ግጥም ብቻ 📘
رفتن به کانال در Telegram
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch @shiyach_bicha ✔ @zefenbicha @leul_mekonnen1
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

65 761
مشترکین
-2524 ساعت
-567 روز
-31830 روز
آرشیو پست ها
◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌
በል እንግዲህ እግዜር
መዝገብህን ክፈት| ጆሮህን ቀስር
ብሶት ልንገርህ| ስጋና አጥንት ሚሰረስር
፩
❛❛እዚህ እታች ሰፈር
ማዳበሪውን እንዳነገተ
ሀይላድ ሲለቅም
መኪና ገጭቶት| አንድ ህጻን ሞተ
ይሙት ግድ የለም
"ነበር አልን እንጂ"
የኖረው ህይወት| ህይወት አይደለም
ትራፊ እንጀራ ለዕልፍ አዕላፍ ያራቀራመተ
ባርከው እያለህ
ሳትባርክለት እርቦት የሞተ
ቀብሮት ወንድሙን
ከአይኑ አብሶ የእንባ ደሙኑ
ኑሮን ሊጋፋ
ለሀይላንድ ልቃሚ አንገት ቢደፋ
ያው እንደወጣ አልተመለሰም
እንደ ጥያቄው እንደ ምኞቱ
የሱን አልን እንጂ
ታሪኩ እራሱ ታሪክ ነው የስንቱ❜❜
በል እንግዲ እግዜር
መዝገብክን ክፈት| ጆሮህን ቀስር
ብሶት ልንገርህ| ስጋና አጥንት የሚሰረስር
፪
ደሞም አንዲት ሴት
የቀሚስ ቅዷ የጭኗ ቁስል
የአርብ ዕለት ጌጥክን ግርፋት ምስል
እንደከተበ
አይኗ በምሬት
የራሄል እንባ እያዘነበ
ስታልጎመጉም እንዲ ትል ነበር
❛❛የጫንክብኝን የህይወት ቀንበር
ችዬ ስጋፋው
ስለምን ወንዱን ስሜት አስከፋው
የገፋ ባሌን
ዝሙት ሀጥያቱን ገና ሳለምደው
ከሞት መራራ
ብልቱ መርቶ የሚያራምደው
በእናቱ እንጀራ
በሰባ እጆቹ ጨፍልቆ ይዞ
የሴት ገላዬን በቁም ገንዞ
በድን ሲያስቀረኝ
ቂም እንዳይመስልህ
በእንባ ዘለላ የሚያናግረኝ
ይልቅ መዳፍክን
የአንገት ማህተቤን| ወሰድ ከህይወቴ
አንቆ ሲደፍረኝ
ምስለ ስዕልህ ገዝፎ ከቤቴ
ተስፋ እንዳይሆነኝ ?
ስንቅ እንዳይሆነኝ ?
ኖረህ ዝምታ እያስደፈረኝ
ሆድ ይፍጀው እንጂ
ችዬ ያልነገርኩህ ብዙ ነበረኝ።❜❜
በል እንግዲህ እግዜር
መዝገብህን ክፈት| ጆሮህን ቀስር
ብሶት ልንገርህ| ስጋና አጥንት የሚሰረስር
፫
ደግሞ'ም ትዝ አለኝ
አንዱ ፈላስፋ የተናገረው
ከትቦ ያኖረው
❛❛የዚህ አለም ቁስል የዚህ አለም ብሶት
ውርቂያኖስ በእንባ እንደመለካት
ተጠማው ያለን በሀሞት ማርካት
እየቀበሩ
ማማረር ሀጥያት ብሎ መመካት
ነድያን አልፎ
ዲያቆን ፍለጋ መቅድስ ማንኳኳት❜❜
ደሞም ትዝ አለኝ
ትዝ አለኝ ብዙ. . . .
በሀረግ በስንኝ እንዴት ይቋጠር ?
ጋን ተሸክሞል ሰው እንደጠጠር!
ይልቅ ዝም ነው !
