fa
Feedback
Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

رفتن به کانال در Telegram

እንኳን ደህና መጡ‼ 📌ማስታወቂያ ለማሰራት👉 @WasuMohammed 📌 ቻናሉን ለመቀላቀል 👉 @Wasulife ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏

نمایش بیشتر
2025 سال در اعدادsnowflakes fon
card fon
240 952
مشترکین
-96724 ساعت
+9 9047 روز
+19 31230 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
ደሴ በትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል‼ ዛሬ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ደሴ ከተማ ቢለን አከባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።አደጋው የደተከሰተው አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ መንገድ ስቶ በመገልበጡ መሆኑንም ነግረውኛል።ከሟቾቹ መካከል ከት/ቤት ስትመለስ የነበረች የኬጅ ተማሪ ትገኝበታለች።ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለሁ። Wasu Mohammed - Mereja
نمایش همه...
😢 118 78😭 45💔 29
የሁለት ሰዎችን ህይወት በማጥፋት የተጠረጠረው ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል‼ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ህዳር 04 እና 05 ቀን 2018 ዓ/ም በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ቦታው 23 ቀበሌ መዝናናኛ ክበብ አካባቢ ነው፡፡ ተከሳሽ እሱ ያውቃል ቢያዝን ከባለቤቱ ከወ/ሮ ሐመልማል አለምነህ ጋር በትዳር ተጣምረው መኖር ከጀመሩ አራት ወራትን አስቆጥረዋል፡፡ ተከሳሽ ከባለቤቱ ጋር በኪራይ ከሚኖሩበት ቤት ህዳር 04 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ሲሆን ከሌላ ወንድ ጋር ስልክ ትደዋወያለሽ በሚል ቂም በቀል በመነሳሳት ሟችን አንገቷን በማነቅ ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረግ በር ዘግቶባት ከአካባቢው ለጊዜው ይሰወራል፡፡ ተከሳሹ በዚሁ ብቻ አላባቃም ከአንድ ቀን በኋላ ህዳር 05 ቀን 2018 ዓ/ም ባለቤቱን ከገደለበት መኖሪያ ግቢ ተመልሶ በመምጣት ከእዚህ ቀደም ከባለቤቱ ጋር በሚፈጠረው ፀብ ያሸማግል የነበረን አለባቸው አየለ የተባለን ጎረቤቱን በሟች ባለቤቱ ይጠረጥረው ነበርና መሳሪያ በመተኮስ በስምንት ጥይት ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ ከአካባቢው ሊሰወርም ችሏል፡፡ የወንጀሉ መፈፀም መረጃ የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራና ክትትል ክፍሉ የወንጀል ስፍራው ላይ በመገኘት የሟች አለባቸው አየለን አስከሬን በማንሳትና ከአካባቢው በሰበሰበው መረጃ መነሻነት የሟች መኖሪያ ቤት ሲከፈት የሐመልማል አለምነህ አስከሬን ሊገኝም ችሏል፡፡ ፖሊስ ከወንጀሉ መፈፀም በመነሳት ተገቢውን የሰውና የኤሌክትሮኒክስ መረጃዎችን በመከታተል ተጠርጣሪውን ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ሞላሌ ከተማ ከተደበቀበት መኖሪያ ቤት የግድያ ወንጀሉን ከፈፀመበት መሳሪያ ጋር በቁጥጥር ስር ሊያውልም ችሏል፡፡ መረጃውን ከፎቶ ጋር ያጋራው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ነው
نمایش همه...
