ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
رفتن به کانال در Telegram
The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

44 133
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-747 روز
-34830 روز
آرشیو پست ها
በስራ መግቢያና መውጪያ ሰዓት በልዩ ሁኔታ ለተፈቀደላቸው ተቋማት ብቻ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለከባድ መኪና የመንቀሳቀሻ ፈቃድ እየሰጠ ነው
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን የትራፊክ መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የከባድ መኪና መንቀሳቀሻ ፈቃድ በልዩ ሁኔታ ለተፈቀደላቸው ተቋማት ብቻ እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡የባለሥልጣኑ የትራፊክ መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ነጻነት በቀለ ከብስራት ሬዲዮ በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት በስራ መግቢያና መውጪያ ሰዓት የከባድ መኪና የመንቀሳቀሻ ፈቃድ ለጠየቀ ሁሉ የሚሰጥ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ፍቃዱ የሚሰጠው ከተማ አስተዳደሩ እያሰራቸው ላሉ የልማት ስራዎች እንደ ኮሪደር ልማት፣ የጫካ ፕሮጅክት እንዲሁም ለአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን፣ ውሃና ፍሳሽ፣ የአበባ፣ የስጋ እና እንጀራ ኤክስፖርት ለሚያደርጉ በኢንዳስትሪ ሚኒስቴር በኩል ፈቃዱ ላላቸው ተቋማት ብቻ እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡በተቋሙ የሚሰጠውን የከባድ መኪና የመንቀሳቀሻ ፈቃድ በቴክኖሎጂ የተደገፈ በጎግል ሽት እና በኪው አር ኮድ አማካኝነት የሚዘጋጅ ነው፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተመሳስሎ በተሰራ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሀሰተኛ የመንቀሳቀሻ ፈቃድ ሰነድ የሚያሰሩ አካላት እንዳሉ የጠቆሙት ሃላፊዋ በዚሁ ተግባር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በመስክ ክትትል እንደተደረሰባቸው ተናግረዋል። እንዲሁም በተያዘው በጀት ዓመት የተሽከርካሪ መስታወት ማጥቆሪያ /ቲንትድ/ ስቲከር ፈቃድ አግልግሎት ወደ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር እንደተዛወረ እየታወቀ በባለሥልጣን መ/ቤቱ የፈቃድ አገልግሎቱ እየተሰጠ እደሚገኝና ሰነዱም ከተቋሙ እንደወጣ አስመስለው ሲገለገሉ የተገኙ ግለሰቦች ለህግ አካል ተላልፈው መሰጠታቸዉን የባለስልጣኑ ዳይሬክተር ወ/ሮ ነጻነት በቀለ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
ሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 10👎 8
Photo unavailableShow in Telegram
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሱዳን በሰው አልባ አውሮፕላኖች በተፈጸመ ጥቃት በርካቶች መገደላቸዉን አስታወቀ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በሱዳን በደረሰው ጥቃት የበርካታ ንፁሀን ዜጎች ህይወት የቀጠፈውን የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ቁጣቸዉን ገለጹ፡፡"ዋና ጸሃፊው በደቡብ ኮርዶፋን በደረሰው አሰቃቂ ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ህጻናት እና ሌሎች ሲቪሎች መሞታቸውን በሚገልጹ ዘገባዎች መደናገጣቸዉን" ቃል አቀባያቸዉ ስቴፋን ዱጃሪች በመግለጫቸው ተናግረዋል።