ሁሌም ዝም . . . .ዝም
የዚህ አለም ቁስል የዚህ አለም ብሶት
የትኛው ጠቢብ| ደራሲ ደርሶት ?
የትኛው አምላክ| እንባን አብሶት ?
ይልቅ ዝም ነው!
ሁሌም ዝም..... ዝም
ሰሚ ሳይኖረን አንናዘዝም!።
፬
እናም በል እግዜር
መዝገብህን ዝጋው| ጆሮ ዳባ አልብስ
የሰማ ሳይሆን
ስሙኝ ያለ ነው የሚያደባብስ!. . .
by የአብስራ_ሳሙኤል
@getem
@getem
@getem❤ 36👍 6😢 6😁 1
◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌
በል እንግዲህ እግዜር
መዝገብህን ክፈት| ጆሮህን ቀስር
ብሶት ልንገርህ| ስጋና አጥንት ሚሰረስር
🖤
፩
❛❛እዚህ እታች ሰፈር
ማዳበሪውን እንዳነገተ
ሀይላድ ሲለቅም
መኪና ገጭቶት| አንድ ህጻን ሞተ
ይሙት ግድ የለም
"ነበር አልን እንጂ"
የኖረው ህይወት| ህይወት አይደለም
ትራፊ እንጀራ ለዕልፍ አዕላፍ ያራቀራመተ
ባርከው እያለህ
ሳትባርክለት እርቦት የሞተ
ቀብሮት ወንድሙን
ከአይኑ አብሶ የእንባ ደሙኑ
ኑሮን ሊጋፋ
ለሀይላንድ ልቃሚ አንገት ቢደፋ
ያው እንደወጣ አልተመለሰም
እንደ ጥያቄው እንደ ምኞቱ
የሱን አልን እንጂ
ታሪኩ እራሱ ታሪክ ነው የስንቱ❜❜
🖤
በል እንግዲ እግዜር
መዝገብክን ክፈት| ጆሮህን ቀስር
ብሶት ልንገርህ| ስጋና አጥንት የሚሰረስር
፪
ደሞም አንዲት ሴት
የቀሚስ ቅዷ የጭኗ ቁስል
የአርብ ዕለት ጌጥክን ግርፋት ምስል
እንደከተበ
አይኗ በምሬት
የራሄል እንባ እያዘነበ
ስታልጎመጉም እንዲ ትል ነበር
❛❛የጫንክብኝን የህይወት ቀንበር
ችዬ ስጋፋው
ስለምን ወንዱን ስሜት አስከፋው
የገፋ ባሌን
ዝሙት ሀጥያቱን ገና ሳለምደው
ከሞት መራራ
ብልቱ መርቶ የሚያራምደው
በእናቱ እንጀራ
በሰባ እጆቹ ጨፍልቆ ይዞ
የሴት ገላዬን በቁም ገንዞ
በድን ሲያስቀረኝ
ቂም እንዳይመስልህ
በእንባ ዘለላ የሚያናግረኝ
ይልቅ መዳፍክን
የአንገት ማህተቤን| ወሰድ ከህይወቴ
አንቆ ሲደፍረኝ
ምስለ ስዕልህ ገዝፎ ከቤቴ
ተስፋ እንዳይሆነኝ ?
ስንቅ እንዳይሆነኝ ?
ኖረህ ዝምታ እያስደፈረኝ
ሆድ ይፍጀው እንጂ
ችዬ ያልነገርኩህ ብዙ ነበረኝ።❜❜
🖤
በል እንግዲህ እግዜር
መዝገብህን ክፈት| ጆሮህን ቀስር
ብሶት ልንገርህ| ስጋና አጥንት የሚሰረስር
፫
ደግሞ'ም ትዝ አለኝ
አንዱ ፈላስፋ የተናገረው
ከትቦ ያኖረው
❛❛የዚህ አለም ቁስል የዚህ አለም ብሶት
ውርቂያኖስ በእንባ እንደመለካት
ተጠማው ያለን በሀሞት ማርካት
እየቀበሩ
ማማረር ሀጥያት ብሎ መመካት
ነድያን አልፎ
ዲያቆን ፍለጋ መቅድስ ማንኳኳት❜❜
ደሞም ትዝ አለኝ
ትዝ አለኝ ብዙ. . . .
