Jafer Books 📚
رفتن به کانال در Telegram
የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን !! አድራሻችን ለገሃር ተወልደ ህንጻ አራት ኪሎ ብርሃና ሰላም ፊት ለፊት አብርሆት ቤተመጻሕፍት ግቢ ውስጥ ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ሳሪስ አዲሱ ሰፈር ጀሞ ለቴሌግራም https://t.me/Jafbok ለፌስቡክ https://www.facebook.com/jaferbookshop?mibextid=ZbWKwL ለዌብሳይት www.jaferbooks.com
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

30 531
مشترکین
-124 ساعت
+607 روز
+21530 روز
آرشیو پست ها
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔዎች ቅጽ 26 እና ቅጽ 27 ትን በመደብራችን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኙታል ።
ጃዕፈር መጸሐፍት
☎️0911932088
0911125324
❤ 18
Photo unavailableShow in Telegram
በበኃይሉ ገ/እግዛብሄር የተጻፉት " ኑሮ እና ፖለቲካ " የተሰኙት ባለ ሶስት ቅጽ መጻሕፍት ከረጅም ጊዜ በኋላ ሶስቱንም በአንድ መጽሐፍ ተካቶ ለንባብ በቅቷል :: መጽሐፉን በሁሉም መደብሮቻችን ያገኙታል ::
🥰 10👍 4🔥 2
ላለፉት 3 ወራት መቄዶኒያ ሲያሰባስበው የነበረውን 5 ቢሊየን ብር በ24 ሰዓት ውስጥ ከመላው ኢትዮጵያዊ ለማሰባሰብ የሚረዳ ድንቅ ሀሳብ የያዘ " በትረዳቢ " የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ በገበያ ላይ ዋለ።
ይህ የወጎች ስብስብ የሆነው መፅሐፍ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን ላይ እየተስተዋሉ ያሉትን ችግሮች ፤ በተለይም በማህበራዊ ፣ በኢኮኖሚያዊ ፣ በሀይማኖታዊ ፣ በፖለቲካው በአጠቃላይ በ " ዊ! " የሚያልቁ ህፀፆችን እየነቀሰ በቀልድ እያዋዛ ቁምነገር የሚያስጨብጥ አልፎም ተርፎም የመፍትሄ ሀሳቦችን የሚያመለክት አዲስ መፅሐፍ።
ይህንን መፅሐፍ በወፍ በረር ስንቃኘው ፤
1) ሀገራችን ከድህነት ማጥ ውስጥ ለመውጣት በግብርናው ፣ በማዕድን ፣ በቱሪዝም ዘርፎች በአጭር ጊዜ ውስጠ ለውጥ የሚመጣበትን መንገድ አቅጣጫ ይጠቁማል።
2) በቀደመውና አሁን ላይ ባለው ትውልድ መካከል ያለውን የባህል፣ የአስተሳሰብ፣ የታሪክ፣ የእሴት ክፍተቶችን ይጠቁማል።
