68 961
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-137 روز
-96730 روز
آرشیو پست ها
Repost from TgId: 1173613158
የኢትዮጵያ ታሪክ በአንድ አንቀፅ ቢገለፅ 'ንጉስ ተነሳ፥ ከውስጥም ከውጪም ተዋጋ፥ አሰረ ገደለ ዘረፈ። ሌላም ንጉስ መጣ፥ ከውጪም ከውስጥም ተዋጋ፥ አሰረ ገደለ ዘረፈ።... በዚህም የተነሳ ጉስቁልና ፣ ድንቁርና እና ኋላቀርነት በምድሪቱ ነገሰ' የሚል ነው።
ታሪክ እኛ አገር የፖለቲካ አሽከር ነው። ታሪክ ነጋሪዎቻችን ከፖለቲካ አሰላለፋቸው አንፃር ያለውን ትርፍ ስለሚያሳሉ እውነት ላይ ለመሸቀጥ አያመነቱም፡፡ ሲከፋም የፖለቲካ ሰዎች የታሪክ ነጋሪ ሆነው ይከሰታሉ። ፖለቲካ ከታሪክ መጋባቱ ሳያንስ የዘቀጠ ፖለቲካ ሲታከልበት ታሪክ መጠፋፊያ ይሆናል። እኛም ታሪካችን ጠልፎ የሚጥለን ገመድ እንጂ መማሪያችን አይደለም።
ቢሆንልን የታሪክ አላማ ከትላንት መማር፥ ጥንካሬን ማስቀጠል፥ ደካማ ጎንን ማረም ና እርስ በእርስ መተሳሰሪያ መሆን ነበረበት። ለዚህ ግን አልታደለንም!
ታሪክ አለን፥ ነገር ግን ታሪክን ይፅፉ ዘንድ ሞያው የሚፈቅድላቸው ዝም ብለዋል። ታሪክ ተራኪዎቻችን ደግሞ አንድም መሰረታዊ የታሪክ ነገራ አላባዊያንን ስተዋል። አሊያም ታሪክን የፖለቲካ ገረድ አድርገዋል። ስለዚህ እንደ ህዝብ ከታሪክ መማርና አገራዊ መተሳሰሪያ ገመድ ለመፍጠር አልታደልንም!
ከ #ነገን_ፍለጋ መፅሐፍ የተወሰደ
@Tfanos
👍 41❤ 2
አእምሮአችን ድንቅ ተአምራዊ ስጦታ ነወ።
የሠው ልጅ አእምሮ በአማካይ 10 ቢሊየን የአእምሮ ህዋሶችን (ኒውሮን ሴሎችን) በውስጡ ይይዛል፡፡ እነዚህ ሴሎች ህዋሶች ደግሞ እርስ በእርስ በ100 ትሪሊየን ጥልፍልፍ መስመሮች ይገናኛሉ። አእምሮዋችን ይህ ነው የማይባል ምስጥራዊ ስሪት አለው፡፡ በዛኑ ልክ ስራውም እጅግ የተወሳሰበ ነው:: በመላ ሰውነታችን በተዘረጋው የመረጃ መረብ በመታገዝ ከአካባቢያችን ጋር በሰላም ያለምንም ችግር እንድንኖር አስችሎናል። በእነዚህ የግንኙነት መስመሮቸ ውስጥ ወደ አእምሮ እና ከአእምሮ የሚተላለፉ መልእክቶች እጅግ በጣም ፈጣን በሆነ መልኩ በሠአት 320 ኪሜ ይጓዛሉ፡፡ በአእምሮና በቀሪው ሰውነታችን መካከል ያሉት ነርቮች መልእክትን ለመለዋወጥ ልክ እንደዋና ጎዳና በመሆን ያገለግላሉ።
በአጭሩ ሰውነታችን በእያንዳንዷ ደቂቃና ቅፅበት እጅግ ከፍተኛ የትራፊክ እንቅስቃሴን ያስተናግዳል ማለት ነው።በአንዲት ነጠላ ሰከንድ ውስጥ ብቻ በሺ የሚቆጠሩ መልእክቶች በተናጠል በአእምሮና በቀሪው የአካል ክፍል መካከል ይመላለሳሉ።በአንዲት ደቂቃ ውስጥ ብቻ ከመቶ ሺህ እስከ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ ኬሚካላዊ ለውጦች በአእምሮአችን ውስጥ ይካሄዳሉ። ሌላው ቀርቶ ይህንን ፅሁፍ በሚያነቡበት ወቅት እንኳን በእያንዳንዷ ሰኮንድ አንድ ሺኛ ጊዜ ውስጥ በሰውነታዎ ጡንቻዎችና በአእምሮዎ መካከል በመቶ የሚቆጠሩ የመልእክት ልውውጦች ተደርገዋል።
እነኚህ መልእክቶች ሲያነቡ መረጃ ከማቀበል ባለፈ ወንበርዎ ላይ ደገፍ ማለትዎን ያነበቡትን ነገር መረዳትዎን፡ የልብዎን ምት፣ እስትንፋስዎን፣ የአይንዎን መርገብገብ ፣የፀጉርዎን ማደግ፡ የአፍንጫዎን ማሽተትና የጆሮዎን መስማት የሚመለከቱ ሊሆኑ ይችላሉ። ከእነዚህ ድርጊቶች ውስጥ አንዱን እንኳን በቅጡ ለመረዳት ቢሞክሩ እጅግ ብዙ ገፅ የኬሚካል ቀመሮችን መፃፍ ይኖርብዎታል፡፡ በዚህ ቀመር ውስጥ ደግሞ አንዷ እንኳን ብትሣሣት የሰውነትን ሚዛን ልታሣጣ ትችላለች። ይህ የሚዛን መዛባት ፀጉርዎን ሲያበጥሩ በድንገት እጆዎችን እና አይንዎን በማበጠሪያው እንዲወጉ ሊያደርግዎ ወይም ሲራመዱ ተንገዳግደው እንዲወድቁ ሊያደርግዎ ይችላል::
የአእምሮችንን የህዋሳት ብዛትና የርስበርስ መያያዣ ስርዓተ በምሳሌ ብንመለከት።የኢትዮጵያ ሁለት እጥፍ የሚሆን ግዙፍ ቦታ እንዳለ እናስብ፡፡ይህ ቦታ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በዛፍ የተሞላ እንደሆነና እያንዳንዱ ዛፍ ደግሞ 10,000 ቅጠሎች እንዳሉት እንቁጠር፡፡ እንግዲህ የእነዚህ ቅጠሎች ድምር የአእምሮ ሴሎች ከሚገናኙባቸው መስመሮች ጋር እኩል ነው ማለት ነው፡፡
ታዲያ የዚህ ውስብስብ ዲዛይንና ምህንድስና ባለቤት ፈጣሪን ልናመሰግነው አይገባብ ትላላችሁ?
አምላክ የሠውን ልጅ እጅግ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ ከመፍጠሩ የተነሣ እጅግ ውስብስብ ስራዎችን እንኳን ያለ እንከን መስራት እንዲችል አድርጎታል። ታዲያ ይህን ታላቅ ስጦታ በአግባቡ አለመጠቀም ሀጥያት አይደለም ትላላችሁ?
✍️ባህሩን ያህያ
የስብዕና ልህቀት
Join: @Human_Intelligence
Join: @Human_Intelligence
🙏 20👍 13❤ 8🥰 1
በተሰማሩበት ሙያ ስኬትዎን የሚወስኑ 6 የሰብዕና መገለጫዎች
ጉጉ፣ ጠንቃቃ እና ተፎካካሪ ነዎት? ከሁኔታዎች ጋር ቶሎ የመላመድ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መቋቋም እና ግራ መጋባትን አምኖ መቀበልን የመሰሉ ምስጢራዊ ችሎታ አለዎት?