141👏 25💔 17😱 14👍 7🥰 5😢 4🎉 1😍 1
Photo unavailableShow in Telegram
"የፀና ፍቃድ ሳይኖር የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት" አቶ ታዬ ደንደአ ጥፋተኛ በተባሉበት "የፀና ፍቃድ ሳይኖር የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት" ወንጀል የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለሕዳር 26 ተቀጠሩ‼ የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ እና የጨፌ ኦሮሚያ አባል አቶ ታዬ ደንደአ በዛሬው ዕለት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥት እና በሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት ቀርበዋል፡፡ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት የቀረቡበት ምክንያት ከዚህ ቀደም ጥፋተኛ በተባሉበት እና ችሎቱን የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት በሰማበት "የፀና ፍቃድ ሳይኖር የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት" ወንጀል ቅጣት ለመስማት ዐቃቤ ሕግ ሕዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ባቀረበባቸው ሦስት ተደራራቢ ክሶች የተከሳሽ የክስ መቃወሚዎች በክስ ለማቅረብ እና ዋስትና የሚመለከት ክርክር ለመስማት ነበር። ለዛሬ በተቀጠረው የቅጣት ውሳኔ መሰረት ችሎቱ በአቶ ታዬ በኩል የቀረቡትን የቅጣት አስተያየቶች በተለይም የጤናቸው ምክንያት በማስረጃ የቀረበበት ባለመሆኑ፤ ውሳኔው ከመሰማቱ በፊት የቅጣት ማቅለያዎችን እንዲያቀርቡ እና የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለሕዳር 26 ቀን 2018 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ጠበቃቸው አበራ ንጉሥ ተናግረዋ። በዛሬ ውሎ አቶ ታዬ ደንደአ በጠበቃቸው በኩል የ"ዋስትና መብት ይፈቀድልኝ" ጥያቄ በችሎቱ በማቅረባቸው ምክንያት ዋስትናን በተመለከተ ሰፊ የሕግ እና የፍሬ ነገር ክርክር አድርገዋል። በዚህም በጠበቃቸው በኩል ያቀረቧቸውን የክስ መቃወሚያዎች ችሎቱ ተቀብሎ ለዐቃቤ ሕግ እንዲደርሰው በማድረግ በቀረቡት የክስ መቃወሚያዎች ላይ አስተያየታቸውን በፅሑፍ እንዲያቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ለታሕሳስ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ሰጥቷል፡፡ በአቶ ታዬ በኩል የወንጀል ሥነ-ስርዓትና የሰበር ውሳኔዎች በዋቢነት በመጥቀስ ዋስትና እንዲፈቀድላቸው በመከራከሪያነት ያቀረቡ ሲሆን፤ ዐቃቤ ሕግም የዋስትና መብት ጥያቄያቸውን ውድቅ እንዲሆን በመቃወም ክርክር ያደረጉ መሆኑን ጠበቃው አብራርተዋል። ዐቃቤ ሕግ በመከራከሪያነት ያቀረበው ብቸኛ ምክንያት "አቶ ታዬ ደንደአ በ'ሆርን ኮንቨርሴሽን' ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ተከትሎ ንግግራቸው ከፍተኛ የሕዝብ ተቀባይነት ያገኘ በመሆኑ፤ ይህም በዋስ ቢወጡ ይህንን ሕዝባዊ ተቀባይነት በመጠቀም ወይም ድጋሚ በመቀስቀስ መንግሥት በሕዝባዊ ዓመፅ ለመጣል ሊንቀሳቀሱ ስለሚችሉ በእስር ሆኖው መከራከር አለባቸው" የሚል መሆኑንም ጠበቃው ገልጸዋል። በዚህም የክርክር ሂደት በሆርን ኮንቨርሴሽን ያደረጉትን ንግግር ተቀባይነት ማግኘቱን ለችሎቱ ግልፅ ለማድረግ በሚል ሀሳብ፤ በእያንዳንዱ ቪዲዮዎች የተሰጡ አንድ ሺሕ የሚሆኑ የተመልካቶች አስተያየቶች መመልከቱን ለችሎቱ አስታውቋል ግራ ቀኙን የሰማው ችሎቱ 'ዋስትና ይፈቀድላቸው' ወይንስ 'አይፈቀድላቸው' የሚለውን ጉዳይ በተመለከተ፤ ለታህሳስ 8 ቀን 2018 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ጠበቃ አበራ ንጉሥ ለአሐዱ ሬዲዬ ተናግረዋል።
نمایش همه...
😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
نمایش همه...
