fa
Feedback
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

رفتن به کانال در Telegram

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

نمایش بیشتر
2025 سال در اعدادsnowflakes fon
card fon
44 133
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-747 روز
-34830 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
በወላይታ ሶዶ ከተማ የአጎቱን ልጅ የሆነችዉን የ3 ዓመት ህፃን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ       በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ከተማ አራዳ ቀበሌ ውስጥ የ 3 ዓመት ህፃን የሆነችውን የአጎቱን ልጅ በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱ ተገልጿል። በአራዳ ቀበሌ ጉሩሞ ኮይሻ ዳሞት ዳጌቾ ቀጠና ውስጥ ተከሳሽ አስፋው ቱቾ የተባለው  ግለሰብ  ለመግደል የሚያስችል ምንም ምክንያት ሳይኖረው  የ3 ዓመት ህጻን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደላት  ሲሆን ግለሰቡ ከሟች ቤተሠብ ጋር ምንም አይት ግጭት እንደሌለው ተረጋግጧል ሲሉ የሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ  ዲቪዥን ኃላፊ  ረዳት ኢንስፔክተር እንግዳ  ወርቁ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። የግድያ ወንጀሉን የፈጸመው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ወንጀሉን ስለመፈጸሙ ሲጠየቅ የአእምሮ ህመምተኛ ነኝ ባለማወቅ ነዉ የፈፀምኩት በማለት ቃሉን ይሰጣል፡፡ ፖሊስም የቀረበለትን ማስረጃ ሲያረጋግጥ ምንም አይነት ህመም እንደሌለበት እና ሆን ብሎ ወንጀሉን መፈፀሙን በማረጋገጥ የቀረበለትን የምርመራ መዝገብ የደረሰው  ለወላይታ  ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ያቀርባል፡፡ ፍርድ ቤቱም የቀረበለትን የክስ መዝገብ በተገቢው መንገድ ካረጋገጠ በኋላ ተከሳሽ በፈጸመው ወንጀል ጥፋተኛ በማለት ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት  በ22 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲሉ ረዳት ኢንስፔክተር እንግዳ ወርቁ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። ሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
21👎 12😢 8🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
በጦርነት በምትታመሰው ሱዳን ወታደራዊ ማመላለሻ አውሮፕላን ተከስክሶ የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ህይወት አለፈ ወታደራዊ ማመላለሻ አውሮፕላን በምስራቅ ሱዳን የአየር ማረፊያ ለማረፍ ሲሞክር መከስከሱ ተሰምታል። አደጋው በጦርነት በወደመችው ሀገር አሳዛኝ ክስተት ሲሆን ሁሉም የበረራ አባላት ህይወታቸው አልፌል። ኢሊዩሺን ኢል-76 የተሰኘው አውሮፕላን ወደ ፖርት ሱዳን ኦስማን ዲግና የአየር ማረፊያ ሲቃረብ መከስከሱን ሁለት ወታደራዊ ምንጮች ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ተናግረዋል። ምንጮቹ በማረፍ ሙከራው ወቅት የቴክኒካል ብልሽት እንዳጋጠመው ጠቅሰዋል።በአውሮፕላኑ ውስጥ ምን ያህሉ ሰዎች እንደነበሩ ያልገለፀው ከመንግስት ጋር የተገናኘው የሱዳን ጦር ሃይል፣ ሁሉም የአውሮፕላኑ አባላት ህይወታቸው ማለፉን ግን ይፋ አድርጓል። በአየር ማረፊያው ላይ የመጨረሻው አሳዛኝ ክስተት ያጋጠመው በግንቦት ወር ሲሆን፣ ሰው አልባ አውሮፕላኖች አየር መንገዱን ጨምሮ በፖርት ሱዳን በርካታ ቦታዎችን መደብደባቸው ይታወሳል። ሰኞ እለት፣ የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች (አር ኤስ ኤፍ) በምዕራብ ኮርዶፋን ግዛት የሚገኘውን ሄግሊግ የነዳጅ ማጣሪያ ስፍራን መያዛቸው ይታወሳል። የሱዳን ጦር ስፍራውን ለቆ ከወጣ በኋላ፣ የሱዳን ትልቁን የነዳጅ ማምረቻ ቦታ አር ኤስ ኤፍ ተቆጣጥሯል ሲል ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል። ወታደራዊ ምንጮች ለአልጀዚራ  እንደተናገሩት ሰራዊቱ ከባብኑሳ ምእራብ ኮርዶፋን እየለቀቀ ይገኛል። አር ኤስ ኤፍ  ካለፈው ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ ስትራቴጂካዊ ስፍራውን ተቆጣጥሯል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
8💔 7
Photo unavailableShow in Telegram
በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል በቀን ከ3 እስከ 4 ለወሲባዊና አካላዊ ጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ሴቶች አገልግሎት ያገኛሉ ተባለ  አሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ካለፉት አምስት ዓመታት አንስቶ ከክልሉ ሴቶች ጉዳይ ጋር በመተባበር እንዲሁም  ዩኒሴፍ በሚያገኘዉ ድጋፍ የአንድ መስኮት አገልግሎት በማቋቋም  አካላዊና ወሲባዊ ጥቃት ለሚደርስባቸዉ ሴቶችና ህፃናት የአንድ ማዕከል አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታዉቋል ። የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር መርቀኒ አወድ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት ሆስፒታሉ በቀን ወሲባዊና አካላዊ ጥቃት ለሚደርስባቸዉ ከ3 እስከ 4 ለሚሆኑ ሴቶችና ህፃናት የአንድ መስኮት አገልግሎት ይሰጣል ። ባለፉት 4 ወራት ለችግሩ ተጋላጭ ለሆኑ 218 ሴቶችና ህፃናት አገልግሎት መሰጠቱን ገልፀዉ ፤ከዚህ ዉስጥ ስድስቱ ህፃናት ሲሆን የተቀሩት ከ18 ዓመት የዕድሜ ክልል በታችና በላይ የሆናቸዉ ናቸዉ ብለዋል ። ይህ የአንድ መስኮት አገልግሎት በዉስጡ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ፣ጠቅላላ ሀኪም ፣ነርስ ፣የፖሊስ አካል ፣አቃቤ ህግና ሌሎችንም ያካተተ ሲሆን የመደፈር ጥቃት የደረሰባቸዉ ሴቶች የእርግዝናና የኤችአይቪ ምርመራ እንዲሁም ሌሎችንም ህክምናዎች እንዲያገኙ ከተደረገ በኃላ ወዲያዉኑ ጉዳያቸዉ በህግ ይታይላቸዋል ተብሏል ። ይህም መጉላላትን በማስቀረት ዉሳኔዎች በፍጥነት እንዲሰጡ የሚኖረዉ ሚና ከፍተኛ ነዉ ያሉት ዳይሬክተሩ አልፎ አልፎ የግብረሰዶም ጥቃት የሚደርስባቸዉ ወንዶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸዉን ገልፀዋል። በመባ ወርቅነህ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
9🤔 4😢 2🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
🛑በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ሳር ቤት ሳይት ተለቋል::
በካሽ 100% ለሚከፍል 35% ቅናሽ
📍ሳር ቤት ቫቲካን 🎯65/35 አከፍፈል (35%ቅናሽ) 👉2መኝታ 81 ካሬ =5.8 ሚሊዮን ብር 👉2መኝታ 106 ካሬ=7.6 ሚሊዮን ብር 👉3መኝታ 139 ካሬ=9.9 ሚሊዮን ብር 👉3መኝታ 152 ካሬ= 11.8 ሚሊዮን ብር 🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል 👉2መኝታ 81ካሬ ቅድመ ክፍያ(20%) = 1.78 ሚሊዮን ብር 👉2መኝታ 106ካሬ ቅድመ ክፍያ(20%)=2.33ሚሊዮን ብር 👉3መኝታ 139ካሬ ቅድመ ክፍያ(20%)= 3.06 ሚሊዮን ብር 👉3መኝታ 152ካሬ ቅድመ ክፍያ(20%)=3.34 ሚሊዮን ብር #ቀሪውን 80% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት * 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇👇👇 +251937341286 +251714558361 📲👇በ WhatsApp ማግኘት ከፈለጉ https://wa.me/251937341286 📲Channel: https://t.me/TemerRealEstateSalesAdvisor 📲Telegram : t.me/AbrhamTemerSales
نمایش همه...
6
Photo unavailableShow in Telegram
ሚያሚ በሦስት አስርት ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ዲሞክራት ከንቲባ መረጠች ዴሞክራቷ ኢሊን ሂጊንስ ለሚያሚ ከንቲባ ሆና ስትመረጥ ከሶስት አስርት ዓመታት በኋላ የዲሞክራት ፓርቲ የመጀመሪያ አባል ሆናለች። የትራምፕ ጠንካራ ድጋፍ ባለባት ፍሎሪዳ እንዲሁም የሂስፓኒክ ነዋሪዎች በሚበዙባት ከተማ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሚደገፉትን ሪፐብሊካን አሸንፋለች። ሲ ኤን ኤን እና አሶሺየትድ ፕሬስ ምርጫው ከተጠናቀቀ ከአንድ ሰአት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሂጊንስ ማሸነፏን ዘግበዋል። የቀድሞዋ ሚያሚ-ዴድ ካውንቲ ኮሚሽነር የሪፐብሊካን ተቀናቃኛቸውን ኤሚሊዮ ጎንዛሌዝን በ18 በመቶ ብልጫ አዲሷ ከንቲባ አግኝታለች። ይህ ውጤይ በ2026 የአጋማሽ ዘመን ምርጫዎች በኮንግረሱ ውስጥ የትራምፕን ብቸኛ የበላይነት ለማስጠበቅ ሪፓብሊካን ያላቸውን ተስፋ አደብዟል። የሂጊንስ ወሳኝ ድል ዲሞክራቶች ባለፈው ወር በምርጫ ካሳኩት ድል ቀጥሎ በፍጥነት የመጣ ስኬት ነው። እ.ኤ.አ. በ 2024 ትራምፕ ከዴሞክራቶች የነጠቁት የሂስፓኒክ ድጋፍ ከዚያን ጊዜ ወዲህ እየከሰመ ስለመሆኑ ሪፓብሊካኑ ያላቸውን ስጋት ያጠነክራል።የ61 ዓመቷ ሂጊንስ በፌስ ቡክ አካውንቷ ላይ ባጋራችው መግለጫ የድሏን ሀገራዊ እንድምታ አልተናገረችም ይልቁንም ውጤቱን በአገር ውስጥ ደረጃ "የአመታት ትርምስ እና ሙስና ላይ አዲስ ምዕራፍ " ነው በማለት ገልጻለች። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
