fa
Feedback
በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

رفتن به کانال در Telegram

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡ @bewketuseyoum19 Creator - @abela1987 📨 For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot Thank you!

نمایش بیشتر
2025 سال در اعدادsnowflakes fon
card fon
222 485
مشترکین
+13924 ساعت
-1327 روز
-1 21030 روز
آرشیو پست ها
✨✨✨ የታፈነ ፍቅር ✨✨✨ ✨✨✨ክፍል 22✨✨✨ ጠዋት ላይ ገና ሰው ሳይነሳ ግን ትላንት ስላደረገችው ነገር ነው ምታጠነጥነው ፣ ትንሽ እረፍት አጥታለች የሆነ ነገር ቅር ቅር ብሏታል ፣ አልኮል አድርጋበት በነጭ ነጠላ ቅዳጅ ያሰረችው እጇ ደጋግሞ ይቆጠቁጣታል .... አንዳች ፍርሃት ግን እየተሰማት ነው..... ግዛውን እዛ ጭር ያለቦታ ስወስደው ያየኝ ሰው ይኖር ይሆን ? አንዳች ምልክት ትቼ መጥቼ ይሆን? ሊፍት የሰጡኝ ሰውዬ መኪናስ ደሜ ተንጠባጥቦ ይሆን መኪናውስጥ እስካሁን ያልደወሉት ለምንድነው ?እንደሁኔታቸው ማታ እራሱ ደውለው አላስተኛ ይሉኛል ብዬ ነበር ።ግን ዝም ብለዋል ! ......የሰላማዊት ፍርሃት የግዛው መሞት አይደለም ፍርሃቷ እሷ መሆኗ ታውቆ እስር ቤት እንዳትገባ ነው ። ከጭንቀቷ የተነሳ እናቷ ናፈቋት ፣ ስልኳን አውጥታ ወደጀርመን እናቷጋር ደጋግማ ምልክት አደረገች ....ቆይታ ስታየው ትደውልልኛለች ብላ ተስፋ በማድረግ ። በአባቷ ቤት የሚኖሩት አክስቷ ናቸው ፣ወይዘሮ ዘበናይ ሰላማዊትን አይወዷትም ፣ ባሏን ተጣልታ ስትመጣ እንኳን ለምን ብለው ታሪኩን አልጠየቁትም ፣ በፊትም አርፋ አትቀመጥም ብለው ተንብየው ነበር ፣ ሰላማዊት ልክ እንደ እናቷ ልቧ ጥቁር ነው ይላሉ ፣ እናቷ ወንድሜን አቃጥላ አቃጥላ ነው የገደለችው ።ከዛ ምን አደረገች ገና ከመሞቱ አዘኑ ሳይለቀን ስለውርስ ጠየቀች ። በጣም ተበሳጨን ...ጥሩነቱ ወንድሜ የኔ ምስኪን ጠቅላላ ንብረቱን በኔ በእህቱ ስም አድርጎት ነበር ። እንዳልሆነላት ስታውቅ ለልጁ ብላ ሞገተችኝ ፣ ይሁን ብዬ ነው እንጂ ልጅቷ እራሱ እንደልብ ባቀርባት እና ዘመዶቼም አብረውኝ ባይኖሩ ከናቷ ትህዛዝ እየተቀበለች ቀስበቀስ ታጠፋኝ ነበር ። ይሄን ያወኩት ሰላማዊትን የወንድሜ ልጅ ብዬ ባቀርባት ፣አይኖቿ ውስጥ ያየውትን ጥላቻ እኔ ብቻ ነኝ ያየውት ድርጊቷም ልክ አልነበረም ሞከርኩ ግን ልጅቷ የለየላት አስመሳይ ናት ፣ ችግር አለ ፣ያው አንድ ክፍል አልከለክላትም ፣ መግቢያዋም በሌላ በር ነው እኔንም አትነካኝም ብዬ ለወንድሜ ስል ሰጥቻታለው ።'ብለው ነው ለጠየቃቸው ዘመድ ሁሉ የሚነግሩት ። ሰላማዊት በበኩሏ ነፃነቷን ወዳዋለች ፣ታሪኩን አግብታ ዘግታ የሄደችውን ቤት ከፍታ ስትገባ ማንም ለምን አላላትም ፣ አክስቷም ሲያይዋት ከሰላማታ ውጪ ፊት አልሰጧትም ፣በዚ ቅር ቢላትም ። እሷም የአባቷን ዘመዶች ወዳ አታውቅም ፣ እናቷ እና ሁለቱ ወንድሞቿ ናቸው ቤተሰብ ለሷ ። አሁንም ቢሆን የታሪኩ ጉዳይ በሰላም ካልተፈታ አብራው መሆን ካልቻለች በግዛው የጀመረችው በታሪኩ አጠናቃ በገንዘብም አይል ቢሆን የማትወደው ውጪ አገር ማለትም ወደጀርመን ለመሄድ ነው ያቀደችው ...........በአሳብ እየተወዘወዘች ሳለ ስልኳ ጮኽ ደንግጣ ዞረች አልጋዋላይ ሞባይሏ እሪ እያች ነው ። እየፈራች ተጠጋችው ፣ ስልክ ቁጥሩን ስታይ ሰውነቷ ተንቀጠቀጠ .......የግዛው ቁጥር ነው። አፏን ከፈተችው የልብ ምቷ ፈጠነ ................🖤🖤🖤🖤🖤 ✍️✍️✍️✍️✍️✍️ኪዶ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 🔵ይቀጥላል,,,,,,,,, ✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️ ♥️ከወደዱት ሼር ያድርጉ♥️ @bewketuseyoum19
نمایش همه...
