️ ንስር አማራ🦅
رفتن به کانال در Telegram
የተቀደሰን ነገር በእግሩ ለሚረግጥ ፥ተመልሶም ያጎረሰውን እጅ ለሚናከስ ርኩስ መጫወቻ የማይሆን የነቃ ማህበረሰብ እስክንፈጥር ድረስ ብዕራችን አይነጥፍም። አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ። 💚💛❤️ እኛን በውስጥ ለማናገር @NISIREamhra2 @NISIREamhraa_bot 👈 ይችን አድራሻ ይጠቀሙ🦅 ንስር ዐማራ🦅 #የግፉአን_ድምፅ t.me/NISIREamhra
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

63 179
مشترکین
-5024 ساعت
-2527 روز
-80230 روز
آرشیو پست ها
🔥የደጋው መብረቅ ኮር ለበርካታ ወራቶች ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ፋኖዎችን በደማቅ ትርዒት ታጅቦ አስመረቀ‼️
አፋብኃ ምስርቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ለአራተኛ ዙርና ለበርካታ ወራቶች ሲሰለጥኑ የነበሩ የእግረኛ ሰልጣኝ ፋኖዎች በዛሬው እለት በድምቀት ተመርቀዋል።
በአንሻ ክፍለ ጦር ለአራተኛ ዙርና ለበርካታ ወራቶች ሲሰለጥኑ የነበሩ እግረኛ ሰልጣኞች በደማቅ ትሪዕታዊ ሰልፍ ታጅበው ታህሳስ 9/2018 ዓ/ም ተመርቀዋል።
በምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ የኮሩና ክፍለ ጦሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኮሩ ም/ዘመቻ መምሪያ አርበኛ ጨለፍ ተስፋው "እናተ የአማራ ህዝብ ሰራዊት ናችሁ በአማራ ህዝብ ላይ የተጋረጠውን ዘር ተኮር ስርዓታዊ አዳጋ አከርካሪውን ሰብራችሁ የህዝባችሁን ህልውና እውን ማድረግ ይጠበቅባችኋል ሲል መልክቱን አስተላልፏል::
አርበኛው ንግግሩን በመቀጠልም የአማራ ህዝብ ከፈጣሪው በታች ከናንተ መዳፍ ሰላሙን እድትሰጡትና ህልውናውን እንድታረጋግጡለት ተስፋ አድርጓል። ተወደደም ተጠላም እኛ አማራዎች መዳኛ መንገዳችን ክንዳችን ላይ ያለው ነፍጣችን ነው። ተገደን በራፋችን ድረስ ገዳዮቻችን መጥተው ነፍጣችንን እናነሳ ዘንድ አድርገውናል። ለዚህ ደግሞ መሰልጠን፣ መታጠቅና ዘመኑ የሚዋጀውን ሆኖ መገኘት ይጠበቅብናል። ያለን አማራጭ አንድና አንድ ማሸነፍና ማሸነፍ ብቻ ነው" ሲሉ መልክቱን አስተላልፏል!
በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የቃል ኪዳን መርሃ ግብርም የነበረ ሲሆን ተመራቂ ፋኖዎች ከስልጠና ባገኙት ሙያዊና ወታደራዊ እውቀት ህዝባቸውን በታማኝነት ለማገልገልና የህዝባቸው መዳኛ ዘብ ሆነው መቆም እዳለባቸው ቃል ኪዳን ፈፅመዋል::
እየተዋጋን እንሰለጥናለን እየሰለጠን እንዋጋለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል
❤ 86🏆 12👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
🔥አፋብኃ ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር‼️
1. ጉና ክፍለ ጦር
👉እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ
የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት አለኝ ያለውን የፈጠራ ፕሮፖጋንዳ ለመፍጠር ቢሞክርም መሬት ላይ ያለውን መራራ ዕውነታ መቀልበሥ አልቻለም። አገዛዙ ሆዳም አማሮችን ሆድ ሞልቶ፣ ወዶ ገብ አማሮችን ተጠቅሞ፣ ጥቁር አማሮችን ከፊት አሰልፎ፣ የጫካው ብአዴኖችን አሰባስቦና በጥቅሉ ፀረ አምሐራ አካላትን ሁሉ ይዞ የአማራ ፋኖን ትከሻ ለመለካካት ይሞክራል።
