አዲስ ነገር መረጃ
رفتن به کانال در Telegram
#አዲስ_ነገር_መረጃ #መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ Addis Ababa , Ethiopia Buy Ads : https://telega.io/?r=UbutLo2z #ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

103 408
مشترکین
-5124 ساعت
-3077 روز
+12730 روز
آرشیو پست ها
ግብፅ በአሰብና ጅቡቲ ወደቦችን ለመገንባት ስምምነት ላይ መድረሷ ተገለፀ፡፡
ዘናሽናል ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው ግብፅ የአፍሪካ ቀንድ አካል ከሆኑት ኤርትራና ጅቡቲ ጋር ወደቦችን ለመገንባት ስምምነት ፈፅማለች፡፡
እንደዘገባው ይህ ስምምነት ግብፅ በአባይ ወንዝ ጉዳይ በገባችበት ውዝግብ በኢትዮጵያ ላይ እያካሄደች ያለው ጫና አንዱ አካል ነው፡፡ ቅርበት ያላቸው ምንጮቹን በዋቢነት የጠቀሰው ዘገባው ግብፅ እንብዛም የሚዲያ ሽፋን ባልተሰጠውና ባልተወራለት መንገድ ከሁለቱ አገራት ጋር የፈፀመችው የስምምነት ፊርማ የኤርትራውን አሰብ ወደብንና የጅቡቲውን ዶራሌ ወደብ ‹‹አቅም ማሳደግ›› የሚል መሆኑን አስረድቷል፡
፡ ሁለቱም ወደቦች በቀይ ባህር ደቡባዊ ክፍል ባብ አልመንደብ ሰርጥ አቅራቢያ የሚገኙ መሆናቸውን የጠቀሰው ዘገባው ጅቡቲና ኤርትራ የኢትዮጵያ ጎረቤቶች ከመሆናቸውም በላይ ኢትዮጵያ ሸቀጦችን የምታስገባው በዶራሌ ወደብ መሆኑን አውስቷል፡፡ ዘገባው ሲቀጥልም ‹‹ግብፅ በቀይ ባህር ላይ ከ2 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ጠረፍ ያላትና ቀይባህርንና ሜዲትራኒያንን የሚያገናኘውን ስዊዝ ካናል የተቆጣጠረች አገር ናት›› ካለ በኋላ በተደጋጋሚ እንደኢትዮጵያ ያሉ የባህር በር የሌላቸው አገራት ወደቀይ ባህር ለመዳረስ የሚያደርጉትን ጥረት ስትቃወም መቆየቷን አስረድቷል፡፡
ዘናሽናል በዘገባው ይህ ብዙ ያልተወራለት ስምምነት ከኤርትራ ጋር የተፈፀመው ከአንድ ወር በፊት ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በካይሮ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት መሆኑን አስታውቆ፣ ግብፅና ጅቡቲ ግን በከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል መፈራረማቸውን አስረድቷል፡፡ እነዚህ ስምምነቶች ከሁለቱም አገራት ጋር ጠንካራ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት የመሰረተችው ግብፅ በወደቦቹ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንድታደርግ የሚያስችላት እንደሚሆንም ገልጿል፡፡ የዘገባው ምንጭ ሲናገሩ ‹‹ይህ ስምምነት በሁለቱ ወደቦች ላይ እያደረግነው ያለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ህጋዊ መሰረት እንዲኖረው ያስችለናል›› ማለታውንም ከጋዜጣው ላይ ተመልክተናል፡፡
@Addis_News
@Addis_News
❤ 18😢 10🤪 7🔥 4
በዲጂታል የክፍያ ተቋማት ላይ ተጥሎ የነበረው የባንክ እገዳ በከፊል ተነሳ‼️
- ከፍተኛ የንግድ ድርጅቶች ኃላፊዎች አሁንም በቁጥጥር ሥር ናቸው
የፌዴራል ባለሥልጣናት በዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ ላይ በወሰዱት እርምጃ ታግደው የነበሩ የባንክ ሂሳቦችን በከፊል አንስተዋል።
የፍትህ ሚኒስቴር ታኅሣሥ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ባስተላለፈው ትዕዛዝ፣ የያጉት ፔይ (YagoutPay) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተሾመ ዓለማየሁን ጨምሮ የ50 ግለሰቦች የባንክ ሂሳቦች እንዲንቀሳቀሱ አዟል። እነዚህ የባንክ ሂሳቦች ከሦስት ሳምንታት በፊት፣ ህዳር 23 ቀን፣ በዘርፉ የታየ የፋይናንስ ብልሹ አሰራርን ለመመርመር በሚል ታግደው የቆዩ ናቸው።
በተጨማሪም፣ ለዘጠኝ ቀናት የባንክ ሂሳቦቻቸው ተገድበው የነበሩ 10 የዲጂታል ክፍያ (Gateway) ኩባንያዎች እገዳው ተነስቶላቸዋል።
የሚኒስቴሩ የሀብት ማስመለስ መምሪያ ዋና ዳይሬክተር ፀጋ ዋቅጅራ ውሳኔውን ለሁሉም ባንኮች በይፋዊ ደብዳቤ አሳውቀዋል።
