Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ
رفتن به کانال در Telegram
እንኳን ደህና መጡ‼ 📌ማስታወቂያ ለማሰራት👉 @WasuMohammed 📌 ቻናሉን ለመቀላቀል 👉 @Wasulife ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

242 360
مشترکین
-57224 ساعت
+10 4727 روز
+19 74730 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
" በትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ የጸጥታ ግምገማ እንዲቀርብልን ጠይቀናል" የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩን ለመወሰን፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ይፋዊ የጸጥታ ሁኔታ ግምገማ እየጠበቀ መሆኑን አስታወቀ።
ምርጫ ቦርድ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጸው፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ የምርጫ ወረዳዎችን በጸጥታ ሁኔታቸው ላይ በመመስረት በአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀጠናዎች በሚል በመለየት ሪፖርት እንዲያቀርብ በይፋ ጠይቋል። ቦርዱ ይህ መረጃ ሳይደርሰው በትግራይ ክልል ምርጫ ስለማካሄድ ምንም ዓይነት ውሳኔ ላይ መድረስ እንደማይችል ገልጿል።
የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጄኔራል ታደስ ጥያቄው እንደቀረበላው ገልፀዋል። በክልሉ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ወይስ አይቻልም በሚለው ጉዳይ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተን ምላሽ እንሰጣለን ያሉት ጀነራል ታደሰ ፣ ምላሹም በዚህ ሳምንት ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
❤ 66😍 7🥴 5🎉 4🕊 3🔥 2💩 2🏆 2🙊 2
Photo unavailableShow in Telegram
" በትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ የጸጥታ ግምገማ እንዲቀርብልን ጠይቀናል" የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩን ለመወሰን፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ይፋዊ የጸጥታ ሁኔታ ግምገማ እየጠበቀ መሆኑን አስታወቀ።
ምርጫ ቦርድ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጸው፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ የምርጫ ወረዳዎችን በጸጥታ ሁኔታቸው ላይ በመመስረት በአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀጠናዎች በሚል በመለየት ሪፖርት እንዲያቀርብ በይፋ ጠይቋል። ቦርዱ ይህ መረጃ ሳይደርሰው በትግራይ ክልል ምርጫ ስለማካሄድ ምንም ዓይነት ውሳኔ ላይ መድረስ እንደማይችል ገልጿል።
የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጄኔራል ታደስ ጥያቄው እንደቀረበላው ገልፀዋል። በክልሉ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ወይስ አይቻልም በሚለው ጉዳይ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተን ምላሽ እንሰጣለን ያሉት ጀነራል ታደሰ ፣ ምላሹም በዚህ ሳምንት ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
❤ 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዶ/ር አብዱ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት ደሴ
ስልክ 0937411111
0938411111
ሊንክ:
https://t.me/+ACPCPoXDK4JlMjA0
❤ 5👏 3👍 2
"ጥቃቱ የተለየ ሃይማኖትን ያላነጣጠረና ዓላማው አሸባሪዎችን መደምሰስ ብቻ ነው"
ዩሱፍ ማይታማ ቱጋር
የናይጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
አሜሪካ በናይጄሪያ በሚገኙ የ 'አይ.ኤስ' ይዞታዎችን ምሽቱን መደብደቧ ተሰምቷል።
ትራምፕ በ 'ትሩዝ ሶሻል' ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ "በእኔ መሪነት አክራሪ ሽብርተኝነት እንዲስፋፋ አንፈቅድም" በማለት፣ በተለይም በንጹሃን ክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት ለመግታት ቆራጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ (AFRICOM) ከናይጄሪያ መንግስት ጋር በመተባበር በሶኮቶ ግዛት ውስጥ የሚገኙ የሽብር ጣቢያዎችን ኢላማ ማድረጉን አረጋግጧል። ጥቃቱ "ዒላማውን የጠበቀ እና የተሳካ" እንደነበርም ተነግሯል።
የናይጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዩሱፍ ማይታማ ቱጋር ጥቃቱ የተለየ ሃይማኖትን ያላነጣጠረና ዓላማው አሸባሪዎችን መደምሰስ ብቻ እንደሆነ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
እንደ ሁኔታው አስፈላጊነቱ ታይቶ ወደፊትም ተመሳሳይ ጥቃቶች ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
ይህ የአሁኑ የአየር ጥቃት፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኅዳር ወር ውስጥ የአሜሪካ ጦር በናይጄሪያ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን ለመመከት ዝግጁ እንዲሆን የሰጡትን ትዕዛዝ ተከትሎ የመጣ እርምጃ ነው።
❤ 59👏 15🤣 11😱 7🙏 7🕊 3😍 3👍 2😁 2🏆 2😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
ተጀምሯል‼
˚🎄✩ የገና ኤክስፖ ታህሳስ 15 ተጀምሯል!˚🎄✩
💥85,000 ካሬ ላይ ያረፈ የከተማው እምብርት በሆነው ለገሀር ሳይት በሽያጭ ላይ ነን!
