TIKVAH-ETHIOPIA
Открыть в Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0998999899 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
Больше2025 год в цифрах

1 573 047
Подписчики
-46124 часа
-1 6017 дней
-2 64930 день
Загрузка данных...
Похожие каналы
Облако тегов
Нет данных
Возникли проблемы? Пожалуйста, обновите страницу или обратитесь к нашему support-менеджеру .
Входящие и исходящие упоминания
---
---
---
---
---
---
Привлечение подписчиков
декабрь '25
декабрь '25
+3 565
в 3 каналах
ноябрь '25
+5 434
в 0 каналах
Get PRO
октябрь '25
+10 710
в 3 каналах
Get PRO
сентябрь '25
+38 343
в 6 каналах
Get PRO
август '25
+6 716
в 4 каналах
Get PRO
июль '25
+5 885
в 3 каналах
Get PRO
июнь '25
+7 838
в 3 каналах
Get PRO
май '25
+7 220
в 2 каналах
Get PRO
апрель '25
+3 976
в 6 каналах
Get PRO
март '25
+7 591
в 3 каналах
Get PRO
февраль '25
+3 610
в 1 каналах
Get PRO
январь '25
+9 170
в 5 каналах
Get PRO
декабрь '24
+7 005
в 2 каналах
Get PRO
ноябрь '24
+14 459
в 4 каналах
Get PRO
октябрь '24
+36 805
в 7 каналах
Get PRO
сентябрь '24
+45 041
в 4 каналах
Get PRO
август '24
+32 002
в 3 каналах
Get PRO
июль '24
+29 509
в 4 каналах
Get PRO
июнь '24
+17 573
в 4 каналах
Get PRO
май '24
+18 474
в 7 каналах
Get PRO
апрель '24
+28 612
в 9 каналах
Get PRO
март '24
+27 551
в 6 каналах
Get PRO
февраль '24
+10 054
в 3 каналах
Get PRO
январь '24
+7 267
в 9 каналах
Get PRO
декабрь '23
+6 565
в 6 каналах
Get PRO
ноябрь '23
+4 990
в 9 каналах
Get PRO
октябрь '23
+55 726
в 12 каналах
Get PRO
сентябрь '23
+5 304
в 7 каналах
Get PRO
август '23
+5 798
в 6 каналах
Get PRO
июль '23
+10 924
в 5 каналах
Get PRO
июнь '23
+192
в 4 каналах
Get PRO
май '23
+6 079
в 6 каналах
Get PRO
апрель '23
+3 717
в 0 каналах
Get PRO
март '23
+2 517
в 0 каналах
Get PRO
февраль '23
+51 346
в 0 каналах
Get PRO
январь '230
в 0 каналах
Get PRO
декабрь '220
в 0 каналах
Get PRO
ноябрь '220
в 0 каналах
Get PRO
октябрь '22
+1 165
в 0 каналах
Get PRO
сентябрь '22
+9 922
в 0 каналах
Get PRO
август '22
+11 915
в 0 каналах
Get PRO
июль '22
+13 795
в 0 каналах
Get PRO
июнь '22
+3 382
в 0 каналах
Get PRO
май '22
+3 363
в 0 каналах
Get PRO
апрель '22
+6 885
в 0 каналах
Get PRO
март '22
+7 552
в 0 каналах
Get PRO
февраль '22
+19 245
в 0 каналах
Get PRO
январь '22
+1 219 483
в 0 каналах
| Дата | Привлечение подписчиков | Упоминания | Каналы | |
| 27 декабря | 0 | |||
| 26 декабря | +2 | |||
| 25 декабря | 0 | |||
| 24 декабря | +35 | |||
| 23 декабря | +25 | |||
| 22 декабря | +92 | |||
| 21 декабря | +112 | |||
| 20 декабря | +63 | |||
| 19 декабря | +135 | |||
| 18 декабря | +112 | |||
| 17 декабря | +82 | |||
| 16 декабря | +330 | |||
| 15 декабря | +44 | |||
| 14 декабря | +79 | |||
| 13 декабря | +93 | |||
| 12 декабря | +57 | |||
| 11 декабря | +319 | |||
| 10 декабря | +754 | |||
| 09 декабря | +314 | |||
| 08 декабря | +110 | |||
| 07 декабря | +78 | |||
| 06 декабря | +48 | |||
| 05 декабря | +188 | |||
| 04 декабря | +300 | |||
| 03 декабря | +66 | |||
| 02 декабря | +64 | |||
| 01 декабря | +63 |
Посты канала
"ቆሻሻው ተንሸራቶ በሁለት ሰዎች የሞት አደጋ አድርሷል። ሰዎቹን ለማውጣት አካባቢው አስቸጋሪ ነው፤ ቢሞከርም እስካሁን አልተቻለም" - የደሴ ከተማ ፓሊስ
በአማራ ክልል ደሴ ከተማ አስተዳደር "መንበረፀሐይ" ተብሎ በሚጠራው የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ትናንት በደረሰ የመምሸራተት አደጋ እስካሁን ባለው መረጃ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የከተማው ፓሊስ መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
