ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
رفتن به کانال در Telegram
The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

44 133
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-22730 روز
آرشیو پست ها
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን የትራምፕ የዩክሬን የሰላም እቅድ መሻሻል አለበት ሲሉ ተናገሩ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሰላም እቅድ በዩክሬን እና በአውሮፓ ተቀባይነት እንዲኖረው ማሻሻያ ያስፈልገዋል ሲሉ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ተናግረዋል ።ባለፈው ሳምንት የቀረበው ባለ 28 ነጥብ የዩናይትድ ስቴትስ የሰላም ሀሳብ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ፣ በኪዬቭ እና በአውሮፓ ውስጥ ብዙዎች የትራምፕ አስተዳደር ዩክሬንን ወደ ሞስኮ በጣም ያጋደለውን ስምምነት እንድትፈርም ሊገፋፋ ይችላል የሚል አዲስ ስጋት ፈጥሯል።
ማክሮን "በትክክለኛው አቅጣጫ የሚሄድ ተነሳሽነት ነው ወደ ሰላም ከሆነ ይህ እቅድ መወያየት፣ መደራደር፣ መሻሻል ይገባቸዋል" ብለዋል፡፡ "እኛ ሰላም እንፈልጋለን ነገር ግን ሰላምን ውጤታማ በሆነ መንገድ መግለጽ አንፈልግም" ሲሉ አክለዋል፡፡ዩክሬናውያን ብቻ ምን ዓይነት የግዛት ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ እንደሆኑ ሊወስኑ እንደሚችሉም አክለዋል።
ከሩሲያ ጋር ሰላም በሚፈጠርበት ጊዜ የዩክሬን የመጀመሪያ የመከላከያ መስመር የራሷን ጦር እንደገና ማፍራት ነው ፣ እናም በዚህ ዙሪጣ ምንም ገደብ ሊኖር አይችልም ሲሉ ማክሮን ተናግረዋ ። እንዲሁም የታገዱ የሩሲያ ንብረቶች በአውሮፓ ውስጥ እንዳሉ እና አውሮፓ ብቻ በንብረቱ ላይ ምን ማድረግ እንዳለበት መወሰን ይችላል ብለዋል ።የዩናይትድ ስቴትስ የሰላም እቅድ በዩክሬን ጦር ኃይል መጠን ላይ ገደብ ያስቀምጣል እንዲሁም ለዋሽንግተን የታገዱ የሩሲያ ንብረቶችን የተወሰነ ቁጥጥር መብትን ይሰጣል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 12👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኦርቢት ኢኖቬሽን ሃብ ከ1ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠሩን አስታወቀ
ኦርቢት ኢኖቮሽን ሃብ በተለያዩ የቢዝነስ ስራዎች ለወጣቶች የስራ እድል እየፈጠረ እንደሚገኝ ተገለጸ።
ኦርቢት ኢኖቬሽን ሃብ የተለያዩ የጤና እና የኢንተርፕረነር ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። በዚህም የኢንኩቤሽን ድጋፍ፣ ዲጂታል ማርኬቲንግ የመሳሰሉ ስራዎችን በተለየ መልኩ ከተለያዩ ተቋማት እና ግለሰቦች ጋር እየሰራ እንደሚገኝ የኦርቢት ኢኖቬሽን ሀብ ማናጀር የሆኑት አቶ ዳዊት ተሾመ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ኦርቢት ኢኖቬሽን ሀብ ስራ ከጀመረ አራት ዓመት በላይ የሆነው ሲሆን በዲጃታላይዝ መልኩ ለሚሰሩ የጤና ተቋማት ጋር እንዲሁም ደግሞ ስራ ፈጣሪ ወጣቶችን ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል።
ስራ ፈጣሪዎች ላይ የሚገጥሙትን የመረጃ ፣የገንዘብ፣የገበያ ትስስር ችግሮችን በመቅረፍ ከስልጠና ጀምሮ የፈጠራ ስራዎቻቸው ገቢ ማግኘት እንዲሁም ለሌሎች የስራ እድል መፍጠር እስከሚችሉ እየደገፋቸው ይገኛል።
ኦርቢት ኢኖቬሽን ሃብ ከ18 በላይ የሚሆኑ ከተሞች መዳረሻ በማድረግ ከስራ ፈጣሪዎች ጋር የተለያዩ ቢዝነሶችን እየሰራ ሲሆን በአሁን ሰዓት በባሌ ሮቤ፣ ሽሬ፣ አሶሳ ፣ጋምቤላ፣ ላሊበላ ከተማዎች ምዘገባ እየተደረገ ይገኛል።
