2025 سال در اعداد

107 335
مشترکین
-4624 ساعت
-3747 روز
-2 08430 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
ፓስፖርት በ30 ቀን ተቋረጠ?
በአንድ ወር ቀጠሮ ይሰጥ የነበረው የፓስፖርት አገልግሎት መቋረጡ ቅሬታ ፈጥሯል።ቀኑ ሲረዝም ብሩ አልቀነሰም‼️
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከሚያቀርባቸው የፓስፖርት አሰጣጥ አገልግሎቶች አንዱ የሆነው በአንድ ወር ቀጠሮ ለዜጎች ይሰጥ የነበረውን ፓስፖርት አቅርቦት፣ የጊዜ ገደቡና ሁኔታው በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት መቋረጡ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡
ሪፖርተር ያነጋገራቸውና ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ ተገልጋይ ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው አገልግሎቱን ለማግኘት ባለፈው ሳምንት የመጀመሪያ የሥራ ቀናት ወደ አገልግሎቱ ዋና መሥሪያ ቤት ጎተራ አካባቢ በሄዱበት ወቅት፣ በአንድ ወር ቀጠሮ በአምስት ሺሕ ብር ክፍያ ሲሰጥ የቆየው የፓስፖርት አቅርቦት አገልግሎት ለጊዜው መቋረጡ እንደተነገራቸው ገልጸዋል።
‹‹ማሟላት የሚገባኝን ሰነዶች ሁሉ ይዤ ጎተራ አካባቢ በሚገኘው መሥሪያ ቤት ደርሼ ወደ ውስጥ ለመግባት ምክንያቴን ለሠራተኞች ባሳወቅኩበት ወቅት፣ በአሁኑ ወቅት እየተሰጠ ያለው ፓስፖርት በሁለት ቀናት በ25,000 ብር ክፍያና በአምስት ቀናት በ20,000 ብር ክፍያ የሚቀርበው ፓስፖርት ብቻ መሆኑ ተነግሮኝ አቅሜ ስለማይፈቅድ ትቼ ተመለስኩ፤›› ብለዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት በሠጡት ምላሽ የሲስተም ሽግግር ላይ ሆነን ነው በአጭር ጊዜ ይስተካከላል ሲሉ እንደነገሩት ሪፖርተር በዘገባው አካቷል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 21😁 3
Photo unavailableShow in Telegram
ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ከ5.6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ የጥራት ችግር ያለበት ማዳበሪያ ግዥ ምክንያት በሙስና ተከሰሱ!
በማዳበሪያ ግዥ ዙሪያ የግዥ መመሪያዎችንና ውሳኔዎችን በመጣስ እንዲሁም የጥራት ችግር የታየበትን የአፈር ማዳበሪያ ወደ አገር እንዲገባ በማድረግ፣ በመንግሥት ላይ ከ5.6 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችና ሌሎች ሠራተኞች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተ።
የፍትሕ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ ክሱን ኅዳር 12 ቀን 2018 ዓ.ም. የመሠረተው ሲሆን፣ ክሱ ሰኞ ኅዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም. ለፌዴራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የከባድ ሙስና ወንጀሎች ችሎት ቀርቧል። ክሱ ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ሕጉን ተላልፈዋል የሚል መሆኑን የሪፖርተር ዘገባ አመልክቷል።
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 25😁 14👍 3🔥 1😭 1
00:15
Video unavailableShow in Telegram
የሆንግ ኮንግ ሰሜናዊ የነዋሪነት ህንጻዎች በሚገኙበት ታይ ፖ አካባቢ በበርካታ ከፍታ ያላቸው የመኖሪያ ህንጻዎች ላይ በደረሰ ከፍተኛ ቃጠሎ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 44 ከፍ ብሏል።
ሌላ 45 ሰዎች በጠና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። በተጨማሪም 279 ሰዎች አሁንም ድረስ አልተገኙም። የእሳቱ ትክክለኛ መንስኤ እስካሁን አልታወቀም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ፖሊስ ከእሳቱ ጋር በተያያዘ በግድያ ወንጀል ሶስት ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።
ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ የኮንስትራክሽን ኩባንያ ዳይሬክተሮች እና አንድ የምህንድስና አማካሪ ናቸው ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
1.65 MB
😭 16❤ 9
Repost from YeneTube
Photo unavailableShow in Telegram
ሰመር ሪል እስቴት
በካሬ 73,318 ብር ብቻ
10% ቅድመ ክፍያ
50% ባንክ የተመቻቸላቸው
Location እንግሊዝ ኢምባሲ አጠገብ
✅ አፓርትመንቶች ቤቶች እንግሊዝ ኢምባሲ ደስ እሚል እይታ ያላቸው ቤቶች በሺያጭ ላይ ነን ከባለ 2 መኝታ - ባለ 4 መኝታ ደረስ
☑️ እስታንድ ባይ ጀኔኔትር
☑️5ሊፍት ያለው
☑️የዋና ገንዳ
☑️ፓርኪንግ
☑️ጅም, እስፓ ,ሚኒ ማርኬት,
☑️ቴራስ
✅ ባለ 2 መኝታ
134.6 ካሬ
137.6 ካሬ
155.6 ካሬ
✅ ባለ 3 መኝታ
183.8 ካሬ
156.9 ካሬ
197.8 ካሬ
✅ ባለ 4 መኝታ
260 ካሬ
ለበለጠ መረጃዎች
📞 0912355631
❤ 11😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
ምርጫ ቦርድ እናት ፓርቲን አስጠነቀቀ
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ እናት ፓርቲ በቦርዱ ላይ ያልተገባ ተጽዕኖ ለመፍጠር ከሚያደርጋቸው ሙከራዎች ሊቆጠብ ይገባል ሲል አዲስ ባወጣው መግለጫ አስጠንቅቋል።
ቦርዱ፣ እናት ፓርቲ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ቦርዱ ፓርቲውን ለማፍረስ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል በማለት ያቀረበው ውንጀላ "መሠረተ ቢስ" እና "ሐሰተኛ" ነው በማለት አጣጥሏል። ፓርቲው ሁሉንም ሕጋዊ ሰነዶችና የበላይ አካላቱን ውሳኔ ባለማቅረቡ የአምስት ፓርቲዎች ቅንጅት እባል እንዳይሆን ለተጣለበት እገዳ ቦርዱን መክሰሱ "ተቀባይነት የሌለው" እና ፓርቲው "ለሕግ ተገዥ" አለመሆኑን ያሳያል በማለት የወቀሰው የቦርዱ መግለጫ፣ ፓርቲው አሁንም ለሁሉም የላዕላይ ምክር ቤት አባላቱ ጥሪ አድርጎ የቅንጅቱ አባል ለመሆን አስወስኖ ሲያቀርብ ቦርዱ እንደሚያጸድቅለት ገልጧል።
ቦርዱ አያይዞም፣ የፓርቲው ውንጀላ ቦርዱ ከፋይናንስ አስተዳደር ጥሠት ጋር በተያያዘ ካኹን ቀደም ባገኘው ግኝት የፓርቲው አመራሮች በሕግ እንዳይጠየቁና ይልቁንም ከስህተታቸው እንዲማሩ አሳልፎት የነበረውን ውሳኔ መልሶ እንዲያጤነው የሚያስገድድ ነው ብሏል።
ቦርዱ የፓርቲው የቀድሞና የአሁን አመራሮች በፓርቲው አሠራርና ገንዘብ አስተዳደር ላይ ካሁን ቀደም ያቀረቧቸውን ቅሬታዎች ለመፍታት ያደረገውን ጥረት ፓርቲው ፋይዳ ቢስ አድርጎ ቆጥሯል በማለትም የቦርዱ መግለጫ ተችቷል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 25👎 5
Photo unavailableShow in Telegram
በሃዋሳ ከተማ በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ተናገረ።
ግለሰቡ በጂንካ ከተገኘው የመጀመሪያው የማልበርግ ቫይረስ ተጠቂ ጋር ንክኪ የነበረው ወደ አካባቢው ተጉዞ ወደ ሃዋሳ ተመላሽ የነበረ ነውም ተብሏል።
ይህ የተባለው የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በማርበርግ ቫይረስ ዙሪያ እየሰሩት ያለውን ስራ በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።
ቫይረሱ ከተከሰተበት ከህዳር 5ቀን እስከ ህዳር 17ቀን 2017ዓ.ም ድረስ 73 የላብራቶሪ ምርመራዎች ተደርገዋል ያሉት ሚኒስትሯ በዚህም 11 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፤ 6ቱ ህይወታቸው አልፏል፤ 5ቱ ደግሞ በህክምና ላይ ናቸው ሲሉም አስረድተዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 21😭 5👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ከማርበርግ ቫይረስ ታካሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው - ዶ/ር መቅደስ