😱 18 14
"እውነት ልጄ ደስ ይላል ቢያንስ እኮ መኪና ከያዝክ እቤት ድረስ በእግርህ የዚን ሰፈር ቅያስ የምትገባው ነገር ከቀረ አላስብም "አሉት "አዎ በቃ አትጨነቂም ከአሁን በዋላ" "እሺ ግን እሱስ "አሉት "ሌላ መኪና ገዛ " "ነው ከሆነ ጥሩ "አሉ ስለ ልጃቸው እየተደሰቱ ፣ ድሮ ድሮ አስታወሱ አካባቢያቸው ላይ መኪና ያለው ሰው አብታምና የተከበረ ሰው ነው ብለው ስለሚያስቡ ጠብ እርግፍ ብሎ የመንደሩ ሰው ሰላም ሲላቸው ፣ የጋሽ እንትናቤት የቀኝ አዝማች እከሌ ግቢ እየተባለ ሲከበሩ ፣ዛሬ ጊዜ ደሞ የሳቸውን ልጅ ባለ ትልቅ ቤት ባለ መኪና ሲያደርግላቸው ምን ይበሉ ከደስታ በስተቀር ተመስገን .......... ✍️✍️✍️✍️✍️✍️ኪዶ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 🔵ይቀጥላል,,,,,,,,, ✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️ ♥️ከወደዱት ሼር ያድርጉ♥️ @bewketuseyoum19
نمایش همه...
🥰 22 6
✨✨✨ የታፈነ ፍቅር ✨✨✨ ✨✨✨ክፍል 21✨✨✨ ግዛው ፣ጁሱን ጠጥቶ እንደጨረሰ በእርካታ መንፈስ ወደ ሰላም አየና "ሰላሜ ታውቂያለሽ ቀኑን ሙሉ ምንም አልበላውም ነበር አመሰግናለው ፣ ባዶ ሆዴን ስለዋልኩ ይኽው ሆዴ በጩኽት እየተረባበሸልሽ ነው ከየት አመጣኽው እንዲ ያለውን ጣፋጭ እያለኝ ነው መሰለኝ 😁"አላት በምስጋና "ተው እንጂ ለምን አልበላህም "አለች ደረቅ ባለ አስተያየት እያየችው "ወይ አንቺ ከየት ይመጣል መብያ 😁 "ብሎ ሳቅ ለማለት ሞከረ ነገርግን የሆድ ቁርጠቱን አልቻለውም "ምነው ደና አይደለኽም እንዴ ?"አለችው "እኔጃ እያመመኝ ነው መሰለኝ "አላት እየተጨነቀ "በቃ ከዚ እንውጣ "ብላ ተነሳች ፣ግዛው ፊቱ እንደተቀያየረ ተከተላት ፣ አየር ሲያገኘኝ ደና እሆናለው ብሎ ቢያስብም ፣አልሆነለትም ፣ ደጁ መሸትሸት ማለቱን አሳውቋል ብዙም መንገደኛ የማይታይበት አካባቢ ጭራሽ ብሶበታል ፣ እየሄዱ ሸብረክ ሸብረክ ማለት ሲጀምር ፣ሰላማዊት በግራ በኩል ካለ እንድ ጠፍጣፋ ዲንጋይ ላይ እንዲቀመጥ እረዳችው ከጀርባው ያለው የዛፍ ቅጠል ሲንኮሻኮሽ ሲሰማ ልቡን ፍርሃት ፍርሃት አለው ከመጨነቁ የተነሳ የሰላማዊትን ሰማያዊ ሹራብ በግራ እጁ አጥብቆ ያዘ ፣ ሰላማዊት ከተቀመጠ በዋላ የያዘውን ሹራቧን ለማስለቀቅ ሞከረች አልቻለችም ፣ "ሰላማዊት ምንድነው ያደረግሺኝ "አላት ፣ "እኔ ምን አደርግሃለው እያሳረፍኩ እኮ ነው ።ያው ቀስ በቀስ እቺን ውሸታም ዓለም ትሰናበታታለህ ላንተም ግልግል ነው "ብላ ሳቀችበት "መርዙን ጁሱ ውስጥ ከተሽዋል እእእእ እንዴት ሞኝ ነኝ እእእ"ብሎ ቀኝ እጁን ጃኬት ኪሱ ውስጥ ከተተው ፣ "ከሰላማዊት ጋር የሚቀልድ ሁሉ የሚገባው ቅጣት ነው !"አለችው ግዛው ጩቤውን እንደምንም ጨብጦ ሲያወጣው ሰላማዊት አየችው እንደምንም ሹራቧን ለማስለቀቅ ጥረት አደረገች ግዛው ባለ በሌለ ኃይል ሰነዘረ ሰላማዊት በቀኝ እጇ ስትከላከል መዳፏን ወጋት እንደመጮኽ ብላ ወደዋላ ተሳበች ግዛው ሹራቧን ጠንክሮ መያዝ አልቻለም ተልፈሰፈሰ ፣ ድንጋዩ ላይ ወደዋላው ጋለል አለ ጩቤው ከስበቀስ ከእጁ ወደቀ ........ሰላማዊት ፈጥና ጩቤውን በማንሳት ቦርሳዋ ውስጥ ከተተችው ፣ እናም ጠጋ ብላ "አንተ ስህተቴ ነበርክ እናም መሄድ አለብህ አለዛ ከባድ ችግር ነበር የምትሆንብኝ ፣ ሁሉንም ያለማንም እገዛ ማድረግ እችላለው ፣ ከእንግዲ የራሴ ሚስጥረኛ እኔው እራሴ ነኝ !! ደናሁን ግዛው ይሄ ዓለም ሲጀመር ለአንተ አይነቱ ምንም አይጠቅምም ከጭንቀት እንደገላገልኩ ቁጠረው ...."አለችው ወደጆሮው ተጠግታ ፣ ግዛው በሰመመን ነበርየሰማት ቀስበቀስ ትንፋሹ ተቋረጠች ።ሰላማዊት መሞቱን ካረጋገጠች በዋላ ጭር ካለው ቦታ ቀስብላ ወጣች የአስባልቱን መንገድ እንዳገኘች አንድ የቤት መኪና ሲመጣ በርቀት ተመለከተች ፣የእጅ ምልክት ስታሳየው መኪናው መጥቶ አጠገቧ ቆመ ፣ መግባት እንደምትችል ገቢናውን ከፍቶ አሳያት ፣ ጋቢና መቀመጥ አልፈለገችም ግን አጉል መግደርደር እንደማያዋጣት ስለተረዳች ፣አመስግና ገባች ፣ ሹፌሩ ተለቅ ያሉና ቦርጫም ናቸው በዛላይ ዘይት የተለቀለቀ የሚመስለው ጥቁር አብረቅራቂ ፊታቸው ያስፈራል ሁለመናቸው ስጋ ነው ብላ ከራሷ ጋር አወራች .... "ከየት ነው ውቢት በዚ ሰአት "አሏት የወርቅ ጥርሳቸውን እያሳይዋት ፣ሰላማዊት በነጭ የበለዙ ድርድር ጥርሶች መሃል የተሰነቀረችውን አንዲት ወርቅ ጥርስ ስታይ 'እኚ ደሞ የየትኛው ክፍለዘመን ሰው ናቸው 'አለች ለራሷ "ምነው ፈርተሻል እንዴ ?"