TIKVAH-MAGAZINE
رفتن به کانال در Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

194 405
مشترکین
-5824 ساعت
-1527 روز
-79430 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
ሩዋንዳ ከኬንያ በመቀጠል በአዲሱ የአሜሪካ የእርዳታ ሞዴል ስምምነት የፈፀመች ሁለተኛዋ ሃገር ሆናለች።
አሜሪካና ሩዋንዳ ለአምስት አመታት የሩዋንዳን የጤና ዘርፍ ለማገዝ የሚያስችል የ228 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ፈፅመዋል።
አሜሪካን ቀዳሚ ባደረገው የትራምፕ ሞዴል ስርም ባለፈው ኬንያ ተመሳሳይ ስምምነት መፈፀሟ ይታወሳል።
በስምምነቱ መሰረት አሜሪካ በሩዋንዳ ኤድስን፣ ወባን እና ሌሎች በሽታዎችን ለመፋለም 158 ሚሊየን ዶላር ስትደግፍ ሩዋንዳ የጤና ኢንቨስትመንቷን በ70 ሚሊየን ዶላር ትጨምራለች።
እንደ ኬንያው ስምምነት ሁሉ አሜሪካ የምትሰጠው እርዳታ ቀስ በቀስ ሲቀንስ የሩዋንዳ መንግስት የፋይናንስ ድርሻ እየጨመረ ይመጣል።
በተጨማሪ ከሩዋንዳ ጋር በመተባበርም የህይወት አድን መድሃኒቶችን ወደሚፈለግበት ቦታ በድሮን ለማድረስ የሚያስችል ስታርትአፕ ይገነባል።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 33👎 15👏 7
Photo unavailableShow in Telegram
በሶማሊያ 50 ህጻናት በዲፍቴሪያ ወረርሽኝ ምክንያት ህይወታቸው አለፈ።
በሶማሊያ በተከሰተው "ዲፍቴሪያ" ወረርሽኝ ቢያንስ 50 ሕፃናት ሞተዋል ሲባል ወደ 1,000 የሚጠጉ ደግሞ በበሽታው ተይዘዋል።
ይህን ተከትሎ ሀገሪቱ ከታህሳስ 6 ጀምሮ የክትባት ዘመቻ ለመጀመር ያቀደች ሲሆን ዘመቻው ከ5 እስከ 15 ዓመት እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ህጻናት ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።
ዲፍቴሪያ በባክቴሪያ የሚመጣ ከባድ በሽታ ሲሆን በዋነኛነት በአፍንጫና ጉሮሮ ላይ ጉዳት የሚያደርስ እንዲሁም የቆዳ ቁስለት ሊያስከትል የሚችል ነው።
በሽታው በሳል ፣ በማስነጥስና በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት በመመሥረት በከፍተኛ ሁኔታ ይተላለፋል።
በሽታውን በክትባት አማካኝነት መከላከል ይቻላል።
መረጃው የ Xinhua ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
😢 39❤ 30🤔 4🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ያልተሳካው የቤኒን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሰት ሙከራ
ፓስካል በተባለ ኮሎኔል የሚመራ የወታደሮች ቡድን የሀገሪቱን ፕሬዚዳንት ከስልጣን ማንሳታቸውን እንደዚሁም ህገመንግስቱን ማገዳቸውን በብሔራዊ ጣቢያ ቀርበው አውጀው ነበር።
በፕሬዚዳንቱ መኖሪያ አካባቢም ተኩስ እንደነበር ሲነገር የብሔራዊ ሚዲያ ጋዜጠኞችም ታግተው ነበር። በወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ታሎንም ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ በፈረንሳይ ኤምባሲ ነበሩ ተብሏል።
ፕረዚዳንቱ በኋላ ላይ በቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው መግለጫ ሰጥተዋል።
የቤኒን የሃገር ውስጥ ሚኒስትር የተወሰኑ ወታደሮችሀገሪቱንና ተቋማቷን ወደ ሁከት ለማምራት ሞክረዋል ያለ ሲሆን ታማኝ እና ለሪፐብሊኩ የቆሙ ወታደሮች ምላሽ ይህንን ሙከራ አክሽፎታል ብሏል።
ቤኒን በአፍሪካ የተረጋጋ ዲሞክራሲ ካላቸው ሃገራት ቀዳሚዋ ስትሆን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉት ወታደሮች ለህዝባቸው አዲስ ዘመን መምጣቱን አብስረው ነበር።
በአፍሪካ መሪዎች ከጊዜ ቆይታቸው በላይ ህገመንግስት በማሻሻል ምርጫ ሲወዳደሩ የወቅቱ የቤኒን ፕሬዚደንት ግን ለሶስተኛ ዙር አልወዳደርም በማለት በመጪው ሚያዚያ ከሚካሄደው ምርጫ ራሳቸውን አግልለዋል።
በአፍሪካ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስቶች የተለመዱ ሲሆን በቅርቡ በጊኒ ቢሳው መፈፀሙ ሲታወስ ባለፉት ጥቂት አመታቶች ደግሞ በቡርኪናፋሶ፣ ጊኒ፣ ማሊ እና ኒጀር መፈፀሙ ይታወሳል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 54👍 9🤣 4
