fa
Feedback
Addis Ababa Education Bureau

Addis Ababa Education Bureau

رفتن به کانال در Telegram

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

نمایش بیشتر
2025 سال در اعدادsnowflakes fon
card fon
150 232
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+677 روز
+34630 روز
آرشیو پست ها
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች ማህበር ለተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ድጋፍ አደረገ። (መስከረም 13/2018 ዓ.ም) በዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተካሄደው መርሀግብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች መሰረታዊ ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ መገርሳ አስፋው ድጋፉን ተረክበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትምህርት ስራ የሁሉንም ባለድርሻ ተሳትፎ የሚፈልግ ተግባር መሆኑን በመገንዘብ ለተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ድጋፍ በማድረጉ በራሳቸው እና በተማሪዎች ስም ምስጋና አቅርበው ቢሮው በቀጣይ ከአየር መንገዱ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች መሰረታዊ ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ መገርሳ አስፋው በበኩላቸው ተቋማቸው የነገ ሀገር ተረካቢ ለሆኑ ዜጎች ድጋፍ በማድረጉ ከፍተኛ ኩራት እንደሚሰማው ጠቁመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር በመሆን የትምህርት ስራው ውጤታማ እንዲሆን በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አመላክተዋል። በመርሀግብሩ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ19 አመት በላይ በአብራሪነት በማገልገል ላይ የሚገኙት ካፒቴን ሚካኤልን ጨምሮ የተቋሙ ሰራተኞች ለተማሪዎች የህይወት ልምዳቸውን አካፍለዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
نمایش همه...
78👍 9🔥 1
نمایش همه...
23👏 7😁 3
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ እና የዘርፉ አስተባባሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በበኩላቸው ቢሮው ለዕውቀት ሽግግር መርሀግብር ትኩረት በመስጠት እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ፕሮግራሙን ዘወትር ሰኞ ማለዳ በማካሄድ ላይ መሆኑን ጠቁመው በዛሬው እለት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ቴክኖሎጂ በመማር ማስተማር ሂደቱ እየሰጠ ባለው ጥቅም እና ጉዳት ዙሪያ ሙያዊ ውይይት ለማካሄድ የተዘጋጀው ርዕሰ ጉዳይ በትምህርት ተቋማት በመተግበር ላይ የሚገኘው በቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት ውጤታማ እንዲሆን አቅጣጫ የሚቀመጥበት መሆኑን አስረድተዋል። በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ካሳ ሚካኤል እና የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ተባባሪ ፕሮፌሰር እዩኤል አባተ ቴክኖሎጂ በመማር ማስተማር ስራው የሚኖረውን አወንታዊ እና አሉታዊ ተጽኖ መሰረት ያደረገ የመከራከሪያ ሀሳብ አቅርበው በተሳታፊዎች ሙያዊ ክርክር የተካሄደ ሲሆን በፕሮግራሙ ማጠቃለያ የውይይቱ ተሳታፊዎች የተስማሙበት ባለ ስምንት ነጥብ የአቋም መግለጫ ቀርቧል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
نمایش همه...
34👍 7🤗 4
የሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር መርሀግብር አካል የሆነ እና "ቴክኖሎጂ በትምህርት ስራ ያለው አወንታዊ እና አሉታዊ ሚና" በሚል ርዕስ ሙያዊ ክርክር (professional debate) ተካሄደ። (መስከረም 12/2018 ዓ.ም) በመርሀግብሩ የቢሮው አጠቃላይ ካውንስል አባላት ፣ የተለያዩ ቢሮዎች የሰራ ሀላፊዎች ፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች እና አስተባባሪዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች ፣ርዕሳነ መምህራን ፣ የግል ትምህርት ቤት ማህበር ተወካዮች እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የመምህራን ማህበር እና የተማሪ ወላጅ ማህበር አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ሴክተሩ ዘወትር ሰኞ ማለዳ ከሚካሄደው የዕውቀት ሽግግር ፕሮግራም ባሻገር በሩብ አመት አንድ ጊዜ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በተመረጠ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሙያዊ ክርክር የሚካሄድበት መርሀ ግብር መዘጋጀቱን እና የዛሬው ዝግጅት የዚሁ አካል መሆኑን አመላክተዋል። ኃላፊው አያይዘውም በዛሬው መርሀ ግብር ቴክኖሎጂ በመማር ማስተማር ሂደቱ እያበረከተ በሚገኘው አወንታዊ እና አሉታዊ ተጽኖ ዙሪያ ሙያዊ ክርክር በማድረግ ቴክኖሎጂን ለመማር ማስተማር ስራው በአግባቡ መጠቀም እንዲቻል ሙያዊ ክርክሩ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል።
نمایش همه...
26👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
ማስታወቂያ በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤ በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 14/2018 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ማሳሰቢያ፡- 1.  የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተማሪዎችን ስሚቀበል ምርጫችሁ ውስጥ ማካተት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። 2.  አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምርጫ ውስጥ የማይካተቱ መሆኑ እናሳውቃለን።
نمایش همه...
70👎 15👍 10
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የትምህርት በሬዲዮ ስርጭት ነገ ይጀምራል፡፡ (መስከረም 11/2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የትምህርት በሬዲዮ ከነገ እለት ማለትም ከ12/1/2018 ዓ.ም ጀምሮ መሰራጨት የሚጀምር መሆኑ ተገለጸ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ዲናኦል ጫላ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን ትምህርት በሬዲዮ ከነገ እለት ጀምሮ መሰራጨት የሚጀምር መሆኑ የገለጹ ሲሆን የሬዲዮ ትምህርቱ ለመደበኛ ትምህርቱ አጋዥ እና ተማሪዎች በቀላሉ መረዳት እንዲችሉ አቅም የሚሆን መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አያይዘዉም የትምህርት ስርጭቱን በመጣው የሬዲዮ ትምህርት ስርጭት መርሀ ግብር መሰረት ተማሪዎች በአግባቡ እንዲከታተሉት ማድረግ ላይ መምህራን ፣ የትምህርት ባለሙያዎች ፣ ሱፕርቫይዘሮችና የትምህርት አመራሮች ትልቅ ሀላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሀላፊው አክለዉም በመጀመሪያው ወሰነ ትምህርት ላይ 15 እና በሁለተኛው ወሰነ ትምህርት ላይ 15 በጥቅሉ 30 ትምህርቶች የሚሰራጩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
نمایش همه...
72👍 7👎 1🥰 1
ዛሬ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ያስገነባናቸውን 1 ሺህ 671 ያህል ቤቶች ለአገር ባለውለታዎች ፣ ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለከፋ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ እና በወንዝ ዳርቻዎች ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አስረክበናል። የቤት ግንባታዎቹ አብሮነትን እና ጉርብትናን የሚያጠናክሩ፣ የህፃናት መጫዎችን ፣ የስፓርት ማዘዉተሪዎችን የያዙ፣ በአጠቃላይ ንፁህና ሰው ልጅ የሚገባውን የከበረ የአኗኗር ዘይቤ የሚያዳብሩ ናቸው። ይህን በጎ ተግባር በእውቀታቸው፣ በሃብታቸው፣ በጉልበታቸው የደገፉ ልበ ቀና ባለሀብቶችን እና ያስተባበሩ አመራሮቻችንን ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ ። ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
نمایش همه...
70👍 13👎 3
نمایش همه...