ኦርቢት ኢኖቬሽን ሃብ ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን በዚህም ከ80 በመቶ በላይ ሴቶች ተጠቃሚ መሆን ችለዋል። ባለፉት ሶስት ዓመታት 580 ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ የቻለ ሲሆን በአሁን ሰዓት ከ1000 በላይ የስራ ዕድሎችን መፍጠር መቻሉ አቶ ዳዊት ተሾመ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በየከተማው የስራ ማስፋፊያ ሲደረግ የዲጂታላይዜሽን ፣የእውቀት እና ገበያ ትስስሮች ከሚያጋጥሙ ችግሮች መካካል ተጠቃሽ መሆናቸውን አክለው ገልጸዋል።
በኤደን ሽመልስ
❤ 9
ታንዛኒያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረ አለመረጋጋት ምክንያት የነጻነት ቀን እንዳይከበር ሰረዘች
ታንዛኒያ በቅርቡ በተከሰተው አለመረጋጋት የተበላሹ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት በማሰብ በሚቀጥለው ወር የሚከበረውን የሀገሪቱን የነጻነት ቀን ድግስ መሰረዟን ጠቅላይ ሚኒስትር ምዊጉሉ ንቸምባ ተናግረዋል።ባለፈው ወር የተካሄደውን አጨቃጫቂ የምርጫ ዉጤትን ተከትሎ የተፈጸሙ ግድያዎችን አስመልክቶ ተቃዋሚዎች እና ሌሎች ኃይሎች በነጻነት ቀን ታህሳስ 9 ለመሰባሰብ ጥሪ ሲያቀርቡ ነበር።
ተቃዋሚዎች የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል ብለው ያምናሉ። መንግስት እስካሁን የሟቾችን ቁጥር ባይገልጽም አጣሪ ኮሚሽን አቋቁሟል።ፕሬዚደንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን በምርጫው 98 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸዉን ቢያዉጁም ተቃዋሚዎች ግን በዲሞክራሲ ላይ ማላገጥ ሲሉ የምርጫዉን ዉጤት ዉድቅ አድርገዋል፡፡
ቁልፍ ተቃዋሚዎቿ በምርጫው እንዳይወዳደሩ ተከልክለዉ ነነር፡፡ ከቁልፍ እጩዎች መካከል አንዱ ቱንዱ ሊሱ ሲሆኑ በአገር ክህደት ተከሰው በእስር ላይ ይገኛሉ፣ የሉሃጋ ምፒና እጩነት በቴክኒክ ምክንያት ውድቅ ተደርጓል።የምርጫ ታዛቢዎች ምርጫው እንደተጭበረበረ እና ከዴሞክራሲያዊ ደረጃዎች በታች መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶችን መኖራቸዉን አስታዉቀዋል፡፡መንግስት ከጥቅምት 29 የምርጫ ቀን ጀምሮ ለአምስት ቀናት ያህል የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረጉ ይታወሳል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 10😁 2
በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ የዝሆን ጥርስ በቁጥጥር ስር ዋለ
በሸገር ከተማ አስተዳደር ገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ በተሰራ ህግን የማስከበር ስራ በርካታ የዝሆን ጥርስ ፣ነዳጅ እና የሀሰተኛ መንጃ ፈቃድ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል ።ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምርያ የተገኘ መረጃ እንዳመለከተው በገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ በህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ በተወሰደ ህግን የማስከበር ስራ ስምንት የዝሆን ጥርስ በህገወጥ መንገድ ከእቃ ስር ተጭኖ ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ሲል በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።
በተጨማሪም 5ሺህ ሊትር ቤንዝል እና 570ሊትር ናፍጣ ከተለያዪ ማደያዎች ተቀድቶ በህገወጥ መንገድ ወደተለያዩ ከተማዋዎች ሊሰራጭ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉም ተገልጿል ።በሌላ በኩልም በህገወጥ መንገድ ሀሰተኛ የመንጃ ፈቃድ በማዘጋጀት ሲሸጡ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል ። በገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ አንድ ቤት ተከራይተው ሀሰተኛ የአሽከርካሪ የመንጃ ፈቃድ በማተም ለግለሰቦች ሲሸጡ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉት ከህብረተሰቡ በተገኘ መረጃ ነው።