በዲሴምበር 4 በካሎጊ ከተማ ሶስት የተለያዩ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት መፈፀማቸው ተሰምቷል፡፡ ሁለቱ ድሮኖች መዋለ ህፃናትን ሲመቱ ሌላኛው ደግሞ ቁስለኞችህክምና ላይ በሚገኙበት ሆስፒታል ላይ መውደቃቸውን በመግለጫው ተጠቅሷል።ጉቴሬዝ በሲቪሎች እና በሲቪል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ሁሉ አውግዘዋል፣ የትምህርት እና የህክምና ተቋማትን ኢላማ ማድረግ የአለም አቀፍ የሰብአዊ ህግን መጣስ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል።
በተመሳሳይ ቀን በሰሜን ኮርዶፋን የአየር ላይ ጥቃት ወደ ሰሜን ዳርፉር የምግብ ርዳታ ሲጭን በነበረ የሰብአዊ ልዑክ ላይ ጥቃት በመሰንዘር የአለም የምግብ ፕሮግራም የጭነት መኪና ላይ ጉዳት በማድረስ ሹፌሩን ክፉኛ አቁስሏል።"ዋና ጸሃፊው ይህ በሰብአዊ እርዳታ ላይ ተጨማሪ ጥቃትን መፈጸም በአስቸጋሪ ወቅት በመሆኑ ያሳዝናል" ብለዋል፡፡ጉቴሬዝ በተፋላሚ ወገኖች ላይ ተጽእኖ ያላቸው ሁሉም ሀገራት እርምጃ እንዲወስዱ እና አቅማቸውን ተጠቅመው ጦርነቱን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ብሎም ግጭቱን የሚያባብሱ የጦር መሳሪያዎችን መላክ እንዲያቆሙ አሳስበዋል ።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 9💔 2
Photo unavailableShow in Telegram
የጉራጊኛ ቋንቋን በስርዓተ ትምህርት ዉስጥ እስከ 8ኛ ክፍል ለማካተት እየተሰራ ነዉ ተባለ
የጉራጊኛ ቋንቋን ለማሳደግ በትምህርት ስርዓቱ ዉስጥ የማካተት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ የተገለፀ ሲሆን በ2017 የትምህርት ዘመን በሙከራ ደረጃ የነበረዉ የ2ኛ ክፍል የጉራጊኛ ትምህርት ወደ ሙሉ ትግበራ መግባቱን የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታዉቋል ።
በዞኑ ጉራጊኛ ቋንቋ በ2017 ዓ.ም የስራ ፣የሚዲያና የትምህርት ቋንቋ እንዲሆን በምክር ቤት መወሰኑን ተከትሎ ቋንቋዉን ይበልጥ ለማሳደግ በቋንቋዉ ከማዉራት ባለፈ በስርዓተ ትምህርት ዉስጥ የማካተት ሂደት በዘንድሮ አመት በ3ኛ ክፍል በ18 ትምህርት ቤቶች በሙከራ ደረጃ እንደሚሰጥ የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
በዞኑ ባለፉት ዓመታት የጉራጊኛ ትምህርት በቅድመ መጀበኛና በአንደኛ ክፍል በሙሉ ትግበራ መሰጠቱን ለጣቢያችን የተናገሩት ኃላፊዉ አምና በሙከራ ደረጃ የነበረዉ የ2ኛ ክፍል የጉራጊኛ ትምህርት በሙሉ ትግበራ መሰጠት መጀመሩን ገልፀዋል ።ለዚህም በዞኑ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ከ13ሺህ 5 መቶ የመማሪያና ማስተማሪያ መፅሀፍት ማሳተም መቻሉ ተናግሯል ።
በቀጣይ ዓመት የ3ኛ ክፍል የጉራጊኛ ትምህርት በሁሉም ትምህርት ቤቶች ወደ ትግበራ እንደሚገባ ተገልጿል ።በተጨማሪም በቀጣይ አራት እና አምስት ዓመታት ዉስጥ የጉራጊኛ ትምህርትን በስርዓተ ትምህርቱ ዉስጥ እስከ 8ኛ ክፍል ለማካተት እየተሰራ መሆኑን የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ገልጸዋል ።
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 65😁 21👍 8👎 4👌 1
ከመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በኋላ በቤኒን ያለው ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ተናገሩ
