2025 سال در اعداد

107 408
مشترکین
-5824 ساعت
-4387 روز
-2 13830 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
በሕፃፅ በርሃብ የተጎዳ የሲቃ ድምፅ ይሰማል!!
ይህ አንጀራ እስኪጋገር ወይንም ምግብ እስኪገዛ ድረስ ያለ ርሃብ አይደለም ።ይህ የሚጋገረውም እንጀራ ሳይኖር ለሚገዛውም ምግብ ገንዘብ ሳይኖር የሚሰማ ከጠወለገ ሰውነት የሚወጣ የርሃብ ድምፅ ነው።
ዱቄት በርሜል ሳይኖር ፣ በምግብ ማጣት ሰውነት ሲመነምን ሰው" ስቃዬ ከሚበዛ ሞቼ እረፍት ባገኝ ይሻለኛል" የሚያስብል ርሃብ ነው።
ይህ በትግራይ ከእንዳስላሰ-ሽረ ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው ሕፃፅ እየተሰማ ያለው ርሃብ ህፃን ፣ትልቅ ፣እናት ፣አባት እና ልጅ ሳይል በመቶዎችን አርግፏል።
ለተራቡት ለመድረስ በቲክ ቶከሮች እና በማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በጎ ጅማሪ ተጀምሯል።ቢዘገዩም የትግራይ አመራሮችም በጉዳዩ ላይ እየመከሩ መሆኑ ተሰምቷል።ይህ ብቻ በቂ አይደለም ። ከችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሁሉም አካላት እርብርብና ቅን ልቦና ይፈልጋል።
@Yenetube @Fikerassefa
😭 66❤ 16👀 3
Photo unavailableShow in Telegram
አገልግሎት ሳይሰጥ ቦታ ይዞ የተቀመጠ ያገለገለ እቃ ካሎት ወደ ገንዘብ ይቀይሩት
✅ ልብ ይበሉ ሁላችንም ቤት አንድ የማንፈልገውና የማንጠቀምበት ያገለገለ እቃ አለ በተቃራኒው ደግሞ ያንን እቃ የሚፈልጉ ግን የት እንደሚገኝ የማያውቁ ሰዎች አሉ።
አላማችን እርሶ የማይጠቀሙበትን ያገለገለ እቃ በቀላሉ ካሉበት ሆነው ፖስት በማስደረግ እንዲሸጡ ማስቻል ሲሆን ያገለገለ እቃ መግዛት ሲፈልጉ ደግሞ በቀጥታ ከእቃው ባለቤት በጥሩ ዋጋ እንዲገዙ ማስቻል ነው።
ስለሆነም እርሶም ቤት አገልግሎት ሳይሰጥ ቦታ ይዞ የተቀመጠ ያገለገለ እቃ ካሎት ፎቶ አንስተው ይላኩልን ወይም በሌሎች ሰወች ፖስት የተደረጉ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives በቀላሉ ያገኛሉ
✅ JOIN 👉 https://t.me/ET_Creatives_Family
ET Creatives
❤ 7
Photo unavailableShow in Telegram
በትግራይ ክልል ህፃፅ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ተጥልለው ከሚገኙ ተፈናቃዮች ውስጥ “ረሃብ” እና “ረሃብ ባስከተለው በሽታ” ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር “ከጊዜ ወደ ጊዜ” እየጨመረ መምጣቱን የተፈናቃዮቹን ጉዳይ የሚከታተሉ አንድ የክልሉ ኃላፊ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።
ህወሓት፣ ስምረት እና ኢሕአፓ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዛሬው ዕለት በየፊናቸው ባወጧቸው መግለጫዎች፤ በህፃፅ ለሚገኙ ተፈናቃዮች አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።
የኤርትራ ስደተኞችን ለማስተናገድ በ2005 ዓ.ም የተቋቋመው ህፃፅ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ፤ በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን፣ አስገደ ወረዳ የሚገኝ ነው።
የስደተኞች መጠለያ ጣቢያው በትግራይ ክልል ጦርነት ወቅት በደረሰበት ጉዳት፤ በውስጡ ተጠልለው የነበሩ ኤርትራውያን ስደተኞች ስፍራውን ጥለው ወደ ሌሎች ቦታዎች ሸሽተዋል።
ለሁለት ዓመት የዘለቀው ደም አፋሳሹ የትግራይ ጦርነት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በተደረገ የግጭት ማቆም ስምምነት በጥቅምት 2015 ዓ.ም. መቆሙን ተከትሎ፤ የህፃፅ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ከምዕራብ ትግራይ ዞን የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን ሲያስተናግድ ቆይቷል።
