ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
رفتن به کانال در Telegram
The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

44 133
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-747 روز
-34830 روز
آرشیو پست ها
በደቡብ ወሎ የግሸን ደብረ ከርቤ እና የመዉሊድ በዓል የቱሪዝም ገቢን ከፍ አድርገዉታል ተባለ
ባለፉት ሶስት ወራት ከቱሪዝም ዘርፍ የተገኘዉ ገቢም ይሁን የቱሪስቶች ቁጥር ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን የደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታውቋል።
ለዚህም ከፍተኛ ጭማሪ መስከረም 21 ቀን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናን የታደሙበት የግሸን ደብረ ከርቤ በዓልና በርካታ የሀገር ዉስጥና የዉጪ ሀገር ቱሪስቶች በታደሙበት ለ3 ተከታታይ ቀናት በድምቀት የተከበረዉ የመዉሊድ በዓል ከፍተኛዉን ድርሻ እንደሚይዙ የደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም ልማት ቡድን መሪ አቶ ይድነቃቸዉ ጌታነህ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ባለፉት 3 ወራት ከ1.9ሚሊዮን በላይ ቱሪስቶች በዞኑ ዉስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን መጎብኘታቸዉንና ከዘርፋም ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን አቶ ይድነቃቸዉ ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ለቱሪዝም ዘርፍ ዋናና አስፈላጊዉ ነገር የመሠረተ ልማቶች መሟላት መሆኑን የገለፁት ቡድን መሪዉ በዞኑ ዉስጥ የሚገኙ የመንገድ ፣የዉሃ ፣የስልክ ፣የመብራት እና ሌሎችንም መሰረተ ልማቶች ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመቀናጀት የማሟላት ስራ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።
በቋሚነት በግሸን ደብረ ከርቤ እየተሰራ ካለዉ 17 ኪሎሜትር የአስፋልት መንገድ በተጨማሪ ክብረ በዓላትን ታሳቢ በማድረግ በተለያዩ አከባቢዎች መሰረት ልማቶችን የማሟላት ስራ ይሠራል ተብሏል።
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 16😁 14👍 3👎 2
በደቡብ ወሎ የግሸን ደብረ ከርቤ እና የመዉሊድ በዓል የቱሪዝም ገቢን ከፍ አድርገዉታል ተባለ
ባለፉት ሶስት ወራት ከቱሪዝም ዘርፍ የተገኘዉ ገቢም ይሁን የቱሪስቶች ቁጥር ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን የደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታውቋል።
ለዚህም ከፍተኛ ጭማሪ መስከረም 21 ቀን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናን የታደሙበት የግሸን ደብረ ከርቤ በዓልና በርካታ የሀገር ዉስጥና የዉጪ ሀገር ቱሪስቶች በታደሙበት ለ3 ተከታታይ ቀናት በድምቀት የተከበረዉ የመዉሊድ በዓል ከፍተኛዉን ድርሻ እንደሚይዙ የደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም ልማት ቡድን መሪ አቶ ይድነቃቸዉ ጌታነህ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ባለፉት 3 ወራት ከ1.9ሚሊዮን በላይ ቱሪስቶች በዞኑ ዉስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን መጎብኘታቸዉንና ከዘርፋም ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን አቶ ይድነቃቸዉ ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ለቱሪዝም ዘርፍ ዋናና አስፈላጊዉ ነገር የመሠረተ ልማቶች መሟላት መሆኑን የገለፁት ቡድን መሪዉ በዞኑ ዉስጥ የሚገኙ የመንገድ ፣የዉሃ ፣የስልክ ፣የመብራት እና ሌሎችንም መሰረተ ልማቶች ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመቀናጀት የማሟላት ስራ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።
በቋሚነት በግሸን ደብረ ከርቤ እየተሰራ ካለዉ 17 ኪሎሜትር የአስፋልት መንገድ በተጨማሪ ክብረ በዓላትን ታሳቢ በማድረግ በተለያዩ አከባቢዎች መሰረት ልማቶችን የማሟላት ስራ ይሠራል ተብሏል።
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
የህንድ አየር መንገድ ባጋጠመዉ የሰራተኞች እጥረት ከ300 በላይ በረራዎች ተሰረዙ
የሕንድ ትልቁ አየር መንገድ ኢንዲጎ ከፍተኛ ቀውስ ገጥሞታል፣ ከማክሰኞ ጀምሮ ከ300 በላይ በረራዎች ተሰርዘዋል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ መንገደኞችም በአገር አቀፍ ደረጃ በረራ እንዲስተጓጎልባቸዉ ሆኗል።ዴሊ፣ ሙምባይ፣ ሃይደራባድ እና ቤንጋሉሩ በህንድ ውስጥ ከፍተኛ የመንገደኞች መጨናነቅ በሚታይባቸዉ አየር ማረፊያዎች የከፋ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
አየር መንገዱ ለተፈጠረው መስተጓጎል ቴክኒካል ብልሽቶችን፣ የአየር ሁኔታን እና አዲስ የሰራተኞች ዝርዝር ህጎችን ተጠያቂ አድርጓል። አየር መንገዱ ከ60 በመቶ በላይ የሀገር ውስጥ ገበያ ድርሻ ያለዉ ሲሆን ዋና ዋና ሜትሮ ከተሞችን እና ትናንሽ ከተሞችን ያገናኛል።ኢንዲጎ ችግሩን ለማረጋጋት እስከ አርብ ድረስ ባለው መርሃ ግብሩ ላይ “ማስተካከያዎችን” አድርጓል።
እንደ ኢንዲያን ታይምስ ዘገባ ሐሙስ ጠዋት ብቻ በዴሊ 33 በረራዎች ኢንዲጎ መሰረዙን ያስታወቀ ሲሆን በቦምቤ ወይም ሙምባይ 85 እንዲሁም 73 በረራዎች በቤንጋሉሩ መሰረዙን ዘግቧል።የሕንድ አቪዬሽን ተቆጣጣሪ የተቋረጠውን ችግር በማጣራት ላይ ሲሆን አየር መንገዱ የተቋረጠውን እና የመዘግየቱን ምክንያት ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቋል።ከኖቬምበር 1 ጀምሮ ኢንዲጎ የበረራ ሰአታትን የሚገድብ እና ተጨማሪ እረፍት በሚሰጠዉ በአዲሱ የበረራ ህግ መሰረት የአብራሪ እና የበረራ መስተንግዶ ሰራተኞች እጥረት አጋጥሞታል ሲሉ የህንድ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች አመላክተዋል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 18🤯 1😱 1
የህንድ አየር መንገድ ባጋጠመዉ የሰራተኞች እጥረት ከ300 በላይ በረራዎች ተሰረዙ
የሕንድ ትልቁ አየር መንገድ ኢንዲጎ ከፍተኛ ቀውስ ገጥሞታል፣ ከማክሰኞ ጀምሮ ከ300 በላይ በረራዎች ተሰርዘዋል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ መንገደኞችም በአገር አቀፍ ደረጃ በረራ እንዲስተጓጎልባቸዉ ሆኗል።ዴሊ፣ ሙምባይ፣ ሃይደራባድ እና ቤንጋሉሩ በህንድ ውስጥ ከፍተኛ የመንገደኞች መጨናነቅ በሚታይባቸዉ አየር ማረፊያዎች የከፋ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