12😁 11🤪 1
Photo unavailableShow in Telegram
ውፍረትን ለማከም‼ የአለም ጤና ድርጅት ለውፍረትእንደ ኦዜምፒክ ያሉትን የGLP-1 የስኳር በሽታ መድኃኒቶችን መጠቀምን መከረ። ​የዓለም ጤና ድርጅት ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ቢሊዮን ሰዎችን የሚያጠቃውን ውፍረት ለማከም ለስኳር በሽታ እና ክብደት ለመቀነስ የሚያገለግሉ የመድኃኒት ክፍልፋዮችን ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው ብሏል። ከእነዚህ መድኃኒቶች አንዱ  ኦዜምፒክ ነው። ክብደት ለመቀነስ ይህን በመርፌ የሚወሰድ መድኃኒት የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። ​​የዓለም ጤና ድርጅት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ኦዜምፒክ እና ዌጎቪ  ያሉ መድኃኒቶች ለውፍረት ሕክምና እንዲታዘዙ እየመከረ ነው። እነዚህ በመርፌ የሚወሰዱ መድኃኒቶች የደም ስኳር ቁጥጥርን ያሻሽላሉ፣ የምግብ ፍላጎትን ይቀንሳሉ እንዲሁም ክብደት ለመቀነስ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። ​የመጀመሪያው የዓለም ጤና ድርጅት በግሉካጎን መሰል ፔፕታይድ-1 (GLP-1) ሕክምናዎች ላይ ያወጣው መመሪያ፣ ሴማግሉታይድን  የመሰሉ መድኃኒቶችን የሚያካትት ሲሆን፣ ውፍረት ላለባቸው አዋቂዎች ይመክራቸዋል። ፍትሐዊ ተደራሽነት እንዲኖር ያበረታታል እንዲሁም በአስፈላጊ መድኃኒቶች ዝርዝር ውስጥ ያካትታቸዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ይህ ሞዴል ዝርዝር በአሁኑ ጊዜ መሰረታዊ እና ሁለንተናዊ የጤና ስርዓት ለማግኘት ድርጅቱ አስፈላጊ ናቸው ብሎ የሚያምንባቸውን 532 ሕክምናዎች ይዟል። ​ሰኞ ዕለት የጸደቀው የዓለም ጤና ድርጅት አቋም፣ የጤና ስርዓቶች የህዝብ ፖሊሲዎቻቸውን እንዲመሩ በመርዳት ለእነዚህ መድኃኒቶች ተደራሽነት እንዲሻሻል ያበረታታል።via:- Fontenina #ዋሱመሐመድ አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
نمایش همه...
66👏 8👍 4🥰 4😱 2🙉 2🏆 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዶ/ር አብዱ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት ደሴ ስልክ  0937411111           0938411111 ሊንክ: https://t.me/+ACPCPoXDK4JlMjA0
نمایش همه...
9
Photo unavailableShow in Telegram
ውፍረትን ለማከም‼ የአለም ጤና ድርጅት ለውፍረትእንደ ኦዜምፒክ ያሉትን የGLP-1 የስኳር በሽታ መድኃኒቶችን መጠቀምን መከረ። ​የዓለም ጤና ድርጅት ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ቢሊዮን ሰዎችን የሚያጠቃውን ውፍረት ለማከም ለስኳር በሽታ እና ክብደት ለመቀነስ የሚያገለግሉ የመድኃኒት ክፍልፋዮችን ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው ብሏል። ከእነዚህ መድኃኒቶች አንዱ ኦዜምፒክ ነው። ክብደት ለመቀነስ ይህን በመርፌ የሚወሰድ መድኃኒት የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። ​​የዓለም ጤና ድርጅት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ኦዜምፒክ እና ዌጎቪ ያሉ መድኃኒቶች ለውፍረት ሕክምና እንዲታዘዙ እየመከረ ነው። እነዚህ በመርፌ የሚወሰዱ መድኃኒቶች የደም ስኳር ቁጥጥርን ያሻሽላሉ፣ የምግብ ፍላጎትን ይቀንሳሉ እንዲሁም ክብደት ለመቀነስ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። ​የመጀመሪያው የዓለም ጤና ድርጅት በግሉካጎን መሰል ፔፕታይድ-1 (GLP-1) ሕክምናዎች ላይ ያወጣው መመሪያ፣ ሴማግሉታይድን የመሰሉ መድኃኒቶችን የሚያካትት ሲሆን፣ ውፍረት ላለባቸው አዋቂዎች ይመክራቸዋል። ፍትሐዊ ተደራሽነት እንዲኖር ያበረታታል እንዲሁም በአስፈላጊ መድኃኒቶች ዝርዝር ውስጥ ያካትታቸዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ይህ ሞዴል ዝርዝር በአሁኑ ጊዜ መሰረታዊ እና ሁለንተናዊ የጤና ስርዓት ለማግኘት ድርጅቱ አስፈላጊ ናቸው ብሎ የሚያምንባቸውን 532 ሕክምናዎች ይዟል። ​ሰኞ ዕለት የጸደቀው የዓለም ጤና ድርጅት አቋም፣ የጤና ስርዓቶች የህዝብ ፖሊሲዎቻቸውን እንዲመሩ በመርዳት ለእነዚህ መድኃኒቶች ተደራሽነት እንዲሻሻል ያበረታታል።via:- Fontenina
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
አንድ ዶላር 154.3993 ብር ተሽጧል‼ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ የተካሄደውን የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አካሂዷል።ለጨረታው 50ሚሊየን ዶላር ቀርቧል። የጨረታው አሸናፊ የጨረታ ዋጋ በአማካይ 154.3993 ብር ሲሆን በአጠቃላይ 17 ባንኮች የጠየቁትን የውጭ ምንዛሪ በጨረታ መውሰዳቸውን ባንኩ አስታውቋል።
نمایش همه...