8
Photo unavailableShow in Telegram
በሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የሚስተዋሉ ህገ ወጥ ተግባራትን ሙሉ ለሙሉ ማስቆም አልተቻለም ተባለ በየእለቱ ለጉብኝት ወደ  ሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፖርክ የሚመጡ ቱሪስቶች  ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም ፓርኩ ህገወጥ ተግባራት የሚከናወንበት መሆኑን የፓርኩ ፅ/ቤት አስታውቋል ። የፓርኩ ፅ/ቤት  ተወካይ ኃላፊ አቶ መልካሙ ላቀው ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በፓርኩ ውስጥ ከህገወጥ ሰፈራ ጋር በተያያዘ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት በተደረገው ጥረት እንዲህ ያለው ድርጊት አሁን ላይ ቀንሷል። ይሁን እንጂ ሰዎች ከብቶቻቸውንና የቤት እንስሳቶቻቸውን ወደ ፓርኩ በማስገባት ስፍራውን ለግጦሽ እንዲውል እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። በፓርኩ ውስጥ ቀደም ካሉት ጊዜያቶች አንስቶ የሰፈሩ ከ2መቶ በላይ አባወራዎች እንዳሉ የተናገሩት ተወካይ ኃላፊው በቦታው ላይ ምንም አይነት ጫና እንዳያሳድሩ የማድረግ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል። ነገር ግን የፓርኩን ደህንነት ሙሉ ለሙሉ ለመጠበቅ እና ለጉዳዮ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት በሚመለከተው አካል በኩል ወደ ሌላ ቦታ መዛወር እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የማድረግ  ስራ እየተሰራ መሆኑን አቶ መልካሙ ገልፀው ይህን ለመከላከል  ለማህበረሰቡ እየተደረገ ያለው የግንዛቤ መፍጠር ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። የፓርኩ አዋሳኝ  በሆነው በጃናሞራ ወረዳ በሚገኙ  አጥገባ እና ድብል ቀበሌዎች ከአጋር አካለት ጋር በመቀናጀት ለ750 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማሳደግ ስራ መከናወኑ ተገልጿል።ለዚህ አላማ በተዘጋጀው መድረክ ፓርኩ  ተጠብቆ ከቆየ ለቱሪስት መዳረሻነት በሚኖረው ፋይዳ እና ከዋልያ ጋር ተያይዞ የሚኖረውን ሀይማኖታዊ ዳራን በማንሳት   ውይይት ተካሂዷል። ቅድስት ደጀኔ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
2
Photo unavailableShow in Telegram
ማንችስተር ዩናይትድ በቅርቡ ከሜክሲኮዉ ክለብ ሞንትሬይ ጋር የተለያየዉን ሰርጂዮ ራሞስን የአጭር ጊዜ መፍትሔ በማድረግ በጥር ዝዉዉር ወደ ኦልድትራፎርድ ሊያመጡት እያሰቡ መሆኑን ካዴናሴር ዘግቧል። ዩናይትድ የአጥቂ ክፍሉ ግብ እያስቆጠረ ቢሆንም በተከላካይ ክፍሉ ድክመት ግን ብዙ ግቦች ተቆጥሮበታል። ታድያ ይህ መረጃ እዉን ከሆነ ሰርጂዮ ራሞስ ለዚህ መፍትሄ ይዞ ይመጣ ይሆን? #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
🤣 36 15👍 7👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዘሌንስኪ ከ60 እስከ 90 ቀናት ውስጥ ለምርጫ ለማካሃድ ዝግጁ ነኝ በማለት አሜሪካና አውሮፓ በጸጥታ ጉዳይ ላይ እንዲረዱን ሲሉ አሳሰቡ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የደህንነት እና የህግ ሁኔታዎች ከተረጋገጡ ከ60 እስከ 90 ቀናት ውስጥ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማድረግ "ዝግጁ" መሆናቸውን በመግለጽ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ሀገራይ በጦርነት ጊዜ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችለውን ድጋፍ እንዲፈጥሩ አሳስበዋል ። ከሮም ወደ ፖላንድ ፕሬዝዳንቱ ሲያቁኑ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የፀጥታ ጉዳይ ቁርጠኝነት እንዲኖራት ትፈልጋለች ብለዋል። ድጋፉም “የጦር መሳሪያ፣ የአየር መከላከያ ስርዓቶ እና የሆነ ነገር ቢከሰት ማዕቀብ እስከመጣል” ዝርዝር ጉዳዮች አሁንም እየተሰራ መሆኑን እና መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል ። አንዳንድ የኔቶ አባላት ስለ ዩክሬን አባልነት ጥርጣሬ እንዳላቸው አፅንዖት ሰጥተዋል። "እኛ እውነተኛ ሰዎች ነን፤ እኛ በእውነት ኔቶን መቀላቀል እንፈልጋለን ያ ፍትሃዊ ነው፤ ነገር ግን ዩናይትድ ስቴትስም ሆነ ሌሎች