እገዳው የተነሳላቸው የክፍያ ተቋማት አሪፍ ፔይ (ArifPay Financial Technologies): አዲስ ፔይ (AddisPay Financial Technologies): ፈናን ፔይ (FenanPay Solutions): ላኪ ፔይ (LakiPay Financial Technologies):
ስታር ፔይ (StarPay Financial Services): ያጉት ፔይ (YagoutPay)
ሳንቲም ፔይ (SantimPay Financial Technologies): ካቻ (Kacha Financial Technology): እና ሲናን ፔይ (Sinan Pay Solutions) ናቸው::
ምንም እንኳን የኩባንያዎቹ የባንክ ሂሳቦች ቢለቀቁም፣ የምርመራው ሂደት ግን ተጠናክሮ ቀጥሏል። የሳንቲም ፔይ፣ የቻፓ ፔይ (Chapa Pay) እና የአሪፍ ፔይ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አሁንም በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ሲሆን፣ “ከፍተኛ የፋይናንስ ሕገ-ወጥነት” ተጠርጥረው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው።
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደጠቆሙት፣ የምርመራው ዋነኛ ትኩረት የግብር ስወራ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር (Money Laundering) ላይ ነው። የፌዴራል ባለሥልጣናት በፍጥነት እያደገ የመጣውን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ጥብቅ ቁጥጥር ለማድረግና ሕጋዊ መስመር ለማስያዝ ቅድሚያ ሰጥተው መስራት እንደሚፈልጉ ይናገራሉ።
@Addis_News
@Addis_News
❤ 14😢 2
ፕሬዝደንት ጣሂብ ኤርዶጋን እስራኤል “ቃሏን አላከበረችም” ሲሉ ወቀሱ
የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲብ ጣሂብ ኤርዶጋን “እስራኤል የገባችውን ቃል አላከበረችም፤ ሰብዓዊ እርዳታ ወደጋዛ እንዳይደርስ ሆን ብላ እንቅፋት እየፈጠረች ነው” ሲሉ እስራኤልን ወቅሰዋል።
ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ይህን ያሉት ትናንት ረቡዕ እርሳቸው የሚመሩት የፍትሕና ዕድገት ፓርቲ የግዛት አስተዳዳሪዎች ስብሰባ በአንካረ በተካሄደበት ወቅት ሲሆን፤ “እስራኤል የገባችውን ቃል እያከበረች አይደለም፤ የተፈበረኩ ማስተባበያዎችን በማቅረብ ሰብዓዊ እርዳታ ወደጋዛ እንዳይገባ ሆን ብላ ችግር እየፈጠረች፤ የሰብዓዊ እርዳታ ሂደቱንም በተደጋጋሚ እያስተጓጎለች ነው” ሲሉ እስራኤልን ወንጅለዋል።
“በእነዚህ አስደሳች ሦስት ወራት ለፍልስጤም የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን፤ እንደቱርክ የገባነውን ቃል አናጥፍም፤ ዝም አንልም፤ አንረሳትም፤ መቼም ቢሆን ጋዛን ብቻዋን አንተዋትም” ሲሉም አክለዋል።
“ከካውካስ እስከ ባልካን፣ ከአፍሪካ እስከ እስያ፣ ማንም ቢሆን በችግር ላይ ሆኖ እርዳታ በሚፈልግበት ጊዜ እኛ ቀድመን እዚያ እንገኛለን። ይህ ትናንት የነበረ፤ ዛሬም ያለ ነገም የማይቀየር የእኛ አቋም ነው” ያሉት ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ቱርክ ለፍልስጤም የምታደርገው ድጋፍ ሀገሪቱ በዓለም አቀፉ ደረጃ የምታራምደው የሰብዓዊ እርዳታ ፖሊሲዋ አንድ አካል መሆኑንም አመልክተዋል።
ቱርክ ሰላምን የምትደግፍ ብትሆንም ኢ-ፍትሐዊነትን ግን እንደማትቀበልም ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን አጽንኦት ሰጥተውበታል።
“ጥንት እንደምናደርገው ሁሉ ዛሬም ለሰላም ያለንን ፍላጎት ሁሉም ሊያውቀው ይገባል። ይህ ማለት ግን ከኢ-ፍትሐዊነት ጋር እናብራለን፤ ጭቆናንም እንታገሳለን ማለት አይደለም፤ ይህን ፈጽመን አናደርገውም” ሲሉም አቋማቸውን አስረግጠዋል።
Addis maleda
@Addis_News
@Addis_News
❤ 18🤣 6😨 1
Photo unavailableShow in Telegram
Ethio-Telecom Jobs 2025 ✅
---—----------------------------
♨️ እንኳን ደስ አላችሁ ለመላው ለስራ ፈላጊ ኢትዮጲያዊያን!
✅ ከ 600- በላይ ክፍት ቦታዎች በ0 አመት እና በልምድ
✅ Number of Positions: 600+
✅positions 0 EXP and with Exp
🔺የትምህርት ደረጃ: በሁሉም የትምህርት ደረጃ
🔺የትምህርት አይነት: በተለያዩ ዲፓርትመንቶች
🔺ቦታ: በተለያዩ የኢትዮጲያ ከተማዎች
🔺የስራ ልምድ: በ 0 ዓመትና በልምድ
🔺 የቅጥር ሁኔታ: በቋሚ ቅጥር
🔺 ብዛት: 600+ በላይ
🔺ደሞዝ: ማራኪ
🟥 ፈጥነው ታች ባለው ሊንክ ይመዝገቡ
⁉️ማሳሰቢያ:- VPN ወይም Psiphon መጠቀም ይኖርባችሗል
👇👇👇👇👇Apply Now👇👇👇👇👇👇
👇👇👇👇
https://reportervacancy.com/ethiotelecom-job-vacancy-2025-apply-now/
--------Follow Our Website--------
👇👇👇👇👇👇
https://reportervacancy.com
--------Join Our Telegram---------
👇👇👇👇👇
https://t.me/reporter_Vacancy
❤ 1
የአባቴን ንብረት ይወርሳል በሚል ቅናት የእህቱን ልጅ ገድሎ ጫት እርሻ ውስጥ የቀበረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ደደር ወረዳ ነዎሪነታቸው የሆኑት አቶ አህመድ ሙነር የሰባ ሶስት አመት አዛዉንት ሲሆኑ በትዳር ህይወታቸውም አንድ ወንድ እና ሴት ልጅ አፍረተዋል።የህግ ባለቤታቸው በህመም ምክንያት በሞት ሲያጡ ልጆቻቸውን ብቻቸውን ማሳደጋቸው የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ካሲዬ አበበ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።አቶ አህመድ ሙነር ልጆቻቸውን በዚህ መልክ እያሳደጉ እያለ ሴት ልጃቸው ከጋብቻ ውጭ ታረግዝና ዘመዶች ጋር በድብቅ ወልዳ ታርሳ እንደመጣችም ተነግሯል።
የተወለደው ልጅ አያት ተቀብለው የአባት መጠሪያ ስምን በራሳቸው አድርገው ፈንዲሼ አህመድ እዚያው ቤተሰብ ማደግ ጀምሯል። ከዓመታት በኋላ ግን የአቶ አህመድ ሴት ልጅ ለጋብቻ ትታጭ እና በሰርግ ድግስ ትዳር መስርታ ከአባቷ ቤት ትወጣለች። ወንድሟ ኤልያስ ግን በተለይ አባት ያላቸውን ንብረት እና ሀብት የሚካፈሉት እህቱ እና ልጇ መሆኑን ሲረዳ የአስራ አምስት ዓመቱን ወንድሙን የእህቱን ልጅ አምርሮ ጠላው።ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም አባቱን እና ወንድሙን ስራ ፍለጋ ወደ ከተማ እንደሚሄድ ነግሯቸው ከቤት ወጥቶ ይሄዳል።
ከሳምንታት በኋላ ግን ስራ በመጥፋቱ ወደ አያቱ ቤት እየተመለሰ ያለው ፈንድሼ አህመድን ኤልያስ አህመድ ጠብቆ በስለታም ሳንጃ የተለያዪ የሰውነት ክፍሎችን በመውጋት ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጎ አስክሬኑን ደብቆ ካዋለው በኋላ በነጋታው የአያቱ የጫት እርሻ ውስጥ በድብቅ ቀብሮ ሰላማዊ ሰው ሆኖ ይቀመጣል።ከበርካታ ወራት ቡኃላ የፈንዲሻ ለስራ ፍለጋ ከቤት ወጥቶ መቅረት ያሳሰባቸው አባት በተለያየ ጊዚያት ሲያፈላልጉ እሱን የሚያዉቁ ሰዎች ስራ በመጥፋቱ ተመልሶ ወደ ቤቱ እንደተመለሰ ቢገልጹም አድራሻው ሊገኝ አልቻለም ።ይሁን እንጂ በኤልያስ እና በፈንዲሼ መካከል ያለው የመጠላላት ስሜት እንዲሁም ስለመጥፋቱ ሲነሳ የሚሰጠው ተቃራኒ መልስ አያት በልጃቸው ላይ ጥርጣሬ እንዲያሳድሩ አድርጓል። በዚህም አባት ልጃቸው ኤልያስን በአካባቢው ባለው የሀገር ሽማግሌዎች የአውጫጭኝ ስርዓት ላይ እንዲቀርብ ሲጠየቅ ፈቃደኛ ያለመሆን አዝማምያ ሲያሳይ ጉዳዩን ፖሊስ ጋር እንዲደርስ ተደረገ።
የደደር ወረዳ ፖሊስም በቀረበው መረጃ መሰረት ኤልያስ መሀመድን በቁጥጥር ስር አድርጎ ሲመረምር ኤልያስ ከአባቴ ያልተወለደው ልጅ ከእናቱ ጋር ሆኖ የአባቴን ንብረት ይወርሳል በሚል ቅናት ስራ እፈልጋለሁ ካለበት ቦታ ከሳምንት በኋላ ሲመለስ ጠብቄ ገድዬ የጫት እርሻው ስጥ ቀብርያለሁኝ በማለት የእምነት ቃሉን ይሰጣል።በተጨማሪም ለወራት በጫት እርሻ ውስጥ የተቀበረው የ15 ዓመቱ ኤልያስ አህመድ አስክሬን ከተቀበረበት ተቆፍሮ በመውጣት ለምርመራ ወደ ሆስፒታል ተልኮ ከተመረመረ በኋላ በክብር እንዲያርፍ ተደርጓል ሲሉ ምክትል ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ ገልፀዋል።ፖሊስም የምርመራ መዝገቡን በአስክሬን ምርመራና በእምነት ቃሉ እንዲሁም የወንጀል ድርጊቱን ሲመራ በነበሩ ማስረጃዎች ተጠናክሮ ለአቃቢ ህግ ልኳል፡፡ አቃቢ ህግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ መስርቷል። ክሱን ሲከታተል የቆየው የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ታህሳስ 9 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ኤሊያስ አህመድ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