3) በመዲናችን አዲሳባ ውሰጥ የህፃናት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እጥረትን ተከትሎ በየጫት ቤቱ፣ በየግሮሰሪውና በየሺሻ ቤቱ የታጎረውን የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ እንዴት መታደግ እንደምንችል ይጠቁማል።
4) ድህነት ኢትዮጲያ ከተባለች ቁና ላይ እየዘገነ በየሀገሩ እንደፈንዲሻ የበተናቸውን ዲያስፖራዎች ለሀገራችን እድገት እንዴት ልንጠቀምባቸው እንደምንችል አቅጣጫዎችን ይጠቁማል።
5) የ80ዎቹ ና የ90ዎቹን ትውልዶች ከልጅነት እስከ እውቀት ያሳለፉትን ጊዜ ማለትም አባባ ተስፋዬን ለማየት ቤት የወለወሉትን፣ አባሮሽ፣ አኩኩሉ ሌባና ፖሊስ፣ እሽኩኔታ፣ ውራተከት፣ ደስቶ ፊንገር፣ መላጣ ሜዳ ላይ ለበረኪና ዋንጫ ኳስ መራገጥ፣ ወንዝ ወርዶ መዋኘት፣ ሆያሆዬ መጨፈር፣ ከጉልቤ ተማሪጋ መደባደብ፣ ከት/ቤት በአጥር ዘሎ ህንድ ፊልም ማየት፣ ከጠላ ቤት ወላጅ ማምጣት፣ ሰኔ 30 ጠብቆ አስተማሪ መፈንከት.... የመሳሰሉትን ትዝታዎች በቀልድ እያዋዛ ልጅነታችንን ያስታውሳል።
6) ለሀገር ለወገናቸው ለፍተው አስታዋሽ አጥተው በየመንገዱ ላይ ንፋስ እንዳመጣው ፌስታል የተጣሉትን አረጋውያንን እና ምግብ፣ ልብስና መጠለያ አጥተው ወገን ባለበት ሀገር ማስቲሽ የሚስቡ ህፃናትን ከወደቁበት አንስተን መጠለያ የምንገነባበትን መንገድ ይጠቁማል።
ይህንን በሳቅ የደመቀ፣ በቁምነገሮች የታጨቀ፣ በመፍትሔ ሀሳቦች የተጥለቀለቀ መፅሐፍ አሁኑኑ በእጆ ያስገቡ።
❤ 15
Photo unavailableShow in Telegram
ማርክ ዳግላስ ትሪዲንግ ኢን ዘ ዞን በተሰኘ ርዕስ ስር የአመታት ምርምርና ተግባራዊ ልምዱን ነው ያካፈለው፣ በተለይ ትሬዲንግን እንደ ሞያ ይዘው ለመቀጠል ለሚሹ ሰዎች እጅግ አስፈላጊ ስንቅ ነው። ትሬዲንግ ኢን ዘ ዞን ወደ ትሬዲንግ በምንገባ ጊዜ የሚያጋጥሙንን
እንቅፋቶችና ፈተናዎች በጥልቀት የምንመለከትበት መፅሐፍ ነው። ለጀማሪዎች ብቸኛው እንቅፋት ገንዘብ የሚገኝበትን መንገድ ማግኘት ይመስላቸዋል። ጀማሪዎች ገንዘብ እንዴት እንደሚሰራ ካወቁ በኋላ፣ የብሮከሮቹን ምክር ታክሎ መግዛትና መሸጥ ብቻውን ሁሌም የሚያዋጣ አካሄድ እንዳልሆነ ሲገባቸው አስተማማኝ የትሬዲንግ ስትራቴጂ መገንባት እንዳለባቸው ይሰማቸዋል። ከዚያ በኋላ ትሬዲንግ ቀላል ይሆናል።
ማድረግ የሚገባህ ህጎቹን መከተል ነው።
ገንዘቡ ተከትሎ ይመጣል።
እጅግ በጣም በብዙ ኢትዮጵያዊያን ትሬደሮች ጥያቄ መሰረት በአማርኛ ተተርጉሞ ለንባብ በቃ!!!
❤ 23
00:29
Video unavailableShow in Telegram
ነገ እሁድ ኤግዚብሽን ማእከል አይቀርም
ከታላቅ ቅናሽ ጋር እንጠብቆታለን
ጃዕፈር መጸሐፍት
☎️
0911932088
0911125324
IMG_5738.MP42.32 MB
❤ 18🕊 2
በንባብ ለሕይወት የመጽሐፍ ኤግዚብሽንና ባዛር ላይ ሕይወት እምሻውን እና አበረ ሽፈራውን በአካል ታገኟቸዋላችሁ ::