በህፃፅ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ከ14 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ተጥልለው እንደሚገኙ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የምዕራብ ትግራይ ዞንን እንዲያስተዳድሩ የሾማቸው አቶ ግደይ አዘናው ገልጸዋል።
የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮችን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉት አቶ ግደይ፤ ከ2015 ዓ.ም. ወዲህ በህፃፅ መጠለያ ጣቢያ “ረሃብ” እና “ረሃብ ባስከተለው በሽታ” ከ330 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
🔴ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16850/
@EthiopiaInsiderNews
😭 30❤ 24
ልዩ መረጃ
“ትግስታችን አልቋል” ሕወሓት ወደ 4ኪሎ የላከው
ህወሓት የህጻጽ ተፈናቃዮችን የረሃብ ጉዳት አስታኮ አመሻሹን ሳምንታዊ መልዕክቱ በሚል ባወጣው መግለጫ፣ ትዕግሴት አልቋል ብሏል፡፡ እንደተለመደው የፌደራል መንግሥቱን የወነጀለው ህወሓት፣ በተደጋጋሚ ያቀረበው ጥሪ ምላሽ አለማግኘቱን ገልጿል፡፡
በፕሪቶሪያ የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ በተደጋጋሚ ጥሪ ባቀርብም ምላሽ እያገኘ አይለም ያለው ህወሓት፣ ከዚህ በኋላ አልታገስም ብሏል። ቡድኑ በመግለጫው ለዘላቂ ሰላም መስፍን ቁርጠንነት ቢኖረኝም፣ የትግራይ ህዝብን ለማጥፋት የሚደረጉ ሴራዎችን አልታገስም ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት “የትግራይ ህዝብን በተለያዩ መንገዶች የዘር ማጥፋት ዘመቻውን ቀጥሏል” በማለት የወነጀለው ህወሓት፣ ትግራይ ያለው የሰብአዊ ቀውስ መባባሱን ጠቁሟል። ለዚህም አስታኮ ማስጠንቀቂያ አዘል መግለጫ ያወጣበትን የህጻጽ ተፈናቃዮ ረሃብ ያነሳ ሲሆን፣ የፕሪቶሪያው ስምምነት ባለመተግበሩ ትግራይ ተደራራቢ ቀውስ እያስተናገደች ነው ብሏል፡፡
ይሁን እንጂ ትግራይ ለገጠማት ቀውስ የፌደራል መንግሥቱን ተጠያቂ የሚያደርገው ራሱ ህወሓት ተፈናቃዮች የፖለቲካ መያዛ በማድረግ ይወነጀላል፡፡ ከህወሓት በተቃራኒ የቆሙ በርካታ የትግራይ ፖለቲካ ኃይሎች ተፈናቃዮች ለችግር የተጋለጡት ሰብዓዊነት እና ፖለቲካ በመቀላቀሉ ነው ይላሉ፡፡
ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በትግራይ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ነው ያለውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል ለመከላከል ጥረት እያደረገ አለመሆኑን አመልክቷል። ህወሓት በመግለጫው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተገቢውን ዕርምጃ መውሰድ አለበት ያለ ሲሆን፣ ትዕግስትም ልክ አለው በማለት አሳስቧል።
ከተፈናቃዮች አፍ ቀምቶ ከእርዳታ ላይ ብር እንደሚሰበስብ የሚነገርለት ህወሓት፣ በህጻጽ የተራቡ ወገኖችን ለመታደግ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ገልጿል። ህወሓት አክሎም አያይዞም “የሸራ ድንኳን ውስጥ የሚኖረው ሕዝባችን የአራዊት ሰለባ ሆኗል” ብሏል።
በትግራይ ቀስ በቀስ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እያሽቆለቆለ በመምጣቱ፣ በሁሉም የተፈናቃይ ካምፖች ውስጥ ከባድ ቀውስ መከሰቱን አመልክቷል። በየዕለቱ ሕዝባችን በረሃብ እና ጠኔ እየሞተ ይገኛል ያለው ህወሓት፣ በህጻጽ የተፈናቃዮች ካምፕ በተከሰተው ረሃብ በርካታ ወገኖቻችንን አጥተናል ብሏል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 36😁 11👍 1😭 1
🚀 Get Found. Get Hired. Get Work Done.
