fa
Feedback
ETHIO-MEREJA®

ETHIO-MEREJA®

رفتن به کانال در Telegram

News & Media Company® USA : Washington Addisababa, Ethiopia🇪🇹 . Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja . ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!! 👉 @ethio_merejabot

نمایش بیشتر
2025 سال در اعدادsnowflakes fon
card fon
110 271
مشترکین
-4624 ساعت
-2877 روز
-1 28930 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል እንደሚሸፍን ተገለፀ፤ ፈተናው ለመውሰድ ብሔራዊ መታወቂያ መያዝ ግዴታ ሆነ የትምህርት ሚኒስቴር የዘንድሮው 2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል እንደሚሸፍንና ተማሪዎች የተማሩትን ይዘቶች እንደሚፈተኑ አስታውቋል። በተጨማሪም ፈተናው ከ10 እስከ 12ኛ ክፍል የአዲሱ ስርዓተ ት/ት ይዘቶችን መሠረት እንደሚያደርግ ገልጿል።በመሆኑም ተማሪዎች፣ መምህራንና ባላድርሻ አካላት ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ አሳስቧል። ሚኒስቴሩ ይህን ያስታወቀው ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ለሁሉም ክልል ት/ት ቢሮዎች፣ ለሁለቱ ከተማ አስስተዳደር ት/ቢሮዎችና ለት/ት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በጻፈው ደብዳቤ ነው። ሚኒስቴሩ በደብዳቤው፤ የዘንድሮውን የ12ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅትን አስመልክቶ ጥቅምት 6/2018 ዓ/ም ከሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊዎች ጋር በበይነ መረብ በተደረገ ስብሰባ ፈተናው ከ9-12 እንዲሸፍን ከስምምነት መድረሱን ገልጿል። በአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ ት/ት ሪፎርም መሠረት የሁለተኛ ደረጃ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በ2015 ዓ.ም የሙከራ ትግበራ በማካሔድ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ መገባቱን ሚኒስቴሩ አስታውሷል። በተያያዘ ዜና የ2018 የሀገር አቀፍ 12 ክፍል ተፈተኝ የብሔራዊ መታወቂያ ከሌለው መመዝገብም ሆነ መፈተን እንደማይችል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቋል። የብሔራዊ መታወቂያን ከፈተናው ምዝገባ ቀደም ብሎ ማውጣትና መያዝ እንደሚገባም አሳስቧል። የተማሪ ቤተሠብ፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና በየደረጃው ያሉ የትምህርት አመራሮችና አካላትም እገዛ እንዲያቀርቡ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ጥሪ አቅርቧል።   @ethio_mereja
نمایش همه...
43👎 10😁 3
Photo unavailableShow in Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላይ የተላለፈው ውሳኔ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጣሪያና ግድግዳ የንብረት ገቢ ግብር መመርያ በማውጣት፣ ግብር መሰብሰቡን በመቃወም እናት ፓርቲ የመሠረተውን ክስ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከመረመረ በኋላ ፓርቲው ያቀረበው ትክክል መሆኑን በማረጋገጥ ያስተላለፈው ውሳኔ፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ተሽሮ ውድቅ ተደረገ፡፡ እናት ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣሪያና ግድግዳ ግብርን አስመልክቶ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ በመመሥረት፣ መመርያው ተግባራዊ እንዳይደረግና ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ፓርቲው ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. ባሠራጨው መረጃ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያስተላለፈውን ውሳኔ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለቱንና አፈጻጸሙ እንዲታገድ ማድረጉን አስታውሶ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ፓርቲው ክሱን የማቅረብና የመከራከር ሥልጣን እንደሌለው በመግለጽ፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ መሻሩን አስታውቋል፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔውን በሻረበት ወቅት ፓርቲው ተከራይ እንጂ ቤትም ሆነ ቦታ የሌለው መሆኑን፣ በጉዳዩ ላይ መብትም ሆነ ጥቅም የሌለው መሆኑንና እንዲከራከር የወከለው አካል አለመኖሩን በመግለጽ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ ሽሮታል፡፡(ሪፖርተር)    T.me/ethio_mereja         ኢትዮ-መረጃ
نمایش همه...
46👎 22👏 11😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቤአኤካ በፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ሊያስገባ ነው ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ/የተ/የግል ማኅበር በፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ፡፡ ቤአኤካ ስምምነቱን ከቻይናው የመኪና አቅራቢ ሻክማን ኩባንያ ጋር የተፈራረመ ሲሆን÷ ኩባንያው በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ መኪኖችን ለቤአኤካ የሚያቀርብ የሚያቀርብ ይሆናል፤ በዚህም ቤአኤካ በፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በመቀበል ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚያስገባና በቅርቡም 150 ተሽከርካሪዎች እንደሚገቡ ተገልጿል። በተጨማሪም ቤአኤካ በፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን መገጣጠሚያ ፋብሪካ ዝግጅት መጠናቀቁንና በመጀመሪያ ዙር 1 ሺህ 500 መኪኖችን ለመገጣጠም መታቀዱ በስምምነቱ ወቅት ተጠቁሟል።    T.me/ethio_mereja         ኢትዮ-መረጃ
نمایش همه...
48👍 15
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴምርፕሮፐርቲስ ⩩ 100% ለሚከፍሉ ከ30% እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ እውነተኛ ቅናሽ አዘጋጅተናል። ⩩ እንዲሁም 40% ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ የ20% ቅናሽ አዘጋጅተናል። 📍 ሊሴ ገ/ማርያም 👉 66 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 7,590,000                  ቅድመ ክፍያ = 10% (759,000) 👉 71 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,165,000                  ቅድመ ክፍያ = 10% (816,500) 👉 132 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,520,000                    ቅድመ ክፍያ 10% (1,452,000) 👉 146 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 16,060,000                    ቅድመ ክፍያ = 10% (1,606,000) 📍ሐይሌ ጋርመንት ባለ 3 መኝታ 👉 139ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,590,000                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,000) 📍 አያት (ፈረስ ቤት) 👉 88 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,360,000                  ቅድመ ክፍያ = 10% (836,000) 👉 108 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 10,260,000                    ቅድመ ክፍያ = 10% (1,026,000) 👉 137 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 15,070,000                    ቅድመ ክፍያ = 10% (1,50,000) ⩩ ቀሪውን 90%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን! +251964439488 +251907232222 Telegram: https://t.me/OusmanTemer WhatsApp: https://wa.me/251964439488
نمایش همه...
8