስለማካሄድ ምንም ዓይነት ውሳኔ ላይ መድረስ እንደማይችል ገልጿል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጄኔራል ታደሰ ጥያቄው እንደቀረበላው ገልፀዋል። በክልሉ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ወይስ አይቻልም በሚለው ጉዳይ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተን ምላሽ እንሰጣለን ያሉት ጀነራል ታደሰ ፣ ምላሹም በዚህ ሳምንት ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል። @Yenetube @Fikerassefa
نمایش همه...
10👍 1
🚀 Get Found. Get Hired. Get Work Done. Are you a professional looking for job opportunities? Are you an employer or service seeker searching for skilled talent? ✅ Register on Jitume and make your profile visible to employers and clients across Ethiopia. 🔹 Open to ALL professions 🔹 Free & easy registration 🔹 Employers can directly find and contact you 🔹 Service seekers can choose verified professionals 👉 Register now and be visible: 🌐 https://jitume.gebeya.com/?utm_source=Jasper&utm_medium=tesfaye_guta_367010&utm_campaign=Jasper 📣 Don’t wait for opportunities—put yourself where opportunities find you!
نمایش همه...
2
Photo unavailableShow in Telegram
አሜሪካ በናይጄሪያ አይኤስ ላይ "ከባድ ጥቃት" ማድረሷን ትራምፕ ተናገሩ! ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ዩናይትድ ስቴትስ በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ኢስላሚክ ስቴት ላይ "ከባድ ጥቃት ማድረሷን" ተናግረዋል።አይኤስን "አጭበርባሪ አሸባሪዎች" ሲሉ የጠሯቸው ትራምፕ ቡድኑ "በተለይ ንፁሕ ክርስትያኖች ላይ ዒላማ ያደረገ ግድያ እያደረሰ ነው" ሲሉ ወቅሰውታል። ፕሬዝደንቱ እንዳሉት የአሜሪካ ጦር "በርካታ የተሳኩ ጥቃቶችን" ፈፅሟል። የዩኤስ አፍሪካ ዕዝ (አፍሪኮም) በበኩሉ የሐሙሱ ጥቃት በሶኮቶ ግዛት የተፈፀመው ከናይጄሪያ ጋር በመተባበር ነው ብሏል።የናይጄሪያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዩሱፍ ማይታማ ቱጋር "አሸባሪዎችን" ዒላማ ያደረገው ጥቃት "ጥምር ኦፕሬሽን" ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቱጋር ተጨማሪ ጥቃቶች ሊፈፀሙ እንደሚችሉ ጠቁመው "በሁለቱ ሀገራት መሪዎች ውሳኔ የሚሆን" መሆኑን ተናግረዋል።ሐሙስ አመሻሹን በትሩዝ ሶሻል ገፃቸው መልዕክት ያሰፈሩት ዶናልድ ትራምፕ "በኔ አመራር ሀገራችን ፅንፈኛ የኢስላም አሸባሪዎች እንዲበለፀጉ አትፈቅድም" ብለዋል።ባለፈው ኅዳር ትራምፕ በናይጄሪያ የኢስላሚክ ታጣቂዎች እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ አሳውቀው እንደነበር ይታወሳል። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀኝ ዘመም አሜሪካዊያን ዘንድ በናይጄሪያ ክርስትያኖች ላይ የዘር ማጥፋት እየተፈፀመ ነው የሚል ወሬ ሲስፋፋ ነበር።በሌላ በኩል የአሜሪካው የጦር ሚኒስትር ፒት ሄግሴዝ ሐሙስ በኤክስ ገፃቸው "የናይጄሪያ መንግሥት ላሳየው ድጋፍ እና ትብብር ምስጋና አቀርባለሁ" ሲሉ ለጥፈዋል።አክለው "መልካም የገና በዓል" ብለዋል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