ቤኒን ከመንግስት ግልበጣ ሙከራ በኃላ "ድርጊቱ በፍፁም ቁጥጥር ስር መሆኑን" እና ዜጎች ወደ መደበኛ ተግባራቸው እየተመለሱ እንደሚገኙ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ታሎን እሁድ እለት በሀገሪቱ የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት አስመልክቶ ሰኞ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ፕሬዝደንት በመንግስት ብሮድካስቲንግ ቤኒን ቲቪ በኩል ለህዝቡ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ትንንሽ የወታደር ቡድን የዲሞክራሲያዊ ስርዓቱን በመቃወም የሪፐብሊካን ተቋማትን ለማጥቃት እና ሀገሪቱን ለማተራመስ እንቅስቃሴ መጀመራቸዉን አስታውሰዋል።
ታሎን እንደ ፕሬዝዳንት እና የሰራዊት ጠቅላይ አዛዥነታቸዉ የሀገሪቱን ደህንነት ለማረጋገጥ አስፈላጊ እርምጃዎችን መዉሰዳቸዉን ገልጸዋል፡፡ የቤኒን ፕሬዝዳንት በተጨማሪም "ሪፐብሊካዊ እና ለአገሪቱ ታማኝ" ሆነው የቆዩትን የሰራዊት ባለስልጣናትን አመስግነው ይህ ሙከራ "ያለ ቅጣት እንደማይታለፍ" ቃል ገብተዋል፡፡የቤኒን ወታደሮች ቡድን እሁድ እለት ቀደም ብሎ ለመንግስት ብሮድካስቲንግ እንደተናገሩት ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ታሎንን ከስልጣን አንስተው ሌተናል ኮሎኔል ፓስካል ትግሪን አዲስ የተቋቋመውን “የተሃድሶ ወታደራዊ ኮሚቴ” እንዲመሩ መሾማቸዉን አስታዉቀዉ ነበር።
የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አላሳኔ ሲዱ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበዉ እንደተናገሩት "በጥቃቅን ወታደሮች" የተደረገው መፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሸፉን ዜጎቹ የእለት ተእለት ተግባራቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።የሀገር ውስጥ የዜና ጣቢያ 24 ሄሬስ አው ቤኒን እንደዘገበው የመከላከያ እና የጸጥታ ሃይሎች ሌተናል ኮሎኔል ፓስካል ትግሪን እየፈለጉ ነው ሲሉ ይፋ አድርገዋል።የተሞከረው መፈንቅለ መንግስት ህዳር ወር መጨረሻ በጊኒ ቢሳው የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ጄኔራል ሆርታ ኢንታ-ኤ የሽግግር ፕሬዝደንት ሆነዉ መሾማቸዉ ይታወሳል፡፡
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 16👎 2😱 1
የጠለፋ እና የእገታ ተግባር የፈፀሙ አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
በምዕራብ ሸዋ እና በሰሜን ሸዋ ሁለት ዞኖች ውስጥ የጠለፋና የእገታ ተግባር የፈፀሙ አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ።እንደ ምዕራብ ሸዋ ዞን የአደአ በርጋ ወረዳ አቃቢ ሕግ ፅህፈት መግለጫ 1ኛ ተከሳሽ ግርማ ሳሕሉ 2ኛ ተከሳሽ ፀጋ ሐይሉ 3ኛ ተከሳሽ ቶሊ ደጉ የተባሉ ሶስት ተከሳሾች ጥቅምት 11 ቀን 2018ዓም ከቀኑ ዘጠኝ ሠዓት ላይ ለአንደኛው ተከሣሽ በግዳጅ የትዳር አጋሩ ለማድረግ የአስራ አራት ዓመቷን ታዳጊ ከወፍጮ ቤት ስትመለስ ጠብቀው የጠለፋ ተግባር ፈፅመው ለማምለጥ ሲሞክሩ ተጠላፊዋ ባሰማችው የድረሱልኝ ጩኸት ስልጠና ላይ የነበሩ የፀጥታ አካላት ሰምተው ተከታትለው በቁጥጥር ስር ዉለዋል።
ሶስቱም ተከሳሾች በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኃላ በፖሊስ የምርመራ መዝገባቸው በበቂ ማስረጃ ተጣርቶ ለአቃቤ ሕግ የተላከ ሲሆን አቃቤ ሕግም በወንጀል ሕግ ቁጥር 587 ንዑስ አንቀፅ 1 ሴትን በመጥለፍ ወንጀል ክስ መስርቷል፡፡ ክሱን ሲከታተል የቆየው የአደአ በርጋ ወረዳ ፍርድ ቤት ጥቅምት 24-2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሶስቱም ተከሣሾች ላይ በእያንዳዳቸው ላይ በሉለት አመት ከሶስት ወር እስራት እንደተወሰነባቸው የአቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫው አመልክቷል።