- እንግዲያውስ እንኳን ደስ አለዎ! በሥነ-ልቦ ባለሙያዎች በተደረገ ጥናት መሰረት እነዚህ ስድስቱ መገለጫዎች በህይወትዎ እና በሚሰሩት ሥራ ስኬታማ እንዲሆኑ ያደርጋሉ።
እውነታው ግን አንዳንድ ልዩነቶች አሉት፡፡ እነዚህ ባህሪያት ሲበዙ ደግሞ ውጤታማነትዎን ሊቀንሱ ይችላሉ። ስለዚህ የስኬት ሚስጥሩ በሁለቱ ፅንፎች መካከል ሚዛንን ጠብቆ መቆየት መቻል እና ጠንካራ እና ደካማ ጎንን ለይቶ ማወቅ ነው።
ይህ አቀራረብ በሥራ ባህሪያችን ላይ ጫና የሚያሳድሩ የተወሳሰቡ የሥነ-ልቦና መገለጫዎችን ለመረዳት ይረዳል። ከዚህ በፊት የሥራ አካባቢ ባህሪያትን ለማወቅ የተደረገው ጥረት አከራካሪ ውጤቶች አስገኝቷል።
በሥነ-ልቦናው ዘርፍ የተገኙ ስኬቶች በሥራ አካባቢ ውጤታማ ያደርጋሉ የሚለውን ግኝት ከግምት ውስጥ በማስገባት የለንደን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎቹ ኢየን መክሪ እና ኤድሪየን ፈርሃም በተሰማሩበት ሙያ ስኬታማ የሚያደርጉ ስድስት የስብዕና መገለጫዎችን አስቀምጠዋል።
መክሪ እንደሚለው እያንዳንዱ መገለጫዎች የራሳቸው የሆነ ውስንነት እና ጠንካራ ጎን አላቸው።ስለዚህ የእያንዳንዱ መገለጫ ጥቅም የሚወሰነው ግለሰቦች በሚሰሩት ሥራ ላይ ስለሆነ መለኪያው ከእያንዳንዱ ሁኔታ ጋር ይቀያየራል።ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት እነዚህ ስድስት የስብዕና መገለጫዎች እንዴት ወደ ስኬት እንደሚወስዱ እንመልከት
1. ጠንቃቃነት
ጠንቃቃ ሰዎች ሁሌም እቅዳቸውን በትክክል ይተገብራሉ።የእያንዳንዱ ውሳኔያቸው የወደፊት ውጤት ተጽዕኖን ያውቃሉ። ስሜታቸውንም መቆጣጠር ይችላሉ። ከአእምሮ ብቃት ምዘና ፈተና በኋላ ይህ የጠንቃቃነት ባህሪ በህይወትዎ ስኬታማ ለመሆን ወሳኝ ነው።በሥራ አካባቢ ለትንሽ ነገሮች ትኩረት መስጠት ስልታዊ በሆነ መልኩ እያንዳንዱን ሥራ ለማቀድ ይጠቅማል።
2. ከአዲስ ነገሮች ጋር ቶሎ መላመድ
ሁሉም ሰው የሚያስጨንቀው ነገር ያጋጥመዋል፤ ዋናው ጥያቄ ግን እንዴት ያልፈዋል የሚለው ነው። ይህ ማለት ሥራዎት እና ሌላ ህይወትዎ ላይ ጫና እንዳሳያሳድር ለመላመድ መሞከር ማለት ነው።ይህ ባህሪ የሌላቸው ሰዎች የሥራ አካባቢ አፈጻጸማቸው ደካማ ነው። ነገር ግን ተገቢውን የሥነ-ልቦና እርምጃ ከወሰዱ ውጤታማ መሆን ችላሉ።
ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ውጤታማ ለመሆን ሲባል አስጨናቂ ጉዳዮች ላይ በደንብ ትኩረትን መስጠት ከተቻለ፤ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ያለ ሰው ያሰበውን ነገር ማሳካት ይችላል።
3. ግራ መጋባትን አምኖ መቀበል
የጥያቄዎን መልስ የሚያውቁበት አይነት ሥራ ነው የሚወዱት ወይስ ግራ የሚያጋባ እና አስጨናቂ የሥራ ቦታ?
የማያውቁትን ነገር የማይፈሩ እና ግራ መጋባትን አምነው የሚቀበሉ ሰዎች የተሻለ ውሳኔ ለመወሰን ይችላሉ። ብዙ ነገሮችንም ከግምት ውስጥ ያስገባሉ።
ይህ ባህሪ ትንሽ አምባገነናዊ ወደ ሆነ አስተሳሰብ ይመራል ይላል መክሪ። እንደዚህ አይነት ሰዎች ትንሽ የምትባለው ነገር ትርጉም እስከምትሰጣቸው ድረስ ስለሚጨነቁ የራሳቸውን ውሳኔየመጨረሻ አድርገው ሊወስዱ ይችላሉ። ግራ መጋባትን አምኖ መቀበል የሚችል ሰው ለማንኛውም አይነት ለውጥ ሁሌም ዝግጁ ነው፡፡ ግራ መጋባትን አምኖ አለመቀበል ግን ሁሌም መጥፎ ነው ማለት አይደለም።
4. ጉጉ መሆን
ከሌሎች ባህሪያት ጋር ሲነጻጸር በሥነ-ልቦና አጥኚዎች ዘንድ ጉጉት ብዙ ትኩረት አልተሰጠውም፡፡ነገር ግን በቅርብ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የማናውቀውን ነገር ለማወቅ ያለን ጉጉት ሁሌም አዲስ ነገር ለመፍጠር ይረዳናል። ይህ ማለት ለአዳዲስ ነገሮች ክፍት የሆነ ጭንቅላት አለን ማለት ሲሆን፤ በምንሰራው ሥራ ደስተኞች እንድንሆን ይረዳናል።አንዳንዴ ግን የበዛ ጉጉት ወዳልተፈለገ የጊዜ ብክነት ሊወስደን ይችላል።
5. አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መቋቋም
ደስ የማይል ነገር ሲያጋጥምዎት ለጊዜው ስለቀለልዎት ብቻ ዝም ብለው ያልፋሉ ወይስ ምቾት ባይሰጦትም ጉዳዩን ተጋፍጠው ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ይሞክራሉ? ከአስቸጋሪ ሁኔታዎች ጋር እራስን ማላመድ መቻል ወደፊት ወደ _ አመራር ቦታ እንድንመጣ እና ለብዙ ነገሮች ውሳኔ መስጠት እንድንችል ይረዳናል።
6. ተፎካካሪ መሆን
ለስኬት ሲባል የሚደረግ ትንቅንቅ እና ጤናማ ያልሆነ ፉክክር ወይም ቅናት ትልቅ ልዩነት አላቸው። ፉክክር ሁሌም ለበለጠ ሥራ የሚያነሳሳ ሲሆን፤ ተጨማሪ ጥረት እንድናሳይና እቅዳችንን እንድናሳካ ሊረዳን ይችላል። ሲበዛ ግን የቡድን ሥራዎችን ያስተጓጉላል። እነዚህ ስድስቱ ባህሪያት በአንድነት በሥራ ገበታችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አላቸው። በተለይ ደግሞ ወደ አመራር ቦታ መምጣት ለሚፈልጉ ሰዎች።
( ምንም እንኳን ጥናቱ ገና ባያልቅም ከላይ የተዘረዘሩት የሰዎች ባህሪያት በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የሥራችንን ፍሬ እና ውጤታማነታችንን ለመለካት ይረዱናል።)
Source - BBC
የስብዕና ልህቀት
Join: @Human_Intelligence
Join: @Human_Intelligence
👍 43❤ 7😢 1
በረከት ወይስ መርገምት
አስተማሪ ወግ
✍️ማክስ ሉካዶ እንደፃፈው
ተራኪ ፦ አንዱአለም
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
4_5774129890731230713.m4a1.73 MB
👍 18
ዛሬም የሚያስፈልጉን ነፃነቶች