አሏት ወደጓን ገርመም እያረጓት ። ሰላማዊት የሚደማ የቀኝ እጇን መዳፍ በሹራቧ ውስጥ መክተቷን ልብ እንዳይሉት እየተጠነቀቀች ነበር ። "አይ ያን ያክል አልመሸም ብዬ ነው "አለች "ቢሆንም እንዳንቺ ያለች ቆንጆ በአስራ ሁለት ሰአት ነው መሰብሰብ ያለባት 😁😁እኛ ወንዶች ከመሸ እንደምንቀየር ጠፍቶሽ ነው በተለይ ቆንጆ ላይ 😁😁"ብለው በራሳቸው ብቻቸውን ሳቁ "ይሆናል ሰው ጋር ደርሼ መምጣቴ ነው ታክሲም ስለሌለ ብዙ ቆይቻለው "አለች "ውይ ታክሲ እኮ ቆየ በዚ በኩል መጫን ካቆመ ትንሽ ወደፊት ተጉዘሽ በጀርባ ካለው መንገድ ላይ ነው የሚጭኑት ፣ እዚ እንደኔ መልካም ሰው ካላጋጠመሽ በስተቀር ትራንስፖርት አይታሰብም"ብለው በትከሻቸው ነካ አደረጓት ፣ፈገግ ለማለት ሞከረች 'የፈላበት ሽማግሌ 'አለች በውስጧ "እና በዚው ለምን አንድ ቦታ ቁጭብለን ተጫውተሽ አትሄጅም "አሏት በፍላጎት እያይዋት "አይ ዛሬ አይሆንም አባቴ ይቆጣኛል እየመጣውነው ስላልኩት "አለች "ውይ ከቁጣ እንኳ አልፈሻል 😁እሺ ባይሆን ስልክሽን እዚላይ ፃፊ "ብለው ስልካቸውን ሰጧት ።ሰላማዊት የምትወርድበት ስለደረሰ በፍጥነት ለመገላገል ስልኳን ፅፋ ሰጠቻቸው ። ሰውዬው በደስታ ተቀብለዋት ፣ልውረድ ያለችበት ቦታላይ አውርደዋት ሄዱ ። ባለትዳርና የአምስት ልጆች አባት ቢሆኑም አልፎ አልፎ ወጣት ሴቶችን የልጆቻቸውን እኩዮች በገንዘብ እየደለሉ አብሮ ማሳለፍ ለምደዋል ፣ እናም ሰላማዊትን አዲስ ገቢ ሊያደርጓት ቋምጠዋል ፣ የድንገት ሲሳያቸውን ፣ለመብላት የጓጉ ይመስላሉ............ ..ሰላማዊት ከሰውየው እንደተለያየች አስታውኪ አስታውኪ የሚል ስሜት ነበር የተሰማት ፣ ወደጥግ ጋር ሄዳ ስትተፋ ቆየችና ፣ እጇን ከሹራቧ አውጥታ አየችው በትንሹ መድማቱን አላቅመም ነበር ሹራቧ ነጭ አለመሆኑና ጨለማ መሆኑ ጠቀማት እንጂ ልብ ብለው ቢያይዋት በተጠራጠሩ ነበር ፣አሁንም ግን ፈርታለች ደሟ ከሹራቧ ካለፈ መኪናው ውስጥ ምልክት መስጠቱ አይቀር............... 🌹ታሪኩ ቤት ሲገባ አዳዬ የውሸት አኩርፈው ጠበቁት ፣በተለይ ሰሞኑን ቢናገሩትም አልተው ያላቸውን አምሽቶ መግባት ሊለምዱት አልቻሉም ፣ ደጋግሞ ሴናጋር ነኝ ቢልም ፣ ተጨንቀዋል ፣ "የኔ አለም ምነው ይህን ነገር ብትተወውስ "አሉት ገና እንደገባ ፣ታሪኩ መልስ ከመስጠት ይልቅ አቅፎ ሳማቸው ፣ በቅርቡ ከነሱ ጋር የተቀላቀሉት ጓደኛቸው እናት ሎሚ በታሪኩ ሁኔታ ሳቁ ፣ እሳቸውንም ሄዶ አቀፋቸው ፣ በዛም አላበቃም ሰራተኛቸውንም አቀፋት ፣ አዳዬ የዛሬው ደሞ ይለያል አሉ በመገረም እያዩት "እማዬ ሴና ጋር ነበርኩ እኮ የኔ ውድ እናት "ብሎ ሳቀ "ኧረ በቃ ተይው ይቀመጥ እንጂ "አሉ እናት ሎሚ ፣ "እሺ እኔማ ተጨንቄ እኮ ነው ዘንድሮ ማን ወዳጅ ማን ጠላት እንደሚሆንብሽ አይታወቅም ፣ ያቺን ምስኪን ልጅ ሴናዬን እንኳ ማን እንደዛ እንዳደረጋት ገና አላወቅንም ፣ "ብለው ተቀምጠው ተከዙ "እሱስ ልክ ነሽ ! ታሪኩ ልጄ አታምሽ እስኪ አንተም እናትህንም እኛንም አታስጨንቀን ካልሆነ ሴናን እዚሁ አምጥተን እስኪሻላት እናቆያት እንከባከባት "አሉ በየዋህነት "እሰይ ያንቺ ይሻላል ። እኔም አስቤ ነበር እኮ በፊት ግን ያምስኪን አባቷ ያለሷ አይሆንለት ፣ "አሉ አዳዬ "ኧረ እማዬ በቃ አትጨነቂ በጊዜ ነው የምመጣው ከአሁን በዋላ "ብሎ ወሬ በመቀየር ማሳቅ ጀመረ ፣ ሁሉም በታሪኩ ወሬ እየሳቁ ነበር አብዝቶ ግን የሚተርክላቸው ስለሴና እና ስለመሳይ ሰለ እራሱ የልጅነት ጊዜ እና የጉርምስና ወቅት ነው አብዝቶ ሴና ሴና ሲል እየታዘቡት ነበር በዛውም ፣ አዳዬ በልባቸው ያቺን ሴጣን ከሚያገባ እህትነቱ ቀርቶበት ሴናን ቢያገባ በተሻለው ነበር ፣ ይላሉ "እስኪ እሁድ ሄደን እኔና ሎሚ አንድ ላይ እንጠይቃታለን "አሉ አዳዬ "ኧረ ደስ ይለኛል እኔም ባያት "አሉ እናት ሎሚ ፣ "በደስታ እወስዳችዋለው ፣ በነገራችን ላይ እማዬ የመሳይን መኪና እኔ ልይዛት ነው "አላቸው
نمایش همه...
