fa
Feedback
Natnael Mekonnen

Natnael Mekonnen

رفتن به کانال در Telegram

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7 Facebook.com/natnaelmekonnen.et Instagram.com/natnaelmekonnen21

نمایش بیشتر
2025 سال در اعدادsnowflakes fon
card fon
180 572
مشترکین
-10924 ساعت
-7587 روز
-2 28030 روز
آرشیو پست ها
00:30
Video unavailableShow in Telegram
ሀብት ከድንቁርና ጋር ሁለት ከባድ ገዳይ ነገሮች ይሄ አርሲ ኔጌሌ ከተማ ውስጥ ነው አሉ። (ሌላ ቦታም ከሆነ ጠቁሙን) አርሲ ነጌሌም ከሆነም የኔጌሌ ከተማ አስተዳደር እና ፖሊስ የለም አልያም በቁሙ ሞቷል ወይንም በይፋ እንዲህ እንዲሆኑ ፈቅዷል ማለት ነው:: ከተማ አስተዳደሩ ይህን ድርጊት በዝምታ ካልፈው ነገ መትረየስ ይዘውለት ይመጣሉ!! አርሲ ነጌሌ ነው የተባለው የሰርገኞቹ ሚዜዎች ጦርሜዳ እንደሚሄድ ሰው ህዝብ መሀል ሰላም ከተማ ውስጥ ሽጉጥ እየተኮሱ ያልፋሉ። እንዲህ አይነት ተራና ህገወጥ ተግባራት ሰላማዊውን ነዋሪ የሚያሸብሩ ብቻ ሳይሆኑ እልም ያሉ የማንአለብኝነትና የብልግና ተግባራት ስለሆኑ ህግ አስከባሪ አካላት እነዚህን ዱርዬዎች በቁጥጥር ስር አውላችሁ ህግና ስርአትን ልታስከብሩ የሚገባ ይመስለኛል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየተለመዱ የመጡ መስመር የለቀቁ የሰርግ ስነስርአቶች እየታዘብን ነው። ሃብታሞች በ V8 ደሃ ህዝብ ላይ መጨማለቅ አንዳች የሚጨምርላችሁ ክብር የለም። መጨማለቁ አልበቃ ብሏችሁ ደግሞ ሰው ሰላም ወጥቶ እንዳይገባ መሃል ከተማ ላይ የጥይት እሩምታ ታሰማላችሁ። ለሚያያችሁ ሰው ለዚህ እኩይ ድርጊታችሁ መንግስታዊ ፍቃድ ያላችሁ ነው የሚመስለው። በምስኪን ህዝብ መሃል ተከባችሁ እየኖራችሁ በዚህ ልክ መቅበጥ ነውረኝነት እንደሆነ አውቃችሁ ጥጋባችሁን በልክ እንድታደርጉት እንጠይቃለን።
نمایش همه...
IMG_0874.MP45.79 MB
Photo unavailableShow in Telegram
በጅንካ ከተማ ምንነቱ በመረጋገጥ ያለ ሄሞራጂክ ፊቨር በሽታ ተከሰተ በደቡበ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ የሄሞራጂክ ፊቨር (Hemorrhagic Fever) በሽታ መከሰቱን የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቁ። የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ እስካሁን ድረስ ስምንት ሰዎች በበሽታው እንደተጠረጠሩ ገልፀዋል። መግለጫው፣ ከከልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተመዘገበውን ይህንን የበሽታ መንስኤ ለማወቅ እና ተጨማሪ ስርጭትን ለመግታት እንዲሁም ለመቆጣጠር ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን ወደቦታው በመላክ የመስክ ግምገማዎች እና የላብራቶሪ ምርመራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል። በተጨማሪም የማህበረሰብ ቅኝት፣ የንከኪ ልየታ፣የቤት ለቤት ልየታ እንዲሁም የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን እያጠናከረ ይገኛል ብሏል። በመሆኑም መላዉ ሕብረተሰባችንና የሚመለከታቸዉ የባለድርሻ አካላት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሌላ ተጨማሪ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ፤ ለመከላከል የሚከተሉትን ምከረ-ሃሳቦች እና ጥንቃቄዎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል። በአፍ፣ አፍንጫ እና ሌሎች የሰውነት ከፍሎች የመድማት፣ትኩሳት፣ማስቀመጥ እና ማስመለስ ምልክት ሲኖር ወደ ህክምና ተቋማት መሄድና በወቅቱ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝቧል። በተጨማሪም፣ ምልክት ከታየበት ማንኛዉም ሰዉ ጋር ንክኪ በሚኖርበት ጊዜ ራስን የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም፣ ሁልጊዜ እጅን በሳኒታይዘር ወይም በውሃና በሳሙና በመታጠብ ማጽዳት አስፈላጊ ነው ተብሏል።
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
