TIKVAH-ETHIOPIA
رفتن به کانال در Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0998999899 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

1 572 276
مشترکین
-46024 ساعت
-1 9487 روز
-3 00530 روز
آرشیو پست ها
" ብር ስታስጋቡ በዚህ አካውንት አስገቡ 1000737657888 " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ " ህዝብ የማዳኑ ቁልፍ መፍትሄ ወደ ቀዬው መመለስ ነው " አለ።
" የረሃብ ችግሩ በሕፃፅ ብቻ የተወሰነ አይደለም በሌሎች የተፈናቃዮ የመጠለያ ማእከላትም አለ " ሲል ገለጸ።
" በሕፃፅ የተከሰተው ረሀብ ወለድ እርዛትና ሞት ለመግታት በአገር ወስጥና በመላው ዓለም የሚገኙት ወገኖች ያሳዩት ተነሳሽነት ይደነቃል " ብሏል።
በሕፃፅ ያለው አሰቃቂ ረሃብ አመኖ የተቀበለው ጊዜያዊ አስተዳደሩ " የተጀመረው እገዛ በመንግስት ተማክሎ ይቀጥል " ብሏል።
" ለሕፃፅ የረሃብ ተጠቂዎች መርጃ ብቻ እንዲውል ታስቦ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተከፈተው የሂሳብ ቁጥር 1000737657888 ነው " ሲል ቢሮው ገልጿል።
ተረጂዎቹ መደገፍ የሚፈልግ ማንኛውም ሰብአዊ ወገን የተጠቀሰው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ብቻ ይጠቀም ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
@tikvahethiopia
😭 637❤ 383😡 165🤔 40🙏 20🕊 18😢 16💔 8😱 5🥰 3
Photo unavailableShow in Telegram
#SafaricomEthiopia
የSMS ጥቅሎች እየገዛን ከምንወዳቸው ጋር እንደልብ መልዕክት እንለዋወጥ! 💬
#SafaricomEthiopia
#Furtheraheadtogether
❤ 107😡 15🤔 14🙏 4💔 1
#ሕፃፅ
" ቤቴና መሶቤ ሙሉ ነበር ከቀዬ ከተፈናቀለኩ በኃላ ግን ሁሉ ባዶ ታሪክ ሆኗል ፤ እኔና 6 ቤተሰቦቼ ከምንበላው ጦማችን የምናድርበት ጊዜ ይበዛል ድረሱልን " - በመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃይ
➡️ " ጊዚያዊ አስተዳደሩና የመንግስት መዋቅሩ ረሀቡ መከሰቱ በማህበራዊ የትስስር ገፃች ከመነገሩ በኃላ መንቃቱ የአመራር ክፍተት ዋነኛ ማሳያ ነው " - አስተያየየት ሰጪዎች
በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን አስገደ ወረዳ ከእንዳስላሰ-ሽረ ከተማ አቅራቢያ የምትገኘው #ሕፃፅ ከደም አፈሳሹ የትግራይ ጦርነት በፊት የኤርትራ ስደተኞች ማቆያ በመሆን ትታወቃለች።
በሕፃፅ የስደተኞችና የተፈናቃዮች የመጠለያ ጣብያ የዛሬውን ያህል በእህል፤ ውሃና ህክምና እጦት የገረጡ ፊቶች ታይተው አያውቁም።
ሕፃፅ በዙሪያዋ ከሚገኘው የወርቅ ማዕድን ሀብት በሚሊዮን የሚገመት ብር የሚዛቅበት ሆና ሳለ በጉያዋ ግን በሀይለኛ ረሀብና ውሃ ጥም ተፈናቃዮች ወደ መቃብር ይሸኙባታል።
አርሶ አደር ጉዕሽ በትግራዩ ጦርነት ምክንያት ከምዕራባዊ ዞን አደባይ ከተባለ ሰፊ እርሻ ያለበት ቦታ ተፈናቅለው በሕፃፅ የመጠለያ ጣብያ በአሮጌ ፕላስቲክ በተሰራ ቤት መኖር ከጀመሩ 5 ዓመታት ተቆጥረዋል።
አርሶ አደሩ በመጠለያ ጣብያዋ ከሚገኙ 16 ሺህ ተፈናቃዮች መካከል ሲሆኑ ' አስቸኳይ እርዳታ ካላገኙ ለቀናት እንኳን በህይወት መቆየት ይከብዳቸዋል ' ተብለው በዞኑ ከተጠኑ 1,700 በላይ የተቸገሩ ወገኖች አንዱ ናቸው።
በድስት ያረረ ወጥ እያሳዩ " ቤቴና መሶቤ ሙሉ ነበር ከቀዬ ከተፈናቀለኩ በኃላ ግን ሁሉ ባዶ ታሪክ ሆኗል ፤ እኔና 6 ቤተሰቦቼ ከምንበላው እራት ጦማችን የምናድርበት ጊዜ ይበዛል ድረሱልን " ሲሉ ተማፅነዋል።