💥ሊኖሩበት ቢፈልጉ ሰላሚዊ መንደር፣ ሊያከራዩት ቢያስቡ በጥሩ ወጋ እና መልሰው እንኳን ቢሸጡት በደንብ የሚያተርፉበት!!
💥ባለ አንድ መኝታ (65.17ካሬ)
💥ባለ ሁለት መኝታ (108.44ካሬ)
💥ባለ ሁለት መኝታ (141ካሬ)
💥 ባለ ሦስት መኝታ (163.91ካሬ)
💥 እንዲሁም እስከ 172 - 495 ካሬ ስፋት ያላቸው ቪላ ቤቶችን በምቹ አከፋፈል በተመጣጣኝ ዋጋ ከኛ ያገኛሉ
በተጨማሪም ከ18 - 384 ካሬ ስፋት ያላቸው ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የንግድ ቦታዎችን እንደምርጫዎ አቀርብንሎት!
✍️ ከ5 - 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ
✍️ ከ 45% የባንክ ብድርጋር እስከ 25 ዓመት
✍️ በተጨማሪም እስከ 20% እንደ አከፋፈሎ ልዩ ቅናሽ ይደረግሎታል
⭐️መንደራችን በውስጥ የያዛቸው ልዩ ልዩ የጋራ መገልገያዎች:
💥 ሶስት ትላልቅ ሊፍቶች
💥 ሱፐርማርኬት ባለ 5ኮከብ ሆቴሎች የልጆች ደይ ኬር ሆሰፒታሎች የዋና ገንዳዋች
💥 አስተማማኝ ና ደህንነቱ የተጠበቀ ሰፊ የመኪና ማቆሚያ
💥 የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ መሳሪያ
💥 ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ
💥 የቆሻሻ መጣያ (Garbage shooter)
💥 ዘመናዊ የገበያ ማዕከሎች
✅ ሌሎች ሳይቶቻችን
📍በተክለ ሀይማኖት
📍በ22 ማዞሪያ
📍ሲኤምሲ
📍አያት
📍ቦሌ አትላስ
መኖር በጊፍት መንደር!
ለበለጠ መረጃ:-
☎️ 0961009336
0936755615
WhatsApp:- https://wa.me/251961009336
❤ 22👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
መረጃውን ተጠቀሙበት‼መቀመጥ ለሚያበዛ ወዳጅዎ ያጋሩት።
ረጅም ሰዓት መቀመጥ ሲጋራ ከማጨስ አይተናነስም ሲባል ሰምተዋል ?