በተደረገው ፍተሻም በርካታ ተዘጋጅተው ሊሰራጩ የነበሩ ሀሰተኛ የተሽከርካሪ መንጃ ፈቃዶች በቁጥጥር ስር ውለዋል ። ፖሊስ ምርመራውን በማጣራት በማስረጃ አጣርተለ ለአቃቢ ህግ መላኩን የገፈርሣ ጉጄ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምርያ ለብስራት የላከው መረጃ ያመላክታል።
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 12
የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ቻድ እና ዮርዳኖስ 70 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ወታደራዊ ዕርዳታን አፀደቀ
የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት የመከላከያ አቅምን እና ክልላዊ ደህንነትን ለማሳደግ በማለም ለዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ቻድ እና ዮርዳኖስ በአውሮፓ የሰላም ተቋም (EPF) ስር ላሉ ታጣቂ ሃይሎች 59.5 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 68.5 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ ዕርዳታን አጽድቋል።ምክር ቤቱ ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦር ኃይሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ 34.5 ሚሊዮን ዶላር ለማድረስ መወሰኑን የምክር ቤቱ መግለጫ ገልጿል።
ርዳታው ከ2026 መገባደጃ በፊት የሚደርስ ሲሆን ሲቪሎችን የመጠበቅ እና የመንግስት ስልጣንን ወደነበረበት ለመመለስ፣ ገዳይ ያልሆኑ መሳሪያዎችን በማቅረብ ትዕዛዝ እና ቁጥጥር፣ ስምምነቶችን እና የህክምና ስራዎችን ለማሻሻል እና የወንዝ ድንበር ቁጥጥር ስራዎችን እንደሚያጠናክር አስታዉቋል።እንደ ምክር ቤቱ ገለፃ፣ 16.7 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ የቻድ ጦር ኃይሎችን ይደግፋሉ፣ ይህም የአውሮፓ ህብረት ድጋፍ ለአገሪቱ እንደሚሰጥ ያመላክታል ፣ ድጋፉ በቦኮ ሃራም እና በሳህል ቀጠና የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ለመዉጋት ያስችላል።
ምክር ቤቱ የዮርዳኖስን ጦር ኃይሎች ለማጠናከር በአጠቃላይ የአውሮፓ ህብረት ድጋፍ በተቋሙ ስር ለዮርዳኖስ 55.25 ሚሊዮን ዩሮ ይሰጣል።መግለጫው "ይህ ውሳኔ የአውሮፓ ህብረት ከዮርዳኖስ ጋር ያለው ግንኙነት እያደገ መምጣቱን የሚያመለክት ሲሆን በቅርቡ በአውሮፓ ህብረት-ዮርዳኖስ ስልታዊ እና አጠቃላይ አጋርነት ፊርማ ምልክት ነው" ብሏል፡፡ድጋፉ የአጭር ርቀት ራዳር፣ የአካባቢ ትዕዛዝ እና ቁጥጥር ስርዓት እንዲሁም ተዛማጅ አቅርቦቶችን እና ስልጠናዎችን ለዮርዳኖስ ጦር በማቅረብ የዮርዳኖስን አየር መከላከያ እና ክልላዊ ደህንነትን ለማሳደግ ያለመ ነው።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 19👎 5
በደቡብ ጎንደር ዞን ሶስት ልጆችን ለተገላገለችው እናት የወተት ላም ተበረከተላት
በደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ወረዳ ወንበሮች ቀበሌ ሶስት ልጆችን ለተገላገለች እናት የወተት ላም ተበርክቶላታል።የእብናት ወረዳ የመንግስት ኮሙዩንኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙባረክ ምህረት ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ/ም በእብናት ወረዳ ወንበሮች ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ እናንየ ክንዴ በእብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሶስት ልጆችን በሰላም ተገላግላለች።