ሌላኛዋ ራሷና ሁለት ታማሚ ልጆችዋ ጊዜ በማይሰጠው ረሀብ ስር መሆናቸውን የገለጸች ተፈናቃይ " በረሃብ ወለድ ሞት ምክንያት ሁለት ሰዎች እየቀብርን ነው " በማለት ከቀናት በፊት ሞተው የተቀበሩ የአንድ አባት መቃብር አሳይታለች።
" ለረሃብ በሽታና ሞት የዳረገን ከቄያችን መፈናቀላችን ፤ መሬታችን ለማረስ አለመቻላችን ነው። ዘርፈ ብዙ ችግሮቻችን የሚፈቱት ወደ ቄያችን ስንመለሰ ብቻ ነው " ብላለች።
በመጠለያ ማእከሉ የሚገኙ ተፈናቃዮች በወር 15 ኪሎ ስንዴ ነው የሚሰጣቸው፤ የብር 300 ዋጋ ያላት ስንዴ ለማስፈጨት ደግሞ 105 ብር ይጠየቃሉ።
" አመራሮች የህዝብን ጉዳይ ዘንግተውታል " - አስተያየት ሰጪዎች
የምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ግደይ አዘናው እና መሰል የመንግስት አመራሮች በህዝቡ ክፉኛ ይተቻሉ።
" አመራሮቹ የህዝብ ጉዳይ ዘንግተው አብዛኛው ጊዚያቸው በፓለቲካ ሽኩቻ ባያውሉ ኖሮ በመጠለያ ጣብያው የተከሰተው አሰቃቂ ረሀብ ለመግታት ከአቅም በላይ አይሆንም ነበር " ይላሉ ቃላቸውን የሰጡ አስተያየት ሰጪዎች።
" አመራሮቹ ህዝቡን መቅደም ሲገባቸው : ረሀቡ መከሰቱ በማህበራዊ የትስስር ሚድያዎች መቀጣጠሉ ተከትሎ መሯሯጣቸው ከህዝብ ዋነኛ አጀንዳ በምን ያህል እንደራቁ ዋነኛ ማሳያ ነው " ሲሉ ተችተዋል።
በሕፃፅ ከሚገኙ ተፈናቃዮች ከ2015 ዓ.ም ወዲህ 300 ሰዎች በረሃብና ረሀብ ወለድ በሽታ ለህልፈት መዳረጋቸው የሚገልፀው የዞኑ መረጃ 50ዎቹ በያዝነው ዓመት መሞታቸውን አረጋግጧል።
በመንግስት እውቅና ያለተሰጣቸው ሌሎች የመረጃ ምንጮች ደግሞ በመጠለያ ጣብያው " በረሀብና ረሃብ ወለድ በሽታ ብቻ 350 ሰዎች አልቀዋል " በማለት ይገልጻሉ።
እጅግ የዘገየም ቢሆን የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ " በሕፃፅ የመጠለያ ጣብያ የተከሰተው አሰቃቂ ረሀብ በዘላቂ ለመግታት " በሚል ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም እየመከረ ይገኛል።
ምስጋና በትግራይ ለሚገኙ ወጣቶች ይሁንና በነሱ ምክንያት ችግሩ ወደ ማኅበራዊ ሚዲያው በመውጣቱ በአሁኑ ሰዓት ሕፃፅ የብዙዎች ትኩረት አግኝቷል። የምግብና የቁሳቁስ እርዳታ ከአቅጣጫው እየተሰበሰበ ነው።
ሰብአዊነት ከሚሰማቸው ለጋሽ ግለሰቦችና ድርጅቶች የሚሰጠው ድጋፍ በትክክል ረሀብ እየገረፋቸው ወደ ሚገኙች ተፈናቃይ ወገኖች መድረሱ ማረጋገጥ ግን ቀጣይና ዋና ስራ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TilvahEthiopiaFamilyMekelle

🕊 1
" ከጥር 23 ጀምሮ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶችን (ስስ ፌስታል) መጠቀም፣ ማምረትና ወደሀገር ውስጥ ማስገባት አይቻልም ! "
ከጥር 23 ጀምሮ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶችን (ስስ ፌስታል) መጠቀም፣ ማምረትና ወደሀገር ውስጥ ማስገባት ያስቀጣል ተብሏል።
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፤ ከጥር 23 ጀምሮ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት ብቻ የሚውሉ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶችን የሚጠቀሙ፣ የሚያመርቱና ወደሀገር ውስጥ የሚያስገቡ አካላትን መቅጣት ሊጀመር መሆኑን አሳውቋል።
ለአንድ ጊዜ አገልግሎት ብቻ የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶችን ማምረት፣ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትና ይዞ መገኘት የሚከለክለው አዋጅ ከሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የጸደቀ ቢሆንም፣ ባለስልጣኑ የስድስት ወራት የሽግግር ጊዜ ሰጥቶ መቆየቱን ገልጿል።
