ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)
رفتن به کانال در Telegram
በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

50 494
مشترکین
-624 ساعت
+27 روز
+10030 روز
آرشیو پست ها
++"+ ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::በእርስዋም ለዘለዓለም
ይኖራሉ::የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::አንደበቱም
ፍርድን
ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ
ነው::በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+ (መዝ. 36:29)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔ::>>>
https://t.me/zikirekdusn
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "አባ ሊቃኖስ ወአባ ሰረባሞን ሰማዕት" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
" ኅዳር 28 "
+*" አባ ሊቃኖስ ዘደብረ ቆናጽል "*+
=>ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት:: አባ ሊቃኖስ ከዘጠኙ (ተስዓቱ) ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው::
+ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው:: በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር:-
1.የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ
2.ዓላማ (የእግዚአብሔር መንግስት) እና
3.ገዳማዊ ሕይወት ነው::
+አባ ሊቃኖስን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው:: እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል:: አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል::
+በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ:: ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት 5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ::
+በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም:: ስለዚህም በ470ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ::
+ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው:: ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው:: ይህች ቦታ ቤተ ቀጢን ትባላለች::
አባ
ሊቃኖስና
8ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደ ገቡ የመጀመሪያሥራቸው
ቋንቋን መማር ነበር::
+ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ
ሥራቸውን አንድ አሉ:: በወቅቱ በአቡነ ሰላማ: በአብርሃ
ወአጽብሐና
በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ
መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አባ ሊቃኖስ እንደ ገና
አቀጣጠሉት::
+ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ
ሰበኩት::የካደውን እየመለሱ: የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ
ለዓመታት ወንጌልን
ሰበኩ:: ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም
ሆነ::
+ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው
ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው:: በዚህም ለሃገራችን
ትልቁን ውለታ ዋሉ:: ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አባ ሊቃኖስ የሚመገቡትም ሆነ
የሚጸልዩት በማኅበር ነበር:: በመካከላቸውም ፍጹም
ፍቅር ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም::
+የነ አባ ሊቃኖስ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ
ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ:: ይህንን ለማድረግ ግን የግድ
መለያየት አስፈለጋቸው:: እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው
ቦታ ሔደ::
*ዸንጠሌዎን በጾማዕት:
*ገሪማ በመደራ:
*አረጋዊ በዳሞ
*ጽሕማ በጸድያ
*አባ ይምዓታ በገርዓልታ
*ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ::
+ልክ እንደ ባልንጀሮቻቸው 8ቱ ቅዱሳን አባ ሊቃኖስም
ከጻድቅነታቸው ባሻገር ለሃገራችን ትልቅ ባለውለታ
ናቸው::በነገራችን
ላይ 'አባ ሊቃኖስ' የመጀመሪያ ስማቸው ሳይሆን
በትምሕርታቸው (በእውቀታቸው) የተደመመ የአክሱም
ሕዝብ ያወጣላቸው ስም
ነው::
+ሊቃኖስን 'ሊቁ አባት' ማለት ነው ብለው የተረጐሙልን
አበው አሉና:: ይሕስ በምን ይታወቃል ቢሉ:- 9ኙ ቅዱሳን
የማኅበር አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደየ ራሳቸው
ገዳማት ሲሔዱ አባ ዸንጠሌዎንና አባ ሊቃኖስ እዚያው
አክሱም አካባቢ
በመቅረታቸው ይሏል::
+ምክንያቱም ሕዝቡና ንጉሡ 2ቱን አበው "አትራቁን"
ብለው ለምነዋቸው ነበርና:: በዚህም የተነሳ አባ
ዸንጠሌዎን ከአክሱም
ከተማ በላይ ባለች ጾማዕት (እንዳባ ዸንጠሌዎን)
በሚሏት ተራራ ላይ ሲያርፉ: አባ ሊቃኖስ ደግሞ ከዚያው
ከጾማዕት 1
ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ደብረ ቆናጽል
(የቀበሮዎችተራራ) ላይ ዐርፈዋል::
+በመካከላቸው ደግሞ የቅድስት ማርያም መግደላዊት
ቤተ ክርስቲያን ይገኛል::
አባ ሊቃኖስ በአታቸውን ካደራጁና ገዳም ካነጹ
በኋላ ደቀ መዛሙርትን አፈሩ: አስተማሩ::
+እጅግ ከበዛው ተጋድሏቸው ባልተናነሰ መንገድ ለ21
ዓመታት ያህል ከተራራው እየተነሱ ወንጌልን ሰብከዋል::
መጽሐፍ
ቅዱስና ሌሎች መጻሕፍትንም ከሱርስት (የሶርያ ልሳን)
እና ከጽርዕ (የግሪክ ልሳን) ተርጉመዋል::
+ሁልጊዜም ለአገልግሎት ሲወጡ በትረ ሙሴአቸውን
አይለዩም ነበር:: ሲሰብኩም: ሲጸልዩም ተደግፈውባት
ነበር:: ታዲያ
ከዘመን ብዛት የእጃቸው መዳፍ መነደሉን
አበው:-"ወበእሒዘ በትር ዘተሰቁረ ዕዱ" ሲሉ ይናገራሉ::
+ዳግመኛ ማታ ማታ ለጸሎት እጆቻቸውን ሲያነሱ እንደ ፋና
ቦግ ብለው ሲያበሩ ይታዩ ነበር:: ጻድቁ አባ ሊቃኖስ
ሥሙር
በሆነ ሕይወታቸው በእግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን
በነገሥታቱና በሕዝቡ ዘንድም ሞገስን አግኝተዋል:: ዛሬም
ድረስ የአክሱም
ሕዝብ ከልቡ ያከብራቸዋል::
+አንድ ወቅትም ሳይገባን (በቸርነቱ) ሒደን ገዳማቸውን
ተመልከተናል:: አበው እንደሚሉት በደብረ ቆናጽል ላይ
ያለው ደን
የብዙ ሥውራን መኖሪያ ነው:: ለ1,500 ዓመታት ተከብሮ
ቢኖርም በ1928ቱ የጣልያን ወረራ ግን እንዳልነበረ ሆኖ
ነበር::
+ዛሬም በቀድሞ ገጽታው አይደለም:: በገዳሙም
ያገኘነው አንድ አባትን ነው::
+ዐይናችን ግን ብዙ ነገሮችን ተመልክቶ አድንቋል:: እንደ
ሰማነውም ዛሬም መካነ ቅዱሳን በመሆኑ የጽዮን
አገልጋዮችም ማረፊያ ነው:: ጻድቁ አባ ሊቃኖስ ያረፉት ሕዳር 28 ቀን
ነው::
+" ቅዱስ ሰረባሞን ሰማዕት "+
+ቅዱሱ ሰው የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ሲሆን የቅዱሳን
ሐዋርያት ዘመድ ነው:: እርሱ ተወልዶ ያደገው በ3ኛው
መቶ ክ/ዘመን
በኢየሩሳሌም ነው:: የዘር ሐረጉ ሲቆጠርም በቀጥታ
ከሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስና ከስምዖን ቀለዮዻ
ይደርሳል::
+በልጅነቱ ያደገው በሥርዓተ ኦሪት ነው:: ወጣት በሆነ
ጊዜ ግን ፈጣሪ በሰጠው ሕሊና ተመራምሮ በክርስትና
ለመኖር ወሰነ:: የወቅቱን የኢየሩሳሌም ኤዺስ ቆዾስ ሒዶ "አጥምቀኝ"
ቢለው "ልጄ! ደስ ይለኝ ነበር:: ግን ወገኖችህ አይሁድ
ይገድሉኛል" ሲል መለሰለት::
+አክሎም "ወደ ግብጽ ሒደህ ግን ብትመጠመቅ የተሻለ
ነው" ስላለው ከኢየሩሳሌም ግብጽ ገባ:: ግብጽ ደርሶ:
ከቅዱስ
ቴዎናስ (16ኛ ፓትርያርክ) ክርስትናን ተምሮ
ተጠመቀ::ቀጥሎም ወደ ገዳም ገብቶ ከመጀመሪያዎቹ
መነኮሳት አንዱ ሆነ::
ምናኔን ከአባ እንጦንስ ተምሮ ስም አጠራሩ ከፍ አለ::
+በተጋድሎውና በንጽሕናው ስለ ወደዱትም የኒቅዮስ
ዻዻስ አደረጉት:: በዘመነ ሲመቱም ጣዖት አምልኮን
ከአካባቢው አጥፍቷል:: ስለዚህ ፈንታም በዲዮቅልጢያኖስ ተይዞ በዚህች ቀን
ተገድሏል:: ሲገደልም ልክ እንደ ቅድመ አያቱ ቅዱስ
እስጢፋኖስ ፊቱ ያበራ ነበር::
=>አምላከ አበው ቅዱሳን መዓዛ ቅድስናቸውን
ያሳድርብን::ከበረከታቸውም ይክፈለን::
=>ኅዳር 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ሊቃኖስ ጻድቅ (ከተስዓቱ ቅዱሳን)
2.ቅዱስ ሰረባሞን ሰማዕት
ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አማኑኤል ቸር አምላካችን
2.ቅዱሳን አበው /አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ/
3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
4.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
5.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)
(Translated by Mhr. Esuendale Shemeles with the permission of Dn. Yordanos Abebe)