(ቁልፍ እና ድልድይ)
ተራኪ-አንዱአለም ተሰፋዬ
@Zephilosophy
@Zephilosophy
_ዛሬም_የሚያስፈልጉን_ነፃነቶች!_ቁልፍ_እና_ድልድይ!_ትረካ_በአንዱዓለም_ተስፋ�.mp333.28 MB
👍 17
"ከፖለቲካ በሸሸህ ቁጥር በእውቀት እና በስነምግባር በምትበልጣቸው ሰዎች በመመራት ትቀጣለህ"
🔥 24👍 5❤ 4🙏 3
Repost from TgId: 1163708603
#ሰውና_ተፈጥሮው
አዲስ መጽሐፍ
👉5ት ድንቅ ትምህርቶችን እነሆ ለቅምሻ፦
The Laws of Human Nature የተሰኘው የሮበርት ግሪን ድንቅ መጽሐፍ #ሰውና_ተፈጥሮው በሚል ርእስ በቅርብ ቀን በገበያ ላይ ዋለ ።
ታዋቂውን 48 Laws of POWER የተሰኘውን መጽሐፍ 48ቱ የኃያልነት ሕጎችን በሚል በተረጎመችው #ሃኒም_ኤልያስ የተተረጎመ ሲሆን፣ ልክ እንደ #የኃያልነት_ሕጎች_መጽሐፍ ጥፍጥ ብሎ ከተዘጋጀው #ሰውና_ተፈጥሮው አዲስ መጽሐፍ ላይ ለቅምሻ 5ቱን ድንቅ ትምህርቶች እነሆ ብለናል፦
#አንድ
#መርዛማ_ሰዎችን_አስወግድ
ከመርዛማ ሰዎች ጋር አብዝተን የምንገናኝ ከሆነ በአካልም ሆነ በአእምሮ ሊጎዱን ይችላሉ ይለናል። እነዚህ ከልክ ያለፈ ትችት የሚሰጡ፣ ምቀኛ፣ ትዕቢተኛ፣ ጠበኛ ወይም ራስ ወዳድ የሆኑ ሰዎችን ያጠቃልላል። እነዚህን ባህሪያት በራሳችን እና በሌሎች እንዴት መለየት እንዳለብን እና ራሳችንን ከእነሱ እንዴት ማራቅ እንዳለብን ያስተምረናል።
#ሁለት
#ስሜታዊነትህን_ተቆጣጠር
ስሜታችን ምን ያህል በጥልቅ እንደሚገዛን እና ውሳኔዎቻችንን እና ድርጊቶቻችንን እንዴት እንደሚነካ አናውቅም። ምክንያታዊነትን በማዳበር እነዚህን ስሜታዊ ተፅእኖዎች እንዴት መቋቋም እንደምንችል ማወቅ የግድ ይለናል። እራሳችንን ጠንቅቆ ማወቅ፣ ስሜቶቻችንን ከሥሮቻቸው መፈተሽ፣ የምላሽ ጊዜያችንን ማዘግየት፣ የአስተሳሰብ እና የስሜታዊነት ሚዛንን ማግኘትን የመሳሰሉ ስልቶችንም ሮበርት ግሪን በመጽሐፉ ይጠቁመናል።
#ሶስት
#ከጓደኞችህ_ጋር_አብረህ_ወደ_ገደል_አትግባ
ከሌሎች ጋር ለመስማማትና ብቻችንን ላለመሆን ብለን የሌሎችን አስተያየት ወይም ግምት ከልክ በላይ እንዳንቀበል ያስጠነቅቀናል። ይህ ግለሰባዊ አቅማችንን እንድናጣ እና ለቡድን አስተሳሰብ እንድንጋለጥ ሊያደርገን ይችላል።
#አራት
#ሳታቋርጥ_የተሻለ_ነገርን_ፈልግ
ባለን ነገር እንዳንረካ እና ሌላ ቦታ ያለን የበለጠ ደስታን የሚሰጥ ነገር እንድንፈልግ ይገፋናል። ከመጠን በላይ የሆነ ምሬትም ወደ ብስጭት፣ ጭንቀት፣ መሰላቸት ወይም ሱስ እንደሚመራን፣ ከዚህ ይልቅም እስካሁን ያገኘነውን በምስጋና ተቀብለን፣ ራሳችንን በማሻሻል ላይ ማተኮር እንዳለብን ያሳየናል።
#አምስት
#በሰዎች_ጭምብል_ስር_ምን_እንዳለ_ተመልከት
ሮበርት ግሪን፣ ሰዎች ብዙውን ጊዜ እውነተኛ ሀሳባቸውን እና ስሜታቸውን ከራስ መተማመናቸውና ከአካላዊ ውበታቸው ስር እንዴት እንደሚደብቁ ያሳየናል። በሌሎች ቃላት እና ድርጊቶች ውስጥ ያሉ የማታለል ምልክቶችን እንዴት መለየት እንደሚቻል ያብራራልናል። እንዲሁም በሰዎች ፊት ሀቀኝነታችንን እና ታማኝነታችንን ሳናጣ እንዴት መጫወት እንዳለብንም ያስረዳናል።
#ሰውና_ተፈጥሮው መጽሐፍ በቅርብ ቀን በገበያ ላይ ይውላል።
👉ሌሎች የሮበርት ግሪን ምርጥ የእንግሊዝኛ መጽሐፍት እጅግ በጥራት ታትመው በገበያ ላይ፦
#The_Laws_of_Human_Nature
@Zephilosophy
@Zephilosophy
👍 17❤ 4🙏 2
ስለ ፍልስፍና
@Zephilosophy
@Zephilosophy
በአገራችን በፍልስፍና ምንነትና ፋይዳ ላይ እስከ ዛሬ ሲንፀባረቅ የቆየው አመለካከት አሉታዊነቱ የሚያመዝን
መሆኑ ከዚህ የእውቀት ዘርፍ ተገቢውን ጥቅም እንዳናገኝ አድርጎናል። እናም ብዙዎች ስለፍልስፍና ያላቸውን አሳቤ ስንመስከት-ከፈጣሪ ጋር መጋጨት፣ ከእውነት ከመራቅ እንዲሁም ከእብደት ጋር የተያያዘ ሆኖ አናገኘዋለን፡፡ ይህ የብዙዎች እምነት ይሁን እንጂ፣ ፍልስፍና ግን በተቃራኒው እውነትን ከመፈለግ- አልያም ጭፍን አመለካከቶችን በጥበብ ከመመርመር ባሻገር ስለፍትህ፣ ስለፖለቲካ፣ ስለ ስነ ውበት፣ ስለ መልካም ስነ-ምግባር አንዲሁም ስለመሰል የትምህርትና የአስተሳሰብ ዘርፎች እንደ የአቅጣጫው የሚያጠናና የሚመረምር አራሱን የቻለ ትልቅ የእውቀት ዘርፍ ነው።
ፍልስፍና ከራሱ አልፎ ለሌሎች ታላላቅ የእውቀት ዘርፎች መሰረት የሆነና የሰው ልጅ ዛሬ እዚህ ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ጉልህ አስተዋፅዖ ያደረገ ነው። ለሁሉም ሩጫ ፍልስፍና የጀርባ አጥንቱ ነው፡፡ ምሰሶ ከሌለው ጎጆ እንደማይቆም ሁሉ፤ ፍልስፍና ከሌለ እውቀትና እውነት አንደጉም ይተናሉ። ምናልባትም ሀገራችን በሌሎች የትምህርት ዘርፎች ያሳየችውን ትጋት ለፍልስፍናም አቋድሳው ቢሆን ኖሮ ፣ ሌሎች ቤት የሚያበራው ሻማ ፣ ጨለማ ውስጥ ሆነን ባላደነቅን ነበር ፣ፍልስፍና ዳቦ አያበላም እያልንም በፈላስፋው የተጋገረውን ዳቦ ተሻምተን ለመቋደስ ባልተገደድንም ነበር።
በአጠቃላይ ፍልስፍና ከጨለማ_ወደ ብርሀን፣ ካለማወቅ ወደማወቅ፣
ከባርነት ወደ ነፃነት፣ ከስህተት ወደ እውነት የሚያሻግር ድልድይ ነው።
ድንቅ የፍልስፍና ቻናል ይቀላቀሉ
Join Now
👇👇👇👇
@Zephilosophy
@Zephilosophy
👍 37❤ 4
“ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ”