" አዋጁ እንደወጣ የወረቀትና ሌሎች አማራጭ ከረጢቶች ወደ ገበያ በመምጣታቸው የፕላስቲክ ስርጭት ቀንሶ የነበረ " ያለው ባለስልጣን መ/ቤቱ " አሁን ላይ ግን በድጋሚ በገበያው ውስጥ እየታዩ ይገኛሉ " ብሏል።
በሽግግሩ ወቅት አዋጁን ሙሉ በሙሉ ለመተግበር የሚያስችሉ የዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ እንደቆዩ ፤ በዚህም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የፕላስቲክ አምራቾች፣ ተጠቃሚዎች እንዲሁም አማራጭ የወረቀት ከረጢት አምራቾች ጋር ውይይት መደረጉን አመልክቷል።
የወረቀትና ሌሎች የከረጢት ዓይነቶችን ማምረት የሚፈልጉ አካላትን ወደ ገበያ ለማስገባት ማሽኖችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡና የብድር አቅርቦት እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑንም አሳውቋል።
" የሽግግር ጊዜው ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ያበቃል " ያለ ሲሆን " ከዚህ ዕለት በኋላ ሕገወጥ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኙ አካላት ተጠያቂ ስለሚሆኑ ሁሉም አስፈላጊውን ዝግጅት ያድርግ " ሲል አሳስቧል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነው።
@tikvahethiopia
❤ 1 144😭 269😡 211🤔 49👏 48🙏 29💔 26🕊 17😢 10😱 7🥰 4
" አንድ ሰው ሸገር በሚባለው ከተማ ውስጥ ከመቶ በላይ ካርታ ያለው ሰው አለ " - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ማስጀመሪያ ስነ ስርአት ወቅት የተገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ዙርያ የእሳት ዳር ወግ አካሂደዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይቱን ያካሄዱት ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ጋር ሲሆን በተጨማሪም ከታዳሚያን ለተነሱላቸው ጥያቄዎችም ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመንግሥት የስራ ሃላፊዎች ባስተላለፉት መልእክት " መንግስታችን ሊፈጥረው የሚፈልገውን መንግስታዊ ቁመና ቀለል ባለ መንገድ ተገንዝበን እዛ ውስጥ ሚናችንን የምንጫወት መሆን አለብን " ብለዋል።
መንግስታቸውም " ቢሮክራሲው ትንሽ መሆን አለበት " ብሎ የሚያምን መንግስት እንደሆነ አክለዋል።
ከቢሮክራሲ እና የመሬት መረጃ (Land Information system) ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ያነሱት ጠ/ሚ ዐብይ (ዶ/ር) እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የመንግስታቸው ኦቨር ሳይት የማድረግ አቅም ማሳደግ ላይ እየሰራ መሆኑን ጥቆማ ሰጥተዋል።
ይህንን አቅም ለማሳደግ እንዲቻልም " በአዲስ አበባ ፣ ሸገር ፣ ቢሾፍቱ ፣ አዳማ እና አንዳንድ ከተሞች ላይ የላንድ ኢንፎርሜሽን ሲስተም (የመሬት መረጃ ስርአት) ከሞላ ጎደል መቶ ፐርሰንት መመዝገብ ተችሏል (ከብዙ አመት ልፋት እና ጭቅጭቅ በኋላ)" ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በዝርዝር ምን አሉ ?
" አንድ ሰው መታወቂያ ለማግኘት በአንድ ቀበሌ በአምስት ብር ሊያገኘው ካልቻለ በሌላ ቀበሌ ሄዶ በአምስት ብር ያገኘዋል ቢሮክራሲው ረዥም ነው ነገር ግን ከፍሎ ያገኘዋል ይህንን በህገ ወጥ መንገድ ፎርጂድ መታወቂያ ያገኘውን ሰው ግን ኦቨር ሳይት አድርጎ ማግኘት አይቻልም።