19👍 2
የፈራሁ የኮራሁ ያጨድኩኝ የዘራሁ በልቼ ጠጥቼ አግኝቼ ነጥቼ ቅር ያልኩ የተመቸኝ እሰይ ያልኩ የቆጨኝ የሳቅኩኝ ያነባሁ የጨከንኩ የባባሁ የወጣሁ የገባሁ ለማፍሰስ ለማፈስ በእቅድ በደመነፍስ የጀገንኩ የሰነፍኩ እንዳቅሜ የሞከርኩ አንድ ሰው፡ የሰው ልጅ እዚች ቦታ ነበርኩ። በዚህ ነፋስ ህይወት ህያው ይሉኝ ወረት ማለፍ መሄድ እንጂ ስለማልችል መቅረት ስለማልችል መቆም ባለኝ ብቸኛ አቅም እስኪ ግጥም ልፃፍ ማለፌን ልጠቁም። ( red-8 ) ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
نمایش همه...
27👍 5👏 1
Repost from TgId: 2202640048
Photo unavailableShow in Telegram
✅ እስኪ እቺን ነገር ሞክሯት $DOGS ዛሬ ሲያስተዋውቋት ነበር 😅 💰 ለChristmas ወደ $400,000 ተዘጋጅቷል 💡 በዚህ ግቡ 👇 START GIFTEST BOT START GIFTEST BOT 🧿 Merge የማድረግ ጌም አለው Icon Generate እያደረጋችሁ ተመሳሳይ የሆነውን መገጣጠም ነው 🧿 Task Section ላይ ገብታችሁ ስሩ Specially የDogs'ን ✅ Level 15 ሰትደርጉ ደግሞ 300 Stars & NFT's የያዘ እጣ ይሰጣል አድለኛ ከሆናችሁ ታሸንፋላችሁ : የመጨረሻ Level ስትደርሱ ደግሞ በውድ የሚሸጥ NFT 🔥 💡 የዛሬ አመት ለChristmas ውድ Stickers ሰተውን ነበር 🙂 @DropGenius1
نمایش همه...
3
✅ አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው ፍጠኑ 👇👇 1⃣ ለወጣ 1000 ብር ካርድ 2⃣ ለወጣ  500 ብር ካርድ 3⃣-2️⃣0️⃣ ለወጣ  100 ብር ካርድ 👉 ዝግጁ ከሆናችሁ START የሚለውን ይጫኑ👇👇👇
نمایش همه...
START ✅
ጀምር 🔥
ቤትዎን በህልምዎ እንዳሰቡት በሚያማምሩና ጥራት ባላቸው ፈርኒቸሮች ማስዋብ ይፈልጋሉ? 🏡✨ 📞 ስልክ: 0911468394 እኛ የቤትዎንና የቢሮዎን ውበት ከጥራት ጋር አጣምረን በዘመናዊና ማራኪ ዲዛይኖች እናቀርባለን። እያንዳንዱ ስራችን የጥራት፣ የጥንካሬና የውበት ማሳያ ነው! ለምን እኛን ይመርጣሉ? ✅ በልዩ ትዕዛዝ (Custom Designs): በፈለጉት ዲዛይን፣ መጠን እና ቀለም የልብዎን ፍላጎት እናሟላለን። ✅ የላቀ ጥራት (Quality Craftsmanship): በሰለጠኑ ባለሙያዎች በጥንካሬ ስለሚሰሩ ለረጅም ጊዜ ያገለግላሉ። ✅ ዘመን የማይሽረው ውበት (Timeless Appeal): ዛሬም ነገም ውበታቸውን እንደጠበቁ የሚዘልቁ ፈርኒቸሮች። 🔴 ከኛ ከሚያገኟቸው አገልግሎቶች በጥቂቱ፦ 🚪 ቁም ሳጥኖች (Wardrobes) 🍽 ኪችን ካቢኔት (Kitchen Cabinets) 🚪 የዉስጥ እና የዉጪ በሮች (Interior & Exterior Doors) 💼 የቢሮ ጠረጴዛዎች (Office Desks) 💄 ድሬሲንግ ቴብል (Dressing Tables) 📺 ቲቪ ስታንዶች (TV Stands) 🪑 ወንበሮች (Chairs) 📚 ሼልፎች (ለመፅሀፍ እና ለስራ ቦታ) 🛌 ምቹ አልጋዎች (Comfortable Beds) የእርስዎን ህልም እውን ለማድረግ ዝግጁ ነን! ለበለጠ መረጃ፣ የዋጋ ዝርዝር ለማወቅ ወይም ለማዘዝ አሁኑኑ ይደውሉልን! 📞 ስልክ: 0911468394 📩 @abela1987 #ፈርኒቸር #የቤትእቃዎች #አልጋ #ቁምሳጥን #ኪችንካቢኔት #የቢሮፈርኒቸር #በኢትዮጵያየተሰራ #አዲስአበባ #ኢትዮጵያ #የእንጨትስራ #ካቢኔት #ጠረጴዛ #FurnitureEthiopia #AddisAbaba #HomeDecorEthiopia #MadeInEthiopia #CustomFurniture #EthiopianFurniture #InteriorDesignAddis
نمایش همه...