ታሪኩ ከተከሰተ ትንሽ ሰንበት ብሏል፡፡ ይህ ታሪክ የሆነው በስፔን ሃገር ነው፡፡ አባትና ልጅ ችላ ቢሉት ቀለል ሊል የሚችልን አንድን የግጭት ሁኔታ በማካበዳቸው ምክንያት ተጣልተዋል፡፡ በጉዳዩ ተጎድቻለሁ ባይ አባት በልጁ ላይ ስለጨከነበትና ይቅር አልለው በማለቱ ምክንያት ልጅ ቤቱን ጥሎ በመሄድ ይጠፋል፡፡ በጊዜው ከነበረበት ንዴት የተነሳ አባት ምንም አልመሰለውም፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ግን ጉዳዩ እያሳሰበው ስለመጣ የልጁን ደህንነት ለማወቅ መፈለግ ጀመረ፡፡ በተለያዩ መንገዶች ሲያጣራ ከቆየ በኋላ ከብዙ ወራት ሙከራ በኋላ በዚያው ከተማ ውስጥ እንደሚኖር አወቀ፤ በትክክል የት እንዳለ ግን ማወቅ አልቻለም፡፡ ልጁ በሕይወት መኖሩንና እጅግም ያልራቀ መሆኑን ሲያውቅ የተከሰተውን ችግር ሁሉ በመርሳት ይቅርታን ሊሰጠው ፈለገ፡፡ ይህንንም ለማድረግ ልጁን ማግኘት ስላልቻለ አንድን የመጨረሻ ሙከራ ለማድረግ ቆረጠ፡፡
በማድሪድ (ስፔን) ከተማ በሚታተመው ብዙ በመነበብ የታወቀ ጋዜጣ ላይ እንዲህ የሚልን መልእክት አወጣ፣ “ልጄ ፓኮ፣ ያለፈውን ስህተተህን ሁሉ ይቅር ስላልኩህ እባክህን ቅዳሜ ከቀኑ በስድስት ሰዓት በዚህ ጋዜጣ ማተሚያ ዋና ቢሮ በር ላይ ላግኝህ፡፡ የሚወድህ አባትህ፡፡” በተባለው ቀን ይህ አባት ልጁን ለማግኘት በተቀጣጠሩበት ቦታ ሲሄድ አንድን አስገራሚ ነገር ተመለከተ፡፡ ስማቸው ፓኮ የሆነና ከአባታቸው ይቅርታን የሚፈልጉ 800 ወጣቶች መልእክቱ የተላከው ከእነሱ አባት ስለመሰላቸው በዚያ ቢሮ በር ላይ ተሰብስበዋል፡፡ በተከሰተው ነገር እጅግ የተገረመው አባት ከዚያ ሁሉ ወጣት መካከል ልጁን ፈልጎ አግኘቶ ከሳመው በኋላ፣ “ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ” አለውና ይዞት ወደቤቱ ወሰደው፡፡
ማሕበራዊ ኑሮ እስካለ ድረስ አለመግባባት የተሰኘው የሕይወት ሂደት የማይቀር ነው፡፡ ይህንን ምስጢር የዘነጉ ሰዎች ትኩረታቸውን ሁሉ በዚያ አለመግባባት ላይ ሲያደርጉ ይገኛሉ፡፡ ትኩታቸውን የሚጥሉበት ነገር የወደፊታቸው ላይ ታላቅ ተጽእኖ እንዳለው የገባቸው ሰዎች ያለፈውን በመተው ወደፊት በመዝለቃቸው ላይ ሲያተኩሩ፣ ሌሎች ግን በአለመግባባትና በጸብ “መንፈስ” ውስጥ የመቆየት ዝንባሌ አላቸው፡፡ ትኩረታቸውን በይቅርታና ከተከሰተው ችግር ባሻገር በመሄድ ላይ ማድረግን ትተው ነገርን በመጎተትና በማካበድ ላይ የሚያደርጉ ሰዎች ወደ ተሻለ ሕይወት ለመዝለቅ የሚያበቃ አመለካከት እንደጎደላቸው አመልካች ነው፡፡
ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ዝንብንና ንብን፡፡ ዝንብ ቆሻሻው፣ መጥፎ ሽታ ያለውና የሞተው ነገር ሲስባት፣ ንብ ደግሞ ንጹህ፣ መልካም ጠረን ያለውና ሕይወት ያለው ነገር ይስባታል፡፡ ዝንብ ቆሻሻን፣ በሽታንና ሞትን ስታዛምት፣ ንብ ስትሰራ ውላ ጣፋጭ ነገርን በማምረት የብዙዎችን ሕይወት ታጣፍጣለች፡፡
አሁንም ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ንስርንና ጥንብ አንሳን፡፡ ንስር ሕይወት ያለውን ነገር ተናጥቆ ሲመገብ፣ ጥንብ አንሳ የከረመን፣ የሞተንና የበሰበሰን ነገር ሲያነሳ ይኖራል፡፡ ምርጫው የእኔ ነው፡፡ ያለፈውንና የሞተውን ነገር መከታተልና ያንን “እየተመገቡ” መኖር፣ ወይስ ያንን ትቶ የወደፊቱን፣ ትኩሱንና በይቅርታ የታደሰውን?
መዘንጋት የሌለብህ እውነታዎች …
• ተበደልኩ በማለት ወደኋላ በመመለስ ወደምታስታውሰው የጊዜ ርቀት የመመለስና ኋላ ቀር የመሆን እድልህ የሰፋ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የዛሬ 10 ዓመት የሆነብህን አሁንም የምትቆጥር ከሆነ በአመለካከትህም ሆነ በኑሮ እድገትህ 10 ዓመታት ወደኋላ ተጎትተህ በመመለስ እንዳዘገምክ አትዘንጋ፡፡
• ይቅር ያላልከው ሰው በአንተ ላይ የበላይነት አለው፡፡ አንተ የሆነብህን ስታብሰለስል ምናልባት እርሱ የግሉን፣ የቤተሰቡንና የሕብረተሰቡን ሕይወት እንዴት እንደሚሳድግ እቅድ እያወጣ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡
• አንተ ይቅር ያላልከው ሰው ምን እንዳደረገብህ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ ስታስተላልፍ፣ ምናልባት እርሱ አዳዲስ እውቀቶችንና ስልጣኔዎችን በማስተላለፍ አልፎህ ሄዶ ይሆናል፡፡
እኔ ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ፣ አንተስ? አንቺስ?
ዶ/ር እዮብ ማሞ
👍 84❤ 29🤔 2
"ወደ መሬት ወድቀን በሰገድን ጊዜ ኃጢአት እንዴት ወደ ታች ጎትታ እንደጣለችን እናስታውሳለን። ዳግመኛም ከወደቅንበት በተነሣን ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ እና ምሕረት እንዴት ከመሬት እንዳነሣንና የሰማዩን ርስት እንደሰጠን እንመሰክራለን"
👍 144❤ 23👏 13
ያገዘፍከውና ያሳነስከው
የዛሬዋ ሕይወት በትናንትናውና በነገው መካከል እንደ ሳንዱዊች የተጣበቀች ሂደት ነች፡፡ እነዚህ ሁለቱ የሕይወት ገጽታዎች በዛሬው የሕይወትህ ሂደት ላይ ትልቅ ድርሻ አላቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከእነዚህ ሁለት ገጽታዎች መካከል ያገዘፈው ህይወትህን የማንቀሳቀስ አቅም አለው፡፡
የትናንትናውን ስታገዝፈው፣ የነገው ይደበዝዛል፤ የነገውን ስታገዝፈው ደግሞ የትናንትናው ይደበዝዛል፡፡ በእነዚህ ሁለት ምርጫዎች መካከል የመወሰን መብቱም አቅሙም አለህ፡፡
ብዙ የተሳካላቸው ሰዎች የትናንትናውን ልምምዳቸው “መልካምም” ሆነ “መጥፎ” ያንን ሳይክዱና ፈጽመው ሳይጥሉት ነገር ግን ከትናንትናው ይልቅ የነጋቸውን በማግዘፍ እንደሚያምኑ ይናገራሉ፡፡
የትናንትናውን በማግዘፍና የነገውን በማግዘፍ መካከል መምረጥ ማለት በመቃብር ውስጥ ባለውና በመሕጸን ውስጥ ባለው መካከል እንደመምረጥ ነው፡፡ የትናንትናህ መቃብር ውስጥ ነው - ሞቷል! በተቃራኒው፣ የነገህ ደግሞ በማህጸን ውስጥ ነው - ሊወለድ ተዘጋጅቷል! የትኛውን ትመርጣለህ? ለየጥኛው ትኖራለህ? የትናውን ስታሰላስል ታሳልፋለህ? ወደየትኛው አቅጣጫ መሄድ ትፈልጋለህ?