በተመሳሳይ በወረጃርሶ ወረዳ ሌንጮ ቦርሱ ቀበሌ የጦር መሣርያ በመታጠቅ የእገታ ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጠተዋል።እንደ ወረጃርሶ ወረዳ አቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫ ደሬሣ ተሾመ እና ጀማል ደምሴ የተባሉ ሑለት ተከሳሾች ለግዜው እጃቸው ካልተያዙ ሑለት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን የጦር መሣርያ በመታጠቅ መስከረም 25 ቀን 2018 ዓም ሁለት ግለሰቦችን አግተው አፍነው ለመውሠድ ሲሞክሩ በፀጥታ ስራ ላይ በተሠማሩ አካላት በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።
ፖሊስም በሁለቱ ተከሣሾች ላይ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሠባሰብ አጠናክሮ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ሕግ የላከ ሲሆን አቃቤ ሕግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በጦር መሣርያ በመታገዝ የእገታ ተግባር መፈፀምን ጠቅሶ ክስ የመሠረተ ሲሆን ክሱን ሲከታተል የቆየው የወረጃርሶ ወረዳ ፍርድ ቤት ሕዳር 24 ቀን 2018ዓም በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሣሽ ደሬሣ ተሾመ ስምንት አመት ከአራት ወር እስራት ሁለተኛ ተከሳሽ ጀማል ደምሴ በስድስት አመት ከስድስት ወራት እስራት እንዲቀጡ የወሠነ መሆኑን የአቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫ አመላክቷል።
በሰመሀር አለባቸው
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 12
Photo unavailableShow in Telegram
ታይላንድ ከካምቦዲያ ጋር ግጭት ውስጥ መግባቷን ተከትሎ የአየር ላይ ጥቃትን ጀመረች
የሮያል የታይላንድ ጦር የካምቦዲያ ጦር በወሰደው እርምጃ ቢያንስ አንድ ወታደር ተገድሎብኛል ሲል ከከሰሰ በኋላ በአወዛጋቢው የካምቦዲያ ድንበር ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል። ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ዊንታይ ሱቫሪ ዛሬ ሰኞ ዕለት በሰጡት መግለጫ በኡቦን ራቻታኒ ግዛት በናም ዩን አውራጃ በቾንግ ቦክ አካባቢ በተፈፀመብን ጥቃት የተነሳ የታይላንድ ጦር የጦር አውሮፕላኖችን አሰማርቷል ብለዋል።
ሱቫሪ ቢያንስ አራት ሌሎች ወታደሮች ቆስለዋል ብለዋል። አክለውም የታይላንድ ጦር "በድንበር አካባቢዎች ለሚኖሩ የተፈናቀሉ ሲቪሎች የሚደረገውን ድጋፍ እያፋጠነ ነው" ብለዋል። ካምቦዲያም ጥቃቱ መፈፀሙን አረጋግጣለች። የካምቦዲያ የብሄራዊ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሊ ሶቼታ ለኤኤፍኤፍ የዜና ወኪል እንደተናገሩት የታይላንድ ወታደሮች ሰኞ ማለዳ ላይ በፕሬህ ቪሄር እና ኦዳር ሜንቼይ አዋሳኝ ግዛቶች በካምቦዲያ ወታደሮች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። ካምቦዲያ የበቀል እርምጃ እንዳልወሰደች አክላ ተናግራለች።
በሀምሌ ወር ለአምስት ቀናት የቆየውን ገዳይ የሁለቱ ሀገራት ግጭት በተኩስ አቁም ስምምነት ካበቃ በኋላ በጎረቤት ሀገራቱ መካከል አዲስ ግጭት ተቀስቅሷል። በሀምሌው ወር ግጭት ቢያንስ 48 ሰዎች ሲገደሉ 300,000 የሚገመቱት ደግሞ ለጊዜው ተፈናቅለዋል፤ ሁለቱ ጎረቤቶች ሮኬቶች እና የከባድ መሳሪያዎች የተኩስ ልውውጥ አድርገዋል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 12🔥 1🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 611 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺሕ 611 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ገልጿል።