በዕለተ ሐሙሥ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ የነውረኛውና የአማራ ጠሉ ብልጽግና አገዛዝ ወንበር ጠባቂ መከላከያ ተብየው፣ አድማ ብተና፣ ሚሊሻ እና ፖሊስ በፈለገው መንገድ ታጣቂውን አሰልፎ ከቅዳሜ ገበያ እሥከ ጥናፋ፣ ከሾለክት እሥከ ደንጎልት #ቆሪጥ(በለጠቸች አንዳርጌ)ን ይዞ በእሥቴ ዴንሳ ብርጌድ አካል በሆነችው አንዷ ሻለቃ ላይ በሌሊት ጥቃት ለመፈጸም ቢሞክርም የባዬው መልካሙ ልጆች፣ የጥንቅሹ ትግል አሥቀጣዮች፣ የገብርዬ ጦር ገበሬዎች፣ የፍቃዴ ራዕይ አሥቀጣዮች፣ የአበበ ፊታውራሪዎች እና ፈለገ ውባንተ አባተዎች የቆሪጥን ጭፍራዎች በመጡበት መንገድ አሥተናግደዋል።
አራዊት ሰራዊቱ በአንዷ ሻለቃ ላይ ዘመቻ ለማድረግ ሲንቀሳቀስ 02ቱ ሻለቆች ደግሞ ጠላትን እያጨዱ መሐል መካነኢዬሡሥ ከተማ በመግባት ማቢ አቦ፣ 03፣ 01፣ ደንጎልት፣ መሐል አደባባይ እና ሌሎች የከተማዋ ክፍሎች ላይ ውጊያ በማድረግ ጠላትን ደምስሰዋል። መካነ ኢዬሡሥ ከተማንም ተቆጣጥረዋል።
ውጊያ የተደረገባቸው ቦታዎችም፦ ቅዳሜ ገበያ፣ ደስኳ፣ አጭቃን፣ ደንጎልት፣ ሾለክት፣ ማቢ አቦ፣ 03፣ 01፣ መሐል መካነ ኢየሱስ አደባባይ፣ አሥተዳደር፣ ጥናፋ እና ሌሎች የከተማው እና ዙሪያ ገባው መዳረሻዎች ናቸው።
ጥበበኞቹ የባዬው፣ ገብርዬ፣ የጥንቅሹ፣ አበበና ፍቃዴ ወንድሞች ጠላትን ሲገርፉት ውለዋል። መካነ ኢየሱስ ከተማ በጅምላ የታሰሩ አምሐሮች በአማራ ፋኖ ክንድ ነጻ ተደርገዋል።
በዚህ አውደ ውጊያ የተሳተፉ ተጨማሪ የጉና ክፍለ ጦር አካላትም፦
👉የጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚና የክፍለ ጦሩ ቃኝና መሐንዲሥ
👉ሐገረ ቢዘን ብርጌድ
👉መቅደላ አምባ ብርጌድ/ናደው ሻለቃ ሲሆኑ በተጨማሪም
👉የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ከደቤረ ታቦርና ከደራ ወደ እሥቴ እንዳይገባ ''ግንዳ ጠመም'' ከተማ ላይ ዘግተው ጠላት እንዳይንቀሳቀስ አድርገውታል።
በጠላት ላይ የተገኙ ዝርዝር ድሎችም፦
✅የተደመሰሰ 17
✅ቁሥለኛ 33
✅የተማረከ ክላሽ 08
✅ ተተኳሽ 1500
✅የፖለቲካ እሥረኞች 56 ናቸው። ተጨማሪ የድምሰሳና ምርኮ መረጃዎችን በቀጣይ እናሳውቃለን።
2.ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር
የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ከአርብ ገበያ ተነሥቶ ማክሰኝ ወደተባለች ከተማ በመሄድ 02 ሞተሮችን እና 06 የአርሶ አደር ክላሽ ዘርፎ ወሥዷል። ጠላት የዘረፈውን ዘርፎ ያወደመውን አውድሞ ወደ አርብ ገበያ እየተመለሰ እያለ በተሰራ የደፈጣ ጥቃት ቁጥራቸው ያልታወቁ የመከላከያ አባላት እሥከወድያኛው ሲሸኙ በርካታ ቁሥለኞች መኖራቸውም ተረጋግጧል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን✊
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA✊
©አፋብኃ ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
09/ዐ4/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 110🙏 12👍 5
🔥#ግባ_በለው‼️
ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለ ሽርጡ ክፍለጦር መርሳ ግንባር ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም የማረኩት መሳሪያና ተተኳሽ ጋር በምስል ማስረጃ!
