ru
Feedback
Addis Ababa Education Bureau

Addis Ababa Education Bureau

Открыть в Telegram

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Больше
2025 год в цифрахsnowflakes fon
card fon
150 232
Подписчики
Нет данных24 часа
+677 дней
+34630 день
Архив постов
የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ከመስከረም 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ ይጀመራል። (ጳጉሜ 1/2017 ዓ.ም) የ2018 የትምህርት ዘመን የትምህርት ቤቶች አከፋፈት አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴር ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር የበይነ-መረብ ምክክር ባደረገበት ወቅት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ እንደገለጹት የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ሰኞ መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ይጀመራል። በትምህርት ካሌንደሩ መሠረት ዓርብ መስከረም 2/2018 ዓ.ም ትምህርት ቤቶች ክፍት ሆነው መምህራንና ተማሪዎች ውይይት የሚያደርጉበትና መስከረም 5/2018 ዓ.ም ደግሞ በይፋ ለሚጀመረው የትምህርት ስራ ቅድመ ዝግጅት የሚያደርጉበት ቀን መሆኑን ክብርት ወ/ሮ አየለች አስታውቀዋል፡፡ በ2018 የትምህርት ዘመን ባለፈው ዓመት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናትና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ወላጆች፣ መምህራንና የዘርፉ ባለድርሻዎች የጀመሩትን የንቅናቄ ተግባር አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባና የትምህርት ቤት ምዝገባም እስከ መጨረሻው ቀን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
Показать все...
56👍 4👎 2👏 1🖕 1
Показать все...
4😁 2👎 1
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ገነነ ዘውዴ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የትምህርት ፍኖተ ካርታና የትምህርት ካርኩለም ተቀርፆ ውጤታማ ስራዎች እሰሩ እንደሚገኙ በመግለፅ በክፍለ ከተማውም የትምህርት ሽፋን ተደራሽነት ላይ በተሰራው ስራ ውጤት መመዝገቡንም ጨምረው ገልፀዋል። በክፍለ ከተማው በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ከ310 ሚሊየን ብር ከህብረተሰቡ በመሰብሰብ የትምህርት ቤት ደረጃ የማሻሻል ስራ መሰራቱንም ጨምረው ተናግረዋል። በጉባኤው የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅህፈት ቤት የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀምና የተማሪዎች ውጤት ትንተና አፈፃፀም ቀርቧል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Показать все...
26🖕 10
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት 32ኛውን የትምህርት ጉባኤ “በዕውቀት እና ክህሎት የበቃ ትውልድ በማፍራት ኢትዮጵያን የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን” በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው እለት አካሂዷል፡፡ (ጳጉሜ 1/2017 ዓ.ም) በትምህርት ጉባኤው የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል ጨምሮ የትምህርት አመራሮች ፣ የዘርፉ ያሉ ሰራተኞች፣ መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በጉባዔው ተሳትፈዋል፡፡ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የትምህርት በአዕንሮ የበለፀገ ትውልድን ለማፍራት ሚና እንዳለው ገልፀው ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት ትውልድን ለማፍራት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡ በትምህርትና ክህሎት የበቃ ትውልድ ለመፍጠር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የክፍለ ከተማው አስተዳደር ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ቴዎድሮስ ገልፀው ለዚህ ደግሞ የሁሉም አካላት ትብብር አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አሊ ከማል በበኩላቸው በትምህርት ትውልድን በማፍራት መጪውን ትውልድ ብሩህ ለማድረግ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል። ትውልድን የምናንፀው ሁሉም አካላት እገዛ ሲኖር እንደሆነና ይህም በትምህርትና ክህሎት የበቃ ትውልድ ለመፍጠር ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል።
Показать все...