በዚህም በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ ስምንት ዙር በረራ 28 ጨቅላ ህፃናትን ጨምሮ 2 ሺሕ 269 ወንዶች እና 314 ሴቶች ወደሀገራቸው መመለሳቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በሳኡዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ከነበሩና ወደሀገራቸው ከተመለሱ ዜጎች መካከል 73 የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ታውቋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ተናግሯል።
መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 27 ሺሐ 722 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 12👍 2😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
ናይጄሪያ በቤኒን የተቃጣውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ለማክሸፍ ወታደሮቿን ማሰማራቷን አስታወቀች
የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኒዩ የቤኒን ወታደሮች ቡድን ያካሄዱትን መፈንቅለ መንግስት ለማክሸፍ ወደ ጎረቤት ቤኒን ተዋጊ ጄቶች እና የምድር ጦር ሰራዊት ማሰማራታቸውን አረጋግጠዋል። የናይጄሪያ ጦር የቤኒን ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ታሎን መንግስት "አፋጣኝ የናይጄሪያ የአየር ድጋፍን" ጨምሮ ሁለት የእርዳታ ጥያቄዎችን ካቀረበ በኋላ የናይጄሪያ ጦር በቤኒን ጣልቃ ገብቷል ብሏል።
ቲኒዩ በመጀመሪያ የናይጄሪያ ተዋጊ ጄቶች ወደ ቤኒን እንዲገቡ እና "የመፈንቅለ መንግስቱን አቀንቃኞች ከብሄራዊ ቲቪ እና ከተሰባሰቡበት ወታደራዊ ካምፕ ለማባረር የአየር ክልሉን እንዲቆጣጠሩ አዘዋል" ሲል መግለጫው ገልጿል። የቤኒን መንግስት "በህገ-መንግስታዊ ተቋማት ጥበቃ እና የታጠቁ ቡድኖችን በቁጥጥር ስር ለማዋል" ድጋፉን ከጠየቀ በኋላ የናይጄሪያ ጦር እግረኛ ወታደሮችን ልኳል።
የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ቲኒዩ ወታደሮቻቸውን አወድሰው "ጎረቤት ሀገርን ለማረጋጋት" እንደረዱ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።የቤኒን ፕሬዝዳንት ታሎን በብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የጸጥታ ሃይላቸው መንግስታቸውን ለመጣል ያደረገውን ሙከራ በተሳካ ሁኔታ መክሸፉን ተናግረዋል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 13👍 1
00:34
Video unavailableShow in Telegram
ከቴምር ሪል እስቴት ምን ይፈልጋሉ
✅አፓርትመንት ወይንስ ሱቅ
🎉እስከ 35% ልዩ ቅናሽ አዘጋጅተናል።
🏡ከባለ 1 መኝታ እስከ ባለ 3 መኝታ ቤቶችን አሉን።
☑️ አፓርትመንት ከፈለጉ
1ኛ ሳር ቤት ሳይት
2ኛ ፒያሳ ሳይት
3ኛ አያት ሳይት
4ኛ ጋርመንት ሳይት
5ኛ ተክለሃይማኖት ሆስፒታል ፈት ለፊት ሳይት
6ኛ አዋሬ ሳይት አሉን።
☑️ ሱቆችን ከፈለጉ
1ኛ ፒያሳ ሚኒሊክ አደባባይ ፊት ለፊት
2ኛ ጋርመንት ሳይት
3ኛ ገላን ሳይት
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇👇👇
+251937341286
+251714558361
📲👇በ WhatsApp ማግኘት ከፈለጉ
https://wa.me/251937341286
📲Channel: https://t.me/TemerRealEstateSalesAdvisor
📲Telegram : t.me/AbrhamTemerSales
13.72 MB
❤ 13
ያንጎ በኢትዮጵያ መተገበሪያው ላይ አዲስ የደንበኛ ደህንነት መጠበቂያ አካተተ