Are you a professional looking for job opportunities?
Are you an employer or service seeker searching for skilled talent?
✅ Register on Jitume and make your profile visible to employers and clients across Ethiopia.
🔹 Open to ALL professions
🔹 Free & easy registration
🔹 Employers can directly find and contact you
🔹 Service seekers can choose verified professionals
👉 Register now and be visible:
🌐 https://jitume.gebeya.com/?utm_source=Jasper&utm_medium=tesfaye_guta_367010&utm_campaign=Jasper
📣 Don’t wait for opportunities—put yourself where opportunities find you!
Photo unavailableShow in Telegram
🟦 LinkedIn rental
LinkedIn account አሎት እንግዲያውስ እኛ ጋር ሲመጡ👉
•100-299 connections: $8 በየሳምንቱ
• 300-499 connections: $13 በየሳምንቱ
• 500-999 connections: $15 በየሳምንቱ
• 1000-1999 connections: $20 በየሳምንቱ
• 2000+ connections: $25 በየሳምንቱ
📱በኢትዮጵያ ትልቁ እና ታማኙ የሊንኪደን አካውንት ተከራይ አሁንም በርካታ አካውንቶችን ተከራይቶ ለቢዝነስ አላማ ማስተዳደር ይፈልጋል።
📱ከፍተኛ ኮኔክሽን ወይም ረጅም አመት ያስቆጠሩ አካውንቶች የተሻለ ክፍያ ያገኛሉ፡፡
in የእርስዎን አካውንት ደህንነት እንደራሳችን አካውንት አድርገን እንጠብቀዋለን።
📱 የእርስዎን አካውንት ከማከራየት ጎን ለጎን ሰው በመጋበዝዎ ኮሚሽን እንከፍላለን
in ስምንት ወር እና 1ዐዐ ኮኔክሽን ዝቅተኛው መስፈርት ነው
📱 ጥራት ያላቸው አካውንቶች እንዲሁም ከ3ዐዐ+ በላይ የሆኑ አካውንቶች welcoming reward ወዲያውኑ ተፈፃሚ ይሆናል።
📱 ዝርዝር መረጃዎችን ከፈለጉ በዚህ አድራሻ ያለዎትን የኮኔክሽን እና የተከፈተበትን አመት
👤Contact Us Now:
📱: @Melech4
☎️: 0967033154
Our telegram channel 👉
https://t.me/linkedinrent255work
❤ 7👍 2👎 1🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እስኪመለሱና የግዛት አንድነት እስኪረጋገጥ ድረስ ምርጫ እንዲራዘም ጠየቀ!