Photo unavailableShow in Telegram
ሶማሊያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ የሙሉ እዳ ስረዛ አገኘች።
የአፍሪካ ልማት ባንክ ሶማሊያ ከ2024-2039 ባለው ጊዜ ልትከፍለው የሚገባን የ17.68 ሚሊየን ዶላር እዳ ሰርዟል። እዳ ስረዛው የመጣው በከፍተኛ እዳ ውስጥ ያሉ ድሃ ሃገሮችን ኢንሼቲቭ በመጨረሷ ነው።
ኢንሼቲቩ በአለም ባንክ በ1996 የተጀመረ ሲሆን አላማውም ጥብቅ የሆኑ መመዘኛዎችን የሚያሟሉና ድህነት ቅነሳ ላይ የሚሰሩ ሃገራትን እዳ በመቀነስ ላይ ያተኮረና ከአይኤምኤፍ፣ አለም ባንክና የአፍሪካ ልማት ባንክ እዳዎችን ሙሉ ለሙሉ እንዲሰርዙ ያስችላል።
በተጨማሪ እዳ ስረዛው የሶማሊያን የውጪ እዳ በ2018 ከነበረበት 5.2 ቢሊየን ዶላር ወደ 557 ሚሊየን ዶላር ዝቅ ለማድረግ የተጀመረ እንቅስቃሴ አካልም ነው።
አይኤምኤፍ እና የአለም ባንክ በ2023 በዚሁ ኢንሼቲቭ ስር ለሶማሊያ የ4.5 ቢሊየን ዶላር የእዳ እፎይታ መስጠታቸው ይታወሳል።
የእዳ እፎይታውም የሶማሊያን የእዳ ለሃገር ውስጥ ጥቅል ምርት ምጣኔ በ2018 ከነበረበት 64% በ2023 ወደ 6% ዝቅ እንዲል አድርጓል።
ሶማሊያ በአለም ባንክ እና አይኤምኤፍ የተቀመጠውን ኢንሼቲቭ ለማጠናቀቅ የማዕከላዊ ባንክ ስራዋን ስታዘምን የፋይናንስ አስተዳደሯን ማጠናከሯና ገቢን ማሳደጓ ተነግሯል።
በተመሳሳይ በርካታ አበዳሪዎች እዳዋን እየሰረዙላት የምትገኘዋ ሶማሊያ በ2024 ከፈረንሳይ 145.6 ሚሊየን ዶላር ስረዛ ማግኘቷ ይታወሳል።
በተጨማሪ ከአረብ የገንዘብ ተቋም የ306.5 ሚሊየን ዶላር እፎይታ አግኝታለች።
አይኤምኤፍ ለሶማሊያ የ30 ሚሊየን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ሊሰጥ ስለመቃረቡ ሲነገር ሶማሊያ በእዳ ስረዛው ገንዘብ የመምህራን ምልመላ ለማካሄድና መሰረተ ልማት እንደምትገነባበት ገልፃለች።
ዘገባው ከባንኩ ድህረ ገፅ እና ከሂራን ኦንላይን የተገኘ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 47🔥 2🤣 1
Photo unavailableShow in Telegram
አባይ ሆምስ
ስመ ጥሩ እና ገናናው አባይ ቴክ ለረጅም ዓመታት የመኪና መገጣጠሚያ እንዲሁም ሌግዠሪ ዶፕሌክስ ቤቶችን በ ፍላሚንጎ ሰርቶ እንዳስረከበ ይታወቃል አሁን ደግሞ በመሃል ሜክሲኮ አፓርትመንት እና የንግድ ሱቅዎችን ለሽያጭ አውጥተናል።
ለመኖሪያ አልያም አትርፈው ለመሸጥ የሚመርጡት
👉 የሳይት አድራሻ :- በመሃል ሜክሲኮ አፍሪካ ህብረት አጠገብ
👉 ቅድመ ክፍያ 10%
👉 ባለ 1 መኝታ
👉 ባለ 2 መኝታ
👉 ባለ 3 መኝታ
👉 እንዲሁም የንግድ ሱቆች በ10, 14, 33.6, 50.4 ካሬ ጀምሮ
በተጨማሪም እንደ አከፋፈሎ ከ 10-20 % ቅናሽ ይደረግሎታል
📍ሜክሲኮ
ለበለጠ መረጃ በ 09-38-95-23-23
❤ 21
Photo unavailableShow in Telegram
"የሞባይል መልዕክት የቲቢ በሽታን ህክምና እንዴት ሊያሻሽል እንደሚችል ጥናት እየተደረገ ነው።" - አፍሪካ ሲዲሲ
የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል ከአለም ባንክ ባገኘው የ100,000 ዶላሮ ድጋፍ በቲቢ በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ በአህጉሪቱ ተጠቂ በሆኑት ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ ጥናት እያደረገ ነው።
ጥናቱ በፈረንጆቹ ህዳር 17 ጅማሬውን ያደረገ ሲሆን ታህሳስ 12 ይጠናቀቃል ተብሏል።
በጥናቱ የሁለቱ ሃገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ የላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ እንደዚሁም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና የድሬደዋ ጤና ቢሮ ተሳታፊ ናቸው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በ2023 10.8 ሚሊየን ሰዎች በቲቢ በሽታ ሲያዙ ከ1.25 ሚሊየን በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
በኢትዮጵያ ከ100,000 ሰዎች 119 ያህሉ በቲቢ በሽታ እንደሚጠቁ መረጃዎች ያመለክታሉ። በላይቤሪያ ይህ ምጣኔ 308 ይደርሳል።
ጥናቱ ምን ላይ መሰረት ያደረገ ነው ?
