TIKVAH-MAGAZINE
رفتن به کانال در Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

194 404
مشترکین
-5024 ساعت
-1767 روز
-81830 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
ኬንያ የሳይበር ጥቃት ተፈጽሞባታል።
በኬንያ በተፈጸመ የሳይበር ጥቃት የፕሬዚዳንቱን ፅህፈት ቤት ጨምሮ የበርካታ ሚኒስቴሮች ድረ-ገጽ ተጠልፎ የነበረ ሲሆን ከሰዓታት በኋላ ዳግም ተመልሷል።
በዚህ የተቀናጀ የሳይበር ጥቃት የፕሬዚዳንቱን ጽህፈት ቤት ጨምሮ የጤና፣ የትምህርት፣ የስራ፣ የአካባቢ፣ የሃገር ውስጥ፣ የቱሪዝምና የቴክኖሎጂ ሚኒስቴሮች ድህረገጽ መጠለፉ ተነግሯል።
ድረ-ገጾቹ መጠለፋቸውን ተከትሎ በድሀረገፆቹ ላይ "Access denied by PCP", "We will rise again", "White power worldwide", and "14:88 Heil Hitler" የሚል ፅሁፍ ታይቷል።
ድህረገፆቹ ከተጠለፉ በኋላም መንግስት በኦንላይን የሚሰጣቸው አገልግሎቶች አቋርጦ ቆይቷል።
የመከላከያ እና የገንዘብ ሚኒስቴር በጥቃቱ ሰለባ አልሆኑም ሲባል ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ ቡድን እስካሁን የለም።
በ2023 በኬንያ መንግስታዊ ተቋማት ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ደርሶ የነበረ ሲሆን የሱዳን የመረጃ መዝባሪዎች ቡድን ኃላፊነቱን ወስዶ ነበር።
ዘገባው የኬንያንስ ነው።
❤ 68🤣 28👏 5👎 3🔥 2
📹
በሀገራችን መከሰቱ የተረጋገጠውን ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) አስመልክቶ
- የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤
- የኅብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ
የሰጡትን መግለጫ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።
ማርበርግ_ቫይረስ_Marburg_Virus_አስመልክቶ_ከጤና_ሚኒስቴር_የተሰጠ_መግለጫ.mp382.26 MB
❤ 38🙏 9🤬 8🤔 3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#Update
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በወቅታዊ የጤና ጉዳይ ላይ የሚሰጡትን መረጃ ከደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።
@TikvahethMagazine
👎 52❤ 27🕊 7
Photo unavailableShow in Telegram
🎤 #Live
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በወቅታዊ የጤና ጉዳይ ላይ ከደቂቃዎች በኋላ መግለጫ ይሠጣሉ። በ @TikvahethMagazine መግለጫውን በቀጥታ የምናስተላለፍ ይሆናል።
🎧 ተከታተሉን !
@TikvahethMagazine
❤ 16🤔 7👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
#Update
በውሃ እጥረት እየተፈተነች ያለችው ኢራን እጇን ለፀሎት ወደ ሰማይ ስትዘረጋ ቴክኖሎጂን በመጠቀምም ዝናብ ለማዝናብ እየሞከረች ነው።
ኢራን ከፍተኛ በሆነ የውሃ እጥረት እየተፈተነች ስትሆን የዋና ከተማዋን የሚያጠጡ ግድቦች አቅምም ወደ 5% ወርዷል።
ይህንንም ተከትሎ ኢራን የ"Cloud seeding" በመጠቀም ዝናብ ለማዝነብ እየሞከረች ነው።
"Cloud Seeding" አውሮፕላንን ወይም ጄኔሬተር በመጠቀም ወደ ደመና ጨዋማ ኬሚካሎችን በመርጨት ዝናብ ለማዝነብ የሚደረግ ሙከራ ሲሆን ይህንን ዘዴ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በተደጋጋሚ ተጠቅመዋለች።
ኢራን ይህንን ዘዴ ኡሪማ በተሰኘው ትልቁ ኃይቋ ላይ ሞክራለች።
ከተለመደው አማካይ የዝናብ መጠን በዚህ አመት የዝናብ መጠኗ በ89 በመቶ እንደቀነሰ የገለጸችው ኢራን ዝናብ እንዲዘንብም የአደባባይ ጸሎት አርብ እለት አድርጋለች።
