ru
Feedback
ግጥም ብቻ 📘

ግጥም ብቻ 📘

Открыть в Telegram

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch @shiyach_bicha@zefenbicha @leul_mekonnen1

Больше
2025 год в цифрахsnowflakes fon
card fon
65 775
Подписчики
-324 часа
-397 дней
-30130 день
Архив постов
‎እኔ አፍቅሬያት ሌላ አፍቅራ ‎እሱም ቀርቶ ወልዳ አግብታ ‎          እያየሁ ‎          እቀናለሁ  ‎ባለፈው ትላንቷ በዛሬው እኔነቴ ‎       እቀናለሁ ጅልነቴ ‎አወየው ጉዳቴ አወዬው ፈተና ‎አትታደል ፍቅር ተብያለሁ ቅና ‎ካንድ አምላክ ቸርነት ብማፀን ብጠና ‎እኔው ባወራኋት በኔው እቀናለው ‎          ወዳታለሁና ‎ ‎እኔ አፍቅሬያት ሌላ አፍቅራ ‎አወየው ጉዳቴ አወየው መከራ ‎ ‎ ‎ዮኒ ‎     ኣትን @yonatoz @getem @getem @getem
Показать все...
22😢 19🔥 7😁 2
ተቁነጥንጣ ቀረበችኝ ተቻኮለች እንዳፈቅራት ፣ ተጨነቀች ወዲያው ደሞ ተቻኩየ ስላቀፍኳት ፣ ትፈጥናለች ለማግኜት ልቤን አርጋው የቀበሌ  ፣ ታምር አርጋ ቆጠረችው በእሷ ፍቅር መቸኮሌ ፣ መቸኮልን አስለምዳኝ ተጣድፎ ዝግታየን አቻኩላ አገባችኝ እይ ስትል እድሜየን ፣ ተቻኩላ አስለምዳኝ ረጋ ያለ አረማመድ  ፣ ተቻኩየ ጥያት ሄድኩኝ ቀድማ ከእኔ እንዳትራመድ ፣ @geez_mulat ግዕዝ ሙላት 🦘 @getem @getem @paappii
Показать все...
37😁 6🔥 5👎 4😢 3🎉 1
አበባዬ ብዬ አላሸታት ነገር ወይ ውሃ አላጠጣት አላስታቅፍ አፈር ወይ አትመጣ ከኔ ፍቅሬን አልናገር ... ጠረኗ አልደረሰኝ ሆና ከሩቅ ሀገር ግና ቆም ብዬ ሳስበው እሷ ንግሥት ሆና ሀገሬን ብታየው እኔ ንጉሥ ሆኜ ጠረኗን ብምገው አበባዋን ቀጥፋ ተፈጥሮውን ለየው ብላ ብጠይቀኝ አሳያት ነበረ ያ ጠቢብነቴን መስኮት ዳር ወስጄ በጠረኑ ብቻ ንብ መንጋ መጥራቴን by ዳግማዊ@Dagimawisisay @getem @getem @paappii
Показать все...