ያንጎ ራይድ ተሳፋሪዎች በጉዞ ወቅት ሊተገብሯቸው የሚችሉ የደህንነት መጠበቂያ እርምጃዎችን በሞባይል መተግበርያው ውስጥ አካቷል።
መተግበሪያው ተሳፋሪዎች የሚሄዱበትን መንገድ ለሚያምኑት ሰው ማጋራት ወይም የጉዟቸውን ሁኔታ የሚያስረዳ አሁናዊ መረጃ ማጋራት የሚያስችል ነው። የተሻሻለው መተግበርያ እያንዳንዱ ተጓዥ ዝርዝር የደህንነት መስፈርቶች መሟላታቸውን የሚያረጋግጥበት አገግሎግሎት፥ በወቅታዊ የጉዞ ሁኔታ መረጃ ላይ ተመስርቶ ምን አይነት የደህንነት እርምጃዎች መወሰድ እንደሚገቡ መረጃ የሚሰጥ እንዲሁም ስለ ጉዞ ደህንነት አጠቃላይ የደህንነት መረጃዎች የሚሰጥ የማዕከል አገልግሎት የተካተተበት ነው።
አዲሱ የደህንነት ማዕከል የመተግበሪያውን አጠቃቀም ማንበብ፣ የግል መረጃን መሙላት፣ የሚያምኗቸውን ሰዎች ስልክ ቁጥር መሙላት፣ የራስን ፎቶ ማንሳት እና ኢ-ሜል መቀየርን የመሳሰሉ ተሳፋሪዎች መሙላት ያለባቸውን ዝርዝሮች ይይዛል። ከዝርዝሩ ውስጥ የጎደለ ነገር ካለ መተግበሪያው ያልተሞላው ላይ ምልክት በማድረግ ተሳፋሪው እንዲሞላው ይጠይቃል። ተሳፋሪዎች የአጋር አሽከርካሪዎችን ስታንዳርድ፣ አደጋ ከተፈጠረ እንዴት እርዳታ መጠየቅ እንደሚችሉ እና የእያንዳንዱ የደንበኛ ደህንነት መጠበቂያ መረጃን አንድ ቦታ ላይ ያገኛሉ። የመተግበሪያው ዋና ገፅ ላይ በፍጥነት የእርዳታ ጥሪ ማድረግ የሚያስችሉ ቁልፎች ይገኛሉ።
ዋናው ትኩረታችን ደህንነት ነው፣ ጠንካራ የደህንነት እርምጃዎችን መተግበር እና የደህንነት ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ተጠቃሚ እንዲታዩ እና ግልጽ እንዲሆኑ ማድረግም አስፈላጊ ነው ብለን እናምናለን። አሁን ለተሳፋሪዎች ልክ እንዲሆን ተደርጎ በተዘጋጀው አዲሱ የደንበኛ ደህንነት መጠበቂያ ተሳፋሪዎች መኪናውን ከጠሩበት ሰዓት ጀምሮ ጉዞው እስኪጠናቀቅ ድረስ በእያንዳንዱ የጉዞ ደረጃ ላይ የእነሱን ደህንነት ለመጠበቅ ምን እየሰራን እንደሆነ በትክክል ማየት ይችላሉ ሲሉ በኢትዮጵያ የያንጎ ተወካይ ዶ/ር ይቅናለም አበበ ተናግረዋል።
የያንጎ ራይድ አገልግሎት አንዱ ዋናው ትኩረት ደህንነት ነው። አጋር አሽከርካሪዎች እና ተሳፋሪዎች ከጉዟቸው በፊት እና በኋላ እና በጉዟቸው ላይ ሆነው የሚገለገሉባቸው ከ25 በላይ ልዩ የሆኑ የደንበኛ ደህንነት መጠበቂያዎች መካተታቸውን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል። እነዚህም የፍጥነት እና የአነዳድ ቁጥጥር፣ የሚጓዙበትን መንገድ እና የጉዞ መረጃውን ለሚያምኑት ሰው ማጋራት መቻል፣ በአደጋ ጊዜ በፍጥነት ጥሪ ማድረጊያ መንገድ እና የመሳሰሉትን ያጠቃልላሉ።
በሰላማዊ ነጋሲ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 23👍 12👏 4👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
🛑በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ሳር ቤት ሳይት ተለቋል::
በካሽ 100% ለሚከፍል 35% ቅናሽ📍ሳር ቤት ቫቲካን 🎯65/35 አከፍፈል (35%ቅናሽ) 👉2መኝታ 81 ካሬ =5.8 ሚሊዮን ብር 👉2መኝታ 106 ካሬ=7.6 ሚሊዮን ብር 👉3መኝታ 139 ካሬ=9.9 ሚሊዮን ብር 👉3መኝታ 152 ካሬ= 11.8 ሚሊዮን ብር 🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል 👉2መኝታ 81ካሬ ቅድመ ክፍያ(20%) = 1.78 ሚሊዮን ብር 👉2መኝታ 106ካሬ ቅድመ ክፍያ(20%)=2.33ሚሊዮን ብር 👉3መኝታ 139ካሬ ቅድመ ክፍያ(20%)= 3.06 ሚሊዮን ብር 👉3መኝታ 152ካሬ ቅድመ ክፍያ(20%)=3.34 ሚሊዮን ብር #ቀሪውን 80% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት * 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇👇👇 +251937341286 +251714558361 📲👇በ WhatsApp ማግኘት ከፈለጉ https://wa.me/251937341286 📲Channel: https://t.me/TemerRealEstateSalesAdvisor 📲Telegram : t.me/AbrhamTemerSales
