ru
Feedback
Tikvah-University

Tikvah-University

Открыть в Telegram
2025 год в цифрахsnowflakes fon
card fon
352 802
Подписчики
-4824 часа
+967 дней
+1 45930 день
Архив постов
Фото недоступноПоказать в Telegram
ተጨማሪ! ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የመምህርነት ሙያን መቀላቀል ለሚፈልጉ የአንድ ዓመት ስልጠና ለመስጠት ምዝገባ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስልጠናው ይሰጣል ከተባለባቸው አምስት ዩኒቨርሲቲዎች በተጨማሪ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እንደሚሰጥ ተገልጿል። የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መመዝገቢያ ሊንክ 👇  https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdRwj89yQ50AiUeZZeDe8tr8aJ5GQZO4B0IqUVJzJJCNJzWPQ/viewform @tikvahuniversity
Показать все...
👎 100 97👏 10😢 9
Фото недоступноПоказать в Telegram
#AAU 75ኛ የምስረታ ዓመቱን እያከበረ የሚገኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቀድሞ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡ ዩኒቨርሲቲው 75ኛ የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን በተያዘው ህዳር እና ታህሳስ ወር በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች እንደሚያከብር መግለፁ ይታወቃል። የበዓሉ አካል የሆነ የባለድርሻ አካላት ውይይት እየተደረገ ሲሆን፤ ቅዳሜ ህዳር 20/2018 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲዎች የእግር ኳስ ውድድር ይጀመራል ተብሏል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ75 ዓመታት ጉዞ የተሰነደበት መፅሐፍ ይመረቃል፡፡ የተቋሙን አጠቃላይ ጉዞ እና የወደፊት ርዕይ የሚያስቃኝ ዘጋቢ ፊልም እየተዘጋጅ መሆኑም ተጠቁሟል። የፓናል ውይይቶች፣ ሴሚናሮች፣ የእግር ጉዞ እና ሌሎች በርካታ ኹነቶች እንደሚካሔዱ ተገልጿል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከታህሳስ 18-24/2018 ዓ.ም ለሚከበረው የቀድሞ ተማሪዎች ሳምንት (Alumni Week) በመላው ዓለም ለሚኖሩ የቀድሞ ተማሪዎቹ ጥሪ አቅርቧል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ምሩቃን በ https://alumni.aau.edu.et/register ድረ-ገፅ በመግባት መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
130👎 10👍 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ጥቆማ ጤና ሚኒስቴር የማርበርግ ቫይረስ ዝግጁነት #የኦንላይን ትምህርት ለጤና ባለሙያዎች መስጠት ጀምሯል። ይመዝገቡ 👇 https://cpd.moh.gov.et/cpd/course/view.php?id=112 የኦንላይን ስልጠናውን ይውሰዱ! ዝግጁነትዎን ይጨምሩ! @tikvahuniversity
Показать все...
20👍 18👎 1👏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
በሽ ሽልማቶች በየቀኑ፣ በየሳምንቱ 💪 -  በቀን፣ ለ2000 አሸናፊዎች 100 ብር - ሳምንታዊ፣ 100ሺህ ለ25 አሸናፊዎች - ትልቁ ሳምንታዊ ሽልማት፣ 1 ሚሊየን ለ32 አሸናፊዎች! ምን ይጠብቃሉ አሁኑኑ የበሽ ጥቅሎችን እየገዙ በሽልማት ይንበሽበሹ! *777*0# ላይ አሁኑኑ ይደውሉ! ዛሬዉኑ የበሽ ጥቅሎችን እየገዙ በሽልማት ይንበሽበሹ! 📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡ https://onelink.to/ewsb22 የቴሌግራም ቦታችን👉🏽 https://t.me/official_safaricomet_bot #SafaricomEthiopia #MPESAsafaricom #furtheraheadtogether #besh
Показать все...
34👎 3👍 1😢 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሰኞ ህዳር 22/2018 ዓ.ም 72ኛ ዙር የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በመገናኛ ካምፓስ ይጀመራል! 👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና 👉 Advanced Graphic + Video Editing + Motion Graphic + Digital Marketing በአንድ ላይ 👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት ☎️   0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Показать все...
