107 335
Подписчики
-4624 часа
-3747 дней
-2 08430 день
Архив постов
የኢትዮጵያ መንግሥት፣ በቅርቡ ከትግራይ ክልል ወደ አፋር ክልል ተተኩሰዋል የተባሉ የከባድ መሳሪያ ጥይቶችን እየመረመረ መሆኑ ተሰማ።
ይህ ክስተት፣ ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን ደማሳሽ ጦርነት ያስቆመው የ2022 የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት (CoHA) "እየተሸረሸረ" [fraying] ነው የሚለውን ስጋት አጠናክሮታል።
የመከላከያ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት፣ መንግስት የተገኙትን ጥይቶች በመሰብሰብ ምርመራ እያካሄደ ነው። የምርመራው አላማም፣ "ሕወሓት ከዚህ ቀደም ሲጠቀምባቸው ከነበሩት የተለዩ አዳዲስ መሳሪያዎች ሊኖሩ ይችላሉ" የሚለውን ስጋት ለማረጋገጥ መሆኑን ምንጮቹ አክለዋል።
ይህ አዲስ ወታደራዊ ውጥረት የተከሰተው፣ በዘመናዊ አፍሪካ ታሪክ እጅግ ገዳይ ከሆኑ ጦርነቶች አንዱን ያስቆመው የፕሪቶሪያ ስምምነት፣ በተለያዩ ምክንያቶች አደጋ ላይ መውደቁን አንድ አዲስ ትንታኔ ባመለከተበት ወቅት ነው።
ሪፖርቱ፣ በቅርቡ በትግራይ እና በአፋር ክልሎች መካከል የተከሰቱት ግጭቶች፣ እንዲሁም በትግራይ አመራሮች እና በፌደራል ባለስልጣናት መካከል "እያደገ ከመጣው እምነት ማጣት" ጋር ተዳምረው፣ ከ2022 መገባደጃ ጀምሮ የተገነባው ስስ ሰላም አደጋ ላይ መውደቁን አመልክቷል።
ትንታኔው ለአሁኑ አለመተማመን በዋነኛነት "ዘገምተኛ እና ወጥነት የጎደለው የስምምነቱ አፈጻጸም" መሆኑን ይጠቁማል።
ምንም እንኳን በሁለቱ ዋና ተዋጊ ኃይሎች መካከል መጠነ ሰፊ ውጊያ ቢቆምም፣ እንደ ትጥቅ መፍታት፣ የታጋዮችን መልሶ ማዋሃድ እና ተፈናቃዮችን መመለስ ባሉ ቁልፍ ድንጋጌዎች ላይ መዘግየቶች እና የጋራ ውንጀላዎች ተበራክተዋል።
የፌደራል መንግሥት፣ የትግራይ ባለስልጣናት "ሙሉ በሙሉ ትጥቅ አልፈቱም" እንዲሁም "በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋር ይተባበራሉ" ሲል ይከሳል።
የትግራይ ክልል አመራሮች በበኩላቸው፣ የፌደራል መንግሥት አስፈላጊ አገልግሎቶችን፣ አስተዳደራዊ ገደቦችን ማንሳትን እና ፖለቲካዊ ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን በማረጋገጥ በኩል "እግሩን እየጎተተ ነው" ሲሉ ይከሳሉ።
በተለይም በሁለቱ ክልሎች አወዛጋቢ በሆነው የትግራይ-አፋር ድንበር ላይ እንደ አዲስ ያገረሸው ግጭት፣ የቆዩ ቁርሾችን በመቀስቀስ ለሰላሙ ስምምነት ትልቅ አደጋ መደቀኑን ሪፖርቱ አስገንዝቧል።
ትንታኔው ሲያጠቃልል፣ ይህ የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ መፍረስ፣ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው የአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት "አስከፊ" አንድምታ እንደሚኖረው አስጠንቅቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 33😁 9🔥 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
በትግራይ ክልል በሕገወጥ የማዕድን ቁፋሮ ላይ በተደረገ ዘመቻ ከ12 ኪሎግራም በላይ ሜርኩሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን ግብረ ኃይሉ አስታወቀ!