በሀረግ በስንኝ እንዴት ይቋጠር ?
ጋን ተሸክሞል ሰው እንደጠጠር!
ይልቅ ዝም ነው !
ሁሌም ዝም . . . .ዝም
የዚህ አለም ቁስል የዚህ አለም ብሶት
የትኛው ጠቢብ| ደራሲ ደርሶት ?
የትኛው አምላክ| እንባን አብሶት ?
ይልቅ ዝም ነው!
ሁሌም ዝም..... ዝም
ሰሚ ሳይኖረን አንናዘዝም!።
🖤
፬
እናም በል እግዜር
መዝገብህን ዝጋው| ጆሮ ዳባ አልብስ
የሰማ ሳይሆን
ስሙኝ ያለ ነው የሚያደባብስ!. . .
#የአብስራ_ሳሙኤል
@getem
@getem
@getem❤ 1
እግረ-መንገድ
_ _ _ _ _ _ _ _
ጡሩንባውን ሰምተኸ፤
እንደ አጋጣሚ...
ከድንኳኑ ዘልቀኸ፤
ከሟች ፎቶግራፍ
ፊትለፊት ተቀምጠኸ፤
በጨዋታ መሐል
ድንገት ቀና ብለኸ፤
ያየኸው እንደሆን፤
ከሳሎን ያኖርከው
ያንተ ፎቶግራፍ
ትዝ ብሎ ይሆን?!
ያ... የልደትኸ ፎቶ
ያ... የምርቃትኸ ፎቶ
ያ... የሠርግኸ ፎቶ፤
የቤትኸን ግርግም
ግድግዳውን ሞልቶ፤
ዙ..ሪ..ያ..ው..ን ያለው፤
አለ'ለት ቀራኒዮ
ከድንኳኑ የሚሰቅለው።
ሳሙኤል አለሙ
@yeketemawmenagn
@getem
@getem
@getem
👍 14❤ 11
ሆያ ሆዬ .....ሆ!
ሆያ ሆዬ.......ሆ!
°°°°°•••••°°°°°•••••
ተቀሰቀሰብኝ ቡሄ ትዝታዬ
ልቤ ስትፈነጥዝ ስትሰክር በፌሽታ
ከእኩዮቼ ጋራ በቡሄ ጨዋታ
በዛ ላይ ነፃነት አይቆጡም ጌታ፡፡
ገመድ እየገመድኩ ጅራፍ ስሰራ
በጩኸቱ ሳበስር ወጥቼ ከጋራ
በሆያሆዬ ዜማ በሞቀው ጭፈራ
ደሞ ይመሽና ችቦዬን ሳበራ
በልጅነት ፍቅር ወረት በማያውቀው
በጭፈራ ወጀብ ልብን በሚያሞቀው
የጌቶችን በር አፍ ሚያበስረው ደርሶ
ባባቶች ምርቃት ሙልሙል ፍቅር ቆርሶ
በእናቶች ስጦታ ከመቀነታቸው
በታቦሩ ብርሃን ሞልቶ ሰላማቸው
አስታቅፈውን ሙልሙል ሲፈስስ ፈገግታቸው
አይ ልጅነት ደጉ ምን አለ ከዚህ በላይ
ችቦ ተለኩሶ ፍቅር በርቶ ሲታይ፡፡
እንኳን አደረሰን!
