fa
Feedback
TIKVAH-ETHIOPIA

TIKVAH-ETHIOPIA

رفتن به کانال در Telegram

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0998999899 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

نمایش بیشتر
2025 سال در اعدادsnowflakes fon
card fon
1 572 820
مشترکین
-46124 ساعت
-1 6017 روز
-2 64930 روز
آرشیو پست ها
"በአንዳንድ ቦታዎች መንገድ አጥረው ሲያበቁ ሰዎች ለማለፍ ሲሄዱ በዚህ በኩል እንዴት ትመጣለህ ተብሎ የሚደበደብባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ከህብረተሰቡ ይሰማል" - አቶ ኢያሱ ሰለሞን "መንገድ የሚያጥሩ አካላት ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምንም መንገዱ ለተገነባለት ዓላማ ጥቅም እንዳይውል ማደረግ ህገወጥ ድርጊት ነው"! የከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ያጠሩ ሰዎች ምክንያታቸው ምንም ቢሆን ማጠራቸው ተቀባይነት እንደሌለው፣ መጠኑ የተለያዩ ቢሆንም በሁሉም አካባቢዎች መንገዶች እንደታጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ። የባለልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኢያሱ ሰለሞን፣ "የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን አጥሮ መዝጋት በስፋት እየተከናወነ ያለ ህገወጥ ድርጊት" መሆኑን፣ አጥሩ እንዲነሳ መልዕክት ሲያስተላልፍ ቢቆይም፣ "ከመሻሻል ይልቅ የመስፋፋት አይነት አስማሚያዎች" መታየታቸውን ገልጸው፣ ባለስጣኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን አጥሮቹን የማፍረስ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ሰዎች የውስጥ ለውስጥ መንገድ ያጠሩበት ምክንያት ምን እንደሆነ ጠይቃችሁ ነበር? ምክንያታቸው አሳማኝ ከሆነ መፍትሄ አስቀምጣችኋል? ከዚህ በፊት የታጠሩ መንገዶችን አጥር የማንሳት ሥራ ተጀምሮ ነበር፤ ለምን ተቋርጦ ቆዬ? ሲል ለአቶ ኢያሱ ጥያቄ አቅርቧል። ኃላፊው ምን መለሱ? "ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምንም መንገዶች በከተማዋ መዋቅራዊ ፕላን መሰረት ሲገነቡ ደረጃቸው ይለያይ እንጂ ትራፊክ ለማሳለጥ ተብለው ነው። የእግረኛውንም የተሽከርካሪውንም እንቅስቃሴ በተገቢው ሁኔታ ለማስተናገድ ነው መንገዶች የሚከፈቱት ከዚህ ውጭ ሌላ ዓላማ የላቸውም። ስለዚህ መንገድ የሚያጥሩ አካላት ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምንም መንገዱ ለተገነባለት ዓላማ ጥቅም እንዳይውል ማድረግ ህገወጥ ድርጊት ነው። ምክንያት የሚለው ነገር ምንም አሳማኝነት ሊኖረው አይችልም። ሰው መንገድ ላጠረበትን ምክንያት የተለያዩ ጉዳይ ሊያነሳ ይችላል፤ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምንም ግን በከተማዋ መዋቅር ለመንገድ የተተወ ቦታ የመንገድ አገልግሎት እንዲሰጥበት ነው። ያ ማለት ደግሞ በአንድ አካባቢ ለሚኖሩ ብቻ የተፈቀደ ሳይሆን የሁሉም ህብረተሰብ የጋራ መጠቀሚያ ነው። አንዳንድ ቦታዎች ላይ መንገድ አጥረው ሲያበቁ ሰዎች ለማለፍ በአካባቢው ሲሄዱ በዚህ በኩል እንዴት ትመጣለህ ተብሎ የሚደበደብባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ከህብረተሰቡ ይሰማል። የመንገድ አካል ስለሆነ ለግንባታ ፈቃድ ስለማይሰጥበት የግል ይዞታ አድርጎ ለማካተት ስለማይሞከር እንጅ፣ የመጋዘን በር የሚመስል፣ ሰው እንኳን ወደ ውስጥ ማለፍ አይደለም ማየት የተከለከለበት እስኪመስል ድረስ አጥር የሚታጠርባቸውም ሁኔታዎች አይተናል። ድርጊቱ ያልተገባ ነው መስተካከል አለበት" ብለዋል። አጥር ማንሳቱ ተቋርጦ መቆየቱን በተመለከተ በሰጡን ምላሽ ደግሞ፣ "በተለያዩ ጊዜያት ሥራዎቹን ለመቀጠል ተሞክሯል። ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ ነበር። ምክንያቶቹን ለመጥቀስ እቸገራለሁ። ተቋርጦ ቢቆይም አሁን መጀመሩ ትክክል ነው" ብለዋል። የውስጥ ለውስጥ መንገዶች መታጠር ስላስከተለው ጉዳት አቶ ኢያሱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ? "ሁሉም ማህበረሰብ በእኩልነት የመጠቀም መብትን ስለሚጋፋ በሰው፣ በትራፊክ እንቅስቃሴው አሉታዊ ተፅዕኖ አምጥቷል። መንገዶች ሲዘጉ በሌሎች መንገዶች ተሽከርካሪዎች ተጨናንቀው ይጓዛሉ፣ ይህም ለትራፊክ አደጋ ተጽዕኖ አሳድሯል። በአደጋ ጊዜ የአደጋ እርዳታ ለማድረስ የእሳት አደጋ፣ የአምቡላንስ እንቅስቃሴ ገድቧል። የከተዋማ ገጽታም ላይ የፈጠረው ችግር አለ" ብለዋል። ይህን ከግምት በማስገባት በመጀመሪያ መንገዶችን የዘጉ አካላት እንዲያነሱ የጊዜ ገደብ ሰጥቶ መልዕክት መተላለፉን የገለጹት አቶ እያሱ፣ "በተሰጠው የ7 ቀናት የጊዜ ገደብ ውስጥ የተወሰኑ ፈቃደኛ ሰዎች በራሳቸው ፈቃድ ያነሱ አሉ፣ ግን አብዛኛው ቦታ ላይ ብዙ ለውጥ አላየንበትም" ሲሉም ተናግረዋል። ስለዚህ ከትላንት ጀምሮ የማንሳት ሥራውን እያከናወኑ እንደሆነ በማስረዳት፣ "ችግሩ አንድ ቦታ ላይ የሚገልጽ አይደለም፤ ስፋትና ጥልቀቱ ቢለያይም በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች ተመሳሳይ ችግሮች አሉ" ብለው፣ "ይህን ለማተካከል ባለፉት ሳምንታት ባለድርሻ አካላት ጠርተን በጉዳዩ አሳሳቢነት ላይ የጋራ ውይይት ተደርጎበታል" ነው ያሉት። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
نمایش همه...
1 191👏 268🥰 22🙏 22🕊 18😡 13💔 11😭 10🤔 9😢 3😱 2
🎄 የገና በዓል ልዩ የቅናሽ ከስጦታ ጋር ከሱፐር ኤስ ጂ ኤስ! 🎁 በዚህ ገና እንግዶችዎን የሚያስደምሙበት፣ የቤትዎን ውበት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድጉ ጥራት ያላቸው የፈርኒቸር ውጤቶችን ይዘንላችሁ ቀርበናል። ያልነውን ካላገኙ ወረታውን እንከፍላለን! ✅ እስከ 40% የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ (ለኪስዎ አዋጭ!) ✅ ለገዢዎች የሚሰጡ ነጻ ስጦታዎች 🎅✨ ✨ ለምን እኛን ይመርጣሉ? •  ጥራት፡ ፈጽሞ በማንደራደርበት ጥራት ለረጅም ጊዜ የሚያገለግሉ ምርቶች። •  ዘመናዊነት፡ የቤትዎን ድምቀት የሚጨምሩ ከተራው ወጣ ያሉ ማራኪ ዲዛይኖች። •  ሰፊ አማራጭ፡ ከቱርክ በቀጥታ የገቡ (Imported) እና በሀገር ውስጥ በከፍተኛ ጥራት የተመረቱ ሶፋዎች፣ አልጋዎችና የቢሮ እቃዎች። •  ነጻ ትራንስፖርት፡ የገዙትን እቃ ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ እስከ ቤትዎ እናደርሳለን! 🚚💨 📍 አድራሻችን፡- ከሜክሲኮ ወረድ ብሎ፣ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት፣ የድሮ ብስራት ኤፍ ኤም (Bisrat FM) ህንጻ። 📞 አሁኑኑ ይደውሉልን፡ 📱 0947 55 55 55 📱 0920 75 33 33 ሱፐር ኤስ ጂ ኤስ ፈርኒቸር - ለተመቻቸ ኑሮ! 🛋✨ 🎄 መልካም የገና በዓል! 🎄
نمایش همه...
105🙏 2🕊 2😭 2
Photo unavailableShow in Telegram
✨🎁 አየር ሰአትና ጥቅል ከውጭ አገራት ይቀበሉ፤ 50% ተጨማሪ የበዓል ስጦታ ያግኙ!! ከውጭ ሀገራት በአጋሮቻችን ✅ Ethio remit        ✅ EZECALL ✅ Prepaynation    ✅ ding ✅ reloady              ✅ Omnivas ✅ Boss በኩል ከ150 ብር ጀምሮ የተላከልዎን የሞባይል አየርሰዓት ወይም ጥቅል ሲቀበሉ:- 💁‍♂️ ለ15 ቀናት የሚያገለግል የ50% ተጨማሪ ስጦታ እናበረክትልዎታለን፡፡ ደንብና ሁኔታዎች 👉 https://bit.ly/4j7iOcI #Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
نمایش همه...
