2025 سال در اعداد

163 169
مشترکین
+324 ساعت
+1157 روز
+40130 روز
آرشیو پست ها
ዛሬ በክረምት በጎፈቃድ መርሃግብር በሀዲያ እና ከምባታ ዞኖች የተገነቡ ሞዴል የገጠር መንደሮችን አስረክበናል። እነኚህ መንደሮች የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮችን ሕይወት ለማሻሻል የምናደርገው ጥረት ተስፋ ሰጪ ጅማሮ ናቸው። ቤቶቹ የፀሃይ ኃይል ማመንጫ የተገጠመላቸው፣ ለማብሰል ደግሞ ከእንስሳት እዳሪ ባዮጋዝ የሚጠቀሙ፣ የተለየ ሳሎን፣ መጸዳጃ እና ሰርቪስ ቤቶች የተሟላላቸው ናቸው። ንጽህናን በሚያረጋግጥ እና የአኗኗር ደረጃን ከፍ በሚያደርግ አኳኋን የተለየ የእንስሳት በረት ተሰርቶላቸዋል። እነዚህ የገጠር ኮሪደር ልማት መንደሮች የገጠሩን አኗኗር የማሳደግ ሕልማችን አካል በመሆን ተስፋፍተው የሚሰሩ ይሆናል።
ባለፉት ሰባት አመታት የክረምት በጎ ፈቃድ በከተሞች ለሚኖሩ ለችግር የተጋለጡ ወገኖች መኖሪያ ቤቶችን ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ በገጠር ኮሪደር ልማት የሥራውን እመርታ ወደገጠር አስፋፍተናል። ግለሰቦች፣ ድርጅቶች እና የዲያስፖራው ማኅበረሰብ እነኚህን ሥራዎች እንዲደግፉ እና እንዲሳተፉ አበረታታለሁ።
ባለፈው ጉብኝቴ ወቅት ያቀረብኩላቸውን የቤትሥራ በመወጣት በአጭር ጊዜ ውስጥ በራስ አቅም የሀምበሪቾ ተራራ ደረጃንም በእጥፍ ሠርተው ላጠናቀቁት አመራሮች ያለኝን ምስጋና አቀርባለሁ። ወደፊትም የየአካባቢ አመራሮች ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሠሩትን ሞዴል መንደሮች በመጪው አመት በየዞኑ ወደ100 ቤቶች እንዲያሳድጉ አሳስባለሁ።
16:10
Video unavailableShow in Telegram
በእናንተ ገንዘብ ሀገር እየተሰራች መሆኑን ዳግም በኩራት ልገልጽላችሁ እወዳለሁ።
24.74 MB
የ7ኛው የታማኝ ግብር ከፋይ እውቅና ሥነሥርዓት ተሸላሚዎች እንኳን ደስ አላችሁ።
ባለፈው ዓመት የምታዋጡት ግብር ለጋራ እድገት እና ለሕዝባዊ ጠቀሜታ በሚውሉ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ እንደሚውል ቃል ገብተን ነበር። ዛሬ በከተማችን ኮሪደሮች የሚታየው ለውጥ ለዚያ ቃላችን ሕያው ምስክር ሆኖ ይታያል። አስታውሱ፣ የዛሬ ጥረታችሁ የነገን ትውልድ የተሻለ መፃኢ እድል እየቀረፀ ነው። ሙስናን እና ሌብነትን ለማስወገድ በምናደርገው ጥረት ሥርዓቶቻችንን ማጠናከራችንን እንቀጥላለን። ግብር ከፋዮችም በመሰል ጎጂ ተግባር የተሠማሩ ሰዎችን ባለመተባበር እንዲያግዙ አሳስባለሁ። በጋራ ግልጽ፣ ተጠያቂነት የሰፈነባት እና የበለጸገች ሀገር እንገነባለን።
10:55
Video unavailableShow in Telegram
Pulse of Africa የአፍሪካ ድምፅ ነው። የአፍሪካ ምስል መገለጫ ነው። የአፍሪካ ባህል መገለጫ ነው። የአፍሪካ ሀብት መገለጫ ነው። ኢትዮጵያ አንሠራርርታ አፍሪካ የምታንሠራራበትን መንገድ አብረን ካልሰራን በቀር ብቻችንን ማደግ ስለማንችል ከአፍሪካ ወንድሞቻችን ጋር በሁሉ ነገር በትብብርና በመደመር በጋራ እንድንቆም Pulse of Africa ሚናውን እንዲጫወት ከአደራ ጭምር ላሳስባችሁ እወዳለሁ።
16.41 MB
የPulse of Africa ሚዲያ ሥራ መጀመር አፍሪካን በአሉታዊ ገጽታ የማቅረብ ሥራን ለመመከት ብሎም የራሳችንን ትርክት በራሳችን የመቅረጽ ተግባራችንን የምናፀናበት ጠቃሚ ርምጃ ነው። ምንም እንኳ አፍሪካ ሰፊ እና እምቅ ሀብት ያላት አኅጉር ብትሆንም አብዛኛውን ጊዜ እንደ አነስተኛ እና አቅመቢስ ተደርጋ ትሳላለች። በዚህ የተነሳ ነው አነስተኛ ግን እጅግ ትርጉም ያለው የPulse of Africa ጅማሮ በመጪዎቹ ጊዜያት ከፍ ወዳለ መሪ አኅጉራዊ ሚዲያ የማደግ መንገድ እጅግ ጠቃሚ የሚሆነው።
አፍሪካ ዐቢይ የኢንደስትሪ ማዕከል እና የአለም ቁልፍ ሚና ተጫዋች የመሆን መንገድ ላይ በማያጠራጥር መንገድ እየተጓዘች ትገኛለች። የPulse of Africa መቋቋም ወደፊት የመመልከት ርምጃ ነው። በአለም መድረክ ጠንካራ እና ቱባ የአፍሪካ ድምፅ የማሰማት መሠረትም ነው።
በሶማሌ ክልል ካሉብ በአመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀናል። በተመሳሳይም በአመት 1.33 ቢሊዮን ሊትር የማምረት አቅም የሚኖረውን ሁለተኛውን ዙር አስጀምረናል። ከፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ ምርት ባሻገር በኃይል ማመንጫ ዘርፉም 1000 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም በመያዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