Dagu
@Addis_News
@Addis_News
❤ 15👍 5😢 5
Photo unavailableShow in Telegram
🌟🌟ታላቅ የበዓል ቅናሽ በካሬ 78,000 ብር
✅እንዲሁም ሙሉ ክፍያ ለሚከፊል በካሬ 54,800
🔷 በ10 % ቅድመ ክፍያ
🔷 50 % የባንክ ብድር የተመቻቸለት
📍Location እንግሊዝ ኢንባሲ አጠገብ ውብ እይታ (Top View) ያላቸው ቤቶች በሽያጭ ላይ እንገኛለን
👉ከባለ 2 መኝታ- ባለ4 መኝታ
✅ ህንፃው ላይ ያሉ ተጨማሪ አገልግሎትች
👉5 ሰፋፊ ሊፍት /elevator
👉የቆሻሻ መጣያ/garbage chute
👉አውቶማቲክ ጀኔረተር/ automatic generator
👉ሰገነት/terrace
👉የመኪና ማቆምያ/car parking
👉 ጂም , እስፖ
👉 የዋና ገንዳ
👉 የልጆች መጫወታ
✨ባለ 2 መኝታ
138 ካሬ
157.3 ካሬ
163.6 ካሬ
✨ባለ 3 መኝታ
152.4 ካሬ
158.1 ካሬ
187.6 ካሬ
211.5 ካሬ
✨ባለ 4 መኝታ
240.7 ካሬ
258.4 ካሬ
📞 ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
0973559591
0919489575
Telegram -@Homef17
❤ 3
Photo unavailableShow in Telegram
ቲክቶከሩ ታኩር በደብረ ብርሃን መጠለያ ለሚገኙ ለመቋቋም በሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ባለሃብቱ አቶ ወርቁ አይተነው ለተፈናቃዮች 15 ሚሊዮን በሰጡበት ወቅት ለቲክቶከሩ ታኩር የ5 ሚሊዮን ብር መኪና ገዝተው እንደሚሰጡት ቃል ገብተውለታል።
👏 81❤ 15👍 13
Photo unavailableShow in Telegram
#መረጃ
የጋምቤላው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ተገለፀ።
ዓለማቀፉ የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን (ኤም ኤስ ኤፍ)፣ በጋምቤላ የተቀሠቀሠው ግጭት በትናንትናው ዕለት ተባብሶ መቀጠሉን አስታወቀ።
ቡድኑ፣ ትናንት ረቡዕ ብቻ ከ100 በላይ "በመሳሪያ የቆሠሉ" ሰዎችን ተቀብሎ ማከሙን ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
ባለፈው ሳምንት ረቡዕ በግጭቱ ለቆሠሉ ታካሚዎች ኩሌ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ የሕክምና እርዳታ መስጠት በጀመረ በ48 ሰዓት ውስጥ ከባድ የመቁሰል አደጋ የደረሠባቸውን 19 ሰዎች ጨምሮ 50 ቁስለኞችን ማከሙን የገለጠው ቡድኑ፣ ባለፉት 7 ቀናት ከ150 በላይ ቁስለኞችን ተቀብያለሁ ብሏል።
ግጭቱ ከጀመረ ወዲህ የበርካቶች ሕይወት መጥፋቱን፣ የአካል ጉዳት መድረሱንና ግጭቱ በዚሁ ከቀጠለ ወደ ሕክምና ጣቢያው የሚገቡ ቁስለኛ ታካሚዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ቡድኑ ገልጧል።
ቡድኑ፣ በቁስለኞች ብዛት ሳቢያ የጋምቤላ ከተማ ሆስፒታል ሳምንቱን ሙሉ የተመላላሽ ሕክምና አገልግሎት ማቆሙንና ሌሎች የሕክምና አገልግሎቶችም መስተጓጎላቸውን ጠቅሷል።
የሲቪሎች ደኅንነት "በጥልቅ" እንዳሳሰበው ቡድኑ የገለጠ ሲሆን፣ የታካሚዎች፣ የጤና ባለሙያዎችና የሕክምና ተቋማት ከጥቃት እንዲጠበቁም ጥሪ አድርጓል። [ዋዜማ] #Gambella
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 12🔥 5😢 1
ግንኙነታችሁ ረጅም ጊዜ እንዲቆይ ከትዳር አጋራችሁ እነዚህን 5 ነገሮች መጠየቅ አቁሙ
ብዙ ሰዎች አጋሮቻቸው የፈለጉትን ያህል ፍላጎታቸውን ስላማያሟሉላቸው ብስጭት ይሰማቸዋል። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን፣ እያንዳንዱ አጋር የማይጨበጡ ፍላጎቶችን መተው ሲችል የፍቅር ግንኙነቱ ይበልጥ ቀላል ይሆናል።
Your Tango ላይ እንፈሰፈረው ፣ አጋሮች በትዳራቸው ወይም በፍቅር ግንኙነታቸው ውስጥ ሁሌ ሊጠይቋቸው የማይገቡ አንዳንድ ነገሮች እኝህ ናቸው;
1. ሁልጊዜ ሃሳብን እንዲረዱ መጠበቅ
በግንኙነቶች ውስጥ ለግጭት መንስኤ ከሚሆኑ ነገሮች አንዱ፣ አጋርዎ ሳይነገረው ሁልጊዜ ውስጣችሁን እንዲረዳ መጠበቅ ነው። እንዲያውም፣ በግልጽ መነጋገር በውል ካልታወቁ ምልክቶች (codes) የበለጠ ውጤታማ ነው። የሚሰማዎትን በግልጽ መናገር ሲጀምሩ፣ "አልተረዳሁም" በሚል የሚመጣው ብስጭት ይቀንሳል።
2. አጋርዎን ለመለወጥ መሞከር
አስከፊ ጉዳት የሌለውን የአጋርዎን ስብዕና ወይም ልምዶች ለመለወጥ መሞከር በጣም አድካሚ ነው። በተጨማሪም፣ ይህ ድርጊት አጋርዎ አክብሮት እንደሌሎት ሊያደርግ ይችላል። አጋርዎ እርስዎ በሚፈልጉት መንገድ እንዲለወጥ ከመገፋፋት ይልቅ፣ መቀበልን ይለማመዱ።
