fa
Feedback
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

رفتن به کانال در Telegram

Journalist-at-large

نمایش بیشتر
2025 سال در اعدادsnowflakes fon
card fon
133 768
مشترکین
-1024 ساعت
-1197 روز
-58130 روز
آرشیو پست ها
በሚያንማር ያሉ ዜጎችን ካሉበት ቦታ ለማውጣት ለሚያስፈልገው የባስ ትራንስፖርት ወጪ መንግስት ክፍያ ለመፈፀም ስላልቻለ ቤተሰቦቻቸው እስከ 20 ሺህ ዶላር እንዳዋጡ ሰማሁ። "እንደዛም ተከፍሎ የመንግስት ልኡክ ቡድን ስለሚያስፈልግ እየጠበቅናቸው ነው፣ ግን ለእሱም እየተግደረደሩ ነው" ያሉኝ እዛው ያሉ ዜጎቻችን ናቸው። ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች እንኳን ሰዎቻቸውን በአውሮፕላን አጓገዘው ከጨረሱ ሰነባብተዋል፣ የእኛዎቹ ለባስ ክፍያ ለመክፈል እና አቀባበል ለማድረግ የሉም። በዚህ መልኩ ወደ ሀገራቸው ሲገቡ "መንግስት ባደረገው የተቀናጀ እና የተሳለጠ እንቅስቃሴ ለሀገራቸው በቁ" ተብሎ መዘገቡ አይቀርም። @EliasMeseret
نمایش همه...
😢 489👍 63😁 43 16🤔 13😱 9🕊 4
Photo unavailableShow in Telegram
የፍትህ ስርዐታችን እዚህ ደርሷል! በእኔ እድሜ ኢትዮጵያ ውስጥ የፍትህ የበላይነት ተረጋግጦ እና ሁሉም ከህግ በታች ሆኖ አላየሁም፣ በዚህ ደረጃ ግን ወርዶ አየዋለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም። ያሳዝናል! ዜናውን ያንብቡ: https://t.me/meseretmedia/934 @EliasMeseret
نمایش همه...
😢 722👍 208😁 38 24🤔 20😱 10🙏 3
Photo unavailableShow in Telegram
አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ላሉ ዜጎቹ ⤵️ "ለግል ደህንነታችሁ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳትረሱ... እንደ ሰልፍ ያሉ ህዝብ ከሚሰበሰቡባቸው ስፍራዎች ራቁ" የፌደራል ፖሊስ በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፁ ፖስቱ ስር የሰጠው አስተያየት ⤵️ "ደርሶኛል" 🤔🤔 @EliasMeseret
نمایش همه...
😁 1 423🤔 165👍 115 35😱 31🙏 21🕊 9😢 3
#በነገራችንላይ በግሌም ሆነ #መሠረትሚድያ ላይ የሚቀርቡ መረጃዎች ለመንግስት አካላት ከፍተኛ ግብአት ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ በማደርገው ክትትል እንደማየው በአንዳንድ አካላት የሚፈፀሙ አስተዳደራዊ በደሎች፣ ዝርፊያዎች እና የሙስና ስራዎች በአብዛኛው እርምጃ ይወሰድባቸዋል፣ ይህንን ማስተካከያቸውን ራሳቸው ተቋማቱ ጭምር መልሰው ያሳውቁኛል። ትችት ማለት ተቃውሞ የሚመስለው በዝቶ እንጂ ከስድብ፣ መዘላለፍ እና መጠላለፍ የዘለለ በመረጃ የተደገፈ ዘገባ መንግስትን ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። ይህንን ደግሞ የፌስቡክ ገፁን አከራይቶ የሚጮኸው አክቲቪስት እንጂ ብዙዎቹ አመራሮች ይረዱታል ብዬ አስባለሁ። መልካም ምሽት! @EliasMeseret
نمایش همه...
👍 1 428 154😁 22🕊 20🙏 17🤔 9😱 9
በኢትዮጵያ የአንድ የጠቅላላ ሀኪም ወርሀዊ ደሞዝ= 11 ሺህ ብር የመንግስት አክቲቪስቶች ወርሀዊ ድጎማ= 240,000 ሺህ ብር #Justice @EliasMeseret
نمایش همه...