135🕊 4😢 2😭 2💔 1
" የቀን ወጫችን 3 ሚሊዮን ብር ሆኗል" - የክብር ዶክተር ቢንያም በለጠ ➡️ " በጤና ዙሪያ የጤና ባለሙያዎችን እገዛ እንፈልጋለን። መቄዶንያ ውስጥ ከ2500 በላይ የአዕምሮ ህሙማን ከ3000 በላይ የአልጋ ቁራኛ የሆኑ አሉ ! " መቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማንና አረጋዊያን መርጃ ማዕከል በየቀኑ 3 ሚሊዮን ብር ለማውጣት በመገደዱ፣ ያስጀመረው ሆስፒታል ባለመጠናቀቁ፣ በየክልል ከተሞች አዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈቱ ለጋሽ እጆች የተለመደ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉለት ጠይቋል። ዛሬ ባካሄደው የውይይትና የምስጋና ፕግራም፣ ባለፈው አመት በርካቶች እንደተረባረቡበት አይነት በቀጥታ ስርጭት ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ የፊታችን የካቲት 1 2018 ዓ/ም እንደሚካሄድ ገልጿል። እስከዚያው ሁሉም መረጃውን በማዳረስ፣ መረጃውን የሚሰሙ ከወዲሁ ተዘጋጅተው የአቅማቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ማዕከሉ ጥሪ አቅርቧል። የካቲት 1/2018 ዓ/ም ገቢ የማሰባሰብ ሥራ ከባለፈው አመት የሚለየው በአሁኑ በመቄዶንያና በማንኛውም የግለሰቦች ዩቱብ በቀጥታ ስለሚተላለፍ መሆኑን የክብር ዶክተር ቢንያም በለጠ ገልጸዋል። በዛሬ መርሃግብር የተገኘው ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ በበኩሉ፣ ባለፈው ዓመት የተሰባሰበ ገቢ ነበር፣ በግንባታ ላይ ያለው የሆስፒታል ህንፃ ከምን ደረሰ? አሁን የሚጎድላችሁ ነገር ምንድን ነው ? ሲል ጠይቋል። የክብር ዶክተር ቢንያም በለጠ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን መለሱ ? " ባለፈው ትልቅ የገቢ ማሰባሰቢያ አድርገን ወደ 900 ሚሊዮን ብር ሰብስበናል። 100 ቤቶች (ድጋፍ ተደርጓል)። እየተሰራ ያለው ህንፃው ግዙፍ ህንፃ ነው፤ ሆስፒታል ነው። ወጩ ብዙ ነው። አሁን ጤና ጥበቃ የሰጠን ፊገር አለ ወደ 6 ቢሊዮን ነው የሚፈጀመው ከእነኢኩፕመንት አሟልቶ ወደ ስራ ለማስገባት። አሁን ፎቁን ለመጨረስ በጣም ትንሽ ነው የቀረን። ብር እንዲሰባሰብ የፈለግነው ሆስፒታሉን ለመጨመረስ፤ በየክልሎች ለጨመርናቸው 12 ቅርንጫፎች ብዙ ኮንስትራክሽን ስላሉ ለመስራት ነው። አስጨርሶ ሰው ለማስገባት ነው፤ ፎቁን ብቻ መጨረስ ሳይሆን ፈርኒቸርም አሟልተን ለሰዎች ዝግጁ ማድረግ ነው የቀረን። አዲስ የተከፈቱት ቅርጫፎች ፦ - ቀብሪድሃር፣ - ሞያሌ፣ - ኮንሶ፣ - ዓዲግራት፣ - ዓድዋ፣ - አምቦ፣ - ጅማ፣ - ሞያሌ...በመሳሰሉት ቦታዎች የሚገኙ ነው። የተጀመሩ ህንፃዎችን እየሰራን ነው ቀብሪድሃር፣ አርባምንጭ፣ ላሊበላ እነርሱን መጨረስ አለብን። ወጫችን ብዙ ነው፤ 56 ቦታ ሰዎችን ማኖር ማለት ነው። ቋሚ ገቢ የውጭ ፈንድ የሌለው፣ በቀን 3 ሚሊዮን ብር ወጭ ያለበት ማዕከል ነውና በጣም ከባድ ነው " ብለዋል። ከህክምና አኳያ ችግር ካለ ስንጠይቃቸውም፣ የአዕምሮ ህሙማኑና አረጋዊያኑ ህክምና እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸው፣ " የጤና ባለሙያ፣ የፊዚትራፒ፣ ነርሶች፣ ዶክተሮች እንፈልጋለን። በግል ሆስፒታሎች ያሉት በሳምንት አንዴ ቢረዱን በጣም ትልቅ እገዛ ነው። ትልቁ ነገር ህክምና ነው። የአልጋ ቁራኛ የሆነ ሰው የሚያስፈልገው ህክምና ነው " ብለዋል። " በጤና ዙሪያ የጤና ባለሙያዎችን እገዛ እንፈልጋለን። መቄዶንያ ውስጥ ከ2500 በላይ የአዕምሮ ህሙማን ከ3000 በላይ የአልጋ ቁራኛ የሆኑ አሉ። ሌላው አረጋዊ፣ አካል ጉዳተኛ ነው" ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። የመቄዶንያ ወጭ በቀን 2 ሚሊዮን መሆኑን ማዕከሉ ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወሳል፤ አሁን ወጩ በምን ምክንያት እንደጨመረ ቲክቫህ የጠየቃቸው ቢንያም (የክብር ዶ/ር)፣ በአመት ውስጥ ብቻ አዳዲስ ቅርንጫፎች በመከፈታቸው መሆኑን በመጥቀስ አስረድተዋል። የማዕከሉ የቀን ወጭ 3 ወደ ሚሊዮን ብር ከፍ ማለቱን፣ በተለይ በአዳዲሶቹ ብራንቾች ብዙ ስራዎች እንዳሉባቸው ገልጸው፣ ሰዎች በማዕከሉ ስልክ ቁጥር 09432020 እየደወሉ እንዲጎበኟቸው፣ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
نمایش همه...