3. ብቸኛው የደስታ ምንጭ እንዲሆኑ ማድረግ
አጋርዎ እርስዎን ደስተኛ የሚያደርግ ብቸኛው ሰው እንዲሆን መጠበቅ በራስዎም ሆነ በግንኙነቱ ላይ ሸክም ይፈጥራል። እያንዳንዱ ሰው ከትዳር አጋሩ ውጪ እንደ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች ያሉ የግል ነጻነቶች ሲኖሩት የፍቅር ግንኙነቱ ይበልጥ ጤናማ ይሆናል።
አጋርዎ የደስታዎ ማሟያ እንጂ ብቸኛው የደስታዎ ምክንያት መሆን እንደሌለበት ያስቡ።
4. እንደ የፍቅር ታሪኮች (ፊልሞች) እንዲሆኑ መጠበቅ
የፍቅር ታሪኮች ብዙውን ጊዜ እውነታዊ ያልሆኑ ክስተቶችን ያሳያሉ፤ በእውነተኛ ህይወት ግን ነገሮች እንደዛ ላይሆኑ ይችላሉ። ዘላቂ ግንኙነት የሚገነባው ከአጋርዎ የሚመጡ ትንንሽ ነገሮችንም ጭምር በመቀበል እና በማድነቅ ነው።
5. አጋርዎ ሁልጊዜ በእርስዎ ሃሳብ እንዲስማማ መፈለግ
በግንኙነት ውስጥ የሃሳብ ልዩነት መፈጠሩ የተለመደ ነው። አጋርዎ በሁሉም ነገር ላይ እንዲስማማዎት ሁልጊዜ አያስገድዱ። ግንኙነቱ ጤናማ እንዲሆን የአጋርዎ አመለካከት ምንም ይሁን ምን ማክበርን ይማሩ።
የማይጨበጡ ነገሮችን መጠየቅ በማቆም፣ አጋርዎ በቅንነት እንዲወድዎት ዕድል ይሰጡታል።
@Addis_News
@Addis_News
❤ 22
አባቶቻችን የሃዘን ብዛት የእንባ ጎርፍ አይን ያጠፋል፣ ፊት ያንጣጣል፣ ልብ ይሰውራል አካልንም ያዝላል ይላሉ፡፡
እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጌታችን ምክንያት ያገኛት ሃዘን እጅግ መራራ ነው፡፡ በምድረ ግብጽ በስደቷ ያፈሰሰችው እንባ ስፍር ቁጥር የለውም፡፡ ጌታችን ከተያዘበት ከምሴተ ሐሙስ ጀምሮ በግርፋቱ፣ በስቅለቱና በሞቱ እስከ ትንሣኤው ድረስ አልቅሳለች፡፡ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላም በጎልጎታ በልጇ መቃብር ላይ “ልጄ ወዳጃ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ፣ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው ስለመሆንህ፣ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስለቻለችህ ማኅፀኔ፣ ከአንተ ጋር ከሀገር ወደ ሀገር ስለመሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡” በማለት ወደእርሱ ወደተወዳጅ ልጇ ስለኛ ስለሰው ልጆች ፍጹም ልመና አቅርበለች፡፡ ጸልያለች፡፡ ጌታችንም እልፍ አእላፍ መላእክት ጋር መጥቶ “እናቴ ማርያም ሰላም ላንቺ ይኹን! እንዳደርግልሽ የምትለምኚኝ ምንድን ነው?” አላት፡፡
እመቤታችንም በስሟ የሚማጸኑትንና መታሰቢያዋን የሚያደርጉትን፣ ለችግረኛ የሚራሩትን፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያንጹትን፤ ዕጣን ጡዋፍ ዘቢብ መባእ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን፤ ለእርሷና ለሃይማኖታቸው ካላቸው ፍቅር የተነሣ ልጆቻቸውን በስሟ የሚሰይሙትን ሁሉ እንዲምርላትና ከሞተ ነፍስ እንዲያድንላት ጠየቀችው፡፡ ጌታችንም“ ይህን ሁሉ እንዳደርግልሽ በራሴ፣ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ” ብሎ የካቲት 16 ቀን ቃል ኪዳን ገብቶላት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ ይህን የድህነት ምክንያት ያገኘንበት የኪዳን ቀን በየወሩ በ16ኛው ቀን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት እያልን የምንዘክረው የምናከብረው ታላቅ በዓል ነው፡፡ በመዝሙር 88÷3 “ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ” ተብሎ እንደተጻፈ፣ ማደሪያው ትሆን ዘንድ ከመረጣት ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ቃል ኪዳን አድርጎበታልና፡፡
በዚህ ቃል ኪዳኗ ድንቅ ተአምራት አድርጋለች፡፡ ከክርስቲያን ወገን የሆነ ሀብት አግኝቶ ያጣ አንድ ሰው ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን “ከብሬ በኖርሁበት አገር ተዋርጄ፣ ሰጥቼ በኖርኩበት ሀገር ለምኜ አልኖርም” ብሎ ጓዙን ጠቅልሎ ከአገሩ ወጥቶ ሲሔድ ሰይጣን ያዘነ ሰው መስሎ ድንጋዩን በምትሐት ወርቅ አስመስሎ “ሥላሴን፣ ጻድቃንን፣ ሰማዕታትንን፣ መላእክትን ካድልኝና ይህን ወርቅ እሰጥሃለሁ” አለው፡፡ ሁሉንም ካደለትና ወርቁን ተቀብሎ መንገድ ሲጀምር ጠርቶ “ምእመናን የሚመኩባት ድንግል ማርያም፣ የአምላክ እናት አይደለችም ብለህ ካድልኝ” አለው፡፡ ሰወየውም “እርሷንስ አልክድም” ቢለው ወርቅ አስመስሎ የሰጠውን ድንጋይ አምጣ ብሎ በዚያው መትቶ ገደለው፡፡ መላእክተ ጽልመት የሟቹን ነፍስ ሊወስዱ ሲሉ መላእክተ ብርሃንም አብረው ቀረቡ፡፡ እመቤታችንንም ይቺ ነፍስ የጠፋች ባንቺ ምክንያት ነውና አማልጃት አሏት ጌታችንን “ልጄ ይህችን ነፍስ ማርልኝ?” አለችው፡፡