❤ 72👏 9👍 7
Photo unavailableShow in Telegram
🔥#የሻለቃ አዛዡ ከ12 ወታደሮች ጋር #ተደመሰሰ‼️
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ጥላሁን ፈንታው ብርጌድ የፋኖ ኃይል መካነሰላም ዙሪያ ወረዳ ቢሊ ታዳጊ ከተማ ውስጥ ከማለዳው 11:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 5:00 ሰዓት በተደረገ ውጊያ የጥላሁን ፈንታው ብርጌድ ፋኖዎች ከፍተኛ የጦር ሜዳ ጀብዱ በመፈፀም 15 ወታደሮችን እና የ45ተኛ ክፍለ ጦር ሻለቃ አዛዥን ደምስሰዋል:: በዛሬው ተጋድሎ ቁጥራቸው በውል ባይታወቅም በርካታ ወታደሮች ቆስለዋል:: ቁስለኞች በአምቡላንስ ተጭነው ወደ መካነሰላም ጄኔራል ሆስፒታል ተወስደዋል::
የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰብሳቢ ሻለቃ አብነው ታደሰ እና የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር አዛዥ አርበኛ ስንደው ገዜ በመሩት ውጊያ ቢሊ ላይ ዛሬ ታህሳስ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ታላቅ ድል ተመዝግቧል:: የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር 45ተኛ ክፍለ ጦር የመካነሰላም ቀጠናን መሸፈን አልቻለም ተብሎ ሰሞኑን የ47ተኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት በድጋፍ ሰጭነት ወደ መካነሰላም መግባቱን ተከትሎ የፋሽስቱ አብይ መንግስት መጠነ ሰፊ ወረራ ለመፈፀም አስቦ የመጀመሪያ ሙከራውን ዛሬ ቢያደርግም ድል ሳይቀናው ቀርቶ አባላቱን አጥቷል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
09/ዐ4/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 78👍 4👏 4
🔥ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር ውጫሌ ከተማ ዙሪያ ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገቡ‼️
ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር የአምባሰል ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ውጫሌ ከተማ ዙሪያ ዛሬ ታህሳስ 9/2018 ዓ.ም ንጋት 12:00 ጀምሮ ወደ ጠላት ምሽግ ዘልቀው በመግባት ባደረጉት ከባድ ተጋድሎ እስከ ቦምብ ጭምር በመጫበጥ በርካታ የጠላት ሃይል ደምስሰውና አቁስለው ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አስመዝግበዋል::
24ኛ ክፍለጦር በተጋድሎው ውጫሌ ከተማ ቁንጥሮ ላይ የጠላትን ምሽግ ሁሉ ደምስሰው በመግባት ትልቅ ጀብድ የፈፀሙ ሲሆን ከ40 በላይ የጠላት ሃይል ሙትና ቁስለኛ አድርገው ለጊዜው ቁጥሩ ያልታወቀ የነፍስ ወከፍ ክላሽና የተለያዩ ተተኳሾችንም ማርከዋል::
የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ከተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢ እና ከኦሮሞ ብልፅግና ልዩ ሃይል ጭምር ታፍሶ ሲመጣ በምድር በመካናይዝድና በአየር ሃይል ጄትና ድሮን ከፍተኛ ድጋፍ ሊደረግለት ቃል ተገብቶለት መጥቶ ውጊያ እያደረገ ያለ ሲሆን አየር ንብረቱ ለድሮን በማይመችበት በዳመና ጊዜ ወኔው ተሰልቦና ውጊያ ከብዶት በጅምላ እየተደመሰሰ እና እየተማረከ ይገኛል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምኒልክ ዕዝ
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
09/ዐ4/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 44👍 20🙏 9💔 4
🔥#ዘመቻ_ማጥራትና_ማፅናት‼️