10
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ሙሉጌታ አሰፋ በ2017 በጀት ዓመት በ53 እና በ57 ቀናት ብቻ ት/ቤቶችን በመገንባት የነበሩ የውጤት ክፍተቶችን በመሙላት አመርቂ ውጤትን ማስመዝገብ የተቻለ መሆኑን በማንሳት በጉባኤው መድረክ የተነሱ ጥያቄዎች በዕቅድ ውስጥ በማካተት የሚሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ዲሪባ በበኩላቸው በመድረኩ በበጀት ዓመቱ በትምህርት ዘርፉ በርካታ ለመማር ማስተማር ስራዎች ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል ፈተናዎች አመርቂ ውጤት ማምጣት የተቻለና በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተናም መሻሻሎች የታዩ መሆኑን ፣ አዋኪ ድርጊቶችን ማስወገድ መቻሉ ፣ በትምህርት ለትውልድ በ63 የትምህርት ተቋማትን በማንቀሳቀስ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ በርካታ ስራዎችን መስራት መቻሉን በማንሳት የትምህርት ስራ ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ባለመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድን ለመገንባት በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ በ32ኛው ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በመተግበር የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ ተናግረዋል። በመጨረሻም በ2017 በጀት ዓመት በበጀት ዓመቱ በቅንጅት ሲሰሩ ለነበሩ ተቋማትና የተሻለ ውጤትና አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተማሪዎች ፣ የጽ/ቤቱ ሰራተኞ ፣ ኮሚቴዎች ፣ ወረዳዎችና ት/ቤቶች የዕውቅናና የሽልማት መስጠት መርሃ-ግብር የተካሄደ ሲሆን በዚህም #በ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ6ኛ በ8ኛ ክፍል የተማሪ ውጤት, በKPI እንዲሁም በሪፎርም ስራዎች 1ኛ.ብሩህ ተስፋ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 2ኛ.አንዶዴ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 3ኛ.አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት #በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በKPI እንዲሁም በሪፎርም ስራዎች 1ኛ.ኢትዮ ጃፓን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 2ኛ.መጋላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 3ኛ. ቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት #በወረዳዎች በKPI እንዲሁም በሪፎርም ስራዎች 1ኛ.ወረዳ 06 ት/ጽ/ቤት 2ኛ.ወረዳ 03 ት/ጽ/ቤት 3ኛ.ወረዳ 13 ት/ጽ/ቤት እንዲሁም በልዩ ተሸላሚ በ6ኛ ፣ በ8ኛ እንዲሁም በ12 ኛ ክፍል ውጤት የአዲስ አበባ ማረሚያ ት/ቤት እንዲሁም ለክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፂሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና የዋንጫና የምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
نمایش همه...
77👍 5👏 4🕊 4👎 2😁 1
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "በእውቀትና በክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሃገር እናደርጋለን!" በሚል መሪ ቃል 32ኛው ክፍለ ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ አካሂዷል። (መስከረም 10/2018 ዓ.ም) በጉባኤው የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ፡የክፍለ ከተማው ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ሙሉጌታ አሰፋ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ዲሪባ ፣ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ አህመድ ጨምሮ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ት/ቤቶች የተውጣጡ ርዕሳነ መምህራን ፣ መምህራን ሱፐርቫይዘሮች ፣ ተማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን በመድረኩ የጽ/ቤት የ2017 በጀት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ፣ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ እንዲሁም የተማሪዎች ውጤት ትንተና ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በበጀት ዓመቱ ለትምህርቱ ዘርፍ ልዩ ትኩረትን በመስጠት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውንና በዚህም የተማሪዎች መጠነ ማለፍን በእጅጉ ማሻሻል የተቻለ መሆኑን በማንሳት ጉባኤው የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ቁርጠኝነትን የምናሳይበት ትልቅና ፍሬያማ መድረክ መሆኑንና በመጥቀስ እንደ ሀገር በትምህርት ዘርፉ ያሉ ስብራቶችን መጠገን የሚያስችል ዘመናዊያና ቀጣይነት ያለው የትምህርት ፓሊሲ መቀየሱንና ለፓሊሲው መሳካት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ፣ ብልሹ አሰራንን በማስወገድ የተማሪ ውጤት ላይ በመስራት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
نمایش همه...
22👍 3🥰 1
نمایش همه...
