fa
Feedback
ግጥም ብቻ 📘

ግጥም ብቻ 📘

رفتن به کانال در Telegram

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch @shiyach_bicha@zefenbicha @leul_mekonnen1

نمایش بیشتر
2025 سال در اعدادsnowflakes fon
card fon
65 745
مشترکین
-924 ساعت
-597 روز
-32030 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
ተከታይ የሌለው አንድ (ሳሙኤል አለሙ) መውደድ.... ባርባ...ባርባው፤ ማፍቀር..... ባርባ...ባርባው፤ ለታዛዡ ልቤ ዋሽታ ለማትገባው። መውደድ.... ባርባ...ባርባው፤ ማፍቀር..... ባርባ...ባርባው፤ ለተገዢው ልቤ ክዳው ለማትገባው። ለታዛዡ ልቤ ዋሽታ ለማትገባው። ቀርበው ሲጠይቁኝ... አንዱን ልቤን እያስለካው፤ አንዴ ልየው ሲሉኝ... አንዱን ልቤን እያስጠጋው፤ ስኖር...አንዴ...አንዴ...አንዴ...አንዴ ላንዴ...ስኖር...ስኖር...ስኖር...ስኖር ስኖር..አንዴ...አንዴ...አንዴ...አንዴ በስንቱ አንዴ-ዎች አንዱን ልቤን፥ ላንዴ ሳስሞክረው፤ አለሁኝ በተስፋ ገዢ እንደቸገረው። ሳሙኤል አለሙ @Samuelalemuu @getem @getem
نمایش همه...
👍 1
መሳቀቅ ካልወሉበት ዉለው ባለቤቱን ማነቅ መደንገጥ ያለርባን አሳቦ ልብ ምት ማቋረጥ መታመም አሜን ለማይል ልብ ሰርክ ሁሌም መሳለም ማርገብገብ ለነደደ እሳት ለዕፍታ መስገብገብ ለማትረጋ እርግብ ጎጆ እየቀለስን በበረረች ቁጥር ስንት ጊዜ አለቀስን እያወቅን ስራችን እንደሌለው ጥቅም በጨዋታ መሃል ስቀን አናስቅም ማርገብገብ ለምዶብን ለጊዜ ተቀማጭ እንራወጣለን እስክንሆን ተለዋጭ መሆንን ሳናውቀው ኑረን በጉድ ሀገር ደሃ አድርጎ አስቀረን ልማድ ሚሉት ነገር ለመሆን ሳንጥር ስንት ጊዜ ፈጀን        በማስሆን አረጀን ለነዋሪ ጊዜ ሆነን አኗኗሪ          አደረገን ቀሪ። ዮኒ      ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
نمایش همه...
👍 29 6
እኔ እማ ወይ አልሞት ወይ አልድን፣ በናፍቆቷ ስዝል በፍቅሯ ስታጠን፤ ገለባው መውደዴ ወይ ከሷ ራስ አይወልቅ፣ ዋጋ አልባ ተሥፋዬ አይለቅ አይላቀቅ፤ የሸበተ ጸጉሬ ማመሃኘት አይተው፣ ላስረጀችኝ እሷ ከገዳም አልገባው፤ ወይ አልሞትኩ ወይ አልዳንኩ ግራ ነው ነገሬ፣ ካንዱ ልጠጋ ነው ከዛሬ ጀምሬ። By @eyadermoges1 @getem @getem @getem
نمایش همه...
20👍 8😁 8🤩 2
( ቆየን አይደል .. ) ============== ቆየን አይደል : የማለዳ አአዕዋፍ ድምጽ ከእርጋታ ጋር ካደመጥን ጀምበር ቀልታ ጎህ ስትቀድ በተመስጦ ካደነቅን ... ቆየን አይደል : እናት አባት ሲመርቁ ከልባችን " አሜን " ካልን ጨቅላ ሕጻናት በየሜዳው ሲቦርቁ በመደሰት ካስተዋልን .... ቆየን አይደል : ዝናብ መቶን ጸሐይ ሞቀን " እፎይ " ካልን ጨረቃ እና ኮከብ ናፍቀን ወደ ሰማይ ቀና ካልን .... ቆየን አይደል ? By @Kiyorna @getem @getem @getem
نمایش همه...