አዲሱን የድርጅታን የአደረጃጀት ማሻሻያ ተከትሎ ወደ ትግላችን ሰርገው የገቡ የጠላት የተልዕኮ እጆች ቀን በቀን እየተቆረጡ ይገኛሉ። የሰራዊታችንን አደረጃጀት በሻለቃ፣ በክፍለጦር፣ በኮር እና በዕዝ መልሶ ከማደራጀት ጎንለጎን በሂደት ሀገር ተራካቢ ሰራዊትና አመራር ለመፍጠር በሚያስችል አግባብ ተቋማዊነትን በጊዜያዊ የመንግስት አስተዳደር መዋቅር ውስጥ ጭምር እየተለማመደ የሚሄድ ድርጅታዊ የማጥራትና የማፅናት ዘመቻ ላይ እንገኛለን።ይህንን ዘመቻ ተከትሎ የጠላትን ስውርና ግልፅ የማፍረስ ተልዕኮ ወስደው በትግላችን ውስጥ ተሰግስገው ትግሉን ሲታገሉ የቆዩ ግለሰቦች የመዋቅር ማሸሻያውን ተከትሎ ወደ እናት ድርጅታቸው እየተመለሱ ይገኛሉ። ወቅቱ ፍሬውን ከገለባው፣ብስሉን ከጥሬው እና ለዓላማው የቆረበውን ቁርባን ከሚያፈርሰው የምንለይበት የማጥራት እና ያጠራነውን የምናፀናበት ወቅት ነውና ሜዳችን ስላልተመቻቸው ወደ እናት ድርጅታቸው በሚሄዱ ባንዳዎች አትሸበሩ።እንዳትልሰው እሳት ሆነባት እንዳትተወው ልጅ ሆነባት እንደተባለችው ወላድ ላም ሆኖብን ነው እንጂ እነዚህ ግለሰቦች ከትግላችን ሜዳ እንዲሸሹ የፈለግነው ገና በትግሉ ጅማሮ ወቅት ነበር። ስለሆነም በሩቅም በቅርብም ያላችሁ የትግላችን ደጋፊዎች ሁሉ ዓላማው አልሳካለት ሲል ወደተልዕኮ ሰጭው በሄደው ባንዳ ሳታዝኑ ከህዝባዊ አላማው ጋር ቆርቦ ከድርጅታን ጋር መስዕዋትነት ለመክፈል በፀናው ታጋይ ደስ ይበላችሁ።
©አርበኛ ዳሞት አለኸኝ 206ኛ ኮር ሰብሳቢ
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
09/ዐ4/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 77🙏 8👍 4
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ለከበባ *ቦታ ላይ ከለሊቱ 7:00 የመጣን ጠላት ከለሊት ጀምሮ እስከ አሁን እየቀጠቀጠው ነው💪
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
09/ዐ4/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 56👍 18
🔥#በልፅግና_ፀሀይ_ላይ_እንደተቀመጠ_በረዶ_ነው‼️
በወቅታዊ ጉዳይ ማለትም
👉ስለ አማራ ፋኖ ትግል
👉እጅ እየሰጡ ስላሉ ሰዎች
👉ከሰሞኑን የፋኖ ዝምታና የአገዛዙ ወረራ ምክንያትና ሌሎች ጥያቄዎችና ምላሾችን የያዘ ውይይት ከአርበኛ ግሩም ምሳሌ (የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ም/ፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ጋር የተደረገ ቆይታ ተጋበዙ‼️
"የምናስተዳድረው ህዝብና ነፃ ቀጠና መሸከም ከሚችለው የሰራዊት ብዛት ከምንገምተው በላይ ከፍ ስላለ አደረጃጄቱን እያዘመን ነው!!"
አርበኛው
https://youtu.be/jNPL25vsHkk?si=aVSpAq5OZn0Wt0pg
❤ 55👍 18
05:20
Video unavailableShow in Telegram
🔥ታፍነው ወደ ማሰልጠኛ ቦታ ሲሄዱ የነበሩ የአማራ ህጻናት በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሀንዲስ ሻለቃ ከመንገድ ላይ መማረክ ተችሏል‼️
ሕፃናትን ለጦርነት ማዋል አለማቀፋዊ ወንጀል ነው። ይህን በመተላለፍ የብልፅግና አረመኔ አመራር በተደጋጋሚ ህፃናትን ከትምህርት ቤት እየመለመለ ወደ ስልጠና እየላከ በጦርነት እያስጨፍጭፍቸው ይገኛል። በውጊያ የማረክናቸው ሕፃናትም የስነልቦና ጫና ውስጥ በመግባታቸው የጤና መታወክና የአዕምሮ ሰላም እንዳጡ በተለያዩ ጊዜ ያረጋግጠው ጉዳይ ነው።
ይህን የመከላከል ሀላፊነት የወደቀበት የአማራ ፍኖ በተለያዩ ጊዜ ስልጠና እንዳይገቡ በደፈጣ ከነመኪና በመማረክ የስነልቦና ስልጠና እና የተሀድሶ ስልጠና እየሰጠ ወደ ቤተሰቦቻቸው መላኩን ተያይዞታል። ከዚህ በፊትም ደብረማርቆስ ዙሪያ በበረኸኛው ጅበላ ብርጌድ በርካታ ህፃናትን በ2016ዓ.ም ማስለቀቁ የሚታወስ ነው።
ዛሬም ታፍነው ወደ ማሰልጠኛ ቦታ ሲሄዱ የነበሩ የአማራ ህጻናት በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሀንዲስ ሻለቃ ከመንገድ ላይ በመማረክ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
©አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ታህሳስ 09/2018 ዓ.ም