🔥 17 13👎 4👍 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
መረጃ በሚከለክሉ ኃላፊዎች ላይ በመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅ የተቀመጠው የቅጣት መጠን፤ ከ20 ሺህ ወደ 150 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ከፍ እንዲል የኢትዮጵያ ብዙሃን መገናኛ ምክር ቤት ጠየቀ። መረጃዎችን በሰነድ መስጠት ሳይቻል ሲቀር፤ ኃላፊዎች በቃለ መጠይቅ ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲሰጡ የሚያስገድድ አንቀጽ በአዋጁ ላይ መስፈር እንዳለበትም ምክር ቤቱ አሳስቧል።   ምክር ቤቱ ይህን ጥያቄ ያቀረበው፤ የመረጃ ነጻነት የአዋጅ ረቂቅን በተመለከተ ዛሬ ሐሙስ ታኅሣሥ 16፤ 2018 በአዲስ አበባ በተካሄደ ውይይት ላይ ነው። በፍትሕ ሚኒስቴር ስር ተዋቅሮ በነበረው የመገናኛ ብዙሃን የስራ ቡድን የተዘጋጀው እና በኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የዳበረው የመረጃ ነጻነት የአዋጅ ረቂቅ፤ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይላካል ተብሎ ይጠበቃል። ምክር ቤቱ አዋጁን ከማጽደቁ በፊት፤ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተጠርተው የሕዝብ አስተያየት እንዲካተትበት እንደሚደረግም በዚህ ውይይት ላይ ተነስቷል። በዚሁ እሳቤ በተዘጋጀው በዛሬው የውይይት መድረክ ላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በአዋጅ ረቂቁ ላይ መሻሻል ይገባቸዋል ባላቸው ጉዳዮች ላይ ምክረ ሃሳቦችን አቅርቧል። ተቋማት ወይም የተቋማት ኃላፊዎች መረጃ ሲጠየቁ “በ48 ሰዓት ውስጥ ምላሽ መስጠት አለባቸው” በሚል በአዋጁ ረቂቁ ላይ የተቀመጠው አንቀጽ በምክር ቤቱ እንዲሻሻል ከተጠየቁት ውስጥ ይገኝበታል። የመረጃ መስጪያ ገደቡ ለአስቸኳይ ጉዳዮች ሲሆን “ከዚያም ባጠረ ጊዜ እንዲሰጥ” የሚል ሀሳብ “ሊካተት ይገባል” ሲል ምክር ቤቱ የማሻሻያ ሃሳቡን ገልጿል። @Yenetube @Fikerassefa
نمایش همه...
11
Photo unavailableShow in Telegram
ይሸጣል ብሎ መለጠፍ ድሮ ቀረ ያገለገለ እቃዎትን ባሉበት ፎቶ በማንሳት ይሽጡ - መግዛትም ይቻላል ✅ ልብ ይበሉ ሁላችንም ቤት አንድ የማንፈልገውና የማንጠቀምበት ያገለገለ እቃ አለ በተቃራኒው ደግሞ ያንን እቃ የሚፈልጉ ግን የት እንደሚገኝ የማያውቁ ሰዎች አሉ። አላማችን እርሶ የማይጠቀሙበትን ያገለገለ እቃ በቀላሉ ካሉበት ሆነው ፖስት በማስደረግ እንዲሸጡ ማስቻል ሲሆን ያገለገለ እቃ መግዛት ሲፈልጉ ደግሞ በቀጥታ ከእቃው ባለቤት በጥሩ ዋጋ እንዲገዙ ማገዝ ነው። ስለሆነም እርሶም ቤት አገልግሎት ሳይሰጥ ቦታ ይዞ የተቀመጠ ያገለገለ እቃ ካሎት ፎቶ አንስተው ይላኩልን ወይም በሌሎች ሰወች ፖስት የተደረጉ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives በቀላሉ ያገኛሉ ✅ JOIN 👉 https://t.me/ET_Creatives_Family ET Creatives
نمایش همه...