55👎 1😢 1🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#DebarkUniversity ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመከታተል ወደ ተቋሙ ለተመደቡ ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል፡፡ ለህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም አድርጎት የነበረውን ጥሪ ያራዘመው ዩኒቨርሲቲው፤ የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 16 እና 17/2018 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል፡፡ ትምህርት ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
116👎 93😱 20😢 17👍 12👏 5🙏 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
ያመልክቱ! ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የመምህርነት ሙያን መቀላቀል ለሚፈልጉ የአንድ ዓመት ስልጠና ለመስጠት ምዝገባ መጀመሩ ይታወቃል፡፡ ስልጠናው በተመረጡ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ ስልጠናውን በቀን መርሐግብር የሚወስዱ ተማሪዎች የትምህርት ወጪያቸው ሙሉ ለሙሉ በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገልጿል። የምዝገባ ጊዜ፦ ከህዳር 16/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ኦንላይን የመመዝገቢያ ሊንኮች፦ ➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.ju.edu.et ➫ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.hu.edu.et/Home/AvailablePrograms ➫ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/6t1BNV9S67oXwzBv9 ➫ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/Y7Hksp5Ymk7Nx7d9A ➫ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፦ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfQcnu1ThOSSsUp9d3XI80NszyyETOwtJPxWNRh68izA7Gd2A/viewform?usp=header @tikvahuniversity
Показать все...
93👍 18🙏 8👎 6👏 6😢 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ዕድልዎን በበሽ ይሞክሩ! ዛሬውኑ በሽ ይግዙ እና እስከ 1 ሚሊዮን ብር የማሸነፍ እድልዎንን ከፍ ያድርጉ። *777*0# ላይ አሁኑኑ ይደውሉ! ዛሬውኑ የበሽ ጥቅሎችን እየገዙ በሽልማት ይንበሽበሹ! 📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፦ https://onelink.to/ewsb22 የቴሌግራም ቦታችን 👉🏽 https://t.me/official_safaricomet_bot #SafaricomEthiopia #MPESASafaricom #furtheraheadtogether #besh
Показать все...
22👍 3👎 1👏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#InjibaraUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ወደ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 09 እና 10/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ አራት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
65👎 20😱 11🙏 7🥰 3👏 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
#MoE በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድራችሁ ያለፋችሁና በየተመደባችሁባቸው ትምህርት ቤቶች በኦንላይን ምዝገባ ያደረጋችሁ ተማሪዎች ወደ የትምህርት ቤቶቹ የምትገቡበትን ቀን በቅርቡ እንደሚያሳውቅ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ ያሳሰበው ሚኒስቴሩ፤ በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን ያልተመዘገባችሁ እስከ ህዳር 22/2018 ዓ.ም ድረስ በ sbs.moe.gov.et አማካኝነት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ በድጋሚ ተገልጿል፡፡ ምዝገባ ያደረጋችሁ ተማሪዎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ድረ-ገፅ ሊንክ https://shorturl.at/2cmep በመጫንና Special Boarding School Students Registration Final List የሚለውን በማውረድ በየተመደባችሁበት ትምህርት ቤት ዝርዝራችሁን ማየት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
86👏 7🥰 1😢 1🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#BahirDarUniversity ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝ የኒቨርሲቲነት ለመሸጋገር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገለፀ፡፡ ራስ ገዝ እንዲሆኑ በመንግሥት ከተለዩ አስር ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አንዱ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ለመሆን የሚያስችለውን የተሟላ ዝግጅት ማድረጉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው የሰው ኃይል ስምሪት፣ ሃብት የማመንጨት አቅም፣ አስተዳደራዊ መዋቅር እና ሌሎች ተግባራትን በማካተት የደረሰበትን ውጤት ለትምህርት ሚኒስቴር መላኩን ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል። ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው ፈቃድ መሰረት ዩኒቨርሲቲው የራስ ገዝነት አሰራሩን ተቀብሎ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል። @tikvahuniversity
Показать все...
60👎 22😱 8🙏 5👍 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
🔔 ሰኞ ህዳር 22/2018 ዓ.ም 6ኛ ዙር የኮምፒውተር፣ የቢሮ ዕቃዎች እና የሞባይል ጥገና እና ኔትዎርኪንግ (Computer, Office Machine and Mobile Maintenance and Networking) ስልጠና በመገናኛ ካምፓስ ይጀመራል! 👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና 👉 የሶፍትዌር ላይ ጥገናን አካቶ የሚሰጥ ☎️   0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Показать все...