65👏 14😱 11🙈 10🙏 3😍 3🕊 1😭 1
Update ከሰሞኑ ደሴ ከተማና አካባቢው መብራት በፈረቃ ሲሰጥ ነበር።ምክንያቱ በኮምቦልቻ ቁጥር -1 ሰብስቴሽን አንዱ ትራንስፎርመር ላይ በተፈጠረ የቴክኒክ ችግር ምክንያት የሀይል መቆራረጥ ስላጋጠመ እንደነበር ተነግሯል።አሁን ላይ በአካባቢው በከፊል ተቋርጦ የቆየውን የኤሌክትሪክ ኃይል በዛሬው ዕለት ሙሉ በሙሉ መመለስ መቻሉን የሰሜን ምስራቅ 1 ሪጅን እወቁልኝ ብሏል።
نمایش همه...
105👏 29👍 20🙏 18🙊 9🙉 8 5🏆 1
Photo unavailableShow in Telegram
ህፃን ልጅ በቆራልዮ ማዳበሪያ ውስጥ ተጠቅልሎ ለማምለጥ‼ 📌ወላጆች ለጥንቃቄ ተጠቀሙበት‼ ይህ  ዛሬ ህዳር 23/2018 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ገደማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላ ዞን ጊዶሌ ከተማ ያጋጠመ ክስተት ነው። ግለሰቡ ቆራሊዮ እያለ በየሰፈሩ ሲዞር ከቆዬ በኋላ በከተማው አርጉባ ቀበሌ ገርሞሃ ከተባለ ሰፈር በምስሉ ላይ የሚታየውን ህፃን ልጅ በቆራልዮ ማዳበሪያ ውስጥ ተጠቅልሎ ለማምለጥ ሰሞክር በህብረተሰቡ ጥቆማ በፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የደራሼ ወረዳ አስታውቋል። ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲጠብቁና አጠራጣሪ ነገር በሰፈራቸው ሲያዩ ለፖሊስ እንዲጠቁሙ መልዕክት ተላልፏል።
نمایش همه...