By @Abuugida
@getem
@getem
@getem
❤ 20👍 14🎉 1
_
ትንሽ
ትንሽ
የቆጠብናትን ሳቅ
ነይ አብረን እንሳቅ
°
የእንባ ላቦት
ፊቱን አጥቦት
የኑሮ አለት ከሚጋፋ
በለቅሶ ጉም የሚጠፋ
የህመም ሲቃ የቋጠረ
ያንገቱ ክር የከረረ
አንቆ እስትንፋስ ለሚነጥቀው
እያላላ ከሚስቀው
የሰው መንጋ
ሳንጠጋ
ገሽሽ ላርግሽ
ካለምኩበት ልመሽግሽ
የፎረፍናት ከፈጣሪ
የደበቅነው ከአሳዳሪ
አለኝ ቦታ
ድረሽ ላፍታ
እዚህ ጋራ ባልልሽም
የማልመው አይጠፈሽም
ተገኚልኝ ከቀጠርኩሽ
ንገሺልኝ ከሰየምኩሽ
°
ካነገትነው| የቀን ቀንበር
ከወረስነው| የቂም መንበር
እሽቅድድም ከበዛበት
የደበቅናት አንዲት ዕለት
ለደም ቁርባን
የበግ መባን
ከለመደው
ከሚወደው
የሸሸግናት
የቀለስናት
አለች ቦታ
ድረሽ ላፍታ
°
የህይወት ምሰሶ
ቁልቁል ተደርምሶ
ጨፍልቆ እስኪገለን
ላፍታ ገሸሽ ብለን
ትንሽ
ትንሽ
የቆጠብናትን ሳቅ
ነይ አብረን እንሳቅ
By @YabisraSamuel
@getem
@getem
@getem❤ 40😁 3
( ስላንተ ደህና ነኝ )
===============
ተስፋዬ መንምኖ ነገዬ አንሶብኝ
መንገዴ እሾህ ሞልቶ ልቤ ደንድኖብኝ
ከሰው የተነሳ እምነቴ ጎድሎብኝ
መኖር እናፍቅ ዘንድ ምክንያት ጠፎቶብኝ
ራሴን ልቀጣ .. ወይ ልከ'ፉ እያለሁ
ልኖር የሞትክልኝ
የዘላለም ወዳጅ አንተን አስባለሁ !
እንዲህ እንደዛሬ ...
የህይወትን ቋጠሮ መፍቻ ሲቸግረኝ
ሰው ያጣ ይመስል
ወጥመዱን ደርድሮ ጠላት ሲታገለኝ
ለእናት አባት ወዳጅ ለዘመድ ግድየለኝ
ፍቅርህን ስል ብቻ
ስላንተ ደህና ነኝ !
በሁሉ ስመረር .. ቃልህ ነው ደባብሶ
ከጭንቅ የሚያድነኝ ።
By @Kiyorna
@getem
@getem
@getem
❤ 53🔥 8🎉 1
አለሁ ጥሩ አለሁ መልካም
መኖር እኔን አያስለካም
ብይ ግጥም ፅፌ የሰጠሁሽ ለታ
እንደዚህ ነበረ የኔ መልእክቱ መግቢያ
ባለፈው ባለፈው ከተለየንበት፣
ካገኘሁሽ ብየ ከተጣላንበት፣
ልመጣ ፈልጌ አንድ ነገር ያዘኝ
የኩራት አባዜ አዙሮ ደበቀኝ
ግን አልቻለም ልቤ ፈለገ ሊመጣ
ኩራት ተወገደ እግሬ ከቤት ወጣ
አጥቼሽ ድጋሚ ከምሰብር ብየ
ደውየ ጠራሁሽ ናፈቅሽኝ አንችየ
ለማውራት ብፈራ ባልችልም መናገር
እወድሻለሁ ማለት መቼስ ኩራት አይደል።
by @Eyob16m
@getem
@getem
@getem
❤ 27👍 13🔥 4🎉 1
ሀገሬስ ገንፎ ናት
በስልጣን ማንኪያቸው የሚቆራርሷት
ቂቤ ወሬያቸውን በርበሬ ስራቸው
ጨመር አርገውባት
እሷ ያዝኩት ስትል
የስጧትን ሁሉ አጣቅሰው አላውሰው
በዛ ስልጣን ማንኪያ በህብረት አብረው
ያውም ክብ ሰርተው
እንደ ጉድ ሚበሏት የሚጎራረሷት
ሀገሬ ለእነርሱ ገንፎ ብቻ እኮ ናት
@topazionnn
@getem
@getem
👍 33❤ 14😢 8🔥 2
[የእንባ
ቅብብል]
ይታየኛል ከአድማሱ ስር ከጀንበሯ ፈቀቅ ብሎ
ድል ነው ብሎ የሚሸል የወዳጁን ስጋ ጥሎ
ለጋ ሚስኪን እናቱ የሀዘን ማቋን ለብሳ
ልጇን ትጠብቃለች የባሏን አፈር መልሳ
የእንባ ቅብብል ነው ደም እያፈሰሱ
ለቅሶ ይቀመጣሉ ከድል ሲመለሱ
የሰው ልጅ በቃሉ መቼ ፍሬ ያፈራል?