በትግራይ ሕገወጥ የማዕድን ቁፋሮን ለመከላከልና ለመዋጋት የተቋቋመው ግብረ ኃይል፣ በክልሉ ባልተፈቀደ የማዕድን ማውጣት ሥራ ላይ ሊውል የነበረ ከ12,000 ግራም በላይ ሜርኩሪ መያዙን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
በማዕድን ሥራ ላይ አደገኛ ኬሚካሎችን መጠቀም የተከለከለ ይሁን እንጂ፣ በክልሉ ውስጥ ባሉ በርካታ አካባቢዎች የሚገኙ የማዕድን አውጪዎች እነዚህን ኬሚካሎች በግልጽ መጠቀማቸውን ቀጥለዋል ተብሏል።
ግብረ ኃይሉ ሥራውን ከጀመረ ወዲህ አደገኛ ኬሚካሎች ተርታ የተመደቡትን ሜርኩሪ [12,998 ግራም] እና ሳይናይድ [105 ኪ.ም] በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተጠቁሟል።
ግብረ ኃይሉ አክሎም የሕግ አሠራሮችንና የቁጥጥር ስልቶችን አፈጻጸም ዝቅተኛነት በመጥቀስ፣ በወረዳዎች የአደረጃጀት መዋቅር እና የመስክ ቁጥጥር አቅም ላይ ሰፊ ክፍተቶች መኖራቸውን አመልክቷል።
በዚህም የግብረ ኃይሉን ተግባራት ለመገምገም፣ ግኝቶችን ለመፈተሽ እና ቀጣይ እርምጃዎችን ለመዘርዘር በአክሱም ከተማ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በስብሰባውም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አማኑኤል አሰፋ፣ ከካቢኔ አባላት፣ ከዞንና ወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከማህበረሰብ ሽማግሌዎች ጋር በመሆን እየተሳተፉ ነው።
በቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ የተቋቋመው ግብረ ኃይሉ፣ በክልሉ የማዕድን ዘርፍ ላይ የመንግሥትን ቁጥጥር ለመመለስ እና በሕገወጥ ማዕድን ቁፋሮ ምክንያት የሚደርሰውን የገቢ ብክነት ለመግታት ያለመ ነው።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 24
ክቡር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ከቀድሞ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ከነበሩት ከክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ጋር የስራ ርክክብ አደረጉ።
🇪🇹ህዳር 1/2018 ዓ.ም🇪🇹
በቅርቡ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት ክቡር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ከቀድሞ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ከነበሩት ከክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል።
በዛሬዉ ዕለት በተደረገዉ የስራ ርክክብ ወደ ሌላ ተቋም የተሾሙት ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ባደረጉት ንግግር በቢሮው በነበራቸው ቆይታ እና ለተመዘገቡ ስኬቶች የማኔጅመንት አባላቱን እና በየደረጃው የሚገኙ የክፍለ ከተማና የኮሌጅ ዲኖችን አመስግነዋል።
በቀጣይም ከአዲሱ አመራር ጋር በመቀናጀት የተጀመሩ ስራዎች ፍፃሜ እንዲያገኙ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በበኩላቸው የቀድሞው አመራር በሳል አመራር በመስጠት ቢሮው አሁን ለደረሰበት ደረጃ እንዲበቃ አስችሏል ብለዋል።
ክቡር አቶ ሚሊዮን አክለውም የጋራ ዓላማ በመያዝ እና እንደ አንድ ቡድን በመሆን የተያዙ ዕቅዶችን ለማሳካት እጅና ጓንት ሆነን እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።
@Yenetube @Fikerassefaክቡር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ከቀድሞ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ከነበሩት ከክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ጋር የስራ ርክክብ አደረጉ።
🇪🇹ህዳር 1/2018 ዓ.ም🇪🇹