3 464🙏 386💔 89🤔 45😭 38😡 37🕊 31🥰 17😢 11😱 7👏 3
" ደግመን ደጋግመን አሳውቀናል " - ጊዜያዊ አስተዳደሩ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በላከው ደብዳቤ በክልሉ ተፈናቃዮች ስላሉበት ሁኔታ ደግሞ ደጋግሞ ማሳወቁን አመልክቷል። " በክልላችን ያለውን ሰብአዊ ቀውስ እና የእርዳታ ፍላጎት በተመለከተ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሰብሳቢነት የሁሉም ክልሎች ፕረዚደንቶች እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነሮች በተገኙበት በየጊዜው በሚካሄደውን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ም/ቤት ላይ አሳሳቢነቱን እየገለጽን መምጣታችን እና ከፌደራል ለድጋፍና ክትትል ወደ ክልላችን በየጊዜው የሚመጡ ቡድኖች በአካል ተግኝተው እያዩት እና እየተረዱት የቆዩት ነው " ብሏል። በተጨማሪ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጨምሮ የክልል እና የፌደራል መንግስታዊ ተቋማትና ዩኒቨርስቲዎች፤ በክልሉ የሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት (Humanitarian Agencies) በጋራ በመሆን የተጠናውን የ2024 Multi-Sectoral Meher Seasonal Assessment መሰረት በክልሉ 2.459 ሚልዮን ተረጂ ያለ መሆኑ በጥናት መረጋገጡን ገልጿል። " በተለያዩ ወቅቶች በሚደረጉ ግንኙነቶች (በደብዳቤ፣ በሪፖርት፣ በስልክ፣ በ-Virtual Meetings፣ በአካል በመገኘትም ጭምር፣ በክልላችን ባሉት የ-Cluster and ECC አደረጃጀቶች) ያሉብንን ችግሮች እያስረዳን የመጣን መሆናችን ይታወቃል " ብሏል። በክልሉ ያለውን ሁለንተናዊ ችግር አገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን አለም እንዲያውቀው እየተደረገ የመጣ ጉዳይ መሆኑ በሚገባ የሚታወቅ መሆኑ ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ ነው ሲልም አክሏል። አሁንም በመጠለያ ጣቢያዎች (IDP Camps) የሚገኙ ተፈናቃዮች የሚሰጣቸው የምግብ ድጋፍ በቂ አለመሆኑን ገልጿል። " ከምግብ ውጪ ያለባቸው መሰረታዊ ፍላጎቶች ፦ - የጤና፣ - ውሃ WaSH፣ - የልብስ እና መሰረታዊ ቁሳቁስ፣ - የመጠሊያ፣ - የእህል ማስፈጫ ዋጋ፣ - የልጆቻቸው ትምህርት ወጪ ... ወዘተ ባለሟሟላታቸው ምክንያት ለነዚህ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸው ወጪ የሚሽፍኑት ከሚሰጣቸው ምግብ (15 ኪ/ግራም እህል፣ 1.5 ኪ/ግራም ጥራጥሬ እና 0.45 ሊትር የምግብ ዘይት በመሆኑ ምክንያት የሚሰጣቸው የምግብ ድጋፍ ይህንን ሁሉ ወጪያቸው ሸፍኖ በሂወት ለመኖር የሚያስችላቸው አለመሆኑ መታወቅ አለበት " ብሏል። ይህንን ሰብአዊ ቀውስ በህፃዕ መጠለያ ጣቢያ ብቻ ሳይሆን በሌሎቹ 146 መጠለያ ጣቢያዎች ጭምር እያጋጠመ ያለ ችግር መሆኑን አስረድቷል። " በየወሩ የምግብ እርዳታ እያቀረቡ ያሉት የJEOP/CRS Partners ከላይ የተጠቀሰው መጠን ያለው ምግብ ባለማቅረባቸው እየተፈጠረ ያለ ችግር ሳይሆን ተፈናቃዮች ከምግብ በተጨማሪ ሌሎች ወጪዎችን ለመሸፈን ተጨማሪ ድጋፎች ባለማግኘታቸው የተፈጠረ መሆኑ ሁላችን ግልጸኝነት ሊኖረን ይገባል " ብሏል በመሆኑም ፓርትነሮች በተለይ ከፕሪቶሪያ ስምምነት ብኋላ ከተጠቃሚዎች ምልመላ እስከ እርዳታ ማሰራጨት እና እርዳታው ለተባለለት አላማ ስለመዋሉ ክትትል (Post Distribution Monitoring) እስከ ማድረግ ያለው ሂደት ያለ ምንም የመንግስት ጣልቃ ገብነት ራሳቸው ችለው እየሰሩ የቆዩ እንደሆነ ገልጿል። አሁንም በክልሉ ላይ በተለይ በተፈናቃዮች፣ በከተማ ነዋሪዎች እና በየቦታው ያሉ ከ1.7 ሚልዮን በላይ ያለምንም ድጋፍ የተመለሱ ተመላሽ ተፈናቃዮች ያለው ከፍተኛ ችግር ከክልሉ እና በክልሉ ከሚገኙ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት አቅም በላይ መሆኑን አመልክቷል። ያለው የነዳጅ እጥረትም ሰብእዊ ድጋፍ በወቅቱ እንዳይደርስ የበለጠ እያባባሰው መሆኑን አስረድቷል። የፌደራል መንግስት፣ የክልል መንግስታትና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ያለውን አስከፊ የሰብአዊ ቀውስ ተረድተው ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። የተፈናቃዮች መሰረታዊ ችግር የሚፈታው ግን ወደ ቤታቸው ሲመለሱ መሆኑን ገልጿል። (ሙሉ ደብዳቤው ከላይ ተያይዟል) ቲክቫህ ኢትዮጵያ @tikvahethiopia
نمایش همه...
622😡 57🤔 26😭 20🙏 19🕊 13💔 9🥰 5😢 3😱 1
" የሚላከው ሰብዓዊ ድጋፍ ለተፈለገው ዓላማ እንዳይወል እያደረገ ይገኛል፤ የሰሞኑ የህፃፅ መጠለያ ጣቢያ ማስረጃ ነው ! " - ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) የህወሓት ቡድን " ሕዝብን በርሃብ በመቅጣት ለፖለቲካ መሣሪያነት የመጠቀም ተግባሩን ዳግም በትግራይ ሕዝብ ላይ እያሳየ ነው " አሉ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር)። የማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ድጋፍ እያሰባሰቡ ያሉ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቀዋል። ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ምን አሉ ? - ህወሓት የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል በመጠለያ ማዕከላትና በልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር የሚያቀርበውን ሰብዓዊ ድጋፍ ለተፈለገው ዓላማ እንዳይወል እያደረገ ይገኛል ብለዋል። የሰሞኑ የህፃፅ መጠለያ ጣቢያ ማስረጃ ነው ሲሉ ገልጸዋል። - ቡድኑ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለመሳብ ሲል በትግራይ ክልል በመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች የሚቀርብን ሰብዓዊ ድጋፍ በመንጠቅ ድራማዊ ፕሮፓጋንዳ እያስተጋባ ነው ብለዋል። - ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የፌደራል መንግስት በግልጽ መረጃና ማስረጃ የሚልከው ሰብዓዊ ድጋፍ የት እንደገባ መጠየቅ አለበት ፤ በቡድኑ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ መደናገር እንደሌለበት ሲሉ ገልጸዋል። - የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል አስተማማኝና ቀጣይነት ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እያደረገ ይገኛል ብለዋል። - በትግራይ ክልል ከባለፈው ጥር 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታኅሳስ ወር 2018 ዓ.ም ድረስ ሁለት ሚሊየን ኩንታል በገንዘብ ሲተምን 32 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሰብዓዊ ድጋፍ ተሰራጭቷል ሲሉ ገልጸዋል። - ህወሓት የሚላከው ሰብዓዊ ድጋፉ ተደራሽ እንዳይሆን በማስተጓጎል፤ ድጋፉን ከችግረኛ ዜጎች በመንጠቅ ዳግም የሕዝብ ጠላትነቱን እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል። - ኮሚሽኑ የድጋፍ ጥሪ ባላቀረበበት ሁኔታ በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በቡድንም ሆነ በተናጠል የሚደረጉ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ የአሰራር ስርዓትን የጣሱ ህገ-ወጥ አካሄዶች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። - የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ሰብዓዊ ድጋፍ በማሰባሰብ ላልተገባ ዓላማ እያዋሉ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። #ENA @tikvahethiopia
نمایش همه...