ይህ አገላለጽ ሳይንቀሳቀሱ ለረጅም ሰዓታት መቀመጥ በጤና ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከሲጋራ ማጨስ ጋር እኩል አደገኛ መሆኑ ስለተረጋገጠ ሰዎችን ለማንቃት እያገለገለ ይገኛል።
በሥራ ምክንያት ሆነ በሌላ በቀን ከ8 ሰዓት በላይ ተቀምጠው የሚያሳልፉ ከሆነ ይህ አገላለጽ በእውነትም ሊያስጨንቆት ይገባል።
በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ረጅም ሰዓት መቀመጥን በዋናነት የሚያስከትሉትን የጤና አደጋዎች እንዲህ ይገልጹታል፦
📌 ለረጅም ሰዓት መቀመጥ የሰውነትን ስብ የማቃጠል አቅም በ90% ይቀንሳል።
📌የደም ግፊትን ይጨምራል።
📌 ከመጠን ላለፈ ውፍረት በማጋለጥ ለስኳር፣ ለልብ ህመም እና ለተለያዩ የካንሰር ዓይነት በሽታዎች ያጋልጣል።
📌 በቀን ከ6 ሰዓት በላይ ተቀምጠው የሚያሳልፉ ሰዎች፣ ከ3 ሰዓት በታች ከሚቀመጡት ጋር ሲነፃፀሩ በ15 ዓመት ውስጥ የመሞት እድላቸው በ40% ከፍ ያለ ነው።
📌 ንቁ እንቅስቃሴ አለማድረግ ለጭንቀትና ለድብርት (Depression) ተጋላጭነትን ይጨምራል።
ይህን ያህል ረጅም ሰዓት መቀመጥ አደጋ ከሆነ ምን እናድርግ ?
ልክ ሲጋራን ማቆም ለጤና ወሳኝ እንደሆነ ሁሉ፣ ለረጅም ሰዓት ያለ እንቅስቃሴ የመቀመጥ ዝንባሌያችንን ማስቀረት የህልውና ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
ለዚህም የሚከተሉት እርምጃዎች እንደ መፍትሄ መቀመጥ ይችላሉ፦
📌 ከተቻለ በ30 ደቂቃው ከወንበር ተነስቶ ለጥቂት ደቂቃዎች እንቅስቃሴ ማድረግ፤
📌 በቀን ውስጥ ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ፈጣን እርምጃ ወይም ስፖርት ማዘውተር፤
📌 ስልክ ሲደወልልዎት ወንበርዎ ላይ ከመቀመጥ ይልቅ እየተንቀሳቀሱ ማውራት፤
📌 በሊፍት ፋንታ ደረጃን መጠቀም የደም ዝውውርን ማሻሻል፤
በአጠቃላይ ወንበር ላይ ረጅም ጊዜን ማሳለፍ ልክ እንደ ሲጋራ ጢስ ቀስ በቀስ ጤናን የሚያውክ በመሆኑ፣ መንቀሳቀስ ለጤናችን ግድ መሆኑን አውቀን በጊዜ እንዘይድበት መልዕክታችን ነው።
❤ 194👍 39🤪 11😱 7😍 6💔 6😢 5🙏 4👌 3🏆 3🫡 1
ህገወጥ ናቸው‼
📌"የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ሰብዓዊ ድጋፍ በማሰባሰብ ላልተገባ ዓላማ እያዋሉ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቡ ይገባል"
📌"በረሃብ ለተጠቁት ሰዎች በሚል የሚደረጉ የድጋፍ ማሳባሰብ ዘመቻዎች ህገወጥ ናቸው።" የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር
የፌደራሉ መንግስት ህወሓትን “ ሰብዓዊ እርዳታ በመስረቅ ” ከሷል።
የፌደራሉ መንግስት “ በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በቡድንም ሆነ በተናጠል የሚደረጉ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ የአሰራር ስርዓትን የጣሱ ህገ-ወጥ አካሄዶች ” ናቸው ሲል በይኗል።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተ/ማርያም(ዶ/ር) ‛ ትህነግ ’ እያሉ የጠሩት ህወሓት “ ሕዝብን በረሃብ በመቅጣት ለፖለቲካ መሣሪያነት የመጠቀም ተግባሩን ዳግም በትግራይ ሕዝብ ላይ እያሳየ ነው ” ሲሉ በብርቱ ወንጅለዋል።
‛ የትህነግ ቡድን ’ እያሉ የጠሩት ህወሓት “ የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል በመጠለያ ማዕከላትና በልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር የሚያቀርበውን ሰብዓዊ ድጋፍ ለተፈለገው ዓላማ እንዳይወል እያደረገ እንደሚገኝ ” የጠቀሱት ኮሚሽነሩ፣ የሰሞኑ የሕጻጽ መጠለያ ጣቢያ ማስረጃ መሆኑን ለኢዜአ ነግረውታል።
ህወሓት ይህን ያደርግበታል ያሉትን ምክንያት አስረድተዋል። እሱም “ በትግራይ ክልል በመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች የሚቀርብን ሰብዓዊ ድጋፍ በመንጠቅ ” ድራማዊ ፕሮፓጋንዳ ማስተጋባት መሆኑን አመልክተዋል።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም የፌደራል መንግስት በግልጽ መረጃና ማስረጃ የሚልከው ሰብዓዊ ድጋፍ የት እንደገባ መጠየቅ አለበት ያሉት ሽፈራው “ በቡድኑ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ መደናገር እንደሌለበትም ” አሳስበዋል።
የፌደራሉ መንግስት አስተማማኝ ድጋፍ እያደረገ ነው ሲሉ የሚከራከሩት ኮሚሽነሩ ሙግታቸውንም በአሐዝ አስደግፈዋል።
በዚህም በትግራይ ክልል ከባለፈው ጥር 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታኅሳስ ወር 2018 ዓ.ም ድረስ ሁለት ሚሊየን ኩንታል በገንዘብ ሲተምን 32 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሰብዓዊ ድጋፍ መሰራጨቱን አስታውቀዋል።
ይሁንና ህወሓት “ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፉ ተደራሽ እንዳይሆን በማስተጓጎል፣ ድጋፉን ከችግረኛ ዜጎች በመንጠቅ ዳግም የሕዝብ ጠላትነቱን እያረጋገጠ እንደሚገኝም ” ጠቅሰው ኮንነዋል።
ህወሓትን በብርቱ የወነጀሉት የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው፣ በተናጠልም ሆነ በቡድን የሚደረጉ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻዎችም “ የአሰራር ሥርዓትን የጣሱ ህገወጥ አካሄዶች ናቸው ” ሲሉ ተናግረዋል።
“የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ሰብዓዊ ድጋፍ በማሰባሰብ ላልተገባ ዓላማ እያዋሉ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባም ” አሳስበዋል።via EBC
❤ 136😢 41👍 16🤣 9🤔 5😱 4🏆 3🆒 3👏 2💔 2
Photo unavailableShow in Telegram
ግብር ሊከፍሉ ነው‼
የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎችና የሶሻል ሚዲያ ነጋዴዎች ግብር ሊከፍሉ ነው‼
📌ከዩቲዩብ (YouTube)፣
📌 ከቲክቶክ (TikTok) እና ከሌሎች የዲጂታል መድረኮች ገቢ የሚያገኙ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት፣ ከሚያገኙት ገቢ ላይ ግብር እንዲከፍሉ የሚያስገድድ አሰራር እየተዘረጋ መሆኑ ተሰማ።
ባለፈው ዓመት በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት፣ በኦንላይን ይዘቶችን በማምረት ገቢ የሚያገኙ አካላት በሙሉ፦
📌በገቢዎች ቢሮ የመመዝገብ፣
📌የግብር መለያ ቁጥር (TIN) የማውጣት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ እንዳስታወቀው፣ ክፍያዎችን የሚያመቻቹ የኦንላይን መድረኮች ለእያንዳንዱ ይዘት ፈጣሪ የከፈሉትን ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ ለቢሮው ሪፖርት የማድረግ ኃላፊነት ይኖርባቸዋል።
ቢሮው ይህንን ስራ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከንግድ ቢሮ እና ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጿል።
የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ሰውነት አየለ እንደገለጹት፣ እስካሁን ከዚህ ዘርፍ የሚገኘው ግብር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በመሆኑም የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ገቢያቸውን በፈቃደኝነት እንዲያሳውቁ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ቢሮው ወደ ማስገደድ ስራ እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል።