63👍 31😢 12🔥 2🎉 2
ተከታይ የሌለው አንድ (ሳሙኤል አለሙ) መውደድ.... ባርባ...ባርባው፤ ማፍቀር..... ባርባ...ባርባው፤ ለታዛዡ ልቤ ዋሽታ ለማትገባው። መውደድ.... ባርባ...ባርባው፤ ማፍቀር..... ባርባ...ባርባው፤ ለተገዢው ልቤ ክዳው ለማትገባው። ለታዛዡ ልቤ ዋሽታ ለማትገባው። ቀርበው ሲጠይቁኝ... አንዱን ልቤን እያስለካው፤ አንዴ ልየው ሲሉኝ... አንዱን ልቤን እያስጠጋው፤ ስኖር...አንዴ...አንዴ...አንዴ...አንዴ ላንዴ...ስኖር...ስኖር...ስኖር...ስኖር ስኖር..አንዴ...አንዴ...አንዴ...አንዴ በስንቱ አንዴ-ዎች አንዱን ልቤን፥ ላንዴ ሳስሞክረው፤ አለሁኝ በተስፋ ገዢ እንደቸገረው። ሳሙኤል አለሙ @Samuelalemuu @getem @getem @getem
نمایش همه...
👍 13🔥 6 5😢 3
#ሩብ_አንድ_ሌሊት መነሻ ሀሳብ ስብሃት /እግዚአብሔር ( ሌቱም አይነጋልኝ 1993 / ) . . እቱ፤ ይቅር ምናባቱ፣ አይነጋ ሌሊቱ። ይለፍ እንደዘበት፤ ይጠቅለል ዐመቱ። ሀሳብ እንደረሳ፤ እንደ ግልገል ሞሳ፤ 'ቅፍሽ ስር ልክረም። ሀሳቤን ሰብስቤ፤ በለዛሽ ተስቤ፤ ከልብሽ ማዕጠንት ሰግጄ ቆርቤ፡፡ በጨዋታሽ ስጥም፣ ሎሚ ጉንጭሽን ሳም፤ ልዛል እንደገና በመዓዛሽ ድክምም፣ ባለንጋ ጣቶችሽ እሽት አከም አከም፤ እወገቤ ግድም፤ ቧጠሺኝ ደም በደም፣ ከዛ..... ጡትሽ መሃል ጋደምምም። በአይኖችሽ ስበት፤ በንግስናሽ ውበት፣ በትንፋሽሽ ሙቀት፤ በእጆችሽ ዳበሳ፣ በከንፈር ቀመሳ። በጣት መነካካት፣ አፍንጫ መለካት። ከዛ ደሞ መሳቅ፣ ከአይኔ ለመራቅ። ከዛ ደሞ ማፈር፣ ሽጉጥ አንገቴ ስር። በፍቅርሽ ........ም፣ እል.............................ም፣ እል.............................ም፣ እል.............................ም፣ ወዲያ ወደ ጥልቁ ወደ ፍቅርሽ አለም፡፡ እሰ...............ይ፤ እሰ...............ይ፤ እሰ...............ይ፤ ሽንቅጥቅጥ ዘመናይ፣ ቁጥብ አሳ መሳይ፤ አደብ አስገዢልኝ ሽርክቱ አመሌን፣ እንደ ፀደይ ልፍካ ደባብሺው አካሌን፡፡ ያድነኝ የሰራሽ ከነፍስሽ ላይ ቆርሶ፣ ልጠግን መንፈሴን ካንቺ ላይ ተገምሶ፡፡ እኔ.......