😡 615 572🤔 50💔 22😢 21🕊 17👏 11😭 9🙏 7🥰 5
" ያለ ስጋት የቀረንን እድሜ እንድንኖር የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አፋጣኝ ምላሽ ይስጠን "-ቅሬታ አቅራቢዎች የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያደረጉ ታካሚዎች የሚወስዱት መድኃኒት አቅርቦት ከወር በላይ ለሚሆን ጊዜ በመጥፋቱ አብዛኛው ህሙማን ወደ ከፋ ችግር ውስጥ እየገባ በመሆኑ አፋጣኝ ምላሽ ይሰጠን ሲሉ የጠየቁ ታማሚዎች ቅሬታቸውን ለጤና ሚኒስቴር ማስገባታቸው ታውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ቅሬታ አቅራቢዎች ለጤና ሚኒስቴር ያስገቡት ደብዳቤ "ያለ ስጋት የቀረንን እድሜ እንድንኖር የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አፋጣኝ ምላሽ ይስጠን" የሚል ተማጽኖን የያዘ ነው። ቅሬታ አቅራቢዎቹ " እኛ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያደረግን ስንሆን በተደጋጋሚ የኩላሊት መድሀኒት አቅርቦት እና የላብራቶሪ ምርመራ መጥፋት እየተከሰተ ለብዙ ችግር እየተዳረግን እንገኛለን " ብለዋል። ለጤና ሚኒስቴር የገባው የተማጽኖ ደብዳቤ በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ውጪ የሚገኙ ጉዳዩ የሚመከታቸውን የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያከናወኑ ዜጎችን በመወከል 35 ሰዎች ፊርማቸውን አኑረውበታል። ደብዳቤው " የንቅለ ተከላ መድሀኒትን በብቸኝነት የሚያቀርበው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል መሆኑ እየታወቀ: በድንገት መድሀኒት አልቋል ማለት ከየት እንድናገኝ ታስቦ እንደሆነ አሳዛኝ ነው " በማለት የመድኃኒቱን ሰአት ማዛነፍ እና ማቋረጥ በህይወት የመኖር እና ያለመኖር ጉዳይ ነው ይላል። በተጨማሪም " መድሀኒታችንን አይደለም ለአንድ ቀን መዝለል ሰዓት እንክዋን ሲዛነፍ በህይወት የመኖር እና ያለመኖር ከዚያ ከተረፈም ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ ወደሚያስከትለው ዳያሊሲስ የሚመልስ ነው " ሲሉ አክለዋል። የመድኃኒት አቅርቦቱ በመቋረጡ ለምኖ ላሳከመ ቤተሰብ ዱብዳ እና አስደንጋጭ ነው ሲሉም የችግሩን ግዝፈት አስረድተዋል። ቅሬታውን ወደ ጤና ሚኒስቴር ያደረሱት ለጳውሎስ ሆስፒታል ንቅለ ተከላ ከፍል እንዲሁም ለአስተዳደር ክፍል ጉዳዩን ቢያሳውቁም ጊዜያዊ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ ማግኘት ባለመቻላቸው ነው። " ከዚህ ቀደም መድሀኒቶቹ ሲጠፉ በጣም ከቆየ 15 ቀን ድረስ ጠፍቶ ቢቆይ ነው " ያሉ ሲሆን አሁን የመድኃኒት አቅርቦቱ ከወር በላይ በመቋረጡ ህሙማን እጃችን ላይ ያለውን መድኃኒት ለሌላው ታማሚ እያዋስን ቆይተናል ነው ያሉት። ከመድኃኒት አቅርቦት ችግሩ ሌላም የታክሮሊሞስ ምርመራ በኬሚካል እጥረት ምክኒያት መቆሙ ጠቅሰዋል። ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለጤና ሚኒስቴር ጉዳዩን በሚመለከት ባስገቡት ደብዳቤ ያቀረቡት የመፍትሄ ሃሳብ ምንድነው ? አንደኛ የመድሀኒት ግዢ ሲፈፀም የታማሚዎችን ቁጥር ባገናዘበ መልኩ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተሞከሮ በመውሰድ የአንድ አመት ግዢ ቢፈፀም። ሁለተኛ እንደ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ህሙማን ቢያንስ ለ2 ወር ከተቻለ ደግሞ የ3 ወር መድሀኒት እጃችን ላይ ቢገባ። ሶስተኛ የከፍለ ሀገር ታማሚዎች ለትራንስፖርት እና ለመኝታ እንዲሁም የምግብን ወጪ ከመድሀኒት ወጪ ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና እያደረገ ስለሆነ ረዘም ላለ ጊዜ የመድሀኒት አቅርቦት ቢያገኙ። አራተኛ የታክ ሌቭል መመርመሪያ ኬሚካል ልክ እንደመድሀኒቱ የአንድ አመት ጊዜን ባገናዘበ መንገድ ቢገባ" የሚሉት ይገኙበታል። እነዚህን እና ሌሎችንም ተጨማሪ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያግዙ ነጥቦችን በዝርዝር በመጥቀስ ለጤና ሚኒስቴር ደብዳቤ ያስገቡት ታካሚዎቹ ጉዳያቸው"ትኩረት ተሰጥቶት ያለ ስጋት የቀረንን እድሜ እንድንኖር የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠን ስንል በትህትና እንጠይቃለን" ሲሉ ተማጽኖአቸውን አቅርበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቅሬታ አቅራቢዎቹ በተቀበለው ቃል ደብዳቤያቸው ታህሳስ ሁለት 2018 ዓም ካስገቡ በኋላ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር በመገናኘት ተወያይተዋል። ዶ/ር መቅደስ ችግራቸውን በመስማት ጉዳያቸውን ወደ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት እንደመሩላቸው ገልጸዋል። ቅሬታ አቅራቢዎቹ በተመሩት መሰረት ወደ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ቢመላለሱም ችግራቸው እስካሁን እንዳልተፈታ ተናግረዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሚመለከታቸው አካላት በማነጋገር ተጨማሪ መረጃ የሚያደርስ ይሆናል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ @tikvahethiopia
نمایش همه...