ቅዳሜ ዕለትም ከቴህራን በስተሰሜን በዚህ አመት ለመጀመሪያ ጊዜ በረዶ የታየ ሲሆን በምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ አካባቢዎች የተወሰነ ዝናብም ዘንቧል ተብሏል።
ኢራን በ50 አመት ውስጥ ከባዱን ድርቅ እያስተናገደች መሆኗንም ገልፃ ውሃ በሚያባክኑት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ብላለች።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 73🙏 21🤣 10🕊 6😢 4👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ደቡብ ሱዳን ባለፈው ታህሳስ ወር የተያዙ 27 ዜጎቿ መለቀቃቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያን አመስግናለች።
ባለፈው ታህሳስ ወር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው የገቡ 27 የደቡብ ሱዳን ዜጎች በሚዛን እስር ቤት የቆዩ ሲሆን ተፈተው ወደ ጁባ ተመልሰዋል።
የዜጎቹን መፈታት ተከትሎም የደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መንደይ ሰማያ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ጋር በስልክ ሲነጋገሩ ለኢትዮጵያ መንግስት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተጨማሪ የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤትም የኢትዮጵያ መንግስትን አመስግኗል።
@TikvahethMagazine
❤ 29🤬 1
Photo unavailableShow in Telegram
በካሽ 100% ለሚከፍል 35% ቅናሽ
📍ሳር ቤት ቫቲካን እና በአዋሬ
🎯65/35 አከፍፈል (35%ቅናሽ)
👉2መኝታ 81 ካሬ = 6 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106 ካሬ=7.8 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139 ካሬ=10.3 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152 ካሬ= 11.8 ሚሊዮን ብር
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 81ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%) = 1.78 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=2.33ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)= 3.06 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=3.34 ሚሊዮን ብር
#ቀሪውን 80% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%-25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
👉👉 መረከቢያ ጊዜ - 2 አመት ከ 6 ወር
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇👇👇
+251980782850
❤ 12
Photo unavailableShow in Telegram
አሜሪካ የመረጃ መንታፊዎች ወደ ሶማሊያ መንግስት የኢ ቪዛ ስርዓት በመግባት የ35,000 ሰዎችን መረጃ መውሰዳቸውን አስታወቀች።
ሶማሊያ ከወራት በፊት የኢ ቪዛ አገልግሎት የጀመረች ሲሆን በሶማሊያ ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ ወደ ቪዛ ስርዓቱ የገቡ መንታፊዎች የአሜሪካ ዜጎችን ጨምሮ የበርካቶችን የግል መረጃ መውሰዳቸውን ገልጿል።
ኤምባሲው የተሰረቀው መረጃ ስም፣ ፎቶና አድራሻዎችን ጨምሮ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲሰራጭ መመልከቱን አስታውቋል።
ዩናይትድ ኪንግደም በበኩሏ ወደ ሶማሊያ ለመሄድ ለሚያስፈልገው ኢ ቪዛ ዜጎቿ ከማመልከታቸው በፊት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክራለች።