፤ በስሉስ ተክኜ፤ ለሳቅሽ መንኜ፤ ዳማ ፈረስ ጭኜ፤ ሽምጥ መጋለብ፣ ሳቢ ደረትሽ ላይ፤ ድንግል መሬትሽ ላይ፤ ሰንደቄን ማውለብለብ፡፡ ግልብ ጋለብ ብትን ስብስብ ያዝ ለቀቅ ጋለል ንቅንቅ ልጓም ንጥቅ ጦሬን ነቅነቅ እልም ውርውር አንገት ስብር ናጥ በጥበጥ እፍር ቅብጥ ጨምቅ ቁንጥጥ እሽት ጭብጥ እቅፍ ቧጠጥ ስንን ሰክን ስፍስፍ ጥንን ፍትት ጥግን ፈንቀል ጀነን በላብ ስጥም ሳቋ ሲጥም . . ሳም ንክስ ብትን ቅስስ ጭልጥ መለስ፣ ሳብ ግፍትር ለስለስ ግትር፡፡ ጎንበስ ቀና ፍርት ዘና ከዛ ተንፈስ ሻጥ መለስ እንደገና፡፡ . . የእግዜር መና። አይይይ ቁንጅና! አቤት ውበት፤ ሴት የሆነ የሴት ገላ፣ የሚመጠጥ ማር ወለላ። መቃ መሳይ ያንገት ማኛ፣ መለስለሷ ማያስተኛ። በየት በኩል በየት ገና፣ አንገቱዋ ስር ትኩስ ዳና። ደረቱዋ ላይ መጋል ፍሬ፣ ነዳፊ ንብ ጥርኝ አውሬ፣ ትላንት ናፍቆት ምን ነሽ ዛሬ? መጠንሰሻ የዳማ ምንጭ፣ የመሰንበት የመኖር ፍንጭ፣ ጡቷ ግድም ጥቁር ነጥብ፣ ፍም ትንፋሽዋ የሚያስጥም። ሴት አካሏ ምትሃተኛ፣ መልኳ ድርብ የመልከኛ። ልዝብ ሳቋ የሚደረጅ፣ መዓዛዋም የደብር ደጅ። እይት ሰረቅ ዳሌ ነቅነቅ ጥርስ ገለጥ ጥብብ መሰጥ ከላይ ረጋ ከታች ጠጋ አይን ጭፍን ድርብ ሽፍን ብትን ብትን ደሞ ስብስብ እቅፍ እስብ ትንፋሽ ስርቅ ልብ ድልቅ ጉስም ጉስም ግርሽት ድፍርስ ፀጉር ነስነስ . . "ኸረ ቀስ" "ኸረ ቀስ" . . ሶስቴ መሄድ ለመመለስ። . . ዘራፍ ወንዱ......!!! ✍️ ዓቢይ ( @abiye12 ) @getem @getem @getem
نمایش همه...
👍 39🔥 17 11😱 9🤩 5👎 1
አበባዬ ነበርክ የትንፋሼ ፊደል የመኖሬ ምክንያት የነፍሴ መታደል መጨከን የምችል አይመስለኝም ነበር እስክትቃወመው የመውደዴን ነገር ምንም ብታፈቅረኝ ውበቴን ብታደንቅ ትችል አልነበር ወይ ህጎቼን መጠበቅ አሁን ስናፍቅህ ከፍቶህ ስትጨነቅ በቀረ ትል ይሆን ምናል ብጠነቀቅ እራሴን እንደምን አረኩት ብቸኛ መልካም ሰው ያገኘች ነበርኩ እድለኛ ወራት አልፈው ነበር ብዙ ሳትጠጋ ድንገት ተቀበልኩህ አንድ ሆንኩኝ ካንተጋ የለሰለሰችው የልጅነትህ ፀሀይ ለመሆን መረጥኩኝ የፍቅርህ ተከታይ ይቅርታህም በዛ የከበደህ ሲቀል እኔም ተበዳይ ሆንኩ በራስ የመታለል እንዳልተማመንኩኝ እንደማልጎዳ ያ ምቹ እቅፍህ ሆነብኝ እንግዳ አይንይህም ከአይኖቼ በድንገት ተለየ ያልከውን ለመሆን እጅጉን ዘገየህ ይቅር እንደምልህ የተማመንክበት ምን ይሆን ያሸሸህ ከሰጠሁህ ገነት ምንድነው ያስናቀህ የጠለቀ ፍቅሬን ለምን አልበቃህም ስትስም ከንፈሬን እኮ እንዴት ችለህ እንዳልሳሳህልኝ ጭንቀቴን አበዛህ እንዴት ጨከንክብኝ እንደምን ልርሳልህ ያን የውሸት እንባ ሀሳቤን ስትቀይር ሆዴን ስታባባ እኔም ተንደርድሬ ከአእቅፍህ ስገባ ቃልህ ተሰበረ ሆንክ የእምነት ሌባ እኔስ ተሞኝቼ ከልቤ አፍቅሬ እፊትህ ማለቅሰው ነበረ የምሬን