1
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለ ገና በዓል በሰላም አደረሳቸሁ !!🎄🎄🎄🎄🎄🎄 የ 47% ቅናሽ ይዘንላችው ስንመጣ በደስታ ነው !! 50% ባንክ የተመቻቸላቸው Location እንግሊዝ ኢምባሲ አጠገብ   ✅  ከ ባለ 2 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ አማራጮችን ከ 138.4 ካሬ አስከ 259.2 ካሬ ይዘን ብቅ ብለናል መልካም የገና በዓል🎄🎄🎄🎄🎄 ለበለጠ መረጃ ☎️ 0912355631
نمایش همه...
4
የህውሃት መግለጫ በእርዳት ጉዳይ
نمایش همه...
👎 32 6👀 5
በማህበራዊ ሚዲያ እርዳታ የምታሰባስቡ ከድርጊታቹ ታቀቡ ተባለ። #FastMereja I የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) እንተናገሩት ህወሓት የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለመሳብ በትግራይ ክልል በመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች የሚቀርብን ሰብዓዊ ድጋፍ በመንጠቅ ድራማዊ ፕሮፓጋንዳ እያስተጋባ መሆኑንም አስረድተዋል። የህወሓት ቡድን በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፉ ተደራሽ እንዳይሆን በማስተጓጎል፤ ድጋፉን ከችግረኛ ዜጎች በመንጠቅ ዳግም የሕዝብ ጠላትነቱን እያረጋገጠ ነው ሲሉ ተናግሯል። በሌላ በኩል ኮሚሽኑ የድጋፍ ጥሪ ባላቀረበበት ሁኔታ በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በቡድንም ሆነ በተናጠል የሚደረጉ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ የአሰራር ስርዓትን የጣሱ ህገ-ወጥ አካሄዶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በዚህም የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ሰብዓዊ ድጋፍ በማሰባሰብ ላልተገባ ዓላማ እያዋሉ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባም አሳስበዋል። @Yenetube @Fikerassefa
نمایش همه...
👎 77 24
🚀 Get Found. Get Hired. Get Work Done. Are you a professional looking for job opportunities? Are you an employer or service seeker searching for skilled talent? ✅ Register on Jitume and make your profile visible to employers and clients across Ethiopia. 🔹 Open to ALL professions 🔹 Free & easy registration 🔹 Employers can directly find and contact you 🔹 Service seekers can choose verified professionals 👉 Register now and be visible: 🌐 https://jitume.gebeya.com/?utm_source=Jasper&utm_medium=tesfaye_guta_367010&utm_campaign=Jasper 📣 Don’t wait for opportunities—put yourself where opportunities find you!
نمایش همه...
4
Photo unavailableShow in Telegram
መረጃ በሚከለክሉ ኃላፊዎች ላይ በመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅ የተቀመጠው የቅጣት መጠን፤ ከ20 ሺህ ወደ 150 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ከፍ እንዲል የኢትዮጵያ ብዙሃን መገናኛ ምክር ቤት ጠየቀ። መረጃዎችን በሰነድ መስጠት ሳይቻል ሲቀር፤ ኃላፊዎች በቃለ መጠይቅ ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲሰጡ የሚያስገድድ አንቀጽ በአዋጁ ላይ መስፈር እንዳለበትም ምክር ቤቱ አሳስቧል። ምክር ቤቱ ይህን ጥያቄ ያቀረበው፤ የመረጃ ነጻነት የአዋጅ ረቂቅን በተመለከተ ዛሬ ሐሙስ ታኅሣሥ 16፤ 2018 በአዲስ አበባ በተካሄደ ውይይት ላይ ነው።በኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የተዘጋጀው የመረጃ ነጻነት የአዋጅ ረቂቅ፤ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚላክ በውይይት መድረኩ ላይ ተገልጿል። ምክር ቤቱ አዋጁን ከማጽደቁ በፊት፤ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተጠርተው የሕዝብ አስተያየት እንዲካተትበት እንደሚደረግም በዚህ ውይይት ላይ ተነስቷል።በዚሁ እሳቤ በተዘጋጀው በዛሬው የውይይት መድረክ ላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በአዋጅ ረቂቁ ላይ መሻሻል ይገባቸዋል ባላቸው ጉዳዮች ላይ ምክረ ሃሳቦችን አቅርቧል። ተቋማት ወይም የተቋማት ኃላፊዎች መረጃ ሲጠየቁ “በ48 ሰዓት ውስጥ ምላሽ መስጠት አለባቸው” በሚል በአዋጁ ረቂቁ ላይ የተቀመጠው አንቀጽ በምክር ቤቱ እንዲሻሻል ከተጠየቁት ውስጥ ይገኝበታል።የመረጃ መስጪያ ገደቡ ለአስቸኳይ ጉዳዮች ሲሆን “ከዚያም ባጠረ ጊዜ እንዲሰጥ” የሚል ሀሳብ “ሊካተት ይገባል” ሲል ምክር ቤቱ የማሻሻያ ሃሳቡን ገልጿል። Vi Ethiopia Insider @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
17😁 7
Photo unavailableShow in Telegram
በአዲስአበባ ሰራተኞች አድማ መቱ የቢዩ ዴሊቨሪ ሰራተኞች በዛሬው እለት አድማ መምታታቸውን አንዳፍታ ሚዲያ አረጋግጧል። ሰራተኞቹ "ጥያቄያችን ሳይመለስ ወደ ስራ አንገባም" ብለዋል። በዛሬው እለት የቢዩ ዴሊቨሪ የምግብ ማዘዣ የስልክ አፕሊኬሽን ስራ ማቆሙን አንዳፍታ ሚዲያ አረጋግጧል። ስለ ሰራተኞቹ አድማ እና ጥያቄ ድርጅቱ እስካሁን ያለው ነገር የለም። @Yenetube @Fikerassefa
نمایش همه...
17👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
አብዛኛዎቹ ሩሲያውያን የዩክሬን ጦርነት በ2026 ያበቃል ብለው እንደሚጠብቁ አንድ ጥናት አረጋገጠ አብዛኛዎቹን ሩሲያውያን በዩክሬን ያለው ጦርነት በ2026 ያበቃል ብለው እንደሚጠብቁ የመንግስት የምርምር ማዕከል ያስታወቀ ሲሆን የሩስያ ሀይሎች በጦር ሜዳ ላይ የሚያደርጉት ግስጋሴ ቢቀጥልም በኪየቭ እና በሞስኮ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ከሩሲያ ህዝብ የተሰበሰበዉ አስተያየት እንዳመላከተዉ በወጪው አመት ሩሲያውያን ጦርነቱ እንደሚያበቃ ብሩህ ተስፋ እንዳላቸዉ ተመላክቷል፡፡ ጥናቱን የሰራዉ ቪቲሲኦኤም የተሰኘዉ ማዕከል ምክትል ኃላፊ ሚካሂል ማሞኖቭ በዓመት መጨረሻ ላይ ሆነዉ እንደተናገሩ በጥናቱ ከተካሄደባቸው 1,600 ሰዎች መካከል 70 በመቶው ለሩሲያ 2026 “የተሳካ” ዓመት እንደሆነ አድርገው ይመለከታሉ ብለዋል።ለብሩህ ተስፋ ዋናው ምክንያት በፕሬዚዳንት ፑቲን ከተገለጹት ብሄራዊ ጥቅሞች ጋር በተገናኘ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻውን ማጠናቀቅ እና የተገለጹትን ዓላማዎች ማሳካት ይቻላል የሚል ተስፋ አድርገዋል፡፡ ማሞኖቭ እንዳሉት የሩስያ ጦር በዩክሬን እያካሄደ ያለውን ጥቃት፣ ዋሽንግተን የዩክሬንን ጦርነት ለመደገፍ ፈቃደኛ አለመሆኗ እና የአውሮፓ ህብረት በዩክሬን ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ ሚናን ሙሉ በሙሉ ለመተካት አለመቻሉ በገንዘብ እና በወታደራዊ ድጋፍ እጥረት ጦርነቱን ለማቆም የመጨረሻው ስምምነት ከሚጠበቀው ቁልፍ ምክንያቶች በስተጀርባ ይገኛል ሲሉ ጠቁመዋል ።በግጭቱ ማጠቃለያ ላይ የሩሲያ ወታደራዊ ዘማቾችን ወደ ህብረተሰብ መመለስ እና በሩሲያ ቁጥጥር ስር ያሉ የዩክሬን ክልሎችን እንዲሁም የሩሲያ የድንበር አካባቢዎችን እንደገና መገንባት ዋና ዋና ጉዳዮች ይሆናሉ ሲሉ ማሞኖቭ አክለዋል። @Yenetube @Fikerassefa
نمایش همه...