❤ 16👍 6🔥 2
ንባብ ለሕይወት ዛሬ ተጀምሮል :: ለሶስት ቀን ብቻ ነው የሚቆየው :: ጃዕፈር መጻሕፍት መደብር በአይነት ብዛት ያላቸው መጻሕፍት ይዘን ቀርበናል ::
❤ 26🥰 2
01:03
Video unavailableShow in Telegram
ንባብ ለሕይወት ዛሬ ይጀመራል :: ለሶስት ቀን ብቻ ነው የሚቆየው :: ጃዕፈር መጻሕፍት መደብር በአይነት ብዛት ያላቸው መጻሕፍት ይዘን ቀርበናል :: በቅናሽ እንደምንሸጥ ሀገር ያወቀው ነው :: ኑ - ጎብኙን - ሸምቱነ ።
8.09 MB
❤ 16👍 5👎 1
ቅንጫቢ ከ"ሰኞ ማክሰኞ"
... ቤቱን ጥሎ የሚሄደው ለሚስቱ እንዳላት፣ ቢራ ለመቀማመስ አልነበረም፡፡ ሰው የማይበዛበት ካፌ ሄዶ ማሕሌትን ለማግኘት ነው፡፡ ማሕሌትና ሚስቱ ይተዋወቃሉ፡፡ ሚስቱ ግን፣ ከማሕሌት ጋር በሌላ ነገር አትጠረጥረውም፡፡ ካፌ ካገኛት በኋላ ጎተራ የሚገኘው ኮንዶሚኒየሟ ይሄዳሉ፡፡ ሚስቱ ስለዚህ ቤት ማለትም የቤቱ ቁልፍ እንዳለው፣ ከውዱ የቤት ኪራይ ግማሹን መክፈሉን ጨምሮ ምንም አታውቅም፡፡
በሉ ቻው አለ፡፡
ቻው ሚስቱም ልጁም ባንድነት ከዝላያቸው ሳያርፉ እየሣቁ መለሱለት፡፡
የሚስቱ ሁኔታ ከዚህ ቀድሞ የማያውቀው እንግዳ ስሜት አሳደረበት፡፡
የሰው ልጅ አርሶ መብላት ሳይጀምር አንስቶ የነበረው፣ ወንዶች በትዳራቸው ላይ የመወስለት ረጅም ታሪክ ውስጥ፣ እንዲህ ባለ ደስታና ጨዋታ ላይ ያለች ሚስቱን ጥሎ ከሌላ ሴት ጋር ሊማግጥ የሚወጣ እንደ እኔ ያለ ባል ይኖር ይሆን? ሲል ራሱን ጠየቀ፡፡
ሌላ ጊዜ፣ ግማሽ ጸጉሯ ከተያያዘበት ላስቲክ አምልጦና ተንጨብሮ፣ ያደፈ ሺቲ ለብሳ ስታጠባ፣ ወይ የእሱን ቱታና ዘልዛላ ቲሸርት ለብሳ የልብስ ማጠቢያ ማሽን ውስጥ ቆሻሻ ልብስ ስትጎሰጉስ፣ ወይ ወጥ ወጥ እየሸተተች ስትቀቅል፣ ወይ በልጆቹ ልብስ መበከት መነጫነጭ ስትጀምር ነው ጥሏት የሚወጣው፡፡
እንደዚህ በኮረዳነት ዘመኗ ከነበረ ውበቷ ጋር በሚስተካከል ሁኔታ አምራ፣ ሰውነቷ በሰኞ ማክሰኞ ጨዋታ እንደ ልጃገረድ ገላ ያለ ክልካይ እየነጠረ ወጥቶ የሄደበት ጊዜ ትዝ አይለውም፡፡
ባዶ እግሯን ናት፡፡
ቆንጆ ረጅም ሽፎን ቀሚስ ለብሳለች፡፡ ለጨዋታው እንዲመቻት፣ ከጉልበቷ በላይ ግማሽ ጭኗን እስኪያጋልጠው ጎትታ ይዛው ትጫወታለች፡፡ ቀይና ፈርጣማ ባቷ፣ ቀይ ለስላሳ ጭኗ ከእዚህ በፊት ዐይቶት፣ ከዚህ ቀደም ነክቶት እንደማያውቅ ቀሚሷን በእጇ ንቅናቄ ሽፍን ግልጥ ስታደርገው ያማልላል፡፡ ሦስት ልጆቹን አጥግበው ያጠቡ ጡቶችዋ ገና እንደደረሰች፣ ገና እንደታየች፣ ገና እንደጎመራች ጮርቃ ልጅ አብረዋት ሲዘሉ ስሜት ያባብላሉ፡፡
ሚስቱ በጡት፣ ባትና ጭን ንቅናቄ፣ አማላይና አፍዝ አደንግዝ ፈገግታዋ ሳትፈልግ እየጠራችው መሰለው፡፡
ዛሬ ምን ሆና ነው እንዲህ የምትሆነው?