ጥናቱ ተካሚዎች ህክምናቸውን እንዳያቋርጡ በስልካቸው መልዕክት መላክ እንደ መፍትሄ መመልከትን ለማጥናት ያቀደ ነው።
በጥናቱ ከሀገራቱ 422 ታካሚዎች በጥቅሉ 844 ታካሚዎች ይሳተፋሉ ሲባል 200 ያህሉ መልዕክት እንዲቀበሉ በማድረግ ለውጡን ለማየት ይሞከራል።
ጥናቱ፥ መልዕክት(SMS) ላይ መሰረት ያደረገ የቲቢ ህክምና ድጋፍን ውጤታማነት የሚመዝን ሲሆን ይህንን የዲጂታል መንገድ ለመጠቀም ያሉ ምቹ እና አስቸጋሪ ሁኔታዎችንም ይዳስሳል።
የጥናቱ ውጤት በኢትዮጵያ፣ ላይቤሪያና ሌሎች ሃገራት ያለውን የቲቢ በሽታ የቁጥጥር ፖሊሲ ፕሮግራሞች ላይ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሏል።
የአፍሪካ ሲዲሲ ፈጠራ የታከለባቸውን መፍትሄዎች በማምጣት በ2035 ቲቢን ለማጥፋት የተቀመጠውን ራዕይም ለማሳካት እንደሚሰራ ጠቁሟል።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 84🙏 7👍 5🤣 4
Photo unavailableShow in Telegram
ደቡብ ሱዳናዊቷ ሞዴል የብሪቲሽ የፋሽን ሽልማትን ካሸነፈች በኋላ በሃገሯ ሰላም እንዲመጣ ጠይቃለች።
አኖክ ያሂ የተባለችው የደቡብ ሱዳን ሞዴል በብሪቲሽ የፋሽን ሽልማት የአመቱ ምርጥ ሞዴል ተብላ ስትመረጥ ጠናካራ መልዕክት አስተላልፋለች።
በመልዕክቷም፥ "አሁን እያዩኝ ላሉ ጥቁር ሴት ልጆች ሁሉ ቀለማችሁ እርግማን አይደለም። እድለኞች አይደላችሁም ማለት አይደለም። ብቁ ናችሁ፤ ችሎታ አላችሁ ከምታስቡት በላይ ጠንካራ ናችሁ" ስትል ተደምጣለች።
ሞዴሏ በንግግሯ በሀገሯ ደቡብ ሱዳን ሰላም እንዲመጣም ጠይቃለች።
የ27 አመቷ ሞዴል ቤተሰቦቿ በጦርነት ምክንያት ከደቡብ ሱዳን ወደ ግብጽ የተሰደዱ ሲሆን አሜሪካ የገባችው በሦስት ዓመት አድሜዋ ነው።
በሽልማቱ ለሁለት ተከታታይ አመታት ከታጨች በኋላ ተሸንፋ የነበረችው ሞዴል ሽልማቱ ታሪኬን የራሳቸው ላደረጉ ሁሉ የተገባ ነው ብላለች።
ዘገባው TRT Africa ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 116👍 16🕊 3🤔 2🤝 1
Photo unavailableShow in Telegram
አሜሪካ በሱዳን ጦርነት ተፋላሚዎች ላይ መጠነ ሰፊ ማዕቀብ ለመጣል እያቀደች መሆኑ ተሰምቷል።
አሜሪካ ከትራምፕ መምጣት በኋላ በሱዳን ሰላም ለማምጣት ሃሳብ አቅርባ እንደነበር ሲታወስ፣ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እቅዱን መቀበሉና የሱዳን ጦር ግን እንደማይቀበል መግለፁ ይታወሳል።
ትራምፕ የሰላም ስምምነቱ እንዳይሳኩ በሚያደርጉ አካላት ላይ ሰፊ ማዕቀብ ለመጣል ማቀዳቸው ተዘግቧል።
አሜሪካ እስካሁን ባለው በተዋጊ ቡድኖቹ መሪዎች እና መቀመጫቸውን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ባደረጉ ተቋማት ላይ ማዕቀብ መጣሏ የሚታወስ ነው።
አሜሪካ በተጨማሪ ከሱዳን ጦር ጋር ግንኙነት አለው ተብሎ የሚዘገበውን የሙስሊም ወንድማማቾች ቡድን በአሸባሪነት ለመፈረጅም እንቅስቃሴ ጀምራለች።
አሜሪካ ሁለቱ አካላት ወደ ሰላም እንዲመጡ ተጨማሪ ግለሰቦች፣ የፋይናንስ ተቋማትና የጦር መሳሪያ አቅራቢዎች ላይ ማዕቀብ ልትጥል አቅዳለች።
የሰላም ስምምነቱን ተቀብሎ የ3 ወራት የተናጥል የተኩስ አቁም አውጄያለሁ ያለው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ውጊያውን ቀጥሏል።
አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች የአረብ ሃገራትን ያቀፈው ቡድን ሰላም ለማምጣት ጥረት እያደረገ ቢሆንም እስካሁን አልተሳካለትም።
ተመድ በተዋጊዎች ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ቢጥልም ተዋጊዎች ከውጪ ኃይሎች በሚያገኙት መሳሪያ መዋጋታቸውን ቀጥለዋል።
አሜሪካ ማዕቀቡን ማስፋቷና ለቡድኖቹ ድጋፍ ያደርጋሉ ባለቻቸው አካላት ላይ ማዕቀብ ለመጣል ማቀዷ ጫና ፈጥሮ ሰላምን ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ተጠብቋል።
ዘገባው የዘ ጋርዲያን ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 55👍 11👏 4
Photo unavailableShow in Telegram
አባይ ሆምስ
ስመ ጥሩ እና ገናናው አባይ ቴክ ለረጅም ዓመታት የመኪና መገጣጠሚያ እንዲሁም ሌግዠሪ ዶፕሌክስ ቤቶችን በ ፍላሚንጎ ሰርቶ እንዳስረከበ ይታወቃል አሁን ደግሞ በመሃል ሜክሲኮ አፓርትመንት እና የንግድ ሱቅዎችን ለሽያጭ አውጥተናል።
ለመኖሪያ አልያም አትርፈው ለመሸጥ የሚመርጡት
👉 የሳይት አድራሻ :- በመሃል ሜክሲኮ አፍሪካ ህብረት አጠገብ
👉 ቅድመ ክፍያ 10%
👉 ባለ 1 መኝታ
👉 ባለ 2 መኝታ
👉 ባለ 3 መኝታ
👉 እንዲሁም የንግድ ሱቆች በ10, 14, 33.6, 50.4 ካሬ ጀምሮ
በተጨማሪም እንደ አከፋፈሎ ከ 10-20 % ቅናሽ ይደረግሎታል
📍ሜክሲኮ
ለበለጠ መረጃ በ 09-38-95-23-23
❤ 22
Photo unavailableShow in Telegram
ታንዛኒያ የ3 አክቲቪስቶችን አካውንት አሳገደች
ታንዛኒያ ባለፈው ወር ካደረገችው ምርጫ ጋር በተያያዘ ንቁ ተሳታፊ ናቸው ያለቻቸውን የ3 አክቲቪስቶችን ኢንስታግራም አካውንት አዘግታለች።
ታንዛኒያ የሶስት አክቲቪስቶችን አካውንት ሜታ ካልዘጋ የሜታን አገልግሎት እንደምታቋርጥ ካስፈራራች በኋላ ሜታ ሁለቱን አካውንቶች ሲዘጋ የአንዱን ደግሞ አግዶታል።
መንግስት የአክቲቪስቶቹ አካውንት ካልታገደ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራምና ዋትስአፕ በታንዛኒያ እንዳይሰሩ እንደሚያደርግ መግለጹ ነው የተነገረው።
አካውንታቸው የተዘጋባቸው አክቲቪስቶች ውሳኔው ተገቢ እንዳልሆነ አንስተው ሜታ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ተጋፍቷል ብለዋል።
አክቲቪስቶቹ የበርካቶች ህይወትን በቀጠፈው የድኅረ-ምርጫ ቀውስ መረጃ በመስጠት እና ህዝቡን በማነቃቃት ሚና ነበራቸው ሲባል ሁለተኛ ዙር ተቃውሞ እየተጠራ ባለበት ጊዜም አካውንታቸው መዘጋቱ ነው የተነገረው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 55😢 11🤔 7👎 4👏 4
Photo unavailableShow in Telegram
ጥርጣሬን ያጫረው የኬኒያ እና የአሜሪካ የጤና ዘርፍ ስምምነት
ኬንያ ከአሜሪካ ጋር የ2.5 ቢሊየን ዶላር የጤና ዘርፍ ስምምነት የተፈራረመች ሲሆን ስምምነቱ እንደ ኤችአይቪ ፣ ወባ፣ ቲቢ እና ፖሊዮ ያሉ በሽታዎችን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል ይውላል ተብሏል።