✞And at that juncture, wanting to pray he voiced, “O Lord!” And the fathers seeing this said,
“While half of his body was deceased,
With the rest half he prayed.”✞And after his scream, when the King had his head beheaded with a sword, the Lord descended and took his soul up to heaven.
✞And when his mother, sister, and wife heard his martyrdom, lamenting and chanting they collected his body parts and shrouded them. And they perfumed it as well. And in Ethiopia, the Monastery (Ark) of this Saint is found in the desert/wilderness of Tach Armachiho. It is an amazing place of blessings.
✞✞✞ Abune Tekle Hawaryat the Ethiopian✞✞✞
=>The Ethiopian Saint, Abune Tekle Hawaryat was one of the major saints that rose in the 15th century. Particularly, he was a father renowned for his asceticism and virtue during the reign of Emperor Zara Yaqob.
✞The Saint is known as “of Debre Tsemona” and sometimes as “of Geberema”. And that may be because these were some of the areas that he struggled in as he had struggled in many places, thus he is called after them.
✞What is mostly known is that he had lived in the land of Shewa, Gojjam, and Afar. Hereafter, let us mention some things regarding the father.
*The Saint used to struggle daily to liken Christ in His passion.
*One day, seeing that a communicant of the Holy Eucharist had vomited on a road and people were removing themselves from the place in disgust, the Saint consumed what was heaved [for the sanctity of the Holy Eucharist]. And that was because his eyes saw the Holy Body and Honorable Blood of the Creator. And at that juncture, the Lord descended from heaven and inscribed luminosity unto the Saint’s countenance. And for that reason, his face used to shine.
*On another day, in his monastery, when people wanted to slay a chicken, because it voiced with a human tongue, “I beseech you in the name of Abba Tekle Hawaryat!”, they let it be.
*The Saint had also dwelt in the desert of Afar (one of the hottest places on earth) for about 14 years.
✞The Saint had lived in a cell for 41 years as well. The Righteous, Abune Tekle Hawaryat, after living in such manner, departed on this day at the age of 71 years.
✞✞✞Saint Philemon the Apostle✞✞✞
=>Saint Philemon was one of the 72 Disciples and is known as “The one with a delightful tongue/speech.” During the Era of the Apostles, because he was very young, he used to serve the fathers hastily, running here and there.
✞After believing and following the Lord, learning for 3 years and 3 months under Him and assuming the gifts of the Holy Spirit, he went forth to preach with St. Andrew. And his diocese, lot, was Lod/Lydda. And when he taught or read, all the people listened to him in awe. Even soldiers that were sent to kill him, taken by his sermon forgot to slay him.