ያለፈው ታሪክ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ካለፈው ታሪክ ይልቅ የነገው ራእይህ ሲገዝፍ ሕይወት ወደፊት ትሄዳለች፡፡ ከመጣህበት ይልቅ የምትሄድበት ሲገዝፍ! ካለፈው ስቃይ ይልቅ ከዚያ በመማር የያዝከው የመለወጥ ሂደት ሲልቅ! ካለፈው ስኬት ይልቅ የነገው የላቀ ደረጃ ሲተልቅ! አስገራሚ ሕይወት!!! አስገራሚ የወደፊት!!!
ዶ/ር እዮብ ማሞ
👍 84❤ 16👏 2🤔 2
ያገዘፍከውና ያሳነስከው
የዛሬዋ ሕይወት በትናንትናውና በነገው መካከል እንደ ሳንዱዊች የተጣበቀች ሂደት ነች፡፡ እነዚህ ሁለቱ የሕይወት ገጽታዎች በዛሬው የሕይወትህ ሂደት ላይ ትልቅ ድርሻ አላቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከእነዚህ ሁለት ገጽታዎች መካከል ያገዘፈው ህይወትህን የማንቀሳቀስ አቅም አለው፡፡
የትናንትናውን ስታገዝፈው፣ የነገው ይደበዝዛል፤ የነገውን ስታገዝፈው ደግሞ የትናንትናው ይደበዝዛል፡፡ በእነዚህ ሁለት ምርጫዎች መካከል የመወሰን መብቱም አቅሙም አለህ፡፡
ብዙ የተሳካላቸው ሰዎች የትናንትናውን ልምምዳቸው “መልካምም” ሆነ “መጥፎ” ያንን ሳይክዱና ፈጽመው ሳይጥሉት ነገር ግን ከትናንትናው ይልቅ የነጋቸውን በማግዘፍ እንደሚያምኑ ይናገራሉ፡፡
የትናንትናውን በማግዘፍና የነገውን በማግዘፍ መካከል መምረጥ ማለት በመቃብር ውስጥ ባለውና በመሕጸን ውስጥ ባለው መካከል እንደመምረጥ ነው፡፡ የትናንትናህ መቃብር ውስጥ ነው - ሞቷል! በተቃራኒው፣ የነገህ ደግሞ በማህጸን ውስጥ ነው - ሊወለድ ተዘጋጅቷል! የትኛውን ትመርጣለህ? ለየጥኛው ትኖራለህ? የትናውን ስታሰላስል ታሳልፋለህ? ወደየትኛው አቅጣጫ መሄድ ትፈልጋለህ?
ያለፈው ታሪክ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ካለፈው ታሪክ ይልቅ የነገው ራእይህ ሲገዝፍ ሕይወት ወደፊት ትሄዳለች፡፡ ከመጣህበት ይልቅ የምትሄድበት ሲገዝፍ! ካለፈው ስቃይ ይልቅ ከዚያ በመማር የያዝከው የመለወጥ ሂደት ሲልቅ! ካለፈው ስኬት ይልቅ የነገው የላቀ ደረጃ ሲተልቅ! አስገራሚ ሕይወት!!! አስገራሚ የወደፊት!!!
ዶ/ር እዮብ ማሞ
Repost from TgId: 1163708603
ስለመፅሐፍ የተነገሩ አባባሎች!
ወዳጆች ዛሬ የአለም የንባብ ቀን እንደመሆኑ የንባብ ባህላችን እንዲዳብር ሊያነሳሱን የሚችሉ ስለመፃሕፍት የተነገሩ የተለያዩ ሠዎችን አባባል ዛሬ ልንዘክር ብዕራችንን ከወረቀቱ አገናኝተናል፡፡
መፅሐፍ የሚሠጡት ጥቅም የታወቀ ቢሆንም በማንበብ ብቻ ግን አዋቂ መሆን አይቻልም ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም መፃሕፍትን ከማንበብ ባሻገር በንባብ ያገኘናቸውን ሃሳቦች ከሃሳባችን ጋር በማስተያየትና በማሻሻል፣ በማሠላሠልና በማስተዋል አዲስ ሃሳብ ካልፈጠርንበት መፅሐፍ ማንበብ ሳይሆን መፅሐፍ መቁጠር ነው የሚሆነው፡፡ ባነበብነው ሃሳብ ተገዝተንና አዲስ የባህሪ ለውጥ ወይም አዲስ ነገር ካልፈጠርንበት ማንበባችን ዕውቀት አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ዕውቀት ስንል በተጨባጭ በተግባር የሚገለፅ ነውና፡፡
ለማንኛውም አባባሎቹን እነሆ እላለሁ..! ሃሳብና አስተያየታችሁ የተጠበቀ ነው፡፡ መልካም ንባብ!