የወ/ሮ እናንየ ክንዴ ሶስት ልጆችን መገላገሏን አስመልክቶ ድጋፍ ማግኘት እንዳለባት በመገንዘብ የእብናት ወረዳ የመንግስት ኮሙዩንኬሽን ጥረት አድርጓል።በእብናት ከተማ የበጎ አድራጎት አስተባባሪ ከሆኑት ወጣቶች መካከል ከወጣት ስጦታው ደመወዝ ጋር በመነጋገር ወ/ሮ እናንየ ክንዴ ሶስት ልጆችን በሰላም መገላገሏን በአሜሪካን ሀገር በጎ አድራጎትን ለምታስተባብረው ሊያ ፋንታሁን መረጃውን መስጠት ተችሏል።
ወ/ሮ እናንየ ክንዴ በሰላም ሶስት ልጆችን በመገላገሏ የተሰማትን ደስታ በመግለጽ ልጆቿ በእንክብካቤ እንዲያድጉ በማስተባበር 60 ሺህ ብር ማበርከት ችላለች ሲሉ ሀላፊው ጨምረው ነግረውናል ።በአካባቢው በአንድ ጊዜ ሶስት ልጆችን መገላገል ያልተለመደ እንደሆነ አቶ ሙባረክ ገልፀው የእናቲቷንም ሆነ የልጆቹን ጤንነት ለመጠበቅ የ60ሺህ ብር የወተት ላም ገዝተው ለወ/ሮ እናንየ ክንዴና ባለቤቷ ማስረከባቸው ተገልጿል።
ወ/ሮ እናንየ ክንዴና ባለቤቷ ለተደረገላቸው ድጋፍም ወ/ሮ አሰገደች መኮነን ፣ የእብናት ወረዳ መንግስት ኮሙዩንኬሽን ጽ/ቤትን ፣ ወጣት ስጦታው ደመወዝና ፋንታሁን አበራን ከልብ አመስግነዋል።
በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 52👍 13🤣 10🙏 2😭 1
የሱዳኑ አርኤስኤፍ በዳርፉር የጦር ወንጀል እየፈፀመ ነው ሲል አምነስቲ አስታወቀ
የሱዳን ፓራሚላታሪ የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይል (አር ኤስ ኤፍ) ተዋጊዎች በዳርፉር ኤል-ፋሸር ከተማ የጦር ወንጀል እየፈፀሙ ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የመብት ተሟጋች ድርጅት ባወጣዉ አዲስ ሪፖርት አመልክቷል።ሪፖርቱ በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሚመራው “ለአለም አቀፍ ጥረቶች ምላሽ” ለሦስት ወራት የሚቆይ የሰብአዊ እርቅ ስምምነት እንደሚተገበር ከገለጸ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ይፋ ሆኗል።
ሱዳን በሚያዚያ 2023 በጦር ኃይሎች እና በአርኤስኤፍ መካከል የተነሳው የስልጣን ሽኩቻ በዋና ከተማይቱ ካርቱም እና በሀገሪቱ ውስጥ ግልፅ ጦርነት በማስከተል ሱዳንን ትርምስ ውስጥ ከቷል፡፡አምነስቲ ባወጣው የመጨረሻ ዘገባ በኤል ፋሸር ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ድርጊት የሚገልጹ 28 የተረፉ ሰዎች ምስክርነታቸውን መሰብሰቡን ገልጿል፣ ከታጠቁ ወንዶች ግድያ እስከ ሴት ልጆች መደፈር ድረስ ሰብዓዊ ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል።
"ይህ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የማያቋርጥ እና በስፋት የሚካሄደው ጥቃት የጦር ወንጀሎችን ሲሆን እንዲሁም በአለም አቀፍ ህግ መሰረት ሌሎች ወንጀሎችን ሊያመለክት ይችላል" ሲሉ የአምነስቲ ሃላፊ አግነስ ካላማርድ ተናግረዋል።"ሁሉም ተጠያቂዎች ለድርጊታቸው ተጠያቂ መሆን አለባቸው" ሲሉ አክለዋል፡፡
በዳርፉር ክልል ያለው ጦርነት ከሚያዚያ 2023 ጀምሮ የጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን መደበኛ ጦር በቀድሞው ቀኝ እጃቸው እና አጋራቸው መሀመድ ዳግሎ ከሚመራው አርኤስኤፍ ጋር መጋጨቱ ይታወሳል።በጥቅምት ወር መገባደጃ ላይ አርኤስኤፍ ከቁጥጥሩ ውጭ ሆና የቆየችውን ሰፊውን ምዕራባዊ የዳርፉር ክልል የመጨረሻውን ዋና ከተማ ኤል-ፋሸርን ይዟል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 19👎 1💔 1
በምዕራብ ኦሞ ዞን ወላድ እናት ይዞ ይጓዝ የነበረ አምቡላንስ የመገልበጥ አደጋ አጋጠመው
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን በመኧንት ሻሻ ወረዳ ቡክቱ ቀበሌ ልዩ ስሙ ባንቡ ተብሎ የምጠራበት አከባቢ ነው አደጋው ደርሷል።