✞And at times, even birds and doves used to listen and talk to him. Today, is the day on which St. Philemon departed.
✞✞✞May the God of the Saints shine upon us their light. And may He grant us from their blessings.
✞✞✞ Annual feasts celebrated on the 27th of Hedar
1. Saint James the Mangled (Intercisus/Sawn/Mutilated)
2. Abune Tekle Hawaryat the Righteous (Ethiopian)
3. Saint Philemon the Apostle
4. Saint Clement the Martyr
5. Saint Timothy the Martyr
6. Abba Gebre Yohannes the Righteous
✞✞✞ Monthly Feasts
1. The Commemoration of the Crucifixion of our Lord and God, the Holy Savior, Jesus Christ
2. Abune Meba Tsion the Ethiopian Righteous
3. St. Macarius the Great (Principal of all the Monks)
4. St. Gelawdewos (Claudius) Martyr (Emperor of Ethiopia)
5. Abba Bifamon/Abe-Fam/Bifam/Phoebammon, Martyr and Righteous
6. Mar St. Victor/Boctor Ebn Romanus, Martyr
✞✞✞“Wherefore, my dearly beloved, flee from idolatry. I speak as to wise men; judge ye what I say. The cup of blessing which we bless, is it not the communion of the blood of Christ? The bread which we break, is it not the communion of the body of Christ? For we being many are one bread, and one body: for we are all partakers of that one bread.”✞✞✞
1 Cor. 10:14-17
✞✞✞ Salutations to God ✞✞✞
#Feasts of #Hedar_27
✞✞✞On this day we commemorate the Martyrdom of Saint James the Mangled (Intercisus), the Departure of Abune Tekle Hawaryat the Ethiopian and Saint Philemon the Apostle✞✞✞
✞✞✞In the name of the Father, the Son and the Holy Spirit, one God. Amen!✞✞✞
✞✞✞ Saint James the Mangled (Intercisus)✞✞✞
=>This name is highly famed and renowned in the Church. St. James is numbered among the major martyrs and is also known as “The Star of Persia”. St. James the Mangled was born and raised in the land of Persia (what is now Iran).
✞During those days, this land hand on one side strong Christians and on the other cruel kings that worshipped idols. St. James after growing in the teachings of Christianity took a wife.
✞And because he had favor before the King, Sakrod, the monarch placed him as an appointee in his palace. And St. James’ life of prayer and fasting started to decline because of the luxuries of the palace. And through time, he became complacent in all the orders of the King.
✞In addition to that, one day, Sakrod said to St. James, “Prostrate to the sun and to fire, and adore them.” And as it (adoration) was a matter that had been eroded through time, thinking, “Alright! Let him be jubilant,” he prostrated to the sun and worshipped it.
✞And when this news was heard across the Christians of the era, it created great anguish. Specially, when his wife, mother, and sister heard what had occurred, their hearts fell into in agony. Then, all three gathered, wrote a letter, signed it and sent to him.
✞And the content of the letter said as follows; “We heard that you denounced your Christian faith, hence we are grieved. Accordingly, we do not want to live around you hereafter. If you are not trustworthy to Christ, Who died for you, it is hard for us to trust you as a child, as a son and as a husband.”
✞And after sending him this letter, they left the area. And when St. James received the letter and read it after entering his house, he was shocked. Because his only kins in this world were his wife, mother and sister, he was internally shaken. He fell to the ground and wept greatly.
✞And when night fell, he went to his place of prayer and knelt. And he saw vividly his error which he had committed after his unnecessary closeness to the King.
✞And standing before our Lord, he lamented, “O Lord! If separation from my kins on earth shakes me this much, how vexing would it be then to separate from Your Love! How would I stand then before Your throne!”
✞And after spending the night crying and in prayer, he repented in the morning. And starting that day, he was engaged in the Love of Christ. Befriending prayer and fasting, he stopped going to the King’s court.