18🔥 2🤮 1
በጉባኤውም በ2018 ዓ.ም በትምህርት ዘርፉ ላይ መሰራት በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ ውሳኔዎች ተላልፏል። በእለቱም የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ከወረዳዎችና ከትምህርት ቤቶች ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር የሚያስችል የትስስር ሰነድ ተፈራርሟል። በመጨረሻም በ2017 የትምህርት ዘመን የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ወረዳዎች፣ ትምህርት ቤቶችና ተማሪዎች እንዲሁም አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሴክተሮች እውቅናና ሽልማት ተበርቶላቸዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Показать все...
12🥰 1💩 1
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት 32ኛው የትምህርት ጉባኤ አካሄደ፡፡ (ጳጉሜ 1/2017) የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም 32ኛው የትምህርት ጉባኤውን በዛሬው እለት አካሂዷል። "በእውቀትና በክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሃገር እናደርጋለን!" በሚል መሪ ሃሳብ በተካሄደው የትምህርት ጉባኤ ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የትምህርት አመራሮችና ሱፐርቫይዘሮች፣ መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በእለቱም በ2017 የትምህርት ዘመን በትምህርት ዘርፍ የተሰሩ ስራዎችና የተማሪዎች ውጤት ትንተና ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የክፍለ ከተማው ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ወጋየሁ ኃይሉ ትምህርት በሀገር ቀጣይ እጣ-ፈንታና ብልፅግና ላይ የራሱ አዎንታዊ አስተዋፅኦ እንዳለው ጠቁመው "ትምህርት ለትውልድ" የሚለውን ተልዕኮ ለማሳካት የትምህርት ተቋማትን ደረጃ በማሻሻል ረገድ በርካታ ተጨባጭ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል። በትምህርት ዘርፍ እየተመዘገበ ያለውን ስኬት ማስቀጠል የሁሉም አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል። የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በላይ ነጋሽ በጉባኤ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርት የትውልድ ግንባታ ማዕከል በመሆኑ በእውቀት፣ በክህሎትና በስነ-ምግባር የታነፁ ተተኪ ትውልድን ለማፍራት ዘርፈ ብዙ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። አቶ በላይ አክለውም ሁለንተናዊ የልማት ስራዎችን በመስራት ለትምህርት ጥራት ተግዳሮት የነበሩ አዋኪ ቦታዎችን በማስወገድ፣ ግብዓት በማሟላት እንዲሁም የትምህርት ቤት ማስፋፊያ ስራዎችን በማጠናቀቅ ምቹ የትምህርት አካባቢን መፍጠር ተችሏል ብለዋል።
Показать все...
36😐 1
ትምህርት ቤቶች ለ2018 የትምህርት ዘመን እያከናወናቸው የሚገኙትን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ምልከታ የሚያደረጉ ሱፕርቫይዘሮችን ለሚያሰተባብሩ አካላት ኦረንቴሽን ተሰጠ፡፡ (ጻጉሜ 1/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፕርቪዥን ዳይሬክቶሬት ለ2018 የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች እያከናወናቸው የሚገኙትን ቅድመ ዝግጅት አስመልከቶ ምልከታ የሚያደርጉ ሱፕርቫይዘሮችን ለሚያሰተባብሩ አካላት ኦረንቴሽን ሰጥቷል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፕርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጥላዩ ዘውዴ ለ2018 የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች እያከናወናቸው የሚገኙትን ቅድመ ዝግጅት አስመልከቶ ምልከታ የሚያደርጉ ሱፕርቫይዘሮችን ለሚያሰተባብሩ አካላት ኦረንቴሽን መሰጠቱን ግልጸው ሱፕርቪዥኑ ትምህርት ቤቶች ለ2018 የትምህርት ዘመን የትምህርት ቤቱን ምድረ ግቢ ምቹና ሳቢ ማድረጋቸዉን ፣ የትምህርት ግብዓቶች በአግባቡ መሰራጨታቸዉን ፣ የሰው ሀይል መሟላቱን ፣ ተማሪዎች ያለ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ መመዝገባቸዉን በአጠቃላይ ለትምህርት አጀማመር መዘጋጀታቸዉን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝና ከጻጉሜ 3-5/2017 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Показать все...