25🔥 2
‎ስወድሽ ተረታሁ ‎በደቂቅ ደቃቁ ‎ግርማነቴን ጣሉት ‎ወረድኩ ከሰንደቁ ‎ ‎ስወድሽ ወደኩኝ ‎ኮኮቤ ነሽ ብዬ ኮኮብ አሰቀልኩኝ ‎ ‎ኮከብነትሽም አልፈየደም አንድም ‎አንቺም ታደያለሽ ወደራስሽ ግድም ‎ ‎ስወድሽ ተደፋሁ ‎ይሁን ባልኩኝ ባለም... ተከፋሁ ‎አይቼ እንዳልገባኝ ስንት ነገር ገፋሁ ‎ ‎ልብሽ ላይፈልገኝ ሁሌ እየነገርሽኝ ‎በፈገግታሽ ብቻ የግልሽ አረግሽኝ ‎ ‎ስወድሽ አስመሰልኩ ‎መልስሽን ወሬሽን እንዳላወኩ መሰልኩ ‎ፍቅር ይሻል ብዬ እያየሁኝ ታዘብኩ ‎ፈገግ እንዳልገባኝ ‎ፈገግ እንዳላወኩ ‎በማስመሰል ንዳድ ‎በድርጊትሽ ታወኩ ‎ ‎ስወድሽ ተረታሁ ‎አንቺን ማጣት ፈራሁ ‎ ‎አብዝቼ ፈለኩሽ ‎አብዝተሽ ገፋሺኝ ‎አታውቂውም እንጂ እንዲህ ነው ያደረግሽኝ ‎  ‎መለስ ወደኋላ ‎መለስ ወደፊቴ ‎የጠቀመሽኝ መስለሽ ገለሺኛል ስንቴ ‎ ‎በበፊት ነገርሽ ዛሬን አግኝተሻል ‎ዙፋን ላይ ወርጄ ዙፋን ላይ ወተሻል ‎ጊዜ አይመጣም ብለሽ ጊዜሽን ወስደሻል ‎ ‎ጊዜ ተገልብጦ ጊዜ ይገፋልና ‎ጠንቀቅ በይ አለሜ ወድሻለሁና ‎ ‎ስወድሽ ተከፋሁ ‎አይቼ እንዳለየሁ ስንት ነገር ገፋሁ ‎ ‎ ‎ ዮኒ ‎      ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
Показать все...
28😢 7🔥 3👍 1😱 1
እርግማን ነው //////////////// አፈር ይብላው፣ ያ ገላሽን መቼስ እንደው አይቀርለት፣ እርጅና ይብላው፣ ያ መልክሽን እሱም እንደው አይቀርለት። መርገም አላውቅ መንገድ ጠፋኝ፣ አንችን ብዬ ሳላገኝሽ በጣም ከፋኝ፣ ልራገም ነው በይ ተቀበይ፣ ልብሽ እንደው እኔን አንዴ ባፈቀረኝ። እርግማን ነው አትሳቂ፣ ሳያገኙ ማፍቀር ህመሙን እወቂ። እርግማን ነው ብሸዬሽ የለ፣ ቂም እንደሆን በፍቅር የለ። ያኔ ድሮ ገፍተሽኛል አዎ አውቃለሁ፣ ይህ እርግማን ሲደርስብሽ ቂሙን ትቼ እወድሻለሁ። ሞኝ አደለው። @abela_black @getem @getem @getem
Показать все...
40🔥 6🤩 5
ምን ሊወስድ ይመጣል (በእውቀቱ ስዩም) አንቺ ጻድቅ መሳይ፥ ጭምት ለማያውቅሽ እኔን አርጎ ፈጥሮኝ፥ ስጋ -ለበስ ጥንቅሽ እንኳንስ መረቄ፥ ቅርፊቴ ማይጣል ሞት በቀጠሮው ቀን፥ ምን ሊወስድ ይመጣል:: @getem @getem @paappii
Показать все...
38👍 6👎 1🔥 1
     🤲አሜን በይ ልመርቅሽ ቆሻሻው ተቃጥሎ ሀገር ምድሩ ፀድቶ ታፍኖ የቆየ ፍቅር አገርሽቶ በጦቢያ ምድር ህዳሩ ሲታጠን በለተ ሚካኤል አሜን ሰላም ይስጠን::                አሜን! ሰላም ውሎ ይደር ቀዬው አድባሩ ከመስጊዱ አዛን ቅዳሴው ከደብሩ አይስተጓጎሉ ኬር ሆኖ መንደሩ::            አሜን! አቦል ጀባ ጀባ ቶና እና በረካ አቦ ሀጃ ይውጣ ጠጥተን እንርካ ኑሯችን ይስመር እንደ ፅጌ ይፍካ::               አሜን! አሜን በይ ይሁን ከአሜን ይቀራል የከረመ በቀል በፍቅር ይሻራል! ቤትሽ ፍቅር ይሙላው ካምናው እጥፍ አርጎ ውልቅ ይበል ችግር ማጣት ተጠራርጎ::           አሜን! ልጆችሽ ይደጉ በእውቀት በምግባር ሰውሮ ያቆያቸው ከጦርነት ግንባር አሜን ልብ ይስጣቸው የሚታይ በተግባር:: አንደበትሽ ይጣፍጥ የነካሽው ይብዛ ያንቺን ስራ አይቶ ሰውዘር አደብ ይግዛ::             አሜን! By @Abuugida @getem @getem @paappii
Показать все...
105👍 6🤩 4🔥 1
ቀሚስሽ ደግ ነው መሰሰት አያውቅም ደጅ ለጠናበት ለጋሽ ነው አይነፍግም አርሂቡ አርሂቡ ሁሉን ተቀባይ ነሽ ቀጭን አትይ ወፍራም ጥቁር አትይ ቀይ መቼ ትመርጫለሽ! አርሂቡ! አርሂቡ ግቡ ተቋደሱ አንተም ያዝ አንተም ያዝ እስኪ ተቃመሱ . እንኩ ነው ልሳንሽ ላንኳኳ በሙሉ ለስሜት አበጋዝ የሚገልብሽ ሁሉ እንኩ ነው በነጋ እንኩ ነው በመሸ ያ ነጩ ቀሚስሽ በመስጠት ጠለሸ እንካ ያልሽው ተቀባይ አጣጥሞ ጣለሽ ልክ እንደ ማስቲካ ወትሮም ቅሉ አያምር በሁሉ የተነካ [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @getem @getem @getem
Показать все...
😁 43 32🤩 15👎 10👍 7😢 6🔥 2
እንደ ፍያታዊ መስቀል ተቀብሮ እንደተረሳ ወይ እንደ መበለት ቀሚስ ተሰጥትቶ እንዳልተነሳ ኖርኩ ለማለት ያህል የ-የዕለት ሌት እያነጋሁ እንዲሁ በዝምታ እንደረጋሁ ! ያው የ ሰማንያ እድሌን ከህይወት ሳልጠጋ ብቻዬን የምቀር ይመስለኛል By Bo Hamian @getem @getem @paappii
Показать все...
18😁 7🔥 1
‎ #ሰሞነኛ ምን ባይኖረን ግራ ግጣም ‎ ካሳባችን አንድ አናጣም ‎ ምን ባንዞር ተተቃቅፈን ‎ ልብ ያወራል አፍ ያፈነን ‎ ‎ምሳር ባልታጣባት በዚች እርኩስ አለም ‎     ሲንግል ሁሉ ነፃ አይደለም!። ‎ ‎ ዮኒ ‎      ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
Показать все...
33👍 8🤩 8
እነዚያ ቀናቶች....... በትዝታ ማህደር ያጠራቀምናቸው፤ ትላንት፣     ከትላንት ወዲያ፣         አምናና ካች አምና ብለን ምንጠራቸው፤ ትዝ አሏቹ  አይደል? ያለቀስንባቸው፤ በተስፋ ተሞልተን ጎንበስ ያልንባቸው፤ ክፉንም ደጉንም ስንት ያየንባቸው........          አይገርምም? ጊዜ ዳኛ ሆኖ ይኸው ዛሬ አለፉ በትዝታ ገፅ ላይ ደብዝዘው ተፃፉ::            ተመስገን! By @Abuugida @getem @getem @getem
Показать все...