✞And the King, Sakrod, who knew what had occurred, had him summoned and asked, “What has happened to you? Why did you separate in worship form I?” Thus, St. James replied, “It is not proper to leave Christ, Who created me, and delight you in idolatry.”
✞Then, the King tried to persuade him. And when James said “No”, he had him lashed and beaten until the Saint’s blood dripped on the ground. He also had him tortured in many different ways. However, St. James persisted in the love of Christ.
✞And the King, who was angered by this, ordered that they mutilate the Saint and not kill him instantly. Thereafter, they started to cut pieces from his body daily. And they mutilated him, his hands starting from his fingers to his arm and his legs from his feet to his thighs. The middle part of his body (his waist and head) was what was left.
✞And while all this happened, he praised the Lord and prayed. He used to say “O Vine! Make me Your branch.” (John 15:5) And the pieces of his body that they had cut away, when they were counted, came to be 42. And the 43rd was the rest of his form that was left.
. . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና:: +"+ (1ቆሮ. 10:14)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
https://t.me/zikirekdusn
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን † ✞✞✞
† ኅዳር ፳፯ †
+"+ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ +"+
=>ይህ ስም በቤተ ክርስቲያን እጅግ ዝነኛና ታዋቂ ነው:: ቅዱስ ያዕቆብ ቁጥሩ ከዓበይት ሰማዕታት ሲሆን የፋርስ ኮከብ በመባልም ይታወቃል:: ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ("ሙ" ጠብቆ ይነበብ) ተወልዶ ያደገው በ4ኛው መቶ ክ/ዘ በምድረ ፋርስ (የአሁኗ ኢራን) ውስጥ ነው::
+ያኔ ይህቺ ሃገር በአንድ ወገን ጠንካራ ክርስቲያኖች: በሌላ ወገን ደግሞ ጣዖትን የሚያመልኩ ጨካኝ ነገሥታት ነበሩባት:: ቅዱስ ያዕቆብም በክርስትና ትምሕርት አድጐ ሚስት አገባ::
+በዘመኑ ከነበረው ንጉሥ ሠክራድ ጋር በጣም ይዋደዱ ነበርና በቤተ መንግስቱ ውስጥ ሹም አድርጐ አስቀመጠው:: በቤተ መንግስት ውስጥ ምቾት የበዛበት ቅዱስ ያዕቆብ የጾምና የጸሎት ሕይወቱ እየቀዘቀዘ መጣ:: በሒደትም ንጉሡ የሚለውን ሁሉ የሚፈጽም ሰው ሆነ::