ቁጥጥሩ ይዘት ፈጣሪዎችን ብቻ ሳይሆን፣ የተለያዩ ምርቶችንና አገልግሎቶችን በማህበራዊ ሚዲያ (Facebook, Telegram ወዘተ) የሚያስተዋውቁና የሚሸጡ ነጋዴዎችንም የሚጨምር መሆኑ ታውቋል።
Via SHEGER FM 102.1
❤ 109👏 24😁 20😱 7😍 5🏆 5😢 3🥰 1🤔 1💔 1
Photo unavailableShow in Telegram
⚠️Attention ሊሴ ገ/ማርያም ጀርባ ቤት ሽያጭ ጨርስን ጥቂት ቤቶች ቀርተዋል ይፍጠኑ
#ቴምርሪልስቴት ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ 8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው
‼️ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ጀርባ
👉2 መኝታ 93ካሬ
10% ቅድመ ክፍያ 1,069,500ብር
ሙሉ ክፍያ 10,695,000ብር
👉 2 መኝታ 100ካሬ
10% ቅድመ ክፍያ 1,150,000ብር
ሙሉ ክፍያ 11,500,000ብር
👉3 መኝታ 132ካሬ
10% ቅድመ ክፍያ 1,518,000ብር
ሙሉ ክፍያ 15,180,000ብር
👉3መኝታ 141ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,621,500ብር
ሙሉ ክፍያ 16,215,000ብር
#ልብይበሉ
🎯100% ለሚከፍል 30% ቅናሽ አለው
#ቀሪውን 90% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 40% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 20%_35% ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
❤ 21👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
“ቤተሰብን ሊያኖር የሚችል ዝቅተኛ የመነሻ ደመወዝ ወለል እንዲወሰን እየተሰራ ነው” ኢሠማኮ
በኢትዮጵያ ቤተሰብን ሊያኖር የሚችል የግል ድርጅት ሠራተኞችን ዝቅተኛ የመነሻ ደመወዝ ወለል ለማስወሰን የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አስታወቀ።
ኮንፌዴሬሽኑ ለጋዜጣ ፕላስ በሰጠው ማብራሪያ፣ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል አለመኖሩ በሠራተኛው ኑሮ ላይ እያሳደረ ያለውን ጫና ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ድሪብሳ ለገሰ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት የግል ሠራተኞች የመነሻ ደመወዝ ወለል ሳይወሰን ቆይቷል።
በአሁኑ ጊዜ ይህንን ችግር ለመፍታትና ቤተሰብን ሊያኖር የሚችል የመነሻ ደመወዝ ወለል የሚወስን ቦርድ ለማቋቋም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
የቦርዱን ማቋቋሚያ ደንብ በተመለከተ ኮንፌዴሬሽኑ አስፈላጊውን ግብዓት መስጠቱን የጠቀሱት አቶ ድሪብሳ፤ ቦርዱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተቋቁሞ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲገባ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ዝቅተኛ የመነሻ ደመወዝ ወለል መወሰኑ የሠራተኞችን ቅሬታ ከመፍታቱም ባለፈ፣ ወቅታዊውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።
❤ 92👏 67🎉 5🍌 5🏆 4🙈 4😱 3🥰 1
"...የፖለቲካም ይሁን ሌላ አላማ ካለው ግለሰብም ይሁን ድርጅት ድጋፍን አንቀበልም" አግማስ ኢትዮጵያ
አግማስ ኢትዮጵያ ተከታዩን ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥቷል።