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) በትግራይ ክልል ተዓማኒ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስፈልጉ አነስተኛ የፖለቲካ እና የፀጥታ ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው ምርጫው እንዲራዘም ጥሪ አቀረበ።
የሳወት ሊቀመንበር አቶ ክንፈ ሃዱሽ ቅዳሜ ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው እስኪመለሱና የክልሉ የግዛት አንድነት እስኪረጋገጥ ድረስ የምርጫው ጊዜ መራዘም እንዳለበት ተናግረዋል።
ክልሉ እየተባባሰ በመጣው የፖለቲካ እና የፀጥታ ቀውስ ምክንያት “ከባድ የህልውና አደጋ” ተጋርጦበታል ያሉት አቶ ክንፈ፤ ስልጣንን ለመያዝ ወይም ለማቆየት በትጥቅ ኃይል ላይ የሚደገፉ የፖለቲካ ኃይሎች ክልሉን ወደ አለመረጋጋት እየገፉት መሆኑን አስጠንቅቀዋል።
“በአሁኑ ወቅት በስልጣን ላይ ያለው በመሳሪያ የሚመራ የፖለቲካ ኃይል ነው” ያሉት ሊቀመንበሩ፣ ገዢው ኃይል ራሱ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት የመጣ መሆኑን እና ሌሎች የፖለቲካ ተዋናዮችም አለመግባባቶችን በወታደራዊ መንገድ ለመፍታት መሞከራቸው መፍትሄ እንደማያመጣ ገልጸዋል።
በተጨማሪም በወታደራዊ አዛዦች የሚመራ የመንግስት መዋቅር ለክልሉ ደህንነትም ሆነ ተዓማኒነት ላለው ምርጫ ተስፋ ከፍተኛ ስጋት እንደሚፈጥር አስጠንቅቋል። “እንዲህ ዓይነቱ መዋቅር ለነጻ እና ፍትሃዊ የምርጫ ሂደት የሚያስፈልገውን ምህዳር ያዳክማል” ብለዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፣ የትግራይ ክልልን ጨምሮ በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች መጪውን ሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 12😁 2
Photo unavailableShow in Telegram
በወልዲያ ከተማ የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ሥርጭት ባልተለመደ ሁኔታ እየጨመረ እንደሚገኝ ተጠቆመ
በወልዲያ ከተማ የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ በመምጣቱ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑን የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ አስታውቋል።
የመምሪያው የኤች አይ ቪ ዘርፈ ብዙ ምላሽ አሥተባባሪ አቶ ሰኢድ ይማም ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በከተማዋ የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ሥርጭት እየጨመረ ይገኛል ።በአመራር በኩል ለጉዳዮ በቂ ትኩረት አለመስጠት፣ስለ በሽታው ለማህበረሰቡ ይሰጡ የነበሩ የግንዛቤ ስራዎች መቀዛቀዝና በወሲብ ስራ የተሰማሩ ሴቶች ከሌላ ቦታ ወደ ከተማዋ መምጣታቸው የበሽታው ስርጭት ከፍተኛ እንዲሆን ካደረጉ ምክንያቶች ውስጥ ይጠቀሳሉ ብለዋል።
ከሐምሌ እስከ ኅዳር 2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት አምስት ወራት ውስጥ 13 ሺህ 5መቶ15 ሰዎች ተመርምረው 1መቶ 12 ሰዎች የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ በደማቸው ተገኝቶባቸዋል።በበጀት ዓመቱ 6 ሺህ 1መቶ71 አዋቂ እና 96 ሕጻናት በጥቅሉ 6 ሺህ 2መቶ 67 ሰዎች መድኃኒት የሚወስዱ መኖራቸውን አቶ ሰኢድ ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል።
የጤና መምሪያው ለጉዳዮ መፍትሄ ለማምጣት የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ ሥርጭት መከላከል እና ቁጥጥር ላይ ያተኮረ ምክክር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አካሂዷል። ሥርጭቱን ለመቆጣጠር በወሲብ ንግድ ሰራተኞች፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ኮሌጆች ላይ ትኩረት በማድረግ የአቻ ለአቻ ውይይት እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገልጿል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 18😭 9
አዋሽ ወይን፣ አራዳ ቢራን ሊገዛ ተቃርቧል!