30
ዜና: በጋምቤላ ክልል በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ቢያንስ 47 ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ፤ የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን ከ100 በላይ በጦር መሣሪያ የቆሰሉ ሰዎችን እያከመ እንደሚገኝ አስታወቀ በጋምቤላ ክልል በተቀሰቀሰ ግጭት በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ቢያንስ 47 ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ፤ ዓለምአቀፉ የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን በዚያው ዕለት ከ100 በላይ በጦር መሣሪያ የቆሰሉ ሰዎችን ማከሙን አስታውቋል። ትናንት ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በክልሉ ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ታርፓም ንዑስ ከተማ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 47 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የጤና ባለሙያ እንደተናገሩት ከሆነ፣ “ይህ ቁጥር በመጀመሪያ ደረጃ መረጃ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊያሻቅብ ይችላል”። “በሰማሁት መረጃ መሠረት 47 ሰዎች ሞተዋል” ያሉት ምንጩ፤ “በቤታቸው ውስጥ እንዳሉ የተቃጠሉ አንዳንድ ሰለባዎች እስካሁን በሟቾች ቁጥር ውስጥ ሳይካተቱ ሊቀሩ እንደሚችሉ” አክለው ገልጸዋል። አክለውም “ነዋሪዎች አሁንም ሟቾችን እየቀበሩ ነው” ብለዋል። ድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን በበኩሉ ትናንት ታህሳስ 15/ 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ በጋምቤላ ክልል ያለው ግጭት ከትናንት ማለዳ ጀምሮ መጠናከሩንና ተቋሙ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከ100 በላይ በጦር መሣሪያ የቆሰሉ ሰዎችን መቀበሉን አስታውቋል። ግጭቱ የሚቀጥል ከሆነ በሚቀጥሉት ቀናት ተጨማሪ ተጎጂዎች ሊመጡ እንደሚችሉም አስጠንቅቋል። አንድ የአከባቢው ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን ጥቃቱ መፈፀሙን ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋግጠዋል፤ ይሁን እንጂ ባለሥልጣናቱ እስካሁን የተረጋገጠ የሟቾችም ሆነ የቁስለኞች ቁጥር እንደሌላቸው ተናግረዋል። ባለሥልጣኑ ጥቃቱ ከድንበር ማዶ በመጡ አካላት የተፈጸመ ነው የሚለውን መረጃ “ክስ” ሲሉ ውድቅ ያደረጉ ሲሆን፣ በጸጥታ ችግሩ ምክንያት ወደ ጋምቤላ ከተማ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችና ሕክምና ፍለጋ የሚመጡ ሰዎች ጭምር መገደባቸውን አረጋግጠዋል። ዝርዝር ዘገባውን ይመልከቱ: https://addisstandard.com/Amharic/?p=10238
نمایش همه...