በቅርቡ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት ክቡር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ከቀድሞ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ከነበሩት ከክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል።
በዛሬዉ ዕለት በተደረገዉ የስራ ርክክብ ወደ ሌላ ተቋም የተሾሙት ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ባደረጉት ንግግር በቢሮው በነበራቸው ቆይታ እና ለተመዘገቡ ስኬቶች የማኔጅመንት አባላቱን እና በየደረጃው የሚገኙ የክፍለ ከተማና የኮሌጅ ዲኖችን አመስግነዋል።
በቀጣይም ከአዲሱ አመራር ጋር በመቀናጀት የተጀመሩ ስራዎች ፍፃሜ እንዲያገኙ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በበኩላቸው የቀድሞው አመራር በሳል አመራር በመስጠት ቢሮው አሁን ለደረሰበት ደረጃ እንዲበቃ አስችሏል ብለዋል።
ክቡር አቶ ሚሊዮን አክለውም የጋራ ዓላማ በመያዝ እና እንደ አንድ ቡድን በመሆን የተያዙ ዕቅዶችን ለማሳካት እጅና ጓንት ሆነን እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 18
Фото недоступноПоказать в Telegram
ቁልፍ የአልሻባብ መሪ ተገደለ
በሶማሊያ በተደረገ ወታደራዊ ዘመቻ ሶስት ከፍተኛ የአልሻባብ አሸባሪ ቡድን መሪዎች መግደሉን የሞቃዲሾ መንግስት አስታወቀ።
ከተገደሉት መካከል በባኩል ግዛት በሚፈፀሙ የሽብር ጥቃቶች ቀንደኛ አቀነባባሪው ሞሀመድ አብዲ ሞሀመድ ኑር ይገኝበታል ተብሏል።
የሶማሊያ መንግስት እንደገለፀው፣ በባኩል እና ቤይ ግዛቶች በርካታ ንፁሃንን የገደለው ሞሀመድ በቅፅል ስሙ ጎፎው የተባለው ግለሰብ በአባል መንደር በተደረገ ልዩ ዘመቻ መገደሉን ነው።
ያህየ ወይም አቡ ካህሊድ እና ሻሪፍ አሚር የተባሉ ተጨማሪ ቁልፍ የሽብር ቡድኑ አባላት በዘመቻው መገደላቸውንም የሞቃዲሾ ወታደራዊ ሀላፊዎች አክለው ተናግረዋል ።
የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር አልሻባብን የመመንጠር ዘመቻው ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ፣ ቡድኑ ጨርሶ እስካልጠፋ ድረስ ሰላም እንደማይኖር በመግለጫው አመላክቷል። አናዶሉ እንደዘገበው ።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 6🔥 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
የገንዘብ ሚኒስቴር የገቢ ግብር (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አፈጻጸም ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት፣ በተለይ በአከፋፋይ ነጋዴዎች ላይ የሚሰላውን አማራጭ አነስተኛ ግብር በተመለከተ ከፍተኛ እፎይታ የሚሰጥ ማብራሪያ ሰጥቷል።
ይህ ውሳኔ ቀደም ሲል የንግዱን ማህበረሰብ አስጨንቆ የነበረውን የትርፍ ህዳግ (Profit Margin) ግዴታ የሚያነሳ በመሆኑ በነጋዴዎች ዘንድ በደስታ ተቀባይነትን አግኝቷል።በሚኒስቴሩ ማብራሪያ መሰረት፣ የአከፋፋዮች አማራጭ አነስተኛ ግብር የሚሰላበት መንገድ ግልጽ ሆኗል።
በዚህ መሰረት ፤ ጅምላ ሻጭ/አከፋፋይ ከአምራቹ ወይም ከአስመጪው ጋር ባደረገው ውል የሚሸጥበት ዋጋ እና የሚያገኘው መቶኛ (ትርፍ ህዳግ) በግልጽ የተወሰነ ከሆነ፣ አማራጭ አነስተኛ ግብሩ የሚሰላው በጠቅላላ የሽያጭ ገቢው ላይ ሳይሆን፣ በውል ወይም በሕግ በተፈቀደለት የትርፍ መቶኛ ላይ ብቻ ይሆናል ተብሏል።ይህ አዲስ አፈጻጸም የገቢዎች ሚኒስቴር በትንሹ 15 በመቶ ማትረፍ አለባችሁ በሚል ያስቀመጠው ግዴታ በንግዱ ላይ የፈጠረውን ጫና የሚያቃልል ነው።
ይሁንና፣ ይህንን ውሳኔ ለመጠቀም አከፋፋዩ የመሸጫ ዋጋ እና የትርፍ ህዳግ በውል መወሰኑን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ሰነድ ለግብር ባለስልጣናት ማቅረብ ይኖርበታል።ይህን የገንዘብ ሚኒስቴር ማብራሪያ ተከትሎ ነጋዴዎች ለካፒታል ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት፣ ውሳኔው የንግዱን እንቅስቃሴ የሚያነቃቃ እና ከገበያ እውነታ ጋር የሚጣጣም ፍትሃዊ እርምጃ እንደሆነ ተናግረዋል።
Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 17👍 2😭 1
Repost from YeneTube
Фото недоступноПоказать в Telegram
በካሽ 100% ለሚከፍል 35% ቅናሽ
📍ሳር ቤት ቫቲካን
🎯65/35 አከፍፈል (35%ቅናሽ)
👉2መኝታ 81 ካሬ =5.8 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106 ካሬ=7.6 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139 ካሬ=9.9 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152 ካሬ= 11.8 ሚሊዮን ብር
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 81ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%) = 1.78 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=2.33ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)= 3.06 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=3.34 ሚሊዮን ብር
#ቀሪውን 80% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ
0901504245
0923579248
❤ 6😭 1
ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡
ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ባደረባቸው ሕመም ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በ87 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ የታሪክ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የተለያዩ የታሪክ መጽሐፍትን ለአንባቢያን አበርክተዋል፡፡
የኢትዮጵያውያንን የጋራ እሴት፣ ባሕልና ቋንቋ በማውሳት የሕዝቦች ታሪክ ጎልቶ እንዲታወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውም ተመላክቷል፡፡
የላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) የአስክሬን ሽኝትና ቀብር ሥነ ሥርዓት የፊታችን ማክሰኛ ሕዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 39😭 30😁 4🔥 1
Repost from YeneTube
Фото недоступноПоказать в Telegram
በካሽ 100% ለሚከፍል 35% ቅናሽ
📍ሳር ቤት ቫቲካን
🎯65/35 አከፍፈል (35%ቅናሽ)
👉2መኝታ 81 ካሬ =5.8 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106 ካሬ=7.6 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139 ካሬ=9.9 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152 ካሬ= 11.8 ሚሊዮን ብር
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 81ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%) = 1.78 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=2.33ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)= 3.06 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=3.34 ሚሊዮን ብር
#ቀሪውን 80% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ
0901504245
0923579248
❤ 6
Фото недоступноПоказать в Telegram
በኮሞሮስ ደሴት አቅራቢያ የስደተኞች ጀልባ ተገልብጣ ታዋቂዋን የሶማሊኛ ድምጻዊ እና ልጇን ጨምሮ የበርካቶች ሕይወታቸው አለፈ!