እርሱም “እናቴ፣ ውሻ ይማራልን?” እኔንና ወዳጆቼን የካደ ነው አላት፡፡ እመቤታችንም፡- “ስምሽን የጠራውን፣ መታሰቢያሽን ያደረገውን እምርልሻለሁ ያልኸው ቃል ይታበላልን?” እኔን ባለመካዱ ሞቷልና አለችው፡፡ ጌታችንም “ምሬልሻለሁ” አላት፡፡ “እንግዲያውስ ነፍሱን ከስጋው ጋር አዋህደህ አስነሳልኝ” አለችው፡፡ አስነሳው በቀሪ ዘመኑም የሚኖርበት ሰጥታው ቤተ ክርስቲያንን እያገለገለ፣ የእመቤታችን፣ የቅድስት ኪዳነ ምህረትን ዝክር እየዘከረ ኖሯል፡፡ “ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ” ባለው አምላካዊ ቃሉ በሰጣት ቃል ኪዳን አማልዳ ታስምራለች፡፡
ይህን ቃል ኪዳኗን ያመኑ፣ በእናትነት ፍቅሯ ከምልጃዋ በረከት የተካፈሉ ገዳማውያን ሌሊትና ቀን ቅድስት ሆይ ለምኝንልን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናናጸና ከእመቤታችን በረከት እንሳተፍ፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
❤ 51
ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ ከነበሩ ግለሰቦች አንዱ የሆነውን ነዋሪነቱ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሚገኝ ናትናኤል ባደግ ገብሬ የተባለን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር የዋለው የማህበራዊ ሚዲያን (YouTube እና tiktok platform) ን በመጠቀም በንግግር ልቅ ፆታዊ ግንኙነትን የሚያበረታታና የሚያስፋፋ አፀያፊ መልዕክቶችን ሲያሰራጭ በመቆየቱ ነው።
ፖሊስ በቁጥጥር ስር በዋለው ናትናኤል ባደግ ወይም "የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ወይም ይዘት ፈጣሪ ነኝ" በሚለው ግለሰብ ላይ ምርመራ ጀምሯል።
በአንዳንድ ኃላፊነት በማይሰማቸው ግለሰቦች በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከህብረተሰቡ ሞራል ባህልና እሴት ባፈነገጠ ሁኔታ አሉታዊ መረጃዎች እየተሰራጩ መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ በማህበረሰቡ በተለይም ታዳጊ በሆኑ ህፃናት ሥነ-ልቦናና ሞራል ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን ገልፆ በቀጣይም ተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ በሚገቡ ግለሰቦች ላይ ተገቢውን ህጋዊ ርምጃ እንደሚወስድም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ያሳስባል፡፡
@seledadotio
@seledadotio
👍 50❤ 30👏 14🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
የሰላም ስምምነት እንደተፈረመ በፍጥነት ፕረዝደንታዊ ምርጫ እናካይዳለን - ዘለንስኪ
ዩክሬይን በአሜሪካ አደራዳሪነት እየተካሄደ ያለው የሰላም ስምምነት እንደተፈረመ በተቻለ ፍጥነት ፕረዝደንታዊ ምርጫ እንደምታካሂድ አስታወቀች።
የዩክሬይኑ ፕረዚደንት ቮለደሚር ዘለንስኪ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንዳሉት ሐገራቸው የሰላም ስምምነቱ የመጨረሻ ረቂቅ በሁለቱም ሐገራት ተቀባይነት አግኝቶ የፊርማ ማኖር ሥነስርአት ከተካሄደ በኋላ በተቻለ ፍጥነት ፕረዚደንታዊ ምርጫን ታካሂዳለች።
በአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አደራዳሪነት የተረቀቀው የሰላም ስምምነት ረቂቅ የአሜሪካ ልዑካን ከዩክሬይን፣ ከሩስያና ከአውሮፓ መሪዎች ጋር ከመከሩበት በኋላ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን መረጃዎች ያመላክታሉ።
በረቂቅ ሰነዱ ከተቀመጡ የመግባቢያ ሐሳቦች ውስጥ የሰላም ስምምነቱ እንደተፈረመ ዩክሬይን ፕረዚደንታዊ ምርጫ ማካሄድ እንዳለባት እንደሚገልጽ አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል።
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 16👍 8
ጠ/ሚ ዐቢይ ከዊሊያም ሩቶ ጋር ያደረጉት ውይይት ሳፋሪኮም እና ኢትዮ ቴሌኮም በአፍሪካ ቀንድ በጋራ ለመስራት እንዲችሉ ድጋፍ መስጠቱ ተገለፀ!