-አዋሽ ወይን ኮማሪን ለመጠቅለል ከስምምነት ሲደርስ፣ የሀይነከን እቅድ በምንዛሬ ለውጥ ምክንያት ተሰርዟል
የዓለም አቀፉ ግዙፍ የቢራ ኩባንያ ሀይነከን፣ የኮማሪ መጠጥ ኩባንያን ለመጠቅለል የነበረው እቅድ መክሸፉ ተሰማ።
ይህን ተከትሎ አንጋፋው አዋሽ ወይን አክሲዮን ማህበር፣ ይፋዊ የግዢ ስምምነት ውስጥ በመግባት የኮማሪን ብራንድ ለመረከብ መቃረቡ ተገልጿል።
ካፒታል ጋዜጣ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ በሀገሪቱ አንጋፋውና ስኬታማው የመጠጥ አምራች አዋሽ ወይን፣ በአራዳ መጠጥ ምርቱ የሚታወቀውን ኮማሪ መጠጥ ኩባንያን ለመግዛት ከስምምነት ደርሷል።
በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ተጠናቆ የነበረው የሀይነከን እና ኮማሪ ስምምነት ሊፈርስ የቻለው በኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጥ ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል። ምንጮች እንደገለጹት፣ በውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ የተደረገው ማስተካከያና የብር የመግዛት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ፣ የኩባንያውን ዋጋ የመወሰንና የክፍያ ስርአቱን ውስብስብ በማድረጉ ስምምነቱ እንዲቋረጥ ምክንያት ሆኗል ሲል ካፒታል ዘግቧል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 13😁 1
00:37
Video unavailableShow in Telegram
👉📌 ልዩ ተጨማሪ ቅናሽ!
🫵 እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ
የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ እስከ 40% የሚደርስ ቅናሽ ይዘንላችሁ መጥተናል።
10% ቅድመ ክፍያ
🌟50% ባንክ የተመቻቸላቸው!!
✅ location እንግሊዝ ኤምባሲ አጠገብ ደስ እሚል እይታ ያላቸው ቤቶች በሽያጭ ላይ ነን ከባለ 2 መኝታ - ባለ 4 መኝታ ደረስ
🌟ህንፃዎች ላይ ያሉ ተጨማሪ አገልግሎቶች
☑️ እስታንድ ባይ ጀኔኔትር
☑️5ሊፍት ያለው
☑️የዋና ገንዳ
☑️ፓርኪንግ
☑️ጅም, እስፓ ,ሚኒ ማርኬት,
☑️ቴራስ
✅ ባለ 2 መኝታ
138.0 ካሬ
163.6 ካሬ
157.3 ካሬ
✅ ባለ 3 መኝታ
187.6ካሬ
158.1ካሬ
152.4ካሬ
211.5 ካሬ
✅ ባለ 4 መኝታ
240 ካሬ
258 ካሬ
💥ቶሎ ይደውሉ ለ 20 ቤቶች ብቻ ነው!
ሰመር ሪልስቴት
🌟ከሀገር ውጪ ለምትኖሩ ባላችሁበት ሆናችሁ መግዛት የምትችሉበትን አማራጭ ይዘን ቀርበናል::
🌟ለበለጠ መረጃ በቀጥታ ወይም በዋትሳፕ ዋናው ቢሮ ይደውሉ
☎️ 0912355631
12.27 MB
❤ 9
የቤልጂየም ገበሬዎች ተቋውሞ
የአውሮፓ ገበሬዎች በግብርናው ዘርፍ እየደረሰባቸው ያለውን የኢኮኖሚ ጫና እና የአውሮፓ ህብረትን ፖሊሲ በመቃወም በቤልጂየም መዲና ብራስልስ በካሄዱት ተቃውሞ፣ የከተማዋ አውራ መንገዶች በድንች ክምር ተጥለቅልቀዋል።
Via:- መናኸሪያ ሬዲዮ
@Yenetube @Fikerassefa
😁 52❤ 21👍 1
የ"ኤፈርት" ኩባንያዎች የባንክ ሂሳብ እገዳም ተነሳ።
በሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ የተመራው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ልዑክ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በክልሉ ያለውን ሥራ አጥነት ለመቅረፍ በኮንስትራክሽን እና በሌሎች ዘርፎች ኢንቨስትመንቱን እንዲጀምር ጥያቄ አቀረበ። የ"ኤፈርት" ኩባንያዎች የባንክ ሂሳብ እገዳም ተነሳ::
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ ከባንኩ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ባንኩ በክልሉ ኢንቨስት ከማድረግ በተጨማሪ ቤት ለሚፈልጉ ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች የብድር አገልግሎት እንዲያመቻች ጠይቀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የፌዴራል መንግስት በትግራይ መልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ (ኤፈርት) ስር በሚገኙ 22 ኩባንያዎች የባንክ ሂሳብ ላይ ተጥሎ የነበረውን እገዳ አንስቷል። የፍትህ ሚኒስቴር ለንግድ ባንኮች በላከው ደብዳቤ መሰረት፣ ሱር ኮንስትራክሽንን ጨምሮ የሌሎች ኩባንያዎች የባንክ ሂሳብ እንዲንቀሳቀስ ተፈቅዷል።