😢 1 121👍 75 47😱 44🤔 33😁 24🙏 21🕊 5
Photo unavailableShow in Telegram
የዲሲፕሊን ግድፈት አለበት የተባለን ግለሰብ ገጠር ገብቶ እንዲሰራ ማዘዝ ምን ማለት ነው? ገጠር ያለው ህዝብስ ዲሲፕሊን ባለው የጤና ባለሙያ መስተናገድ የለበትም? ይህ የሚያሳየን ወጣት ዶክተሩ ጥፋት ኖሮበት ሳይሆን የሰሞኑን የጤና ባለሙያዎችን ድምፅ ስላሰማ ለመቅጣት ነው፣ ይህ ደግሞ አደገኛ አዝማሚያ ነው። የጤና ባለሙያዎች በሰላማዊ ሁኔታ መብታቸውን እየጠየቁ ነው፣ በተለያዩ ቦታዎች ግን የማሸማቀቅ ስራ እየተሰራ እንዳለ የሚደርሱኝ መረጃዎች ያሳያለ። This will backfire! ዜናውን መሠረት ሚድያ ላይ ለማንበብ: https://t.me/meseretmedia/923 @EliasMeseret
نمایش همه...
👍 647😢 118 35🙏 7😁 6😱 5🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
#GoodNews ቦይንግ የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ መክፈቱ መልካም ዜና ነው የዚህ ክስተት ዋናው መንስኤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተከታታይ ስኬት እና ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ከምስረታው ጀምሮ የነበረው ታሪካዊ ትስስር ነው። አሁንም ይህ ትብብር በሌሎች ሀገራት እንደሚታየው ወደ አውሮፕላን ቁሶች ማምረት እና በሀገር ውስጥ ያለውን የ Maintenance, Repair እና Overhau (MRO) አገልግሎቶችን ወደማሳደግ እና ማዘመን እንዲያድግ ምኞታችን ነው። #FlyEthiopian #Boeing @EliasMeseret
نمایش همه...
👍 888 147😁 23😱 9🙏 8🤔 5🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
መምህራንን በእንዲህ አይነት መልኩ ማሰቃየት አላማው ምንድነው? ስላስተማሩ ብቻ ከዚህ በፊትም ህይወታቸውን ያጡ መምህራን በአማራ ክልል አሉ፣ አሁንም በዚህ መልኩ እና ከዚህ በባሰ ሁኔታ የሚሰቃዩ አሉ። ትክክል አይደለም ብሎ መግለፅ ጉዳዩን ማሳነስ ይሆናል፣ ከግፍም በላይ ነው። በክልሉ በየቀኑ የሚቀጠፉትን ዜጎች፣ በድሮን የሚጨፈጨፉትን ወጣቶች እና ወጥተው የሚቀሩ የሀገር ተረካቢዎችን በተመለከተ ድምፅ ስንሆን እንደቆየነው ሁሉ እንዲህ አይነት ድርጊት ስናይም የማውገዝ ስብዕና እና የሞራል ልዕልና ሊኖረን ይገባል።  @EliasMeseret
نمایش همه...
😢 986👍 315 46😁 33😱 30🕊 13🙏 10🤔 9
Photo unavailableShow in Telegram
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል ይሁንላችሁ፣ ይሁንልን። @EliasMeseret
نمایش همه...
758🙏 223👍 107😁 15🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
#FakeNewsAlert ይህ መረጃ ነጭ ውሸት ነው! ቀላሉ ማስረጃ እና ማንም በሰከንዶች ጉግል አድርጎ የሚረዳው ሀቅ አለ፣ እሱም እሷ በለጠፈችው ፎቶ ላይ የሚታየው እና ታድሶ መብረር ቻለ ተብሎ በመንግስት ሚድያዎች ጭምር ስሙ ተጠቅሶ የነበረው DHC Buffalo የተባለ የካናዳ ስሪት አውሮፕላን ሲሆን እሷ የምታወራው ስለ ሶቪየት ህብረት አውሮፕላን ነው። ማስረጃው: https://www.baesystems.com/en/heritage/de-havilland-canada-dhc-5-buffalo ምናልባት ለማለት የፈለገችው በአንድ ወቅት ሶቪየቶች ለኮ/ል መንግስቱ ሰጥተውት ስለነበረው "መሸሻ" የሚል ቅፅል ስም ስለነበረው Tupolev ስሪት አውሮፕላን ሊሆን ይችላል፣ እሱ ግን ሌላ አውሮፕላን ነው። ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል እና፣ ስለዚህ "መሸሻ" ስለተባለ የሶቪየት አውሮፕላን በቅርቡ የሰማሁትን ላካፍላችሁ። ሶቪየቶች ይህን አውሮፕላን ለኮ/ል መንግስቱ ከሰጡ በኋላ ፕሬዝደንቱ አልተጠቀሙበትም ነበር። ሙሉ ነጭ የተቀባው እና ጭራው ላይ የኢትዮጵያ ባንዲራ ያለው "መሸሻ" ለበርካታ አመታት በቢሾፍቱ አየር ሀይል ግቢ ቆሞ ነዋሪዎች ያዩት ነበር። ከዛም ኢህአዴግ ከገባ በኋላ እና ሜቴክ ከተቋቋመ በኋላ ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ይህን የሶቪየት አውሮፕላን ለጠ/ሚር መለስ ዜናዊ የ VIP አውሮፕላን እንዲሆን እቀይረዋለሁ በማለት ቆራርጠው፣ ቀጥለው፣ ነቃቅለው፣ ሰካክተው ጨረሱ። ከዛ ለበረራ ብቁነት ምዝገባ ሲቪል አቪዬሽንን ሲጠይቁ ተቆጣጣሪዎቹ "ይሄ ለበረራ ብቁ አይደለም" ብለው ፍቃድ እንደተከለክሉ እና ከዛ በኋላም ቆሞ እንደቀረ ሰምቻለሁ። * ከላይ ያለውን መረጃ የፃፍሽው ትክክለኛው የኮ/ል መንግስቱን ትዝታዎችን የፃፍሽው ገነት አየለ ከሆንሽ መንግስቱ የነገሩሽን ደግመሽ አጣሪው @EliasMeseret
نمایش همه...
👍 599😁 172 46🙏 19🤔 9😱 3
Photo unavailableShow in Telegram
#FactCheck የመንግስት ሚድያዎች "የቀድሞው ፕሬዝደንት መንግስቱ ኀይለ ማርያም አውሮፕላን" የሚል መረጃ ደጋግመው ሲጠቀሙ ታይተዋል፣ ይህ ደግሞ አሳሳች ነው። ኮ/ል መንግስቱ ሲጠቀሙ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን እንጂ የራሳቸው አውሮፕላን አልነበራቸው። ይኼ ነገር ምናልባት ከሰሞኑ ቅንጡ እና የ VIP አገልግሎት የሚሰጥ አውሮፕላን ሀገር ቤት አገልግሎት ሊጀምር ስለሆነ እና ጠ/ሚሩ ይጠቀሙበታል ስለተባለ እሱን ዜና ማደንዘዣ እንዳይሆን ብዬ አሰብኩ። ሙሉ ዘገባው ኢትዮጵያ ቼክ ገፃ ላይ: https://t.me/ethiopiacheck/2548 @EliasMeseret
نمایش همه...
👍 1 052😁 311 50🙏 20😢 18🤔 16😱 4🕊 4
Photo unavailableShow in Telegram
"የኬንያ ዜጎች እንኳን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጭምር ተጓጉዘው ሀገራቸው ገብተዋል"- በሚያንማር የሚገኙ ዜጎች በስልክ ከነገሩኝ በሚያንማር የሚገኙ ዜጎች ጉዳይ አሳሳቢም፣ አስገራሚም እየሆነ ነው። ከ740 በላይ ዜጎቻችን ተይዘውበት ከነበረው አደገኛ ካምፕ በአንድ ታጣቂ ቡድን ነፃ ሆነው አሁን ላይ በግዜያዊ መጠለያ ውስጥ ቢገኙም ተረክቧቸው ወደ ሀገራቸው የሚመልሳቸው አካል አጥተው እንዳሉ በርካቶች በአጭር ፅሁፍ መልዕክት እና በስልክ ነግረውኛል። አንዳንዶቹ በተስፋ መቁረጥ ራስን የማጥፋት ሙከራ አርገዋል፣ ኮማ ውስጥ ያሉ አሉ፣ የአካል ጉዳትም የደረሰባቸው አሉ። ውጭ ጉዳይ አንድ ሰሞን ጉዳዩን ይዞት እንደነበር ሰምተን ነበር፣ አሁን ላይ ምንም ነገር የለም፣ ሲጠየቁ "ፕሮሰስ ላይ ነው" የሚል ምላሽ ይሰጣሉ። ዜጎቻችንን ከካምፑ ነፃ ያወጡት ታጣቂዎች እንኳን "መንግስታችሁ በፍጥነት ካልወሰዳችሁ ወደነበራችሁበት ካምፕ ከመመለስ ውጭ ምርጫ የለንም" እያሏቸው ነው። ኬንያን ጨምሮ ሌሎች 25 ሀገራት ዜጎቻቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በመጠቀም አጓገዘው አውጥተዋል። ጉዳዩን በቶክዮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይዞት ነበር ተብሎ ነበር፣ አሁን ደህሞ ህንድ ያለው ኤምባሲ እየተከታተለው ነው ከሚል ውጭ ምላሽ የለም። የሚገርመው 400 የሚሆኑት የመመለሻ ትኬት አላቸው፣ ሊረዷቸው የሚችሉ NGO ድርጅቶችም አሉ፣ ነገር ግን መንግስት የመመለስ (repatriation) ሂደቱን ካልጀመረ ምንም ማድረግ አይቻልም። ልጆቹ አንዴ ተታለው ተወስደዋል፣ መንግስት ግን ሊደርስላቸው አይገባም? ሀገር ማለት ህዝብ ማለት አልነበር? በአፋጣኝ ትኩረት ካልተሰጠው አሳዛኝ ውጤት ይታየኛል። @EliasMeseret
نمایش همه...