‹‹መፅሐፍ አንድ ቁምነገር አለው፡፡ ይሄም እግርህን ከቤትህ ሳታነሳ ዓለምን እንድትዞር ያደርግሃል›› (ጁምባ ራሂሪ)
‹‹አንባቢ ከመሞቱ በፊት አንድ ሺ ኑሮ ይኖራል፡፡›› (ጆርጅ ማርቲን)
‹‹መፅሐፍት ተንቀሳቃሽ አስማቶች ናቸው›› (ስቴፈን ኪንግ)
‹‹እንደ መፅሐፍ ያለ ታማኝ ጓደኛ የለም፡፡›› (ኸርነስት ኸርሚንግወይ)
‹‹ አንድ ነገር አንርሳ! አንድ መፅሐፍ፣ አንድ እስኪብርቶ፣ አንድ ሕፃን፣ አንድ መምህር ዓለምን መለወጥ ይችላሉ፡፡›› (ማላላ ዮሶፍዜ)
‹‹ዓለም መፅሐፍ ናት፡፡ ዓለምን ተጉዘው ያላዩ መፅሐፍ ይግለጡ፡፡›› (ቅዱስ አውግስጦስ)
‹‹መፅሐፍ በየዕለቱ የሚያጋጥመንን የህይወት ጉድፍ የሚያስወግድልን የነፍሳችን ማጠቢያ ነው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው)
‹‹ማንበብ ለአዕምሮ ሲሆን አዕምሮም አካላችን ምን ማድረግ እንዳለበት ያቀናጃል›› (ያልታወቀ ሠው)
‹‹መፅሐፍ ከባድ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ዓለሙ ሁሉ በእርሱ ታጭቋልና፡፡›› (ኮሜሊያ ፈንክ)
‹‹ዛሬ አንባቢ የሆነ ነገ መሪ ይሆናል፡፡›› (ማርጋሬት ፉለር)
‹‹ዛሬ ልታነበው የምትችለውን መፅሐፍ ለነገ አታቆየው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው)
‹‹ካነበብኩ መላው ዓለም ለእኔ ክፍት ነው፡፡›› (ሜሪ ማክሎድ ቤቱን)
‹‹አንዳንድ መፅሐፍት ነፃ ይተዉናል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ነፃ አድርገው ይሠሩናል፡፡›› (ራልፍ ዋልዶ ኤመርሠን)
‹‹መፅሐፍ ወደፊት ልንሆን የምንፈልገውን የያዘ ህልማችን ነው፡፡›› (ኔል ጌማን)
‹‹ቤተ-መፃሕፍቶች ልክ እንደጥሩ ትዝታ መዓዛቸው ያውደኛል፡፡›› (ጃኩሊን ውድሰን)
‹‹መፅሀፍ አስተሳሰባችንን የሚያቀጣጥል መሣሪያ ነው፡፡›› (አላን ቤኔት)
‹‹ሌላ ሠው ያነበበውን ብቻ እያነበብክ ከሆነ ሌላ ሠው የሚያስበውን ብቻ ነው እያሠብክ ያለኸው፡፡›› (ሐሩኪ ሙራካሚ)
‹‹ቤት ያለመፅሐፍት ማለት አካል ያለነፍስ ማለት ነው፡፡›› (ሲስሮ)
‹‹ተራ ሠዎች ትላልቅ ቲቪ አላቸው፡፡ ብልህ ሠዎች ግን ቤተመፃሕፍት አላቸው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው)
"መፅሀፍ ማለት በኪሳችን ይዘነው የምንዞረው በመልካም ፍሬዎች የተሞላ እርሻ ነው።” ቻይናውያን
“መፅሀፍ ስናነብ ወደ ውስጣችን በጣም ጠልቀን በመግባት ስለራሳችን የበለጠ ብዙ ነገሮችን ማወቅ እንጀምራለን።”
ዊልያም ሀዝሊት
@Zephilosophy
@Zephilosophy
👍 24
📖📚 ስለ መፅሐፍት ጥቅሶች 📖📚
ᜰ꙰ꦿ➢ “
⚜️⚜️⚜️⚜️
ᜰ꙰ꦿ➢ “በመመገቢያ ጠረጴዛህ ላይ መፀሀፎች ይሙሉ።ከዛም በጣም ደስተኛ ትሆናለህ። ትራስህም መፀሀፍቶችን ይሁኑ ከዛም ፍፁም የሠላም እንቅልፍ ትተኛለህ።” #ፊይዶር ዶስቶኸስኪ
⚜️⚜️⚜️⚜️
ᜰ꙰ꦿ➢ “ለአንድ ሰአት ብቻ ካነበብክ ወይም የማንበብ ልምድ ካለህ መጨነቅህ አይቀርም። ከሁለት ሰአታት በላይ የማንበብ ልምድ ካለህ ግን በምድር ላይ እንዳንተ ደስተኛ ሰው አይኖርም።” #ቻርለስ ዴ ሴኮንዳት
⚜️⚜️⚜️⚜️
ᜰ꙰ꦿ➢ “ሠዎች ህይወትን አንድ የሆነ ነገር ነው ብለው ይገልፃሉ። ለእኔ ግን ህይወት ማለት ማንበብ ማለት ነው።” #ሎጋ ስሚዝ
⚜️⚜️⚜️⚜️
ᜰ꙰ꦿ➢ “ማንበባቸውን ተከትሎ በየዘመናቸው ታላቅ ስራን የሰሩ ጀግኖች ቁጥራቸው ስንት ይሆን?” #ሔነሪ ዳቪድ
⚜️⚜️⚜️⚜️
ᜰ꙰ꦿ➢ “መፅሀፍ የሚያነቡ ሠዎች ብቸኝነት አያጠቃቸውም።” #አጋታ ክርማለት
⚜️⚜️⚜️⚜️
ᜰ꙰ꦿ➢ “መፅሀፍ ማንበብ ነፍስን ያክማል።” #በቴክሳስ ላይብረሪ መግቢያ ላይ የተፃፈ
💫💫💫💫
ᜰ꙰ꦿ➢ “መፅሀፍ የሌለበት መምሪያ ቤት ማለት መስኮት የሌለበት ቤት ማለት ነው።” #ሎነሬች ማን
💫💫💫💫
ᜰ꙰ꦿ➢ “ሠው መንፈሱን መመገብ የሚችለው መፀሀፍትን በማንበብ ብቻ ነው።” #ኤድዊን ማርክሃም
💫💫💫💫
ᜰ꙰ꦿ➢ “የተራበ ከብት ሳር ሲግጥ የሚሰማውን ደስታ ይህል ነው የሠው ልጅም መፅሀፍትን ሲያነብ ከፍተኛ ደስታን የሚያገኘው።” #ሎርድ ቸስተርፌልድ
💫💫💫💫
ᜰ꙰ꦿ➢ “አንድ ሠው ለልጁም ሆነ ለመላው ማህበረሰብ ከሚሰጠው ስጦታዎች ሁሉ ትልቁ አንብቦ ሰዎችን እንዲያነቡ ማስቻሉ ነው።” #ካርል ካጋን
💫💫💫💫
ᜰ꙰ꦿ➢ “መፅሀፍትን ማንበብ መታደል ነው። ምክንያቱም ባነበብን ቁጥር አለማችንን በሚገባ እናውቃታለንና።”
#ኒል ጌይንማን
ᜰ꙰ꦿ➢ “እኔ ዘወትር የማስበው በቀጣይ ስለማነበው መፀሀፍ ብቻ ነው።” #ሮኦልድ ዳህልሰዓት ተሸካሚው
ምንጭ ፦ የፍልስፍና ማዕድ
በጥበበኛው ሰለሞን
“አንድ ቀን በሕይወትህ ላይ እንዲጨመርልህ ምን ያህል ትከፍላለህ?”
ሰዓት ተሸክሞ የሚዞር አንድ ሰው፣ በመንገድ ያገኘውን አንድ ህጻን ልጅ ጠየቀ ...
ህጻኑም ያለማመንታት “አምስት ሳንቲምም አልከፍልም" አለ፡፡
ዳግም ሰዓት ተሸክሞ የሚዞረው ሰው ተመልሶ መጣና ትናንት ህጻን የነበረውን የዛሬውን ወጣት ጠየቀው “አንድ ቀን በሕይወትህ ላይ እንዲጨመርልህ ምን ያህል ትከፍላለህ?”
“ቢበዛ አንድ ወይም ሁለት ብር” ወጣቱም መለሰ፣ ግድ በሌለው አኳሃን፡፡
ይህ ወጣት ሸምግሎ ለሞቱ አንድ ሐሙስ በሚጠባበቅበት ጊዜ ሰዓት ተሸካሚው ተመልሶ መጣ፡፡
“አንድ ቀን በሕይወትህ ላይ እንዲጨመርልህ ምን ያህል ትከፍላለህ?”
"በባህር ውስጥ ያሉ እንቁዎችን፣ በሰማይ ላይ ያሉ ከዋክብትን ሁሉ እከፍላለሁ” ሽማግሌው መለሰ፡፡
ከፍልስፍና እሳቤዎች መኻል ላይ ልናነሳው የወደድነው ጊዜ ነው፡፡ የሰው ልጅ ስለ ሁለንተና ባወቀ እና ይበልጥ በተራቀቀበት መጠን፣ መልስ አልባ ጥያቄዎችን ያነሳል። ከየት መጣን? ጊዜ መጀመሪያ አለው? ጊዜስ በራሱ ምንድን ነው? በጊዜ መስመር ውስጥስ እንዳሻን ወደ ፊት እና ወደ ኋላ መመላለስ ይቻለናል?