ይህ እገዳ ተጥሎ የነበረው በህወሓት የውስጥ የሥልጣን ሽኩቻ ምክንያት በፍርድ ቤት ትእዛዝ እንደነበር ይታወሳል። እገዳው መነሳቱ ውጥረትን ያረግባል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኞችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች የባንክ ሂሳባቸውን እንዲያንቀሳቅሱ ያስችላቸዋል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ በበኩላቸው፣ ባንኩ በትምህርት እና በጤና ተቋማት መልሶ ግንባታ ላይ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለልዑኩ አረጋግጠዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 26😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር 'ምንም ችግር' የለባትም፤ የምትፈልገው በሕዳሴ ግድብ ላይ ሕጋዊ አስገዳጅ ስምምነት ብቻ ነው – አብደል ፈታህ ኤል-ሲሲ
የግብፁ ፕሬዝዳንት ይህንን የተናገሩት፣ በሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ አጋርነት ፎረም የሚኒስትሮች ጉባኤ ከተሳተፉ የአፍሪካ ልዑካን ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።
ከኢትዮጵያ ጋር ልዩነቶች ቢኖሩም "ግብፅ በጭራሽ ዛቻ ሰንዝራ አታውቅም" ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ አለመግባባቶች በውይይት እና በፖለቲካዊ መፍትሄዎች መፈታት አለባቸው ብለዋል ሲል የሀገሪቱ ሚዲያ ዘግቧል።
እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ፣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሕዳር ወር መጨረሻ ባወጣው መግለጫ፣ ግብጽ የ21ኛውን ክፍለ ዘመን እውነታ ያልተረዱ ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎች ኢትዮጵያ ላይ እያቀረበች ነው ሲል ከሷል፡፡
ሚኒስቴሩ "... ባለሥልጣናቱ (የግብጽ) ትኩረቱን በኢትዮጵያ ላይ ብቻ ያልተገደበ የአፍሪካ ቀንድን የማተራመስ ዘመቻ እያካሄዱ ነው.... ኢትዮጵያን በፍጹም ሊያስፈራራት ያልቻለውን ይህን ያረጀ አሠራር የምንሰናበትበት ጊዜ አሁን ነው" ብሏል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 29😁 11👎 2😭 1👀 1
Photo unavailableShow in Telegram
በጋምቤላ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች ተጨማሪ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዳይፈፀሙ ለመከላከል „በቂ የጸጥታ አካላት በአስቸኳይ እንዲሰማሩ እንዲደረግ“ ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ።
ኢሰመኮ ዛሬ ታኅሣሥ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ከኅዳር 28 ቀን ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ በጋምቤላ ወረዳ (አቦል)፣ በጋምቤላ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የተፈጠሩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና ሥጋቶችን እየተከታተለ መሆኑን አስታውቋል።
በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡመድ ኡጁሉ መገደልን ተከትሎ በከተማውና በአካባቢው ባሉት ወረዳዎችና ቀበሌዎች ግጭት መፈጠሩን የገለፀው ኢሰመኮ በተለያዩ አከባቢዎች የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ ኢሰመኮ በአሀዝ ሳይጠቅስ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን አስታውቋል። የሰዎችን እና የመጓጓዣ አማራጮችን እንቅስቃሴ የሚገድብ የሰዓት እላፊ በክልሉ መንግሥት መጣሉን የገለፀው ኢሰመኮ ባንኮችንና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት ማቋረጣቸውን ይፋ አድርጓል።