ለማትስተካከል ላትቀየር ነገር እኔንም ስታገኝ ከሰነፎች ሀገር ድካሜን ሳሳይህ አክመኧኝ ነበር የተጠገነ ልብ ዳግመኛ ሊሰበር እጆችህን ይዤ አይኖቼን ጨፈንኩ መራኧኝ ወዳንተ ከራሴም ራቅኩ ተደበቄ ሳለሁ ካንተ ተለጥፌ ሙቀትህን ስሰርቅ ስዳስ በመዳፌ አበባና ሻማው በድንገት ተረሳ መልክህ ተለወጠ እጅህም ተነሳ ልቤም ደነገጠ እየጠረጠረ ለማመን ከበደው ልክ እንዳልነበረ ያደረከው ነገር ሰበቡን ባቶስድም አስለመደኧኛል ስህተት መደጋገም ፍቅሬን ያቆሸሽከው ሳታውቅ አልነበረም By - @mondalit @getem @getem @paappii
نمایش همه...
👍 20 20😢 9😱 2
............... ሰአሊው በሸራው ዕርቃን መሳል ከለመደ ጸሀፊውም በብዕሩ ዳሌና ጭን ከወደደ አትሸፍኝው ከአደባባይ ተጸየፊው ጨርቅሽን ጣይ ጥበብ ይሆን የአምላክ ስእል ዕርቃን መቆም ከአደባባይ ስጋና ነፍስ ከአንድ አስራ ለዘሞተች ገሀድ አለም ውቡ ገላሽ ውበት ይሁን የተፈጥሮ ንጽህ ቀለም ምክንያት አሽቶ ቢመኝሽም ዕርቃኗን ነች በሚል ቀመር ልባስ የወሲብ ሽፋን ቢሆን እንስሳ እንስን ቢደፍር ነበር የለም የለም አንቺን አይቶ ዝሙት የለም እልፍ ብጥይ ጥለት ገፈፈሽ በሸራው ተዳራሽ በብዕር በገሀድ በሰራው ውል ለሌለው ሀሳብ የገፈፉት ገላ አደባባይ ስትቀርብ ጥበብ ነች ተብላ ጣይና ጨርቅሽን ሁኚው የገሀድ ቀለም የለም የለም አንቺ አይቶ ዝሙት የለም By @mad12titan @getem @getem @getem
نمایش همه...
👍 28 6👎 4
ነይ በሰማያዊ ሰማዩ ላይ አንሳፈፍ በፍቅራችን ምናብ እንበል እና ከፍ መኖር ውልክፍክፉ ሳያደናቅፈን ነይ ሀሴት እናድርግ በመውደድ ተቃቅፈን ነይ አብረን እንብረር ይህ መኖር ሳይጠልፈን በህይወት ውበቷ የመኖርን ክርታስ ሰብረን እንጣለው መኖርን አናስታውስ በአብሮነታችን አለምን እንራሳ ለኛ አይገባንም ያለም ግሳንግሷ መኖርን እንካድ ፍቅርን እናሳድ እግዜር ይቀዬመን ሀጥያታችን ይብዛ አብረን እንጥፋ እና አለምን እንግዛ ነይ መዓት ይውረድብን ሀጥያታችን በዝቶ አንድ አንቺ ካለሺኝ ምን ሊጎድለኝ ከቶ ነይ.................... by kerim @getem @getem @getem
نمایش همه...
22👍 12👎 11😱 1
በነጭ ምዕመናን ታቦቷ ታጀበ ዲያቆኑ ተነሳ ሊቃችን ወረበ ጭብጫቦ እልልታው      ዝማሬው ይበልጣል ማርያም ማርያም ሲባል       ስምሽ ይጣፍጣል። ማርያም ዮኒ     ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
نمایش همه...