አየር መንገዱ ለተፈጠረው መስተጓጎል ቴክኒካል ብልሽቶችን፣ የአየር ሁኔታን እና አዲስ የሰራተኞች ዝርዝር ህጎችን ተጠያቂ አድርጓል። አየር መንገዱ ከ60 በመቶ በላይ የሀገር ውስጥ ገበያ ድርሻ ያለዉ ሲሆን ዋና ዋና ሜትሮ ከተሞችን እና ትናንሽ ከተሞችን ያገናኛል።ኢንዲጎ ችግሩን ለማረጋጋት እስከ አርብ ድረስ ባለው መርሃ ግብሩ ላይ “ማስተካከያዎችን” አድርጓል።
እንደ ኢንዲያን ታይምስ ዘገባ ሐሙስ ጠዋት ብቻ በዴሊ 33 በረራዎች ኢንዲጎ መሰረዙን ያስታወቀ ሲሆን በቦምቤ ወይም ሙምባይ 85 እንዲሁም 73 በረራዎች በቤንጋሉሩ መሰረዙን ዘግቧል።የሕንድ አቪዬሽን ተቆጣጣሪ የተቋረጠውን ችግር በማጣራት ላይ ሲሆን አየር መንገዱ የተቋረጠውን እና የመዘግየቱን ምክንያት ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቋል።ከኖቬምበር 1 ጀምሮ ኢንዲጎ የበረራ ሰአታትን የሚገድብ እና ተጨማሪ እረፍት በሚሰጠዉ በአዲሱ የበረራ ህግ መሰረት የአብራሪ እና የበረራ መስተንግዶ ሰራተኞች እጥረት አጋጥሞታል ሲሉ የህንድ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች አመላክተዋል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
ታይሰን በቁጥጥር ስር ዋለ!!
በተለያዩ የዉንብድና ወንጀሎች ሲፈለግ የነበረዉ ተጠርጣሪ ታይሰን በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የተጠርጣሪዉ መያዝ የህግ የበላይነትን የሚያረጋግጥ እና በክልሉ ወንጀል ፈፅሞ መሰወር እንዳማይቻል ማሳያ መሆኑም ተገልጿል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ኮሚሽነር ታከለ ታደሰ እንደገለፁት ተጠርጣሪው አገኘሁ አሰፋ ኃይሌ (ታይሰን) የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈፀም በፖሊስ ሲፈለግ እንደነበር ገልፀዋል።
ተጠርጣሪዉ በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ዬቢጦ ቀበሌ በተለምዶ 460 ተብሎ በሚጠራበት መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም በስፍራው ፍልጥ ለመጫን የገቡትን አሽከርካሪና ረዳቱን ያለእኔ እዉቅና ገብታችሁ አስጭናችኃል በሚል በታጠቀዉ ህገ-ወጥ ሽጉጥ ረዳቱን በቀኝ ደረቱ ላይ አንድ ጊዜ ተኩሶ በመምታት ጉዳት አድርሶበት ከአከባቢዉ መሰወሩን ተናግረዋል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ከፌደራል ፖሊስ፣ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በተደረገዉ ክትትል በአዲስ አበባ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስረድተዋል።
ተጠርጣሪዉ ከዚህ ቀደም በነብስ ግድያ፣በዉንብድና ወንጀሎች ተከሶ 16 አመት ተፈርዶበት እንደነበር ፖሊስ በወንጀል ሪከርድ መዝገቡ ላይ ተመዝግቦ እንደሚገኝ ጨምረዉ አስረድተዋል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በግለሰቡ ላይ የጀመረዉን የምርመራ ዉጤት እንዲያገኝ ቀደም ሲል በአካባቢው የዉንብድ፣የነብስ ግድያና ሌሎች ወንጀሎችን ይፈፅም እንደነበር እና ህብረተሰቡ ፖሊስ ዘንድ ቀርቦ ማስረጃ እንዲሆንጠይቀዉ ምርመራዉ እንደተጠናቀቀ ለዐቃቤ ህግ በመላክ ክስ እንደሚመሠረትበት ምክትል ኮሚሽነር ታከለ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል።