36👏 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
#DebreBerhanUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመከታተል የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ በተመደባችሁበት ካምፓስ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ሁለት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
122👍 27👎 8😱 5👏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#DebreMarkosUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመከታተል የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሆናችሁና የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A-L የሚጀምር እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የሆናችሁና የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A-B የሚጀምር በቡሬ ካምፓስ፤ ሌሎች የተፈጥሮ ሳይንስና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ10ኛ ክፍል እና የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቃችሀብት ውጤት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ስምንት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
160🙏 8😱 5👎 4🥰 3😢 3👏 1
#ጥቆማ የድኅረ-ምረቃ ዲፕሎማ በአማራጭ የመምህራን ስልጠና (Post Graduate Diploma in Alternative Teachers Education) በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ይማመሩ! በ2018 ዓ.ም አዲስ በተጀመረው የድኅረ-ምረቃ ዲፕሎማ በአማራጭ የመምህራን ስልጠና አመልካቾችን ተቀብሎ በቀን እና በማታ መርሐግብሮች ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ የስልጠና ፕሮግራሙ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ ተመዝጋቢዎች ከመምህርነት ስልጠና ውጪ ባለ በማንኛውም መስክ የመጀመርያ ዲግሪ ያላቸው እና በቀኑ መርሐግባር የሚማሩት በቀጣይ በመምህርነት ለመሰማራት ፈቃደኛ የሆኑ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ የስልጠና ፕሮግራሙ በአንድ ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን፤ በቀን መርሐግብር የሚማሩ ተማሪዎች የትምህርት ወጪያቸው ሙሉ ለሙሉ በመንግሥት የሚሸፈን ይሆናል፡፡ ማመልከት የሚቻልባቸው የትምህርት ዓይነቶች፦ ➫ በቋንቋ ትምህርት ዘርፎች ➫ በተፈጥሮ ሳይንስ እና ማቲማቲክስ ዘርፎች ➫ በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፎች ➫ በኬሪየር እና ቴክኒክ ➫ በሳይኮሎጂካል ኬርጊቪንግ ➫ በሄልዝ ኤንድ ፊዚካል ኤዱኬሽን የምዝገባ ጊዜ፦ መስፈርቱን የምታሟሉ የትምህርት ፈላጊዎች ከህዳር 17 እስከ ታህሳስ 04/2018 ዓ.ም ድረስ በዩኒቨርሲቲው ሬጂስትራር በአካል በመቅረብ ወይም በኦንላይን ማመልከት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡  ኦንላይን ለመመዝገብ 👇 https://forms.gle/Y7Hksp5Ymk7Nx7d9A (በዩኒቨርሲቲው ማመልከት የሚቻልባቸው የትምህርት ዓይነቶች ሙሉ ዝርዝር ከላይ ከተያየዘው ምስል ይመልከቱ፡፡) @tikvahuniversity
Показать все...
131👎 12👍 8👏 2
በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች እና ተዛማጅ የትምህርት መስኮችን ዝርዝር
Показать все...
አማራጭ_የመምህራን_ስልጠና_ትምህርት_አይነቶች.pdf1.85 KB
👍 41 28👎 11😢 7👏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመጀመሪያ መንፈቀ-ዓመት መረጃን በተዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርት የመረጃ ስርዓት (HEMIS) እንዲያስገቡ አሳስቧል፡፡ በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ህዳር 16/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ ሰርኩላር፥ ሁሉም ተቋማት መረጃቸውን በተዘጋጀው ሲስተም ላይ የማስገባት ግዴታ እንዳለባቸው ይገልጻል። በመሆኑም የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው መንፈቀ-ዓመት ሁሉም መረጃዎች ተሟልተውና በየተቋሙ አመራር ተረጋግጠው እስከ ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም በሲስተሙ (http://hemis.ethernet.edu.et) እንዲያስገቡ ጠይቋል፡፡ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ይህን ተከታትሎ የማስፈፀም ኃላፊነት እንደተሰጠው የተገለፀ ሲሆን፤ መረጃውን የማያስገቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመንግሥት በሚሰጡ አገልግሎቶች እንደማይስተናገዱ ተጠቁሟል። @tikvahuniversity
Показать все...
69👎 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 20/2018 ዓ.ም 6ኛዙር የህንፃ ኤሌክትሪክ፣ የዲሽ መስመር እና የሲሲቲቪ (CCTV) ካሜራ ዝርጋታ ስልጠና በመገናኛ ካምፓስ ይጀመራል! 🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ! 👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና 👉 Security Solutions ዝርጋታ በተጨማሪነት የሚሰጥበት  👉 ከትምህርት ቢሮ የCOC ምዘና የተዘጋጀለት ☎️  0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Показать все...
55🙏 5
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር ለፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተወዳድረው ያለፉ መምህራንን ስም ዝርዝር እና የተመደቡበትበትን ተቋም ይፋ አድርጓል። የተመረጡ መምህራን በየተመደቡበት የፌደራል ልዩ 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ባሉባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ህዳር 22/2018 ዓ.ም ድረስ ሪፖርት አድርጉ ተብሏል። ከስር በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች አማካኝነት የልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮችን በማግኘት ተጨማሪ መረጃ መውሰድ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡ ➫ ጋምቤላ - 0911590938 ➫ አምቦ - 0920189695 / 0989123320 ➫ ጅግጅጋ - 0922648636 ➫ ወልቂጤ - 0943165470 ➫ ቦንጋ - 0913192165 @tikvahuniversity
Показать все...
181👍 6😱 4👎 2👏 1😢 1