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
09/ዐ4/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
41.83 MB
❤ 58👍 6
🔥#መረረኝ_እንደሬት‼️
ስቀምሰው መረረኝ
አለኝ አልዋጠኝ
እንደገና ከፋኝ።
ሆነብኝ እንደኮሶ
የሀገሬ ስቃይ መጣ ተመልሶ
ከፋኝ እንደገና መረረኝ እንደሬት
እንዴት ሰው ባገሩ መቀመጫ ማጣት
ኧረ ተነስ ጎበዝ ኧረ ተነስ ወጣት
አንድ ላይ እንሁን ጠላትን እንመክት
ወንድምህ ጓዳኛህ ሲገደል ዝምብለህ መመልከት
መች ይሆናል እና በተናጠል መሞት
አንተንም አይለቅህ ይመጣል ነገ ጧት።
ኧረ አማራው ምረር ኧረ አማራው ተነስ
ባንዳ መጦልሃል ታሪክን ለመውረስ
አንት ያማራው ፋኖ አንተ የኔ አለኝታ
ተኩሶ የማትስት ግንባር የምትመታ
ኧረ ናልኝ ፋኖ የሀገሬ ዋልታ።
ኧረ የምሬን ነው ፋኖን እመወደው
ከግንባራቸው ላይ ፍቅሩ ታዘባቸው
ዱአንም ጨምረው ድርሳን ይደግማሉ
በድሽቃ በሞርተር ዝናብ ያዘንባሉ።
ለጠላት ጭንቀት ነው ለወዳጅ ደስታ
ሳሚዬ ደሳለኝ ያማራው መከታ
ያ ዘመነ ካሴ እነ ሀብቴ ወልዴ ያሳምነው ልጅ
ለፀብ አይመቹም ለፍቅር ነው እንጅ።
ሌባው ቢከዳ ቢሰናበት
እንዳትወላውል ፋኖ መክት
አማራነት ነው ያንተ ኩራት።
የጎጃሙ ልጅ ጀግናው ዘመነ
ስሙ ሲጠራ ጥላት በነነ።
የሸዋየው ልጅ ናልኝ ደሳለኝ
ዋልታ መከታ ያላንተም የለኝ
የጎንደር ጀግና ሀብትዬ ወልደ
ጠላቱን ነዳው እያሳደደ።
የቤተ አማራው የወሎ ጀግና
ምሬ ወጃጆ ቆራጥ ሳተና
ባንዳ ይርዳል ይንቀጠቀጣል
ፋኖ ሲነሳ እግሬ አውጭኝ ይላል
እንኳን ተኩሶ ስሙ ያስፈራል
ያማራው ፋኖ አንገት ይበሳል
ይቆያል እንጅ ድል መች ይቀራል።
አንድ አማራ ብለህ ተነስ
ጎጃም ሸዋ ወሎ ጎንደር
አትከፋፈል በጎጥ በመንደር
እንዲያ ስሆን ነው ድል የምበስር።
አመሰግናለው!!!
አንድ አማራ☝
አድስ ትውልድ፣ አድስ አስተሳሰብ ፣ አድስ ተስፋ
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
ድል ለፋኖ!!!!!!!!!!!!
ገጣሚ ከ***ዩንቨርስቲ የንስር ቤተሰብ
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
09/ዐ4/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 131👍 28🙏 4🏆 3😍 1
Photo unavailableShow in Telegram
🔥#ትንቅንቁ_አሁንም_እንደቀጠለ_ነው‼️
ከደንበጫ በሌሊት በተለያዩ ሶስት አቅጣጫ ተነስቶ ወደ ኮረብታ ቀበሌ ለመግባት የሞከረውን የጠላት ሀይል የ201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦር ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ እስከ 12:00 ሰዓት ድረስ ከፍተኛ የሆነ ትንቅንቅ በማድረግ ልዩ ቦታው #ትግሬ_ደብደቦ፣ወይንም #ጉላማዶ እና #አደራካብ ላይ በመጣበት እግሩ እንደእባብ ተቀጥቅጦ የተመለሰ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ልዩ ቦታው #ዋንባ ላይ ጠላት በከበባ ውስጥ ይገኛል ።
በደረሰበት ከፍተኛ ምት ዋዳን ፂወን 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በመግባት ሙሉ ቁሳቁሶችን ያወደሟቸው ሲሆን ትንቅንቁ እንደቀጠለ ነው።
♦️♦️አዲስ ትውልድ፣♦️
📍አዲስ አስተሳሰብ፣📍📍
💧💧አዲስ ተስፋ💧
ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም
©የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
08/ዐ4/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 103👍 33💔 7🏆 5🎉 2
Photo unavailableShow in Telegram
🔥#ሰበር_ዜና‼️
የብልፅግና ሰራዊት 37 አስከሬኑን ጥሎ በሸሸበት ፍልሚያ የምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት በመቶ የሚቆጠር ጠላት በመደምሰስ እና በማቁሰል እንዲሁም የቡድን እና በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::