92👍 13
Фото недоступноПоказать в Telegram
የጽናት ቀን ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር ኢትዮጵያ ብልጽግናዋን የምታረጋግጠው መሠረቷን ለማጽናት በሚችሉ ብርቱ እጆች ነው፡፡ በሁሉም ዘርፎች በምናደርገው ተጋድሎ የኢትዮጵያን መሠረት እናጸናለን፡፡ ለማናቸውም ችግሮች የማትበገር፣ ፈተናዎችን ወደ ዕድል የምትቀይር፣ በመጪው ዘመንም ከዓለም ኃያላን ተርታ የምትሰለፍ ብርቱ ሀገር በደምና በላብ እንገነባለን፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Показать все...
64👎 28👍 21👏 7🏆 7💩 6
መስታወቂያ! Beeksisa! (ነሀሴ 30/2017 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Показать все...
176👍 23😁 21👏 9🍌 9🔥 8🥰 2
መስታወቂያ! Beeksisa! (ነሀሴ 30/2017 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Показать все...
103🥱 10👎 7👍 5🤔 4🥰 3
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ  አቶ ዲናዖል ጫላ እንደጠቆሙት መንግስት ትምህርት ላይ ልዩ ትኩረት በማድረጉ የተማሪ ስነ-ምግባርና ውጤት እየተሻሻለ ነው ብለዋል፡፡ በ2017 ዓ.ም ትምህርት ቤቶች ስርዓተ ትምህርቱን ሪፎርም በማድረግ፣ አዕምሮን የሚያጎለብት የስፖርት መርኃ-ግብሮችን በማከናወን፣ ተማሪዎች ትምህርት ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ የተማሪዎች ምገባ፣ የተማሪዎች ጤናን መጠበቅ፣ ሰርቶ ማሳያ የትምህርት ቤቶች የከተማ ግብርናና የተማሪዎች ቴክኖሎጂ እውቀት ግንባታ ላይ ትኩረት ተደርጎ የተሰራ መሆኑን ገልፀው ሁሉም ባለድርሻ ይህን እንዲያጠናክር ምክትል ቢሮ ኃላፊው አሳስበዋል፡፡ በ2017 የትምህርት ዘመን በትምህርት ለትውልድ ህብረተሰቡን ያሳተፈ ንቅናቄ በማድረግ ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ በገንዘብ የሚተመን የትምህርት ቤቶች አንኳር ችግሮች መፈታት መቻሉን የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዱጋሳ ፍቃዱ ገልፀዋል፡፡                መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Показать все...
70🤨 7
የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት 32ኛውን የትምህርት ጉባኤ “በዕውቀት እና ክህሎት የበቃ ትውልድ በማፍራት ኢትዮጵያን የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን” በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው እለት አካሂዷል፡፡ (30/12/2017 ዓ.ም) የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን አበራና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናዖል ጫላን ጨምሮ የትምህርት አመራሮች፣ የዘርፉ ያሉ ሰራተኞች፣ መምህራንና ተሸላሚ ተማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በጉባዔው ተሳትፈዋል፡፡ የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን አበራ በመክፈቻ ንግግራቸው መንግስት ኢትዮጵያን ታላቅና ገናና ለማድረግ በትምህርትና ክህሎት የበቃ ትውልድ መፍጠር ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ባለራዕይ ህዝብ እንዲፈጠር እየሰራ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ለአንድ አገር እድገት ትምህርት ወሳኝ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲፀና፣ ልማትና ሁሉን አቀፍ ዕድገት እንዲመጣም የሚያስችል በመሆኑ ትምህርት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ በክፍለ ከተማው ያሉ ባለድርሻ አካላት የትምህርት ዘርፍ ስራዎችን በማጠናከርና በማዘመን ሂደት ያላቸውን አስተዋፅኦ አጠናክረው በመቀጠል አገሪቱ የብልፅግና ተምሳሌት እንድትሆን በሚደረገው ርብርብ የድርሻቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
Показать все...