#ዳጉ_ጆርናል
🤣 26❤ 11
በሌለበት ውሳኔ የተላለፈበትና ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ወደ ዩጋንዳ ሲልክ የነበረ ፍርደኛ በቁጥጥር ስር ዋለ
በቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ አስተዳደር ደሎ ቀበሌ ቤት በመከራየት በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን ከተለያዩ አካባቢዎች በማሰባሰብ ወደ ዩጋንዳ የሚልክ ግለሠብ በሌለበት የፍርድ ውሳኔ የተላለፈበት የነበረ ሲሆን ግለሰቡን ፖሊስ ተከታትሎ በቁጥጥር ስር በማዋል ለማረሚያ ቤቶች ማስረከቡን የቦረና ዞን ፖሊስ አስታውቋል።
የቦረና ዞን የፖሊስ ዋና መምርያ የወንጀል ምርመራ ክፍል መግለጫ እንዳመለከተው፣አንደኛ ተከሳሽ ጐዳ ቦሩ የተባለ ግለሠብ በሕገወጥ መንገድ ሰው የማዘዋወር እና ድንበር የማሻገር ወንጀል ተከሶ በፍርድ ቤት የዋስትና መብት ከተጠበቀለት በኃላ ተሸሽጎ የሕግ ውሳኔ በሌለበት ተሰጥቷል። ተከሳሽ ከተለያዩ አካባቢዎች በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን በማሰባሰብ ቤት በመከራየት ፣ለወራት በማስቀመጥ ወደ ዩጋንዳ ሀገር እንደሚልኩ በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡የካቲት 26 ቀን 2017ዓ/ም ከቀኑ አስራ አንድ ሰዓት ላይ ተከሳሽ ትራንስፖርት በማዘጋጀት ከቡሌ ሆራ ከተማ በህገወጥ መንገድ ወደ ያቤሎ ከተማ ደሎ ከተማ በማምጣት ወደ ተከራየው ቤት ለአንድ ወራት ካስቀመጠ በኋላ ወደ ዩጋንዳ አገር በሕገወጥ መንገድ ለመላክ ሲዘጋጅ በቁጥጥር ስር ዉሏል።
ፖሊስ በግለሰቡ ላይ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ የምርመራ መዝገቡን በበቂ ማስረጃ በማጠናከር ለአቃቢ ሕግ ልኳል፡፡ አቃቢ ሕግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር እና ድንበር የማሻገር ወንጀል ክስ የመሠረተ ሲሆን ክሱን ሲከታተል የቆየው የቦረና ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 25 ቀን 2017ዓም በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሳሽ ጐዳና ቦሩ በሌለበት የአስራ ስድስት አመት ከስድስት ወር እስራት እና ሀምሳ ሺህ ብር መቀጮ ወስኖበታል።
ተከሳሹ ለጊዜዎ በዋስ ከተለቀቀ በኃላ ተሰውሮ በሌለበት ውሳኔ የተላለፈበት ሲሆን ፖሊስ ተከሳሹን ተከታትሎ ለማረሚያ ቤት እንዲያስረክብ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ፖሊስ ህዳር 21 ቀን ተሰውሮ የነበረውን ተከሳሽ ከተሸሸገበት በክትትል በመያዝ ለማረሚያ ቤት ማስረከቡን የምርመራ ክፍሉ መግለጫ አመላክቷል።
በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 15👏 1