51👍 19🔥 6🤩 2
‎ "ልብህን አድምጥ" የምትል መሪ ቃል ‎    አባነነኝ ካለም ፅሁፍ ልብ ያነቃል ‎ ‎ ልቤን አዳመጥኩት ‎              ሞልታዋለች እሷ ‎ ፍቅርን አሸተተኝ ‎              ካካሏ ከነብሷ ‎ ሳላስብ ወደድኳት የድንገት የድንገት ‎ ፍቅር ሃሳብ ‎ ፍቅር ስሌት ባንድ እሷ ሞላበት ‎ ተመኘሁኝ እድል ግቤን ‎          ከሷ ጋራ እንዲያጣምረኝ ‎ አልሆነለት ሁለት ወገን ‎         ጊዜን ወስዶ ወይ አልማረኝ ‎ ‎ ‎  "ልብህን አድምጥ" የምትል መሪ ቃል ‎    አባነነኝ ካለም ፅሁፍ ልብ ያነቃል ‎ ‎ነቃሁኝ ‎አፈቀርኩ ‎ ሻትኩኝ ልቧን ለኔ ‎አይ እድል ጠማማው ‎አላገኛት ጎኔ ‎ ‎ ‎ ዮኒ ‎      ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
Показать все...
38🔥 6👍 4
የቀይ አስኳል ፍም ገላ የልጅነት ምጥን ቅጠል አንቺን ነክቶ ማስመለስ ነው ሲያድሩ ውለው ለመቃጠል የለሆሳስ አዝራር ድምፅ የዝግታ ውበት ካላ ! ያንቺን መርጋት የሚያክል ሌላ ኩሬ ወዴት አለ ? ክንዴ ስር ያለው ሙቀት አንገትሽ ነው የሚያውሰው ወዝ ሆኜ መልካም ጠረን ካንቺ ሌላ ማን አዋሰው ይሄ እግሬ በረድ ሆኖ ሌቱን ሙሉ ሚቀዘቅዝ ያንቺን ትንፋሽ እስኪያነቃው ከብርድ ጋር ይቋመራል በእንቅጥቅጥ የእርክዝ ' ' @geez_mulat🦘 ግዕዝ ሙላት @getem @getem @getem
Показать все...
34🔥 4😁 2
መውድስ ብቻ ሳቋ እንደ ፀበል ፥ ያስለፈልፋል ከንፈሯ እንደ ዛር ፥ ግጥም ያጽፋል አይኗ ያበራል ደግሞም ያስፈራል ልብ ፥ ኩላሊት ይመረምራል ፤ የሰው ልጅ እንዴት እንደዚህ ያምራል ? የሌለ ውበት የሌለ እውነት ታይቶ ፥ ተሰምቶ ፤ የማያውቅ አይነት ታምር ናት ታምር ሁሌ ምታምር የውብ ነገሮች ፥  ጠቅላላ  ድምር ! ደማም ፥ መልከ-ጥር አዳዲስ ቃላት ፥ የምታስፈጥር አምራ እምራ ማታልቅ ፥ በታየች ቁጥር ልቤም ተረትቶ ሌላ የኑሮ ፥ ኮተቱን ትቶ ከገላዋ ላይ ፥ ውበት ይቆጥራል ከሰው መሆኗን ከእኛ መሆኗን ፥ ይጠራጠራል የሰው ልጅ እንዴት እንደዚህ ያምራል ? By Habtamu Hadera @getem @getem @paappii
Показать все...