148👍 19🔥 7🤩 7👎 6😁 2
ባለቅኔ ነበርኩ ባለኝ ሰዓት ቅኔ ያ...ኔ! ቅኔ ይሏት እርግብ አፍኜ ስመግብ ስታዜም ስሰማት መዝሙሯን ስቀማት ቀምቼ ሳፏጨው የሷን እየቀዳሁ፡ አድማስ ላይ ስረጨው፤ የሰማ ታማሚ፡ መስሎት የፈለቀኝ ወደኔ እየመጣ፡ ፈውስ ሲጠይቀኝ፤ እሷ የምትለውን፡ ስሰማ ሳቀብል ከሷ የሚፈሰውን፡ ስቀዳ ሳፀብል የዳነው መስካሪ፡ ታምሬን ሲነዛ ደጄን የሚናፍቅ፡ አማኝ እየበዛ ለፀጋ ለስሜ፡ ሲመታለት ድቤ በድንገት አምልጣኝ፡ በረረች እርግቤ። ሄደች ከነድምጿ፡ በስም አስቀርታኝ ሄደች ከነፈውሷ፡ ከገድሌ ጋር ትታኝ የምበትንላት፡ ጥሬ ቀርቶኝ ከጄ ቢረክስም በዜማ የፀደቀው ደጄ በፈውስ ናፋቂ፡ ሰርክ ይጨናነቃል ምስኪን! ኪን እርግቤ እንኳንስ መሄዷን ፡መኖሯን ማን ያውቃል? ብቻዬን አዘልኩት፡ አግኝቶ ማጣቱን ጸጋው የተቀማ ፡ስም ሆኖ መቅረቱን ማቃቴን አፍኜ፡ ብቻዬን ታመምኩት በነበር ስወደስ ፡መቻልን ቃተትኩት፥ ግን አልሆነልኝም አልጮህ ድምፅ የለኝም ያድናቂዬ ድቤ፡ ዜማው ይበልጠኛል አልጠፋ እንደርግቤ ማን ክንፍ ይሰጠኛል? ታዲያ ከዚህ ስቃይ፡ ማን ያስመልጠኛል? እውነት! ባለቅኔ ነበርኩ፡ ያ...ኔ! ቅኔ ይሏት እርግብ፡ እያለች ከጎኔ ዜማዋ ሲያደምቀኝ ትንፋሿ ሲሞቀኝ አርፎ እንደማጣጣም፡ እየቀዳሁ ስቀኝ ያየ ሲያጨበጭብ፡ የሰማ ሲያደንቀኝ ስጨምቃት ተጨንቃ የምታስጨንቀኝ አንድ እርግብ ነበረች፤ አሁን ግን የለችም! ለጠየቀኝ ሁሉ ፡እሺ ስል በርራለች። ልክ እንደዛ ተረት፡ የልጅ መጫወቻ ባለቅኔ ነበርኩ፡ አሁን ግን ፍራቻ ሁሉን ነገር ላጣው፡ የቀረኝ ስም ብቻ። By Red-8 @getem @getem @paappii
نمایش همه...
30👍 23🔥 13😢 1
ጥለሺኝ እየሄድሽ ..... መንገዷን ጨርቅ አርገው፣ ህይወቷንም ቀና፤ የምል አይነት እንከፍ, የምል አይነት ጀዝባ ፡ አይደለውምና፦ ኋላ አደናቅፎኝ ከፎቅ ላይ ብጥልሽ ስለምትጎጂ፤ ከተፋታን ወዲህ መንገዱ ያሰጋል ተጠንቅቀሽ ሂጂ። © @mikiyas_feyisa @getem @getem @paappii
نمایش همه...