ስምምነቱን ተከትሎ የጤና ስምምነቱ የታካሚዎችን መረጃ መስጠትን ይጨምራል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ ተፈጥሯል።
ሆኖም ኬንያ የዜጎቿ የህክምና መረጃ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እንደሚቀመጥና የግል መረጃን በማይነካ መልኩ የተመረጠ መረጃ ብቻ እንደሚጋራ ገልጿል።
ኬኒያዊያን ግን የስምምነቱ ሙሉ መረጃ እንዲሰጣቸው በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመወትወት ላይ ናቸው።
ስምምነቱን የፈረሙት የአሜሪከ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ ማርክ ሩቢዮ ተመሳሳይ የጤና ስምምነቶች ከበርካታ የአፍሪካ ሃገራት ጋር እንደሚፈረሙ ተልጿል።
ከዚህ በተጨማሪ አሜሪካ ከዚህ በኋላ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ለመደገፍ ቢሊየን ዶላሮችን እንደማታወጣና ከዚህ በኋላ የገንዘብ ድጋፍ በቀጥታ ለመንግስታት እንደሚሰጥ ገልፀዋል ተብሏል።
በስምምነቱ መሰረት አሜሪካ 1.7 ቢሊየን ዶላር፣ ኬንያ ደግሞ 850 ሚሊየን ዶላር ትሸፍናለች ተብሏል።
በቀጣይም 10 የሚጠጉ የአፍሪካ ሀገራት ከኬኒያ ጋር የተደረገውን ስምምነት አይነት እንደሚፈርሙ ይጠበቃል ተብሏል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 83🤔 8👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለደቡብ ሱዳን-ኢትዮጵያ-ጂቡቲ የትራንስፖርት ኮሪደር 214.4 ሚሊየን ዶላር አፀደቀ።
አህጉራዊው የአፍሪካ ልማት ባንክ ሶስት ሃገራትን ለሚያስተሳስረውና ንግድን ያሳልጣል ለተባለው የደቡብ ሱዳን-ኢትዮጵያ-ጂቡቲ ሁለተኛው የትራንስፖርት ኮሪደር ግንባት የ214.4 ሚሊየን ዶላር ፋይናንስ አፅድቋል።
ከፋይናንሱ ውስጥ 181.5 ሚሊየን ዶላር ለኢትዮጵያ፣ 29.71 ሚሊየን ዶላሩ ለጂቡቲ እና 1.96 ሚሊየን ዶላር የሚሰጥ ይሆናል።
በኢትዮጵያ ፋይናንሱ የ67 ኪሎሜትር የፈጣን መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን ይደግፋል ሲባል የ50 ኪሎሜትር መጋቢ መንገዶችንም ያሻሽላል ተብሏል።
በጂቡቲ ፋይናንሱ የ18 ኪሎሜትር መንገድ ሲያሻሽል በደቡብ ሱዳን ሃገሪቷን ከኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ጋር ለማስተሳሰር ዋና ለሆነው የ280 ኪሎሜትር መንገድ የቴክኒክ ጥናት ይውላል።
በኢትዮጵያ 300 ሴቶችና ወጣቶች ስልጠና ያገኙበታል የተባለ አዲስ የስልጠና ማዕከል ይከፈታል ተብሏል።
ባንኩ ኮሪደሩ በሶስቱ ሃገራት መካከል ያለውን ንግድ ያሳድጋል ሲል የባህር በር የሌላቸውን ሁለቱን ሃገራት ከጂቡቲ ወደብ ጋር በማስተሳሰር ሚናው የጎላ ነው ብሏል።
በሱዳን በኩል ምርቷን ለአለም ገበያ የምታቀርበው ደቡብ ሱዳን ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ እንደፈለገችው ምርቷን መላክ ያልቻለች ሲሆን በኢትዮጵያ በኩል ከጂቡቲ ወደብ ጋር ለመተሳሰር መወሰኗ ይታወሳል።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 64👍 19👎 4🤔 4🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለደቡብ ሱዳን-ኢትዮጵያ-ጂቡቲ የትራንስፖርት ኮሪደር 214.4 ሚሊየን ዶላር አፀደቀ።