83
ጥቁር እሳት እ..ፍ🔥 እ..ፍ💧 አጥፉት ሳቱን ሊያቃጥለን ከደጅ ደርሷል፣ አፈር አምጡ ወይም ቅጠል ውሃ ያልነው ሰደድ ሆኗል ፣ እባካችሁ አትጩኹ ፀጥታ ነው የሚያጠፋው፣ ድብልቅልቅ መሆኑ ነው ጩኸታችን ሚያኮላትፈው፣ ( አንቺ ሴት ) እሪ አትበይ ከጥግ ከጥግ አትለውጭም ምንም ለእሳት ፣ አንድያውን ካገር መጥፋት ወይም አፈር ቅጠል ማንሳት ፣ አትቅለስለስ ጎረቤቴ አትደበቅ ካልሆነ ፍም ፣ ቀን ይፈጅ ይሆን እንጅ ይሄ እሳት ካንተ አያልፍም ፣ (አንተ ) ' አልጋ ስር አትደበቅ እንዳልሰማ ጩኸታችን ፣ እሳትህ ነው አይባልም እኔ ስልህ እሳታችን ፣ የችግኝ ዛፍ ቁረጭልኝ ባገር በዝቷል ቅጠል ችግኝ ፣ እሳቱ ጋር አለሁበት ከለምለም ጋር አትፈልጊኝ ፣ ባንድ ሰፈር ጎጆ ሰርተን የኔ ደጅ ላይ ቢቃጠልም ፣ እሳት ሲባል ተጓዥ እንጂ በተናጥል አያቃጥልም ፣ የከመርኩት የጤፍ ቦታ ቀድሞ ከእኔ ቢያስርበኝም፣ የጎረቤቴ ዝምታ እንጂ ራህብማ አልጎዳኝም፣ አይደርስ መስሎት ሰደድ እሳት እንደለኮስኩ ለሰው አማኝ ፣ ቢነደኝ ነው የእሳት እሳት ሳያወድመኝ የሚያጣቃኝ ፣ እፍ በይ ይሄን እሳት እፍ በለው ተባበረኝ፣ ዘንቦ እስኪቆም የእግዜር እንባ የውሃ አምላክ እስኪፈርደኝ ፣ ..............ለዚህ እሳት ዕንባ አውሰኝ፣ ግዕዝ ሙላት 🦘 @geez_mulat @getem @getem @getem
Показать все...
34👍 4
     በምን ላማልልሽ? ምን ቃል ይስብሻል የቱ አቀራረብ ምን ዘዴ ልዘይድ ወዳንቺ ለመቅረብ? አንቺ ሆይ ንገሪኝ..... በትዝታሽ ዞትር እንዳልብሰለሰል ምን ቅኝት ልጋብዝሽ ባቲ ወይስ አምባሰል? ምን ዘዴ ልጠቀም ልብሽ ለማማለል? ጦማር ልላክልሽ በፖስታ አሽጌ ልብሽ ሚያቀልጡ ውብ ቃላት ፈልጌ÷ እንዴት ልግለፅልሽ እንድትሆኝ የግሌ እኔ ያንቺ እንድሆን ከነ ሙሉ አመሌ፡፡? አንቺን ሚገልፅልኝ የማማልልበት አፍቃሪዬ ሆነሽ በእጄ ማስገባበት ምን ዘፈን ጋብዤሽ ልብሽ ውስጥ ልግባበት? በግጥም ልንገርሽ በስንኝ ቋጥሬ ገጣሚ ነኝ ብዬ ቃላትን ደርድሬ÷ እንዴት ላማልልሽ እንዲገባሽ ፍቅሬ? ነጠላ ለብሼ ቅዳሴ ላስቀድስ አንቺን ለማማለል ሄጄ ራሴን ላድስ÷ ስንት ሱባኤ ልያዝ የትስ ገዳም ልግባ? ስለቴ ሰምሮልኝ ልብሽ ውስጥ ልገባ? ቡሩሽ ልግዛ ቀለም ልሳልሽ በሸራ? በጥበብ ላማልልሽ ጥሪት ሳላፈራ? ወይስ እየበተንኩ ገንዘብን በጉራ? የቱን በጎ ስራ እየሄድኩ ልሳተፍ? አንቺንም ፅድቅንም ልቤ እንድታተርፍ? በዱር በገደሉ እየወጣሁ ልደር ጠላትን ልመክት ዘብ ልሁን ለሀገር? በምን ላማልልሽ ልጠቀም ምን ዘዴ እንዴት ልግለፅልሽ እኔ አንቺን መውደዴ?            @Abuugida       by ᵗˢᵉᵍˢʰ @getem @getem @getem
Показать все...
41🔥 7🤩 6👍 2👎 1
ማነሽ? . የነፋስ ኃይል እንደጣላት ቢጫ ቅጠል በመኖር ዳር እጣ ጥዬ በርጥብ መሬት ተንጋልዬ አፈር ሆኜ ለመሬቱ ትንፋሽ ሆኜ ለዋሽንቱ ስንት ዘመን ስንት ጊዜ ብኩን ጥላ የምታቀፍ በተስፋ ስም የሞት ገላ ስንት ንጋት የምደገፍ? ምነው ህይወት ምንድን ፍቺ ምነው ጊዜ ማነሽ አንቺ ፡፡፡ ሲራክ ወንድሙ @getem @getem @getem
Показать все...