12👎 3
በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ የግል ትምህርት ቤት መምህራን በጨዋታ የማስተማር ዘዴ ላይ ስልጠና መስጠት ተጀመረ:: (መስከረም 10/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ትግበራ ዳይሬክቶሬት በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ የግል ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን በጨዋታ የማስተማር ስነ ዘዴ ላይ ስልጠና መስጠት ጀምሯል:: ስልጠናው ለ4 ቀናት በጨዋታ የማስተማር ስነ ዘዴ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰጥ መሆኑን የገለፁት የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ትግበራ ዳይሬክተር ወ /ሮ በላይነሽ የሻው ስልጠናው ቀደም ሲል ለመንግስት ቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን መሰጠቱን አስታውሰው አሁን ለግል ትምህርት ቤት መምህራን እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች በጨዋታ የማስተማር ስነ ዘዴን ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ለመስጠት እንዲችሉ ያደርጋል ብለዋል:: አክለውም ቢሮው የትምህርት ጥራትን ለማምጣት የተለያዩ ዘዴዎች ቀይሶ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሯ ስልጠናው ብቁ የሆኑ በጨዋታ የማስተማር ስነዘዴን ተግባራዊ ማድረግ የሚችሉ መምህራን ለማፍራት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች በተለያየ ጊዜ እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል:: አሰልጣኞችም ስልጠናው የታለመለትን ግብ መምታት እንዲችል የቀረቡ የስልጠና ዘዴና ቁሳቁሶችን በመጠቀም ለሰልጣኞች በቂ እውቀት እንዲያስጨብጡና ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን በጨዋታ የማስተማር ስነዘዴ በተግባር ላይ በማዋል ብቁ ትውልድ ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፉ አሳስበዋል:: በስልጠናው በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች ቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን እየተሳተፉ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያሳያል ::
نمایش همه...
35
በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ግርማ ደቻሳ ከተማሪ ምዘገባ ጋር በተገናኘ ከየክፍለ ከተማው የተሰበሰበ መረጃ ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዷል። Haalli galmee barattootaa sirna barnootaa Afaan Oromoo sadarkaa irra jiru gamaggamame. (Fulbaana 10/208ALI) Gamaggama kana irratti Abbootii Adeemsaa Garee Raawwii Sirna Barnnootaa Afaan Oromoo Kutaa Magaalaa, Qindeessitoota sirna barnootaafi Qindeessitootni Supperviizhinii Afaan Oromoo Kutaa Magaalaa kan hirmaatan yoo ta'u, gabaasni galmee barattootaa tokkoon tokkoon Kuta Magaalaa irraa walitti qabame dhiyaatee mariin taasifameera. Itti aanaan itti gaafatamaa Biiroo Barnootaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee Obbo Diinaa'ol Caalaa haasaa baniinsa sagantichaa irratti dabarsaniin, erga Bulchiinsa magaalichaati Sirni Barnootaa Afaan Oromoo  hojiirra oolee kaasee barattoonni hedduun carraa afaan dhalootaa isaaniitiin barachuu akka argatan ibsaniiru. Bara barnootaa 2018ALItti barattoonni Sirna Barnootaa  Afaan Oromoo keessatti baratan sadarkaa eegamuun gara mana barumsaa akka dhufan, Hoggantootaafi ogeessotni kutaa Magaalaa  deeggarsaafi hordoffii barbaachisaa ta'e akka taasisan hubachiisaniiru. Dabalataanis, Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee keessatti bara 2018ALItti qormaata xumura kutaa 6ffaatiif barattoonni Afaan Oromoofi Afaan Amaaraa akka afaan lammaffaatti barataniif raabsa kitaaba barnootaa irraa eegalee hojiiwwan deeggarsaafi hordoffii adda addaa hojjetamuu akka qaban ibsaniiru. Bakka bu'aa Daayirektoreetii Qophiifi Raawwii Sirna Barnootaa Afaan Oromoo Biiroo Barnootaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee, Obbo Girmaa Dachaasaa galmee barattootaa waliin wal-qabatee ragaalee Kutaa Magaalaa irraa walitti qabaman irratti gabaasa dhiyeessuun mariin taasifameera. መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
نمایش همه...