ከማርበርግ ቫይረስ ታካሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው 349 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው አሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ።ሚኒስትሯ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ፥ እስካሁን የማርበርግ ቫይረስ ምርመራ ከተደረገላቸው 73 ሰዎች መካከል 11ዱ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።
በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና አምስቱ ደግሞ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡ከታካሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው 349 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን÷ ከእነዚህ ውስጥም 119 ሰዎች ነጻ መሆናቸው ተረጋግጦ ከማዕከል መውጣታቸውን ጠቁመዋል።
የማርበርግ ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ብሔራዊ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬከተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ በበኩላቸው፥ የቫይረሱን ሥርጭት ለመቆጣጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በየኬላዎች የሚደረገውን ቁጥጥር የማጠናከር፣ የቅኝት ሥራዎችን የማስፋትና ለሕብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ ላይ ትኩረት ተደርጓል ነው ያሉት፡ማሕበረሰቡ ከጤና ሚኒስቴር የሚሰጡ የጥንቃቄ መመሪያዎችን በመተግበርና ጥቆማዎችን በመስጠት ሃላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 26😭 7
Photo unavailableShow in Telegram
"በዓለም ዙሪያ በየ10 ደቂቃው አንድ ሴት በፍቅረኛዋ ወይም በቤተሰቧ አባል ትገደላለች" - ተመድ
በዓለም ዙሪያ በየ10 ደቂቃው አንዲት ሴት በምታውቀው ሰው ትገደላለች።ገዳዩ የፍቅር አጋሯ፣ ባለቤቷ ወይም ቤተሰቧ ሊሆን እንደሚችል አዲስ የወጣ የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ይጠቁማል።
በተመድ ሪፖርት መሠረት በየቀኑ 137 ሴቶች ይገደላሉ። ይህም በመላው ዓለም በአዋቂ ሴቶች እና በታዳጊ ሴቶች ላይ ከሚፈጸም ግድያ 60 በመቶ ነው።ፀረ የሴቶች ጥቃት ቀን ኅዳር 4/2018 ዓ.ም. ውሏል ታስቦ ውሏል።
ሪፖርቱም ቀኑን ታሳቢ አድርጎ ነው ይፋ የተደረገው።የመንግሥታቱ ድርጅት እንደሚለው ሴቶች በዋነኛነት የሚገደሉት በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ መሆኑ እጅግ አስጊ ነው።ሴቶች ላይ ያነጣጠረ ግድያ (Femicide) ከመኖሪያ ቤት ውጪም ይፈጸማል። በበቂ ሁኔታ ግን መረጃ አልተሰበሰም።
የተባበሩት መንግሥታት የሴቶች ጉዳይ ፖሊሲዎች ክፍል ኃላፊ ሳራ ሄንድሪክስ "ሴቶች ላይ ያነጣጠረ ግድያ ድንገት የሚከሰት አይደለም። መነሻው ለረዥም ጊዜ የሚዘልቅ ተከታታይ ጥቃት፣ ትንኮሳ እና ዛቻ ነው። ይህም በበይነ መረብም በአካልም ይፈጸማል" ይላሉ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c14vl7ngk1ko
@YeneTube @FikerAssefa
😭 24❤ 19😁 3
Photo unavailableShow in Telegram
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) የተሰማ አዲስ መረጃ: የዲጂታል ክፍያ አገልግሎቶች ለጊዜው ይቋረጣሉ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) በቅርቡ በሚያከናውነው የሲስተም ማሻሻያ ሥራ ምክንያት፣ ሁሉም የዲጂታል ክፍያ አገልግሎቶች ለተወሰነ ጊዜ እንደሚቋረጡ አስታውቋል።
መቼ እና ለምን ያህል ጊዜ?
* ቀን: ረቡዕ፣ ህዳር 17 ቀን 2018 ዓ.ም.
* ሰዓት: ከሌሊቱ 9:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ።
* ምክንያት: የሲስተም ማሻሻያ ሥራ።
የትኞቹ አገልግሎቶች ናቸው የሚቋረጡት?
በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚከተሉት የባንኩ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎቶች ይቋረጣሉ፦
* ሞባይል ባንኪንግ
* ሲቢኢ ብር (CBE Birr)
* ኢንተርኔት ባንኪንግ
* ኤቲኤም (ATM) ማሽኖች
* ፖስ (POS) ማሽኖች
* ኮር ባንኪንግ አገልግሎቶች (Core Banking Services)
ባንኩ ደንበኞቹ ይህንን መረጃ በመረዳት፣ አስፈላጊውን የገንዘብ እና የክፍያ ዝግጅት ከወዲሁ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
CBE በዚህ የአገልግሎት መቋረጥ ምክንያት ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግርም ይቅርታ መጠየቁን ገልጿል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 17👍 3👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሰመር ሪል እስቴት
በካሬ 73,318 ብር ብቻ
10% ቅድመ ክፍያ
50% ባንክ የተመቻቸላቸው
Location እንግሊዝ ኢምባሲ አጠገብ
✅ አፓርትመንቶች ቤቶች እንግሊዝ ኢምባሲ ደስ እሚል እይታ ያላቸው ቤቶች በሺያጭ ላይ ነን ከባለ 2 መኝታ - ባለ 4 መኝታ ደረስ
☑️ እስታንድ ባይ ጀኔኔትር
☑️5ሊፍት ያለው
☑️የዋና ገንዳ
☑️ፓርኪንግ
☑️ጅም, እስፓ ,ሚኒ ማርኬት,
☑️ቴራስ
✅ ባለ 2 መኝታ
134.6 ካሬ
137.6 ካሬ
155.6 ካሬ
✅ ባለ 3 መኝታ
183.8 ካሬ
156.9 ካሬ
197.8 ካሬ
✅ ባለ 4 መኝታ
260 ካሬ
ለበለጠ መረጃዎች
📞 0912355631
❤ 2
Repost from YeneTube
Photo unavailableShow in Telegram
ሰመር ሪል እስቴት
በካሬ 73,318 ብር ብቻ
10% ቅድመ ክፍያ
50% ባንክ የተመቻቸላቸው
Location እንግሊዝ ኢምባሲ አጠገብ
✅ አፓርትመንቶች ቤቶች እንግሊዝ ኢምባሲ ደስ እሚል እይታ ያላቸው ቤቶች በሺያጭ ላይ ነን ከባለ 2 መኝታ - ባለ 4 መኝታ ደረስ
☑️ እስታንድ ባይ ጀኔኔትር
☑️5ሊፍት ያለው
☑️የዋና ገንዳ
☑️ፓርኪንግ
☑️ጅም, እስፓ ,ሚኒ ማርኬት,
☑️ቴራስ
✅ ባለ 2 መኝታ
134.6 ካሬ
137.6 ካሬ
155.6 ካሬ
✅ ባለ 3 መኝታ
183.8 ካሬ
156.9 ካሬ
197.8 ካሬ
✅ ባለ 4 መኝታ
260 ካሬ
ለበለጠ መረጃዎች
📞 0912355631
❤ 6👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የምርመራና ክትትል አባላትና አመራሩ፣ ወንጀሉ ከተፈፀመ ዕለት ጀምሮ በርካታ ፖሊሳዊ ቴክኒኮችን በመጠቀም ባሰባሰበው መረጃ ወንጀል ፈፃሚውን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
በተደረገበት ምርመራም ግለሰቡ ሁለት ተመሳሳይ ወንጀሎችን መፈፀሙንና አማረ ደሳለኝ በሚል ሃሰተኛ ስምና በሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የጥበቃ አገልግሎት በሚሰጥ ተቋም በጥበቃ ሰራተኛነት መቀጠሩን አረጋግጧል፡፡
ግለሰቡ ሰርቶ በወዙ ከመኖር ይልቅ በአቋራጭ ለመበልፀግ ባለው ብርቱ ፍላጎት፣ በሥራ ባልደረባው ላይ የግድያ ወንጀል ፈፅሞ ለመሰወር ቢሞክርም፣ ወንጀል ፈፅሞ ከህግ ተጠያቂነት የሚቀር የለምና ግለሰቡን በቁጥጥር ስር በማዋል ወንጀሉን እንዴት እንደፈጸመው መርቶ ማሳየቱን ፖሊስ ጠቁሟል፡፡
ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በማደራጀት በአቃቤ ህግ በኩል ክስ የመሰረተበት ሲሆን፤ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ከባድ ውንብድና ሁለተኛ ወንጀል ችሎት፣ ተከሳሽ ጌታሁን ሙላት ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጡ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት የሚቀጥሯቸውን ሰራተኞች ማንንነት፣ የተያዦቻቸው ህጋዊነትና የሚያቀርቡትን ሰነድ ትክክለኛነት የማረገጋጥ ግዴታ እንዳለባቸውና ይህንን ግዴታቸውን ሳይወጡ ቀርተው ለሚያጋጥም ማንኛውም አይነት ችግር ፈቃዳቸው መሰረዝን ጨምሮ በህግ እንዲጠየቁ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 32👍 7😁 1
በአፋር ክልል ኤርታሌ አቅራቢያ በ10 ሺህ ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከሰተ በተባለ ፍንዳታ ምክንያት የህንድ አየር መንገዶች በረራዎችን መሰረዛቸው ተገልጿል።
