fa
Feedback
ATC NEWS

ATC NEWS

رفتن به کانال در Telegram

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA ለመልዕክት 👇🏻 @mujaabot For Advertisement👇🏿 @atcads

نمایش بیشتر
2025 سال در اعدادsnowflakes fon
card fon
127 455
مشترکین
-6624 ساعت
-2667 روز
-76830 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
በኬንያ የትልልቅ ድርጅቶች ስራ አስፈፃሚዎች ከመምህራን በ214 እጥፍ የተሻለ ክፍያ ያገኛሉ ተባለ። የኬንያ አስር ግዙፍ ድርጅቶች ዋና ስራ አስፈፃሚዎች በአማካይ ከኬንያ መምህራን በ214 እጥፍ የተሻለ ክፍያ እንደሚያገኙ ኦክስፋም ኬንያ አስታውቋል። ኦክስፋም አክሎም፥ ለዋና ስራ አስፈፃሚዎቹ የሚደረገው አማካይ የክፍያ ጭማሪ ከአስተማሪዎቹ የ6 አመት ደመወዝ ጋር እኩል መሆኑንም ገልጿል። በተጨማሪ በኦክስፋም ሪፖርት በኬንያ የሚገኙ 125 ሃብታሞች ከ77 በመቶው ወይም 42.6 ሚሊየን ህዝብ የበለጠ ሃብት እንዳላቸው ተመላክቷል። ከ2019-2023 ባለው ጊዜም 1% የሚሆኑት ሃብታሞች የሃገሪቱን ሁለት አምስተኛ ሃብት እንደያዙና የነዚህ 1% ሃብታሞች ሃብት ከቀሩት 99% አንፃር በእጥፍ ማደጉ ተነግሯል። እነዚህ 1% ሃብታሞችም የሃገሪቱን የፋይናንስ ሃብት 78% መያዛቸው ሲነገር ከ2015 ወዲህም በከፍተኛ ድህነት የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር በ7 ሚሊየን መጨመሩ ተነግሯል። በ125ቱ የኬንያ ሃብታሞች የተያዘው ሃብት ወደ 100 ሽልንግ የመገበያያ ገንዘብ ቢቀየር ሙሉ የናይሮቢ ግዛትን እንደሚሸፍን የኦክስፋም ሪፖርት አሳይቷል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ ጤና ሚኒስቴር የማርበርግ ቫይረስ ዝግጁነት #የኦንላይን ትምህርት ለጤና ባለሙያዎች መስጠት ጀምሯል። ይመዝገቡ 👇 https://cpd.moh.gov.et/cpd/course/view.php?id=112 የኦንላይን ስልጠናውን ይውሰዱ! ዝግጁነትዎን ይጨምሩ! ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
Join Ethiopia's premier competitive programming hackathon. A full-day, on-site event dedicated to advanced problem-solving, data structures and algorithms. Form a team of three and compete in divisions open to both advanced (Elite) and intermediate (Open) coders for national recognition and exciting prizes! 🏆 🗓 ቅዳሜ, ኅዳር 27 2018 (December 6, 2025) ⏰ 3፡00 - 11፡00 ሰአት (9:00 AM – 5:00 PM) 📍 CapStone ALX Tech Hub, Lideta 🔗 Register now: https://luma.com/9pobz8sd #ALXEthiopia #CodeLeagueEthiopia #CompetitiveProgramming #DSA #dohardthings #ALXAfrica #lifeatALX
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#WolkiteUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ሁለት መጠኑ 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ ብሔራዊ የፋይዳ መታወቂያ (National ID)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#AksumUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ በተጠቀሱት ቀናት አክሱም ከተማ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ተብሏል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ አራት 3x4 የሆነ የቅርብ ፎቶግራፍ፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ተጨማሪ! ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የመምህርነት ሙያን መቀላቀል ለሚፈልጉ የአንድ ዓመት ስልጠና ለመስጠት ምዝገባ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስልጠናው ይሰጣል ከተባለባቸው አምስት ዩኒቨርሲቲዎች በተጨማሪ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እንደሚሰጥ ተገልጿል። የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መመዝገቢያ ሊንክ 👇  https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdRwj89yQ50AiUeZZeDe8tr8aJ5GQZO4B0IqUVJzJJCNJzWPQ/viewform ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#AAU 75ኛ የምስረታ ዓመቱን እያከበረ የሚገኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቀድሞ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡ ዩኒቨርሲቲው 75ኛ የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን በተያዘው ህዳር እና ታህሳስ ወር በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች እንደሚያከብር መግለፁ ይታወቃል። የበዓሉ አካል የሆነ የባለድርሻ አካላት ውይይት እየተደረገ ሲሆን፤ ቅዳሜ ህዳር 20/2018 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲዎች የእግር ኳስ ውድድር ይጀመራል ተብሏል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ75 ዓመታት ጉዞ የተሰነደበት መፅሐፍ ይመረቃል፡፡ የተቋሙን አጠቃላይ ጉዞ እና የወደፊት ርዕይ የሚያስቃኝ ዘጋቢ ፊልም እየተዘጋጅ መሆኑም ተጠቁሟል። የፓናል ውይይቶች፣ ሴሚናሮች፣ የእግር ጉዞ እና ሌሎች በርካታ ኹነቶች እንደሚካሔዱ ተገልጿል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከታህሳስ 18-24/2018 ዓ.ም ለሚከበረው የቀድሞ ተማሪዎች ሳምንት (Alumni Week) በመላው ዓለም ለሚኖሩ የቀድሞ ተማሪዎቹ ጥሪ አቅርቧል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ምሩቃን በ https://alumni.aau.edu.et/register ድረ-ገፅ በመግባት መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ያመልክቱ! ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የመምህርነት ሙያን መቀላቀል ለሚፈልጉ የአንድ ዓመት ስልጠና ለመስጠት ምዝገባ መጀመሩ ይታወቃል፡፡ ስልጠናው በተመረጡ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ ስልጠናውን በቀን መርሐግብር የሚወስዱ ተማሪዎች የትምህርት ወጪያቸው ሙሉ ለሙሉ በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገልጿል። የምዝገባ ጊዜ፦ ከህዳር 16/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ኦንላይን የመመዝገቢያ ሊንኮች፦ ➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.ju.edu.et ➫ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.hu.edu.et/Home/AvailablePrograms ➫ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/6t1BNV9S67oXwzBv9 ➫ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/Y7Hksp5Ymk7Nx7d9A ➫ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፦ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfQcnu1ThOSSsUp9d3XI80NszyyETOwtJPxWNRh68izA7Gd2A/viewform?usp=header ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#DebarkUniversity ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመከታተል ወደ ተቋሙ ለተመደቡ ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል፡፡ ለህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም አድርጎት የነበረውን ጥሪ ያራዘመው ዩኒቨርሲቲው፤ የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 16 እና 17/2018 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል፡፡ ትምህርት ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#InjibaraUniversity በ2018 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) በትምህርት ሚኒስቴር ወደ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከታህሳስ 09-10/2018 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3×4 የሆነ ሁለት ፎቶግራፍ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#BahirDarUniversity ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝ የኒቨርሲቲነት ለመሸጋገር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገለፀ፡፡ ራስ ገዝ እንዲሆኑ በመንግሥት ከተለዩ አስር ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አንዱ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ለመሆን የሚያስችለውን የተሟላ ዝግጅት ማድረጉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው የሰው ኃይል ስምሪት፣ ሃብት የማመንጨት አቅም፣ አስተዳደራዊ መዋቅር እና ሌሎች ተግባራትን በማካተት የደረሰበትን ውጤት ለትምህርት ሚኒስቴር መላኩን ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል። ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው ፈቃድ መሰረት ዩኒቨርሲቲው የራስ ገዝነት አሰራሩን ተቀብሎ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#DebreBerhanUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመከታተል የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ በተመደባችሁበት ካምፓስ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ሁለት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#DebreMarkosUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመከታተል የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሆናችሁና የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A-L የሚጀምር እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የሆናችሁና የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A-B የሚጀምር በቡሬ ካምፓስ፤ ሌሎች የተፈጥሮ ሳይንስና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ10ኛ ክፍል እና የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቃችሀብት ውጤት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ስምንት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመጀመሪያ መንፈቀ-ዓመት መረጃን በተዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርት የመረጃ ስርዓት (HEMIS) እንዲያስገቡ አሳስቧል፡፡ በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ህዳር 16/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ ሰርኩላር፥ ሁሉም ተቋማት መረጃቸውን በተዘጋጀው ሲስተም ላይ የማስገባት ግዴታ እንዳለባቸው ይገልጻል። በመሆኑም የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው መንፈቀ-ዓመት ሁሉም መረጃዎች ተሟልተውና በየተቋሙ አመራር ተረጋግጠው እስከ ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም በሲስተሙ (http://hemis.ethernet.edu.et) እንዲያስገቡ ጠይቋል፡፡ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ይህን ተከታትሎ የማስፈፀም ኃላፊነት እንደተሰጠው የተገለፀ ሲሆን፤ መረጃውን የማያስገቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመንግሥት በሚሰጡ አገልግሎቶች እንደማይስተናገዱ ተጠቁሟል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#WerabeUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3×4 የሆነ ሁለት ፎቶግራፍ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ከህዳር 21 እስከ ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም ድረስ registrar.wru.edu.et የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የተጠየቁ መረጃዎችን እንድትሞሉ ይጠበቅባችኋል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
نمایش همه...