አህጉራዊው የአፍሪካ ልማት ባንክ ሶስት ሃገራትን ለሚያስተሳስረውና ንግድን ያሳልጣል ለተባለው የደቡብ ሱዳን-ኢትዮጵያ-ጂቡቲ ሁለተኛው የትራንስፖርት ኮሪደር ግንባት የ214.4 ሚሊየን ዶላር ፋይናንስ አፅድቋል።
ከፋይናንሱ ውስጥ 181.5 ሚሊየን ዶላር ለኢትዮጵያ፣ 29.71 ሚሊየን ዶላሩ ለጂቡቲ እና 1.96 ሚሊየን ዶላር የሚሰጥ ይሆናል።
በኢትዮጵያ ፋይናንሱ የ67 ኪሎሜትር የፈጣን መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን ይደግፋል ሲባል የ50 ኪሎሜትር መጋቢ መንገዶችንም ያሻሽላል ተብሏል።
በጂቡቲ ፋይናንሱ የ18 ኪሎሜትር መንገድ ሲያሻሽል በደቡብ ሱዳን ሃገሪቷን ከኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ጋር ለማስተሳሰር ዋና ለሆነው የ280 ኪሎሜትር መንገድ የቴክኒክ ጥናት ይውላል።
በኢትዮጵያ 300 ሴቶችና ወጣቶች ስልጠና ያገኙበታል የተባለ አዲስ የስልጠና ማዕከል ይከፈታል ተብሏል።
ባንኩ ኮሪደሩ በሶስቱ ሃገራት መካከል ያለውን ንግድ ያሳድጋል ሲል የባህር በር የሌላቸውን ሁለቱን ሃገራት ከጂቡቲ ወደብ ጋር በማስተሳሰር ሚናው የጎላ ነው ብሏል።
በሱዳን በኩል ምርቷን ለአለም ገበያ የምታቀርበው ደቡብ ሱዳን ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ እንደፈለገችው ምርቷን መላክ ያልቻለች ሲሆን በኢትዮጵያ በኩል ከጂቡቲ ወደብ ጋር ለመተሳሰር መወሰኗ ይታወሳል።
ዘገባው የሱዳን ፖስት ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
Photo unavailableShow in Telegram
#እንዲህም_አለ!
ጊኒ የሰራተኞችን የክፍያ አስተዳደር ስርዓት ካስተዋወቀች በኋላ 233 ቢሊየን የጊኒ ፍራንክ ማዳኗን አስታወቀች።
ጊኒ በስራ ገበታ ላይ የማይገኙ ሰዎች ደመወዝ እየበሉ ነው በሚል በ2024 እ.ኤ.አ 60 ቢሊየን የጊኒ ፍራንክ በማውጣት ለመቆጣጠር የሚያስችል ስርዓት ገንብታለች።
ስርዓቱ የሰራተኞችን ማንነት የሚያረጋግጥ ከመሆኑ በተጨማሪ የደመወዝ ክፍያን የሚያረጋግጥ እንደዚሁም ያልተለመዱ የመታወቂያ ቁጥሮችን የሚለይ ነው።
በጊኒ ከተመዘገቡት 277,000 የመንግስት ሰራተኞች መካከልም ስርዓቱ ከመጣ በኋላ 130,000 የሚሆኑት ብቻ ተረጋግጠዋል።
ስርዓቱ ወደ ትግበራ ከገባ በኋላም ጊኒ 233 ቢሊየን የጊኒ ፍራንክ ወይም 26 ሚሊየን ዶላር ማዳኗን ገልፃለች።
ዘገባው የኢኮፊን ኤጀንሲ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 97🔥 14🤔 12
Photo unavailableShow in Telegram
የካሳንቺስ አዲሱ ፕሮጀክታችን ከካሬ 80,000 ብር ጀምሮ ሽያጭ ጀምረናል!!!
እስከ ታህሳስ 29 ብቻ የሚቆይ ከፍተኛ ታላቅ ቅናሽ!
🏡 የቤቶች መጠን
• 1 መኝታ – 97.18 ካሬ
• 2 መኝታ – 120.97 ካሬ
• 3 መኝታ – 176.00 ካሬ
…እና ሌሎችም ብዙ አማራጮች ይገኛሉ!
💰 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ በመክፈል ቀሪውን በሶስት አመት የሚከፍሉት!