„የፌዴራሉ እና የክልሉ መንግሥታት ተገቢ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል“ ያለው ኢሰመኮ
በግጭቶችና ጥቃቶች ላይ ተሳታፊ የሆኑ ቡድኖች እና ግለሰቦች ላይ ተገቢ የወንጀል ምርመራ እና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ጥረቶች የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል“ ሲልም አሳስቧል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 12😭 1
Photo unavailableShow in Telegram
አለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) የወጣው አዲስ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በተለያዩ አገራት ወደ ውጭ መላክ ሳይቻል የተያዘው የአየር መንገዶች የገንዘብ መጠን አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። በተለይም በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ያለው የገንዘብ መጠን መጨመሩን ሪፖርቱ ጠቁሟል።
በተቋሙ መረጃ መሠረት፣ በኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሳይላክ የቆየው የገንዘብ መጠን 54 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል። ይህም ባለፈው ዓመት ጥቅምት 2024 ላይ ከነበረበት 43 ሚሊዮን ዶላር የ11 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል።
በጎረቤት ሀገር ኤርትራ በኩል የተያዘው የገንዘብ መጠን ደግሞ 78 ሚሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም አገሪቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ገንዘብ ከያዙ ሀገራት 6ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።
ኢትዮጵያ በ2024 አጋማሽ ላይ የብርን ዋጋ በገበያ እንዲወሰን ማድረጓን ተከትሎ፣ የተያዘው ገንዘብ ከ149 ሚሊዮን ዶላር ወደ 43 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ ብሎ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ አሃዙ በድጋሚ ማደግ መጀመሩ ተመልክቷል።
በዓለም ዙሪያ በድምሩ 1.2 ቢሊዮን ዶላር የተከማቸ ሲሆን፣ 89 በመቶው የሚገኘው በሚከተሉት 10 አገራት ውስጥ ነው ። በተለይ በቀዳሚነት አልጄሪያ 307 ሚሊዮን ዶላር ፣ ሞዛምቢክ 91 ሚሊዮን ዶላር ኤርትራ ደግሞ 78 ሚሊዮን ዶላር በስምንተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘዉ ኢትዮጵያ ደግሞ 54 ሚሊዮን ዶላር መድረሱ ተነግሯል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 15😁 1
🚀 Get Found. Get Hired. Get Work Done.
Are you a professional looking for job opportunities?
Are you an employer or service seeker searching for skilled talent?
✅ Register on Jitume and make your profile visible to employers and clients across Ethiopia.
🔹 Open to ALL professions
🔹 Free & easy registration
🔹 Employers can directly find and contact you
🔹 Service seekers can choose verified professionals
👉 Register now and be visible:
🌐 https://jitume.gebeya.com/?utm_source=Jasper&utm_medium=tesfaye_guta_367010&utm_campaign=Jasper
📣 Don’t wait for opportunities—put yourself where opportunities find you!