Good News : ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) ከ50 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚታደሙበትን ጉባኤ እንድታስተናግድ ተመረጠች! ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በኋላ የሚካሄደውን የዓለማችን ዋነኛውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ፀባይ ለውጥ ጉባኤን እንድታስተናግድ ብራዚል ውስጥ እየተካሄደ ባለው የዘንድሮ ስብሰባ ላይ ተመረጠች። ኮፕ በመባል የሚታወቀውን እና በየዓመቱ ከሚካሄደውን የአየር ፀባይ ለውጥ ጉባኤ በአውሮፓውያኑ 2027 የሚደረገውን “ኮፕ32” ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ የተመረጠችው ናይጄሪያን በመብለጥ ነው። ኮፕ የሚለው ስያሜ ‘ኮንፈረንስ ኦፍ ፓርቲስ’ የሚሉት ቃላት ምህጻረ ቃል ሲሆን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ፀባይ ለውጥ ስምምነት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ የዓላማችን ዋነኛው የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ ነው።በጉባኤው ከአሜሪካ በስተቀር መላው የዓለም አገራት እና ሌሎችም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የሚታደሙ ሲሆን፣ ወሳኝ ድርድሮች እና ስምምነቶች የሚደረሱበት ነው። ይህ ዓመታዊ ጉባኤ መካሄድ የጀመረው በአውሮፓውያኑ 1992 የአየር ፀባይ ለውጥ የዓለማችን ስጋት መሆኑ በመንግሥታቱ ድርጅት ተቀባይነት አግኝቶ ከስምምነት ከተደረሰ በኋላ ነው።ኢትዮጵያ ይህንን ጉባኤ ለማዘጋጀት መመረጧ በጉባኤው አጀንዳ ላይ እና በማብቂያው ላይ በሚተላለፉ ውሳኔዎች ላይ ከፍተኛ ሚና እንዲኖራት እንደሚያደርግ የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል።
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ኑሮዎን እና ንግደዎን የከተማችን Downtown በሆነችው Mexico ያድርጉ እጅግ ዘመናዊ የመኖሪያ ኮምፓውንድ በ መሀል ከተማ  Mexico በማስታወቂያ ዋጋ በ 10 % ቅድመ ክፍያ ቤት ይግዙ። ☎️+251986687513 ☎️+251929261190 🏠 ቀድመው በመምጣት ሚሊዬኖችን ያትርፉ አባይ ሆምስ | Abay Homes ➣ የ ከተማችን እጅግ ዘመናዊና ቅንጡ የመኖሪያ ኮምፓውንድ በማይታመን ዋጋ በመሀል አዲስ አበባ ሜክሲኮ አፍሪካ ህብረት አጠገብ ለኑሮ ቢሉ ለንግድ ተመራጭ ቦታ ላይ  በተመጣጠነ ዋጋ ለሽያጭ አቅርቧል ➣ ከ  ባለ አንድ መኝታ እስከ ባለ ሶስት መኝታ ቤቶችን ማግኘት ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ ይደውል          👇 ☎️+251986687513 ☎️+251929261190 ዘመናዊ መኖሪያ መንደር አዲስ አበባ ሜክሲኮ አፍሪካ ህብረት አጠገብ ኢትዮጵያ WhatsApp:- +251986687513 Telegram :- @realesrateconsultant Email:- Yohannesmisganew5@gmail.com
نمایش همه...
ሐዋሳ ከተማ አዲስ ከንቲባ ተሾመላት። የሐዋሳ ከተማ ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ጥራቱ በየነን የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል። ‎አቶ ጥራቱ በየነ ከዚህ ቀደም ከነሐሴ 24 ቀን 2011 ዓ.ም እስከ 2013 ዓ/ም የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ሲመሩ የቆዩ ሲሆን ላለፉት ሶስት ዓመታት ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማው ከፍተኛ አመራር ሆነው አገልግለዋል። በአዲስ አበባ አመራርነት ጊዜያቸውም በአመራር ብቃታቸው ስማቸው ጎልቶ ሲነሳ ቆይቷል።
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴምርፕሮፐርቲስ #እነሆ_አዲስሳይት 📍 ሳር ቤት #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 11.4ሚሊዮን #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) 📍 አዋሬ #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 145ካሬ = 10.3ሚሊዮን #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 78ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.7ሚሊዮን) 👉 135ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 14.8ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.9ሚሊዮን) 👉 157ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.4ሚሊዮን) ⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን! +251964439488 +251907232222 Telegram: https://t.me/OusmanTemer WhatsApp: https://wa.me/251964439488
نمایش همه...