ፑቲን ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ለመምከር ወደ ኒዉ ዴሊ አቀኑ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በህንድ የሁለት ቀናት ጉብኝት እየጀመሩ ሲሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር እና ሁለቱም ሀገራት በሚያካሂዱት አመታዊ ጉባኤ ላይ ይመክራሉ፡፡በጉብኝቱ ወቅት ዴሊ እና ሞስኮ በርካታ ስምምነቶችን ይፈራረማሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም ዩናይትድ ስቴትስ ህንድ የሩሲያ ዘይት መግዛቷን እንድታቆም ግፊት ከጨመረች ከወራት በኋላ ነው።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ጦርነቱን ለማቆም ከሩሲያ እና ከዩክሬን ጋር ተከታታይ ውይይት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ህንድ እና ሩሲያ ለበርካታ አሥርተ ዓመታት የቅርብ ወዳጆች ሲሆኑ ፑቲን እና ሞዲ ጠበቅ ያለ ግንኙነት አላቸው።ህንድ በአለም ሶስተኛዋ ከፍተኛ የድፍድፍ ነዳጅ ዘይት ተጠቃሚ ስትሆን ከሩሲያ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ነዳጅ ስትገዛ ቆይታለች። ሩሲያ ዩክሬንን ከመውረሩ በፊት ህንድ ከሩሲያ የምታስገባው ነዳጅ ዘይት 2.5 በመቶ ብቻ ድርሻ ነበረዉ፡፡
በሩሲያ ምርት ላይ በአውሮፓ ገበያ ላይ ማዕቀብ መጣሉን ተከትሎ የሩሲያን ነዳጅ በቀነሰ ዋጋ ህንድ በመሸመት በአጠቃላይ ከሩሲያ የምትገዛዉን ነዳጅ ከ2.5 በመቶ ወደ 35 በመቶ ከፍ ብሏል።ህንድ በነቀሰ ዋጋ ምርቱን በማግኘቷ ደስተኛ የነበረች ቢሆንም ከሞስኮ ነዳጅ በመሸመቷ ከአሜሪካ ከፍተኛ ታሪፍ ተጥሎባታል፡፡በሌላ በኩል ከፑቲን ጉብኝት በፊት ህንድ ዘመናዊ የሆኑ የሩሲያ ተዋጊ ጄቶች እና የአየር መከላከያ ዘዴዎችን ለመግዛት ማቀዷን ዘገባዎች ጠቁመዋል።
በሠራተኛ እጥረት የተጠቃችው ሩሲያ ህንድን እንደ ጠቃሚ የሰለጠኑ ሠራተኞች ምንጭ ታያለች።ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት እሷን ለማግለል ምዕራባውያን ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካ ለማሳየት ይህንን ጉብኝት ትጠቀምበታለች፡፡
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 9
ማስታገሻ በሚል ማንኛውም መድኃኒት ከሃኪም ትዕዛዝ ውጪ ከመውሰድ ህብረተሰቡ ሊጠነቀቅ እንደሚገባ ተነገረ
መድሃኃኒቶችን ያለ ሀኪም ትዕዛዝ መጠቀም እንዲሁም ከታዘዘው መጠን በላይ መውሰድ ለጸረ ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድ እንደሚያስከትል በወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የላብራቶሪ ዳይሬክተር እና የጸረ ተህዋሲያን መላመድ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት ባህረዲን ዳሪ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድ ምክንያት ታማሚዎች ታክመው መሄድ ከሚገባቸው በላይ በጤና ተቋማት እንዲቆዩ ላልተፈለገ ወጪ እንዲሁም ለከፋ የጤና ችግር ተጋላጭ እንደሚያደርጉ እና በሽታ የመከላከል አቅም እንደሚቀንሱ ተጠቁሟል ።
የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች ከህክምና ባለሙያ ትዕዛዝ ውጪ መውሰድ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንደሚያስከትል ተጠቁሟል። ሰዎች ለራስ ምታት እና ለተለያዩ ህመሞች ከፓራስታሞል ጀምሮ ዳይክሎፌን እያሉ የሚወስዷቸው መድሃኒቶች ደረጃቸው ከፍ እያለ በሄደ ቁጥር የሚያስከትለው ችግርም እንደሚጨምር ተጠቁሟል።በተጨማሪም በንጽህና ጉድለት የጸረህዋሲን ጀርሞች መላመድ ከታማሚ ወደ ታማሚ ስለሚተላለፉ ንጸህናን መጠበቅ እንደሚገባ ተነግሯል።
በአለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ በሰዎች ፣በአካባቢ እንዲሁም በእንስሳት ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳትን የሚያስከትል ሲሆን ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር እንዲሁም ሌሎች ጉዳቶችንም ለመቆጣጠር የሚመለከተው አካል ሁሉ በትኩረት ለለሰራበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑ ተጠቁሟል።ማንኛውም ሰው ህመም ስለተሰማው ብቻ ማስታገሻ በሚል ማንኛውንም አይነት መድሃኒቶች መውሰድ እንደሌለበት እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሃገራት ላይ ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት እንደሚያደርስ በወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የላብራቶሪ ዳይሬክተር የጸረ ተህዋሲያን መላመድ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት ባህረዲን ዳሪ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በወራቤ ሆስፒታል በሽታወን የመከላከል ስራ በትኩረት በኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 10👌 2👍 1
በያንጎ የተዘጋጀው የመረቆች ውድድር አሸናፊዎች ይፋ ሆኑ
የዛሬው “የመረቆቹ ውድድር ” ሽልማት ታታሪ አሽከርካሪዎችን ለማክበር፣ ቤተሰባዊነትን ለማጠንከር፣ በበለጠ የላቀ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመሰጥት ለማበረታት የተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል።
መረቆቹ ውድድር ከኖቬምበር 1 እሰከ 30 ድረስ ለነበሩ እያንዳንዱ ጉዞ ዕጣ በማውጣት ከ1-10 ለወጡት በደረጃቸው መሰረት ሽልማታቸውን ወስደዋል።
በያንጎ አዘጋጅነት በያንጎ በመረቅ ሲካሄድ የነበረው የሾፌሮች ውድድር አሸናፊዎቹ በዛሬው ዕለት መለየታቸውን የመረቅ ቴክ ኦፕሬሽን ማናጀር ማህደር ዳዊት ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያንጎ ስራ ከጀመረ ሁለት ዓመት የተቆጠረው ሲሆን በዛሬው ዕለት የያንጎ ቋሚ አሽከርካሪዎችን ሽልማት አበርክቶላቸዋል።
የያንጎ ባለብዙ-ተግባር መተግበሪያ በአፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ፣ በአውሮፓ እና በመካከለኛው ምስራቅ ባሉ ከ25 በላይ አገሮች ውስጥ በርካታ የዲጂታል ከተማ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ብስራት ሰምቷል። የያንጎ ብዙ ባለ ብዙ ቋንቋ መተግበሪያ በአንድሮይድ እና አይ.ኦ.ኤስ (iOS) ላይ በነጻ ይገኛል።
እስካሁን በያንጎ መተግበሪያ ከፍተኛ መጠን የሰራው አንድ አሽከርካሪ በወር 183 ሺህ ብር መሆኑ የመረቅ ቴክ ኦፕሬሽን ማናጀር ማህደር ዳዊት ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 11👎 1🔥 1🙏 1👌 1
Photo unavailableShow in Telegram
አውስትራሊያ ለዩክሬን የ62ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ ዕርዳታ ልትሰጥ ነዉ