በርካታ ሀገራት ዩክሬንን እስካሁን ድረስ በኅብረቱ ውስጥ እንደማያዩት በእርግጠኝነት እናውቃለን "ሲሉ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ዙሪያ ላይ በይፋ አስተያየት ቢሰጡም ጉዳዩ በቅርብ ጊዜ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ግንኙነት እንዳልተነሳ ዜለንስኪ በድጋሚ ገልፀዋል። ትራምፕ ቀደም ሲል ዩክሬን ምርጫ የምታደርግበት "ሰዓቱ አሁን" ነው ኪየቭ "ምርጫ ላለማካሄድ ጦርነትን እየተጠቀመች ነው" በማለት ሲከራከሩ ቆይተዋል። ለረዥም ጊዜ ድምጽ አለመስጠት የዩክሬንን ዲሞክራሲ የመናድ አደጋ እንዳለውም ትራምፕ አስጠንቅቀዋል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
12👎 5😁 2
#ነዳጅ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋን ይፋ ማድረጉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል። የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር የዓለም የነዳጅ ዋጋን መነሻ በማድረግ ከታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀነ-6፡00 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋን ነው ይፋ ያደረገው። የአውሮፕላን፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ አና የከባድ ጥቁር ናፍጣ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ የሚቀጥል ሲሆን ፤ የቤንዚን፣ የነጭ ናፍጣ እና የኬሮሲን ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ግን ጭማሪ ተደርጎበታል። በእዚህም መሰረት ፦ - ቤንዚን 129.12 ብር በሊትር - ነጭ ናፍጣ 129.12 ብር በሊትር - ኬሮሲን 129.12 ብር በሊትር እንዲሸጡ የተወሰነ መሆኑ ታውቋል። #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
😭 14👎 8 4😁 3
Photo unavailableShow in Telegram
በአዲስ አበባ 4ተኛ ዙር የመልሶ ግንባታ 2000 የተለያዩ አቅም ያላቸውን ትራንስፎርመሮች ይተከላሉ ተባለ የአዲስ አበባ ዲስትሪቡሽን ኔትዎርክ ማጠናከሪያ 4ኛ ምዕራፍ ፕሮጀክት ስራ በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ኤሌትሪክ አገልግሎት አስታውቋል ፡፡ በሸገር እና በአዲስ አበባ ከተሞች ያለውን  የኃይል አቅርቦት አስተማማኝ ለማድረግ 703 ኪ.ሜ የዲስትሪቡሽን ኔትወርክ መልሶ ግንባታ እና አቅም ማሳደግ ሥራ  እየተከናወነ መሆኑን  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮምኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዋር አብራር ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ በፕሮጀክቱ 56 ወጪ መስመሮች እና በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ወጪ ሆነው እስከ ማሰራጫቸው ድረስ ሙሉ የመልሶ ግንባታ እና ማሻሻያ የሚሰራበት ፕሮጀክት ነው፡፡  እንዲሁም የአዲስ አበባ 4ኛ ዙር የዲስትሪቡሽን መልሶ ግንባታ ፕሮጀክት 2000 የተለያዩ አቅም ያላቸውን ትራንስፎርመሮች እንደሚተከሉ እና  2000 ነባር ትራንስፎርመሮችን ደግሞ አቅም የማሳደግ  ሥራ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ በፕሮጀክቱ 62 የሎድ ብሬክ ስዊች ገጠማ ሥራ የሚከናወን ሲሆን ይህም ከተፈቀደው የኃይል አጠቃቀም በላይ የሚቆጣጠር ይሆናል፡፡ በአሁኑ ወቅት የፖል ተከላ ሥራ እየተከናወነ ሲሆን እስካሁን 1ሺ927 ምሰሶ ተከላ ሥራ ተከናውኗል ፡፡ የፕሮጀክት ሥራው አጠቃላይ የፊዚካል ሥራው አፈፃፀም 32.83 በመቶ  የደረሰ ሲሆን የፋይናንስ አፈፃፀሙ ደግሞ 20 በመቶ ደርሷል፡፡ ፕሮጀክቱ በዓለም ባንክ የበጀት ምንጭ እየተከናወነ መሆኑ አቶ አንዋር አብራር ጨምረው ለብስራት ሬድዮ  ተናግረዋል  ፡፡ በምህረት ታደሰ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
10👎 3🤔 1