2👍 2
ከባለጌ ልብ ውስጥ ቅንጣት ትህትና ከትሁትም ሀሳብ ሚጢጢ ብልግና ብታይ አይግረምሽ አለም ይህ ነውና ቀኔንም በሙሉ አኩኩሉ ስልሽ ትያለሽ አልነጋም እኔስ ምኔ ሞኙ ላልደረሰ ጸሎት ስለት አላስገባም ስሜን አስጥተሽው ሁሉ እየዘገነ ከራሴ መልክ በልጦ የሳልሽኝ ገነነ የቀረቡኝ ሁሉ በእኔ ላይ በር ዘጉ ማክበርሽ ባይደርሰኝ ተይ ናቂኝ በወጉ ባትሰሚኝም እንኳን ካየሁት ልንገርሽ አትታለይ በዓለም ትናንትሽን እይው የማለልሽ እንጂ የሞተልሽ የለም እናንተ ጠቢባን ትዝታን ስትስሉ ቀለሜን ተዋሱ ተስፋ ስትነድፉ ከእኔ ገፅ ጥቀሱ ስሙን እያላችሁ እውነት ስትዘግቡ እኔን አዳምጡና ይሄን ቃል ከትቡ ትናንቱን ያወቀ ነገውን አይንቅም ማቀፍ የለመደ በቀላሉ አይወድቅም ከትናንቴ ሳመልጥ ነገየ ሲርቀኝ ጊዜ ይሉት ቀመር ዛሬ ላይ ሲያቆመኝ ወድቆ መነሳቱን ተክኜበታለሁ ሳይሸኙኝ መሄዱን እችልበታለሁ ፀሀይ ሌት ይወጣል? ጉጉት ቀን ያፈጣል? እኮ ስታስቢው ልቤስ ከዚህ ኋላ ያንቺን ልብ ይመርጣል? ✍️ አቤኒ ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
نمایش همه...
18👏 5
Photo unavailableShow in Telegram
ማሳሰብያ !!! ለሴቶች እና እግር ኳስ ለማያቁ ወንዶች አይመከርም! ትክክለኛ የእግር ኳስ አፍቃሪ የሆነ ብቻ Join ይበል👇👇👇
نمایش همه...
Join
Repost from N/a
Photo unavailableShow in Telegram
🌹♥️🌹የሴት ጓደኛ ለመያዝ አስበህ ታውቃለህ ምን ልበላት ብለህ ቃላትስ አተህ ታውቃለህ🌹🌹 እንግዲያውስ የፍቅር ቃላት ፍለጋ አበቃ በቀላሉ ማግኘት ትችላለህ🥰🌹👇🌹👇🌹
نمایش همه...
🌷❤️✨የፍቅር ቃላት✨❤️🌷
🌷❤️✨አፈቅርሻለሁ ለማለት✨❤️🌷
🌷❤️✨አፈቅርሀለሁ ለማለት✨❤️🌷
🌷❤️✨የጋብቻ ጥያቄ✨❤️🌷
🌷❤️✨ፍቅረኛ ለመያዝ✨❤️🌷
🌷✨❤️ሴት ልጅ እንድትወድህ❤️✨🌷
🌷❤️✨ወንድ ልጅ እንዲወድሽ✨❤️🌷
🌷❤️✨የፍቅር አባባል ✨❤️🌷
🌷❤️✨የፍቅር ታሪኮች✨❤️🌷
🌷❤️✨ሰርፕራይዝ ለማደረግ✨❤️🌷
😌ፎንቃ MOOD🥰
نمایش همه...
😘⚡️ፎንቃ life⚡️😘
😘Join😘
Betty እባላለሁ እድሜ  23 ነው በጣም ቆንጆ  እና ለ kiss የሚገፋፋ ከንፈር አለኝ ስራዬ የ ሆቴል  አስተናጋጅ ነኝ በምሰራበት ሆቴል በጣም ብዙ ደምበኞች ነበሩኝ  ቀኑን ባላስታውስም ወደ 2:30 አካባቢ ይሆናል ከደንበኞቼ አንዱ መኝታ ቤቱ ድረስ ቢራ እንዳመጣለት ይጠይቀኛል እኔም ቢራዉን ወሰድኩለት ክፍሉ ስገባ ግን ያልጠበኩት See More....
نمایش همه...
1
See More...