+አንድ ቀን ግን ሠክራድ ቅዱስ ያዕቆብን "ለእሳትና ለጸሐይ ስገድ: እነሱንም አምልካቸው" ሲል ጠየቀው:: ከመጀመሪያ የተሸረሸረ ነገር ስለ ነበረ "እሺ! ደስ ይበለው" ብሎ ለፀሐይ ሰገደ:: እርሷንም አመለከ::
+ይህቺ ዜና በዘመኑ ክርስቲያኖች ዘንድ ስትሰማ ታላቅ ሐዘንን ፈጠረች:: ይልቁኑ ሚስቱ: እናቱና እህቱ ይህንን ሲሰሙ አንጀታቸው አረረ:: በዚህ ምክንያትም 3ቱ ተሰብስበው አንድ ደብዳቤ ጽፈው: ተፈራርመው ላኩለት::
+የደብዳቤው ይዘት እንዲህ ይላል:- "አንተ ክርስትናህን መካድህን ሰምተን አዘንን:: በዚህም ምክንያት ከዚህ በሁዋላ በአካባቢህ መኖርን አንፈልግም:: ለሞተልህ ለክርስቶስ ካልታመንሀ እኛ አንተን እንደ ልጅ: እንደ ወንድምና እንደ ባል ልናምንህ ይከብደናል::"
+ይህንን ደብዳቤ ልከውለት እነርሱ አካባቢውን ለቀቁ:: ቅዱስ ያዕቆብ ደብዳቤውን ተቀብሎ: ወደ ቤቱ ገብቶ ሲያነበው ደነገጠ:: በዚህ ምድር ያሉት ዘመዶቹ ሚስቱ: እናቱና አንዲት እህቱ ብቻ ናቸውና ውስጡ ተሸበረ:: ተደፍቶም ምርር ብሎ አለቀሰ::
+ሲመሽም በቤቱ ውስጥ ወደ ነበረው የቀድሞ የጸሎት ቦታ ሒዶ ተንበረከከ:: ከንጉሡ ጋር በነበረው ያልተገባ ቅርርብ የፈጸመው ስህተት ሁሉ ቁልጭ ብሎ ታየው::
+በጌታችን ፊት ቁሞም "ጌታ ሆይ! በምድር ካሉ የሥጋ ዘመዶቼ መለየት እንዲህ ካሸበረኝ: ካንተ ፍቅር መለየትማ እንደ ምን ይጨንቅ ይሆን! በሰማያዊ ዙፋንህ ፊትስ እንዴት ብዬ እቆማለሁ!" ሲል አምርሮ አለቀሰ::
+ሙሉውን ሌሊት በእንባና በጸሎት አድሮ በጠዋት ንስሃ ገባ:: ከዚያች ቀን ጀምሮም ፍጹም በክርስቶስ ፍቅር ተጠመደ:: ጾምና ጸሎትን ወዳጆቹ አድርጐ ከንጉሡ እልፍኝና አደባባይ ቀረ::
+ይህንን ያወቀው ንጉሡ ሠክራድ ወደ እርሱ አስጠርቶ "ምን ሆነሃል? ስለ ምንስ በአምልኮ ከእኔ ተለየህ?" አለው:: ቅዱስ ያዕቆብም መልሶ "የፈጠረኝን ክርስቶስን ትቼ አንተን በባዕድ አምልኮ አስደስትህ ዘንድ የሚገባ አይደለም" ሲል ተናገረው::
+ንጉሡ ቅዱሱን አስቀድሞ ሊያታልለው ሞከረ:: እንቢ ሲለው ግን ደሙ በመሬት ላይ እስኪንጠፈጠፍ ድረስ አስገረፈው:: አስደበደበው:: ጭንቅ መከራዎችንም አሳየው:: ቅዱስ ያዕቆብ ግን በፍቅረ ክርስቶስ ጸና::
+በዚህ የተበሳጨው ንጉሡ እንዲቆራርጡት: ግን ቶሎ እንዳይገሉት አዘዘ:: ከዚያ ቀን በሁዋላ በቀን በቀን እየገቡ ከአካሉ ይቆርጡ ጀመር:: ከእጣቶቹ ተነስተው እጆቹን እስከ ክንዱ: እግሮቹን እስከ ታፋው ድረስ ቆረጡ:: መሐል አካሉ (ወገቡና ራሱ) ብቻ ቀረ::
+ይህ ሄሉ ሲሆን እርሱ ጌታን ይቀድሰው: ይጸልይም ነበር:: "የወይን ግንድ ሆይ! እኔን ቅርንጫፍህ አድርገኝ" (ዮሐ. 15:5) ይለው ነበር:: ከአካሉ እየቆረጡ የጣሉትም ሲቆጠር 42 ሆነ:: 43ኛ ደግሞ የተረፈ አካሉ ነበር::
+ያን ጊዜ ሊጸልይ ፈልጐ "ጌታ ሆይ!" ብሎ ጮኸ:: ይህንን አበው:-
"መንፈቀ አካሉ ጸለየ መዊቶ መንፈቁ" ብለው ገልጸውታል:: ግማሽ አካሉ ሙቶ በቀረው ይጸልይ ነበርና ንጉሡም ከጩኸቱ በሁዋላ አንገቱን በሰይፍ ሲያስመታው ጌታችን ወርዶ ታቅፎ ወደ ሰማይ አሳረገው::
+እናቱ: እህቱ: ሚስቱ ይህንን ሲሰሙ እያለቀሱና እየዘመሩ አካሉን ሰብስበው ገንዘውታል:: ሽቱም አርከፍክፈውበታል:: የዚህ ቅዱስ ገዳም (ታቦት) በኢትዮዽያ: ታች አርማጭሆ በሚባለው በርሃ ውስጥ ይገኛል:: ድንቅ የሆነ የበረከት ቦታም ነው::
+"+ አባ ተክለ ሐዋርያት +"+