📩 ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይደውሉ +251936002200 093 080 7780
info@pvtcenter.com
Private Center Real Estate — Your Foundation Stone for Success
በአዲስ አበባ በኪራይ ሳጥን ንግድ ፈቃድ ያወጡ 388 ድርጅቶችን ማሸጉን የከተማው ንግድ ቢሮ ገለጸ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 በሚገኘው ኬኬር ህንፃ ውስጥ ንግድ ፍቃድ የወጣባቸው 388 ህገ- ወጥ ሳጥኖችን ማሸጉን የከተማዋ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።
ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል የተባሉት 388 የንግድ ድርጅቶች በግድግዳ ላይ በተለጠፉ ሳጥኖች ንግድ ፍቃድ በማውጣት ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ስለመገኘታቸውም ነው የተጠቀሰው።
ቢሮው አክሎም፥ ንግድ ፍቃድን በር ለበር በቴክኖሎጂ የመመዝገብ ሥራ በሳጥኖቹ ንግድ ፍቃድ በማውጣትና በውስጡ ካሽ ረጂስተር ጭምር በማስቀመጥ ህገ-ወጥ ንግድ ሲፈፀምባቸው ተደርሶበት የማሸግ ሥራ ተከናውኗል ብሏል።
እነዚህ የንግድ ፍቃዶች የኪራይ ውልና ሌሎች መስፈርቶችን በማሟላት በኦንላይን ምዝገባ የወጡ መሆናቸውን የክ/ከተማው ንግድ ጽ/ቤት ንግድ ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ሽመልስ ላቀው ተናግአዋል።
ቡድን መሪው አክለውም ከ388ቱ ሳጥኖች መካከል 228 የሚሆኑት ንግድ ፍቃድ ያላደሱ መሆናቸውን ገልፀው በተደጋጋሚ በተደረገላቸው ጥሪ መገኘት ባለመቻላቸው በበር ለበር ምዝገባ ሊደረስባቸው ችለዋል ብለዋል።
የንግድ ፍቃድ የወጣባቸው ሳጥኖችን ከማሸግ ባሻገር በቀጣይ የችግሮቹን ትክክለኛ ምክንያት በማጣራት መፍትሄ እንደሚሰጠው ነው የተገለጸው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 68🤣 23👏 7👍 5🤔 4👎 1🤯 1🤬 1
"በ09 ቁጥራቸው የተመዘገቡ ደንበኞች መተግበሪያው መግባት እና ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ እገዳ ተጥሎባቸዋል" - ኤምፔሳ ኢትዮጵያ
ኤምፔሳ ኢትዮጵያ "M-PESA ለሁሉም" የተሰኘ በማንኛውም ሲም ካርድ የሚሰራ የሞባይል የክፍያ ሥርዓት ወደ ገቢያው ማስገባቱን ከቀናት በፊት አስታውቆ ነበር።
ሆኖም ዛሬ ባወጣው መግለጫ፥ "መተግበሪያውን ለመጠቀም በ09 ቁጥራቸው በራሳቸው ፈቃድ የተመዘገቡ ደንበኞች አገልግሎቱን በኢትዮ ቴሌኮም ዳታ ተጠቅመው እንዳያገኙ ወደ መተግበሪያው መግባት እና ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ እገዳ ተጥሎባቸዋል።" ሲል አስታውቋል።
M-PESA ኢትዮጵያ አገልግሎቱን ለማስጀመር ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የከፍያ መፈጸሚያ ሰነድ አውጪ ፈቃድ (Payment Instrument Issuer License) እንደተሰጠው እና ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ተገቢውን ፈቃድ ማግኘቱን አንስቷል።
M-PESA ኢትዮጵያ ጉዳዩን የሚመለከታቸው ተቆጣጣሪ አካላት እንዲያውቁት እና ችግሩን በአስቸኳይ ለመፍታት እንዲቻል እየሰራ እንደሚገኝ በመግለጫው ላይ አንስቷል።
"M-PESA ለሁሉም" የተሰኘው መተግበሪያ በልዩ ሁኔታ ደንበኞች የሳፋሪኮም ሲም ካርድ ባይኖራቸው እንኳን አሁን በሚጠቀሙበት ስልክ ቁጥራቸው አገልግሎቱን መጠቀም የሚያስችላቸው እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 54🤣 25🤔 7👎 3🤷♂ 2
Photo unavailableShow in Telegram
"የወባ በሽታ በኢትዮጵያ ፣ ማዳጋስካርና የመን በልዩ ሁኔታ ጨምሯል" - የዓለም ጤና ድርጅት
° በ2024 ብቻ በወባ በሽታ 610 ሺህ ሰዎች መሞታቸውን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