አውስትራሊያ ለዩክሬን የ62 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ ወታደራዊ ዕርዳታ ማዘጋጀቷን አስታውቃለች፤ በተጨማሪም በሩሲያ ላይ ማዕቀብ እንደምትጥል ይፋ አድረርገዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር እና የመከላከያ ሚኒስትር ሪቻርድ ማርልስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ በጋራ በሰጡት መግለጫ ፓኬጁ ለዩክሬን አስፈላጊ ወታደራዊ መሣሪያዎችን ለማቅረብ በኔቶ ተነሳሽነት ቅድሚያ ለተሰጠው የዩክሬን መዋጮን ይህ ድጋፍ ያካትታል ።
"አውስትራሊያ ለዩክሬን የምታደርገውን ድጋፍ የማይናወጥ ነው። እነዚህ ቃላቶች ዩክሬን ከሩሲያ ህገወጥ እና ኢ-ሞራላዊ ወረራ ለመከላከል በምታደርገው ጥረት ተጨባጭ ለውጥ ያመጣሉ" ሲሉ ማርልስ ተናግረዋል።በተጨማሪም ካንቤራ ከሩሲያ ጋር የተገናኙ 45 ተጨማሪ መርከቦች ላይ ማዕቀብ የጣለች ሲሆን በዚህም ማዕቀቡ የተጣለባቸውን መርከቦች አጠቃላይ ቁጥር ወደ 200 አድርሷል ።
ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ የአውስትራሊያ አጠቃላይ ድጋፍ ለዩክሬን ከ1.12 ቢሊዮን በላይ በወታደራዊ ዕርዳታ ተሰጥቷል።በሌላ በኩል እሮብ እለት ጃፓን ለዩክሬን 25.7 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ በመስጠት ሀገሪቱን የተቀበሩ ፈንጂዎች ለማጽዳት እንደምትረዳ አስታውቃለች። የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በዩክሬን የጃፓን አምባሳደር ማሳሺ ናካጎሜ እና የዩክሬን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ኢጆር ክላይመንኮ የእርዳታ ፓኬጁን በኪየቭ ተፈራርመዋል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 6👎 3🕊 1
ዶሮ ወጥ አልሰራሽልኝም በማለት ባለቤታቸውን በሶስት ጥይት ተኩሰው የገደሉት የ75 ዓመት አዛውንት በእስራት ተቀጡ
በሰሜን ሸዋ ዞን ፍታል ከተማ 01ቀበሌ ነዋሪ እና የልጆች አባት የሆኑት አቶ ቦጋለ ሃይሉ የሰባ አምስት ዓመት አዛውንት ናቸው።አቶ ቦጋለ ከወይዘሮ አባይቱ ከበደ ጋር ትዳር መስርተው ይኖሩ እንደነበረ የሰሜን ሸዋ ዞን ዓቃቢ ህግ ፅ/ቤት የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ አቃቢ ህግ ዳዊት ንጉሴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
አቶ ቦጋለ ሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከገበያ አንድ ዶሮ ገዝተው ይመጡና ባለቤታቸውን ዶሮ አምሮኛል ስሪልኝ የሚል ትዕዛዝ በመስጠት ምሽት አስራ አንድ ሰዓት ላይ ከገበያ የገዙትን ዶሮ ያስረክባሉ።ወይዘሮ አባይቱ የባለቤታቸውን ትዕዛዝ በመቃወም ዶሮ እኮ ሲሰራ ብዙ ግብዓቶች ይፈልጋል ያንን ሳታሟላ ዶሮ አምሮኛል ስሪልኝ አይባልም፤ በማለት ሲመልሱ በመካከላቸው አለመግባባት ተፈጥሮ ወደ ፀብ ያመራል።
በዚህ ጊዜ ድምፃቸው ተሰምቶ የማያቀው ባል እና ሚስት በተሰማው ጩኸት ጎረቤት መሃል ገብቶ ያገላግላል። አቶ ቦጋለ ሃይሉ በቁጥር ኤ ኤል-34021 የተመዘገበ ማካሮፍ ሽጉጥ በመያዝ ከቤት በመውጣት መጠጥ ቀማምሰው ከአንድ ሰዓት በኋላ ሲመለሱ ዶሮ ሳይታረድ ስለ ጠበቃቸው በንዴት ወተት እያለቡ ያሉትን ባለቤታቸው አባይቱ ከበደን አከታትለው በሶስት ጥይት በመምታት ጉዳት አድርሰው ሊያመልጡ ሲሞክሩ በፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ተጎጂዋ ወደ ፍታል ጤና ጣቢያ ተልከው በህክምና ላይ እያሉ ህይወታቸው እንዳለፈ አቃቢ ህግ ዳንኤል ለብስራት ሬዲዮ ገልጸዋል ። ፖሊስም የሟች አስክሬን ለምርመራ ወደ አቤት ሆስፒታል በመላክ ካስመረመረ በኋላ ባገኘው ማስረጃ ሟች የተለያየ ሶስት የሰውነት ክፍሎቿ መመታቱ አረጋግጧል።ፖሊስም የምርመራ መዝገቡን በተገቢው ማስረጃ አጠናክሮ ለአቃቢ ህግ የላከ ሲሆን አቃቢ ህግም ከፖሊስ የተላከው የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ መስርቷል፡፡ ክሱን ሲከታተል የቆየው የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ቦጋለ ሃይሉ በአስራ ዘጠኝ ዓመት እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን አቃቢ ህግ ዳንኤል ንጉሴ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
💔 26❤ 12😁 10🤔 7👍 1😢 1
ጀርመናዉያና የፈረንሳይ ዜጎች ከሩሲያ ጋር ከፍተኛ የጦርነት ስጋት ይኖራል ብለዉ እንደሚያስቡ አንድ የዳሰሳ ጥናት አመላከተ
በጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ኔዘርላንድስ እና በሌሎች በርካታ የአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት የሚኖሩ ዜጎች ሩሲያ ከሀገራቸው ጋር ልትዋጋ የምትችልበት ዕድል ከፍተኛ እንደሆነ ያምናሉ ሲል አንድ ጥናት አረጋግጧል።በጥናቱ የተካሄደው በመላው ዘጠኝ የአውሮፓ ሀገራት ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆኑት መላሾች የጦርነት አደጋዉ “ከፍተኛ” ወይም “በጣም ከፍተኛ” ነው ሲሉ መናገራቸዉን የፈረንሳይ የሕዝብ አስተያየት ሰጪ ክላስተር 17 ጥናት ሐሙስ ዕለት ይፋ አድርጓል።
ፖላንድ ከሩሲያ ጋር ድንበር የምትጋራ ሲሆን ቀደም ሲል የሶቪየት ኅብረት አካል የነበረች ሲሆን እስካሁን ድረስ የጦርነት ጭንቀት ዉስጥ መሆናቸዉን 77 በመቶ የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ከፍተኛ የግጭት ስጋት ታይተዋል ሲል ጥናቱ አመልክቷል።በቤልጂየም እና በኔዘርላንድስ፣ 59 በመቶ የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ከፍተኛ የጦርነት ስጋት አለ ሲሉ በግምት ግማሽ ያህሉ ጀርመናውያን፣ የፈረንሣይ እና ስፓኒሽ ዜጎች ተመሳሳይ ምላሽ ሰጥተዋል።
ጣሊያኖች የጦርነት ስጋት የመኖር ዕድሉ አነስተኛ ነዉ ሲሉ 34 በመቶ ምላሽ ሰጪዎች የተናገሩ ሲሆን ፖርቱጋላውያን እና ክሮኤሽያውያን በተመሳሳይ ጦርነት የመቀስቀስ እድሉ አነስተኛ ነዉ።ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ጥናቱ ከተካሄደባቸው አውሮፓውያን ግማሽ ያህሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን እንደ “አውሮፓ ጠላት” ይመለከቷቸዋል በሚል በጥናቱ ተመላክቷል፡፡
ፈረንሳይበ1996 የተቋረጠውን የውትድርና አገልግሎት ከቀጣዩ አመት ጀምሮ በበጎ ፈቃደኝነት እንደምትጀምር ባለፈው ሳምንት አስታውቃለች።የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እርምጃውን ለሩሲያ ጥቃት ምላሽ እንደሆነ በግልፅ ገልፀው ሞስኮ ማንኛውንም "የድክመት ምልክት" ለመጠቀም እንደምትፈልግ አስጠንቅቀዋል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 6👍 1🤔 1