የተቃውሞ ሰልፍ ህወሓት ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም በአፋር ክልል መጋሌ ወረዳ ትንኮሳ መፈፀሙን ተከትሎ ትናንት ህዳር 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ በአፋር ክልል በተለያዩ ከተሞችና ወረዳዎች የህውሓትን ወታደራዊ ትንኮሳ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ። ትናንት በመጋሌ ወረዳ የተቃውሞ ሰልፍ የተካሄደ ሲሆን ዛሬ ህዳር 2/2018 ዓ.ም በፋንቲ ራሱ ቴሩ ወረዳ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ሲሆን የኤርትራ ተላላኪ የሆነውን የህወሓት ቡድን ተልእኮ እናፈርሳለን " የህወሓት ቡድን ጥቅምት 26 ቀን በአፋር ክልል መጋሌ ወረዳ በሰላማዊ ህዝብ ላይ የከፈተውን ጦርነትና ማፈናቀል እናወግዛለን እንታገላለን " ህወሓት እስካለ ድረስ ኢትዮጵያ ሰላም አትሆንም። ህወሓት ለራሱ ለትግራይ ህዝብ ጠላት ነው" ህወሓት የአፋር ታሪካዊ ጠላት ነው"የሚሉ መፈክሮች በሰልፉ ላይ ተንፀባርቀዋል።
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ኑሮዎን እና ንግደዎን የከተማችን Downtown በሆነችው Mexico ያድርጉ እጅግ ዘመናዊ የመኖሪያ ኮምፓውንድ በ መሀል ከተማ  Mexico በማስታወቂያ ዋጋ በ 10 % ቅድመ ክፍያ ቤት ይግዙ። ☎️+251986687513 ☎️+251929261190 🏠 ቀድመው በመምጣት ሚሊዬኖችን ያትርፉ አባይ ሆምስ | Abay Homes ➣ የ ከተማችን እጅግ ዘመናዊና ቅንጡ የመኖሪያ ኮምፓውንድ በማይታመን ዋጋ በመሀል አዲስ አበባ ሜክሲኮ አፍሪካ ህብረት አጠገብ ለኑሮ ቢሉ ለንግድ ተመራጭ ቦታ ላይ  በተመጣጠነ ዋጋ ለሽያጭ አቅርቧል ➣ ከ  ባለ አንድ መኝታ እስከ ባለ ሶስት መኝታ ቤቶችን ማግኘት ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ ይደውል          👇 ☎️+251986687513 ☎️+251929261190 ዘመናዊ መኖሪያ መንደር አዲስ አበባ ሜክሲኮ አፍሪካ ህብረት አጠገብ ኢትዮጵያ WhatsApp:- +251986687513 Telegram :- @realesrateconsultant Email:- Yohannesmisganew5@gmail.com
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) አስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ እየተካሄደ ነው፡፡ በሽኝት ሥነ ሥርዓቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች የሥራ ባልደረቦችና ወዳጅ ዘመዶች ተገኝተዋል። የላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ሥርዓተ ቀብርም ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ይፈጸማል፡፡ የታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ባደረባቸው ሕመም ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል፡፡ ላጲሶ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ የታሪክ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የተለያዩ የታሪክ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አበርክተዋል፡፡ የኢትዮጵያውያንን የጋራ እሴት፣ ባሕልና ቋንቋ በማውሳት የሕዝቦች ታሪክ ጎልቶ እንዲታወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውም ተጠቁሟል፡፡
نمایش همه...
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ‘ሲቢኢ በእጄ’ የተሰኘ የዲጂታል ቁጠባ እና ብድር አገልግሎት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል። በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ የባንኩ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ እና የሌሎች ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል። አቶ ኤፍሬም በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ ንግድ ባንክ ዘመኑን የዋጁ አዳዲስ አገልግሎቶችን በማፍለቅ ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት እየሰጠ ነው። የአገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ዲጂታል ለማድረግ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል። ‘ሲቢኢ በእጄ’ ዲጂታል የቁጠባና ብድር አገልግሎት እስከ 150 ሺህ ብር ድረስ ብድር ያለማስያዣ ማግኘት ያስችላል ብለዋል። አገልግሎቱን ለማግኘትም ተቋማት የሠራተኞችን ወርሃዊ ደመወዝ በሲቢኢ ብር ለመክፈል ስምምነት መፈጸም እንዳለባቸው አብራርተዋል። በአገልግሎቱ የመንግስት ሰራተኞችን ቅድሚያ ተጠቃሚ ለማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫና ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች ተደርገዋል ነው ያሉት።
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴምርፕሮፐርቲስ #እነሆ_አዲስሳይት 📍 ሳር ቤት #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 11.4ሚሊዮን #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) 📍 አዋሬ #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 145ካሬ = 10.3ሚሊዮን #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 78ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.7ሚሊዮን) 👉 135ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 14.8ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.9ሚሊዮን) 👉 157ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.4ሚሊዮን) ⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን! +251964439488 +251907232222 Telegram: https://t.me/OusmanTemer WhatsApp: https://wa.me/251964439488
نمایش همه...