😁 52👍 15🔥 9 6🤩 2👎 1
የናፈቀኝ ነገር ያልኖርኩበት ሃገር! ማንም ሰው ሳያውቀኝ÷ ከዜሮ መጀመር ጠዋት የምሰማው የማላውቃትን ወፍ፣ አዲስ አዘማመር። የፈለግሁት ነገር መኖሪያ መቀየር ልብሴንም መቀየር ለየት ቢልልኝ የምጠጣው ውሃ÷ የምስበው አየር። መራመድ የሚያምረኝ በአዲስ ጎዳና ላይ ÷ በኔ እግር የነቃ ባገኝ አዲስ ሃሳብ አዲስ አይነት እውነት ÷ ወይም አዲስ ቋንቋ። ማየት የምመኘው ÷ያልራቀ ወደላይ ሰማያዊ ሳይሆን ÷አዲስ አይነት ሰማይ በማላውቀው ቀለም ÷ አዲስ አይነት ፀሃይ። . . . የማውቀውን ሁሉ መተካት በመሻት ወደማይታወቅ ህይወቴን ብሸሻት የማልሰለቸውን ÷ አጣሁት ፈልጌው (ስገምት ችግሩን) አዲሱን የሚያስረጅ ÷ እኔ ነኝ አሮጌው። በርግጥ እንኳን ማርጀት ÷ መኖር ይለመዳል? መሰልቸትን መቻል÷ ከናፍቆት ይከብዳል? በማውቀው አኗኗር÷ መኖር ከከበደኝ ወደማይታወቅ ÷ ልቤ ካሰደደኝ እኔ የሌለሁበት ÷ ማንስ በወሰደኝ? ወላጅ ባገኘሁኝ በሆነ አይነት ታምር÷ ዳግም በወለደኝ?? By Haileleleul Aph @getem @getem @getem
نمایش همه...
👍 44 36🔥 3😱 3😢 1
የመሃን መሓላ (የሞገሤ ልጅ) ከጠበልተኞች ደጅ፣ ደጅ ጠኚ መሃል፣ ሱባኤ ሳትይዝ ሰርክ ሳትጠበል፤ መታመሟን አውቃ፣ ላለመዳን አምና፣ ከእምነቷ ሳስታ አለመቻል ታጥና፤ ቅናትን ስራ አርጋ፣ ብቸኝነት ወርሷት፣ ሠው መሃል ሠው አታ ሠው መፈለግ ታክቷት፤ ዐይኗን አደራርቃ፣ በልቧ እያነባች፣ ድካሟ ደግፏት ጽናቷን እያጣች፤ ከጠበልተኞች ደጅ፣ ስለት ደርሶ ልታይ፣ ንግሥ ኪዳን ሳትል ከደጀሠላም ዋይ፤ ተሥፋ የገረፋት፣ ማግኘቷን አርቆ፣ ማሕጸን ለማርጠብ እልፍ አስጠብቆ፤ ያሰለቸ ተሥፋ፣ ሚራዡ ምትሓት፣ ልጄን ይንሳኝ የሚል መሓላ አስለመዳት። ብትዋሽ ሟች የለ፣ አይመሰክር ቆሞ፣ ጠፊም መጪም ሳይኖር ቃልኪዳን ታትሞ፤ ልጄን ይንሳኝ ፍርሚያ፣ ዋጋ ያላገኘ፣ ተሥፋን ባጣች መሃን አንደበት የዋኘ፤ ቢዋሽ ጉዳት አልባ፣ ባይዋሽም ምንም፣ የሌሎች ዶግማ ቃል ለመሃን አይከብድም። የሌላት አይሞትም፣ የሌላት አይመጣ፣ ናፍቆት ቅናት በልቷት ከተሥፋ ተቋርጣ፤ ልክ እንደወለዱት፣ መሆን እያማራት፣ ልጅ አፏን እንዳይሸሽ መሃላዋ ይዞት፤ ዋሽታም “ልጄን ይንሳኝ”፣ ለእውነትም “ይንሳኝ”፣ ልማድ ሆኖባታል ላታጣም ላታገኝ። By @eyadermoges1 @getem @getem @paappii
نمایش همه...
👍 35 10😢 9🔥 1
ማዘን በኛ ይበቃ ፎቶዋ ይከልከል እሷን ያየ ሁሉ በፍቅር አይበከል ዮኒ      ኣታን @yonatoz ንሸጣ: ገጣሚ እንደልቡ @getem @getem @getem
نمایش همه...