❤ 20👎 4
ባለቤቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ የተሰወረውን ግለሠብ ተከታትሎ ለመያዝ የህብረተሠብ ድጋፍ ተጠየቀ
በቢሾፍቱ ከተማ ዲባዬ ክፍለ ከተማ ድሬ ወረዳ ቃጂማ ሠፈራ የተባለ አካባቢ ነዋሪ የሆነው ግለሠብ የሕግ ባለቤቱን በአሰቃቂ ሆኔታ ገድሎ በር ዘግቶባት የተሰወረ እንደሆነ ተገልጿል።
ተፈላጊው ግለሠብ ታሪኩ አበራ አብዲ የተባለ ሲሆን ከሟች ድርቤ ባይሣ ደሬሣ ጋር ትዳር በመመስረት አንድ ሴት ልጅ አፍርተዋል፡፡
ይሑን እንጂ ሕዳር 24 ቀን 2018ዓም በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ዲባዬ ክፍለ ከተማ ድሬ ወረዳ ቃጂማ ሠፈራ የተባለ አካባባ ታሪኩ አበራ አብዲ የተባለው ድርቤ ባይሣ ደሬሣ የተባለችውን ባለቤቱን ና የልጁን እናት በአሠቃቂ ሁኔታ ገሎ በር ዘግቶባት ለግዜው የተሠወረ ቢሆንም ፖሊስ አስፈላጊውን ክትትል እያደረገ ይገኛልሲሉ የቢሾፍቱ ከተማ አቃቢ ሕግ ፅህፈት ቤት የተለያዪ ወንጀሎች ምርመራ ክፍል ኃላፊ አቃቢ ሕግ ሠኝ ነሞምሣ ገልፀዋል።
በመሆኑም ተፈላጊ ታሪኩ አበራ አብዲ የተባለውን ግለሠብ በድብቅ ሊንቀሣቀስ ስለሚችል በአቅራቢያው ባለ የፖሊስ፣የፀጥታና ፍትሕ ፅህፈት ቤቶች መረጃ እንዲሰጥም ትብብር ጠይቀዋል።
በቤዛዊት አራጌ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 25🤬 8💔 6👎 2😭 2
ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ 1628 ተማሪዎች አስመረቀ
ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ ከሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እውቅና ባገኘበት በአውሮፕላን ጥገና ቴክኒሽያንነት ተማሪዎችን ተቀብሎ በማሰልጠን በዛሬው እለት የመጀመሪያውን ባች ያስመረቀ ብቸኛ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሆኗል።
ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ በድህረ ምረቃ፣ በቅድመ ምረቃ፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና እና በሰርተፊኬት ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ለ12ኛ ዙር በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር አስመርቋል።
ኮሌጁ በቅርቡ ናሽናል ዩኒቨርስቲ የመሆን ዓላማ ሰንቆ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል ያሉት የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ሰብስቤ ተፈሪ፣ ከዚህ አዲስና ትልቅ ግብ ጋር በተያያዘ ኮሌጁ የስልጠና ዘርፎችን በማስፋት በጤናው ዘርፍ በቅድመ ምረቃ ደረጃ በነርሲንግና በፋርማሲ ስልጠና መስጠት መጀመሩን አክለው ገልፀዋል።
ከ11 ዓመት በፊት የተቋቋመው ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ የናሽናል ኢንቨስትመንት ግሩፕ አባል እና የናሽናል ኤርዌይስ እህት ኩባንያ ሲሆን በሃገራችን በአቪዬሽን፣ በሆቴልና ቱሪዝም እያደገ የመጣውን የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት ከሟሟላት አኳያ ለዘርፉ እድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።