35🥰 7🤩 2💩 1
የ2018 ዓ.ም የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ተማሪዎች ምዝገባ ያለበት ደረጃ ተገመገመ። (መስከረም 10/2018 ዓ.ም) በግምገማው የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎች እና የዘርፉ አስተባባሪዎችን ጨምሮ የክፍለ ከተማ የአፋን ኦሮሞ ሱፐርቪዥን አስተባባሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በመርሀግብሩ ከየክፍለ ከተማው የተሰበሰበ የተማሪ ቅበላ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት መተግበር ከጀመረ አንስቶ በርካታ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመማር እድል ማግኘታቸውን ገልጸው በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት በአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት የሚማሩ ተማሪዎች በሚጠበቀው ደረጃ ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመጡ በክፍለ ከተማ የሚገኙ ዘርፉን የሚከታተሉ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ የሚጠበቅባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል። ምክትል ቢሮ ኃላፊው አያይዘውም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 ዓ.ም አፋን ኦሮሞን እና አማርኛን እንደ 2ኛ ቋንቋ ለሚማሩ ተማሪዎች የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በትምህርት አይነቶቹ የሚሰጥ በመሆኑ ተማሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ የመማሪያ መጽሐፍ በአግባቡ ከማድረስ ጀምሮ የተለያዩ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል።
نمایش همه...
24
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ " በእመርታና ማንሰራራት የታጀበ ሕዝባዊ በዓላትን በጋራ እናክብር " በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የመስቀል እና ኢሬቻ በአላት አከባበር ላይ ለማወያየት የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበዋል :: ሰነዱን ባቀረቡበት ወቅት በአላቱ የቱሪዝም ወር በሆነው በዚህ ጊዜ የሚከበሩ እንደመሆናቸዉ የባህል እሴቶቻችንን በተገቢ ሁኔታ ለማሳየት ልንጠቀምባቸው ይገባል ብለዋል :: የውይይቱ ተሳታፊዎችም ቢሮው የተለያዩ ሀገራዊ በዓላት ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበሩ የሚፈጥረውን የግንዛቤ መድረክ አድንቀው በአላቱ በሰላም እንዲከበሩ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል :: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
نمایش همه...
59👍 8🥰 3
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመስቀል እና እሬቻ በአላትን አስመልክቶ ውይይት አካሄደ:: (መስከረም 9/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ 2018 ዓ.ም የሚከበሩ የመስቀል እና እሬቻ በአላት አከባበርን አስመልክቶ አጠቃላይ የቢሮው ሰራተኞች በተገኙበት ውይይት አካሂዷል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ የዘንድሮ መስቀል እና ኢሬቻ በዓላት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተመርቆ ወደተግባር በገባበት እንዲሁም ከተማችን አዲስ አበባ በኮሪደር ልማት በደመቀችበት ጊዜ የሚከበር መሆኑ ከሌላው ጊዜ ለየት እንደሚያደርገው ገልፀው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የዓለም ቅርስ የሆኑት እነዚህ በዓላት ሀይማኖታዊ እና ታሪካዊ እሴታቸውን በጠበቀ መልኩ ደምቀው እንዲከበሩ በጋራ መስራት አለብን ብለዋል:: አቶ ሲሳይ መስቀል እና ኢሬቻ የዓለም ማህበረሰብ የሚታደምባቸው ለከተማችን ኢኮኖሚ መነቃቃት ትልቅ አስተዋፅኦ ያላቸው በአላት መሆናቸውን በመረዳት ሰራተኞች በቢሮ እና በሚኖሩበት አካባቢ በአላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ ብሎም የኢትዮጵያን እንግዳ ተቀባይነትና አብሮ የመኖር ባህላችንን የምናሳይባቸው በአላት እንዲሆኑ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል::
نمایش همه...
30
በጉባኤው ማጠቃለያ ማህበሩ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣ ለትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣ ማህበሩን ላለፉት አምስት አመታት በፕሬዘዳንትነት ለመሩት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ እና በየደረጃው ለሚገኙ የማህበሩ አመራሮች፣ በአመቱ ውጤታማ አፈጻጸም ላስመዘገበ የልደታ ክፍለ ከተማ ህዳሴ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ሾማ አብዲሳ እንዲሁም ከማህበሩ ጋር በአጋርነት በመስራት ውጤታማ ለሆኑ ተቋማት ዕውቅና ከመሰጠቱ ባሻገር ማህበሩን ለቀጣይ አራት አመታት የሚመሩ ስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ ተካሂዷል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
نمایش همه...