መሬትን ብንወስድ አንድ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን ባለው ሁኔታ የኢንቨስትመንት ሃሳብ ኖሮት በመንግስት ተቋማት መሬት ለማግኘት አመልክቶ መሬት ማግኘት ማለት ምጽአት እንደመጠበቅ ከባድ ነገር ነው ቀላል ጉዳይ አይደለም።
አንድ ሰው የኢንቨስትመንት ሃሳብ ኖሮት መንግሥት ጋር ሄዶ መሬት ጠይቆ ማግኘት አይችልም በህገወጥ መንገድ መሬት የወሰዱ ሰዎችን ግን መንግሥት ኦቨር ሳይት አድርጎ መያዝ አይችልም።
ለመጣው አያስተናግድም የሚሰርቀው እና ያለአግባብ የወሰደውን ደግሞ መያዣ መንገድ የለውም።
ምሳሌ በጂኦ ስፓሻል ኢንፎርሜሽን የመሬት ኢንፎርሜሽን ሲስተም መገንባት በየከተማው ተጀምሯል ከጀመርን ቆይቷል አልተሳካልንም።
አዲስ አበባ ፣ሸገር ፣ቢሾፍቱ ፣አዳማ ፣እና አንዳንድ ከተሞች ላይ የላንድ ኢንፎርሜሽን ሲስተም (የመሬት መረጃ ስርአት) ከሞላ ጎደል መቶ ፐርሰንት መመዝገብ ተችሏል (ከብዙ አመት ልፋት እና ጭቅጭቅ በኋላ)።
ምን አገኘን የተባለ እንደሆነ አንድ ሰው ሸገር በሚባለው ከተማ ውስጥ ከመቶ በላይ ካርታ ያለው ሰው አለ።
ይህ ከመቶ በላይ ካርታ ወደ ጂኦስፓሻል ሲስተም ካልገባ በቀር ከእዚያ ሁሉ የተከመረ ወረቀት በምን አይነት መነጽር ለይተን ይህንን ሰው ብቻ ለይተን ልናወጣ እንችላለን ? አናገኝም።
የጂኦ ስፓሻል ሲስተም ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይገነባ የነበረው ፍላጎት እና የቢሮክራሲው መጨናነቅ የሚታወቅ ቢሆንም ዋና አላማው ግን ጥቂት ሌቦች አላግባብ የወሰዱትን መሬት መንግስት ኦቨር ሳይት ማድረግ እንዳይችል ለማድረግ ነው።
አሁን ያሳካነው አዲስ አበባ ወይም ሸገር ሊሆን ይችላል የተሟላ የመረጃ ልውውጥ (ዳታ ኤክስቼንጅ) ከሌለን ይህ ሸገር ላይ 100 ካርታ ያለው ሰው ቢሾፍቱ 20፣ ጅማ 30፣ ነቀምት 40 ሊኖረው ይችላል ዳታ ኤክስቼንጅ ካልተሟላ ማወቅ አንችልም።
መንግስት ሩቲን (የተለመደ ነገር መስራት) ላይ ሳይሆን ማተኮር ያለበት ኦቨር ሳይት ማድረግ ላይ መሆን አለበት።
ለምሳሌ አንድ ሰው አታሎ ፓስፖርት ቢያወጣ የእኛ ሩቲን ቀላል እና አውቶሜትድ በመሆኑ ምክንያት ሸውዶን ቢወስድ የኦቨር ሳይት አቅማችን ጠንካራ ከሆነ ሳምንት አይገለገልበትም እንይዘዋለን።
ኦቨር ሳይት ጠንካራ ካልሆንን ግን ፎርጂዱን ለመከላከል የምንፈጥረው ቢሮክራሲ ስራ ያጓትታል እንጂ መንግስትን ውጤታማ አያደርገውም "ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
" ህብረተሰቡ፣ የቲክቫህ ቤተሰቦችም ማወቅ ያለባቸው በረራን ለአደጋ ከሚያጋልጡ ክስተቶች ብዙው ፐርሰንት በአየር ሁኔታ ሊከከሰቱ በሚችሉ ችግሮች መሆኑን ነው " - ኢንስቲትዩቱ
" በተለይ ደሴ በጣም አስቸጋሪ ኤርፖርት ነው። ቶሎ ገልጦ ካልታየ ብዙ የበረራ አደጋዎች ሊያስከትል የሚችል መሆኑ ስለታወቀ ችግሩን ለማስወገድ አየር መንገዱ ይህን ለመወሰን ተገዷል! "
የኢትዮጵያ አየር መንገድ "በአየር ፀባይ" ምክንያት ወደ ደሴ ከተማና አካባቢዋ በረራ ማቋረጡን ዛሬ በይፋ ማሳወቁ ይታወቃል።
የበረራ መስተጓጎሎች ሲያጋጥሙ፣ " በአየር ፀባይ ምክንያት ነው " ከመባል የዘለለ ሙያዊ ትንተና ሲሰጥባቸው አይስተዋልም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ፦
- በረራ እስከማቋረጥ የደረሰው በደሴ በኩል የሚስተዋለው የአየር ፀባዩ ምንድን ነው የሆነው ?
- በተፈጠረው የአየር ፀባይ ሁኔታ በረራ ባይቋረጥ የሚከሰተው ነገር ምንድን ነው ?
- የደሴው የአየር ፀባይ እስከመቼ ይቆያል? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎችን ለኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አቅርቧል።
በኢንስቲትዩቱ የአቬሽን ሚቲዎሮሎጂ የአገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳ ፈቃዱ ምን መለሱ ?