የምስራቅ አማራ ኮር አንዱ ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር እና የምስራቅ አማራ ኮር ሁለቱ ታጠቅ ክፍለ ጦር ዛሬ ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ መርሳ ከተማ ዙሪያ በጥምረት ባደረጉት ከባድ ተጋድሎ በመቶ የሚቆጠር ጠላት በመደምሰስና በማቁሰል እንዲሁም የቡድን እና በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
ጠላት ከመርሳ ከተማ በምዕራብ በኩል ያሉ የፋኖ ቀጠናዎችን ለማጥቃትና ከቻለም ለመቆጣጠር አቅዶ በብዙ ግንባሮች ማለዳ በጀመረው ውጊያ የዋርካው ልጆች ባደረጉት ከባድ መከላከልና መልሶ ማጥቃት በመቶ የሚቆጠር ጠላት በመደምሰስና በማቁሰል ብሎም የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ወደ መርሳ ከተማ የሸኙት ሲሆን 37 አስከሬኑንም ሳያነሳም እግሬ አውጭኝ ብሎ ለመሽሽ ተገዷል::
በተጋድሎው በምርኮ የተገኙ ድሎች፦
ምስራቅ አማራ ኮር 2 ታጠቅ ክፍለ ጦር
•1 ብሬን
•23 ክላሽ
•1393 የክላሽ ተተኳሽ
•700 የብሬን ተተኳሽ
•17 የደረት እና 8 የወገብ ትጥቅ
•12 ምርኮኛ (አራቱ የቆሰሉ)
ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለ ጦር
•11 ክላሽ
•1800 የብሬን ተተኳሽ
•1500 የክላሽ ተተኳሽ
•7 የደረት እና 4 የወገብ ትጥቅ
•7 F1 ቦምብ
• 950 ስቃጥላ የታሸገ ምግብ
በአጠቃላይ ምኒልክ ዕዝ በተጋድሎው በሁለቱ ክፍለጦሮች አማካኝነት አንድ ብሬን 34 ክላሽ እንዲሁም ከ5300 በላይ ተተኳሽና የእጅ ቦምቦችን ጨምሮ በርካታ ንብረቶችን ያገኘ ሲሆን ከ950 በላይ ስቃጥላ የታሸገ ምግብም አግኝቷል::
በቀጣይ በተጋድሎው በምርኮ የተገኙ ድሎችን የቪዲዮ እና የምስል ማስረጃዎችን የምናደርስ ይሆናል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
08/ዐ4/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 150👍 15🙏 15🎉 5
Photo unavailableShow in Telegram
🔥#አዎ_ፅንፈኞች_ነን‼️
የጥላቻ መርዝን ተግቶ በተሳሳተ የፖለቲካ ትርክት ተመርቶ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ሰማይ ስርም ብቻ ሳይሆን ከሰብዕና ካርታ ጭምር እስከ ወዲያኛው ፍቀው ሊያጠፉን በመጡ ጠላቶቻችን ላይ ያለን አቋም የማያወላዳ እና መሃል ሰፋሪ ተብሎ ሊገለፅ የማይችል ነው።በስመ ሚዛናዊነት አምርረው በሚጠሉን ጠላቶቻችን ላይ ያለንን አመለካከት እና እይታ እንድንቀይር በማሰብ በየመድረኩ እና በየሚዲያው ፅንፈኞች ለምትሉን መልሳችን አዎ ፅንፈኞች ነን ነወ።መሃል ሰፋሪ በ2 ጥይት ይመታል እንዲሉ አበው ከምድረ ገፅ ሊያጠፋን ያለ የለለ አቅሙን አሰባስቦ ለመጣ ፅንፈኛ ጠላት በስመ አመክኒዮ እና ሰብዓዊነት ግልብ ካባ ተሸውደን በአንድ ጊዜ ግንባራችንን እና ጀርባችንን ተመትተን #ለመውደቅ አንፈቅድም።መስመራችን ጥርት ያለ እና የማያወላዳ በሆነ ቁጥር በጠላት ካምፕም ሆነ በወገን ካምፕ የጠላት የተልዕኮ የኮርቻ ፈረስ የሆነው ሁሉ ፅንፈኛ ቢለን ለሴኮንድም #ከዓላማችን አንድ ጋት ፈቀቅ እንዳንል ያደርገናል እንጂ በተራ ፕሮባጋንዳቸው አንሸበርም። ሓዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም እንኳን ወንጌልን ለአህዛብ ለማስተማር በወጣበት ጊዜ የዘመኑ ገዢዎች እና ጋሻ ጃግሪዎች ፅንፈኛ እና አሸባሪ የሚል ክስ ማቅረባቸውን ልብ ይሏል።
©አርበኛ ዳሞት አለኸኝ
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
08/ዐ4/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 158👍 34🏆 8
Photo unavailableShow in Telegram
የደብረወርቅ ሟቾች ስም ዝርዝር‼️‼️
በጀብደኞቹ የ74ኛ ክ/ጦር ተዋጊዎች ወደ አፈርነት የተቀየሩ ባንዳዎች ስም ዝርዝር ደርሶናል ለቅሶ ላልደረሳችሁ የብልፅግና ማህበርተኞች እነሆ:-