ሰይፍ እየመዘዘ ለሞት ይጠራራል?
ይብቃ! ግድ አይደለም!
ሽንፈት አይደለም!
ያቃቃረን የቂም ቁርሾ
ያዘማመተን ለበቀል
በአንዲት ጀንበር ባይካስም
ግዳይ ጠርቶ ሰውን መጣል
----ጨለማውን አይመልስም!
የአብስራ ሳሙኤል
@getem
@getem
@getem❤ 38👍 9🔥 1
፨፨፨ ፨፨፨
አጥቤ እንዳነፃው
በምህረት ተሰጥቶኝ
ተጨማሪ እድል፡
ጨለማ አይደለውም
ሚስተካከል ቀኔን
በእንባ የምገድል
ስህተት አትቁጠሩ
ጣታቹ የኔን ግብር
እያመለከተ፦
ምንም ልምድ የለኝም፥
መጀመሪያዬ ነው
ስኖር እንደናንተ።
@mikiyas_feyisa
@getem
@paappii
❤ 44👍 4🔥 3😱 3🤩 1
ያኔ ...ትምህርት ቤት ሳለን፤
ሰዓት አሳለፉ አረፈዱ ተብለን፤
በደረቅ አርጬሜ እንገረፋለን፤
ነገር ግን በህይወት.....
ይደርሳል እያልን፤
ጥቂት ካረፈድን፤
ህይወታችን ሁሉ ይመሰቃቀላል፤
ዳግም ላይመለስ ይዘበራረቃል።
..........................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
❤ 45😢 7🔥 3👎 1
ትተነው ላልመጣነው ልጅነት
.
መክሰስ አትሆንም ለራት አትበቃም
መርጠህ አታውቅም ፈቅደህ አትነቃም
ብዬ ላፈንኩህ ሳላመነታ
ልጅነቴ ሆይ ባክህ ይቅርታ!
ልትስቅ ስትል ላልኩህ በኩርኩም
ልራመድ ስትል
አርፈህ ተቀመጥ ላልኩህ አትቁም
በሳቅህ ግርጌ ቁጣ ፀንሼ
ትልቁን ህፃን
አዋቂ ላልኩህ ከድሜህ ቀንሼ!
ሌት ባታሸንፍ ቀን ባትረታ
አብራኝ በቀረች አንዲት ትርታ
ልጅነቴ ሆይ ባክህ ይቅርታ!
አንጠልጥዬህ ባልፍ በትዝታ ቋት
የጊዜን መንገድ
ሊጓዟት እንጂ ከቶ ላይርቋት
ትቼህ የመጣሁ ጥንት ቢሆንም
የርምጃ ያህል አልተራራቅንም።
ለተሞላበት ችኮላ ጥድፊያ
እሰጥ ይመስል ምቹ ማረፊያ
ስላመጣሁህ
ወደማይገባህ የማደግ ልፊያ
ልጅነቴ ሆይ ባክህ ይቅርታ!