" አደገኛ የሆኑ/በረራን የሚያስታጉሉ የአየር ንብረት ክስተቶች ከሚባሉት አንዱ በኤርፖርቶች አካባቢ የጉም ክምችትና የመብረቅ ሁኔታዎች ማጋጠም ነው። የአውሮፕላን መንደርደሪያ ሜዳን ሊያሳይ በማይችል ሁኔታ በጉም ሲሸፈን አውሮፕላኑ እንዳይንቀሳቀስ፣ ማረፍና መነሳት እንዳይችል ሊያደርገው ይችላል።
በአንዳንድ በጣም ትልልቅ እንደ ቦሌ ኤርፖርት አይነት የአየር ማረፊያዎች (የኢንስትሩመንት ላንዲንግ ሲስተም አይኤልኤፍ የሚባል ስላላቸው) ካልሆነ በስተቀር አውሮፕላኑ ሊያርፍና ሊነሳ በማይችልበት ሁኔታ ይሄ ያጋጥማል። ስለዚህ የአየር ሁኔታው እንስከሚስተካከል በረራዎች ሊስተጓጎሉ ይችላሉ።
ጭጋግ፣ ደመና፣ ሀይለኛ ዝናብ ሲኖር አካባቢው ለእይታ የሚያስቸግር ሲሆን ለበረራ አደገኛ ነው። በአቬሽን ኢንዳስትሪ ውስጥ የተሳፋሪውን የህይወት፣ ንብረት ደህንነት ለማረጋገጥ የበረራ ደህንነትን ማረጋገጥ ወሳኝ ስለሆነ ቀድሞ ጥንቃቄ ተወስዶ በረራ የሚቋረጥበት አጋጣሚ አለ።
በአብዛኛው በደቡብ ምዕራብና በሀገሪቱ የስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች እስከ ላይ ድረስ ባለው ሁኔታ፣ የሀገራችንን የምስራቅና የሰሜን አካባቢዎችን ይዞ የደመና ሽፋኖች ይታያሉ። ትንበያው እንደሚያሳው በተለየ መልኩ የጭጋግ ሁኔታዎች ከትላንት ጀምሮ እስከ ዛሬ፣ ለነገም በሚሆን ደረጃ ስላለ ነው አየር መንገዱ በተለይ በደሴ፣ ወደ ሰሜኑ ባሉ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች ለጊዜው በረራዎችን ያቋረጠው " ብለዋል።
በረራው ባይቋረጥ ሊከሰት የሚችለው ነገር በተመለከተ መሪ ስራ አስፈጻሚው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?
" ህብረተሰቡ፣ የቲክቫህ ቤተሰቦችም ማወቅ ያለባቸው በረራን ለአደጋ ከሚያጋልጡ ክስተቶች በብዙ ፐርሰንት/በዋነኝነት በአየር ሁኔታ ሊከሰቱ በሚችሉ ችግሮች መሆኑን ነው። ትልቁ ነገር ከሁሉም ነገር በፊት የበረራ ደህንነትን ማስቀደም ነው።
የአቬሽን ኢንዱስትሪው የሚያስቀድመው ለበረራ ደህንነት ነው፣ ችግር እንዳያጋጥም ከወዲሁ ይጠነቀቃል። በእንደዚህ አይነት ሁኔታ አውሮፕላኖች ይረፉ፣ ይነሱ ቢባል በተለይ ደሴ በጣም አስቸጋሪ ኤርፖርት ነው። በተራራዎች መካከል ያለ ነው፣ በአንድ በኩል ብቻ መግቢያ ነው ያለው የአውሮፕላን መንደርደሪያው።
ቶሎ ገልጦ ካልታየ ብዙ የበረራ አደጋዎች ሊያስከትል የሚችል መሆኑ ስለታወቀ ችግሩን ለማስወገድ አየር መንገዱ ይህን ለመወሰን ተገዷል " ብለዋል።
በረራ ያስተጓጎለው የደሴ የአየር ፀባይ እስከመቼ ይቆያል ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ፣ " በነገው እለትም ሊያጋጥም እንደሚችል መረጃዎች ያሳያሉ። የደመና ሽፋኑ ወደ ደቡብና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ብቻ ተወስነው ስለሚቆዩ ደሴ አካባቢ ቀስ በቀስ እየጸዳ ይሄዳል፤ ሆኖም ግን የኢንስቲትዩቱን ድረ ገጽ መከታተል ጠቃሚ ይሆናል " ሲሉ መልሰዋል።
በየብስ ትራንስፖርትም አሽከርካሪዎች ከወትሮው በተለዬ ፍጥነት እንዲቀንሱ ጭምር የደሴ ከተማ ፓሊስ አሳስቧል፣ የአየር ፀባዩ ከየብስ ትራንስፖርት ጋር በተያያዘ ያለው ሁኔታስ ምንድን ነው ? የሚል ጥያቄም ለአቶ ካሳ አቅርበናል።
እሳቸውም፣ " አካባቢው ላይ የሚስተዋለው ከጉም መለስ ያለ ጭጋግ ነው/ በጭጋግና በጉም መካከል ያለ ነው። ያ ደግሞ የየብስ ትራንስፖርት ላይም እይታን ይጋርዳል " ሲሉ ትዕዛዝ የተሞላበትን መንስኤ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" እግዚአብሔር ረድቶን ይህን ልጅ ለማትረፍ ስላበቃን፣ ስላስተማረን ፤ አስተማሪዎቻችንም ይህንን ሞያ ስላስተማሩን ከልብ አመሰግናለሁ " - ዶ/ር ራሄል አበባየሁ
🩺" ብዙ ሒደቶችን አልፈን ህክምናውን በስኬት በማጠናቀቃችን ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል " - ዶ/ር ቢኒያም ተሾመ
በሳምሪታን ቀዶ ህክምና ማዕከል (Samaritan Surgical Centre) ለመጀመሪያ ጊዜ በማሽን የተቆረጠ እጅን በተሳካ ሁኔታ መቀጠል መቻሉን የአጥንት ቀዶ ህክምና የከፍተኛ አደጋዎች እና መገጣጠሚያ ቅየራ ሰብ-ስፔሻሊስት ዶ/ር ቢኒያም ተሾመ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ይህንን የተቆረጠ እጅ ወደነበረበት ለመመለስ፦
- የጽዳት ሰራተኞች፣
- የሰመመን ባለሞያዎች፣
- ነርሶች፣
- አናስቴዚዮሎጂስት፣
- የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት፣
- የቫስኩላር ሰርጀሪ ባለሙያ፣
- የፕላስቲክ ሰርጀሪ ባለሙያዎች እና ሌሎችም በርካታ የህክምና ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል ብለዋል።
ዶክተር ቢኒያም ተሾመ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በዝርዝር ምን አሉ ?