75😢 65👍 21😱 15💔 8😭 6🎉 5
ህፃን ልጅ በቆራልዮ ማዳበሪያ ውስጥ ተጠቅልሎ ለማምለጥ‼ 📌ወላጆች ለጥንቃቄ ተጠቀሙበት‼ ይህ ዛሬ ህዳር 23/2018 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ገደማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላ ዞን ጊዶሌ ከተማ ያጋጠመ ክስተት ነው። ግለሰቡ ቆራሊዮ እያለ በየሰፈሩ ሲዞር ከቆዬ በኋላ በከተማው አርጉባ ቀበሌ ገርሞሃ ከተባለ ሰፈር በምስሉ ላይ የሚታየውን ህፃን ልጅ በቆራልዮ ማዳበሪያ ውስጥ ተጠቅልሎ ለማምለጥ ሰሞክር በህብረተሰቡ ጥቆማ በፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የደራሼ ወረዳ አስታውቋል። ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲጠብቁና አጠራጣሪ ነገር በሰፈራቸው ሲያዩ ለፖሊስ እንዲጠቁሙ መልዕክት ተላልፏል።
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ 8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው #ቴምርሪልስቴት አሁን ደግሞ በተለያዩ ሳይቶቻችን ላይ እስከ 35% ልዩ ቅናሽ ላይ ነን #ይፍጠኑ ‼️ተክለሀይማኖት ሆስፒታል ፊት ለፊት 🎯የክፍያ አማራጭ 70/30 👉3 መኝታ 110ካሬ ሙሉ ክፍያ 8,547,000 ብር 🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ 👉3 መኝታ 110ካሬ      10%ቅድመ ክፍያ 1,210,000ብር      ሙሉ ክፍያ 12,100,000ብር ‼️ሀይሌጋርመንት African CDC ፊት ለፊት   🎯የክፍያ አማራጭ 70/30 👉3 መኝታ 139ካሬ 10,216,500ብር ሙሉ ክፍያ 🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ 👉 ባለ 3መኝታ (139ካሬ) ሙሉ ክፍያ = 14,595,000ብር ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,500ብር ) ‼️አያት 🎯 65/35 የክፍያ አማራጭ 👉3 መኝታ 111 ካሬ ሙሉ ክፍያ 7,936,500ብር 🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ 👉3 መኝታ 111ካሬ 10% ቅድመ ክፍያ 1,221,000ብር ሙሉ ክፍያ 12,210,000ብር ‼️አያት ፈረስ ቤት 🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ 👉3 መኝታ 108ካሬ 6,669,000ብር ሙሉ ክፍያ 6,669,000ብር ሙሉ ክፍያ 🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ 👉3 መኝታ 108ካሬ 10%ቅድመ ክፍያ ሙሉ ክፍያ 10,260,000ብር ቅድመ ክፍያ 1,026,000ብር     #ልብይበሉ ቀሪውን 90% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት * 40% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 20%_35% ቅናሽ አዘጋጅተናል                ለበለጠ መረጃ ይደውሉ        👇👇👇👇👇👇      +251939770177      +251996856273 https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant WhatsApp. https://wa.me/251939770177
نمایش همه...
26👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጋር "ተጨማሪ ውይይት" እንደማይደረግ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብዲላቲ ተናገሩ። ከቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ላለፉት 13 ዓመታት የተደረጉ ውይይቶች "አንዳችም መፍትሔ" አላመጡም ብለዋል። የሕዳሴ ግድቡ ከተመረቀ በኋላ በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል ያለው ግንኙነት "የበለጠ መሻከሩን" ጠቅሰው፤ በዚህ መካረር ምክንያት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ "ስጋት ሊሰማው" እንደሚገባም ተናግረዋል። ባለፉት 13 ዓመታት በአገራቱ መካከል የተደረገው ውይይት ውጤት ባለማስገኘቱ፤ ግብፅ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት "የውሃ ደኅንነቷን እንደምታስከብር" አክለዋል። ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ ጋር የተደረጉ ውይይቶች ምንም ውጤት ባለማስገኘታቸው "በቀጣይም ንግግር ማድረግ አስፈላጊ አይደለም" ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ። የግድቡ ጉዳይ "ከኢትዮጵያጋር ካለን የሁለትዮች ግንኙነት ጋር የሚያያዝ ነው" ያሉት ሚኒስትሩ፤ ግድቡን "እንደተናጠል እርምጃ ነው የምንቆጥረው" ብለዋል። አክለውም "ሕገ ወጥ ነው" ሲሉ የመንግሥታቸውን አቋም አንጸባርቀዋል። ግድቡን "ከዓለም አቀፍ ሕግ ጋር የሚጣጣም አይደለም" ሲሉ የገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ "ዓለም አቀፍ ሕግ በግልጽ እንደሚለው ማንኛውም ድንበር ተሻጋሪ ወንዝ በዓለም አቀፍ ሕግ መርሆዎች መመራት አለበት። ይህም ማለት ማሳወቅን እና ጉዳት አለማስከተሉን ማረጋገጥ ያስፈልጋል" በማለት አብራርተዋል። ከአንድ ወር በፊት ግብፅ ብሔራዊ ጥቅሟን እና የውሃ ደኅንነቷን ለማስጠበቅ "አስፈላጊ የሆኑ ሁሉንም እርምጃዎች እንደምትወስድ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ መናገራቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ በሰጠችው ምላሽ፤ ግብፅ "ሕገ ወጥነት እና የበላይነት በተሞላው መንገድ" የዓባይ ወንዝን ለመቆጣጠር መሞከሯን ቀጥላለች ብላለች። አል ሲሲ፤ ግብፅ በዲፕሎማሲ እና እንደ መንግሥታቱ ድርጅት ባሉት ዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ መተማመኗ እንደ ድክመት መቆጠር የለበትም ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ፤ ኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በማስተዳደር ረገድ እየተከተለች ያለውን "ኃላፊነት የጎደለው" አካሄድ አገራቸው "እጇን አጣጥፋ አትመለከትም" ብለዋል። የኢትዮጵያ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሰጠው ምለሽ፤ "ኢትዮጵያ በዓባይ የመጠቀም መብቷን አሳልፋ እንደማትሰጥ" አስረግጧል። "ከኢትዮጵያ ጠላቶች በኩል በእጅ አዙር ጫና ቢበረታም" የኢትዮጵያ ዕድገት "አይቀለበስም" ሲልም አክሏል። (ቢቢሲ) Wasu Mohammed - Mereja
نمایش همه...
126🤣 37👍 19👏 6🎉 4🕊 2🙈 2 1😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
Ads. ይህ ከስር ያለው ሚስጥሮች የሚወጡበት ወሳኝ ቻናል ነው።ገብተው ሰብስክራይብ ካደረጉ አነጋጋሪ መረጃዎችን በቅድሚያ ያገኛሉ።👇 https://www.youtube.com/channel/UCmFPL7JZ5i5utdYQXcnPRQw https://www.youtube.com/channel/UCmFPL7JZ5i5utdYQXcnPRQw
نمایش همه...
10
Photo unavailableShow in Telegram
በእሳት አደጋ የሶስት ህፃናት ህይወት አለፈ‼ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ስልጤ ዞን በተከሰተ እሳት አደጋ የሶስት ህፃናት ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። አደጋው ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ሚቶ ወረዳ በሰሶ ቆሻሜ ቀበሌ ቀጠና ሁለት ተብሎ በሚጠራዉ መንደር እንደተከሰተ ያስታወቀው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፓሊስ የአደጋው ዝርዝር መረጃ እንደሚገልፅ በፌስቡክ ገፁ ላይ አመልክቷል። Wasu Mohammed - Mereja
نمایش همه...
😢 56 39😱 6💔 6👍 2🙉 2
Photo unavailableShow in Telegram
9
ድንበር ተሻጋሪ ግዳጅ‼ ‹‹አየር ኃይል የሚገነባው ለሰፈር ግዳጅ አይደለም፤ ድንበር ተሻጋሪ ግዳጆችን ማሰብ አለብን›› ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ በፋና ቴሌቪዥን ካደረጉት ቃለመጠይቅ የተወሰደ
نمایش همه...
👍 67 49😁 33🤣 11🎉 3🏆 3😱 2🕊 2🙈 2👏 1
📍አድራሻ - በመሀል ከተማ በኮሊደር ልማቷ ባሸበረቀችው  ለቡ ማብራት-ሀይል 💥ሊኖሩበት ቢፈልጉ ሰላሚዊ መንደር፣ ሊያከራዩት ቢያስቡ በጥሩ ወጋ እና መልሰው እንኳን ቢሸጡት በደንብ የሚያተርፉበት!! 💥ስቱዲዮ (59 ካሬ) በ 260ሺህ ብር 💥ባለ አንድ መኝታ (77.3ካሬ) በ 341ሺህ ብር 💥ባለ ሁለት መኝታ (127.2ካሬ) በ 561ሺህ ብር 💥ባለ ሦስት መኝታ (150.5 ካሬ) በ 664ሺህ ብር 💥 ባለ አራት መኝታ (194 ካሬ) በ 855 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ 💥 እንዲሁም እስከ 295ካሬ ስፋት ያላቸው ፔንትሃውስ ቤቶችን በምቹ አከፋፈል በተመጣጣኝ ዋጋ ከኛ ያገኛሉ በተጨማሪም  ከ27 - 190 ካሬ ስፋት ያላቸው ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የንግድ ቦታዎችን እንደምርጫዎ አቀርብንሎት! ✍️ በ10% ቅድመ ክፍያ ብቻ ✍️ ከ 60% የባንክ ብድርጋር እስከ 25 ዓመት ✍️ በተጨማሪም እስከ 35%  እንደ አከፋፈሎ ልዩ ቅናሽ ይደረግሎታል ✍️ ሁሉም ቤቶች ተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል, ስቶር እና የላውንድሪ ክፍሎች ያሏቸው። ✍️ መንደራችን በውስጥ የያዛቸው ልዩ ልዩ የጋራ መገልገያዎች: 💥 አራት የመንገደኞች እና አንድ የእቃ አሳንሰር 💥 አምስት የዋና ገንዳዋች 💥 አስተማማኝ ና ደህንነቱ የተጠበቀ ሰፊ የመኪና ማቆሚያ 💥 የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ መሳሪያ 💥 ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ 💥 የቆሻሻ መጣያ (Garbage shooter) 💥 ዘመናዊ የገበያ ማዕከሎች @Dmcreales ለበለጠ መረጃ ☎️ 0940625843
نمایش همه...