😢 455👍 174 18🤔 8🙏 8🕊 5
Photo unavailableShow in Telegram
ጠ/ሚሩ ቪየትናም ናቸው! ቪየትናም ደግሞ በቅርብ አመታት የአለማችን ግዙፍ የማምረቻ (manufacturing) ማዕከላት መገኛ ሆናለች። ሀገሪቱ ከአይፎን እስከ ሳምሰንግ ስልኮች፣ ከአዲዳስ እስከ ናይኪ ልብስ እና ጫማዎች እንዲሁም ግዙፍ የመኪና እና መርከብ አምራች ኩባንያዎች የስበት ማዕከል ሆናለች። የዛሬ አመት ገደማ ጠ/ሚር አብይ ሲንጋፖርን ሲጎበኙ ያዩት የከተማ ልማት ለኮሪደር ልማት ላይ መነቃቃትን ፈጥሮ ነበር ተብሎ ተዘግቦ ነበር። አሁንም የቪየትናም ጉብኝታቸው እጅጉን እየተዳከመ ላለው እና ከፍ ያለ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ላለው የሀገራችን የአምራች ኢንደስትሪ ዘርፍ መነቃቃትን ይፈጥር ዘንድ ምኞቴ ነው። ፎቶ: የቪየትናም የማምረቻ ኢንደስትሪዎች በከፊል @EliasMeseret
نمایش همه...
🙏 816👍 343😁 209 88🕊 17🤔 11😢 4😱 3
የህግ ትምህርት ቤት እያለን የፍትህ ዋና መሰረት እንደሆነ ተደጋግሞ የምንማረው በፍርድ ቤት ጥፋተኝነት ተረጋግጦ ቅጣት እስኪጣል ንፁህ ሆኖ የመገመት መብት "presumption of innocence" ነበር። ከሰሞኑ በኢቢኤስ ጉዳይ ዶክመንተሪ ሰርተው ያልረኩት አካላት ትናንት እና ዛሬ ክፍል ሁለት ቀጥለዋል። በሌላ በኩል ሁለት ግለሰቦች ክስ መስርተውበት ፍርድ ቤት ሲጠበቅ የነበረ የአዲስ አበባ ነዋሪ አክቲቪስትን ፖሊስ "አድራሻውን አጣሁ" ብሎ ለፍርድ ቤት መልሷል። መንግስት ለህግ ያለውን ንቀት እንዲህ እያሳየ እንዴት ህግ ይከበር? የፍትህ ስርዐቱን የሚመሩት እንደ ፍትህ ሚኒስቴር ያሉ አካላት ይህን ሲያዩ እና ማስቆም ሲያቅታቸው እንዴት ያፍሩ ይሆን? @EliasMeseret
نمایش همه...
👍 1 119😢 184 61😁 40🙏 29😱 17🤔 10🕊 5
Photo unavailableShow in Telegram
እንደ USAID እና UAE AID መሆኑ ነው! ከእያንዳንዱ ዜጋ ከደሞዙ እና ከኪሱ በግድ ገንዘብ ሰብስቦ ለጎረቤት ሀገር ጭምር እርዳታ ሊሰጡ አስበዋል። ይህን ህዝብ ያላግጡበታል አይገልፀውም። ከጤና ባለሙያ እስከ መምህራን፣ ከተማሪ እስከ አርሶአደር አይቶት የማያውቀው ድህነት እየገረፈው ይገኛል፣ ምላሹ ግን "ይበልጥ እናራቁትሀለን" ሆኗል። #Enough @EliasMeseret
نمایش همه...