👍 19 9👎 3😁 3
Photo unavailableShow in Telegram
ይድረሰ:- ለኩርፊያ (ሳሙኤል አለሙ) ° ° የሻማው ብርሃን ደብዝዞ የንፋስ ሽውታ ጠረገው፤ አፋችኑ ቃላት አርግዞ አምጦ መውለድ አቃተው፤ ዝም...ዝም...ዝም ጭልም-ልም-ልም ገዘፈ ድቅድቁ ጨለማው፤ ቃላችንን ሾተላይ ቀማው። ° ° እንደ'ኔና እንደ እሷ ጀምበሩ ሳይነጋ መሰሎቻችን ጋ አፋቸውን ሊያዘጋ ጥድፍ-ድፍ-ድፍ...ሲል ርብት-ብት-ብት...ሲል ደርሶ አፋችንን ቆልፎበት። ደጃፉ ላይ ፥ ስደርስበት። ° ° ቀኝህን ለሚመታ ግራውን ስጡት እንዳለው ጌታ ሳትነፍገው የእግዜሩን ሰላምታ እንደ ዲዳ ዝም ካለህ ላፍታም... ላፍታም.... ሳታመንታ ኩርፊያን <እንኳን ደስ አለህ!> በልልኝ! ° ° ይኸው እኔና እሷ ሰርክ ኩርፍ ኩ-ርፍ-ርፍ ሰርክ እቅፍ እ-ቅፍ-ቅፍ ይኸው እኔና እሷ እንደ ቄጤማው ፥ እንደ አውዳመቱ፤ ድንገት ካየኸው ፥ የኩርፊያን ፊቱ፤ ትላንቱ ለምልሞ ፥ ዛሬ ክስመቱ። ° ° እንደ ጳጉሜ ሶስት ዕለቱ ዕንባውን አዘነብነው። የሩፋኤል ፀበል አይደል ክፋቱን አያድነው። ከጫጫታው አልፈን ነጎድጓዱን አክለነው። ጭቅጭቁን አድ'ምጦ በዜማ አቀነቀነው። ° ° ተወው በክረምቱ ፥ ይርገጥ ዳንኪራ ተወው በዕንባችን ፥ ይስከር ያሽካካ በፀደዩ ብርሃን ፥ እንደምንፈካ ዘንግቶታናልና! ° ° የዛሬዋን ዕድል ከቆጠረው ከድል ትርኢት ያዘጋጅ እንግዳም ይጥራ ፥ ድግሱንም ይደግሰው እንደ ንጉስ አይዙር ፥ ግማሽ ቀኑን የሚነግሰው ተወው! ሳሙኤል አለሙ @Samuelalemuu @getem @getem
نمایش همه...
👍 25 7
ግጥምና አበባ በርግጥም በርግጥም አትጨክኚም አይደል በአበባ በግጥም ትወጃለሽ አይደል? ሀቅን በቃል መግደል ? ትፈቅጃለሽ አይደል ? በስንኝ መደለል? ( እንግዲህ... ) እውነት እንኪገባሽ ፍቅር በአፍሽ ጥላ መውደድ በዓይንሽ ጥላ ናፍቆት እንዲያረቅሽ ህይወት በአንቺ ገላ እስከዚያ ግን ድረስ ተስፋ ተሞልቼ... ባዶ እጄን ልመለስ እየከፋኝ ልግባ እስክሰጥሽ ድረስ ግጥምና አበባ! By Sirak Wondemu @getem @getem @paappii
نمایش همه...