የእሱ እንዳልሆነች ሁሉ ሰረቅ እያደረገ ደጋግሞ ዐያት፡፡
በኋላ፣ የተከፋፈለ ሐሳቡን ከቀጠሮው ጋር አስታርቆ ከግቢው ሲወጣ ዝላይዋን አላቆመችም ነበር፡፡
የዛሬውን ቀጠሮ ለመያዝ ያሳለፈውን ድብብቆሽ አሰበ፡፡
በመጀመሪያ ከሚስቱ ተደብቆ ተከታታይ ቴክስቶችን ላከ፡፡ የተላከው ቴክስት መድረስና አለመድረሱን ሳያረጋግጥ ልጆቹ፣ ጌም እንጫወት ብለው ወስደው ስልኩ እጇ ቢገባና የላኩትን ቴክስት ብታነበውስ? የሚል ሐሳብ ድቅን አለበት፡፡ የተላከውን ቴክስት ወዲያው አጠፋ፡፡
አሁንም ስልኩ እጁ በሌለበት (አሁንም ልጆቹ ጌም እንጫወት ብለው ወስደው)፣ ስልኩን መነጣጠቅ፣ መጣላትና ማልቀስ ቢጀምሩ ከሚነጣጠቁት ልጆቿ ቀምታ (ብዙ ጊዜ የሚሆን ነገር ነው) ለእሱ ልትመልስለት ስትል፣ ለተላከው ቴክስት የማሕሌት ምላሽ ቢገባና ብታየውስ? የሚል ሥጋት ሽው ሲለው፣ አይ ብደውልላት ይሻላል ብሎ ተነሳ፡፡ ወሬው እንዳይሰማ በረንዳ ላይ ወጥቶ በተደጋጋሚ ለማሕሌት ደወለ፣
የደውሉላቸው ደንበኛ መሥመሩን እየተነጋገሩበት ስለሆነ በመሥመር ላይ ይጠብቁ
ይሄ መልእክት ለደቂቃዎች ተደጋገመ (ከማን አባቷ ጋር እያወራች ነው? ብሎ ሲያስብ፣ ቅናት ቢጤ ሽው አለው)፡፡ ቆየት ብሎ ደወለ፣
የደወሉላቸው ደንበኛ መሥመር ስለተያዘ
እሷም ለመደወል እየሞከረች ነው ብሎ አሰበና ትንሽ ጠብቆ ድጋሚ ደወለ፤ አነሳች፡፡
ማሕሌት፣ ሃይ ማሬ ከማለቷ፣
የበረንዳው በር ተከፍቶ ሚስቱ፣ በዚህ ሰዐት እዚህ በረንዳ ላይ ምን ታደርጋለህ? ግባ እንጂ? ብርድ እኮ ነው አለችው፡፡
ስልኩን የማሕሌት ጆሮ ላይ ዘጋና፣ ለሚስቱ፣ እሺ ብሎ ቀጥታ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባና በሩን ቆለፈ፡፡ የመቀመጫውን ክዳን ዘግቶ እንደ ወንበር ሽንት ቤቱ መቀመጫ ላይ ዐረፍ አለ፡፡
ደወለ፣
የደወሉላቸው ደንበኛ ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ስለሆኑ ትንሽ ቆይተው ይደውሉ
ደሙ ፈላ፡፡ እንደገና ደወለ፡፡ ይጠራል ግን አታነሳም፡፡
እንደገና ደወለ፣
የደወሉላቸው ደንበኛ መሥመር ስለተያዘ…
እሷም ለመደወል እየሞከረች ነው ብሎ አሰበ፡፡ ደወለች፡፡
ሊያነሳ ሲል፣ አሞሃል እንዴ? በሰላም ነው ይህን ያህል ሰዐት ሚስቱ ነበረች፡፡
ደህና ነኝ ደህና ነኝ አላት፡፡ ተመልሳ መሄዷን ለማረጋገጥ ኮቴዋ ከበሩ እስኪረቅ ጠበቀና ስልኩን አነሳ፡፡ ለሹክሹታ በቀረበ ድምፅ ማሕሌትን አዋራና ስልኩን ዘጋው፡፡ እንዲህ መከራውን ዐይቶ ነው እንግዲህ ቀጠሮውን የያዘው፡፡
0
የተቀጣጠሩበት ካፌ ደርሶ ማሕሌትን ለመጠበቅ ቁጭ አለ፡፡ ብዙ ግዜ፣ እሷ ስለምታረፍድ፣ እንደተቀመጠ የሚያደርገው ነገር፣
ደርሻለሁ የት ነሽ? የሚል ቴክስት መላክ ነው፡፡ ሁሌ፣ እስክትመጣ፤ መጥታ ተያይዘው እስኪሄዱ፤ ሄደው ለብቻቸው እስኪሆኑ ድረስ፣ ይጓጓል፡፡
ስለዚህ፣ ደርሻለሁ የት ነሽ? ከሚለው ቴክስት በኋላ፣ ይደውላል፤ ከዛ በተከታታይ ቴክስት ያጣድፋታል፡፡
ዛሬ ግን፣ ባትመጣ ሲል ተመኘ፡፡ ገረመው፡፡ እስከዛሬ እንዲህ ያለ ስሜት ተሰምቶት አያውቅም፡፡
❤ 11👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
" Innovation Media and Communication Strategy for Development " By Neguse Tefera .
❤ 4👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በዶክተር አለማየሁ እሸት የተዘጋጀውና ታሪካዊ ልቦለድ ይዘት ያለው " ባህራን " የተሰኘው መጽሐፍ ለንባብ በቃ ::
👍 17❤ 6👎 3⚡ 1
Photo unavailableShow in Telegram
" የአዳም ቁጥር " የተሰኘው የምሕረት መስፍን የግጥም መድብል ለንባብ በቃ :: መጽሐፉን በመደብሮቻችን ሁሉ ያገኙታል ::
👍 23❤ 3