በአሪ ዞን የድሽታግና የዘመን መለወጫ በዓል እየተከበረ ይገኛል 👉 በዓሉ በማርበርግ  ቫይረስ ምክንያት ዘንድሮ በአደባባይ እንደማይከበር ተገልጿል የ2018 ዓ.ም የኣሪ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል ወይም ድሽታ ግና በዓል 10ኛ ዙር ዓመታዊ ክብረ-በዓል ከታህሳስ 1  ጀምሮ ይከበራል ። የኣሪ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል ድሽታ  ግና ልዩ ትኩረትና  ክብር አግኝቶ ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት የአደባባይ በዓል ሆኖ ሲከበር ተቀባይነት እያደገ በመምጣቱ ዞናዊ ከመሆን አልፎ ክልላዊና ሃገራዊ በዓል ሆኖ እየተከበረ እንደሚገኝ ተገልጿል ። ይሁን እና በዘንድሮ 10ኛው የዲሽታግና በዓል በአካባቢው ባጋጠመ የማርበርግ ቫይረስ  ምክንያት በአደባባይ መከበሩ ቀርቶ ሁሉም  በየራሱ በግል እንደሚያከበር የዞኑ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት  ባለሙያ የሆኑት አቶ የሱፍ አህመድ   በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።  በዓሉ ከዘመን መለወጫነት ባሻገር ለሰላም   ለአንድነትና ለሃገር ብልጽግና ካለው ፋይዳ አኳያ  በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ወካይ ቅርሶች ውስጥ ለማስመዝገብ "ባህል ለቱሪዝምና ህብረ-ብሄራዊ አንድነት!" በሚል መሪ ቃል  ይከበራል። ከህዳር ወር ጀምሮ በጂንካ ከተማ ድንገት የተከሰተው የማርበርግ ቫይረስ በሽታ የዘንድሮውን የአደባባይ በዓል ለማክበር አለመቻሉ በዓሉን በአደባባይ የማይከበረው  የበሽታው መተላለፊያ ምክንያት ንክኪ በመሆኑ እና ለህዝቦች ደህንነት ሲባል እንደሆነ ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል ሲሉ አቶ የሱፍ አህመድ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
12👎 4
Photo unavailableShow in Telegram
በታይላንድ እና ካምቦዲያ ድንበር ግጭት ከ500 ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ በታይላንድ እና በካምቦዲያ መካከል ያለው ጦርነት ለሶስተኛ ቀን የቀጠለ ሲሆን ድንበር ዘለል ጥቃቶች እና የአየር ወረራዎች ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ንፁሀን ዜጎች ቤታቸውን ጥለው መጠለያ እንዲፈልጉ አስገድዷቸዋል ሲል ባለስልጣናት ገልጸዋል። የሁለቱ የደቡብ ምስራቅ እስያ ጎረቤቶች ባለስልጣናት በዚህ ሳምንት ቢያንስ 13 ወታደሮችን እና ሲቪሎችን የገደለውን እንዲሁም ከ500 ሺ በላይ ሰዎችን ከሁለቱም የድንበር አከባቢዎች ለደህንነት እንዲሰደዱ ያደረገውን ግጭት እንደገና በማነሳሳት እርስ በእርሳቸው እየተወነጃጀሉ ይገኛል። የታይላንድ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሱራሰንት ኮንግሲሪ በሰጡት መግለጫ ከ400 ሺ በላይ ሰዎች ወደ ደህና መጠለያዎች ተወስደዋል ብለዋል ። ለደህንነታቸው አደገኛ ነው ብለን በገመትነው ስፍራ ሲቪሎች እንዳይቆዩ በብዛት መፈናቀል አለባቸው ብለዋል። የታይላንድ ጦር ረቡዕ ማለዳ ላይ ከካምቦዲያ የተተኮሱ ሮኬቶች በሱሪን ፋኖም ዶንግ ራክ ሆስፒታል አቅራቢያ በማረፋቸው ታማሚዎችና የሆስፒታሉ ሰራተኞች ወደ አስተማማኝ ስፍራ በመግባት እንዲከለሉ ማስገደዱን አስታውቋል። በአጎራባች ካምቦዲያ 101 ሺ 2 መቶ 29 ሰዎች በአምስት አውራጃዎች ወደሚገኙ አስተማማኝ መጠለያዎች እና ወደ ዘመዶቻቸው ቤት ተወስደዋል ሲሉ የካምቦዲያ ብሔራዊ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሊ ሶቼታ ተናግረዋል ። በካምቦዲያ ሚዲያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስር የሚተዳደረው ካምቦዲያነስ ድረ-ገጽ የታይላንድ ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች በሀገሪቱ በሚገኙ ሁለት ቦታዎች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ዘግቧል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
6🕊 2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ትራምፕ የአውሮጳ መሪዎችን ደካማ ሲሉ ተቹ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአውሮፓ መሪዎችን “ደካማ” ሲሉ በመተቸት አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገውን ድጋፍ ልትቀንስ እንደምትችል ጠቁመዋል። ከፖሊቲኮ ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለ ምልልስ፣ የአውሮፓ ሀገራት ስደተኞችን ለመቆጣጠር እና ዩክሬን ከሩሲያ ጋር የምታደርገውን ጦርነት ለማስቆም ቆራጥ ርምጃ መውሰድ ተስኗቸው፥ ኪየቭ “እስክትወድቅ ድረስ” እንድትዋጋ ፈቅደዋል ሲሉ ከሰዋል። ጦርነቱን ለማስቆም በዩናይትድ ስቴትስ መሪነት በሚደረገው ጥረት የአውሮፓ መሪዎች የአህጉሪቱን የረዥም ጊዜ ጥቅም ያሳጣል ብለው በመስጋት ሚናቸውን ለመቅረጽ ሙከራ አድርገዋል። ለትራምፕ ንግግር የአፀፋ ምላሽ የሰጡት የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢቬት ኩፐር በአውሮፓ የምንመለከተው ሁሉ "ጥንካሬ" ነው ብለዋል። በመከላከያ ረገድ መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ ማድረግ እና ለኪየቭ የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ አንስተዋል። ትራምፕን እና የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪን በመጥቀስ ሁለት ፕሬዚዳንቶች "ለሰላም እየሰሩ ነው" ስትል ሚኒስትሯ የተናገረች ሲሆን አንድ ፕሬዝዳንት በማለት የጠቀሰቻቸው ፑቲን ግን እስካሁን ድረስ ተጨማሪ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና የሚሳኤል ጥቃቶችን በመጠቀም ግጭቱን ለማባባስ ጥረት አድርገዋል ስትል አክላለች። ትራምፕ በዜለንስኪ የሰላም ስምምነት ላይ ጫና ማድረጋቸውን የቀጠሉት ሲሆን ዩክሬን ግዛቷን ለሞስኮ አሳልፋ እንድትሰጥ አሳስበዋል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
15😁 5👍 2👎 2🤣 2
የወላይታ ሕዝብ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ በሕንድ፣ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ጥበቃ ኮሚቴ ጉባኤ ተካሂዷል። በዚህ ጉባዔ ላይ ኢትዮጵያ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ያቀረበችው የወላይታ ሕዝብ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በሰው ልጅ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ዝርዝር ስር ተመዝግቧል። "ጊፋታ" በወላይታ ማኅበረሰብ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ በዓል ሲሆን፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የሕዝቡ የማንነት መገለጫ የሆነ የአሮጌው ዓመት ማብቂያና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ የመሸጋገሪያ በዓል ነው፡፡ ጊፋታ እድሜ፣ ጾታ፣ ሃይማኖት ወይም ሌላ ማኅበራዊ ደረጃ ሳይለይ ለሁሉም ሠላም እና ማኅበራዊ ትሥሥር አስተዋጽኦ በማድረግ በዩኔስኮ የተለዩትን ዘርፎች ያካተተ ሁሉን አቀፍ ተግባራትን በማበረታታት የሚከበር በዓል መሆኑ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ አስችሎታል። በሀገራችን 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በተከበረ ማግስት የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል፣ "ጊፋታ" በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ አጋጣሚውን ታሪካዊ ያደርገዋል። በዚህ ጉባዔም ላይ የቱሪዝም ሚንስትር ሠላማዊት ካሳ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ንግግር አድርገዋል። #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
30👎 4
የአዲስ አበባ አነስተኛ እና መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ  ተሽከርካሪዎች መናሃሪያ ውስጥ ተሳፋሪ እንዳያወርዱ በመከልከሉ አሽከርካሪዎች እና ተጓዥ መንገደኞች መቸገራቸውን ገለጹ የአዲስ አበባ አነስተኛ እና መለስተኛ የህዝብ  ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ስምሪት መናሃሪያ ውስጥ ተሳፋሪዎችን ማውረድ በመከልከሉ ለችግር መጋለጣቸውን አሽከርካሪዎች እና ተጓዦች ለብስራት ሬድዮ ቅሬታቸው አቅርበዋል።ከዚህ ቀደም አሽከርካሪዎች ተሳፋሪ መንገደኞችን  እና እቃቸውን  ከተለያየ ቦታ በመጫን መጨረሻ ላይ የአዲስ አበባ አነስተኛ እና መለስተኛ ስምሪት መናሃሪያ በማራገፍ ተጓዦች ለእንግልትና የስርቆት ወንጀሎች እንዳይጋለጡ ያደርጉ እንደነበረ ገልዋል። በአሁኑ ጊዜ በመከልከሉ በተሳፋሪዎች ተጓዦች ላይ ከፍተኛ እንግልት እና መጉላላት መፈጠሩን ገልፀዋል። ከዚህም ሌላ መንገድ ላይ ተሳፋሪ ተጓዦች ሲያወርዱ ከትራፊክ ኤጀንሲ እና ፖሊሶች እንዲሁም ከትራንስፖርት ተቆጣጣሪዎች ጋር አላስፈላጊ ነገር  ውስጥ እየገቡ በመሆኑ ተጓዦችን የሚያራግፉበት ቦታ እንዲመቻች ጠይቀዋል።ተጓዥ ተሳፋሪዎች በበኩላቸው መናሃሪያ ውስጥ ማራገፍ በመከልከሉ በእቃ ማውረድ በኩል በየመንደሩ ካሉ ወጣቶች ጋር ግጭት እየተፈጠረ እና  መንገድ የማያቁ ተጓዦች ለስርቆት መጋለጣቸውን ተጠቁሟል። የሚመለከተው አካል ይህንን ተገንዝቦ የማስተካከያ እርምት እንዲ ወስድ ጠይቀዋል። የአዲስ አበባ አነስተኛ እና መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ስምሪት መናሃሪያ ሃላፊ አቶ ሳሙኤል ሳቀታ የቀረበውን ቅሬታ አስመልክቶ በሰጡት መልስ መናሃሪያ በአሁን ጊዜ 85 መስመሮችን በመሸፈን የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ነው ብለዋል። በዚህም  በዋነኝነት ከአዲስ አበባ- ደጀን ፣ ቡታጅራ፣ወልቂጤ ፣አዳማ፣ መስመር ላይ ያሉ ከተሞችን ያማከለ የህዝብ ትራንስፖርት እንቅስቃሴ የሚያስተናግድ መናሃሪያ መሆኑን ጠቅሰው ፣በአሁኑ ሰዓት ካለው የተሽከርካሪ ብዛት ጋር  ወደተለያየ ቦታ የሚጓዘው የትራንስፖርት ተገልጋይ ማህበረሰብ እና መናሃሪያ ውስጥ የሚራገፈው ተገልጋይ መናሃሪውን በማጣበቡ ይህ ግዚያዊ መፍትሄ ስራ ላይ መዋሉን ገልፀዋል። እንደ አማራጭም የአዲስ አበባ አገር አቋራጭ መናሃሪያ ከስምሪት በኋላ አሽከርካሪዎች ለተገልጋዮች ማራገፊያ እንዲያገለግል ስምምነት ላይ የተደረሰ መሆኑን ገልጸዋል ። ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የትራፊክ ማኔጅመንት ፣ፖሊስና የትራንስፖርት ፅ/ቤት ውይይት ተደርጎ የመግባቢያ ሃሳብ ላይ መደረሱን አቶ ሳሙኤል ሳቀታ ጨምረው ገልፀዋል።ለበርካታ ዓመታት የአውቶብስ ተራ የሚገኘው አነስተኛ እና መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ስምሪት መናሃሪያ የማስፋፍያ ፕሮጀክት በቅርብ ስለሚጀምር የተገልጋዩ እና የአሽከርካሪዎች ቅሬታ ይፈታል የሚል ግምት እዳላቸው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
22🙏 3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
1
በሰሜናዊ ጃፓን በሬክተር ስኬል 7.5 በተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በርካቶች ቆሰሉ ሰኞ ምሽት በሰሜን ምስራቅ ጃፓን በሬክተር ስኬል 7.5 በሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ 30 ሰዎች ሲቆስሉ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ተገደዋል፡፡የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው በ 50 ኪ.ሜ ጥልቀት፣ ከአኦሞሪ ክልል የባህር ዳርቻ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው ሲል የጃፓን የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታውቋል። በዚህም የሱናሚ ማስጠንቀቂያዎችን ተሰጥቷል፡፡ አንዳንድ የባቡር አገልግሎቶች ተቋርጠው በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች የኤሌክትሪክ አገልግሎት አጥተዋል።ባለስልጣናት በተጨማሪም በመጪዎቹ ቀናት ጠንከር ያለ መንቀጥቀጥ ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡ህዝቡ ቢያንስ ለአንድ ሳምንት በንቃት እንዲጠብቅ ማሳሰቢያ መሰጠቱን የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል ። የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናይ ታካይቺ በመሬት መንቀጥቀጡ የተጎዱ ዜጎች ጋር ባደረጉት ቀይታ “የዕለት ተዕለት የመሬት መንቀጥቀጥ ዝግጁነታቸዉን እንዲያጠናክሩ መክረዉ የቤት እቃዎችን አቀማመጥ ጥንቃቄ እንደሚያደርጉ አሳስበዋል፡፡ መሬት መንቀጥቀጥ ከተሰማዎት ወዲያውኑ ለቀው ለመውጣት ተዘጋጁ” ሲሉ አክለዋል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
11😱 7👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
♦️🌴ቴምር ሪልስቴት ሱቅ ሽያጭ የተንጣለለ ዘመናዊ G+4 ሞል በቃሊቲ(ገላን)
💢8 ሳይቶችን ሰርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ቃሊቲ(ገላን) ለሽያጭ ያወጣነው ሱቅ
🛑ቃሊቲ( ገላን ) ሱቅ ሽያጭ  🎯አራተኛ Floor ላይ       👉ጠቅላላ ክፍያ = 2.5 ሚሊዮን ብር       👉የካሬ መጠን = 23.5ካሬ       👉ቅድመ ክፍያ = 500,000 ብር 🎯ሶስተኛ Floor ላይ       👉ጠቅላላ ክፍያ = 2.6ሚሊዮን ብር       👉የካሬ መጠን = 26.8ካሬ       👉ቅድመ ክፍያ = 600,000 ብር 🎯ሁለተኛ Floor ላይ       👉ጠቅላላ ክፍያ = 2.8 ሚሊዮን ብር       👉የካሬ መጠን = 26.8ካሬ       👉ቅድመ ክፍያ = 800,000 ብር 🎯አንደኛ Floor ላይ       👉ሙሉ ክፍያ = 3.2 ሚሊዮን ብር       👉የካሬ መጠን = 26.4ካሬ       👉ቅድመ ክፍያ = 1.2 ሚሊዮን ብር 🎯Ground ላይ ባለ 16 ካሬ       👉ጠቅላላ ክፍያ = 4.3 ሚሊዮን ብር       👉ቅድመ ክፍያ = 1.8 ሚሊዮን ብር 🎯Ground ላይ ባለ 26 ካሬ       👉ጠቅላላ ክፍያ = 4.5 ሚሊዮን ብር       👉ቅድመ ክፍያ = 2 ሚሊዮን ብር 🎯Ground ላይ ባለ 24 ካሬ       👉ጠቅላላ ክፍያ = 6.9 ሚሊዮን ብር       👉ቅድመ ክፍያ = 3 ሚሊዮን ብር ☎️ለበለጠ መረጃ ይደውሉ 👇👇👇👇👇👇 +251937341286 +251714558361 📲👇በ WhatsApp ማግኘት ከፈለጉ https://wa.me/251937341286 📲Channel: https://t.me/TemerRealEstateSalesAdvisor 📲Telegram : t.me/AbrhamTemerSales
نمایش همه...