3.52 MB
21😱 2👍 1👏 1
የመንግስት ሠራተኞች ግብር‼ ከፍተኛ ግብር የሚጣልባቸው የመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ ከ150,000 ብር ጀምሮ እንዲሆን ተጠየቀ‼ 📌የሠራተኞች መነሻ የደመወዝ ወለል 8,384 ብር እንዲሆን ጥያቄ ቀርቧል። 📌 መንግሥት መነሻ ወለል ከ1,200 እስከ 2,000 ብር በሚል ረቂቅ አዋጅ አቅርቧል‼ ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ 8,384 ብር የሆነ ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን ገለጸ፡፡ የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለሪፖርተር እንዳሉት፣ ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ 8,384 ብር የሆነ ተቀጣሪ ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲደረጉ ለመንግሥት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በሥራ ላይ ቆይቷል የተባለውን የገቢ ግብር አዋጅ 979/2008ን ለማሻሻል ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ከተባሉ ባለድርሻዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እስከ ሁለት ሺሕ ብር የሚከፈላቸው ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ ተደንግጓል፡፡ ኢሠማኮ እስከ 8,384 ብር ድረስ የሚከፈላቸው ተቀጣሪዎች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ ለገንዘብ ሚኒስቴር በደብዳቤ እንደጠየቀ አስታውቋል፡፡ አቶ ካሳሁን በዓለም ባንክ መረጃ መሠረት ዕለታዊ ገቢው ከሦስት ዶላር በታች የሆነ ሰው ደሃ በመሆኑ፣ የመንግሥት የገቢ ግብር በዚህ ወለል ሥር ያሉ ተቀጣሪዎችን ታሳቢ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡ በማናቸውም ቀጣሪ ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞች በወር ከ8,384 ብር እስከ 22,974 ብር ደመወዝ የሚያገኙ ሠራተኞች፣ አሥር በመቶ ግብር እንዲጣልባቸው መንግሥትን መጠየቁን ኢሠማኮ ገልጿል፡፡ ከ22,975 እስከ 44,530 ብር ወርኃዊ ደመወዝ ተከፋዮች የ15 በመቶ፣ ከ44,531 እስከ 72,336 ብር የሚከፈላቸው ደግሞ 20 በመቶ፣ እንዲሁም ከ72,337 እስከ 107,449 ብር የ25 በመቶ ግብር እንዲጣልባቸው ኢሠማኮ በደብዳቤው አሳስቧል፡፡ ከ107,450 እስከ 150,107 ብር ድረስ የሚከፈላቸው ሠራተኞች 30 በመቶ ግብር፣ እንዲሁም 150,108 ብር እና ከዚያ በላይ የሚከፈላቸው ተቀጣሪ ሠራተኞች ደግሞ 35 በመቶ ግብር እንዲከፍሉ ለመንግሥት ባቀረበው ደብዳቤ ኢሠማኮ መጠየቁን ገልጿል፡፡ አሁን በሥራ ላይ ባለው የሠራተኞች የገቢ ግብር አዋጅ መሠረት እስከ 600 ብር ድረስ የሚከፈላቸው ሠራተኞች ከግብር ነፃ ሲሆኑ፣ ከ10,900 ብር ጀምሮ ደግሞ 35 በመቶ ግብር እንዲከፍሉ ይገደዳሉ፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ከአንድ ሳምንት በፊት ለውይይት ይፋ ባደረገው የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ 1,200 ብር፣ 1,600 ብር እና 2,000 ብር ወርኃዊ ደመወዝተኞች ከግብር ነፃ እንዲደረጉ ድንጋጌ መኖሩ ይታወሳል፡፡ የመንግሥት የገቢ ግብር ማሻሻያው ሠራተኞች ያለባቸውን ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ ታሳቢ ያላደረገ እንደሆነ የተለያዩ የውይይት ተሳታፊዎች አስተያየት መስጠታቸው አይዘነጋም።
نمایش همه...