=>ኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ተክለ ሐዋርያት በ15ኛው መቶ ክ/ዘመን ከተነሱ ዐበይት ጻድቃን አንዱ ናቸው:: በተለይ በጻድቁ ንጉሥ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን በተባሕትዎም: በትሩፋትም እጅግ የተደነቁ አባት ነበሩ::
+ጻድቁ ሲጠሩ "ዘደብረ ጽሙና": አንዳንዴም "ዘገበርማ" እየተባሉ ነው:: ምናልባትም በብዙ ቦታ ላይ ስለ ተጋደሉ በእነዚህ: ቦታዎችም ላይ ስለ ነበሩ ሊሆን ይችላል እንደዚህ ተብለው የተጠሩት::
+በብዛት የሚታወቀው ደግሞ በምድረ ሸዋ: ጐጃምና በምድረ አፋር አካባቢ በመኖራቸው ነው:: እስኪ አንዳንድ ነገሮቻቸውን እናንሳ:-
*ጻድቁ ክርስቶስን በመከራው ይመስሉት ዘንድ ዘወትር ይተጉ ነበር::
*አንዴ ሥጋ ወደሙ የተቀበለ አንድ ሰው በመንገድ ላይ ሲያስመልሰው ተመልከተው ሁሉ ተጸይፎ ሲሸሽ እሳቸው ግን ደስ እያላቸው ተመግበውታል:: ምክንያቱም የእርሳቸው ዓይን የሚመለከተው የፈጣሪን ሥጋና ደም ነው:: በዚህ ጊዜም ጌታ ከሰማይ ወርዶ በግንባራቸው ላይ ፀሐይን ስሎባቸዋል:: በዚህ ምክንየትም ፊታቸው ያበራ ነበር::
*አንዴ ደግሞ በገዳማቸው አንድ ደሮ ለእንግዳ ሊያርዱት ሲሉ "በአባ ተክለ ሐዋርያት ተማጽኛቹሃለሁ!" በማለቱ ትተውታል::
*በአፋር በርሃ አካባቢ ለ14 ዓመታት ኑረዋል::
+በአንድ በአት ውስጥም ለ41 ዓመታት ኑረዋል:: ጻድቁ አቡነ ተክለ ሐዋርያት እንዲህ ተመላልሰው በተወለዱ በ71 ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈዋል::
+"+ ቅዱስ ፊልሞና ሐዋርያ +"+
=>ቅዱስ ፊልሞና ከ72ቱ አርድእት አንዱ ሲሆን ብዙ ጊዜ "ጥዑመ-ቃል (አንደበቱ የሚጣፍጥ)" ተብሎ ይጠራል:: በዘመነ ሐዋርያት በጣም ልጅ በመሆኑ እየተሯሯጠ ለአበው ይታዘዝ ነበር::
+ጌታን አምኖ ተከትሎ: ለ3 ዓመት ከ3 ወር ተምሮ: ከቅዱስ መንፈሱ ነስቶ: ከቅዱስ እንድርያስ ጋር ለስብከት ወጥቷል:: ሃገረ ስብከቱም ልዳ ነበረች:: እርሱ ሲያነብ (ሲያስተምር) ሰው ሁሉ በተመስጦ ይሰማው ነበር:: ሊገድሉት የመጡ ወታደሮች እንኩዋ በተደሞ መግደላቸውን ይረሱት ነበር::
+አንዳንድ ቀን ደግሞ ወፎችና ርግቦች ያደምጡት: ያዋሩትም ነበር:: ይህቺ ቀን ለቅዱስ ፊልሞና ዕለተ ዕረፍቱ ናት::
=>አምላከ ቅዱሳን ብርሃናቸውን ያብራልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
=>ኅዳር 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
2.አቡነ ተክለ ሐዋርያት ጻድቅ
3.ቅዱስ ፊልሞና ሐዋርያ
4.ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሰማዕት
5.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት
6.አባ ገብረ ዮሐንስ ጻድቅ
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
2.አቡነ መብዓ ጽዮን ጻድቅ
3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
4.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
5.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
6.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
=>+"+ ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? .