👍 19 12😱 2🎉 2🤩 1
እንዲገባሽ! (የሞገሤ ልጅ) ከመከፋት ያልፋል፣ ሃዘኔ ሃዘን ነው ይከምራል አጭዶ፣ ላላልቅ ያነደኛል፣ ከሃሳብ ወላፈን ናፍቆት እሳት ማግዶ። ባታውቂ ነው እንጂ.. አልመጣም ማለትሽ በናፍቆት ያስምጣል፣ ከሰመመን ዘፍቆ ከቅዠት ያሰምጣል፣ ከራስ ስጋ አጣልቶ ከመንፈሥ ያርቃል፣ ሠው ማጣትም ከብዶ ሠው ማግኘት ይጨንቃል፣ ስሜት እንደ ጥይት ድንገት ይባርቃል፣ ያልበላን ሠውነት ረሃብ ያጠረቃል፣ የእስከአሁኑ እንዲህ ነው ነገንስ ማን ያውቃል? ህ! ህ! እህህ! ደሞ ያልነገርኩሽ.. ክርሥቶሥ የኛ ሺ ለሱ አንድ እለት፣ ለኔ ስትቀሪ.. አልመጣም ማለትሽ ቀኔን አርጎት ሳምንት፣ ባልነግርሽ ነው እንጂ.. ስላላወቅሽልኝ መምጣት የምትረሺው፣ ብነግርሽ ኖሮ እማ.. ባትመጪም እንኳን ከመቅረትሽ ጀርባ ጉዳቴን ባየሺው። ደሞ የረሳሁት.. በአንድ የቀን ጉዱ አንቺነትሽ ወርሶኝ፣ እኩል እኔን ላንቺ ለማካፈል ቆርሶኝ፤ ድሮም አንድ አጥንቴ አንቺ ዘንድ ቀርቶ፣ እሱን እንደማግኘት መከፈሌ በዝቶ፤ ወይ ይዘሽ አልያዝሽው ደጅ ጥናት ጎዳው፣ ወይ ለኔ አልሆነ ራሴን ራሴ ከዳው፤ አንቺም ለመምጣትሽ አጠረኝ ማስረጃ፣ ሁለት አድርገሽኝ ሠው መሆኔን እንጃ። እባክሽ መውደዴን ችለሽ አታኩርፊው፣ ልቤ ቆሞ ደክሟል ራርተሽ አሳርፊው፤ የኔ ብቻ ሁኚ የኔ ብቻ አለም፣ መድከሜ ላይቋጭ ላያልቅ አይርዘም፤ የኔ ብቻ ሁኚ ካምላክሽ ቀጥሎ፣ ላንቺም ግፍ ነው ማለፍ ታማሚሽን ጥሎ፤ ስለዕመቤቴ እሩሩዋ እናት፣ ቢጤሽን መጽውቺኝ ልብሽን ልመጽወት። ያኔ እድናለሁ፣ እጠነክራለሁ አላለቃቅስም፣ አሁን ላይ ግን ከኔ፣ ማጥፋቴ ስም ሊያሰጥ አይነቃቀስም። ተረዳሽኝ አይደል? አዎ ተረድተሻል። እንጂ እማ ወዳጁን፣ ካልታመመ በቀር ማስከፋት ማን ይሻል? አዎ ተረድተሻል! ይበልጥ እንዲገባሽ.. ምን ከቤት ቢገፋ፣ ባልለመደው ንፋስ ሊገረፍ ቢሰጥም፣ ያበደ ውሻ እንጂ፣ ያልታመመ ውሻ የጌታውን እግር ሊጎዳ አይነክስም። አሁን ዘልቆ ገባሽ? አዎ ተረድተሻል! ስለዚህ እብድ ውሻሽ ለነከሰሽ ሊክስ ጤነኛ እንዲሆን ይቅርታሽን ይሻል። By @eyadermoges1 @getem @getem @paappii
نمایش همه...
👍 37 15😢 9
Photo unavailableShow in Telegram
ይፍጠኑ!!! ከተለያየ አቅጣጫ በጥራት የተነሱ 5 ፎቶዎችን በ @Ribki30 ላይ ይላኩልን።
نمایش همه...
👍 5
"ያ ባሏ ፈታት አሉ...ወስልታበት" "አየህ አይደል ለክፉ ክፉ ሲያዝበት?" "ኧረ ከሷ ውጭ ሴት አያውቅም ነበር" "ሚስትህ ነግራኝ ባይሆን አላምንህም ነበር" ዘማርቆስ @getem @getem @getem
نمایش همه...
😁 47 14👍 12🤩 5👎 3😱 3