" ባለኝ መረጃ መሰረት በሀገራችን የተቆረጠ እጅን ለመቀጠል የተደረጉ የቀዶ ህክምናዎች የሉም። እጁን የቀጠልነት ልጅ ጉዳት የደረሰበት ስጋ ቤት ላይ ማሽን ለማስተካከል በሚሞክርበት ወቅተ ነው።
እጁን ሙሉ በሙሉ ቆርጦትም አልቆመም፣ ደረቱን ቀዶታል፣ ወደ ውስጥ አለመግባቱ ነው እንጂ የደረቱ ጉዳት ከፍተኛ ነበር የሚሆነው።
የልጁ እጅ ከክርኑ በላይ ሙሉ በሙሉ ነው የተቆረጠው፣ ልጁ በአስቸኳይ ወደ ጤና ተቋም መሔድ ችሏል፣ ይህ ትልቅ ነገር ነው፣ የሄደበት ተቋም ጥሩ በመሆኑ ይፈስ የነበረውን ደም በማስቆም የተቆረጠውን እጁን በበረዶ ለብቻው አስቀምጠውታል። ይህም ዳግም ለመቀጠል በጣም ወሳኝ ነው።
በሰአቱ የአጥንት ቀዶ ህክምና ቡድኑ በሳምሪታን ቀዶ ህክምና ማዕከል ሌላ ቀዶ ህክምና እየሰራን ነበረ። ጉዳዩ ተነገረን፣ ፕላስቲክ ሰርጀሪውም በአቅራቢያችን ነበር። ጉዳት የደረሰበት ልጅ በአስቸኳይ እንዲመጣ አደረግን፣ ልጁ እና እጁ እየብቻ ነው የመጣው።
የህክምና ቡድኑ እጁ ቢቀጠል ውጤታማ የመሆን እድል እንዳለው ከሳይንሱ ጋር በመገመት በድፍረት ለመስራት ወስነን መስራት ችለናል።
በደቂቃዎች በእጁ ውስጥ ብረት በማስገባት ለደም ስር ከቀዶ ህክምና ባለሞያዋ በፍጥነት ሰርተን አጠናቀቅን። ከዛም በኋላ vascular surgical ባለሙያዋ ዶክተር ራሔል የደም ስሮቹን የማያያዝ ስራ በሰአቱ ሰርታ ማጠናቀቅ በመቻሏ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጋለች።
አሁን ላይ የሚቀሩ ቀዶ ህክምናዎች አሉ፣ ምክንያቱም የእጅ እንቅስቃሴዎቹን ጋር በተያያዘ መሰራት ያለባቸው ጉዳዮች አሉ። እጁን ማትረፍ ችለናል፣ አንድ ቆዶ ህክምና ይቀረናል። ይህ የእጁን እነቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም እንኳ በበቂ ሁኔታ መመለስ የሚያስችል ነው።
ዋናው ነገር እጁን ማትረፍ ነበር ተሳክቷል፣ የእጅ ስራው ብዙ ነው፣ እግር እና እጅ የሚለያየው መሰረታዊ ነገር ይህ ነው፣ እግር ሲቆረጥ ለመቀጠል ብዙ አያለፋም፣ እጅ ደግሞ ስራው ውስብስብ ነው፣ በወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ከእጁ ማግኘት ያለበትን አገልግሎት ያገኛል።
ይህ ቀዶ ህክምና ለተሰራለት ሰው በጣም ትልቅ ነገር ነው፣ እንደ ቀዶ ህክምና ሀኪምም ስራውን በቡድን በስኬት መስራት በመቻላችን ደስ ብሎናል፣ ብዙ ሒደቶችን አልፈን ህክምናውን በስኬት በማጠናቀቃችን ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል።
የመጀመሪያም እንደመሆናችን መጠን ሌላም ጊዜ እንድንሰራ ያደፋፍረናል፣ ማህበረሰቡም ግንዛቤ ይኖረዋል፣ ሌሎች ባለሙያዎችም መስራት እንደሚችሉ እና እጅ ሲቆረጥ መቀጠል እንደሚችሉ ይማሩበታል " ብለዋል።
የደም ሥር ቀዶ ህክምና ሰብ ስፔሻሊስት ዶክተር ራሄል አበባየሁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?