❕ሙሉ ታሪኩን ለመመልከት ❕
✨✨✨ የታፈነ ፍቅር ✨✨✨ ✨✨✨ክፍል 20✨✨✨ ጭር ያለ አካባቢ ነው ብዙም እግረኛ የማይበዛበት ፣ አንዲት አነስተኛ ካፌውስጥ ግዛውና ሰላማዊት ፣ ከዚ በፊት የተፈጠረውን ነገር ሁሉ የረሱ መስለው በተረጋጋ ሁኔታ እያወሩነው ። በተለይ ሰላማዊት ፍፁም ሌላ ሰው ሆናለች ፣ ግዛው 'እቺ እብድ ስትገርም እራሷን መቀያየር ትችልበታለች ፣ ሆሆ ነው በስልክ ያናገርኩት ሌላ ሰው ነው 'ይላል በውስጡ ደሞ እንዴት አምሮባት ነው የመጣችው ። "ሳላም ግን ምንድነው እንዲ የሚቀያይርሽ "አላት በሞኛሞኝ አይን እያያት "ጥሩ ስሜት ላይ አልነበርኩም ፣እራቅ ብዬ የሰነበትኩት የዘመድ ለቅሶ ስለነበረ ነው ። ለዛነው ስልክ አጥፍቼ የከረምኩት ፣ ስመለስ አንተ ጉዳዩን እንዳልጨረስከው የሚገልፅ ሚሴጅ አነበብኩ ታውቃለህ ስልኬን እንኳን የከፈትኩት ከክፍለ ሃገር ስመለስ ነው ፣እዛ መብራት የሌለበት ገጠር ውስጥ ሆኜ ፣ጉዳዩ አልቋል ብለህ ከነገርከኝ በዋላ እርፍ ብዬ የሰነበትኩት አንድም እንዳይጠረጥሩኝ አጋጣሚውን በዛው መጠቀሜ ነበር ። ታዲያ አልሆነም ስትለኝ ምን ልሁን ካንተ ጋር ስንት ነገር አስበን ...?"አለችው በውስጧ እየሳቀችበት ፣ ግዛው በሞኝነት የምትለውን አዳመጣት ። እራሱንም እንደጥፋተኛ ቆጠረ ፣ ሰላማዊትን ሊበቀልበት አስቦ ይዞት የመጣውን ጩቤ በኪሱ ውስጥ እንዳለች ነካካት ፣ መልሶ ቀፈፈው ፣ ነገሮችን መረዳት አቅቶት ፣ሰላማዊትን ለማጥፋት ያሰበውን አሳብ እረገመ ። "ይቅርታ አሁንም እኮ ጉዳዩን ማስተካከል ይቻላል አትጨነቂ አደርገዋለው ፣እንዲሁም ባለፈው የሰጠሺኝን መርዝ እጠቀመዋለው "አላት "እ እንዴት አድርገ ከኤርሚ ካፌ አለቀቅክም እንዴ?"አለችው "ለጊዜው ዞር አልኩኝ እንጂ እዛው ተመልሻለው ፣ "አላት "እሺ ግን ተጠንቀቅ መርዙ ገዳይ ነው "አለችው "ችግር የለም በነገራችን ላይ የልጅቷን ስልክ ነጥቄያት ነበር ፣እያወራች ሳለ አምጭው ስላት እንዴት ክው እንዳለች " "ምን አይታሃለች እንዴ ?"ብላ ጠየቀችው ደንግጣ "በጨረፍታ ነው "ብሎ አቅማማ "ስልኳ የታለ!" "እንዴ ወዲያው ነው ሲሙን የጣልኩት ከዛ አንቺ ዝም ስትዬኝ ሸጬ ነው የቤቴን ክራይ የከፈልኩት "አላት በማሳዘን "እሺ አንዴ ካርድ ገዝቼ ልምጣ ወይስ ...."አለችው መቶብር እያወጣች ፣አስተናጋጁ ሁለት ጁስ ይዞ መጥቶ አስቀምጦ ተመለሰ "እኔ ገዝቼ አመጣልሻለው ወንድ እያለ ሴት አይነሳም "አላት እየተፍለቀለቀ ፣እሷም ሆነ ብላ ነበር ። "እሺ ፈጥነህ ተመለስ "ብላ ሸኘችው ወጥቶ መሄዱን ካረጋገጠች በዋላ አካባቢዋን ገልመጥ ገልመጥ አድርጋ ቦርሳዋን ፈታተሸች ..... ግዛው የአምሳብር ካርድና ማስቲካ ገዝቶ መጣ ሲሰጣት ሳቀች "በራስ አሳብ ነው እንዴ የምትገዛው " "አዎ እዛ ስደርስ ነው ባለስንት እንደሆነ አለመጠየቄን የተረዳውት እና ገምቼ ገዛው "ብሎ እሱም ሳቀ ፣ "በል ጠጣ "አለችው የውስጧን ንዴት ለመደበቅ እየጣረች ፣ ግዛው ጁሱን ተስገብግቦ መጠጣት ጀመረ ፣ ሰላማዊት ፈገግ አለች................. 🥀 "ሴን መቼም ዛሬ ሌላ ዓለም ላይ በድንገት የተከሰት አይነት ስሜት ነው እየተሰማኝ ያለው ፣ እንጃ የደስታ የፍርሃት ግራ የመጋባት አይነት ድብልቅልቅ አይነት ነገር ነው አይምሮዬ ላይ የሚመላለሰው"አላት ታሪኩ ከእቅፉ አውጥቶ አይን አይኗን እያያት ፣ "በርግጥ ለምን እንዲ ተሰማህ ልል አልችልም እስከዛሬ ድረስ ላንተ ያለኝን ስሜት አታውቅም ነበር ፣ እኔነኝ ፍቅርህን አፍኜ የኖርኩት ለኔ መናገሬ ግልግሌ ነው ። ላንተ ደሞ አዲስ ስሜት ነው እ ታሬ እባክህ ፍቅሬን አትፍራው "አለችው ልትሸኘው ከቤታቸው ወጥተው ነበር አንድ ጥግ ቆመው የሚያወሩት ፣ የአካባቢው ጭር ማለት እንዲተቃቀፉ ድጋፉን ሰጥቷል ፣ "ፍቅርሽን መቼም አልፈራውም ግን መሳይ ምን ይለኛል ብዬ ሳስብ ፈራው ፣ አንቺ እንደ እህቴ ነበርሽ ፣"አላት "አዎ አንተ እንደ ወንድሜ ነበርክ ወንድምነትህን ዛሬም እፈልገዋለው ከነ ፍቅርህ "አለችው "እሺ የኔውድ ይቅርታ አስጨነኩሽ አይደል ፣ ምን አይነት ፈሪ ነኝ ፣ፈሪ ብቻ አይደለውም እውርም ጭምር ነኝ ። እንዴት ያንቺን ስሜት ማየት አቃተኝ ፣ ባይ ኖሮ እኮ ያቺ የተበላሸች ልጅ በሕይወቴ የመግባት እድሉን አታገኝም ነበር"አለ በቁጭት "ተወው እሱን በቃ ያለፈው አልፏል "አለችው ሴና እጇን እያሻሸች "በረደሽ አይደል በቃ ጊቢ ነገ እንገናኛለን ፣"ብሎ ግንባሯን በመሳም መልሶ እስከቤቷ በመሸኘት ፣ ወደቤቱ እያፏጨ ......ደስታውን በፈገግታ እየገለፀ ......ደሞ እያፏጨ ......ደሞ እያፏጨ .............. ✍️✍️✍️✍️✍️✍️ኪዶ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 🔵ይቀጥላል,,,,,,,,, ✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️ ♥️ከወደዱት ሼር ያድርጉ♥️ @bewketuseyoum19
نمایش همه...
27
አሁን Online ላላችሁ ብቻ 💸የካርድ ሽልማት አለ። ካርዱ ሊለቀቅ ❽ ደቂቃ ብቻ ነው የቀረው Join ብላችሁ ጠብቁ
نمایش همه...