እነዚህን መልስ አልባ እንቆቅልሾችን ፍልስፍናዊ መልስ እንስጣቸው ብንል፣ ጊዜ በራሱ እንቅፋት ይኾንብናልና ለአሁኑ በጊዜ ወደ ኋላ መመለስ ይቻላልን? ከተቻለስ ምን ይከሰታል እና ጊዜስ ምንድን ነው የሚሉትን ሃሳቦች ብቻ እናብላላለን፡፡
ጊዜ ሰዓታችን የሚለካው ነገር እንደሆነ እናስባለን፡፡ ምድር ላይ ያሉ ክስተቶችንም በቅደም ተከተል እናስቀምጥበታለን። እናም ጊዜ በእለት ተዕለት መንከላወሳችን ውስጥ ትልቅ ስፍራን ይይዛል፡፡ ጥድፊያችንንም ኾነ እርጋታችንን የሚወስነው ጊዜ ነው፡፡ ሆኖም እንደምናስበው ወይም ይህ ነው ብለን እንደጠራነው አይነት ጊዜን በቀላሉ ፍቺ ሰጥተን አውቀነዋል ማለት አንችልም። ለብዙ ዘመናት ሳይንሳዊያን እና ፍልስፍናውያን በጊዜ ጉዳይ ሲጨቃጨቁ ኖረዋል።
ፈላስፎችን ብዙው ክርክራቸው የሚያተኩረው፣ አሁን፣ አላፊው ጊዜ እና የወደፊቱ ላይ ነው፡፡ የጊዜን የፍልስፍና እሳቤዎች በሶስት አጠቃለን መመልከት እንችላለን፡-
የአሁናዊነት (Presentism) ፍልስፍና አራማጆች የእውኑ ዓለም አሁንን እና አሁንን ብቻ ይይዛል ይሉናል፤ ትናንት አልፏል እና የእውነት አይደለም፤ ነገም አልደረሰምና የእውነት አይደለም፤ የእውነት የሆነ ነገር ቢኖር አሁን ብቻ ነው፡፡ ያለፈው ትዝታችን፤ ያልደረሰው የወደፊቱም እንዲሁ ትንበያ ብቻ ነው። እውነት የአሁን ቅጽበት ላይ ብቻ ትገኛለች።
በአንጻሩ የአላፊነት (growing-past) ፍልስፍና አቀንቃኞች እውነት አላፊው እና የአሁን ጊዜ ላይ ብቻ ትገኛለች ፤ ያልተከወነው የወደፊቱ ጊዜ የእውኑ ዓለምን አይወክልልንም ይላሉ፡፡ ዳይኖሰሮች የእውነት ናቸው፤ የአድዋ ጦርነት እውነት ነው ሆኖም ወደ ፊት መከሰቱ የማይቀረው የእኔ እና ያንተ ሞት ግን እውነት አይደለም።
ሶስተኛው የጊዜ እሳቤ የዘላለማዊነት(eternalism) ይሰኛል። በአሁን፣ በአላፊ እና በወደፊት ጊዜ መካከል የእውነትነት ልዩነት የለም ይለናል። ለምሳሌ የአዶልፍ ሂትለር በጀርመን መነሳት የአላፊ ጊዜን አይጠቁምም፤ ላንተ ያለፈ ጊዜ ቢሆንም ለአርስቶትል ገና ያልተከሰተ የወደፊት ክስተት ነው።
ሆኖም ጊዜ በራሱ ምንድን ነው?
ጥንታውያን ኢትዮጵያውያን፤ ህንዶች፣ ግብጾች እና ግሪካውያን ጊዜን በተለያዩ መንገዶች ይገልጹት ነበር። ጥንታውያኑ ሰዎች ስለጊዜ አላቂነት ወይም ዘላለማዊነት፣ ስለ ጊዜ እንዲሁ ፈሳሽነት አልያም ዙሮ ገጠምነት (ለምሳሌ ቀን ይደጋገማል፤ አመትም እንደ አዲስ ይጀምራል) የተለያዩ መላምቶች ነበሯቸው፡፡
ሬኒ ዴካርቴ 'ጊዜ ምን ማለት ነው?' ለሚለው ጥያቄ እንዲህ ይለናል:- “ቁስ አካሎች፣ ለምሳሌ አንተ ዘላለማዊ አይደለህም። እንዲያውም ከቅጽበታት ያለፈ እድሜ የለህም፡፡ በአንጻሩ እግዚአብሔር አንተን ጨምሮ ዓለምን በሙሉ በየቅጽበታቱ ይፈጥራል። ከአምስት ደቂቃ በፊት ያለው ዓለም እና አሁን ያለንበት ዓለም ይለያያል። ከቅጽበት በኋላም የሚኖረው ዓለም፣ አሁን ላይ ካለው ዓለም ይለያል። እናም የአሁኑን ቅጽበት ከቀጣዩ ቅጽበተ ዓለም የሚያቆራኘው ነገር ምን ይባላል?... ጊዜ። እግዜርም በእያንዳንዱ ቅጽበት አንተን እና ዓለምን ደጋግሞ ከጥቂት ልዩነቶች ጋር ይፈጥርሃል።”
ሁሉም እንስሳቶች ማለት ይቻላል አሁንን ነው የሚኖሩት፤ ሆኖም ሰው ትንኝ አይደለምና ትናንት ምን እንደነበር ያስታውሳል፤ ነገም እንደሚመጣ ያውቃል። ለጊዜም ያለን እይታም ከእንስሳት ለይቶናል፤ እናስባለን ... እናሰላስላለን እንወስናለን፡፡ ትናንት የረገጥነውን ፈንጂ ዛሬ ላይም መልሰን አንረግጠውም፡፡ ተፈጥሮ ጊዜን እንድናውቅ አድርጋናለች። ጊዜ የእውነት ያለ ነገር ነው? መስመሩስ እንዲሁ እንደ ወንዝ ወደፊት ብቻ የሚፈስ ነውን? መጀመሪያ እና መጨረሻስ አለውን?
@Zephilosophy
@Zephilosophy
👍 58❤ 9🔥 3😢 1
Repost from TgId: 1163708603
ከወሲብ ባሻገር
ኦሾ፣ አንተ ወሲብ የማይረባ ነገር መሆኑን ስትናገር ሰምተን እንደገና ሞክረነው ነገር ግን አልገባንም የማይረባ የሆነው ምኑ ላይ ነው?”