አግማስ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከኢፌድሪ ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶት ባለስልጣን ፈቃድ ወስዶ መንቀሳቀስ ከጀመረ አራት አመታትን አስቆጥሯል።
በነዚህ አመታት ውስጥ በርካታ በጎ ተግባራትን የፈጸመና የመንግስት አጋዥም ሆኖ የቆየ ድርጅት ነው። በተለይም ተፈናቃይ ወገኖች ጋር በተያያዘ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በእለት ደራሽ ድጋፍና በቅርቡ ደግሞ በደቡብ ወሎ ሀርቡና ደጋን መጠለያ ካምፖች የዘላቂ መፍትሄ መርህን በመከተል በርካታ ወገኖችን እያደራጀ ወደ ስራ አስገብቷል።
አግማስ ኢትዮጵያ እያንዳንዱን ስራዎቹን ሲሰራ በየአካባቢው ከሚገኙ የመንግስት መዋቅር ጋር የፕሮጀክት ስምምነት ( project Agreement) በመፈራረም ነው። ከክልልም ይሁን ከፌደራል መንግስት በሚቀመጡ አቅጣጫዎች መሰረት እየሰራ የቆየ ሲሆን በዚህም ድርጅታችን ከተለያዩ የዞን ሴክተር መስሪያ ቤቶች የእውቅናና የምስጋና ሰርቲፌኬቶችን ተቀብሏል።
አግማስ ኢትዮጵያ ይህንን በጎ ተግባርና ወገኖችን በዘላቂነት ወደ ስራ የማስገባት እንቅስቃሴውን ለመደገፍ ያለመ የቀጥታ ስርጭት ( online) የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላለፉት ስድስት ቀናት ያደረገ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ላይም አንዳንድ ከድርጅታችን መርህ ጋር አብረው የማይሄዱ አካሄዶችን አይተናል።
ድርጅታችን ከፖለቲካ ከዘርና ሀይማኖት የጸዳና ገለልተኛ ሆኖ የሚሰራ በመሆኑ ምንም አይነት የፖለቲካም ይሁን ሌላ አላማ ካለው ግለሰብም ይሁን ድርጅት ድጋፍን የማይቀበል መሆኑንም ለማረጋገጥ እንወዳለን።
በዚህም መሰረት እንድህ አይነት አመለካከት ያላቸው ጉዳዮን ከድርጅታችን ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው በማረጋገጥ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብራችንንም በይፋ ማጠናቀቅና መዝጋታችንን እንገልጻለን።
አግማስ ኢትዮጵያ - ታህሳስ 16/2018
❤ 110😱 9👍 5🎉 5💔 5😍 4🕊 2🍌 2🏆 1
Photo unavailableShow in Telegram
˚🎄✩ የገና ኤክስፖ ታህሳስ 15 ይጀምራል!˚🎄✩
💥85,000 ካሬ ላይ ያረፈ የከተማው እምብርት በሆነው ለገሀር ሳይት በሽያጭ ላይ ነን!
💥ሊኖሩበት ቢፈልጉ ሰላሚዊ መንደር፣ ሊያከራዩት ቢያስቡ በጥሩ ወጋ እና መልሰው እንኳን ቢሸጡት በደንብ የሚያተርፉበት!!
💥ባለ አንድ መኝታ (65.17ካሬ)
💥ባለ ሁለት መኝታ (108.44ካሬ)
💥ባለ ሁለት መኝታ (141ካሬ)
💥 ባለ ሦስት መኝታ (163.91ካሬ)
💥 እንዲሁም እስከ 172 - 495 ካሬ ስፋት ያላቸው ቪላ ቤቶችን በምቹ አከፋፈል በተመጣጣኝ ዋጋ ከኛ ያገኛሉ
በተጨማሪም ከ18 - 384 ካሬ ስፋት ያላቸው ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የንግድ ቦታዎችን እንደምርጫዎ አቀርብንሎት!
✍️ ከ5 - 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ
✍️ ከ 45% የባንክ ብድርጋር እስከ 25 ዓመት
✍️ በተጨማሪም እስከ 20% እንደ አከፋፈሎ ልዩ ቅናሽ ይደረግሎታል
⭐️መንደራችን በውስጥ የያዛቸው ልዩ ልዩ የጋራ መገልገያዎች:
💥 ሶስት ትላልቅ ሊፍቶች
💥 ሱፐርማርኬት ባለ 5ኮከብ ሆቴሎች የልጆች ደይ ኬር ሆሰፒታሎች የዋና ገንዳዋች
💥 አስተማማኝ ና ደህንነቱ የተጠበቀ ሰፊ የመኪና ማቆሚያ
💥 የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ መሳሪያ
💥 ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ
💥 የቆሻሻ መጣያ (Garbage shooter)
💥 ዘመናዊ የገበያ ማዕከሎች
✅ ሌሎች ሳይቶቻችን
📍በተክለ ሀይማኖት
📍በ22 ማዞሪያ
📍ሲኤምሲ
📍አያት
📍ቦሌ አትላስ
መኖር በጊፍት መንደር!