Join
Photo unavailableShow in Telegram
ገራሚ ገራሚ Profile Picture ለምትፈልጉ ብቻ አሁኑኑ Join👀
نمایش همه...
🖼 Join 🖼
✨✨✨ የታፈነ ፍቅር ✨✨✨ ✨✨✨ክፍል 19✨✨✨ ታሪኩ ከስራ መልስ ወደነ ሴና ቤት እየተጣደፈ አመራ ፣ ከመስሪያ ቤቱ ተነስቶ ታክሲ ይዞ ወደነሴና ቤት በሚወስደው አቅጣጫ ሲደርስ ወርዶ መንገድ ሲጀምር ሰላማዊት መከተሏን አላቆመችም ፣ ፊቷን በተቻላት መጠን ለመቀየር ሞክራለች አብዝታ ሜካፕ ከመጠቀሟ የተነሳ አስቀያሚ ሆናለች ፣ በቀላሉ ማንም እንዳይለያት በማሰብ ፣ጥቁር ሻርብ ለብሳለች ፣ሻርቡ ከአናቷላይ እየተንሸራተተ በወረደ ቁጥር በፍጥነት ትመልሰዋለች ፣ ታሪኩ የገባበት ታክሲ ውስጥ ስትገባ ነገሬ ብሎ አላያትም ፣ አሳቡ ሴና ጋር ነው ፣ ሴናን ከአደጋው በዋላ ቶሎቶሎ የማየት ፍላጎቱ ጨምሯል ፣ ወሬዋ አስተያየቷ ሁኔታዋ ሁሉ ወደሷ እንዲሮጥ እያደረገው ነው ። ሴና ታሪኩ አስቀድሞ ስለደወለላት ሁሌ እንደምታደርገው እራሷን አስተካክላ በጉጉት እየጠበቀችው ነበር ። ታሪኩ አንኳኩቶ ተከፍቶለት ሲገባ ፣ ሴና ተነስታ ተቀበለችው ፣ ታሪኩ አይኖቿ ውስጥ የሚያየው ነገር አዲስ ስሜት እየፈጠረበት ነበር ፣ "ሴኑ እንዴት ነሽ ዛሬ "አላት እቅፍ አድርጎ እየያዛት "ደና ነኝ ታሬ አሁንማ በቃ ጠንከር ብያለው ስራ ለመጀመር እየተዘጋጀው ነው "አለችው እቅፉ ውስጥ እንዲያቆያት እየተመኘች "በእውነት ያን ያክል ደና ነሽ "አላት እየፈራ ከእቅፉ አውጥቶ እየተመለከታት "አሃ ምን ሆነሃል ደና አልመስልም እንዴ ስታየኝ "አለችው ቅር እያላት "አይ እኔማ እራስ ምታቱ አሁንም ያለ ስለመሰለኝ ነው "አላት ደንገጥ ብሎ "በል ቁጭበል መክሰስ እንድታመጣ ለትግስት ልንገራት "አለችው ወደ ቤት ሰራተኛቸው ለመሄድ እየተዘጋጀች "ኧረ እኔ አልራበኝም ነይ ቁጭ በይ "አላት "አይ ቢያንስ ቀለል ያለ ነገር እንድታመጣልን እነግራታለው እኔም ከአንተ ጋር እበላለው "ስትለው "በእውነት እሺ በቃ ይምጣልን "አላት ። ፈገግ ብላ ወደ ኪችን ገባች ፣ ታሪኩ በሴናላይ አዳዲስ ስሜቶች እየመጡ ሲያስቸግሩት ለማባረር ይሞክራል ። ሴና መጥታ አጠገቡ ስትቀመጥ ወደጎን አያት ፣ ፊቷ ሙሉ በሙሉ በቀድሞ ቦታው ተመልሷል የተሰፋውን ጭንቅላቷን ለመሸፈን ያሰረችው ሻሽ ይበልጥ ውበቷን ጨመረው እንጂ አላጎደለባትም ፣ ሲፈን ልዩ እኮ ናት አለ በልቡ ፣ አሁን እቺን የመሰለች ሴት ላይ እጅ ይነሳል ምን አይነት ጭካኔ ነው ? ኡፍፍፍፍፍፍ "ደና ነህ ታሬ ?" "ደና ነኝ ምነው ደና አልመስልም ?" "ትክዝ እያልክ እኮ ነው !" "እእ ያው ማን እጁን ደፍሮ እንዳነሳብሽ እያሰብኩ ነው" "ተወው ፈጣሪ በፈቀደ ሰአት ያሳየናል " "ይሁን እሺ "አላት ። አተኩሮ ሲያያት ልቧ መቅለጥ ጀመረ ፍርሃት ተሰማት ፣ "ሴና " "አቤት "አለች ድምጿ ድክም እያለባት " ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የሆነ የተለየ አየር እየነፈሰ ያለ እየመሰለኝ ነው" "የየምን አየር "አለችው አንዳች አይን ወደሱ እያቀረባት ። ታሪኩ ሰውነቷ ሲነካው ደንግጦ ተነሳ ። ሴና ቀና ብላ አየችው ፣ከዚ በዋላ ምንም ነገር መደበቅ የምትችል አልመሰላትም ተነስታ ፊት ለፊቱ ቆመች ፣በጣም ስለቀረበችው አይኑን የሚያሳርፍበት አጣ "ሴና......" "ታሬ በቃ ከዚ በላይ አልችልም ይበቃኛል እኔ ብዙ ታግያለው ከልጅነታችን ጀምሮ የተቆጣጠርኩት ስሜቴ ተጠራቅሞ ሊፈስ ደርሷል ...ተከላከልኩ ፣ ያንን በማድረጌ አላተረፍኩም ዝምታዬ አንተን ከሌላ ጋር እንድትሄድ አደረገህ ብዙ ቁጭቶችን አሳልፌያለው ...ታሬ ላንተ ያለኝን የተፈነ ፍቅሬን የምገልፅበት ጊዜ ነው ብዬ አስባለው ........"