32👏 3👍 1
Показать все...
30
Показать все...
👏 30 24👎 24👍 7
Фото недоступноПоказать в Telegram
የ2017 ዓ.ም የጳጉሜ ቀናት በተለያዩ ስያሜዎች ይከበራሉ (29/12/2017 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Показать все...
92👍 31😁 16👎 15🤣 8🤡 5👌 4🌚 4🔥 2
ብርሃን የዓይነስዉራን አዳሪ ትምህርት ቤት ከክልልና ከተማ አትዳደር ትምህርት ቢሮ ተወካዮችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት አካሄደ፡፡ (28/12/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ብርሃን የዓይነ-ስዉራን አዳሪ ትምህርት ቤት “ልዩ ፍላጎት ያላቸዉን የዓይነ-ስዉራን ተማሪዎች ዉጤትና ስነምግባር ለማሻሻል ላይ ሁሉም ክልል የበኩሉን ሚና ይወጣ” በሚል መሪ ሀሳብ ከክልልና ከተማ አትዳደር ትምህርት ቢሮ ተወካይዎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት አካሄዳል፡፡ በብርሃን የዓይነ-ስዉራን አዳሪ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ወይዘሮ ዉብአለም ደበበ የመወያያ ሰነዱን ባቀረቡት ወቅት ትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ስራዉን ለማሳካት ብዙ ስራዎች መሰራቱን ገልፀዋል፡፡ ዳይሬክተራ አክለዉም የትምህርት ቤቱን ራዕይና አላማን ለማሳካት የክልልና ከተማ አትዳደር ትምህርት ቢሮዎች ትብብር አስፋላጊ መሆኑንና ትምህርት ቤቱ የሀገር ሀብት በመሆኑ ይህንን ሀብት በመጠቀም ሰብዓዊ ሀብት ግንባታ ላይ እንዲዉል ለማድረግ ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት መወጣት አለበት ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ ዉይይቱ የተሻለ ነገር ለማምጣትና ሁሉም በባለቤትነት ኃላፊነቱን እንዲወጠ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም የክልል ትምህርት ቢሮዎች በተማሪ ምልመላ ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራትና ግንዘቤን ማስጨበጥ እንዲሁም ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንዳለበቸዉ አሳስበዋል፡፡ በቀጣይም ሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችና ተወካዮች ከትምህርት ቤቱ ጋር ስለተማሪዎች ወጤትና ስነምግባር እንዲሁም መማር ማስተማር ሂደት ዙርያ የሚወያዩበት መድረኮች እንደሚኖሩ ስምምነት ላይ በመድረስ የጋራ ስራ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
Показать все...
😡 166🖕 162🍌 151👎 143😢 140🤬 139🥱 137😈 137💔 124💩 113 99👍 15🤮 7😁 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1500ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። (28/12/2017 ዓ.ም) በዓሉን ስናከብር የነብዩ መሐመድ የፍቅርና የአብሮነት አስተምሮትን በመተግበር ምንጊዜም እንደምናደርገው ለወገኖቻችን ያለንን ፍቅር የምንገልፅባቸውን የበጎነት ፣ የልግስናና የቸርነት ተግባራትን በማከናወን ፤ አብሮነትን ፣ ወንድማማችነትንና መተሳሰብን በማጠናከር ሊሆን ይገባል። ከዚህም ጎን ለጎን ያለንበት ወቅት የኢትዮጵያ ማንሠራራት እውን የሆነበት ጊዜ በመሆኑ በ2017 የትምህርት ዘመን ያስመዘገብናቸውን ውጤቶች በማጣጣም ፣ በማስረጽና በማስቀጠል ፤ በ32ኛው የትምህርት ጉባኤ ላይ የተቀመጡትንና ከመግባባት ላይ የደረስንባቸውን የትኩረት ነጥቦች በ2018 የትምህርት ዘመን ውጤታማ ሆነው የትምህርት ልማት ስራችን ለስኬት እንዲበቃ የሚጠበቅብንን ሁሉ በማድረግና እጅ ለእጅ ተያይዘን ለላቀ አፈጻጸም በመትጋት ጭምር መሆን ይኖርበታል፡፡ በመጨረሻም እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የጤና እና የመረዳዳት እንዲሆን እመኛለሁ፡፡ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Показать все...