መነሻው ከችሩ ሐሩት ጤና ጣብያ አድርጎ ወደ ጀሙ ወላድ ይዞ የመጣ ኮድ 5 ኢ ት 02329 የቀይመስቀል አምቡላንስ ተሽከሪካሪ ላይ የመገልበጥ አደጋ መድረሱ ተገልጿል ።
አምቡላንሱ ሪፈሪ ይዞ ወደ ሆስፒታል ከሻሻ ከተማ በመነሳት ወላድ እናት ይዞ ህይወቷን ለማትረፍ በመጓዝ ላይ እያለ ፍሬን እንቢ ብሎት መገልበጡን ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
በአደጋው በተሽከርካሪ ውስጥ የነበረችው ወላድ እናት ላይ ምንም አይነት ጉዳት ያልደሰባት ሲሆን አሽከርካሪው ላይ ቀላል ጉዳት ደርሶበታል።በመሆኑም ወቅቱ የፀሐይ ወቅት በመሆኑ አሽከሪካሪዎች ሲንቀሳቀሱ እና ከመንቀሳቀሳቸው በፊት ከፍጥነት ወሰን በላይ ከማሽከርከር ሊቆጠቡ ይገባል ሲሉ ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 29🙏 16😢 6👍 3
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በአዲስ አበባ የሚገኙ የሕግ ታራሚዎችን ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በርቀት ለማስተማር የሚያስችለውን ፈቃድ አገኘ
ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ የሚገኙ የሕግ ታራሚዎችን ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በርቀት ለማስተማር የሚያስችል ፈቃድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን መገኘቱን ተገልፃል፡፡በጉዳዩ ዙርያ ለዝግጅት ክፍላችን ማብራሪያ የሰጡት የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የትምህርትና ስልጠና መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስመራ አብደታ እንዳሉት የጤና ችግር ላለባቸው፣ በማረሚያ ቤት ሥራ እየሰሩ ለመማር ለሚፈልጉ እና ዕድሜያቸው ከፍ በማለቱ በክፍል ወስጥ ተቀምጠው መማር ለማይፈልጉ ታራሚዎችን በርቀት ለማስተማር የተገኘው ፈቃድ በትምህርቱ ዘርፍ ከፍተኛጠቀሜታ እንዳለው ገልፀዋል፡፡
የርቀት ትምህርት ፈቃዱ በማረሚያ ቤት የሚሰጠውን የትምህርት ዕድል ያሰፋል፤ ያሉት መሪ ሥራ አስፈፃሚው ሰርተፊኬቱ በኮሚሽኑ በእርምት ላይ የሚገኙ ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑ የሕግ ታራሚዎች የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የታራሚዎችን የትምህርት ዕድል ለማስፋት ፖሊሲውን አሻሽሎ ለፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የርቀት ትምህርት ፈቃድ በመስጠቱ አቶ አስመራ አብደታ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በድሬዳዋ፣ በዝዋይና በሸዋ ሮቢት ማረሚያ ማዕከል የሚገኙ የሕግ ታራሚዎች የርቀት ትምህርት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል እንዲሁም ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጋር ተቀራርበው እንደሚሰሩም ገልፀዋል፡፡
#ዳጉ_ጆርናል
👏 17❤ 7
Photo unavailableShow in Telegram
ዩክሬን በፈፀመችዉ ጥቃት ሶስት ሰዎች መገደላቸዉን ሩሲያ አስታወቀች
በክራስኖዶር እና በሮስቶቭ አዋሳኝ ክልሎች የሚገኙ የሩሲያ ባለስልጣናት ዩክሬን በአንድ ጀምበር በፈጸመችዉ የአየር ድብደባ ጉዳት አድርሳለች ሲሉ ተናግረዋል። የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር 249 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ተኩሶ መምታቱን ይፋ አድርጓል።
የሮስቶቭ ክልል ተጠባባቂ ገዥ ቢያንስ ሶስት ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል። ዩሪ ስሊሳር በቴሌግራም ላይ ባሰፈሩት መልዕክት "የዛሬው ምሽት የጠላት ጥቃት ታላቅ ሀዘንን አምጥቷል" ሲል ጽፈዋል።በክልሉ የወደብ ከተማ ታጋንሮግ ከሟቾቹ መካከል አንዱ ሪፖርት ያደረጉት ከንቲባ ስቬትላና ካምቡሎቫ "አስፈላጊ የአጸፋ ምላሽ እርምጃ ይሰጣል" ሲሉ ቃል ገብተዋል።