star reaction 3 861😢 306🙏 77😭 62💔 61🕊 21😡 21👏 6😱 1
" ጧሪ ቀባሪ ልጃችንን ነዉ የነጠቁን " - የሟች ወላጅ አቶ ባና ቦና ይባላሉ ‎ነዋሪነታቸው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ቡንቲ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ እንደሆነ ለቲክቫህ  ኢትዮጵያ ተናግረዋል። አቶ ባና ቦና ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ልጃቸው አብነት ባና ቦና  ከጓደኛዉ ጋር ሆነዉ ሞተር ሳይክል ለማስጠገን ወደ አርባምንጭ ከተማ እንደሄዱ ገልጸዋል። ሞተር ሳይክላቸውን አስጠግነዉ ሲመለሱ ግን በጋርዱላ ዞን ደራሼ ወረዳ ገበል በኖ ቀበሌ ' ሆልቴ ' ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ሲደርሱ የፖሊስ አባልን ጨምሮ የተወሰኑ ሰዎች አንድ ሚኒባስ አስቁመዉ ተሳፋሪዎችን እያወርዱ ያገኟቸዋል። እነሱንም ሞተር እንዲያቆሙ ሲጠይቁ ከቆሙ በኋላ ገንዘብና ስልኮቻቸዉን ከዘረፉ በኋላ ጥቃት ፈፅመዉባቸዉ ልጃቸዉ መገደሉን አቶ ባና ቦና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል። ‎ ‎ሟች አብነት ባና ገና የ19 ዓመት ወጣት ሲሆን ታናናሹቹ እንዲማሩ ትምህርቱን አቋርጦ በእርጅና ዉስጥ ያሉ አባትና እናቱን በማገዝና በመጦር ላይ የነበረ ወጣት እንደሆነ ወላጅ አባቱ ተናግረዋል። " ልጄ መገደሉን የሰማሁት ስንፈልገዉ አድረን ጥቃቱ በተፈፀመ ማግስት በአከባቢው በሚገኝ አንድ የበቆሎ ማሳ ዉስጥ በዘግናኝ ሁኔታ ተገድሎ ተገኝቶ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ተደዉሎልን ነዉ " ብለዋል። ወላጅ አባት " ጧሪ ቀባሪ ልጃችንን ነዉ የነጠቁን " ሲሉ በታላቅ ሀዘን ዉስጥ ሆነዉ ተናግረዋል። ‎ ‎" ልጃችን በምን ጥፋቱ ገና በለጋ ዕድሜው እንደተገደለ የምናዉቀዉ ነገር የለም " የሚሉት አባት ስለተፈጠረዉ ሁኔታ ከሞት አፋፍ የተረፈዉ ጓደኛዉና አብሮ አደጉ ካሳሁን መንገድ ላይ ከወደቀበት ሹፌሮች አንስተዉ አርባምንጭ ሆስፒታል ካደረሱት በኋላ ለቤተሰቡ መደወሉን ሰምተን የጋርዱላ ዞን ፖሊስን ደጋግመን ጠይቀናል ብለዋል። " የዞኑ ፖሊስ ተጎድቶ አርባምንጭ ከገባዉ ልጅ ውጪ የተጎዳም ሆነ የሞተ ሰዉ አለመኖሩን ሲገልፁ ቆይተዉ በማግስቱ አስክሬኑ ጋርዱላ ሆስፒታል መሆኑን በመግለፅ ወደ ጉማይዴ ወሰን አከባቢ በሚትገኝ ሀይቤና ቀበሌ በፖሊስ አጅበዉ በማምጣት ከማስረከብ በስተቀር 'ስለ ገዳዮቹም ሆነ አሟሟቱ የዞኑ ፖሊስ በግልፅ የነገረን ነገር የለም' " ብለዋል። ‎ ‎ከጥቃቱ የተረፈዉ ካሳሁን ምን አለ? ‎ " ‎በዕለቱ አርባምንጭ ሞተር አሰርተን በሰላም ወደ ቤታችን እየተመለስን ነበር። ጋርዱላ ዞን ደራሼ ወረዳ ገበልበኖ ኦልቴ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ስንደርስ አንድ አነስተኛ ሚኒባስ ቆሞ ተሳፋሪዎች ሲወርዱ እኛንም ሞተር እንድናስቆም ጠየቁን። የደንብ ልብስ የለበሰ ፖሊስ በቦታዉ ስለነበር ምንም ጥርጣሬ ዉስጥ ሳንገባ በቆምንበት ነበር የያዝነዉን። ገንዘብና የእጅ ስልካችንን በግድ ከወሰዱብን በኋላ 'ሄደዉ ለጉማይዴዎች ያቃጥራሉ፤ማንነታችንን ስላዩ እንግደላቸዉ' መባባል ሲጀምሩ እኔም በፊናዬ ጓደኛዬም በፊናው በእግር መሸሽ ጀመርን ለመጨረሻ ጊዜ ማስታዉሰዉ አብነትን ከጥቃት ፈፃሚዎቹ አንዱ በያዘዉ ስለት ማጅራቴን ሲወጋኝ ነዉ። ‎ ‎በደመነፍስ ስሮጥ ከወደቅኩበት ስነሳ በቆሎ ማሳ ዉስጥ ነበርኩ፤ እንደምንም አቅሜን አሟጥጬ ወደ መንገድ ወጣሁና አንድ መኪና አስቁሜ ወደቅኩኝ እግዚአብሔር ይስጣቸው አንስተዉ አርባምንጭ ሆስፒታል ወሰዱኝ፤ትንሽ ስሻለኝ ለቤተሰብ ደዉዬ የደረሰብኝን ነገርኳቸው። ‎ ‎የጓደኛዬን ሞት የሰማሁት በማግስቱ ቤተሰብ መጥቶ በጀልባ ወደ ቤት ከወሰዱኝ በኋላ ነዉ " ብሏል። ‎ ‎ኮሬ ዞን በጉዳዩ ዙሪያ ምን ይላል ? ‎ ‎ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን አስመልክቶ ያነጋገራቸው የኮሬ ዞን ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሲዳሞ ማዳሞ በጋርዱላ ዞን ደራሼ ዙሪያ ወረዳ ሁለት የኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ ቡንቲ ቀበሌ ወጣቶች ላይ ጥቃት ተፈፅሞ ወጣት አብነት መገደሉንና ሌላኛው ጓደኛዉ መትረፉን ገልፀዋል። የጋርዱላ ዞን ፖሊስ ጥቃት አድራሾችን አጣርቶ ለፍርድ እንዲያቀርብ የጋራ መድረክ ፈጥረዉ መነጋገራቸውን ገልፀዋል። ‎ ‎የጋርዱላ ዞን በጉዳዩ ዙሪያ ምን አለ ? ‎ ‎ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ መረጃ ለማግኘት ወደ ጋርዱላ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታዬ ታምሩ የእጅ ስልክ ደዉሎ ቢያነጋግራቸዉም አጠቃላይ የፀጥታ ጉዳዮችን አስመልክቶ መረጃ መስጠት የሚችሉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ብቻ መሆናቸውን ገልጸዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግንኙነት ኪታሞን ቢያነጋግሯቸውም ለጊዜው በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ መስጠት እንደማይችሉ ገልፀዋል። ‎ ‎ቀናትን ጠብቆ ድጋሚ ብንደዉልላቸዉም ስልክ ባለማንሳታቸው ምላሻቸው በዚህ ዘገባ አልተካተተም። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ #TikvahEthiopiaFamilyHawassa @tikvahethiopia
نمایش همه...
star reaction 1😭 1 187 915💔 82😡 53🕊 30😢 19🤔 9😱 8🙏 8👏 2
ድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድን(MSF) ስለ ጋምቤላ ግጭት ምን አለ ? " በታህሳስ 15፣ 2018 ብቻ ከ100 በላይ በመሳሪያ የቆሰሉ ሰዎችን ተቀብያለሁ "- ድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድን ድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድን በጋምቤላ ክልል ተባብሶ የቀጠለው ግጭት የበርካቶችን ህይወት እየቀማና ጉዳት እያደረሰ መሆኑን አሰታውቋል። ቡድኑ በክልሉ ተባብሶ የቀጠለው ግጭት እንዳሳሰበው ገልፆ በትናንትናው እለት ታህሳስ 15፣ 2018 ብቻ ከ100 በላይ በመሳሪያ የቆሰሉ ሰዎችን መቀበሉን አስታውቋል። ታህሳስ 8፣ 2018 የሃኪሞች ቡድኑ ኩሌ ስደተኞች ካምፕ ወደሚገኘው ፋሲሊቲው የተጎዱ ሰዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን ተከትሎ ምላሽ ለመስጠት የሚሆን ስራ መጀመሩን ገልፆ በመጀመሪያው 48 ሰዓት ውስጥ 50 የቆሰሉ ሰዎቾ መምጣታቸውንና 19 ያህሉ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ እንደሆኑ ገልጿል። ድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድን ባለፉት 7 ቀናት 150 የቆሰሉ ሰዎችን መቀበሉን ገልፆ የጤና ሚኒስትርን ድጋፍ ለመደገፍ የሚያገለግሉ የጅምላ ጉዳት ምላሽ ለመስጠት የሚውሉ መሳሪያዎችን ለጋምቤላ አጠቃላይ እና ለጋምቤላ የመጀመሪያ ሆስፒታሎች ማከፋፈሉን ገልጿል። ቡድኑ የተፈጠረው ግጭት መደበኛ የሆነውን የጤና አገልግሎት ረብሿል ያለ ሲሆን ያለ አድሎ ድጋፍ ለሚሹ ሁሉ አገልግሎት መስጠቱን እንደሚቀጥልና የጤና ባለሙያዎች፣ ታካሚዎች እና የጤና ተቋማት እንዲከበሩ ጠይቋል። #TilvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
نمایش همه...
224😢 70😭 16🙏 8🕊 6😡 2🤔 1