" ቀዶ ህክምናውን ለማከናወን 6 ስአት ወስዶብናል፣ የ20 አመት ወጣት ልጅ ነው። ልጁ በጣም እድለኛ ነው፣ የተቆረጠን እጅ እና እግር ይዞ የመምጣት ባህልም ሆነ ልምድ እንደ ሀገር የለንም። የዚህን ልጅ የተቆረጠ እጁን በበረዶ ያስቀመጡለት የህክምና ባለሙያዎች በጣም ጎበዞች ናቸው። ያለ ኦክስጅን ረጅም ጊዜ መቆየት እንዲችል አድርገውለታል።
የብዙ ሰው እርብርብ ነው ስኬታማ ያደረገው። ከዚህም በሗላ ክትትል እና rehabilitation ያስፈልገዋል። ጥገና ስንሰራ የደም ሁኔታው በጣም እየዋዠቀ ሲያስቸግር ነበር። የደም ዝውውሩን መድሀኒት እየተጠቀምን ነው ያስተካከልነው። ስለሆነም የነርቭ ጥገናው ረፈድ ባለ ጊዜ መሰራት ስለሚችል ቅድሚያ እጁን ለማዳን ባደረግነው ጥረት አሳክተነዋል። በቅርብ ቀን የነርቭ ጥገና እናደርግለታለን።
ጉዳት የደረሰበትን ልጅ እጅህን እንቀጥልልህ የመዳን እድሉ ግን 50/ 50 ነው፣ እንሞክርልህ ብለን ስንጠይቀው እሱም አስታማሚዎቹም ፍቃደኛ ሆነው በጥሩ ሁኔታ ተሰርቶለት ተሳክቶልናል። ይህ ማለት ግን ሁሌም ይሳካል ማለት አይደለም።
እግዚአብሔር ረድቶን ይህን ልጅ ለማትረፍ ስላበቃን፣ ስላስተማረን፣ አስተማሪዎቻችንም ይህንን ሞያ ስላስተማሩን ከልብ አመሰግናለሁ።
እስካሁን ባለው ሂደት በጣም ደስተኛ ነኝ፣ ከዚህም በኋላ ክትትል እና rehabilitation አድርጎ ልጅየው በደንብ Functional ሆኖ እግዚአብሔር ተጨምሮበት እንደምናየው ተስፋ አደርጋለሁ።
የህክምና ቡድኑ መደነቅ አለባቸው፣ እኛ የምንሰራው እግዚአብሔር የፈቀደልንን ብቻ ነው። ሰርተንም ላይሳካልን ይችላል፣ አሁን ላይ ግን ስለተሳካልን ከዚህም በኋላ ገፋፍተን በደንብ መስራት እንደምንችል በማሳየታችን ደስ ብሎኛል " ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
" ህወሓት ከተፈናቃዮች ሳይቀር በማስገደድ ወርሀዊ የፓርቲ መዋጮ እየጠየቀ ነው " - ሳልሳይ ወያነ ትግራይ
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ " በትግራይ በጠበንጃ የሚመራ የፓለቲካ ሀይል ስልጣን ላይ ተቀምጧል " ሲል ክስ አሰማ።
ህወሓት ከተፈናቃዮች ሳይቀር በማስገደድ ወርሀዊ የፓርቲ መዋጮ እየጠየቀ ነው ያለው ፓርቲው በእንዳስላሰ-ሽረ የተፈናቃዮች የማቆያ ማእከል የሆነውን በማስረጃ አቅርቧል።
በማቆያ ማእከሉ የነበሩት የ6 ልጆች አባት ተፈናቃይ በህወሓት የፓርቲ ወርሃዊ ክፍያ እንዲከፈሉ ይጠየቃሉ ይላል ፓርቲው።
አባትየው " እኔ የፓርቲ አባል አይደለሁም ፤ ብሆንም በዚህ ወቅት የመክፈል አቅም የለኝም " በማለት እንደመለሱ ገልጿል።
" የፓርቲ አባል አይደለሁም ወርሃዊ መዋጮ አልከፍልም " ያሉት አባት በህወሓት አባላት በፕላስቲክ የተሰራ ቤታቸው ፈርሶ ከመጠለያ ማእከሉ እንዲባረሩ መደረጋቸው ፓርቲው አሳውቋል።
ፓርቲው በትግራይ ህዝብ ጫንቃ በጠበንጃ የሚያዝ የፓለቲካ ሀይል ተጭኗል ቢልም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ሳይመለሱ የክልሉ ግዛታዊ አንድነት ሳይረጋገጥ ምርጫ መካሄድ የለበትም ሲል አሳስቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
@tikvahethiopia
❤ 481😡 200😭 117🤔 23😢 22🕊 21🙏 8💔 8😱 7👏 6🥰 5
" በቂ የጸጥታ አካላት በአስቸኳይ ይሰማሩ " - ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከኅዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ በጋምቤላ ወረዳ (አቦል)፣ በጋምቤላ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭትና የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና ሥጋቶችን እየተከታተለ መሆኑን አሳውቋል።
እስካሁን ባሰባሰበው መረጃ በጋምቤላ ከተማ የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡመድ ኡጁሉ መገደልን ተከትሎ በከተማውና በአካባቢው ባሉት ወረዳዎችና ቀበሌዎች ግጭት ተፈጥሮ በተለያዩ አከባቢዎች የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ መቆየቱን ገልጿል።
በዚህም ሳቢያ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን፣ የሰዎችን እና የመጓጓዣ አማራጮችን እንቅስቃሴ የሚገድብ የሰዓት እላፊ በክልሉ መንግሥት መጣሉን፤ ባንኮችንና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት ማቋረጣቸውን እንደተገነዘበ አመልክቷል።
በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭትና የሰላም መደፍረስ በፍጥነት በማስቆም በሰዎች በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደኅንነት፣ ከቦታ ቦታ የመዘዋወር፣ የንብረት፣ የሥራ እንዲሁም ሌሎች ሰብአዊ መብቶች ላይ ተጨማሪ ጥሰቶች እንዳይደርሱ ለመከላከል በቂ የጸጥታ አካላት በአስቸኳይ እንዲሰማሩ እንዲደረግ ኢሰመኮ አሳስቧል።
" በክልሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጠሩ ግጭቶችን በዘላቂነት ለማስቆም፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እና ወደፊት ተመሳሳይ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳይከሰቱ ለመከላከል የፌዴራሉ እና የክልሉ መንግሥታት ተገቢ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል " ብሏል።
በአካባቢው ተሰሚነት ያላቸው የሀገር ሽማግሌዎችን እንዲሁም የሃይማኖት እና የማኅረሰብ መሪዎችን በማሳተፍ ውይይቶችና ዕርቆች እንዲካሄዱ እንዲሁም ከአጋር ድርጅቶችና ባለድርሻዎች ጋር በትብብር በመሥራት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ተገቢውን ሕክምና እና ካሳ እንዲያገኙ እንዲሁም እንዲቋቋሙ ማድረግ ይገባል ሲልም ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
❤ 836😭 131🕊 54💔 25🙏 18🥰 10😢 10🤔 9😱 8😡 1
" ዛሬ እና ነገ ወደ ደሴ የሚያደረገውን በረራ ለማቋረጥ ተገድጃለሁ " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ሰዓት በደሴ እና አካበቢዋ ባለው ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ ምክንያት በዛሬው እና በነገው ዕለት ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን በረራ ለማቋረጥ መገደዱን አሳውቋል።
አየር መንገዱ ከሚቲዎሮሎጂ በሚደርሰው መረጃ መሰረት የአየር ፀባዩ እንደተስተካከለ በረራዎቹ ወደመደበኛ አገልግሎታቸው የሚመለሱበትን ጊዜ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
በአገልግሎቱ መቋረጥ ለሚፈጠረው መጉላላት ይቅርታም ጠይቋል።
@tikvahethiopia
ብፁዕ አቡነ ያሬድ ከምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ተነሱ። ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ሀገረ ስብከቱን እንዲመሩ ተመድበዋል።
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የምሥራቅ አርሲ ሀገረስብከትን
እስከ ግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ጉባኤ
ድረስ ደርበው እንዲመሩ በቋሚ ሲኖዶስ ተመደቡ።
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ከሚመሩት ሀገረ ስብከት በተጨማሪ የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከትን እስከ ግንቦት 2018 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ጉባኤ ድረስ ደርበው እየመሩ እንዲቆዩ በቋሚ ሲኖዶስ ተወስኖ በቅዱስ ፓትርያርኩ በተጻፈ ደብዳቤ ተመድበዋል።
ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ከሚገኙ ካህናት፣ አባ ገዳዎች፣ሀደ ሲንቄዎች፣ ወጣቶችና ምዕመናን የቀረበለትን ተደጋጋሚ አቤቱታ ሲቀርብለት ነበር።
ይህን መነሻ በማድረግ አጣሪ ልዑክ መድቦ ችግሩ በዝርዝር ተጠንቶ እንዲቀርብለት ካደረገ በኋላ ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ብፁዕ አቡነ ያሬድ ከምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ተነስተው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርሰቲያን የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስነት ሥራቸውን እያከናወኑ እስከ ግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ጉባኤ እንዲቆዩ ውሳኔ አስተላልፏል።
የቅዱስ ሲኖስ ምልዐተ ጉባኤ ጥቅምት 2018 ዓ.ም ባደረገደው ጉባኤ ቋሚ ሲኖዶስ የተከሰተውን ችግር በመመርመር መፍትሔ እንዲሰጥ ውሳኔ ማሰተላለፉ ይታወሳል።
መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TilvahEthiopiaFamilyAA

❤ 2

#EOTCTV
@tikvahethiopia
❤ 1