300👍 53😢 11🥴 10🏆 9🤝 7🙏 6🎉 3👀 3😍 2👏 1
ለዘንድሮው ሀጅ 740 ሺህ ብር ተጠይቋል‼ የኢትዮጵ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ1447 ዓ.ሒ ወይም የ2018 ዓ.ል የሐጂ አገልግሎትን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥቷል፡፡ መግለጫውን በንግግር የከፈቱት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከዲያስፖራ ሙስሊሞች ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል አንዱ የሆነው በሀገራቸው በኩል ሀጅ የማድረግ ፍላጎት ምላሽ እንዲያገኝ ያከናወናቸው ተግባራት ውጤት ለማምጣት በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛል ብለዋል። ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅ አገልግሎትና መስተንግዶውን እንግልት አልባ ለማድረግ የምዝገባ ማዕከላትን በቴክኖሎጂ እና በሰለጠነ የሰው ኃይል ማደራጀትን ጨምሮ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲያከናወኑ መቆየቱ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሀጅ አገልግሎት እና መስተንግዶ አሰጣጡን ከማዘመን ባሻገር ተደራሽ ለማድረግም ሰፊ ስራ የተሰራ ሲሆን ለአገልግሎትና መስተንግዶ የሚከፈለው ዋጋ ከብር የመግዛት አቅም መቀነስ ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳይጨምር አስፈላጊ ስራዎች ስለመሰራታቸው ተብራርቷል፡፡ ጠቅላይ መክር ቤቱ ግልጽ ጨረታ በማውጣት በሳዉዲ አረቢያ አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶች በስፋት እንዲወዳደሩ ማድረጉ የክፍያ ዋጋው ከዶላር አንፃር ቅናሽ እንዲያሳይ አስችሏልም ብሏል፡፡ ብር ከዶላር አንፃር ያለው የምንዛሪ ዋጋ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተዳከመ በመሆኑ የሐጅ አግልጎት ክፍያው ከብር አንጻር እንዲጨምርም እንዳስገደደም ነው በመግለጫው የተገለጸው። በዚህ መሰረት የሀጅ አገልግሎት ከባለፈው ዓመት በ693 ዶላር እንዲቀንስ ቢደረግም የብር አቅም በመዳከሙ ብቻ የክፍያ ዋጋው ወደ 7 መቶ 40 ሺህ ብር ከፍ ሊል እንደቻለ ተጠቅሷል። ጠቅላይ ምክር ቤቱ ህዝበ ሙስሊሙ በሀሰተኛ መረጃዎች ሳይስተጓጎል ከዛሬ ኅዳር 22/ 2018 ዓ.ል ጀምሮ በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች እየሄደ እንዲመዘገብም ጠይቋል፡፡ መግለጫውን የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ አባልና ዋና ጸሀፊ ዑስታዝ ተምኪን አብዱላሂ በአማርኛ፣ የስራ አስፈጻሚ በአላልና የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠሪ ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ በኦሮምኛ እንዲሁም የስራ አስፈጻሚ አባልና ምክትል ፕሬዝደንት ሸይኽ ጁነይድ ሀምዛ በሶማሊኛ ቋንቋዎች ለመገናኛ ብዙሀን ቀርቧል። የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
نمایش همه...
148😱 47👍 28😭 14😁 9💩 7😍 7🙊 7🏆 3🔥 1