5
Photo unavailableShow in Telegram
በቤንሻንጉል ጉምዝ በንጋት ሀይቅ 1ሺህ 973 ቶን የዓሳ ምርት መመረቱ ተገለፀ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በታላቁ ህዳሴ ግድብ በንጋት ሀይቅ ላይ በ2018 በጀት ዓመት ከሀምሌ ወር ጀምሮ 1ሺህ 973 ቶን የዓሳ ምርት መመረቱን የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የግብርና ቢሮ የአሳ ሀብት ባለሙያ አቶ ቡሸን ፉፋ ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል። በህዳሴ ግድብ ንጋት ሀይቅ ላይ በሰፊ እየተመረተ ያለው የዓሳ አይነት ቆሮሶ፣ ናይል ፐርች፣ ነጭ ዓሳ እና አምባዛ የተባሉ የአሳ አይነቶች እንደሚመረቱ ገልፀው ምርቱ በከፍተኛ ሁኔታ ወደ አሶሳ፣ ማዕከላዊ ገበያ የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም ወደ አዲስ አበባ እየተከፋፈለ እንደሆነ ገልፀዋል። በተጨማሪም በዓሳ ምርት ላይ የተደራጁ ወጣቶች እና ማህበራት ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ለማስገባት የዓሳ ምርት በሚፈለገው መልኩ እንዲመረት መንግስት ከልማት አጋር ድርጅቶችን በማሳተፍ ዘመናዊ የዓሳ ማስገሪያ ግብዓቶችን እንደ ጀልባ፣ መረብ፣ የዓሳ ማጓጓዥያ ፍርጅ መኪና እና የማቆያ ፍሪጅ ለሟሟላት ሰፊ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የግብርና ቢሮ የአሳ ሀብት ባለሙያ አቶ ቡሸን ፉፋ ለብስራት ሬዲዮ ጨምረው ገልፀዋል። በሰመሀር አለባቸው #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
17👎 2🔥 1
የሱዳን አየር ሃይል በከተሞች፣ በገበያዎች እና በትምህርት ቤቶች ላይ ባደረሰው የቦምብ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸዉ ተሰማ የሱዳን አየር ሃይል በፈጸመዉ የቦምብ ጥቃት ቢያንስ 1,700 ንፁሀን ዜጎች በመኖሪያ ሰፈሮች፣ በገበያዎች፣ በትምህርት ቤቶች እንዲሁም በተፈናቃዮች መጠለያ ካምፖች ላይ መገደላቸዉን በሀገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት የአየር ወረራ ላይ በተደረገው ጥናት ተመላክቷል።የሱዳን ምስክሮች ፕሮጀክት በሚያዝያ 2023 በጀመረው ግጭት ትልቁን የታወቁ ወታደራዊ የአየር ጥቃቶችን መረጃ ማዘጋጀቱን አስታዉቋል። የአየር ኃይሉ ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች መመሪያ አልባ ቦምቦችን መጠቀሙን የሰጠው ትንታኔ ያሳያል።መረጃው የሚያተኩረው በጦር አውሮፕላኖች በሚሰነዘረው ጥቃት ላይ ሲሆን ይህም የሱዳን ጦር ሃይል ብቻ ነው ሊንቀሳቀስ የሚችለው ብሏል። ተቀናቃኙ፣ ፓራሚሊተሪ የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች (አር ኤስ ኤፍ) የጦር አውሮፕላን የለውም ሲል ሪፖርት አመላክቷል። አር ኤስ ኤፍ በሱዳን ምዕራብ ዳርፉር ግዛት የዘር ጭፍጨፋ ፈጽሟል በሚል በዩናይትድ ስቴትስ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሷል በሚል በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወግዟል።ፕሮጀክቱን የሚመሩት ማርክ ስኖክ "ለብዙ ጉዳቶች እና ጥሰቶች አርኤስኤፍ ተጠያቂ ናቸው፣ እና ትክክል ይመስለኛል" ብለዋል። እንዲሁም የሱዳን ጦር ለድርጊታቸው ተጠያቂ መሆን ያለበት ይመስለኛል ሲሉ አክለዋል። በሌላ በኩል ከ700 የሚበልጡ ሱዳናውያን ከደቡብ እና ሰሜን ኮርዶፋን በከፋ የፀጥታ ችግር ሳቢያ በአንድ ቀን ውስጥ ተፈናቅለዋል ሲል የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) አስታውቋል።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመስክ ቡድኖች 650 ሰዎች ቅዳሜ ዕለት በሰሜን ኮርዶፋን ውስጥ በአር-ራሃድ አካባቢ ከኢምራን መንደር ሸሽተዋል ሲሉ ቀሪዎቹ ሰዎች ደግሞ ከደቡባዊ ኮርዶፋን ግጭትን ፍራቻ ወደተለያዩ አካባቢዎች ተንቀሳቅሰዋል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
11🤔 2🤯 2