ታዋቂዋ የሶማሊኛ ድምጻዊ ሆዳን አደንን እና በርካታ የሶማሌ ስደተኞችን ያሳፈረች ጀልባ በፈረንሳይ ሥር በምትተዳደረው ማዮቴ የባሕር ዳርቻ አካባቢ ተገልብጣ የበርካቶች ሕይወት ማለፉ ተሰማ።ድምጻዊት ሆዳን አደን በመድረክ ስሟ ሆዳን አፍሪካ በሚል የምትታወቅ ሲሆን በጀልባው ውስጥ ከሴት ልጇ ጋር እንደነበረች እና የሁለቱም ሕይወት ማለፉ ተገልጿል።
የድምጻዊቷ የቅርብ የሥራ አጋር እና ጓደኛ ሆነው አብዱልቃድር ፊልፊል በጀልባው ውስጥ 15 ሰዎች እንደነበሩ እና አንድ ሰው ብቻ በሕይወት መትረፍ መቻሉን ለቢቢሲ ተናግሯል።ሌሎች የመረጃ ምንጮች እንዲሁ በጀልባዋ ላይ የነበሩት ስደተኞች ቁጥር 20 ይጠጋል ብለዋል።
የድምጻዊቷ ሞት ታዋቂ ግለሰቦች ጭምር የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ወደ አውሮፓ በሕገ ወጥ መንገድ በባሕር ለመሄድ ሕይወታቸውን እንዴት ለአደጋ እንደሚያጋልጡ ያሳየ ነው ተብሏል።የቅርብ ጓደኛዋ አብዱልቃዲር ፊልፊል "ሆዳን ጠንካራ እና ሥራዋን የምትወድ ነበረች፤ ከአባቷ የወረሰችውን የጥበብ ፍቅር ለማሳካት በጥልቅ የምትተጋ ነበረች።" ብሏል።
"ፈጣሪ ነፍሷን ይቀበላት" ሲል የተናገረው ጓደኛዋ ለአድናቂዎቿ እና ለቤተሰቦቿ መጽናናትን ተመኝቷል።ሆዳን ድምጻዊነትን የጀመረችው ከዓመታት በፊት በስደት በምትኖርበት የኬንያ መዲና ናይሮቢ ነበር።ሶማሊያ ውስጥ ሙዚቀኞች እና ድምጻውያን ተቀባይነት ስለሌላቸው ከአገራቸው ውጭ ሰርተው ስም እና ዝና ካተረፉ በርካታ የአገሪቱ የጥበብ ባለሙያዎች መካከልም አንዷ ነበረች።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cn97pllyr0no
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 46😭 24😁 3👀 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የ #ኢትዮጵያ አየር መንገድ የ #አሜሪካ ፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር መመሪያ በአሜሪካ -አፍሪካ በረራዎቹ ላይ ተጽዕኖ እንደማይፈጥር አስታወቀ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቡድን፣ የአሜሪካ የፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር (FAA) ያወጣው አዲስ መመሪያ ወደ አሜሪካ እና ከአሜሪካ በሚያደርጋቸው ዓለም አቀፍ በረራዎች ላይ ተጽዕኖ እንደማይፈጥር አስታወቀ።
አየር መንገዱ ትናንት ጥቅምት 28 ባወጣው መግለጫ፣ አፍሪካንና አሜሪካን የሚያገናኙ ሁሉም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች በታቀደላቸው መርሃ ግብር መሰረት እንደሚከናወኑ አረጋግጧል።
ይሁን እንጂ፣ ሌላ አየር መንገዶችን በመጠቀም ከአሜሪካ ከተሞች ወይም ከሌሎች መዳረሻዎች የሚመጡ ተሳፋሪዎች በመመሪያው ምክንያት "የበረራ ሰዓት ማስተካከያ” ወይም “ተጨማሪ የማረጋገጫ ሂደቶች” ሊገጥማቸው ይችላል ሲል አስገንዝቧል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ምድብ ውስጥ ለሚገኙ ተጓዦች "ለጉዟቸው ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጡ እና ከመነሳታቸው በፊት የግንኙነት ዝርዝሮችን ከየአየር መንገዶቻቸው እንዲያረጋግጡ" መክሯል።
አየር መንገዱ አክሎም፣ የአሜሪካ መግቢያ በሆኑት ዋሽንግተን ደለስ (IAD)፣ ኒው ዮርክ JFK (JFK)፣ ኒዋርክ (EWR)፣ ቺካጎ (ORD) እና አትላንታ (ATL) በኩል የሚጓዙ መንገደኞች የሚመለከታቸውን አየር መንገዶች እንዲያጣሩ እና ለግንኙነቶች ተጨማሪ ጊዜ እንዲያቅዱ አሳስቧል።
መግለጫው፣ "የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አሜሪካ፣ አፍሪካ እና ሌሎች ቦታዎች ለሚጓዙ ሁሉም ደንበኞቹ አስተማማኝ፣ ምቹና እንከን የለሽ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ ነው" ብሏል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 39😁 5👍 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
የስኳር በሽታ፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና የልብ ህመም ካለብዎ የአሜሪካ ቪዛ ማመልከቻዎ ሊከለከል ይችላል ተባለ
የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በዩናይትድ ስቴትስ ለመኖር የሚያመለክቱና እንደ ስኳር በሽታ ወይም ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያሉ የጤና ችግሮች ያለባቸው የቪዛ አመልካቾች ማመልከቻቸው ሊከለከል ይችላል የሚል መመሪያ አውጥቷል።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሐሙስ አዲስ መመሪያዎችን አውጥቷል።
መመሪያዎቹ እንደሚገልጹት በእንደዚህ ዓይነት የጤና ችግሮች የሚሰቃዩ አመልካቾች ለዩናይትድ ስቴትስ "የህዝብ ሸክም" ወይም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊሆኑ እና የመንግሥትን ሀብት ሊያሟጥጡ ስለሚችሉ፣ ወደ አሜሪካ ከመምጣታቸው በፊት እነዚህ ጉዳዮች ይረጋገጣሉ።
ዋሽንግተን የሚገኘው የዜና ማሰራጫ KFF Health News እንደዘገበው መመሪያው ለአሜሪካ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽ/ቤቶች ተልኳል።
ከዚህ ቀደም የአሜሪካ ቪዛ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ እንደ ተላላፊ በሽታዎች፣ የክትባት ታሪክ፣ የአእምሮ ጤና እና የአካል ብቃት ብቻ ይታዩ ነበር። ይሁን እንጂ አዲሱ ፖሊሲ ሌሎች የጤና ችግሮችንም ይጨምራል፤ ከእነዚህም መካከል የልብ በሽታ፣ የመተንፈሻ አካላት በሽታ፣ ካንሰር፣ ስኳር በሽታ፣ ሜታቦሊክ፣ የነርቭ እና የአእምሮ ጤና ችግሮች ይገኙበታል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 21👎 6
Фото недоступноПоказать в Telegram
በካሽ 100% ለሚከፍል 35% ቅናሽ
📍ሳር ቤት ቫቲካን
🎯65/35 አከፍፈል (35%ቅናሽ)
👉2መኝታ 81 ካሬ =5.8 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106 ካሬ=7.6 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139 ካሬ=9.9 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152 ካሬ= 11.8 ሚሊዮን ብር
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 81ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%) = 1.78 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=2.33ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)= 3.06 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=3.34 ሚሊዮን ብር
#ቀሪውን 80% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ
0901504245
0923579248
ህወሃት የተቀበሩ ከባድ መሳሪያዎችን እያወጣ ወደ አፋርና ራያ እያስጠጋ መሆኑን የስምረት ፓርቲ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ጠዓመ አረዶም ገልፀዋል።
Via:- አዩዘሀበሻ
@Yenetube @Fikerassefa
😁 44👀 28👍 20❤ 9
Фото недоступноПоказать в Telegram
በካሽ 100% ለሚከፍል 35% ቅናሽ
📍ሳር ቤት ቫቲካን
🎯65/35 አከፍፈል (35%ቅናሽ)
👉2መኝታ 81 ካሬ =5.8 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106 ካሬ=7.6 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139 ካሬ=9.9 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152 ካሬ= 11.8 ሚሊዮን ብር
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 81ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%) = 1.78 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=2.33ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)= 3.06 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=3.34 ሚሊዮን ብር
#ቀሪውን 80% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ
0901504245
0923579248
❤ 7
Фото недоступноПоказать в Telegram
"በፕሪቶሪያ በድርጅት እንጂ በግለሰብ የተፈረመ ስምምነት የለም" ሲሉ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ፡፡ ከሚዲያ ጠፍተው የቆዩት የህወሀት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ዛሬ ብቅ ብለው ከህወሀት ልሳን ወይን ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል፡፡
በዚህ ቃለምልልሳቸውም የፕሪቶሪያው ስምምነት የተፈረመው ‹‹ስለ›› ተብሎ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ‹‹ስለ›› የተባለው ደግሞ ህወሀትንና የፌዴራል መንግስትን ለመግለፅ እንደሆነ ጠቅሰው እንደድርጅት እንጂ እንደግለሰብ የተፈረመ ስምምነት የሌለ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ህወሀት ዛሬ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት የፕሪቶሪያን ስምምነት በግልፅ መጣሱን ገልጿል፡፡
ለዚህም እንደማሳያ ‹‹መንግስት የድሮን ጥቃት ፈፅሟል›› ያለው ህወሀት ጨምሮም መንግስት ሁሉንም ልዩነቶች በሰላማዊ የፖለቲካ ውይይት የመፍታት ግዴታውን እንዲወጣ አሳስቦ ከዚህ የጥፋት ተግባሩም እንዲቆጠብ አስጠንቅቋል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 37😁 23🔥 7👍 3👎 3
#መረጃ: የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የሰራተኞችን ደሞዝን መክፈል አልችልም አለ።
የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አድሱን የደሞዝ ማሻሽያ ምክንያት በማድረግ ህገወጥ 13,000 (አሥራ ሦስት ሽህ ) ሠራተኛች የመደብ መታወቂያ ጥቁር የሌላቸውን ዝርዝር መረጃ ዉስጥ በማጨቅ አጠቃላይ 125,000 (አንድ መቶ ሃያ አምስት ሽህ) ሠራተኛች ደመወዝ መጠየቁን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል።
የክልሉ ፓብልክ ሰርቪስ በኩል የተላከው መረጃ እና የፈደራሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የሚያቀው የሰው ኃይል ቁጥር 112,000 (አንድ መቶ አስራ ሁለት ሽህ ) ጋር ስነጻጸር የ13,000 መነሻዉ ያልታወቀ ሰዉ ሃይ ተገኝቷል ነዉ የተባለው።
በሌላ በኩል ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ዓመታዊ የሰራተኞች የደመወዝ ወጪ 4.6 ቢሊየን ብር ደርሷል ተብሏል። ከተማዋ አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢ አሰባሰብና አፈጻጸም መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ 4.8 ቢሊየን ብር በመሆኑ፤ ቀሪው ሁለት መቶ ሚሊዮን ብር የልማት ሥራዎችን ለማከናወን አስቸጋር ያደርገዋል ተብሏል።
መንግሥት የዘጎችን የኑሮ ጫና ለማቃለል የደመወዝ ጭማሪ ማድረጉና የደመወዝ ጭማሪውም ከጥቅምት ወር ደመወዝ ጋር ተካቶ እንደሚከፈል ማወጁ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎ የክልል መንግሥታት በፋይናንስ ልማት ቢሮና በፓብልክ ሰርቪስ ቢሮ አማካይነት መረጃ እንድቀርብ መታዘዙም ይታወቃል።