የደሴ ከተማ ፓሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ጥላሁን ታደሰ በሰጡን ቃል፣ " አደጋ ደርሷል። አካባቢው የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ነው። ቆሻሻው ተንሸራቶ በሁለት ሰዎች የሞት አደጋ አድርሷል። ሰዎቹን ለማውጣት አካባቢው አስቸጋሪ ነው፤ ቢሞከርም እስካሁን አልተቻለም " ብለዋል።
ከቦታው የወጣው መረጃ፣ ቆሻሻው ተንሸራቶ ሰዎቹን ወደረጅም ገደል እንዳስገባቸውና እንደተጫናቸው፣ አንድ አብሯቸው የነበረ ሰው አራት ጊዜ ተንከባሎ በተዓምር እንደተረፈ ያመላከቱ ሲሆን፣ ኮማንደር ጥላሁን በበኩላቸው፣ " የተደራረበ ቆሻሻ ስለነበር ሲናድ ወደገደል ይዟቸው ሄደና ተጫናቸው። አንድ ሰው ተርፏል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
" ሰዎቹን ለማውጣት ሌላ ተጨማሪ አደጋ የሚያስከትል ሁኔታ ነው ያጋጠመን " ያሉት ፓሊስ አዛዡ፣ ለማውጣት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፣ " የከተማ አስተዳደሩ ሎዶር ለማቅረብ እየሞከረ ነው፤ ግን ቦታው የሚደረስበት አይደለም፤ ገደሉ ርቀት አለው። አሁንም ወደ ቦታው ልንሄድ ነው " ብለዋል።
እስካሁን ባላቸው መረጃ መሰረት ሌላ ጉዳት የደረሰበት ሰው እንደሌለ፣ አንድ ከሟቾች ጋር አብሮ የነበረ ሰው በህይወት መትረፉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ፓሊስ አዛዡ "አዛሳኝ ነገር ነው የደረሰው፤ በጣም አዝነናል" ብለዋል።
ሰዎቹ አደጋ የደረሰባቸው ምን ሊያደርጉ ወደቦታው ሄደው እንደሆነ ስንጠይቃቸው፣ "በአካባቢ ሰው ይሄዳል። አሁን እርግጠኛ ሆኘ እንደህ ነው ማለት አልችልም፤ አብሮ የነበረና ከአደጋው የተረፈውን ሰው መጠየቅና ማረጋገጥ ይጠይቃል" ሲሉ መልሰዋል።
ኮማንደር ጥላሁን ባስተላለፉት መልዕክት፣ "በቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ቆሻሻ በየጊዜ ስለሚደፋ በቀላሉ የመናድ ባህሪ አለው። የጠነከረ መሬት አይደለም። ስለዚህ ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት ቦታ ላይ ልጆቹን መላክ፤ አዋቂውም በቀላሉ መዳፈር የለበትም" ሲሉ መክረዋል።
"ለአካል ጉዳት፣ ለሞት ያጋልጣል። አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች ቤተሰቦች ከባድ ሀዘን ነው ያጋጠማቸው። ስለዚህ ሌላውም ሰው ከእንደዚህ ወደቦታው ከመሄድ መቆጠብ አለበት" ሲሉ አሳስበው፣ አደጋ ለደረሰባቸው ሰዎች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahethiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
49 32100
| 2 | " የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል። በርካታ እንግዶች ወደ ሀዋሳ ገብተዋል " - የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተስፋዬ ዴቢሶ በየዓመቱ በታሕሳስ ወር በሐዋሳ ከተማ በታላቅ ድምቀት ከሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል ዝግጅት ጋር በተያያዘ ቆይታ አድርገዋል።
" በየዓመቱ በታላቅ ድምቀት በሐዋሳ ከተማ ለሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል ሁሉንም የጸጥታ መዋቅሮች ያካተተ የጋራ ግብረ ሃይል ቅድመ ዝግጅቶች ሲያደርግ ቆይቷል " ብለዋል።
ባለፉት ቀናትም በርካታ ቁጥር ያላቸው እንግዶች ወደ ከተማዋ መግባታቸውን ገልጸዋል።
ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ባለፉት ጊዜያት በአልጋ፣ ትራንስፖርትና ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ላይ ይስተዋሉ የነበሩ የዋጋ ጭማሪዎች እንዳይኖሩ ባለድርሻ አካላትን ያካተተ ግብረ ሃይል የቅኝትና ቁጥጥር ስራዎች ሲከናወን መቆየቱን አስረድተዋል።
በተለይም ከዚህ ቀደም ደላሎች አስቀድሞ አልጋ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ኮንትራት በመውሰድ ዋጋ እጥፍና ከዚያ በላይ አድርጎ የማከራየት ተግባራት እንደነበሩ በክትትል እንደተደረሰበትና ይህ ዘንድሮ እንዳይኖር በልዩ ትኩረት ሲሰራ መቆየቱንም አብራርተዋል።
በሌላ መልኩ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከዛሬ ጀምሮ በዓሉ ተከብሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ፦
- ከሱሙዳ አደባባይ እስከ ሳዉዝ ስታር ኢንተርናሽናል ሆቴል፤
- ከሱሙዳ አደባባይ በፒያሳ መስመር እስከ ኬርአዉድ ኢንተርናሽናል ሆቴል፤
- ከሱሙዳ አደባባይ በሎጊታ አድርጎ እስከ ትሩፋት መብራት፤
- ከሱሙዳ አደባባይ እስከ ሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ያሉ መንገዶች ለሁሉም ተሽከርካሪዎች ዝግ መደረጋቸውን አሳውቀዋል።
ለሞተር ሳይክሎች ደግሞ በዓሉ ተከብሮ እስኪያልፍ በከተማዋ ዋና መንገዶች መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።
እንግዶች እንዳይቸገሩ ለ24 ሰዓታት አገልግሎት የሚሰጡ የታክሲ ተሽከርካሪዎች ተመዝግበው የተሰማሩ መሆናቸውንና ታርጋ የሌላቸው ማንኛውም አይነት ተሽከርካሪዎች እንደ ሁልጊዜው ሁሉ በከተማዋ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ አስታውቀዋል።
እንግዶች በሀዋሳ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታ ማንኛውንም ዓይነት መረጃ ለፖሊስ መስጠትም ሆነ መቀበል ቢፈልጉ በነፃ የስልክ መስመር 7614 የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ፤ 8295 የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መጠቀም እንደሚችሉ ኮሚሽነር ተስፋዬ ዴቢሶ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
@tikvahethiopia | 62 570 |
| 3 | ለደዋዮ ለየት ያለ የጥሪ ማሳመሪያ ሙዚቃ መጋበዝ እንደሚችሉ ሰምተዋል? አገልግሎቱን ለማግኘት አሁኑኑ ወደ *722# ይደውሉ!