በሌላ በኩል የዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ በሩሲያ ሚሳኤሎች እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ተመታለች፤ ባለስልጣናቱ ቢያንስ ሁለት የመኖሪያ ቤቶች መመታታቸውን ተናግረዋል።በቴሌግራም በተጋራ የዩክሬን መንግስታዊ መረጃ መሰረት የአደጋ ጊዜ አገልግሎት ሁለት ሰዎች ሲሞቱ 6 ቆስለዋል ብሏል።
የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት በበኩሉ በከተማው መሃል በሚገኘው በፔቸርስክ አውራጃ አንድ ከፍታ ያለው ሕንፃ ተመትቷል፣ የእሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ስር ከመዋሉ በፊት በሶስት ፎቆች ላይ ጉዳት አድርሷል።ፕሬዚደንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የአየር ኃይላቸው ሀገር አቀፍ የሚሳኤል ማስጠንቀቂያ በመስጠት "ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ጫና እንደማትቀንስ ማወቅ አለብን" ብለዋል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 8👏 1
ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ አርቲስት አለማየሁ ታደሰን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ
👉አምባሳደርነቱ የበጎ ፍቃድ ነው
ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ አርቲስት አለማየሁ ታደሰን በድርጅቱ ታሪክ የመጀመሪያው የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሰየሙን አስታውቋል፡፡ ይህም ድርጅቱ የማህበረሰብ ተሳትፎን ለማጎልበት እና በመላው ኢትዮጵያ ያሉ ህጻናትን እና ወጣቶችን የመጠበቅ እና የማብቃት ተልዕኮውን ለማጎልበት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ለብስራት ሬዲዮ የተናገሩት በኤስኦኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ዳይሬክተር አቶ ሣህለማርያም አበበ ናቸው ፡፡
ድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር ለመሰየም የወሰነው ፕሮግራሞቹን እያሰፋ ባለበትና የሀገር ውስጥ ሃብት የማሰባሰብ ጥረቱን እያጠናከረ ባለበት ወቅት ነው። ይህም ለብዙ ማህበረሰቦችን ለመድረስ፣ ሰፊ ተሳትፎን ለማነሳሳት እና ዘላቂነት ያለው ድጋፍን ለማረጋገጥ በማለም ነው ብለዋል፡፡
ኤስኦኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ ተልዕኮውን የሚያጎላ፣ የህጻናትን መብት የሚያስከብር እና በአገር ውስጥ የሚገኙት ባለ ድርሻ አካላት መካከል መተማመንን ለማጠናከር የሚረዳ በጎ ተጽእኖ ፈጣሪ አካል ስለሚያስገልግ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
የብራንድ አምባሳደሩ ሚናም ድርጅታዊ አጋርነትን ለማስፋት፣ የገንዘብ ማሰባሰብ ጥረቶችን ለማጎልበት እና በቂ የወላጅ እንክብካቤ ሳያገኙ የሚያድጉ ህጻናት እና ወጣቶች የበለጠ የህዝብ ትኩረት እንዲያገኙ ለማስቻል ያለመ ነው ብለዋል።
የአርቲስት አለማየሁ ታደሰ ምርጫም በጥንቃቄ እና ግልፅ አሰራርን የተከተለ ሲሆን ይህም የእጩነት ምዕራፍ፣ የአስመራጭ ኮሚቴ ዝርዝር ግምገማ እና ሰፊ የሰራተኞች ተሳትፎን ያካተተ እንደነበር ገልፀዋል።
አርቲስት አለማየሁ ታደሰም ከኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች “የብራንድ አምባሳደር መሆን ከማዕረግ በላይ የሆነ እና ትክክለኛ ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያበቃ ትልቅ ሃላፊነት እና እድል መሆኑን ተናግሯል ።
በምህረት ታደሰ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 23👍 12