By Yadel Tizazu
@getem
@getem
@paappii
❤ 48👍 11😢 3🔥 2
ከ ልክ በላይ ነብስን ማጥፋት
ለማይሆኑ ልብን ማልፋት
ሰርክ ማለም ተንቀልቅሎ
ቀልብን ልብን ላንድ ጥሎ
በነሱ ዘንድ አለመዋል
በሳቅ ብቻ ለይስሙላ
ትርፉ ድካም ትርፉ ብክነት
መውደቅ ብቻ ወደኋላ
ኑሮን መሳል ካንድ ወገን
አሳብቦ አሳብዶ
ከሁለት ባንዳቸው
አንዱ ብቻ ጠልቶ
አንዱ ብቻ ወዶ።
ልክ ላልሆነ መፈላለግ
እንደገባኝ እንደገባን
ባይን ብቻ ቀርቶ
ቃላት ካላግባባን
ለይስሙላ መኖር አንድ ሆንን እያሉ
አይሰምረውምና ፍቅር ይዘት ውሉ
ልክን ለማበጀት
እቅድን አስምርን ለአንድ አመት በጀት
እንሞክር ግድ የለም
ብዙ ማፍቀር ልክ አይደለም።
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
❤ 38🔥 4🤩 1
ጉድፍ ሳይታከለው ሳይኖረው ጥላሸት
መልኩን ሳይለዋውጥ በቀንም በመሸት
ምላስ ያልበዛበት የሽንገላዎች ቃል
ልብሽን ማፍቀሬ ከአይኖቼ ያስታውቃል
ፀሃይ ከጨረቃ ከዋክብት ደመና
ሰማይና ጠፈር ጎህ አየር ቀረና
ላንቺነትሽ ቃላት ላንቺነት ምሳሌ
ረቂቅ ሆኖበት ምላሴና ቃሌ
ምንም ባደርግ ምንም
ከጥጎች እስከ ጥግ
ለንዳንቺ አይነት ቆንጆ
የለውምና ህግ
መሰየሜን ተውኩት
ቃላት አያገኙም ልብሽን ለሚያውቁት
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
❤ 30🔥 6👍 4
( አጭሯ ፍቅሬ )
===========
አሁን በቀደም ለት
ለሐምሌ መባቻ አንድ ሳምንት ሲቀር
ያቺ የቀድሞ ፍቅሬ
ሠርክ የምትጓጓለት ልደቷ ቀን ነበር ..
እንደ ሰው ምሰጣት
ኢምንት ባይኖረኝ
በዚህ የደስታ ቀን ከምትቀየመኝ
ለክፉ ቀን ብዬ ከሸሸግኩት ቃላት
ውዱን መርጬላት
ለዘመናት ይዤው ከቆየሁት ጥበብ
ጥቂት ሰውቼላት
ማንም የማይደርሰው
ድንቅ ረጅጅጅጅጅጅጅም ግጥም
ስጦታ ጻፍኩላት !
ግና ከዚያ ወዲያ ታሪክ ተቀየረ
ፍቅሬ አኮረፈችኝ ፈገግታዋም ቀረ
ስንት ተጨንቄ የዘረፍኩት ቅኔ
ልቧን ሰባበረ ...
ወዮ !
የልቤን ጭማቂ የከንፈሬን ፍሬ
ነበር ያቀበልኳት
አረ በሚካኤል የሰማ እስቲ ይፍረደኝ
ምን እንደበደልኳት
ብዬ ወገን ዘመድ ልኬ ሳስጠይቃት
(መልሷ እኔኑ አሳቀኝ)
ግጥሜ መርዘሙ ነበር ለካ ያስከፋት
የረሳሁት ነገር ... ፍቅሬ ለካ አጭር ናት
የረዘመ ሁሉ አሽሙር የሚመስላት !!
እኒያ ከዚያ ወዲያ
እንደ ጎልማሳ ጢም ግጥም ስከረክም
አንድ ሃረግ ሳወጣ አንድ ሃሳብ ሲደክም
እንደኛው ሲጎላ አንደኛው ሲጨልም
እንደነበር ተውኩት
በእርሷም ጨከንኩባት
ምን ልታረግልኝ ሀሳብ ካማሳጠር
የሷን ቁመት ማርዘም መቅለሉ ካልገባት !!!
By @kiyorna
@getem
@getem
@getem
❤ 64😁 39👍 6🔥 3👎 1