01:27
Video unavailableShow in Telegram
ግብ ግብ - የ 10 ቢሊዮን ብሮች ትንቅንቅ የሀገርን እና የሕዝብ ጥቅም ለማስከበር የሚከፈለው መስዋዕትነት እንዴት ያለ ነው ለሚለው በትንሹ ማሳያ ነው። ኃላፊነት የሰጠኸን ሕዝብና መንግስት ቃል ኪዳን ለመፈጸም በቃልህና በአቋምህ ከፀናሕ ለምን ጥቅሜ አልተከበረም የሚሉ ሃይሎች አምርረው ይጠሉሀል ፣ ይዘምቱብሀል ። ታዲያ ዛቻውን ፣ ስም ማጥፋቱን ፣ በገንዘብ ማባበሉን ፣ የግድያ ሙከራውን ተቋቁመህ በምንም ሁኔታ ከራስ በለይ የሕዝብና የመንግሥት ጥቅም ይበልጣል ማለትህ ትውልድን የሚያኮራ ተግባር ይሆናል። ይህ የሕዝብንና የመንግስት ጥቅምን ለማስከበር የተካሄደውን ትንቅንቅ ትእይንት በቅርብ ቀን በፋና ቲቪ ይጠብቁ ::
نمایش همه...
IMG_0801.MP417.18 MB
ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ አሻጥሮችን ሲፈጽሙ የተደረሰባቸው 112 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ በተቀናጀ መንገድ ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ አሻጥሮችን ሲፈጽሙ የተደረሰባቸው 112 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ ፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለፋና ዲጂታል እንደገለጸው ÷ መንግሥት ተግባራዊ ያደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በመጻረር በተደራጀ መንገድ በሚፈጽሙ ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ አሻጥሮች ዙሪያ በተቀናጀ መልኩ ምስጢራዊ የመረጃ ስምሪት ሲከናወን ቆይቷል፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የክልል የፀጥታ አካላትና በሕብረተሰቡ ጥቆማ በተደረገ የተቀናጀ ሥምሪት በፋይናንስ አሻጥር የተሰማሩ 112 ኢትዮጵያውያንና የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል፡፡ ከሕገ ወጥ ተግባሩ ጋር ትስስር የነበራቸው 519 የባንክ አካውንቶች የታገዱ ሲሆን ÷ የተለያዩ ኤግዚቢቶች መያዛቸውም ተጠቅሷል፡፡ ሕገ ወጥ ሃዋላዎች ፣ የገንዘብ ዝውውሮች፣ የውጭ ምንዛሪ ስወራዎች ፣ የግብር ስወራዎች፣ ሕገ ወጥ ገንዘብን ሕጋዊ የማስመሰልና ሌሎች ተመሳሳይ ወንጀሎች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያስከትሉ እንዲሁም አሸባሪዎችንና የታጠቁ ቡድኖችን ለመደገፍ ሲውሉ መቆየታቸውን መግለጫው አመልክቷል፡፡ በተለይም ሕገ ወጥ በሆኑ ዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች፣ ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ማስተላለፊያ መተግበሪያዎች፣ የክሪፕቶ ከረንሲ መተግበሪያዎች፣ ሕገ ወጥ የሃዋላ አዘዋዋሪዎችና ደላላዎች፣ በወጪና ገቢ ንግድ ላይ አሻጥር የፈፀሙ አስመጪዎችና ላኪዎች እንዲሁም ሕጋዊ ንግድ ሳይኖራቸው በሕገ ወጥ ሃዋላ ላይ በመሰማራት ከፍተኛ ገንዘብ በማንቀሳቀስ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ባደረሱ አካላት የማያዳግም ሕጋዊ ርምጃ መወሰዱ ተጠቁሟል፡፡ በተለያዩ ዓለማት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚልኩት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ የብሔራዊ ባንክን መመሪያ በሚጥስ ሁኔታ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያስከትሉ የቆዩ ሕጋዊ ፈቃዳቸው በፈጸሙት ተደጋጋሚ ጥፋት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰረዘባቸው ዓለም አቀፍ የሃዋላ አስተላላፊዎችና ሕገ ወጥ የሃዋላ ድርጅቶችም ርምጃው የተወሰደባቸው ናቸው። በተጨማሪም በሀገር ውስጥ ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ማስተላለፊያ መተግበሪያዎችን በመጠቀም ሀብትን ከሀገር በማሸሽ ላይ ያሉ ድርጅቶች ባለቤቶችም በቁጥጥር ሥር ውለዋል። የብሔራዊ ባንክ ሕግን በሚጥስ ሁኔታና ያለምንም ፈቃድ የክሪፕቶ ከረንሲ መተግበሪያን በመጠቀም በሕገ ወጥ መንገድ የውጭ ምንዛሪን ሲያዘዋውሩ የነበሩ አካለት ላይም ርምጃ ተወስዷል፡፡ በሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም ላይ በማነጣጠር ሲፈጸም የነበረው ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ትላልቅ የመንግሥት ፕሮጀክቶችን ለማስተጓጎል፣ ሕዝብ በመንግሥት ላይ ቅሬታ እንዲያድርበት እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንዳያንሰራራ በተቀናጀ መንገድ ሲፈጽሙት እንደነበረ ነው የተገለጸው፡፡ የሀገርን ደኅንነት ስጋት ላይ በሚጥሉ እና የሀገርን ኢኮኖሚ በሚጎዱ አሻጥሮች ላይ ተሳታፊ የሆኑ አካላትን በመከታተል የማያዳግም ርምጃ ለመውሰድ የተጀመረው የተቀናጀ ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡ መላው ሀገር ወዳድ ዜጋ መሰል ወንጀሎችንና ወንጀለኞችን በማጋለጥ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርቧል፡፡
نمایش همه...
በዛሬው እለት ህዳር 1/2018 ዓ.ም በአፋር ክልል አብዓላና ዙሪያዋ የሚኖሩ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል። ሰላማዊ ሰልፉን አስመልክቶ ከክልሉ ኮሚኒኬሽን ባገኘነው መረጃ ነዋሪዎቹ በህወሓትና በሻዕብያ “ ትብብር “ በአከባቢያቸው ተቃጥቷል ያሉትን ጥቃት ክፉኛ አውግዘዋል። “ ህዝቡ ወደ ቀዩ ይመለስ የትግራይ ኃይል ከያዘው የዓፋር መሬት ይውጣ “ ያሉት ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ፤ ይህን ሳይሆን ከቀረ ከዓፋር እና ከፌደራል መንግስታት ጋር ተሰልፈው መብታቸው ለማስከበር እንደሚንቀሳቀሱ ዝተዋል።
نمایش همه...
" ህጻናት ታግተው ገንዘብ መጠየቂያ ተደርገዋል፣ ወላጆች ገንዘብ መስጠት ስላልቻሉ ህጻናቱ ተገድለዋል " - አጣሪ ኮሚቴው " ግድያው አንድን ሃይማኖት እና ብሄርን ትኩረት ያደረገ አይደለም የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከጥቅምት ወር አጋማሽ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በሚገኙ አንዳንድ ወረዳዎች በሚኖሩ ዜጎች ላይ የተፈጸሙ ግድያ ፣እገታ እና ዝርፊያ በሚመለከት ልዑካኑን በአካባቢው በመላክ በጉዳዩ ላይ ሲያደርግ የቆየውን ጥናት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል። በቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ውጤት መሰረትም ገባኤው ጥቃቱ አንድን ሃይማኖት እና ብሄርን ትኩረት ያደረገ ግድያ ተፈጽሟል በማለት ሲዘዋወር የነበረውን መረጃ አጣጥሏል። ጉባኤው ሪፖርቱን የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ሲል የጠራው " ያላለቀ በመሆኑ ፣የተጠቀሱት ወረዳዎች የተራራቁ በመሆናቸው እንዲሁም መሰረተ ልማት ውስንነት ያለበት ከመሆኑ አንጻር ሁሉም ቦታ ላይ ደርሶ የመጨረሻ ሪፖርት ለማውጣት ጊዜ የሚፈልግ በመሆኑ ነው " ብሏል። የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ " ጥቅምት ወር አጋማሽ ጀምሮ በምስራቅ አርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በተለይም በአምስት ወረዳዎች የተፈጠረ ክስተት አለ በእዚህም የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ አካል ጎድሏል ፣የተፈናቀሉ እና የጠፉ ንብረቶች ብዙዎች አሉ " ሲሉ ክስተቱን በተመለከተ መብራሪያ ስጠተዋል። ጉባኤው በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ እንዳሳወቀው ጉዳዩን በአካባቢው በመሄድ አጣርተው የመጡት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የተወከሉ ሦስት ፣ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና ከኦሮሚያ እስልምና ከፍተኛ ምክር ቤት ሁለት፣ ከጉባኤው ሁለት ባለሞያዎች በአጠቃላይ በዋና ሰብሳቢ፣ በምክትል ሰብሳቢ እንዲሁም በጸሃፊ የተዋቀረ 10 ልኡካን ናቸው። ቀሲስ ታጋይ " ይህ የመጀመሪያ ደረጃ ምልከታ እና የማጣራት ሪፖርት ነው፣ ቀጣይ ተጨማሪ ማጣራት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ካሉ ቦታው ድረስ እየሄዱ የማጣራት ስራ ጊዜ የሚፈልግ ነው በሦስት እና በአራት ቀናት ብቻ የሚያልቅ አይደለም ወራትም ሊወስድ ይችላል" ነው ያሉት። የአጣሪ ኮሚቴው ሰብሰቢ መላከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የመጀመሪያ ደረጃ የጥናት ሪፖርቱን ውጤት በሚመለከት ምን አሉ ? " ዝርዝር ሃሳቡ በዋናው ማጠቃለያ ሪፖርት ላይ የሚገልጽ ሆኖ ጥናቱ የተደረገው ጉና፣ ሽርካ ፣ሆንኩሎ አቤ፣ መርቲ ወረዳዎች ናቸው። አንደኛ በጉና ወረዳ ናኖ ጃዊ ቀበሌ ገበሬ ማህበር የሰው ህይወት መጥፋት፣ የንብረት መውደም ፣ዝርፊያ እንዲሁም እገታ ተፈጽሟል። የክስተቱ ሁኔታ 12/02/18 ዓም ከቀኑ ስምንት ሰአት ታጣቂዎች አስገድደው ከማህበረሰቡ ጋር ምሳ በሉ በመጨረሻም የመንግስት ታጣቂ ሃይል መምጣቱን ሲያውቁ የተወሰኑ ሰዎችን አግተው እና ንብረት ይዘው ወደ ጫካ ሸሹ። 13/02/18 ዓም ምሽት ተመልሰው ተጨማሪ ሰው አግተው ወሰዱ። 14/02/18 ዓም ያገቷቸውን ሰዎች ገደሏቸው ከተጎጂ ቤተሰቦች እና ካነጋገርናቸው ሰዎች በተሰጠ ምላሽ ይህንን ድርጊት የፈጸሙት ራሳቸውን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት/ሸኔ፣ ወይም ፋኖ ናቸው የሚል ምላሽ ነው። አንዳንድ ግለሰቦች ደግሞ በሰጡት ምላሽ ማንነታቸውን እንደማያውቁ ነገር ግን በለሊት የሚንቀሳቀሱ ምንም አይነት የሃይማኖት መገለጫ የሌላቸው ግለሰቦች መሆናቸውን ነው። ሁለተኛ በሸርካ ወረዳ 17/02/18 ዓም የሰው ህይወት ጠፍቷል እገታም ተፈጽሟል በወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኙ ዜጎች ላይ በተለያየ ጊዜ ዘር ፣እምነት እንዲሁም እድሜ እና ጾታ ሳይለዩ ግድያዎች ተፈጽመዋል። ህጻናት ታግተው ገንዘብ መጠየቂያ ተደርገዋል፣ ወላጆች ገንዘብ መስጠት ስላልቻሉ ህጻናቱ ተገድለዋል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ህጻናቱ ተለቀው ወላጆች ከነገንዘባቸው ተወስደው ተሰቃይተዋል። የተቀሩት ወረዳዎችም ተመሳሳይ ድርጊቶች መከናወናቸው ምላሽ ተሰጥቶናል። የመንግስት በኩል የተገኘው ምላሽ ወታደራዊ እርምጃ መወሰዱን እና በመንግስት መዋቅር ጭምር መስዋዕትነት እየተከፈለ መሆኑን ተገልጾልናል። በችግሩ ተጋላጮች ክስተቱ አንድ ወገንን ወይም ብሔር እና ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ አለመሆኑን እና ሁሉንም የጎዳ መሆኑን ተገልጾልናል። አጥኚ ቡድኑ በአራት ወረዳዎች በመንቀሳቀስ እና እውነታውን ለባለድርሻ አካላት ለማቅረብ ስራውን የጀመረ ሲሆን በአራት ወረዳዎች ባስቀመጠው የጥናት እቅድ መሰረት ተግባራዊ ስራውን ያከናወነ በመሆኑ ጥቅል ዝርዝር ሁኔታዎች ማለትም የሟች ማንነት ፣የአሟሟት ሁኔታ፣ ብዛት ፣የሃይማኖት ስብጥር በቀጣይ በጥናት የሚካተቱ እና የቀሩትን ወረዳዎች ባማከለ መልኩ የሚያቀርብ ይሆናል " ብለዋል። ምክትል ሰብሳቢ ሃጂ አብድልሃኪም ሁሴን በሰጡት ቃል አንድ ወገን ላይ ያተኮረ ግድያ ተፈጽሟል መባሉ ስህተት መሆኑን ገልጸው " አጥቂዎቹ አንድን ሃይማኖት እንደማይለዩ ፣እንዲሁም ታጣቂዎቹ የሁሉም ሃይማኖት ስብጥር እንደሆኑ በአንዳንድ ወቅት በአጋቾቱ ታግተው ከተለቀቁ ሰዎች በተገኘ መረጃ ተገልጾልናል " ብለዋል።
نمایش همه...