01_ደመላሽ ካሳ የወረዳ አስተዳደር መረጃ ሀላፊ
02 _ሳጅን ምትኩ ሞላ ፖሊስ
03 _ሳጅን እንዳወቀ አማረ ፖሊስ
04 _አልኸኝ አያል ሚኒሻ
05 _ይሔነው እንዳላመው ሚኒሻ
06 _ጌታየ ቢረሰው ሚኒሻ
07 _ባየ አልሀኝ ሚኒሻ
08 _ያለው ታረቀኝ ሚኒሻ
09 _ተዋቸው አፍኔ ሚኒሻ
10 _ጌታሠው እስካሁን ሚኒሻ
11 _ካሰው አቻም ሚኒሻ
12 _አሰፋ ማርኬ ሚኒሻ
13 ጌታሰው ቢረሰው ሚኒሻ
እነዚህ በስም የታወቁት ሲሆኑ በስም ያልታወቁ ከ15 በላይ ሚኒሻ አለ በተጨማሪም (35 ) መከላከያ ተደምስሷል። 17 ሆስፒታል ከገቡ ቁስለኞች መካከል (2) ቱ ደይመዋል።
ውጊያውን የመራችሁ ጓዶቹ ክብር ይገባችኋል‼️‼️
👍 101❤ 87🙏 18👏 14😢 6🏆 1
🔥የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ቆቦ ከተማ ዙሪያ ከባድ ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገቡ‼️
የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ አሃድ ቆቦ ከተማ ዙሪያ ልዩ ስሙ ካራኤላ የተባለ ቦታ ላይ መሽጎ ያለ ጠላት ጋር ትናትና ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም ጧት 3:00 ጀምሮ እስከ ምሽት 1:00 ድረስ በተደረገ ተጋድሎ ከ30 በላይ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በመደምሰስና በማቁሰል ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
ቆቦ ከተማ ዙሪያ ካራኤላ የተባለ ቦታ ላይ መሽጎ ያለ ጠላት ወደ በዋ ሚካኤል እስከ ተኩለሽ ለመቆጣጠር በማሰብ ማጥቃት ያደረገ ሲሆን ልዩ ዘመቻዎቹ ባግባቡ በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ እስከ ቆቦ ከተማ ጫፍ ድረስ ተከትለው በመምታት ከባድ መሳሪያውን ጨምሮ ይዞ እንዲሸሽ አድርገውታል::
በልዩ ዘመቻ ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ የደረሰበት ጠላት እንደለመደው የበቀል አፈ ሙዙን ወደ ንፁሃን በማዞር ሞርተርና መድፍ በማስወንጨፍ የንፁሃንን ህይወት ቀጥፏል:: ከሰው ህይወት በተጨማሪ ቤትና ንብረትም አውድሟል እንስሳቶችንም ጨፍጭፏል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
08/ዐ4/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 63👍 4🎉 3👏 2
🔥#የድል_ዜና‼️‼️
═══❁✿❁═══
በዛሬዉ እለት በቀን 08/04/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃ ከይላላ እስከ ጃሂማላ ሰፊ ቀጠና በሸፈነዉ አዉደ ዉጊያ በጠላት ላይ ድልን መቀዳጀት ችሏል።
በዚህም መሰረት ከ20 በላይ የጠላት ሀይል የአብይ አህመድ ቅጥረኛ ተላላኪዎችን መደምሰስ ሲቻል በርካቶችን ደግሞ ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል ሲል የ105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ር ህዝብ ግንኙነት ገልጿል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ❕
©የአፋብሀ ምዕ/አ/ቀ/ቴዎድሮስ -ዕዝ የ105ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት ፍሬዘር መንግስት ዘለቀ
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
08/ዐ4/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 65👍 4🙏 2
🔥ላስታ አሳምነው ኮር ከ32 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት በመደምሰስ እና ከ50 በላይ በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፀፉ‼️
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር በድብኮና ግራር አምባ እንዲሁም ዳቦ ከተማ ቀጠናዎች በወሰደው የተጠና የደፈጣ ጥቃት በጠላት ላይ ታላቅ ድል ተቀዳጀ።