ኮሌጁ እውቅና ባገኘባቸው በድህረ ምረቃ፣ በቅድመ ምረቃ የመጀመሪያ ዲግሪ መርሃግብሮች፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መርሃግብሮች እንዲሁም ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እና ከአለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) ባገኘው ፍቃድ በአውሮፕላን ጥገና ቴክኒሽያን፣ በበረራ መስተንግዶ ፣በትኬት በርቀት መርሃ ግብር በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ እንዲሁም በቢዝነስ ማኔጅመንት እና ማርኬቲንግ ማኔጅመንት ፕሮግራሞች ስልጠና ይሰጣል።
ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ ከአለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) እና ከዓለም ኮሜርሻል ሜኔጅመንት (ICM) ባገኘው እውቅና መሰረት በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸው ስልጠናዎች እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፣ በሚሰጠው የስልጠና ጥራትም ከ IATA ICM የ2009፣ 2010 እና የ2011 ለ3 ተከታታይ አመታት የአፍሪካ ምርጡ የስልጠና ማዕከል የሚል ሽልማት ማግኘቱን ብስራት ሰምቷል።
ኮሌጁ ለ12ኛ ጊዜ በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም በኢንተርናሽናል ትሬድ እና ኢኮኖሚክስ እንዲሁም ሎጅስቲክስ እና ሰፕላይ ማኔጅመንት 130 ተማሪዎችን አስመርቋል። በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና በደረጃ 4 በአካውንቲንግና ፋይናንስ፣ ፍሮንት ኦፊስ፣ ሃርድዌርና ኔትወርክ ሰርቪስ፣ ማርኬቲንግና ሴልስ ማኔጅመንት እንዲሁም በነርሲንግ እና ፋርማሲ 1035 ተማሪዎችን አስመርቋል።
በሰርተፊኬት ስልጠና በኤርክራፍትና ሜንቴናንስ ቴክኒሻን፣ ኤርላይን ካቢን ክሪው፣ ፍላይት ኦፕሬሽን ኦፊሰር እና በቲኬቲንግና ሪዘርቬሽን ያሰለጠናቸው 370 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን በአጠቃላይ 1628 ተማሪዎች አስመርቋል።
በሰላማዊ ነጋሲ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 21👍 3
ለም ሆቴል አካባቢ ተደራራቢ አውቶቡስ የቀላል ባቡር የኤሌክትሪክ ገመድ በመበጠሱ አገልግሎት አቆመ!
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት መስመር ላይ የሚገኘው ከሃያት ወደ ጦር ኃይሎች የሚወስደው መስመር አገልግሎት መገናኛ አካባቢ ለም ሆቴል መሻገሪያ ላይ በተፈጠረ ብልሽት ምክንያት መቋረጡ ታውቋል።
ብልሹቱ የተከሰተው ለም ሆቴል አቅራቢያ በቅርቡ ለመተላለፊያነት በተሰራ መንገድ ላይ ሲሆን፣ በተለይም ተደራራቢ የአንበሳ አውቶቡስ መንገዱን ሲያቋርጥ የቀላል ባቡሩን ማስተላለፊያ የኤሌክትሪክ ገመድ በመበጠሱ አደጋው እንደደረሰ ተገልጿል።
በዚህ አደጋ ምክንያት የባቡር አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ፣ በወቅቱ በመስመሩ ላይ የነበረው ባቡርም ተሳፋሪዎችን ለማውረድ መገደዱን ካፒታል ተመልክቷል።
መረጃዎች እንደሚያሳዩት ይህን መሰል የባቡር መሠረተ ልማት ብልሽት (የኤሌክትሪክ ገመድ መበጠስ) ከዚህ በፊት አጋጥሞ አያውቅም።
የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የኤሌክትሪክ ገመዱን በአስቸኳይ ለመጠገን ጥረት እያደረገ ነው። የሃያት-ጦር ኃይሎች መስመር ተጠቃሚዎችም አገልግሎቱ ወደ መደበኛ ሥራው እስኪመለስ ድረስ የትራንስፖርት አማራጮችን እንዲጠቀሙ ተጠይቀዋል።
ባለሥልጣናት በአሁኑ ወቅት የደረሰውን ጉዳት መጠን በመገምገም ላይ ሲሆኑ፣ አገልግሎቱ በፍጥነት ወደ መደበኛ ሥራው እንዲመለስ የሚያስችላቸውን ጥረት እያደረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
Via Capital
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 20😁 3