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና በኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መካከል በአዲስ አበባ የተካሄደው ውይይት፤ ሳፋሪኮም እና ኢትዮ ቴሌኮም በጋራ እንዲሰሩ የፖለቲካ ድጋፍ አስገኝቷል ተባለ። ይህም በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የዲጂታል እና የመሠረተ ልማት ትብብር ለማሳደግ አዲስ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።
ከውይይቱ በኋላ የወጡ መግለጫዎች፤ መሪዎቹ በሁለቱ የቴሌኮም ኩባንያዎች መካከል ስልታዊ አጋርነት እና ኢንቨስትመንት እንዲኖር ለመደገፍ መስማማታቸውን አመልክተዋል። ስምምነቱ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር እና ቀጣናዊ ግንኙነትን ለማስፋፋት እየተደረገ ያለው ሰፊ ጥረት አካል መሆኑም ተጠቁሟል።
መሪዎቹ የዲጂታል መሠረተ ልማት ለንግድ እና ለፈጠራ እድገት ቁልፍ መሆኑን ገልጸው፤ ለአፍሪካ የልማት፣ የሰላም እና የመረጋጋት ጉዞ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሜ አረጋግጠዋል።
ፕሬዝዳንት ሩቶ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መግለጫ፤ ውይይቱ የኢኮኖሚ ትስስርን ማጠናከር እና ለሁለቱም አገራት ዜጎች ተጨባጭ ጥቅም በሚያስገኙ ተግባራት ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል።አክለውም “የኢኮኖሚ ትብብርን ለማሳደግ፣ ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማስፈን እና ሕዝቦቻችንን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን ለመደገፍ በጋራ እንሰራለን” ብለዋል።
Via AS
@Addis_News
@Addis_News
❤ 14👍 6😢 4
Photo unavailableShow in Telegram
የሰዓት ገደብ ተጣለ‼️
የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት፣ ጋምቤላ ከተማን ጨምሮ የጸጥታ ችግር ባለባቸዉ አካባቢዎች ከዛሬ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ የሚቆይ ሰዓት እላፊ ላልተወሰነ ጊዜ መጣሉን አስታወቀ።
የክልሉ መንግሥት ዛሬ ምሽት 11:30 ገደማ ባወጣው መግለጫ፣ ለሥራ ከተመደቡ የጸጥታ ኃይሎች በስተቀር ሰዎችም ኾኑ ተሽከርካሪዎች በሰዓት እላፊው ወቅት እንዳይንቀሳቀሱ ከልክሏል።
ከጸጥታ አካላት ውጪ በማናቸውም ቦታ ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ክልክል መሆኑንም የክልሉ መንግሥት አስታውቋል። የክልሉ መንግሥት የሰዓት እላፊውን ያወጀው፣ በክልሉ በተለይም በጋምቤላ ከተማ እንዲኹም በጋምቤላ እና ኢታንግ ወረዳዎች ከኅዳር 28 ጀምሮ በተከሠቱ ግጭቶች እና የጸጥታ መደፍረስ ሳቢያ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን ተከትሎ ነው።
በክልሉ ግጭት የተቀሠቀሠው፣ የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኡመድ ኡጁሉ በታጠቀ ግለሰብ ከተገደሉ በኋላ ነበር።
የክልሉ መንግሥት በግጭቱ እስካሁን የስንት ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ እና ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ስንት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ይፋ አላደረገም።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 15👍 3
አቶ አርሰናል ፤ የትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ ሆነው ተሾሙ
ከሰሞኑ የሀረሪ ክልል መንግስት ባካሄደው የአመራር ሽግሽግ አቶ አርሰናል አብዲ የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ ሆነዉ ሹመት ማግኘታቸውን ዳጉ ጆርናል ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ያገኘዉ መረጃ ያመለክታል ።
በተጨማሪም ክልሉ አቶ ሳዳም መሀመድን የክልሉ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ሀላፊ በማድረግ ሹመት ሰጥቷል።
የእንግሊዙ አርሰናልስ በዚህ አመት የዋንጫ ሹመት ያገኝ ይሆን?(dagu)
@seledadotio
@seledadotio
🤣 100🤪 11❤ 8👍 5🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
👨💼 እቤትዎ ሆነው ስራ መስራት ይፈልጋሉ?👍
⌛🖥 የኦንላይን ስራዎች የሚሰሩበት እና እንዲሁም የስራ ማስታወቂያዎችን የሚያገኙበት አሪፍ አፕልኬሽን፤ ባሉበት ቦታ ሆነው በስልኮ በቀላሉ የሚሰሩበት እና በየወሩ ተከፋይ የሚሆኑበት አፕ❗️
💥🎮በቀላሉ ከታች ባለው ሊንክ አፑን ዳውንሎድ በማድረግ መስራት እና መጠቀም ትችላላችሁ።