ታህሳስ 07/2018 ዓ/ም ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የአገዛዙ ብልፅግና ልሳናት የላሊበላ ከተማ አስተዳደር፣የላስታ ወረዳና የቡግና ወረዳ የካቢኔ አባላትን ከጋሸና ወደ ላሊበላ ከተማ ለማሳለፍ የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ከጋሸና እርፋ እስከ ግራር አምባ ዘርግቶ የነበረ ቢሆንም የኮሩ ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ እና ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር ሁለት ሻለቃዎች በድብኮ ቀጠና እንዲሁም በዳቦ ከተማ ቀጠና እሸት ክፍለ ጦር ሁለት ሻለቃዎች ደፈጣ በመጣል ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውት ጠላት ሙትና ቁስለኛውን እያንጠባጠበ ሊሄድ ተገዷል።
በዚህ የደፈጣ ጥቃት 32 የአገዛዙ ሰራዊት ሲደመሰስ ከ50 በላይ የቆሰለ እንዲሁም ዙ-23ቱ በዲሽቃ ተመትቶ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን በዚህ የተበሳጨው የአገዛዙ ሰራዊት ዙ-23 በዘፈቀደ በመተኮስ የሦስት ንፁሀንን መኖሪያ ቤትና አምስት የአርሶ አደር የጤፍ ክምር እስከ 35 ኩንታል ሊወጣ የሚችል እህል ያቃጠለ ሲሆን በአራት ንፁሃን ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት አድርሷል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ታህሳስ 06 ለ 07 /2018 ዓ/ም ሌሊት በአቢሰግ፣በሙጫ በረት፣በእርፋ፣በታሎ ደብር አቅጣጫ እሸት ክፍለ ጦርን እርፋና ገለሶት ላይ አፍናለሁ ብሎ የመጣን የአገዛዙን ሰራዊት እሸት ክፍለ ጦር አንገቱን አስደፍቶ እንደመለሰው መዘገባችን ይታወቃል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
07/ዐ4/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 115👍 38🏆 14💔 10
Photo unavailableShow in Telegram
🔥#ግባ_በለው💪
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ጠገዴ / ማክሰኞ ገበያ ወረዳ ደቅ አባ ጊዮርጊስ ተብሎ ከሚጠራዉ ስፍራ አስደማሚ ተጋድሎ በማድረግ የማረከው የጦር መሳሪያና የአገዛዙ ሚሊሻ ሀይል‼️
ማጥራትና ማብቃት እንዲሁም ማጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል!!
#ባንዳ_እጅ_ስጥ ‼️
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
07/ዐ4/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 86👍 38🏆 5👏 4
🔥መልሶ ማደራጀቱን በማጠናቀቅ ከተሞችን ታርጌት ያደረገ ውጊያ እያደረግን እንገኛለን‼️
የአፋብኃ ቴድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር የጠላትን ካምፕ በጥልቀት በማጥናት በሌሊቱ በ5 የተለያዩ ቦታወች ውጊያው በመክፈት የ74ኛ ክ/ጦር ከ5ቱ ሬጅመንቶች የተውጣጣ ሃይል እና የክ/ጦሩ ቃኝ እና መሃንዲስ በውጊያው ተሳትፈውበታል።
ዉጊያውንም በወርቁ ማደያ፣ በፖሊስ ጣቢያው ፣ በጠዛ ወንዝ፣ በአዲሱ ገበያ እና በቴክኒክ በኩል ሙሉ ከበባ በማድረግ የደ/ወርቅ ፖሊስ ጣቢያን ጨምሮ ሙሉ ከተማዋን ለ6:00 ተቆጣጥሮ ቆይቷል ለህዝባችን ነፃነት በማለት ከተማውን ለቀን መውጣት ችለናል።
በዛሬው አውደ ውጊያ የተማረኩ
👉ከ27 በላይ ክላሽ
👉 1650 የክላሽ ተተኳሽ
👉 29 ቦንብ እስካሁን ምርኮ ተደርጓል። በርካታ ፖሊስ፣አድማበትን፣ምኒሻ ተደምስሷል። በረካቶችንም በእጅ በመያዝ ተችሏል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
©አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
07/ዐ4/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 131🙏 12👍 9🎉 8