ከሁሉም በላይ ፕሮጄክቱ የጋዝ ማምረቻ ብቻ አይደለም። ለማዳበሪያ ማምረቻ ወሳኝ የሆነውን ግብዓት በማቅረብ ለምግብ ሉዓላዊነት ጥረታችን የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ ያገለግላል። ለኃይል ማመንጫ እና የክሪፕቶ-ማይኒንግ ሥራዎቻችን አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ያቀርብልናል። ዛሬ በሶማሌ ክልል የጀመርናቸው ከተያያዠ መሠረተ ልማቶች ግንባታ ጋር በአጠቃላይ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች በተገቢ ክትትል እስከ መጠናቀቂያቸው ይደርሳሉ። የጀመርነውን ለመጨረስ ሁልጊዜም በጽናት እንደሠራነው ሁሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት ይደርሳሉ።
ዛሬ ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ የሚያኮራ ታሪካዊ ሁነት ተፈፅሟል። የሁለት አሻጋሪ ፕሮጀክቶች የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠናል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር የሚገነባው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና በጎልደን ኮንኮርድ ግሩፕ የሚገነባው የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ መሠረት አስቀምጠናል።
የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ከሂላል የነዳጅ ስፍራ ድፍድፍ ነዳጅ በማውጣት፣ በማጣራትና በማጠራቀም በአመት 3.5 ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም አለው። በሌላ በኩልም የማዳበሪያ ፋብሪካው ከካሉብ የጋዝ ስፍራ በማውጣት እና 108 ኪሎሜትር የማጓጓዣ ቱቦ በመጠቀም በአመት 3 ሚሊዮን ቶን አምርቶ ያቀርባል።
እነዚህ ፕሮጀክቶች የኢንደስትሪ እድገትን ከማሳየት በላይ ናቸው። እድሎቻችንን የመጠቀም፣ ትብብሮችን የማጠናከር እና ሰላምን የማጽናት የጋራ ኃላፊነታችንን የሚያሳዩ ናቸው። በመሆኑም ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በኅብረት እና በአንድነት ለእድገት መሰባሰባችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ጥሪ አቀርባለሁ። ይኽን ስናደርግ እውነተኛውን የኢትዮጵያዊ ማንነት መንፈስ በሚያከብር መንገድ በአለም መድረክ የኢትዮጵያን ስፍራ ከፍ እናደርጋለን።
ዛሬ የተመለከትናት ጂግጂጋ ባለፈው ጥር ከተመለከትናት ይዞታዋ በሚታይ መልክ የተቀየረች ናት። በመላው ከተማዋ በሺሆች የሚቆጠሩ አዳዲስ መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ ሲሆን በኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች በሁሉም አካባቢ የመኖሪያ ሁኔታን በግልጽ እያሻሻሉ ይታያሉ። የከተማ ማዕከሎቻችንን ስናዘምን የምንገነባው ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገም መሠረት እያኖርን መሆኑን መገንዘብ ይገባናል። ርዕያችን እንደኢትዮጵያዊ እና አፍሪካዊ ጠቃሚ በሆኑልን ጉዳዮች ላይ የተተከለ መሆኑን ማስታወስ ይገባናል።
በዚህ መንፈስ የሶማሌ ክልል በቱሪዝም አዳዲስ እድሎችን እየከፈተ ይገኛል። ወደመጠናቀቂያ ምዕራፍ በደረሰው የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ለምስራቁ የሀገራችን ክፍል አዲስ ዋጋ የጨመረ እድል እየፈጠረ ነው። በአጠቃላይም የተመለከትነው የሥራ እድገት በጂግጂጋ እና በመላው ክልሉ የሚስተዋለውን መነቃቃት የሚገልጽ ነው።
02:46
Video unavailableShow in Telegram
I sincerely hope our next meeting will be in Addis Ababa
23.87 MB
ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በተለያዩ ዘርፎች ላይ አጠቃላይ ውይይት አካሂደናል። እነዚህም የኃይል ማመንጫ፣ ግብርና፣ የጤና ጥበቃ ልማት እና የመከላከያ ትብብርን ያካትታሉ። በተለይም ለማኅበረሰብ አገልግሎት የሚውል ንፁህ ኃይል ለማቅረብ የጋራ የኒኩሊየር ኃይል ማመንጫ ለማልማት ስምምነቶችን በመፈራረም የጋራ ፍላጎቶቻችንን የሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ ተማክረናል።
I held comprehensive discussions with President Vladimir Putin on various sectors, including energy, agriculture, healthcare development, and defense cooperation. Notably, we deliberated on shared interests, including the signing of agreements to jointly develop a nuclear power plant to provide clean energy for societal benefit.