13
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር "በሁለንተናዊው የተጠናከረ ማህበር ለሁለንተናዊ የመምህራን እና ከተማችን እድገት" በሚል መሪ ቃል ለሁለት ያካሄደውን 23ኛ መደበኛ ጉባኤ አጠናቀቀ። (መስከረም 9/2018 ዓ.ም) በጉባኤው የማህበሩ የአራት አመት አፈጻጸምን ጨምሮ የውስጥ እና የውጭ ኦዲት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ከመካሄዱ ባሻገር የጉባኤው ተሳታፊዎች ከማህበሩ ጋር በጋራ ከሚሰሩ የተለያዩ ተቋማት ለተገኙ አመራሮች የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበው ምላሽ ተሰቷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በጉባኤው ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ከተማ አስተዳደሩ የመምህራን ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ቅድሚያ በመስጠት የተለያዩ ተግባራት ከማከናወኑ ባሻገር ማህበሩ ሙያዊ ነጻነቱ ተጠብቆ ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸው ማህበሩ በቀጣይ የአባላቱን መብት እና ጥያቄ እንዲመለስ ከመስራት ባሻገር የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል ሙያዊ ኃላፊነቱን መወጣት እንደሚገባው አስገንዝበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ በበኩላቸው ጉባኤው ስኬታማ እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበው ማህበሩ በቀጣይ በጉባኤው የተቀመጡ አቅጣጫዎችን መሰረት በማድረግ የአባላቱ ጥያቄ እንዲመለስ እና የመማር ማስተማር ስራው ውጤታማ እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ የሚሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
نمایش همه...
21
የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ /ቤት ትምህርት ቤት መሻሻልና ግብዓት ቡድን ስልጠና ሰጠ:: (መስከረም 9/2018 ዓ.ም) የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየውን የትምህርት ቤት መሻሻል ሥራዎች በትምህርት ቤት ማሻሻል ፖርታል ውስጥ ለሚያስገቡ ባለሞያዎች ስልጠና በመስጠት ላይ መሆኑን አሳውቋል:: የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን ታደሰ በስልጠናው መክፈቻ ተገኝተው ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የትምህርት ቤት ደረጃን ለማሻሻልና ምቹ የመማሪያ አካባቢን ለመፍጠር በተሰራ ሰፊ ሥራ ለመማር ማስተማር ምቹ የሆኑ ትምህርት ቤቶች ማግኘት መቻሉን ገልፀው:: ስልጠናውን እየወሰዱ ያሉ ባለሙያዎች መረጃውን ለሚመለከተው አካል በአግባቡ ተደራሽ በማድረግ የትምህርት ቤቶችን ችግር በማየት የትምህርት ስራን ማገዝ ለሚፈልጉ አካላት በቂ መረጃ በማድረስ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥሩ አሳስበዋል:: የክፍለ ከተማው አስተባባሪ ወ/ሮ መአዛ ተስፋ ስልጠናው በዋናነት በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የተሰሩ ሥራዎችን በትምህርት ቤት መሻሻል ፖርታል ውስጥ እንዲቀመጥ በማድረግ ትምህርት ቤቶቹ ያሉበትን ደረጃና ገፅታ ማወቅ ለሚፈልግ ማንኛውም አካል ለማሳወቅ እንዲሁም በትምህርት ለትውልድ የተሳተፉ የቀድሞ ተማሪዎች :ወላጆች :መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በትምህርት ቤት መሻሻል ሥራ ያደረጉት ተሳትፎ ያስገኘውን ውጤት ማየት እንዲችሉ ያደርጋል ብለዋል :: አክለውም በቀጣይም የጎደሉ ነገሮች ላይ አስተዋፅኦ ለማድረግ በቂ መረጃ እንዲያገኙ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል :: በስልጠናው በክፍለ ከተማው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ዋና ርእሰ መምህራን እና የአይሲቲ ባለሙያዎች እየተሳተፉ እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ::
نمایش همه...
43👍 9