ብላ አይን አይኑን አየችው ። ታሪኩ መናገር አቃተው ፣ አይኖቹ በእንባ እረጠቡ ፣ እጁ ተንቀጠቀጠ ፣ "ታሬ በግድ እንድታፈቅረኝ እየጠየኩ አይደለም ፣ ትንሽ ብቻ እዘንልኝ እሱ ብቻ ይበቃኛል ከዚ በላይ ላንተ ያለኝን ስሜት መደበቅ አልችልም "አለችው የሚንቀጠቀጡ እጆቹን እየያዘች "ሴና አንቺን ያለመውደድ የምችል ይመስልሻል ፣ "ብሎ በሚንቀጠቀጥ ከንፈሩ ግንባሯን ሳመው "አፈቅርሃለው ታሪክ !"አለችው "ሴናዬ "ብሎ ውስጡ ሊሸሽጋት የሚጥር ይመስል በጣም አስጠግቶ ያዛት ። ሴና እስከዛሬ አፍና የያዘችውን የፍቅር ስሜቷን በመግለጿ ቀለላት ደረቱን ተደግፋ በረጅሙ ተነፈሰች ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ 🥀 ሰላማዊት ታሪኩ ከነ ሴና ቤት አልወጣ አላት! ጠበቀች ጠበቀች ምን እያደረጉነው እስካሁን የሚለው የቅናት ስሜት አንገበገባት ፣ ታሪኩን ደጋግማ እረገመች ሴናን በሞተች ብላ ተመኘች ፣ የምትሆነውን አሳጣት አንድ የስልክ እንጨት ተደግፋ በእልህ እንደተወጠረች የነ ሴናን ጊቢ ታያለች ፣ቆየባት ...ለምን ታሪኩን እንደምትከተለው ለራሷም የገባት አትመስልም ታሪኩን መልሳ እጇ ማስገባት የፈለገችበት ምክንያት እራሱ አልገባትም ፣ ግን አንዳች ኀይል ወደታሪኩ እየገፋ ያመጣታል ፣ስለከዳት ልታጠፋው የምትፈልግም ይመስላታል ፣በሷ መፋታት የተደሰቱትን ሁሉ አዘን መስጠትም ነው አላማዋ ፣ ይሙቱ ሁሉም ይሙቱ ...........ብላ ተራገመች ......ወደ በሩ ሂጂ ሂጂ ከሚለው ስሜቷ ያባነናት ፣ የስልኳ ጩኽት ነበር .... ሳምሶን ይላል "አቤት "አለችው በቁጣ "እንዴ ወይዘሮ ምን ያስጮኽሻል "አላት "ምን ፈልገህ ነው ሳምሶን"አለችው ሰላማዊት የነሴናን ግቢ በንዴት እያየች "ኧረ በሙሉ ስሜ ጠራሽኝ ለዚም ተዳረስን ምን ሆነሽ ነው"አላት "አትጩኽ ባክህ አሁን ምን እንደምትፈልግ ተናገር አለዛ ልዝጋው" "እንዴ ምን ድነው ነገሩ ላገኝሽ ስለፈለኩ ነው የደወልኩት "አላት ተቆጥቶ "ለምን እንዳሻህ ሲያስፈልግህ የምታገላብጣት ሸሌ አደረከኝ እንዴ"አለችው ለንግግሯ ሳትጨነቅ "ምን አንቺ ልክስክስ እና ምንድነሽ "አላት ሳምሶን ቱግ ብሎ "ውሻ ሄደህ ሴት ውሻ ፈልግ ከአሁን በዋላ እነደውም እንዳትደውልልኝ እሺ "አለችው በጩኽት ፣ ለምን ሳምሶን ላይ እንደዛ በቁጣ እንደምትጮህ ለራሷም አልገባትም በቃ በንዴቷ ሰአት በመደወሉ ተጠቂ ሆኗል ፣ እሷ ንዴት ማብረጃ ብታደርገውም ፣ ሳምሶን ግን በቀላሉ ሊያየው አልፈለገም በጣም ተበሳጭቷል አጠገቡ ብትሆን ይጨፈላልቃት ነበር ፣ "አገኝሻለው አንቺ በረሮ ጨፍልቄ ነው ምገልሽ ልክስክስ"አላት "ከንተ የባሰ ልክስክስ አለ ?አንተ ነህ ከትዳሬ ያፋታኽኝ እዘቅት ውስጥ የከተትከኝ "አለች በጩኽት "ማን ጠራሽ ካለውበት የመጣሽው አንቺ እንዳገባ ሰው አርፈሽ አትቀመጪም ነበር "አላት "በቃ ዝም በል !!!" "አገኝሻለው እጨፈልቅሻለው እንደዛ ከንቱ ባልሽ በቀላሉ የምተውሽ እንዳይመስልሽ እሺ"ብሎ ስልኩን ዘጋው ፣ሰላማዊት ተራገመች .....ወይኔ ሰላማዊት ........ድጋሚ ስልኳ ሲጠራ ሳምሶን መስሏት "ምንድነው ሳምሶን ተወኝ በቃ!"ብላ ጮኽች "ተረጋጊ ግዛው ነኝ ቀጠሮ አችንን እንዳትረሺው ላስታውስሽ ብዬ ነው በምሽት የቀጠርሺኝ አንቺ ነሽ እና እየመሸ ሲመጣ ጓጓው "አላት እየሳቀ "አትጓጓ እመጣልሃለው !"አለች በለበጣ ቀስ በቀስ ወደራሷ ተመልሳ ወደቤቷ ተጓዘች ቀስ በቀስ ሁላችሁንም እበቀላችዋለው 'እያለች ደጋግማ እየተራገመች ለግዛ ወደደገሰችለት ድግስ ከመሄዷ በፊት መዘጋጀት እንዳለባት ከራሷጋር እያወራች ፈጠነች...............🥀 ✍️✍️✍️✍️✍️✍️ኪዶ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ 🔵ይቀጥላል,,,,,,,,, ✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️ ♥️ከወደዱት ሼር ያድርጉ♥️ @bewketuseyoum19
نمایش همه...
24
Photo unavailableShow in Telegram
ገራሚ ገራሚ Profile Picture ለምትፈልጉ ብቻ አሁኑኑ Join👀
نمایش همه...
🖼 Join 🖼