📱📱 DOWNLOAD ለማድረግ 📱📱
🔽🔽🔽🔽
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.habeshanjobs.habeshanjobs
⚡️ @Habeshan_Jobs_Com
⚡️ @Habeshan_Jobs_Com
❤ 6
በምልጃዋ ያመኑትን ሁሉ ሊምርላት ቃል ኪዳን ሰጣት
ነቢዩ ቅዱስ ሕዝቅኤልም የዘለዓለም ድንግልናዋን በትንቢት መጽሐፉ ምዕራፍ 44÷1 ሲናገር “ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በስተውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ፤ ተዘግቶም ነበር። እግዚአብሔርም ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፣ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል፤” ብሎአል። የተዘጋ የመቅደስ በር የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። “ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፤” የሚለው ኃይለ ቃል በድንግልና ጸንታ እስከ ዘለዓለሙ እንደምትኖር ይነግረናል። “ሰው አይገባበትም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል” ሲልም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ፀንሳ፣ በድንግልና የወለደችው ኢየሱስ ክርስቶስ የባህርይ አምላክ በመሆኑ፣ ከርሷ በተዋህዶ ሰው የሆነ የባህርይ አምላክ እንጂ ዕሩቅ ብእሲ አይወለድምና በድንግልና እንደጸናች ትኖራለች ማለቱ ነው።
“እግዚአብሔር አንድ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወድዶአልና። ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም፤” ይላል። ዮሐንስ 3÷17፣ 1ኛ ዮሐንስ 4÷10። ይህን መውደድ ይህን ፍቅር የገለጸው ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሕቱም ድንግልና በመወለድ ነው። የእመቤታችን ድንግልና በሦስት ወገን ነው፤ በሥጋዋ÷ በነፍሷና በልቡናዋ ነው። ይህ ድንግልና የዘለዓለም ድንግልና ነው። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ “ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፣ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፣ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች፤” ብሎአል። ኢሳይያስ 7÷14።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመጽነሷ በፊት፣ በጸነሰችም ጊዜ፣ ከጸነሰችም በኋላ ድንግልናዋ የጸና ነው፤ ከመውለዷ በፊት፣ በወለደችም ጊዜ፣ ከወለደችም በኋላ ኅትምት በድንግልና ናት። የውዳሴ ማርያም አንድምታ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ያላትን አብራርቶ ይነግረናል፡፡ እመቤታችን መልአኩ ሲያበስራት “ወንድ ሳላውቅ ይህ ነገር እንደምን ይሆንልኛል?” የሚል ጥያቄ አንስታ ነበር፡፡ ይህን ያለችው ክብር ይግባትና የወንድ ሀሳብ በአእምሮዋ ፈጽሞ ተመላልሶ ስለማያውቅ ነው፡፡ ሌሎች ሴቶች ስለወንድ ከመናገርና በሕጋዊ ሩካቤ ከመገናኘት ቢታቀቡ ከማሰብ ግን አይነጹም፡፡ እምቤታችን ግን ከመናገር ከማድረግ ከማሰብ ንጽህት ናት፡፡ ከዚህች ቅድስት ድንግል ጋርም በመቃብሩ ስፍራ በጎልጎታ ተደፍታ ስትለምነው በምልጃዋ ያመኑትን ሁሉ ሊምርላት ቃል ኪዳን ሰጣት፡፡
በሥላሴ አኗኗር ወልድ ለአብ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ልጅ እንደሆነ ሁሉ ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያምም ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ልጇ ነው። በጳጳስ ወንበር ቄስ፣ በንጉሥ ዙፋን ራስ ደፍሮ እንደማይቀመጥ ሁሉ በአምላክ ዙፋን በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን ማን ያድራል? ለዚህም ነው እግዚአብሔር ለነቢዩ ለሕዝቅኤል አስቀድሞ የነገረው። ጠቢቡ ሰሎሞንም በመኃ 4÷12 “እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፣ የተዘጋ ምንጭ፣ የታተመ ፈሳሽ ናት፤” ብሎአል። እንደተቆለፈች አምላክ ብቻ አድሮባት የወጣባት ገነት፣ እንደተዘጋች የዘለዓለምን ሕይወት ክርስቶስን ያመነጨች፣ እንደታተመች የሕይወትን ውኃ ክርስቶስን በአራቱም ማዕዝን አፍስሳ የተጠሙ ነፍሳትን ያረካች፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብቻ ናት።
ልዩ እናትነቷን ያመኑ፣ ምልጃዋን ተስፋ ያደረጉ ገዳማውያን ዘወትር በጸሎታቸው ይጠሯታል፡፡ ገዳማቸውን እንደገፍ በአታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
❤ 74🥱 5🤪 2