❤ 6
Photo unavailableShow in Telegram
በጋምቤላ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች ተጨማሪ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዳይፈፀሙ ለመከላከል „በቂ የጸጥታ አካላት በአስቸኳይ እንዲሰማሩ እንዲደረግ“ ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ።
ኢሰመኮ ዛሬ ታኅሣሥ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ከኅዳር 28 ቀን ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ በጋምቤላ ወረዳ (አቦል)፣ በጋምቤላ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የተፈጠሩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና ሥጋቶችን እየተከታተለ መሆኑን አስታውቋል። በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡመድ ኡጁሉ መገደልን ተከትሎ በከተማውና በአካባቢው ባሉት ወረዳዎችና ቀበሌዎች ግጭት መፈጠሩን የገለፀው ኢሰመኮ በተለያዩ አከባቢዎች የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ገልጿል።
ከዚህም በተጨማሪ ኢሰመኮ በአሀዝ ሳይጠቅስ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን አስታውቋል። የሰዎችን እና የመጓጓዣ አማራጮችን እንቅስቃሴ የሚገድብ የሰዓት እላፊ በክልሉ መንግሥት መጣሉን የገለፀው ኢሰመኮ ባንኮችንና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት ማቋረጣቸውን ይፋ አድርጓል።
„የፌዴራሉ እና የክልሉ መንግሥታት ተገቢ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል“ ያለው ኢሰመኮ „በግጭቶችና ጥቃቶች ላይ ተሳታፊ የሆኑ ቡድኖች እና ግለሰቦች ላይ ተገቢ የወንጀል ምርመራ እና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ጥረቶች የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል“ ሲልም አሳስቧል።
Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 9👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የአፍሪካ ዋንጫ በየአራት አመት ልዩነት ሊካሄድ ነው
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ዋንጫ ከፈረንጆቹ 2028 ጀምሮ በየአራት አመቱ ሊካሄድ ነው አሉ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ፡፡
ፕሬዚዳንቱ ይህንን ይፋ ያደረጉት ከ2025 የሞሮኮ አፍሪካ ዋንጫ በፊት የካፍ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያደረገውን ስብሰባን ተከትሎ ነው፡፡
ውድድሩ ከፈረንጆቹ 1968 ጀምሮ በየሁለት አመቱ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፥ ከ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በየአራት አመት ልዩነት ይካሄዳል ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም የውድድሩ አሸናፊ ሀገር 5 ነጥብ 2 ሚሊየን ፓውንድ ሽልማት የሚያገኝ ሲሆን፥ በአዲሱ እቅድ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ሀገር 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ፓውንድ የገንዘብ ሽልማትን ያገኛል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 32👍 13👎 11👀 2
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚመረቁ ወጣቶች ቁጥር ቢጨምርም፣ በትምህርት ጥራት መጓደልና በስራ ገበያ ፍላጎት አለመጣጣም ምክንያት ስራ አጥነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አዳዲስ ጥናቶች አመለከቱ።
አሁናዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በከተሞች የወጣቶች ስራ አጥነት መጠን ከ25 በመቶ በላይ የደረሰ ሲሆን፣ ችግሩ በተለይ በወጣት ሴቶች ላይ የበረታ ሆኖ ተገኝቷል። ከዩኒቨርሲቲ ምሩቃን መካከል 42 በመቶ የሚሆኑት መደበኛ ስራ ለማግኘት ረጅም ጊዜ እንደሚፈጅባቸው ተጠቁሟል።
ለዚህም ዋነኛው ምክንያት የትምህርት ስርአቱ የሚሰጠው እውቀት ከኢንዱስትሪው ተጨባጭ ፍላጎት ጋር መራራቁ እንደሆነ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
ይህንን ክፍተት ለመሙላት ዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ያንጎ ግሩፕ (Yango Group)፣ በSTEM (ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ማትማቲክስ) ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶችን ለማብቃት የሚያስችለውን "ያንጎ ፌሎውሽፕ" ፕሮግራም በኢትዮጵያ ጨምሮ በስድስት የአፍሪካ ሀገራት በይፋ ጀምሯል።
ታኅሣሥ 09 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ይፋ የሆነው ይህ መርሐ ግብር፤ እድሜያቸው ከ18 እስከ 25 ለሆኑ ወጣቶች የገንዘብ ድጋፍን፣ የአማካሪነት አገልግሎትን እና የተግባር ልምምድ እድሎችን ያመቻቻል። ፕሮግራሙ ተማሪዎች ለማህበረሰባቸው ተግዳሮቶች የፈጠራ መፍትሄ እንዲያዘጋጁ በማብቃት፣ ለወደፊት ዝግጁ የሆነ የሰው ኃይል ለመገንባት ያለመ መሆኑም ተጠቁሟል።
ፍላጎቱ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እስከ ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ማመልከት እንደሚችሉ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ፕሮግራሙ የተለያየ ብቃት ያለውና ለወደፊት ዝግጁ የሆነ የሰው ኃይል በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል።
Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👎 14❤ 10😁 1