😢 1 545😁 397👍 232🤔 73 62😱 43🙏 18🕊 14
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ እንግዲህ ዛሬ ጠዋት የሆነ ነው! ባለፈው ሳምንት ባደረግኩት አጭር ዳሰሳ በአንዲት ግለሰብ መታገት ወይም አለመታገት ዙርያ የመንግስት ሚድያዎች፣ የክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮዎች፣ ባለስልጣናት እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ማህበራዊ ሚድያ ላይ ከ610 ግዜ በላይ ዜናዎችን አጋርተዋል (ለምሳሌ ጉዳዩ ይመለከተዋል ተብሎ የማይታሰበው የትራንስፖርት ሚኒስቴር ብቻ 12 ግዜ በብርቱካን ዙርያ በፌስቡክ ገፁ መረጃ አጋርቷል)። ይህ ቁጥር መንግስት ያደራጃቸው አክቲቪስቶች እና የሚድያ ሰራዊት ፖስቶችን ሳይጨምር ነው። እንደዛሬው አይነት የዜጎች እገታ እና ግድያ ግን አይመለከታቸውም? ለዚህ ነው በአንዲት ግለሰብ ዙርያ ደጋግመው ዶክመንተሪ ሲሰሩ ስናይ እውነት ለመደበቅ እንደሆነ የምንረዳው። ዛሬ የተከሰተውን አሳዛኝ እገታ እና ግድያ ለማንበብ: https://t.me/meseretmedia/872 @EliasMeseret
نمایش همه...
👍 1 142😢 368 50😁 24🤔 22🙏 14😱 6🕊 5
Photo unavailableShow in Telegram
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ያሉት ኢቢሲ ሁለት እና ሶስት ጋዜጠኞች በበጎ ፈቃደኝነት ህዝብን ከሚያገለግሉበት ኢትዮጵያ ቼክ ላይ ኮፒ-ፔስት ሲያደርግ ማየት ያስደንቃል፣ ምንጭ መጥቀስ የሚድያ ስነምግባር ነው። ኢትዮጵያ ቼክ ከ10 ሰዓት በፊት ያወጣው መረጃ: https://www.facebook.com/share/p/1ExjnJuxCZ/ የኢቢሲ ኮፒ-ፔስት ⬆️ @EliasMeseret
نمایش همه...
😁 456👍 146 12🕊 10🤔 5😱 5
Photo unavailableShow in Telegram
የ 'ለውጡ' ዘመን ለጋዜጠኞች እና ለሚድያ ተቋማት ምን ይዞ መጣ? ቀድሞውንም ሚድያውን በመበደል እና በመተብተብ የተካነው የኢህአዴግ ስርዐት ተቀይሮ አዲስ መንግስት ሲመጣ እና የዛሬ 6 አመት የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ጠ/ሚሩ በተገኙበት ለመጀመርያ ግዜ በኢትዮጵያ ሲከበር በስፍራው ነበርኩ፣ በተደረጉት ንግግሮች ከፍተኛ ተስፋ ተሰምቶኝ ነበር። አሁን? ለውጡ እስር፣ እንግልት፣ ስደት፣ ሞት እና ፍርሀትን ከኢህአዴግ ዘመን በባሰ ይዞ ከተፍ እንዳለ ግልፅ ነው። ባለፈው አንድ አመት ብቻ ከ40 በላይ ጋዜጠኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ታስረዋል፣ በርካቶች ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው ለስደት ተዳርገዋል እንዲሁም ሀገር ቤት ስራቸው ላይ ያሉትም በስጋት ስራቸውን እየከወኑ ይገኛሉ። ሚድያው በለውጡ ዘመን የረጅም ዘመን እስራት ላይ ይገኛል። @EliasMeseret
نمایش همه...
👍 997😢 62🙏 62 52😁 35🤔 6
Photo unavailableShow in Telegram
የቀደሙ ታሪኮቻቸውን፣ መሪዎቻቸውን፣ ህዝቦቻቸውን እና ስርዐቶቻቸውን የሚያከብሩ እና በወጉ የሚዘክሩ ሀገራት ያስቀናሉ! ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ የሚገኙትን የቶማስ ጄፈርሰን እና የማርቲን ሉተር ኪንግ መታሰቢያዎችን ጎበኘን። @EliasMeseret
نمایش همه...
👍 799 128😁 30🤔 11😢 3
Photo unavailableShow in Telegram
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን፣ ዒድ ሙባረክ! መልካም በዓል! @EliasMeseret
نمایش همه...
👍 544 104🙏 39😁 20🤔 10😢 2