2😭 2
Photo unavailableShow in Telegram
በጎፋ ዞን በ6 ወራት ዉሰጥ 2 ሺህ 173 የወንጀልና የፍትሐብሔር ክስ መዝገቦች ዉሳኔ አግኝተዋል ተባለ በጎፉ ዞን በ2018 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ከቀረቡ 2 ሺህ 273 የወንጀልና የፍትህብሔር ክስ መዝገቦች ዉስጥ 2ሺህ 173 መዝገቦች ዉሳኔ ማግኘታቸዉንና አፈፃፀሙም 89 በመቶ መድረሱን የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ብላቴ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል ። የሴቶችንና ህፃናት ደህንነት ከማስከበር አንፃር በስድስት ወሩ ከቀረቡ 221 መዝገቦች ዉስጥ 204ቱ ዉሳኔ ማግኘታቸዉንና የማጥራት ምጣኔ 92 በመቶ መመዝገቡ ተገልጿል ።በተጨማሪም 22 የሙስና ክስ ወንጀል መዝገቦች የቀረቡ ሲሆን የሙስና ወንጀሎች ዉስብስብ እንደመሆናቸው መጠን በሁሉም ላይ ክስ ተመስርቶ በሂደት ላይ መሆናቸዉን ለጣቢያችን የተናገሩት ኃላፊዉ በ5ቱ መዝገቦች ላይ ከ5 እስከ 14 ዓመት የሚደርስ የእስራትና የገንዘብ መቀጮ ዉሳኔ ተላልፏል ። ከታክስና ኢኮኖሚ ወንጀሎች ጋር የተያያዙ 8 መዝገቦች ቀርበዉ በሂደት ላይ ናቸዉ ተብሏል ። ከዚህም 3.14 ሚሊዮን ብር ወደ መንግስት ካዝና ገቢ ተደርጓል። @Yenetube @Fikerassefa
نمایش همه...
13
Repost from YeneTube
00:37
Video unavailableShow in Telegram
👉📌 ልዩ ተጨማሪ ቅናሽ! 🫵 እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ እስከ 40% የሚደርስ ቅናሽ ይዘንላችሁ መጥተናል። 10% ቅድመ  ክፍያ 🌟50% ባንክ የተመቻቸላቸው!! ✅ location  እንግሊዝ  ኤምባሲ  አጠገብ ደስ እሚል እይታ ያላቸው ቤቶች በሽያጭ ላይ ነን ከባለ 2 መኝታ - ባለ 4 መኝታ ደረስ 🌟ህንፃዎች ላይ ያሉ ተጨማሪ አገልግሎቶች ☑️ እስታንድ ባይ ጀኔኔትር ☑️5ሊፍት ያለው ☑️የዋና ገንዳ ☑️ፓርኪንግ ☑️ጅም, እስፓ ,ሚኒ ማርኬት, ☑️ቴራስ   ✅  ባለ 2 መኝታ 138.0 ካሬ 163.6 ካሬ 157.3  ካሬ ✅  ባለ 3 መኝታ 187.6ካሬ 158.1ካሬ 152.4ካሬ 211.5 ካሬ ✅ ባለ 4 መኝታ 240 ካሬ 258 ካሬ 💥ቶሎ ይደውሉ ለ 20 ቤቶች ብቻ ነው! ሰመር  ሪልስቴት    🌟ከሀገር ውጪ ለምትኖሩ ባላችሁበት ሆናችሁ መግዛት የምትችሉበትን አማራጭ ይዘን ቀርበናል:: 🌟ለበለጠ መረጃ በቀጥታ ወይም በዋትሳፕ ዋናው ቢሮ ይደውሉ  ☎️  0912355631       
نمایش همه...
12.27 MB
6
🚀 Get Found. Get Hired. Get Work Done. Are you a professional looking for job opportunities? Are you an employer or service seeker searching for skilled talent? ✅ Register on Jitume and make your profile visible to employers and clients across Ethiopia. 🔹 Open to ALL professions 🔹 Free & easy registration 🔹 Employers can directly find and contact you 🔹 Service seekers can choose verified professionals 👉 Register now and be visible: 🌐 https://jitume.gebeya.com/?utm_source=Jasper&utm_medium=tesfaye_guta_367010&utm_campaign=Jasper 📣 Don’t wait for opportunities—put yourself where opportunities find you!