🍌 142😢 122👎 120🖕 119💩 113😈 109🤬 107🤮 100🥱 94 63👍 9
በክፍለ ከተማው በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር በተከናወኑ ተግባራት በተማሪዎች ውጤት ላይ ከፍተኛ መሻሻል መስተዋሉን የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍራኦል ሞሲሳ ገልጸው የከተማ አስተዳደሩ ባካሄደው 32ኛ የትምህርት ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን መሰረት በማድረግ የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል ጽህፈት ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል። በጉባኤው ማጠቃለያ በ2017 ዓ.ም የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና የትምህርት ተቋማት ዕውቅና ተሰቷል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Показать все...
44👏 6🖕 2
የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የ2017 ዓ.ም የትምህርት ጉባኤውን በዕውቀት እና ክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን በሚል መሪ ቃል አካሄደ። (ነሀሴ 28/2017 ዓ.ም) በጉባኤው የጽህፈት ቤቱ የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም እቅድ ከመገምገሙ ባሻገር በክፍለ ከተማው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በ2017ዓ.ም የተመዘገበው የተማሪ ውጤት ትንተና ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ እና የመርሀግብሩ የክብር እንግዳ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ዘርፉ እየተመዘገበ ለሚገኘው ውጤት የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እያበረከተ የሚገኘው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው የጉባኤው ተሳታፊዎች የክፍለከተማውን የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም በመገምገም በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ስራ አስፈጻሚ እና የስራና ክህሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አራርሳ ቢቂላ በበኩላቸው ጉባኤው በበጀት አመቱ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ታስቦ የሚካሄድ እንደመሆኑ የክፍለ ከተማው አስተዳደር በጉባኤው የሚቀመጡ የትኩረት መስኮችን መሰረት በማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አመላክተዋል።
Показать все...
42👍 7👏 1🤔 1
የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡ (ነሀሴ 28/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በ32ኛው የትምህርት ጉባኤ ምክንያት ሳይካሄድ የቆየ ቢሆንም በዛሬው እለት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል። በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአይሲቲ ባለሙያ የሆኑት አቶ እንዳሻው ተሾመ በሳይበር ሴኪዩሪቲ ላይ መሰረት ያደረገ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ 32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ከነሃሴ 26-27 ዓ.ም ድረስ በመከናወኑ እና ሁሉም ሰራተኞች በጉባኤው ላይ በመሳተፋቸው ምክንያት የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብሩ ለዛሬ መዛወሩን ጠቅሰው ጉባኤው በድምቀት እንዲከናወን በኮሚቴዎች ውስጥ ተካተው ለሰሩ ሰራተኞች ፣ ባለሙያዎች ፣ ዳይሬክተሮችና ለማኔጅመንት አባላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳምሶን መለስ ዘመኑ የቴክኖሎጂ እንደመሆኑ መጠን ሰራተኞች እራሳቸዉንና የሚጠቀሙባቸውን የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ከተለያዩ ጠላፊዎች/ከሀከሮች ለመጠበቅና የሚጠቀሙባቸውን የይለፍ ቁጥሮች ሚስጥራዊነት ለማረገገጥ የቀረበው ሰነድ ግንዛቤ የሚያጨብጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Показать все...
62👍 9😁 4👏 2🫡 2🔥 1