የገንዘብ ሚኒስቴር የገቢ ግብር (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አፈጻጸም ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት፣ በተለይ በአከፋፋይ ነጋዴዎች ላይ የሚሰላውን አማራጭ አነስተኛ ግብር በተመለከተ ከፍተኛ እፎይታ የሚሰጥ ማብራሪያ ሰጥቷል። ይህ ውሳኔ ቀደም ሲል የንግዱን ማህበረሰብ አስጨንቆ የነበረውን የትርፍ ህዳግ (Profit Margin) ግዴታ የሚያነሳ በመሆኑ በነጋዴዎች ዘንድ በደስታ ተቀባይነትን አግኝቷል።በሚኒስቴሩ ማብራሪያ መሰረት፣ የአከፋፋዮች አማራጭ አነስተኛ ግብር የሚሰላበት መንገድ ግልጽ ሆኗል። በዚህ መሰረት ፤  ጅምላ ሻጭ/አከፋፋይ ከአምራቹ ወይም ከአስመጪው ጋር ባደረገው ውል የሚሸጥበት ዋጋ እና የሚያገኘው መቶኛ (ትርፍ ህዳግ) በግልጽ የተወሰነ ከሆነ፣ አማራጭ አነስተኛ ግብሩ የሚሰላው በጠቅላላ የሽያጭ ገቢው ላይ ሳይሆን፣ በውል ወይም በሕግ በተፈቀደለት የትርፍ መቶኛ ላይ ብቻ ይሆናል ተብሏል።ይህ አዲስ አፈጻጸም የገቢዎች ሚኒስቴር በትንሹ 15 በመቶ ማትረፍ አለባችሁ በሚል ያስቀመጠው ግዴታ በንግዱ ላይ የፈጠረውን ጫና የሚያቃልል ነው። ይሁንና፣ ይህንን ውሳኔ ለመጠቀም አከፋፋዩ የመሸጫ ዋጋ እና የትርፍ ህዳግ በውል መወሰኑን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ሰነድ ለግብር ባለስልጣናት ማቅረብ ይኖርበታል።ይህን የገንዘብ ሚኒስቴር ማብራሪያ ተከትሎ ነጋዴዎች ለካፒታል ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት፣ ውሳኔው የንግዱን እንቅስቃሴ የሚያነቃቃ እና ከገበያ እውነታ ጋር የሚጣጣም ፍትሃዊ እርምጃ እንደሆነ ተናግረዋል። Via…Capital
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴምርፕሮፐርቲስ #እነሆ_አዲስሳይት 📍 ሳር ቤት #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 11.4ሚሊዮን #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) 📍 አዋሬ #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 145ካሬ = 10.3ሚሊዮን #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 78ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.7ሚሊዮን) 👉 135ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 14.8ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.9ሚሊዮን) 👉 157ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.4ሚሊዮን) ⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን! +251964439488 +251907232222 Telegram: https://t.me/OusmanTemer WhatsApp: https://wa.me/251964439488
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
አጣሪ ኮሚቴው በአርሲ ዞን “ የተፈጸመውን ግድያ በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ የምርመራ ሪፖርቱን ይፋ ሊያደርግ ” ነው‼️ የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን የተፈጸመውን ግድያ እንዲያጠራ ያሰማራው አጣሪ ኮሚቴ የደረሰበትን የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት በነገው ዕለት ይፋ እንደሚያደርግ አዲስ ማለዳ ለማወቅ ችላለች። ጉባኤው፣ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አራት ወረዳዎች “ የተከሰተውን ችግር ” ሲል የገለጸውን ግድያ በቦታው በአካል በመገኘት የማጣራት ሥራ ለመሥራት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተወከሉበት አንድ አጣሪ ኮሚቴ በአስቸኳይ በማቋቋም ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም  “ ችግር ወደተከሰተባቸው ሂዶ የማጣራት ሥራ እንዲሠሩ ማድረጉን ” አስታውሷል። በዚህም አጣሪ የልዑካን ቡድኑ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን ይፋ እንደሚያደርግ፣ ጉባኤው ለመገናኛ ብዙኃን ያሰራጨው የጋዜጣዊ መግለጫ ጥሪ ያመላክታል። በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን፣ በጉና፣ በመርቲ፣ በሸርካ እና ሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ተከታዮች መገደላቸውን ቤተ ክርስቲያኒቱን ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መግለጣቸውና ድርጊቱን ማውገዛቸው ይታወሳል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ጉባኤው  ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር “ ኃይማኖቶች ለሰላም፣ ለአንድነትና አብሮነት ” በሚሉ መሪ ቃላት አምስተኛውን ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ህዳር 3 እና 4 ቀን 2018 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ለማካሄድ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን ገልጧል። በነገ መግለጫው ከሪፖርቱ በተጨማሪ ጉባኤው በዚህ ኮንፈረንስ ላይም ገለጻ እንደሚሰጥ አስታውቋል።
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴምርፕሮፐርቲስ #እነሆ_አዲስሳይት 📍 ሳር ቤት #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 11.4ሚሊዮን #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) 📍 አዋሬ #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 145ካሬ = 10.3ሚሊዮን #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 78ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.7ሚሊዮን) 👉 135ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 14.8ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.9ሚሊዮን) 👉 157ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.4ሚሊዮን) ⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን! +251964439488 +251907232222 Telegram: https://t.me/OusmanTemer WhatsApp: https://wa.me/251964439488
نمایش همه...
02:07
Video unavailableShow in Telegram
ለዘመናት ታፍኖ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ በቁጭት ሲመላለስ የነበረ የባህር በር ጥያቄ ፈንድቶ ወጥቷል። ከዚህ በኋላ ይሄን ጥያቄ የሚያቆመው አንዳች ሃይል የለም። የኢትዮጵያ ልጆች፣ ከትንሽ እስከትልቅ፣ ዶክተሩም፣ ወታደሩም፣ የተማረውም ያልተማረውም አለም አቀፍ ካፒቴኖች ሳይቀሩ ዛሬ ስለባህር በር ያወራሉ። በዚህ ሰአት ከላይ ከመሪው እስከተራው የኢትዮጵያ ገበሬ ኢትዮጵያውያን ጥያቄያቸው አንድ ነው....የባህር በር!! ኢትዮጵያ ላይ የተሰራው ሴራ የትም አለም አልተሰራም። ብዙ ሐገሮች ከባህር በሺህ ኪሎሜትር ርቀት ላይ ሆነው እንኳን ከውሃ ለመገናኘት ረዣዥም ካናሎችን ሰርተው ከውሃ ሲገናኙ ኢትዮጵያ የራሷ የነበረን ባህር በወንበዴዎች የጫካ ምክር ተነጥቃ ለአስርት አመታት ተከርችሞባት እንደእስረኛ መቆየቷ ሳያንስ መብቷን እንኳን እንዳትጠይቅ ሐገር ይመራሉ ባልናቸው ሐገር ጠሎች ታፍና ቆይታለች። ዛሬ ይህ ተከርችሞበት የነበረ መዝገብ ተገልጦ ኢትዮጵያ ታሪካዊ መብቷን ቀና ብላ እየጠየቀችና የባእድ ሐገርን የባህር በር እያዩ ሲቆጩ የኖሪ ልጆቿ ከአለም ጫፍ እስከጫፍ ጥያቄውን እያስተጋቡት ይገኛሉ። የኢትዮጵያ የኩስመና ታሪክ ግብአተ መሬቱ ቀርቧል። የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጥያቄ ነው። የኢትዮጵያ Resurrection ምልክት ነው። በቀጠናው የሚኖረንን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሐይል ለዘልዘለሙ የምንቀይርበት ወሳኝ ቁልፍ ነው። ለዘመናት “ግንድ ይዞ ይዞራል” እየተባለ በቁጭት ሲዘፈንለት የነበረውን ታላቁን አባይ አቁመንና መትረን ለአለም እንዳሳየነው ወደቀይ ባህር በቅርቡ በኩራት ወጥተን ለልጆቻችን የታፈረች ሐገር እንደምናወርስ ቅንጣት ጥርጥር የለንም። ኢትዮጵያውያን ነን!
نمایش همه...
IMG_0743.MP411.02 MB