የአለም ጤና ድርጅት የወባ በሽታ አሁንም አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሶ በ2024 610,000 ሰዎች መሞታቸውንና አብዛኛው ሞትም ከሰሃራ በታች ባለው አፍሪካ እና በህፃናት ላይ መመዝገቡን ገልጿል።
ድርጅቱ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 282 ሚሊየን ደርሷል ያለ ሲሆን ለመጨመሩ የድጋፍ መቋረጥ፣ የአየር ንብረት ለውጥና በሽታው መድሃኒት መላመዱ ምክንያት ሆኗል ብሏል።
የአለም ጤና ድርጅት በ2000ዎቹ እ.ኤ.አ በወባ በሽታ የተመዘገበው ስኬት ሊቀለበስ ይችላል ብሎ አስጠንቅቋል።
በ2024 በሽታው በኢትዮጵያ ፣ ማዳጋስካርና የመን በልዩ ሁኔታ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል።
ዘገባው የአፍሪካ ኒውስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
😢 37❤ 21👍 6🕊 3🤣 2
#አፋልጉኝ
ስም: ተፈራ ተሾመ መታፈሪያ
እድሜ: 53
ረቡዕ በቀን 24/03/2018 ዓ.ም ከሸገር ከተማ አለምገና(ኬንቴሪ) ካለው ቤቱ ለስራ ብሎ ወጥቶ አልተመለሰም።
የለበሰው ልብሴ፡ ውሃ ሰማያዊ ሱሪ፣ ጥቁር ጃኬት እና ነጭ ጫማ
ሁለት እናታቸው የሌለች ሕፃናት ልጆች አሉት
ስራ የሚሰራበት አካባቢ
ኮልፌ ፣ አጠና ተራ፣ ሽሮ ሜዳ ፣ ሰንዳፋ አካባቢዎች
ስልክ
0909668955 አብረሃም
0911505185
0989019046 በሱፍቃድ
@tikvahethmagazine
😢 72❤ 38🙏 5🔥 1
"ወደ ሁለቱ ሃገራት ታላላቆቹን ድርጅቶቻችንን እንልካለን፤ የከበሩ ማዕድናትን አውጥተን እንከፍላለን ሁሉም ብዙ ገንዘብ ያገኛል" - ትራምፕ
የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜና
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ፕረዚዳንት ፌሊክስ ሼሲኬዲ የሰላም ስምምነት በዋሽንግተን ተፈራርመዋል።
ኮንጎ፥ በሃገሯ ምስራቃዊ ክፍል ያለውን የኤም 23 ታጣቂ ኃይል ሩዋንዳ ትደግፋለች ብላ በተደጋጋሚ ትከስ የነበረ ሲሆን የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ይህንን ለማቆም ተስማምተዋል።
ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካን የሰላም ተቋም ስያሜ ወደ ዶናልድ ትራምፕ የሰላም ተቋም ከቀየሩ በኋላ ስምምነቱ በተቋሙ ውስጥ ተፈፅሟል።
ትራምፕ ስምምነቱን ለአፍሪካና ለአለም ትልቅ ቀን ሲሉ የገለፁ ሲሆን የሁለቱን ሃገራት መሪዎችም ብልህ ሲሉ ገልፀዋል።
በስምምነቱ መፈረም ወቅት በትራምፕ ግብዣ የኬንያውን ፕሬዚዳንት ጨምሮ የአንጎላ፣ የቡሩንዲ እና የቶጎ መሪዎች ሲገኙ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት እንደዚሁም የኳታር እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።
ፖል ካጋሜ ትራምፕ ወገንተኛ ስላልሆኑ ስምምነቱ ተፈፅሟል ያሉ ሲሆን ፌሊክስ ሼሴኬዲ ሩዋንዳ ስምምነቱን ታከብራለች ብለን እንጠብቃለን ብለዋል።
በስምምነቱ የአማፂው ኤም 23 ሳይካፈል ሲቀር፥ ትራምፕ አሜሪካ ማዕድናትን ከሁለቱም ሃገራት ለመግዛትም የሁለትዮሽ ስምምነት ታደርጋለች ብለዋል።
ትራምፕ " ወደ ሁለቱ ሃገራት ታላላቆቹን ድርጅቶቻችንን እንልካለን፤ የከበሩ ማዕድናትን አውጥተን እንከፍላለን ሁሉም ብዙ ገንዘብ ያገኛል" ብለዋል።
የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት በ2023 ባወጣው መረጃ ኮንጎ ብቻዋን 25 ትሪሊየን ዶላር የሚያወጣ የማዕድን ክምችት አላት።
ግጭቱ ያለበት የምስራቃዊ ኮንጎም በማዕድን የበለፀገ እንደሆነ እና ታጣቂው ጭምር በህገወጥ መንገድ አውጥቶ ራሱን የሚያጠናክርበት እንደሆነ ይታወቃል።
ዘገባው ከቢቢሲ እና አልጄዚራ የተገኘ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 50🤣 25😢 15👎 4