نمایش همه...
2
Photo unavailableShow in Telegram
የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት፣ ጋምቤላ ከተማን ጨምሮ የጸጥታ ችግር ባለባቸዉ አካባቢዎች ከዛሬ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ የሚቆይ ሰዓት እላፊ ላልተወሰነ ጊዜ መጣሉን አስታወቀ። የክልሉ መንግሥት ዛሬ ምሽት 11:30 ገደማ ባወጣው መግለጫ፣ ለሥራ ከተመደቡ የጸጥታ ኃይሎች በስተቀር ሰዎችም ኾኑ ተሽከርካሪዎች በሰዓት እላፊው ወቅት እንዳይንቀሳቀሱ ከልክሏል። ከጸጥታ አካላት ውጪ በማናቸውም ቦታ ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ክልክል መሆኑንም የክልሉ መንግሥት አስታውቋል። የክልሉ መንግሥት የሰዓት እላፊውን ያወጀው፣ በክልሉ በተለይም በጋምቤላ ከተማ እንዲኹም በጋምቤላ እና ኢታንግ ወረዳዎች ከኅዳር 28 ጀምሮ በተከሠቱ ግጭቶች እና የጸጥታ መደፍረስ ሳቢያ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን ተከትሎ ነው። በክልሉ ግጭት የተቀሠቀሠው፣ የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኡመድ ኡጁሉ በታጠቀ ግለሰብ ከተገደሉ በኋላ ነበር። የክልሉ መንግሥት በግጭቱ እስካሁን የስንት ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ እና ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ስንት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ይፋ አላደረገም። [ዋዜማ] @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
20👍 2
ዜና፡ ጠ/ሚ ዐቢይ ከዊሊያም ሩቶ ጋር ያደረጉት ውይይት ሳፋሪኮም እና ኢትዮ ቴሌኮም በአፍሪካ ቀንድ በጋራ ለመስራት እንዲችሉ ድጋፍ መስጠቱ ተገለፀ! በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና በኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መካከል በአዲስ አበባ የተካሄደው ውይይት፤ ሳፋሪኮም እና ኢትዮ ቴሌኮም በጋራ እንዲሰሩ የፖለቲካ ድጋፍ አስገኝቷል ተባለ። ይህም በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የዲጂታል እና የመሠረተ ልማት ትብብር ለማሳደግ አዲስ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል። ከውይይቱ በኋላ የወጡ መግለጫዎች፤ መሪዎቹ በሁለቱ የቴሌኮም ኩባንያዎች መካከል ስልታዊ አጋርነት እና ኢንቨስትመንት እንዲኖር ለመደገፍ መስማማታቸውን አመልክተዋል። ስምምነቱ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር እና ቀጣናዊ ግንኙነትን ለማስፋፋት እየተደረገ ያለው ሰፊ ጥረት አካል መሆኑም ተጠቁሟል። መሪዎቹ የዲጂታል መሠረተ ልማት ለንግድ እና ለፈጠራ እድገት ቁልፍ መሆኑን ገልጸው፤ ለአፍሪካ የልማት፣ የሰላም እና የመረጋጋት ጉዞ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሜ አረጋግጠዋል። ፕሬዝዳንት ሩቶ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መግለጫ፤ ውይይቱ የኢኮኖሚ ትስስርን ማጠናከር እና ለሁለቱም አገራት ዜጎች ተጨባጭ ጥቅም በሚያስገኙ ተግባራት ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል።አክለውም “የኢኮኖሚ ትብብርን ለማሳደግ፣ ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማስፈን እና ሕዝቦቻችንን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን ለመደገፍ በጋራ እንሰራለን” ብለዋል። Via AS @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
19😁 3👍 1🔥 1