ገድለ አቡነ ሐብተ ማርያም
2012
አቡነ ሀብተማርያም.m4a55.03 MB
✝እንኳን አደረሰነ!
☞ወርኀ ኅዳር ቡሩክ። ወአመ ፳ወ፮፦
✝ጾመ ስብከተ ጌና፥ ዘነቢያት ወዘአበው ቀደምት ቅዱሳን (ወይእቲ ጾመ አዳም)
✝ወተዝካረ በዓሎሙ ለቅዱሳን፦ ሣራ ወርብቃ፥ ወቶማስ ሐዋርያ
❖ወበዓለ ቅዱሳን አበው፦
✝ክቡራን ወዐቢያን፥ ወመስተጋድላን፥ ከዋክብት ብሩሃን፥ ሰማዕታተ ናግራን ኄራን፥ መኃትዊሃ ለቤተ ክርስቲያን (እድ ወአንስት፥ አዕሩግ ወሕጻናት፥ ካህናት ወዲያቆናት)
✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ አባ ኂሩት ጻድቅ፥ ወሰማዕት አረጋዊ (አቡሆሙ ለሰማዕታተ ናግራን)
✝ቅድስት ወቡርክት፥ ድማኅ ሰማዕት፥ ወ፪ቲ አዋልዲሃ ቡሩካት (ዘናግራን)
✝ዐቢይ ወክቡር፥ ካሌብ ጻድቅ፥ ንጉሠ ኢትዮጵያ፥ መናኔ መንግሥት (ዘአድኀና ለሀገረ ናግራን)
✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ አባ ሀብተ ማርያም ብጹዕ ወንጹሕ፥ ወጻድቅ ኢትዮጵያዊ፥ ብእሲ ሔር፥ ብእሴ እግዚአብሔር፥ ወሐዋርያ ትሩፈ ምግባር፥ ወረዐየ ኅቡዐት (ዘደብረ ይሰበይ፥ መካነ ብጹዓን)
✿ቅድስት ገዳሙ፥ ወቅዱሳን ውሉዱ (መነኮሳት)
✝ቅድስት ወቡርክት፥ ዮስቴና ጻድቅት (እሙ)
✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ አባ ኢየሱስ ሞዐ ጻድቅ፥ ዘደብረ ሐይቅ፥ ብእሲ ትሩፍ፥ ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን (ወመምህረ ብጹዓን)
✿ቅድስት ገዳሙ፥ ወቅዱሳን ውሉዱ (መነኮሳት)
✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ አባ ኢያሱ ጻድቅ፥ ብእሲ መስተጋድል (ረድኡ ለአቡነ ሀብተ ማርያም)
✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ቢላርያኖስ ሰማዕት፥ ወረድኦሙ ለሰማዕታት (ዘሀገረ ሮሜ)
✝ቅድስት ወቡርክት፥ ኪልቅያ ሰማዕት (ብእሲቱ)
✝ቅድስት ወቡርክት፥ ታቱስብያ ሰማዕት (እኅቱ)
✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ አባ ጎርጎርዮስ ጻድቅ፥ ኤጲስ ቆጶስ ዘደሴተ ሰንሲላ
✿አበው ክቡራን፥ ጌርሎስ፡ ወምክዋስ፡ ወማርልዮስ
❖ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡