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether | 54 076 |
| 4 | "ድሬዳዋን እንደ ቦርደር ነው የሚሸጋገሩበት። በሚያሳዝን ሁኔታ በልመና ሁሉ የተሰማሩ ከአማራና ትግራይ ክልሎች የመጡ ሰዎች አሉ። በጣም የሚበዙት ከአማራ ክልል ናቸው’’ - የድሬዳዋ ሴቶች ፌዴሬሽን
በጦርነት እና ጸጥታ አለመረጋጋት ሳቢያ ከአማራ እና ትግራይ ክልሎች ተነስተው ለመሰደድ ድሬዳዋን እንደመውጫ ለመጠቀም የሚሞክሩ ዜጎች በከተማዋ በልመና ተሰማርተው እንደሚገኙ በጥናት መረጋገጡን የድሬዳዋ ከተማ ሴቶች ፌዴሬሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የድሬዳዋ ከተማ ሴቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ኢፍቱ አባስ፣ ‘’ድሬዳዋን እንደ ቦርደር ነው የሚሸጋገሩበት። በሚያሳዝን ሁኔታ በልመና ሁሉ የተሰማሩ በተለይ ከአማራና ትግራይ ክልል የመጡ አሉ። በጣም የሚበዙት ከአማራ ክልል ናቸው” ብለዋል።
“ሲመጡ ወደሌላ ሀገር ለመሸጋገር ነው የእነሱ ፍላጎት’’ የሚሉት ኢፍቱ፣ በቅርቡ ስለጉዳዩ ጥናት እንደተደረገ፣ ጥናቱን ለማድረግ ያነሳሳቸው አንዲት እናት አስፋልት ስትሻገር ሁለት ልጆቿ በመኪና ተገጭተው ሲሞቱባት ወደትውልድ ስፍራዋ ወስዳ እንድትቀብር በመጠየቅዋ በከተማዋ ተፈናቃዮች እንዳሉ በመገመቱ መሆኑን አስረድተዋል።
‘’ያ አደጋ እንደ እናት ያማልና ይህን ነገር ምንድን ነው ማድረግ ያለብን? እስኪ ጥናት ይሰራ ምን ያክል ሰዎችስ ያሉት? ከተማው ውስጥ መኖር የሚፈልጉ ካሉ ዜጎች ናቸውና እንዲኖሩ ምን መሰረታዊ ነገር ልናሟላላቸው ይገባል? በሚል ከሲነርጅ፣ ከሴቶች ፌዴሬሽን ጋር ሆነን ተቀናጀተን ጥናቱ ባለፈው ክረምት ተሰርቷል” ብለዋል።
“ከህጻናት ጋር በትንሹ ወደ 200 ሰዎች ተገኙ” ሲሉም ከአማራና ትግራይ ክልሎች በጸጥታ ችግር ተፈናቅለው ወደ ድሬዳዋ ከተማ የሸሹ ዜጎች መኖራቸው በጥናቱ እንደተረጋገጠ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
“ቤቶችን ለሦስት፣ ለአራት እየተከራዩ የሚኖሩ አሉ፣ ባልተመቼ ሁኔታ ነው እየኖሩ ያሉት የሚባል ነገር መጣ፣ ከዚያም እነርሱን (ሸሽተው የሄዱትን) ለማግኘት ተሞከረ፣ ኢንተርቪው ተደረጉ። አብዛኛዎቹ እዛው (ከነበሩበት ከትውልድ ቦታቸው) ያለው የሰላም ሁኔታ ስላልተረጋጋ ባንመለስ ነው የሚሻለው ብለው ውስጣቸው ጥሩ ነገር አልተሰማቸውም” ነው ያሉት።
“አንዳንዶቹ ደግሞ 'የትራንስፖርት ከቻላችሁን ወደዛው ብንመለስ ነው የሚሻለን' የሚሉም ተመለከትን” ያሉት ፕሬዚዳንቷ፣ መመለስ የሚፈልጉት የመመለስ ስራ እንደተሰራ፣ በአንፃሩ አሁንም በድሬዳዋ እየኖሩ ያሉ እንዳሉ፣ ህጻናቱም ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸዋል።
“ደብተር እንዲገዛላቸው፣ በሚቀርባቸው ቦታ በመንግስት እንዲመዘገቡ አደረግን። ግን አሁንም ማድረግ አለብን ብዬ የማስበው ስራ ብንፈጥርላቸው፣ በዘላቂ መንገድ በራሳቸው ዳቦ የሚያገኙበትን መንገድ ብናመቻችላቸው ጥሩ ነው። ግን አይርባቸውም፣ ሆኖም አለመራባቸውን አይደለም ማየት ያለብን፣ ሁሌም መለመን ስነልቦናን እየጎዳ ነው የሚመጣው” ነው ያሉት።
“አብዛኛዎቹ በልመና ነው ያሉት፣ ስራም የሚሰሩ አሉ፣ በርበሬም እየቀነጠሱ ለሌሎች እያዘጋጁ እየሰሩ ቢያንስ አልራባቸውም። ወንዶችም ማስቲካ ይዘው እየዞሩ የሚሰሩ አሉ። ግን ዘለቄታ አለው ብዬ አላስብም። በዚህ ሁኔታስ እስከመቼ ነው የሚቀጠለው የሚለው ጥያቄ ውስጥ ይከታል” ያሉት ወ/ሮ ኢፍቱ፣ ለዚህም መንግሳታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን እያነጋገሩ መሆኑን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በወባና መሰል ገዳይ በሽታዎች እንዳይጠቁ በማንኛውም ጤና ጣቢያ ሂደው በነጻ እንዲታከሙ መደረጉንም ፕሬዚዳንቷ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia | 147 293 |
| 5 | ሱፐር ኤስ ጂ ኤስ ፈርኒቸር !
🎄የገና በዓል ልዩ የቅናሽ ከስጦታ ጋር ከሱፐር ኤስ ጂ ኤስ!
በዚህ ገና እንግዶችዎን የሚያስደምሙበት፣ የቤትዎን ውበት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድጉ ጥራት ያላቸው የፈርኒቸር ውጤቶችን ይዘንላችሁ ቀርበናል። ያልነውን ካላገኙ ወረታውን እንከፍላለን!
✅ እስከ 40% የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ (ለኪስዎ አዋጭ!) ✅ ለገዢዎች የሚሰጡ ነጻ ስጦታዎች🎅✨
✨ ለምን እኛን ይመርጣሉ?
• ጥራት፡ ፈጽሞ በማንደራደርበት ጥራት ለረጅም ጊዜ የሚያገለግሉ ምርቶች።
• ዘመናዊነት፡ የቤትዎን ድምቀት የሚጨምሩ ከተራው ወጣ ያሉ ማራኪ ዲዛይኖች።
• ሰፊ አማራጭ፡ ከቱርክ በቀጥታ የገቡ (Imported) እና በሀገር ውስጥ በከፍተኛ ጥራት የተመረቱ ሶፋዎች፣ አልጋዎችና የቢሮ እቃዎች።
• ነጻ ትራንስፖርት፡ የገዙትን እቃ ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ እስከ ቤትዎ እናደርሳለን! 🚚
📍አድራሻችን፡- ከሜክሲኮ ወረድ ብሎ፣ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት፣ የድሮ ብስራት ኤፍ ኤም (Bisrat FM) ህንጻ።
📞 አሁኑኑ ይደውሉልን፡ 📱 0947555555 📱 0920753333
ሱፐር ኤስ ጂ ኤስ ፈርኒቸር - ለተመቻቸ ኑሮ! 🛋✨ 🎄 መልካም የገና በዓል! 🎄 | 131 575 |
| 6 | " ከተሞቻችን ገበሬዎችን እያፈናቀሉ ድሃና ለማኝ እያደረጉ ነው " - ባጫ ከበደ (ዶ/ር)
🔴 " እንደሀገር ወጥ የሆነ የመሬት አስተዳደር ፖሊሲ የለንም "- አቶ ቱሉ በሻ
" ላንድ ፎር ላይፍ ኢትዮጵያ " የተሰኘው ሀገር በቀል ተቋም " የመሬት አስተዳደርን ማጠናከርና የመሬት መብቶችን ማረጋገጥ " በሚል መሪ ቃል 3ኛው የኢትዮጵያ የመሬት ቀን የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።
በዚህ መድረክ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የኢትዮጵያ የሕዝብ አስተዳደር ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት፣ በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ባጫ ከበደ (ዶ/ር) እና በGIZ አፍሪካ ህብረት የመሬት አስተዳደር አማካሪ አቶ ቱሉ በሻ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
በዚሁ ወቅት ባጫ (ዶ/ር) ፥ በሀገሪቱ የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ላይ የሚታዩ ስር የሰደዱ ችግሮችን በሚመለከት ጠንከር ያሉ ኃሳቦች አካፍለውናል።
ባጫ ከበደ (ዶ/ር) በዝርዝር ምን አሉ ?
" ከተሞቻችን ገበሬዎችን እያፈናቀሉ ድሃና ለማኝ እያደረጉ፣ በሀገሩ እንዳይኖር አድርገዋል። ይህ እኔንም ይሰማኛል፤ አዲስ አበባንም መመልከት ይቻላል፤ ሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ችግር አለባቸው።
ይህን ችግር ለመቅረፍ ደግሞ መስዋዕትነት ያስፈልጋል። መሬት ለኢንቨስተሮች ስንሰጥ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ያቀፈ መሆን አለበት። አንድን ሰው ከመሬቱ ላይ አፈናቅሎ ሌላ ሰው ማምጣት ልክ አይደለም።
ሰው ሀብት አያግኝ አይደለም፤ ነገር ግን የአካባቢው ማኅበረሰብ በልማት ውስጥ መቀናጀት አለበት፤ ይህ ከሆነ የመሬት ባለቤትነት በቀላሉ ይመጣል።
ከመሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር ጋር በተገናኘ ከሥርዓት ወደ ሥርዓት እየተወራረሱ የመጡ፣ አሁን ላይ ተደራራቢ የሆኑ ችግሮች አሉ።
አክለውም በቴክኖሎጂ ሽግግር ምክንያት የመጡ ተግዳሮቶች አሉ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜም የመሬት አስተዳደር እና የተቋማዊ አሰራር ውስብስብነት እየጨመረ መጥቷል።
ይሁንና ይህንን ችግር ለመቅረፍ በባለሙያው ዘንድ የአቅም ግንባታ ሥራዎች እየተሠሩ አይደለም፤ በትምህርት ደረጃ፣ በካሪኩለምና በምናስተምራቸው ትምህርቶች ላይ ክፍተቶች አሉ። ትምህርቶቹ ሀገራዊ ወይም ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘቡ አይደሉም።
ሀገራችን የምትከተላቸው ሪፎርሞች ከቬትናም፣ ከቻይና፣ ከአሜሪካ እና ከእንግሊዝ የመጡ ወይም በቀጥታ የተቀዱ ናቸው። እነዚህ ነገሮች ቢስተካከሉ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን መቅረፍ ይቻላል።
አሁን ላይ መንግሥት በፖሊሲ የፈቀደውን አሠራር ለሕዝቡ እስከ መከልከል ተደርሷል። መንግሥት ፈቅዶ አድርጉልኝ፣ መረጃ ስጡልኝ ብሎ 'አንሰጥም' የሚሉም አሉ። ይህን ለመከላከል መንግሥት ያለውን የመሬት ክምችት ማወቅ አለበት " ብለዋል።
የመሬት አስተዳደር አማካሪው አቶ ቱሉ በሻ ምን አሉ ?
"እንደሀገር ወጥ የሆነ የመሬት አስተዳደር ፖሊሲ የለንም። አሁን ላይ የመሬት ጉዳዮችን የሚነኩ የሴክተር ፖሊሲዎች ናቸው።
የከተማ እና የገጠር መሬት አስተዳደር ተብሎ በመከፈሉ አንድ ወጥ የሆነ የመሬት አስተዳደር እንዳይኖር አድርጓል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ የገጠሩ ማህበረሰብ ቁጥር እየጨመረ ነው፣ ከተሞች እየተስፋፉ ነው፣ ወጣቱ መሬት የለውም፣ ስራ አጡ እየበዛ ነው፣ ስለዚህ መሬትን በዘላቂነት መጠቀም የሚያስችል ተቋማዊ አደረጃጀት እና አንድ ወጥ የሆነ የመሬት አስተዳደር ፖሊሲ ሊኖረን ይገባል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahethiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia | 205 532 |
| 7 | #Update
#Gambella
" ከተርፋም የተላኩ ተጎጂዎች ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው። 50 ተጎጂዎች ልከውልናል ትናንት። ሁለቱ መንገድ ላይ ህይወታቸው አልፏል። 48ቱ ሆስፒታል ደርሰዋል " - ጋምቤላ ሆስፒታል
⚫️ " በአሁኑ ወቅት ትልቁ የተቸገርንበት የደም እጥረት ነው። አብዛኛዎቹ ተጎጂዎች ብዙ ደም እየፈሰሳቻው ነው! "
በጋምቤላ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ወቅት ተጎድተው ህክምና ላይ ለሚገኙ ታካሚዎች የመድኃኒትና የደም እጥረት እንዳጋጠመው የጋምቤላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ዛሬ ከሰዓት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
በአሁኑ ወቅት በሆስፒታሉ ብቻ ከ65 በላይ ታካሚዎች እንዳሉ አመልክቷል።
በኃላፊነት ላይ የሚገኙ አንድ ሆስፒታሉ አካል በሰጡን ቃል፣ " እንደ ሆስፒታል በከተማው ውስጥም እንቅስቃሴ ስለሌለ መድኃኒት ለማግኘት ተቸግረናል " ሲሉ ገልጸዋል።
" የመድኃኒት እጥረት አለ ፤ ከተለያዩ ቢሮዎች እና አጋር ድርጅቶች ጋር በመነጋጋር እርዳታ እንዲያደርግልን ጠይቀን እየጠበቅን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
የምን አይነት መድኃኒት እጥረት አጋጠማችሁ ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ " አንድ ተጎጂ ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስበት በተለይ በጥይት የተመታ ሲሆን የሚያስፈልጉ የስቃይ፣ የኢንፌክሽን መከላከያ (አንቲባየቲክስ) የሚባሉ መድኃኒቶች፣ የሚፈሰውን ደም ለማስቆም የሚረዱ መድኃኒቶች እጥረት በዋናነት አጋጠሞናል " ብለዋል፡፡
" በአሁኑ ወቅት ትልቁ የተቸገርንበት የደም እጥረት ነው። አብዛኛዎቹ ተጎጅዎች ብዙ ደም እየፈሰሳቻው ነው። በክልሉ ደም ባንክ አቅርቦት አልነበረም። ስለዚህ ከብሄራዊ ደም ባንክ የተወሰነ ደም እንዲልኩልን ጠይቀናል" ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡
ታዲያ የጠየቃችሁት የደም ድጋፍ ተልኮላችኋል ? የሚያስፈልጋችሁስ ምን ያክል ነው ? ለሚለውን ጥያቄም፣ " እስካሁን አልተላከልንም እስከ ነገ እንልካለን እያሉ ነው። ቢያንስ ከ100 ዩኒት በላይ ደም ቢሰጡን የተሻለ ነው፣ ቢያንስ እስከ 100 ዩኒት ያስፈልገናል። ምክንያቱም አንድ ተጎጅ ብቻ ብዙ ደም ስለሚፈሰው እስከ አምስት ዩኒት ሊጠቀም ይችላል " ሲሉ መልሰዋል።
ከመድኃኒት እጥረት ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር ሲያስረዱም፣ " አሁንም ሆስፒታሉ እየተሯሯጠ ነው ያለው " ያሉ ሲሆን፣ በተለይ ከደም መፍሰስ ጋር በተያያዘ የሚያስፈልገው " የፍሉድ መድኃኒት " ችግር በመኖሩ የክልሉ ጤና ቢሮ እንዲልክላቸው መጠየቃቸውን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በክልሉ በሚገኘው ኝንኛንግ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚሰሩ ሀኪም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን ሰጥተዋል።
ሀኪሙ ከትላንት ወዲያ በኢታንግ ልዩ ወረዳ በነበረው ተኩስ የተጎዱ ከ50 በላይ ሰዎች ወደ ጋምቤላ የመጀመሪያ ሆስፒታል ሪፈር እንደተደረጉ ገልጸዋል።
መንገድ ዝግ በመሆኑ ወደ እነርሱ ተቋም የሄዱት ሁለት ተጎጅዎች እንደሆኑ አስረድተዋል።
ከተርፋም በፊት በነበረው ጥቃት ጭምር 10 ሰዎች በሆስፒታሉ መታከማቸውን፣ ባለፈው ሳምንት ወደ ጅማ ሪፈር ተጽፎላቸው የነበሩ ሦስት ተጎጅዎችም ወደ አዲስ አበባ ሪፈር ተብለው ገና በህክምና ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ከትናንት ወዲያ በኢታንግ ልዩ ወረዳ (ተርፋም ቀበሌ) በነበረው ተኩስ የተጎዱ ስንት ታካሚዎች ወደ ሆስፒታሉ መጥተዋል ? ሲንል የጠየቃቸው የጋምቤላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አካል በበኩላቸው፣ " ከተርፋም የተላኩ ተጎጅዎች ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው። ወደ 50 ተጎጅዎች ልከውልናል ትናንት " ብለዋል።
" ከእነዚህ መካከል ሁለቱ መንገድ ላይ እያሉ ሕይወታቸው አልፏል። 48ቱ ናቸው ሆስፒታል የደረሱት፡፡ አሁን ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛሉ። 48ቱ ሁሉም ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው " ሲሉ አክለዋል።
ከተርፋም ተኩስ በፊትም በተለያዩ ወረዳዎች ተኩስ እንደነበር ይታወቃል፣ በዚያ ወቅት በአጠቃላይ ምን ያክል ተጎጅዎች ናቸው ወደ ሆስፒታሉ መጥተው ህክምና ያገኙት ? ለሚለው ጥያቄ፣ " በየጊዜው መንገድ ላይ ባስ፣ የሆስፒታል አውምቡላንስ ላይ ጭምር ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ነበሩ " ብለዋል፡፡
" በሌላ ተቋም ሪፖርት የሚደረጉ አሉ " የሚሉት የሆስፒታሉ አመራር፣ የጋምቤላ የመጀመሪያ ሆስፒታል ቀጥታ ሪፖርት ማድረግ በሚችለው ብቻ ከተርፋሙ ግጭት በፊት ወደ ሆስፒታሉ 22 ቁስለኞች እንደሄዱ፣ 10 በመንገድ ላይ እንደሞቱ፣ በሌሎች ተቋማት ሪፖርት ከሚደረጉት ጋር ሲሆን ወደህክምና ያቀኑ ቁስለኞች ቁጥር ከዚህ ከፍ እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡
በተርፍም ጥቃት ወደ ሆስፒታሉ ለህክምና ከሄዱት 48 ተጎጅዎች በተጨማሪ በፊተኛው ጥቃት ለህምክና ወደ ጋምቤላ ሆስፒታል የሄዱ 18 ተጎጅዎች አሁንም በሆስፒታሉ እንዳሉም አመራረሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በመድኃኒት እጥረት ወይም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አጋጥሟቸው እንደሆነ ስንጠይቃቸውም፣ " አንድ ተጎጁ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ ህይወታቸው አልፏል " ብለዋል። በተኩሱ የቆሰሉት ሴቶችና ህፃናት ጭምር መሆናቸውን፣ በሆስፒታሉ ሦስት ሴቶችና አንድ ህፃን፣ በሌሎች ተቋማትም በርካቶች እንዳሉ ገልጸዋል።
"የተዘጋው መንገድ መከፈት አለበት። እኛ የመጡትን ተጎጂዎች አብዛኞቻቸው ዘግይተው ነው የደረሱት። አንድ በሽተው ቁስል ካለበት ኢንፌክሽን ሳይፈጥርበት ነው መታከም ያለበት። ነገር ግን መንገድ በመዘጋቱ ቁስለኞች አብኞቻቸው ኢንፌክሽን ከፈጠረባቸው በኋላ ነው የተላኩት" ሲሉም ገልጸዋል።
በጋምቤላ ሆስፒታል ያጋጠመውን የመድኃኒት እና የደም እጥረት ለመፍታት ምን እንደተደረገ እንሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሚመለከታቸው ተቋማትን የሚጠይቅ ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahethiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia | 185 911 |
| 8 | እስራኤል ለሶማሊላንድ የሃገርነት እውቅና ሰጥታለች። በዚህም ለሶማሊላንድ የሃገርነት እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ ሃገር ሆናለች።
ላለፉት 30 አመታት የሃገርነት እውቅና ለማግኘት ጥረት ላይ የነበረችው የነበረችው ሶማሊላንድ በመጨረሻም ሙከራዋ ተሳክቶ ከእስራኤል የሃገርነት እውቅና አግኝታለች።
የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር እስራኤል እና ሶማሊላንድ የሙሉ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን ለመጀመር፣ አምባሳደሮችን ለመመደብና ኤምባሲዎችን ለመክፈት መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኔያሁ ከሶማሊላንዱ ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን እውቅናው ታሪካዊ ነው ብለውታል።
ኔታኔያሁ ዛሬ ሶማሊላንድን እንደ ነፃ እና ሉዓላዊ ሃገር እውቅና መስጠታቸውን አውጀዋል።
እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና የሰጠችው አመት ከፈጀ ንግግር በኋላ መሆኑንም አስታውቃለች።
እስራኤል እውቅናውን የሰጠችው በፕሬዚዳንት ትራምፕ አነሳሽነት በተረቀቀው የአብርሃም ስምምነት አማካኝነት መሆኑ ተገልጿል።
እነማን ተቃወሙ ?
ሶማሊያ ፦ የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ሶማሊላንድ አንዷ የሶማሊያ አካል መሆኗን በመግለፅ የእስራኤልን ውሳኔ ተቃውማለች። የሀገሪቱ ግዛታዊ አንድነት እንዲከበር አሳስባለች።
ግብፅ ፦ ግብፅ ከሌሎች ጋር በመሆን እስራኤል የሰጠችውን እውቅና ተቃውማለች። የሶማሊያ አንድነት እና ሉዓላዊነት እንዲከበር አስገንዝባለች።
ቱርክ ፦ ቱርክ የእስራኤልን ውሳኔ ተቃውማለች።
ጅቡቲ ፦ ጅቡቲም የእስራኤልን ውሳኔ በመቃወም ከግብፅ ፣ ቱርክ እና ሶማሊያ ጋር በመሆን መግለጫ አውጥታለች።
@tikvahethiopia | 188 869 |
| 9 | "በአንዳንድ ቦታዎች መንገድ አጥረው ሲያበቁ ሰዎች ለማለፍ ሲሄዱ በዚህ በኩል እንዴት ትመጣለህ ተብሎ የሚደበደብባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ከህብረተሰቡ ይሰማል" - አቶ ኢያሱ ሰለሞን
"መንገድ የሚያጥሩ አካላት ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምንም መንገዱ ለተገነባለት ዓላማ ጥቅም እንዳይውል ማደረግ ህገወጥ ድርጊት ነው"!
የከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ያጠሩ ሰዎች ምክንያታቸው ምንም ቢሆን ማጠራቸው ተቀባይነት እንደሌለው፣ መጠኑ የተለያዩ ቢሆንም በሁሉም አካባቢዎች መንገዶች እንደታጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
የባለልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኢያሱ ሰለሞን፣ "የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን አጥሮ መዝጋት በስፋት እየተከናወነ ያለ ህገወጥ ድርጊት" መሆኑን፣ አጥሩ እንዲነሳ መልዕክት ሲያስተላልፍ ቢቆይም፣ "ከመሻሻል ይልቅ የመስፋፋት አይነት አስማሚያዎች" መታየታቸውን ገልጸው፣ ባለስጣኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን አጥሮቹን የማፍረስ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ሰዎች የውስጥ ለውስጥ መንገድ ያጠሩበት ምክንያት ምን እንደሆነ ጠይቃችሁ ነበር? ምክንያታቸው አሳማኝ ከሆነ መፍትሄ አስቀምጣችኋል? ከዚህ በፊት የታጠሩ መንገዶችን አጥር የማንሳት ሥራ ተጀምሮ ነበር፤ ለምን ተቋርጦ ቆዬ? ሲል ለአቶ ኢያሱ ጥያቄ አቅርቧል።
ኃላፊው ምን መለሱ?
"ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምንም መንገዶች በከተማዋ መዋቅራዊ ፕላን መሰረት ሲገነቡ ደረጃቸው ይለያይ እንጂ ትራፊክ ለማሳለጥ ተብለው ነው።
የእግረኛውንም የተሽከርካሪውንም እንቅስቃሴ በተገቢው ሁኔታ ለማስተናገድ ነው መንገዶች የሚከፈቱት ከዚህ ውጭ ሌላ ዓላማ የላቸውም። ስለዚህ መንገድ የሚያጥሩ አካላት ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምንም መንገዱ ለተገነባለት ዓላማ ጥቅም እንዳይውል ማድረግ ህገወጥ ድርጊት ነው።
ምክንያት የሚለው ነገር ምንም አሳማኝነት ሊኖረው አይችልም። ሰው መንገድ ላጠረበትን ምክንያት የተለያዩ ጉዳይ ሊያነሳ ይችላል፤ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምንም ግን በከተማዋ መዋቅር ለመንገድ የተተወ ቦታ የመንገድ አገልግሎት እንዲሰጥበት ነው። ያ ማለት ደግሞ በአንድ አካባቢ ለሚኖሩ ብቻ የተፈቀደ ሳይሆን የሁሉም ህብረተሰብ የጋራ መጠቀሚያ ነው።
አንዳንድ ቦታዎች ላይ መንገድ አጥረው ሲያበቁ ሰዎች ለማለፍ በአካባቢው ሲሄዱ በዚህ በኩል እንዴት ትመጣለህ ተብሎ የሚደበደብባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ከህብረተሰቡ ይሰማል።
የመንገድ አካል ስለሆነ ለግንባታ ፈቃድ ስለማይሰጥበት የግል ይዞታ አድርጎ ለማካተት ስለማይሞከር እንጅ፣ የመጋዘን በር የሚመስል፣ ሰው እንኳን ወደ ውስጥ ማለፍ አይደለም ማየት የተከለከለበት እስኪመስል ድረስ አጥር የሚታጠርባቸውም ሁኔታዎች አይተናል። ድርጊቱ ያልተገባ ነው መስተካከል አለበት" ብለዋል።
አጥር ማንሳቱ ተቋርጦ መቆየቱን በተመለከተ በሰጡን ምላሽ ደግሞ፣ "በተለያዩ ጊዜያት ሥራዎቹን ለመቀጠል ተሞክሯል። ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ ነበር። ምክንያቶቹን ለመጥቀስ እቸገራለሁ። ተቋርጦ ቢቆይም አሁን መጀመሩ ትክክል ነው" ብለዋል።
የውስጥ ለውስጥ መንገዶች መታጠር ስላስከተለው ጉዳት አቶ ኢያሱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ?
"ሁሉም ማህበረሰብ በእኩልነት የመጠቀም መብትን ስለሚጋፋ በሰው፣ በትራፊክ እንቅስቃሴው አሉታዊ ተፅዕኖ አምጥቷል።
መንገዶች ሲዘጉ በሌሎች መንገዶች ተሽከርካሪዎች ተጨናንቀው ይጓዛሉ፣ ይህም ለትራፊክ አደጋ ተጽዕኖ አሳድሯል። በአደጋ ጊዜ የአደጋ እርዳታ ለማድረስ የእሳት አደጋ፣ የአምቡላንስ እንቅስቃሴ ገድቧል። የከተዋማ ገጽታም ላይ የፈጠረው ችግር አለ" ብለዋል።
ይህን ከግምት በማስገባት በመጀመሪያ መንገዶችን የዘጉ አካላት እንዲያነሱ የጊዜ ገደብ ሰጥቶ መልዕክት መተላለፉን የገለጹት አቶ እያሱ፣ "በተሰጠው የ7 ቀናት የጊዜ ገደብ ውስጥ የተወሰኑ ፈቃደኛ ሰዎች በራሳቸው ፈቃድ ያነሱ አሉ፣ ግን አብዛኛው ቦታ ላይ ብዙ ለውጥ አላየንበትም" ሲሉም ተናግረዋል።
ስለዚህ ከትላንት ጀምሮ የማንሳት ሥራውን እያከናወኑ እንደሆነ በማስረዳት፣ "ችግሩ አንድ ቦታ ላይ የሚገልጽ አይደለም፤ ስፋትና ጥልቀቱ ቢለያይም በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች ተመሳሳይ ችግሮች አሉ" ብለው፣ "ይህን ለማተካከል ባለፉት ሳምንታት ባለድርሻ አካላት ጠርተን በጉዳዩ አሳሳቢነት ላይ የጋራ ውይይት ተደርጎበታል" ነው ያሉት።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia | 218 260 |
| 10 | 🎄 የገና በዓል ልዩ የቅናሽ ከስጦታ ጋር ከሱፐር ኤስ ጂ ኤስ! 🎁
በዚህ ገና እንግዶችዎን የሚያስደምሙበት፣ የቤትዎን ውበት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድጉ ጥራት ያላቸው የፈርኒቸር ውጤቶችን ይዘንላችሁ ቀርበናል። ያልነውን ካላገኙ ወረታውን እንከፍላለን!
✅ እስከ 40% የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ (ለኪስዎ አዋጭ!) ✅ ለገዢዎች የሚሰጡ ነጻ ስጦታዎች 🎅✨
✨ ለምን እኛን ይመርጣሉ?
• ጥራት፡ ፈጽሞ በማንደራደርበት ጥራት ለረጅም ጊዜ የሚያገለግሉ ምርቶች።
• ዘመናዊነት፡ የቤትዎን ድምቀት የሚጨምሩ ከተራው ወጣ ያሉ ማራኪ ዲዛይኖች።
• ሰፊ አማራጭ፡ ከቱርክ በቀጥታ የገቡ (Imported) እና በሀገር ውስጥ በከፍተኛ ጥራት የተመረቱ ሶፋዎች፣ አልጋዎችና የቢሮ እቃዎች።
• ነጻ ትራንስፖርት፡ የገዙትን እቃ ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ እስከ ቤትዎ እናደርሳለን! 🚚💨
📍 አድራሻችን፡- ከሜክሲኮ ወረድ ብሎ፣ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት፣ የድሮ ብስራት ኤፍ ኤም (Bisrat FM) ህንጻ።
📞 አሁኑኑ ይደውሉልን፡ 📱 0947 55 55 55 📱 0920 75 33 33
ሱፐር ኤስ ጂ ኤስ ፈርኒቸር - ለተመቻቸ ኑሮ! 🛋✨ 🎄 መልካም የገና በዓል! 🎄 | 191 822 |
| 11 | ✨🎁 አየር ሰአትና ጥቅል ከውጭ አገራት ይቀበሉ፤ 50% ተጨማሪ የበዓል ስጦታ ያግኙ!!
ከውጭ ሀገራት በአጋሮቻችን
✅ Ethio remit ✅ EZECALL
✅ Prepaynation ✅ ding
✅ reloady ✅ Omnivas
✅ Boss
በኩል ከ150 ብር ጀምሮ የተላከልዎን የሞባይል አየርሰዓት ወይም ጥቅል ሲቀበሉ:-
💁♂️ ለ15 ቀናት የሚያገለግል የ50% ተጨማሪ ስጦታ እናበረክትልዎታለን፡፡
ደንብና ሁኔታዎች 👉 https://bit.ly/4j7iOcI
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia | 191 533 |