ለበለጠ መረጃ:-
☎️ 0961009336
0936755615
WhatsApp:- https://wa.me/251961009336
❤ 20👏 2
ኢሳያስ አሰብን አሳልፈው ሰጡት እየተባለ ነው‼
ግብፅ በአሰብና ጅቡቲ ወደቦችን ለመገንባት ስምምነት ላይ መድረሷ ተገለፀ፡፡
ዘናሽናል ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው ግብፅ የአፍሪካ ቀንድ አካል ከሆኑት ኤርትራና ጅቡቲ ጋር ወደቦችን ለመገንባት ስምምነት ፈፅማለች፡፡
እንደዘገባው ይህ ስምምነት ግብፅ በአባይ ወንዝ ጉዳይ በገባችበት ውዝግብ በኢትዮጵያ ላይ እያካሄደች ያለው ጫና አንዱ አካል ነው፡፡ ቅርበት ያላቸው ምንጮቹን በዋቢነት የጠቀሰው ዘገባው ግብፅ እንብዛም የሚዲያ ሽፋን ባልተሰጠውና ባልተወራለት መንገድ ከሁለቱ አገራት ጋር የፈፀመችው የስምምነት ፊርማ የኤርትራውን አሰብ ወደብንና የጅቡቲውን ዶራሌ ወደብ ‹‹አቅም ማሳደግ›› የሚል መሆኑን አስረድቷል፡
፡ ሁለቱም ወደቦች በቀይ ባህር ደቡባዊ ክፍል ባብ አልመንደብ ሰርጥ አቅራቢያ የሚገኙ መሆናቸውን የጠቀሰው ዘገባው ጅቡቲና ኤርትራ የኢትዮጵያ ጎረቤቶች ከመሆናቸውም በላይ ኢትዮጵያ ሸቀጦችን የምታስገባው በዶራሌ ወደብ መሆኑን አውስቷል፡፡
ዘገባው ሲቀጥልም ‹‹ግብፅ በቀይ ባህር ላይ ከ2 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ጠረፍ ያላትና ቀይባህርንና ሜዲትራኒያንን የሚያገናኘውን ስዊዝ ካናል የተቆጣጠረች አገር ናት›› ካለ በኋላ በተደጋጋሚ እንደኢትዮጵያ ያሉ የባህር በር የሌላቸው አገራት ወደቀይ ባህር ለመዳረስ የሚያደርጉትን ጥረት ስትቃወም መቆየቷን አስረድቷል፡፡
ዘናሽናል በዘገባው ይህ ብዙ ያልተወራለት ስምምነት ከኤርትራ ጋር የተፈፀመው ከአንድ ወር በፊት ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በካይሮ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት መሆኑን አስታውቆ፣ ግብፅና ጅቡቲ ግን በከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል መፈራረማቸውን አስረድቷል፡፡
እነዚህ ስምምነቶች ከሁለቱም አገራት ጋር ጠንካራ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት የመሰረተችው ግብፅ በወደቦቹ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንድታደርግ የሚያስችላት እንደሚሆንም ገልጿል፡፡ የዘገባው ምንጭ ሲናገሩ ‹‹ይህ ስምምነት በሁለቱ ወደቦች ላይ እያደረግነው ያለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ህጋዊ መሰረት እንዲኖረው ያስችለናል›› ማለታውንም ከጋዜጣው ላይ ተመልክተናል፡፡
❤ 150😱 36😁 16😢 11🙉 11🕊 6👏 4👍 2🏆 2🎉 1😈 1