በሰሜን-ምስራቅ ኢትዮጵያ አፋር ክልል ኤርታሌ እሳተ ገሞራ አቅራቢያ የሚገኘው የሐይሊ ጉቢ እሳተ ገሞራ ከትላንት በስቲያ እሁድ (ኅዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም.) ከሺህ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ፍንዳታ ማድረጉን ተከትሎ ዓለም አቀፍ የአየር ትራፊክ ከፍተኛ መስተጓጎል ገጥሞታል።
ከፍንዳታው የወጣው አመዳማ ደመና በርካታ አገራትን ተሻግሮ የህንድ ሰማይን በመሸፈኑ የህንድ አየር መንገዶች የሆኑት ኤር ኢንዲያ እና አካሳ ኤር በረራዎችን ለመሰረዝ ተገደዋል።
የህንድ አየር መንገዶች ማክሰኞ ዕለት ባወጡት መግለጫ፣ ከፍንዳታው የወጣው አመድ የአየር መንገዱን እንቅስቃሴ በማወኩ የተወሰኑ በረራዎችን መሰረዛቸውን አስታውቀዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 30😭 6😁 3👀 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትስዊች እና ማስተርካርድ ስትራቴጂካዊ የክፍያ ስምምነት ተፈራረሙ!
ኢትስዊች እና ማስተርካርድ በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን ለማሳደግ እና አገሪቱን ከዓለምአቀፍ የፋይናንስ መረብ ጋር ያላትን ትስስር ለማጠናከር የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ ትናንት ህዳር 15/2018 ዓ.ም የተፈረመ ሲሆን ፈጠራ የታከለበት፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው የክፍያ መንገዶችን ለማዘጋጀት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ተብሏል።
በስምምነቱ ኢትስዊች በማስተርካርድ ኢንተርፌስ ፖይንት (MIP) እና በማስተርካርድ ዓለም አቀፍ የክፍያ መግቢያ አገልግሎቶች (MPGS) አማካኝነት ከማስተርካርድ መረብ ጋር ቀጥተኛ ትስስር እንደሚፈጥር ተጠቁሟል።
ይህም የኢትዮጵያ ንግዶች ዓለም አቀፍ ክፍያዎችን መቀበል እንዲችሉ በማድረግ፣ ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ዕድሎችን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያስፋፋ ተመላክቷል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ባንኮች በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ኤቲኤሞች፣ የሽያጭ መቆጣጠሪያ ተርሚናሎች (POS terminals) እና በድረገፅ ነጋዴዎች ዘንድ ዓለምአቀፍ ተቀባይነት ያላቸውን የቅድመ ክፍያ የውጭ ምንዛሬ ካርዶችን እንዲያወጡ እንደሚያስችላቸው ተገልጿል።
ይህም ለተጠቃሚዎች የክፍያ ምቾትን በእጅጉ ከፍ የሚያደርግ ከመሆኑም ባሻገር አገሪቱ ወደ ጥሬ ገንዘብ አልባ (cash-lite) ኢኮኖሚ የምታደርገውን ሽግግር የሚደግፍ መሆኑ ተጠቁሟል።
(AS)
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 15👍 4👎 1😭 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኬንያ ለኡጋንዳ የባሕር በር እንደምትሰጥ አረጋገጠች
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጎረቤታቸው ኡጋንዳ በኬንያ በኩል በነዳጅ ቧንቧ፣ በመንገድ እና በባቡር ሐዲድ አማካኝነት በሕንድ ውቅያኖስ ላይ የባሕር በር እንድታገኝ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
ኬንያ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧዋን የሚያስተዳድረውን የመንግሥት ኩባንያ ከኡጋንዳ ጋር በጋራ ባለቤትነት ለመያዝ ፍቃደኛ መሆኗን ገልጠዋል፤ በተጨማሪም በቻይና እርዳታ የተዘረጋው የባቡር ሐዲድ በቅርቡ እስከ ካምፓላ እንደሚዘረጋ ይፋ አድርገዋል።
ይህ ማረጋገጫ የመጣው የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ኡጋንዳ በኬንያ በኩል የባሕር በር ካላገኘች በሁለቱ አገራት መካከል ጦርነት ሊቀሠቀስ እንደሚችል ከተናገሩ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው።
@Yenetube @Fikerassefa
🔥 38👍 27❤ 19👀 1