ሶማሊያ የቪዛ አገልግሎቱን የምትሰጥበትን ድህረገጽም ያለ ምንም ማብራሪያ ቀይራለች።
የመረጃ ምዝበራውን ተከትሎም ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ከ60 የሚልቁ የውጪ ሃገራት የደህንነት ባለሙያዎች ሶማሊያን ለቀው ወጥተዋል።
ባለሙያዎቹ የግል መረጃቸው በመውጣቱ የጥቃት ኢላማ እንዳይሆኑ በመስጋት ለቀው እንደወጡም ተነግሯል።
በሶማሊያ መንግስት በኩል ይፋዊ የሆነ መግለጫ ባይሰጥም የመረጃ ምዝበራውን ተከትሎ ከፍተኛ ድንጋጤ መፈጠሩ ግን ተነግሯል።
ዘገባው የቢቢሲና የዴይሊ ኤክስፕረስ ነው።
@TikvahEthMagazine
❤ 68🤣 23😢 7👍 5🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኮንጎና ታጣቂው ኤም 23 በምስራቃዊ ኮንጎ ያለውን ግጭት ለማስቆም ያለመ የማዕቀፍ ስምምነት ተፈራረሙ።
የበርካታ ሰዎችን ህይወት የቀማውን ውጊያ ሲያደርጉ የቆዩት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎና የኤም 23 ታጣቂ በኳታር ዶሃ ሰላምን ለማምጣት ያለመ የማዕቀፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ከስምምነቱ ጀርባ የአሜሪካ ድጋፍ እንዳለ የተገለፀ ሲሆን በመካከኛው ምስራቅና አፍሪካ የፕሬዚዳንት ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ማሳድ ቡሎስ ማዕቀፉ ስምነት ነገሮችን መያዙን ገልፀው ስድስቱ እንዴት እንደሚተገበሩ ለመስማማት ስራ እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።
ማሳድ ቡሎስ ሁለቱ አካላት የእስረኞች ልውውጥና የተኩስ አቁም ማድረግን በተመለከተ በፍጥነት መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።
በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም 23 ታጣቂ ቡድን በማዕድን በበለጸገው ምስራቃዊ ኮንጎ ለአመታት እየተዋጉ ሲሆን በርካታ ንፁሃንንም ገድለው ማዕድናትንም ዘርፈዋል።
ኮንጎ ለታጣቂው ድጋፍ የምትሰጠዋን ሩዋንዳን በተደጋጋሚ ሰትከስ እንደነበር ይታወሳል።
ሁለቱ አካላት ባለፉት ወራት በርካታ ስምምነቶችን የተፈራረሙ ሲሆን አተገባበሩ ላይ ጥያቄዎች ሲነሱ የአሁኑ የሰላም ማዕቀፍ ስምምነት ግን ሁለቱ አካላት ከግጭት ወጥተው ዘላቂ የሰላም ውይይት እንዲፈርሙ ለማድረግ ተስፋ ተጥሎበታል።
መረጃው የሮይተርስ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 50😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
🌟 ታማኝነት
🌟 ጥራት
🌟 ማሕበረሰብን መገንባት የሚታወቀው የናተው አያት አሁን ደሞ
✨ በካሳንቺስ
✨በልደታ
✨በሴሚሲ ሚካኤል
✨በቤልየር
✨በአያት
⚡️በ ካሬ ከ 89,815 ብር ጀምሮ አፓርትመንት እና የ ንግድ ሱቆች ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ሣይደረግቦት የራስዎ ያርጉ!
💥 ለበለጠ መረጃ 2519-77-63-06-93 በቀጥታ @ayat121921 በቴሌግራም በዋትሳፕ ይደውሉ
❤ 13
Photo unavailableShow in Telegram
አፍሪካ በ25 ዓመት ውስጥ ከፍተኛ ነው የተባለን የኮሌራ ወረርሽኝ እያስተናገደች ነው።
የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል ሲዲሲ አፍሪካ በሩብ ምዕተ አመት ውስጥ ከፍተኛ ነው የተባለ የኮሌራ ወረርሽኝ ቀውስ ውስጥ ገብታለች ብሏል።
ማዕከሉ 300,000 ያህል ሰዎች በበሽታው መያዛቸውንና 7000 ያህሉ መሞታቸውን ገልፆ የሟቾች ቁጥር ከባለፈው አመት በ30% ጨምሯል ብሏል።
በሽታው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንጎላና ቡሩንዲ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው ሲባል የበሽታው ማዕከል በነበረችው ኮንጎ በሽታውን መቆጣጠር ስለመቻሉ ሲዲሲ ገልጿል።
ዘገባው የአፍሪካ ኒውስ ነው።
@Tikvahethmagazine
❤ 29😢 13👎 11
Photo unavailableShow in Telegram
እስራኤል በጋዛ የነበሩ ከ700 በላይ የውሃ ጉድጓዶችን ማውደሟ ተነገረ።
እስራኤል በጋዛ ጦርነት በጋዛ የሚገኝን 85 በመቶ የውሃ ጉድጓድ ማውደሟን የከተማዋ ባልስልጣናት አሳውቀዋል።
የውሃ ጉድጓዶቹ በመውደማቸውም በጋዛ በነፍስ ወከፍ ከጦርነቱ በፊት 90 ሊትር በቀን የነበረው ድርሻ ወደ 15 ሊትር መውረዱ ተነግሯል።
የእስራኤል ጦርነት በጋዛ ከተማን የሚያጠጡ 3 የውሃ ምንጮችን ያጠቃ ሲሆን ከእነዚህ የውሃ ምንጮች የሚገኘው ውሃ ከአንድ አመት በፊት በ35 በመቶ መቀነሱ ተነግሮ ነበር።
የጋዛ የከርሰምድር ውሃ በቀን 262,000 ኪዩቢክ ሜትር ውሃን ለከተማዋ የሚያቀርብ ሲሆን በጦርነቱ በደርስባቸውም ጉዳት የሚያመርቱት የውሃ መጠን በቀን ከ93,000 ኪዩቢክ ሜትር በታች ሆኖ ነበር።
የጨው ውሃን ከሚያጣሩ የጋዛ ማጣሪያዎች መካከል በቀን 10,000 ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የሚያጣራው ሙሉ ለሙሉ ከስራ ውጪ ሲሆን ሌሎቹም የማጣራት አቅማቸው ከግማሽ በላይ ቀንሷል።
ጋዛ ካጋጠማት የውሃ ችግር በተጨማሪ በጦርነቱ 2 ሚሊየን ሜትር የፍሳሽ ማስወገጃ በመውደሙ ቆሻሻ ውሃ ወደተቀረው የውሃ አካል እየገባ እየገባ መሆኑንም አስታውቃለች።
ዘገባው የአናዶሉና የዋፋ ነው።
@TikvahethMagazine
😢 119❤ 33💔 17🤬 12🤔 6👍 1👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
በቻይና መንግስት ይደገፋሉ የተባሉ የመረጃ መንታፊዎች በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የታገዘ የመጀመሪያ ነው የተባለ የሳይበር ጥቃት ፈፅመዋል ተባለ።
አንትሮፒክ የተባለው የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ተቋም ባወጣው ሪፖርት በቻይና መንግስት የሚደገፉት የመረጃ መንታፊዎች የራሱን የ"Claude code model" በመጠቀም 30 ድርጅቶች ላይ ጥቃቱን መፈፀማቸውን አስታውቋል።
ድርጅቶቹ በዋነኝነት የቴክኖሎጂ ፣ የፋይናንስ እና የመንግስት ተቋማት ናቸው ተብሏል።
አንትሮፒክ ጥቃቱ የተወሳሰበ መሆኑን ገልፆ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ሞዴሉ በራሱ ጥቃቶችን እንዲፈፅም እንደተደረገ ገልጿል።
አንትሮፒክ አክሎም ይህ ያለ ሰው ጣልቃ ገብነት የተፈፀመ የመጀመሪያው የሳይበር ጥቃት እንደሆነም አሳውቋል።
ተቋሙ የሰው ሰራሽ አስተውህሎቱ በራሱ ከ80%-90% የሚሆነውን ስራ እንደሚሰራና ሰዎች የመጨረሻ ውሳኔ ብቻ እንደሚሰጡ በመግለፅ በሳይበር ደህንነት ዙሪያ እየመጣ ስላለው ተጨማሪ ስጋት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
ከተሞከረው ጥቃት ጥቂቱ መሳካቱ ሲገለፅ ቻይና ከጥቃቱ ጀርባ እንደሌለች በኤምባሲዋ በኩል ገልፃለች።
ዘገባው የፎክስ ኒውስ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 40👍 3🤯 3
Photo unavailableShow in Telegram
በካሽ 100% ለሚከፍል 35% ቅናሽ
📍ሳር ቤት ቫቲካን እና በአዋሬ
🎯65/35 አከፍፈል (35%ቅናሽ)
👉2መኝታ 81 ካሬ = 6 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106 ካሬ=7.8 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139 ካሬ=10.3 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152 ካሬ= 11.8 ሚሊዮን ብር
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 81ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%) = 1.78 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=2.33ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)= 3.06 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=3.34 ሚሊዮን ብር
#ቀሪውን 80% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%-25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
👉👉 መረከቢያ ጊዜ - 2 አመት ከ 6 ወር
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇👇👇
+251980782850
❤ 22
Photo unavailableShow in Telegram
❇️25% ልዩ ቅናሽ ለ50 ቤቶች ብቻ
❇️ ከ 454,315.00 ብር ጀምሮ
✅መሰረተ ልማቶች በበቂ ሁኔታ በተሟሉላቸው፤
✅የከተማችን ምቹ የመኖሪያ መንደሮች
✅በካዛንቺስ ቤተመንግስት ፊት-ለፊት
✅ በሲ.ኤም.ሲ፣
✅በመሪ እና
✅በአያት አካባቢዎች
✅በ 10% ቅድመ ክፍያ
✅ከ 45 ካሬ እስከ 160 ካሬ ባለ 4 መኝታ።
✅በኢትዮጵያ ብር ብቻ ተዋውለው ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ሣይደረግቦት
✅የቤት ባለቤት ይሁኑ።
⚠️ቀድሞ የመጣ ቀድሞ ይስተናገዳል❗️
ለበለጠ መረጃ:
☎️ 251977630693 በቀጥታ @ayat121921 በቴሌግራም፣ በዋትሳፕ ይደውሉ
Photo unavailableShow in Telegram
በ"ChatGpt" የተፃፈው የፓኪስታን ጋዜጣ ፅሁፍ
የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ከመጣ በኋላ ሁሉም በየዘርፉ ለመጠቀም እየሞከረ ሲሆን በ1941 በፓኪስታን መታተም የጀመረው "Dawn" የተሰኘው ጋዜጣ ሰሞነኛ ተግባር ግን መነጋገሪያ ሆኗል።
በጋዜጣው ላይ ፀሃፊ የሆነው አንዱ ጋዜጠኛ ስለ መኪና ሽያጭ መጨመር የሚያብራራ ፅሁፍ የፃፈ ሲሆን በፅሁፉ መካከል ከቻትቦቱ የተሰጠዎ ምላሽ ተካቶበታል( በምስሉ የሚታየው)።
የሰው ሰራሽ አስተውህሎቱን ብዙዎቹ "ChatGpt" እንደሆነ ሲጠቅሱ በፅሁፉ ውስጥም በተካተተው ምላሽ ፊት ገጹን ሊሰራለት እንደሚችል ሲጠይቀው ተካቷል።
ጋዜጣው ፅሁፉ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተሰራ መሆንን ያመነ ሲሆን ኦንላይን ባለው ይዘት ላይ ማሻሻያ በማድረግ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት እንደተሰራ የሚያሳይ ማስታወሻ አካቶበታል።
ጋዜጣው ተግባሩ ፖሊሲውን የጣሰ እንደሆነ ገልፆ ምርመራ መጀመሩንም ገልጿል።
ዘገባው ከፋይናንሻል ኤክስፕረስ የተወሰደ ነው።
@TikvahethMagazine
🤣 267❤ 76👍 9🤔 8😢 4
Photo unavailableShow in Telegram
ደቡብ ኮሪያ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ስትል ሁሉንም አይነት በረራ አቁማ ነበር።
ደቡብ ኮሪያ 500,000 ያህል ተማሪዎቿ ከባድ የሚባለውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና እየፈተነች ሲሆን ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ቦታቸው በጊዜ እንዲደርሱ ሲባል ሌሎች በረራዎች ለግማሽ ሰዓት ቆመው ነበር ተብሏል።
በሁሉም ኤርፖርቶች ተማሪዎች ለፈተናው ሲቀመጡ እንዳይጉላሉ በማሰብ አውሮፕላኖች ለ30 ደቂቃ ከማረፍና ከመብረር ተከልክለው ነበር።
በውሳኔው 65 አለም አቀፍ በረራዎችን ጨምሮ 140 በረራዎች ሲስተጓጓሉ አውሮፕላኖችም ከ3000 ሜትር ከፍታ በታች ከመብረር ታግደው ነበር።
በተጨማሪ ተፈታኞች በጊዜ እንዲደደርሱ ቢሮዎች ከተለመደው ሰዓት በአንድ ሰዓት ዘግይተው እንዲከፈቱ ተደርጓል።
ደቡብ ኮሪያ ዘንድሮ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ተፈታኞችን እያስፈተነች ሲሆን ቁጥሩም ከ2019 በኋላ የተመዘገበ ከፍተኛው የተፈታኝ ቁጥር ነው ተብሏል።
ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የተለያዩ የትምህርት አይነቶችን መርጠው ሲፈተኑ ፈተናው እስከ 13 ሰዓት ድረስ ሊፈጅ ይችላል።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 168🤣 43🤔 8👏 5😢 3👎 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
የአለም ባንክ ለኬንያ የቤት ልማት ፕሮጀክት ብድር ሊሰጥ ነው።
የአለም ባንክ ለኬንያ የቤት ግንባታ ፕሮጀክት 1.35 ቢሊየን ዶላር ሊያሰባስብ ሲሆን 375 ሚሊየን ዶላር በብድር መልክ ራሱ ባንኩ ሲሰጣት ከሌሎች አበዳሪዎች 900 ሚሊየን ዶላር ብድር እንድታገኝ ይረዳታል ተብሏል።
በተጨማሪ የነዳጅ ላኪዎች ድርጅት ወይም ኦፔክ ለቤት ግንባታው 75 ሚሊየን ዶላር ይሰጣል ተብሏል።
አለም ባንክ ኬንያ የ2 ሚሊየን ቤቶች እጥረት እንዳለባት አንስቶ ፍላጎቷ በአመት በ250,000 አባወራዎች እየጨመረ እንዳለ ነገር ግን የምታቀርበው ከ50,000 በታች እንደሆነ ገልጿል።
ብድሩ በመጪው ግንቦት ወር እንደሚፀድቅ ሲጠበቅ ዊሊያም ሩቶ በ2027 ሰርተው ለማጠናቀቅ ላቀዷቸው 1 ሚሊየን ቤቶችም ተስፋ የሰጠ ሆኗል።
ዘገባው የኬንያንስ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 55👎 7😢 6🤔 4
Photo unavailableShow in Telegram
የሱዳን ጦር አዛዥ ጀነራል አል ቡርሃን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሳሪያውን እስካላስቀመጠ ድረስ የሚኖር የሰላም ስምምነትና ንግግር እንደሌለ ገለጹ።
አል ቡርሃን ኃይሉ መሳሪያውን ሳያስቀምጥ የሚኖር ንግግር እንደሌለና ኃይሉም ሆነ የሚደግፋቸው በሱዳን ተቀባይነት እንደሌላቸው ገለጸዋል።
ጀነራሉ" ወይ እናጠፋቸዋለን አልያም ህይወታችን እስክንሰጥ እንዋጋለን" ሲሉም ተደምጠዋል።
አል ቡርሃን ጦርነቱ በድርድር ሳይሆን ሁሉም መዋጋት የሚችል ሰው በመዋጋትና አማፂውን በማሸነፍ የሚጠናቀቅም ነው ብለዋል።
የሱዳን የፈጥኖ ደረሽ ኃይሉ ባሳለፍነው ሳምንት ለሰላም ንግግር ዝግጁ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።
በተያያዘ ዜና የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ ማርክ ሩቢዮ ከተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች አቻቸው ሼህ አብዱላሂ ቢን ዛይድ ጋር በሱዳን ዙሪያ መክረዋል።
በስልክ ስላደረጉት ንግግር በዝርዝር የተባለ ነገር የሌለ ሲሆን ጦርነቱ ሊቆም በሚችልበት ነገር ዙሪያ መክረዋል ተብሏል።
ኤምሬቶች የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ትደግፋለች ተብላ የምትከሰስ ስትሆን ሩቢዮም ከሚደግፏቸው ጋር ንግግር ይኖረናል ሲሉ ከቀናት በፊት መናገራቸው ይታወሳል።
መረጃው የአናዶሉ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 56👎 20🤔 3👍 1🤣 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቮዳኮምና ስታርሊንክ በአፍሪካ ኢንተርኔትን ለማስፋፋት ተስማሙ።
ሁለቱ ተቋማት በአፍሪካ የገጠራማ አካባቢዎች የኢንተርኔት ተደራሽነትን ለማስፋትና ለቢዝነሶች ፈጣን ኢንተርኔት ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ፈፅመዋል።
በስምምነቱ መሰረት የስታርሊንክ የሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎት በቮዳኮም የሞባይል ኔትዎርክ በኩል ሲሰጥ በገጠራማ አካባቢዎች ለሚገኙ ትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማት ፈጣን አገልግሎት መስጠት ያስችላል።
በተጨማሪ ቮዳኮም የስታርሊንክን መሳሪያዎች እና አገልግሎቶች በአፍሪካ ለሚገኙት ቢዝነሶች የመሸጥ መብት ተሰጥቶታል።
ቮዳኮም በ2030 የደንበኞቹን ቁጥር 260 ሚሊየን ለማድረስ እየሰራ ሲሆን ስምምነቱ ይኸንን ራዕይ እንዲያሳካ ያግዘዋል።
ስታርሊንክ በ25 የአፍሪካ ሃገራት እየሰራ ሲሆን ስምምነቱ ሌሎች አዳዲስ ተጠቃሚዎችን እንደሚጨምርለት ታምኖበታል።
@TikvahethMagazine
❤ 30👍 9👎 4🤔 2😢 2