🔥 23 15👍 4👎 1
CHAPTER ስንት ? ነን ? ' ' መቼስ ታውቀዋለህ ካለም ኋላ መሳነፍን መቼም ታውቂዋለሽ ከእዳ ጉንፋን ጭንቀት ማስነጠስን እኔስ አውቀው የለ ማላውቀው ምን አለ፣ ገና ገና እያልኩ እድሜዬ መምህሬ ስንት ቻፕተር ዘለለ ፣ ' ' ግዕዝ ሙላት🦘 @geez_mulat @getem @getem @getem
Показать все...
34👍 1
‎ ባካል ከማያቃት በፍቅር ተይዞ ‎ እድለኛ ልቤ ያፈቅራል ተጉዞ ‎ ‎ ባካል ላላወቃት ሲገባ ሲወጣ ‎ እድለ ቢስ ልቤ በእንቢታ ተቀጣ ‎ ‎ ሰርክ ላይተው ማፍቀሩን ‎ ሰርክ ላይተው መውደዱን ‎ እምቢታውን ታቅፎ ‎ ይኖራል የግዱን። ‎ ‎ ዮኒ ‎      ኣታን @yonatoz ‎ ‎Share @Yonny_Athan ‎Share @Yonny_Athan
Показать все...
52😁 5👍 4👎 3
' ' ማግኜቴ እንኳ ይበቃኛል ም'ር'ቅ ሳግ ሳላምጥ በመሳምሽ አረፍ ይላል በዚች ዓለም ስናወጥ ተንጠልጥሎ ይታየኛል እየተውለበለበ ዛፉ ላይ ገመዱ ፀጉርሽ እስክዳብስ ፍዳ ውሎ ነው የአለም ሰርዶ ግምዱ አፍንጫየን ይሸተዋል የሙት ቀብር የሌላቸው ቁራ ሁሉ የተዋቸው ክፋት ምኑ አጥመልምሎ ነፍስ ሰጦ የጣላቸው እኒያ ዘንዳ ውዬ ውዬ አንቺ ዘንዳ አልጋችን ውስጥ የናርሲየስ ጠረንሽን ይውጠኛል እንደ' ስምጥ ደሞ ይታየኛል ጌጡ ምናምኑ አሳብዶ ሚያንቀዠቅዥ የእኔ ልብለጥ ዓለም ስሄድ ባዶ ራቁት የእብድ ቁሻሽ የሚያፀይፍ ማይወደድ እነሱ ጋ ውዬ ውዬ... አንሶላው ውስጥ ገባ ብለን ባዶ ራቁት ሆነን በእቅፍ ዓለም ጨርቅ ትለብሳለች ሀፍረት ክብርን የምትቀጥፍ ደሞ ሳየ ፀጉራቸውን እሳት ለግቶ ያወረደው ክልቲምልቲ ሳሙናው ጣቱ ምኑ የደረደው ቅማል ወርሶት የሚዋጋ ለዓይኔ ስጋ የሚታየው ከዛ ውዬ ውዬ... ፀጉርሽ እንኳ መስክ አደለ ፍቅር ያለው ሚመስጥ ከቅብብዝ ባለሽቶ ከዓለም ፍቅር የሚያቀብጥ፣ ጣቴ እንኳ የሚረጋው ከሸክሙ ከሽክረቱ ፀጉርሽን ሲዳብስ ነው የሚመለስ ጣትነቱ ያቺ ጎጆ ስናፍቃት ካለም ስውል እንደ እስር፣ ከዚች ጠበባ የዓለም ግጭት ማታ አለኝ ያንቺ ፍቅር፣ ' ' @geez_mulat🦘 ግዕዝ ሙላት @getem @getem @getem
Показать все...
35🔥 3🎉 2