እየነገርኳችሁ የነበረው ስለ ሌላ ነገሮች ነው፡፡ እሺ እነሱን ሞከራችኋቸው፡፡ በየቀኑ ስለ መመሰጥ እነግራችኋለሁ ነገር ግን እያረዘማችሁ (ላለማድረግ እያዘገያችሁ) ወሲብን ግን ትሞክራላችሁ አያችሁ ይህ ነው እንግዲህ ቀሽምነታችሁን የሚያሳየው፡፡
ወሲብ የማይረባ አይደለም እናንተ ናችሁ የማትረቡት፡፡ ለዚህ ነው በእናንተ ምክንያት ተራ ወሲብ የማይረባ የማይሆነው፡፡ ማሳደግ ካልቻላችሁ፣ ንቁም ካልሆናችሁ ቀሽምነቱን ልትረዱት አትችሉም፡፡ በተመሳሳይ ደረጃ ሆናችሁ መገንዘብ አትችሉም፡፡
ወደ እብዶች ቤት ሂዱ አንድ እብድ ፈልጉና “እብድ ነህ" በሉት ነገር ግን ቅሉ ፍፁም ይናደድባችኋል፡፡ ማንም እብድ መሆኑን አይቀበልም፡፡ "ምን እያወራችሁ ነው? ከእኔ በስተቀር አለም በሙሉ እብድ ነች" ይላችኋል፡፡ አንድ እብድ እብድነቱን አመነ ማለት በእርግጠኝነት ከእብድነት አለም እየወጣ መሆኑን ማወቅ ይኖርባችኋል፡፡
መመሰጥን ማግኘት ካልቻላችሁ የተሻለ መመልከት፣ ከተለየ አቅጣጫ መረዳት አትችሉምና የማይረባ መሆኑን ልትረዱት አትችሉም፡፡ አሁን እናንተ ምንም የምልከታ አቅጣጫ የላችሁም፡፡ ዝግ ናችሁ ዝግ፡፡
ወደ መስታውት ቅረቡ አፍንጫችሁ መስታወቱን እስኪነካ ድረስ፡፡ አስተውሉ በፍፁም ፊታችሁን ማየት አትችሉም፡፡ የመስታውቱ ችግር አይደለም፡፡ ከመስታወቱ ራቅ ስትሉና ቦታ ስትሰጡት አንፀባርቆ ፊታችሁን ያሳያችኋል ስለዚህ ከመስታውቱ ራቁ።
ወሲብ ትልቁ ተወዳጅ ነገር ይመስላል፡፡ ወንድ በሴት ይማረካል ሴትም በወንድ ትማረካለች፡፡ አንዱ የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ የወሲብ አጋሩ ያለው ይመስለዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ሁለቱንም ለማኝ ያደርጋቸዋል፡፡ ፍላጐታቸውን ሁሉ ከወሲብ ጥላ ጀርባ የሚያገኙት ይመስላቸዋል፡፡
እንደዚህ አይነት ነገሮችን እንድትሰሩ የሚያደርጋችሁ ውስጣችው ያለው ሆርሞናችሁ ነው፡፡ ስነህይወታዊ ቀመር ነው፡፡ ምን እየሰራህ እንደሆነ፣ ለምን እየሰራኸው እንደሆነ ማየት ብትችል ለራስህ ይገርምሀል። ወሲብ በመፈፀምህ ያገኘኸው ነገር ምን ይሆን?፡፡ንቁ መንፈስ ውስጥ በምትገባበት ወቅት ምን እያወራሁ እንደሆነ ይገባሀል፡፡ ነገር ግን ንቁ መንፈስህ ጥልቅነት የሌለው በመሆኑ እያደገ ይገድልሀል እናም ወደ ነበርክበት የስህተት ጐዳና ትመለሳለህ።
እንደገና ሞክረው ነገር ግን ስትሞክረው እያስተዋልክ እና እየተመሰጥክ ይሁን፡፡ ያን ጊዜ ወሲብን ፈፅመህ ላለማድረግ ትወስናለህ ወይም ተፈጥሯዊ አስገዳጅ ሀይል መሆኑን ትረዳለህ፡፡
እኔን ልትሸውዱኝ አትችሉም፡፡ እኔ ወሲብ የማይረባ ነው ስላልኳችሁ የፈፀማችሁት ይመስላችኋል?፡፡ ወሲብ በጣም ምርጥ ነው፣ ወሲብ በጣም የማይረባ ነገር ነው ብላችሁ አልያም ስለወሲብ አለመናገርን ብመርጥ እናንተ ከመፈፀም ወደኋላ አትሉም፡፡
ወደ አእምሯችሁ ተመልከቱ፡፡ እንዴት እራሳችሁን እያታለላችሁ እንደሆነ ለመረዳት ሞክሩ፡፡ አለበለዚያ እኔ ምን እያወራሁ እንደሆነ የንቃት ደረጃችሁ ካላደገ ፈፅሞ ልትገነዘቡኝ አትችሉም፡፡ የበለጠ ነገር ለማየት ከፈለጋችሁ ከዚህ የበለጠ ማሻሻል (ማደግ) አለባችሁ፡፡
ለምሳሌ እኔ አንድ መንገድ ዳር ላይ ያለ ዛፍ ጫፉ ላይ ሆኜ እናንተ በመንገዱ ላይ እየሄዳችሁ ጋሪ እየመጣ ነው" ብላችሁ "ምንም ጋሪ አይታየኝም ጋሪ የለም ትሉኛላችሁ፡፡ ነገር ግን እኔ ጋሪውን ማየት የምትችሉት ወደ እናንተ በቀረበ ጊዜ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ አልፏችሁ ሲሄድ እንደገና ከእይታችሁ ውጪ ይሆናል፡፡
አሁንም ወደ በለጠ ከፍታ በወጣችሁ ቁጥር የተሻለ ማየት ትችላላችሁ፡፡ የከፍታ ቁንጮ ላይ ስትሆኑ ሁሉንም ነገር ታያላችሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ያለፈም ይሁን መጪ ጊዜ የለም ያለው አሁን ብቻ ነው፡፡ እውነታው ሲገባችሁ ወሲብ በጣም የማይረባ አና ለረጅም ጊዜ በባርነት የሚይዝ መሆኑን ትረዱታላችሁ፡፡ እያጣጣልኩት (እየነቀፍኩት) አይደለም ነገር ግን እውነታው ይህ ነው እኔም የተናገርኩት ያንኑ ነው፡፡ አያችሁ በውስጡ ዘልቃችሁ በመግባታችሁ በባርነት አስሮ ምን እየሰራችሁ እንደሆነ እንኳን ማየት እንዳትችሉ ወደ ንቃት እንዳትመጡም አድርጓችኋል።
ወሲብ ከሚያሰክሩ (ስነህይወትህ) ውስጥ ነው፡፡ በደምስሮችህ ውስጥ የሚያሰራጨው ነገር በሱስ ተለክፈህ ምን እንደምትሰራ እንዳታውቅ እና ስሜቶችህን መቆጣጠር እንዲሳንህ ያደርጋል፡፡ በተደጋጋሚ እንድትፈፅመው የሚያስገድድህ ያልታወቀ ሀይል አለ እንደፈለጋችሁ ልትጠሩት ትችላላችሁ፡፡ በንቁ ጊዜያቶችህ ግን የማይረባ ነገር ስለምትረዳ "ምን እየሰራሁ ነበር? ለምን? ምን ነገርስ አገኘሁ?" በማለት ትጠይቃለህ፡፡ለዚህ ነው ብዙ ሴቶች ከወሲብ በኋላ የሚያለቅሱት እና የሚያዝኑት ምክንያቱም ሁሉም ነገር ትርጉም አልባ ሆኖ ያገኙታል፡፡ ለጊዜው ስሜትን የሚያነሳሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በተመሳሳይ ሁኔታ ቢደጋገምም የትም አያደርስም፡፡ ወንዱ ከወሲብ በኋላ ወዲያውኑ ይተኛል ምክንያቱ ደግሞ በተረጋጋ መንፈስ ስላደረገው ነገር ማሰብ አለመፈለጉነው ጧት ሲነሳ ሁሉንም ነገር ይረሳል፡፡
በርግጥ ይገበኛል ጥሩ ነው ብለህ አምነህ የምትኖርበትን ልምድ ሲያንቋሽሹብህ አትወድም። ማንም ጅል ሲባል ደስ አይለውም፡፡ የምትረበሸው ስለ ወሲብ ባለህ ጥያቄ ሳይሆን በህይወትህ በራሱ ነው፡፡ ጅል ከሆነ እና ከኖርክባት አንተም ጅል እየሆንክ ነው። በርግጥ ያስቆጣል ነገር ግን በዚህ አጋጣሚ ከሱ የተሻሉ መልካም ነገሮች በህይወት ውስጥ መኖራቸው መናገር ይኖርብኛል፡፡ወሲብ ጅማሮ እንጂ ፍፃሜ አይደለም፡፡ እጥብቀህ እስካልያስከው ድረስ እንደ መጀመሪያ ያህል ከተጠቀምክበት ምንም ችግር የለውም፡፡
ፍቅር ከሰራህ በኋላ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያህል በዜን እሳቤ ተቀመጥ ያን ጊዜ የምለው ይገባሀል፡፡ ወሲብ ጅል ነው የምለው ለምን እንደሆነ ይገባሀል፡፡ ከወሲብ በኋላ ለአንድ ሰዓት ያህል ስለተፈጠረው ነገር አስብ፡፡ አውቀህ ነው ወይስ ስሜትህ አስገድዶህ? አውቀህ ከሆነ ጅል አይደለህም፡፡ ተገዢ ከነበርክ ግን ጅል መሆንህን ተረዳው ምክንያቱም እየደጋገምክ በመፈፀም ራስህን ለበለጠ ባርነት እየሰጠህ ነው፡፡
በተመስጦ ብቻ ነው ምን እያወራሁ እንደነበረ ሊገባህ የሚችለው፡፡ በክርክር የሚወሰን ጥያቄ አይደለም፡፡ በራስህ ንቃት፣ በራስህ ግንዛቤ እና በራስህ ተመሰጦ የሚወሰን መሆኑን ተገንዘብ፡፡
ኦሾ
የዜን መንገድ
@Zephilosophy
@Zephilosophy
👍 59❤ 6😢 2