ይህንን ተከትሎ በክልሉ ፓብልክ ሰርቪስ ቢሮ አማካይነት የ112,000 (የአንድመቶ አሥራሁለት ሽህ) ሠራተኛች ዝርዝር መረጃ የተላከ ስሆን፤ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በኩል ደግሞ 125,000 (አንድ መቶ ሃያ አምስት ሽህ) ሠራተኞች ደመወዝ መጠየቁ ታውቋል:: ይህንን ልዩነት ለማስተካከል የክልሉ ፋይናንስ የላከዉ መረጃ በደንብ እንዲፈተሽ ጠቅላይ ምንስተሩ አቅጣጫ አስቀምጧል ነዉ የተባለዉ።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 20😁 15
Фото недоступноПоказать в Telegram
አዲሱን የደሞዝ ጭማሪ መክፈል እንደማይችል የሲዳማ ክልል ፋይናንስ ቢሮ አስታወቀ
ቢሮው በሰጠዉ መግለጫ የፌዴራል መንግስት የክልሉን የመንግሥት ሠራተኛ ከግምት ውስጥ ሳያስገባ የመደበው በጀት ጉድለት በማሳየቱ መክፈል እንዳልቻለ ገልፆል።
ችግሩን ለመፍታት ቢሮው ከፐብሊክ ሰርቨስ ኮሚሽንና ከፋይናንስ ሚኒስቴር ጋር በመናበብ እየሠራ እንደሚገኝና በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንደሚከፍል አስታዎቋል።
Via:- ማለዳ ሚዲያ
@Yenetube @Fikerassefa
😁 31❤ 10👍 1👎 1👀 1
ህወሓት የድሮን ጥቃት እንደተፈጸመበት ገለጸ
በአፋር ክልል ጥቃት የከፈተው ህወሓት የድሮን ጥቃት እንደተፈጸመበት አስታውቋል።
ህወሓት የድሮን ጥቃት የተፈጸመበት ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም መሆኑን ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
የኢትዮጵያን መንግሥት የድሮን ጥቃት በመፈጸም የከሰሰው ህወሓት፣ በአፋር ክልል በከባድ መሳሪያ የተደገፈ ጥቃት መክፈቱ ይታወቃል።
የህወሓት መግለጫ 👇
😁 17❤ 15👍 11😭 3👀 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
በኡጋንዳ አማፂ ቡድን መሪ ጆሴፍ ኮኒ ላይ የጦር ወንጀል ክስ መመሰረቱን የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አረጋገጠ
የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ዳኞች በዩጋንዳው አማፂ መሪ ጆሴፍ ኮኒ ላይ የተፈጸሙ የጦር ወንጀሎችን እና የሰብአዊ መብት ወንጀሎችን አረጋግጠዋል፣ ፍርድ ቤቱ የእስር ማዘዣ ካወጣ ከሁለት አስርት አመታት በኋላ ክሱ ተመስርቷል። በእስር ላይ የሚገኘው ኮኒ ግድያ፣ ወሲባዊ ባርነት እና አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ 39 ክሶች ቀርቦበታል።
ኮኒ ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለረዥም ጊዜ ሸሽቷል።ከ2002 እስከ 2005 በሰሜን ዩጋንዳ የሎርድ ሬዚስታንስ ጦርን በመምራት ኮኒ በወንጀል ተጠያቂ ናቸው ብሎ ለማመን በቂ ምክንያቶች እንዳሉ ዳኞች ተናግረዋል።በአማፂዎቹ ከተፈፀመባቸው ወንጀሎች በተጨማሪ ኮኒ እራሱን ፈፅሟል በተባሉ 10 ወንጀሎች እንዲሁም ሚስቱ እንዲሆኑ ካስገደዳቸው ሁለት ሴቶች ጋር ተያይዞ ተጠያቂ ሊሆን እንደሚችል ዳኞቹ ተናግረዋል።
ኮኒ በሲቪል ሰፈሮች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም፣ ሰላማዊ ሰዎችን እንዲገድሉ እና እንዲበድሉ፣ ንብረታቸውን እንዲዘርፉ እና እንዲወድሙ እንዲሁም ህጻናትና ሴቶችን አፍነው ከአማፂ ቡድኑ ጋር እንዲቀላቀሉ ቋሚ ትእዛዝ ሰጥቷል። የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተጠርጣሪ በሌለበት ክስ ሲያረጋግጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ይህም ማለት ኮኒ ከተያዘ ጉዳዩ በመደበኛነት ወደ ችሎት ሊቀጥል ይችላል ማለት ነው። በአይሲሲ ህግ መሰረት፣ ተከሳሹ በፍርድ ቤት ሳይገኝ የሙሉ ክስ ሂደት ሊጀመር አይችልም።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 6

