TIKVAH-MAGAZINE
Открыть в Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524
Больше2025 год в цифрах

194 438
Подписчики
-5824 часа
-1527 дней
-79430 день
Архив постов
Фото недоступноПоказать в Telegram
🚨በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ
🎄መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለውስን ቤቶች ብቻ 🎄35%🎄ቅናሽ እንዳደረግን ስንገልፅልዎ በታላቅ ደስታ ነው እርሶም ይሄን ቅናሽ በመጠቀም መሀል ፒያሳ ላይ የቤት ባለቤት የመሆን ሀሳብ ካሎት ፈጥነው ይመዝገቡ🎄
🏡ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት
💎ባለ 1 መኝታ በ 514,500 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 840,000 ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 1,207,500 ብር ቅድመ ክፍያ
🔥እንዲሁም የቤቱን 65% ሲከፍሉ 35% በድርጅቱ የሚሸፈን ይሆናል (35% ቅናሽ)
💎ባለ አንድ መኝታ ሙሉ ክፍያ 3,344,250 ብር
💎 ባለ ሁለት መኝታ ሙሉ ክፍያ 5,460,000 ብር
💎 ባለ ሶስት መኝታ ሙሉ ክፍያ 7,848,750 ብር
-በግንባታ ላይ የሚገኙ
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelMERITRealtor)
https://t.me/addisapartmentforu
❤ 11😢 2🕊 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ደቡብ አፍሪካ ሰባት የኬንያ ዜጎችን ከሃገሯ ልታባርር ነው።
ደቡብ አፍሪካ አሜሪካ የደቡብ አፍሪካ ነጭ ዜጎችን በስደተኝነት ለመቀበል ለጀመረችው ፕሮግራም ተገቢ ባልሆነ ሰነድ ሲሰሩ የነበሩ 7 የኬንያ ዜጎችን ማሰሯንና ወደ ሃገራቸው እንደምትመልሳቸው ገልፃለች።
አሜሪካ ሰዎቹን መቀመጫውን ኬንያ ካደረገ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ይህንኑ ሂደት እንዲያሳልጡ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዲመጡ እንዳደረገች ተነግሯል።
ደቡብ አፍሪካ ኬንያውያኑ የያዙት ቪዛ የቱሪስት ቪዛ ነው ስትል በስራ ላይ መገኘታቸው የሃገሪቱን ህግ የጣሰ ነው ብላለች።
አሜሪካ ከትራምፕ መምጣት በኋላ በደቡብ አፍሪካ ያሉ ነጮች የዘረኝነት ጥቃት ይፈፀምባቸዋል በሚል ወደ ሃገሯ በስደተኝነት እንዲመጡ የፈቀደች ሲሆን 50 አፍሪካነርሶችም ባለፈው ግንቦት በቻርተርድ አውሮፕላን ወደ ዋሽንግተን አምርተዋል።
በተደጋጋሚ አሜሪካ ይህንን ሂደት ለማሳለጥ ከኬንያ በቱሪስት ቪዛ ያመጣቻቸውን ሰዎች ትጠቀማለች ሲባል የተያዙት ሰባት ኬንያውያን ለአምስት አመት ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዳይገቡ እንደሚደረግም ደቡብ አፍሪካ ገልፃለች።
ዘገባው የTRT ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
📣 #Ad በእጆዎ ለቤት ወይም አፖርትመንት ፈላጊዎች አዲስ መላ! የሞባይል መተግበሪያውን ያውርዱና ይቀላቀሉን 👉 https://beijoholding.com/
❤ 37👏 2🤣 2
00:18
Видео недоступноПоказать в Telegram
በኢራን ከባድ ዝናብ ከዘነበ በኋላ የውሃ አካላት ወደ ቀይ ደም ቀለም መቀየራቸው ተነገረ።
ከ50 አመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ድርቅ እየተፈተነች ባለችው ኢራን ዝናብ ከዘነበ በኋላ የሆርሙዝ ደሴት በቀይ ውሃ መሸፈኑ ተነግሯል።
በኢራን 100 ሚሊሜትር መጠን ያለው ዝናብ የጣለ ሲሆን ይህም ከኢራን አማካይ ወርሃዊ የዝናብ መጠን በ5 እጥፍ የበለጠ ነው።
ከባድ ዝናቡ የውሃ እና የአሸዋውን ቀለም የቀየረው ሲሆን አንዳንዶች ሁነቱን ከመንፈሳዊ ነገሮች ጋር አያይዘውታል።
ሳይንቲስቶች ግን ቀይ ደም የሚመስለው ቀለም የሆርሙዝ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የአይረን ኦክሳይድ ክምችት ስላለውና ኦክሳይዱ ከዝናብ ጋር ሲገናኝ የሚፈጠር እንደሆነ ተናግረዋል።
የሆርሙዝ ደሴት የአለማችን ዋነኛ የነዳጅ መስመር በሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ የሚገኝ ሲሆን በተለያዩ ቀለማት ያሸበረቀ በመሆኑ ቀስተዳመናማው ደሴት የሚል ስያሜም አለው።
ይኸው ደሴት በሚገኝበት የኢራን የአስተዳደር ክፍል በከባድ ዝናቡ የተነሳ መንገዶችም ተዘግተዋል።
በአማካይ በዚህ አመት የዝናብ መጠኗ በ89% የቀነሰባት ኢራን ዳግም መዝነብ መጀመሩን ተከትሎ ሰዎች አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን ገልፀዋል።
ከወር በፊት ባለው የዝናብ እጥረት የተነሳ የዋና ከተማዋ ቴህራን 10 ሚሊየን ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ ሊደረጉ ይችላሉ መባሉ ይታወሳል።
ዘገባው የቴሌግራፍ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
insider_paper_watch_heavy_rains_on_iran_s_southern_hormuz_isla.mp41.19 MB
❤ 72🤔 33😢 14🙏 14🕊 5🔥 1🤣 1
114 ጫማ ከፍታ ያለው ሃውልት በመጥፎ የአየር ሁኔታ የተነሳ በብራዚል ወድቋል።
በሪዮ ግራንዴ የሚገኘውና በአሜሪካው የነፃነት ሃውልት አምሳያ የተሰራው ይኸው ሃውልት በመጥፎ አየር በነበረው ንፋስ የተነሳ ሲወድቅ ጉዳት አላደረሰም ተብሏል።
በአካባቢው በሰዓት ከ50-56 ማይልስ በሰዓት ፍጥነት ያለው ንፋስ ከሰሞኑ እየነፈሰ ሲሆን ይህም ለሃውልቱ መውደቅ ምክንያት ሆኗል።
በአካባቢው ከባድ ዝናብ ይጥላል ተብሎ እየተጠበቀ ሲሆን ማስጠንቀቂያም ለነዋሪዎች ተሰጥቷል።
😀 | @tikvahethmagazine
5.23 KB
❤ 32🤣 7
Фото недоступноПоказать в Telegram
የአውሮፓ ፓርላማ ውርጃን በህብረቱ ለማሳለጥ የሚያስችል ውሳኔ አሳልፏል።
የአውሮፓ ፓርላማ በሃገራቸው ልጅ ማስወረድ ያልቻሉ ሴቶች ወደ ሌላ የህብረቱ አባል ሃገር ሄደው በነፃ እንዲያስወርዱ የሚያስችላቸው ፈንድ እንዲመሰረት ወስኗል።
እንደ ማልታ ባሉ የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ውርጃ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የማይፈቀድ ሲሆን ፖላንድ የጤና ስጋት ካለና ከወሲብ ጥቃት ጋር የተያያዘ ከሆነ ትፈቅዳለች።
በሌላኛው ፅንፍ ደግሞ እንደ ፈረንሳይ ያሉ ሃገራት ውርጃን ህገመንግስታዊ መብት አድርገውታል።
በርካታ የአውሮፓ ሃገራት ውርጃ ላይ ቁጥጥር ለማድረግ አዳዲስ ህጎችን እያወጡ ባሉበት ሁኔታ ፓርላማው " ድምፄ ምርጫዬ" በሚል ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች ፊርማ አሰባስበው ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሏል።
ውሳኔው በመጪው መጋቢት ወር በአውሮፓ ከፍተኛው ኮሚሽን ተቀባይነት ካገኘ ወደ ስራ ሲገባ በሃገራቸው ልጅ እንዳያስወርዱ የተከለከሉ ሴቶች ወደ ሌላ የህብረቱ አባል ሃገር ሄደው በነፃ ማስወረድ ይችላሉ።
የፓርላማው ውሳኔ በሊብራሎች፣ በሶሻሊስቶችና በግራ ዘመም ቡድኖች ድጋፍ ሲያገኝ በአጠቃላይ 358 የድጋፍ፣ 202 የተቃውሞ እና 79 ድምፀ ተዓቅቦ ነበረው።
ፓርላማው በውሳኔው የውርጃ መብት በአውሮፓ ህብረት የመሰረታዊ መብቶች ቻርተር ውስጥ እንዲካተትም ጠይቋል።
ውሳኔውን በርካቶች ነፃነት የሰጠ ነው ብለው ሲያሞግሱት በሌላኛው ጎራ ደግሞ የሰዎችን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል ኢ ሰብዓዊ ተግባር ነው ብለውታል።
ዘገባው የሮይተርስ እና ዩሮ ኒውስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
👎 88❤ 31😢 8👏 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሱዳን ወደ አፍሪካ ህብረት አባልነት እንድትመለስ አምባሳደሯ ጠየቁ።
በኡጋንዳ የሱዳን አምባሳደር አህመድ ኢብራሂም የሱዳን ከአፍሪካ ህብረት አባልነት መታገድ በሱዳን ያለውን ጦርነት ለማስቆም የሚወሰዱ የአፍሪካ ኢንሼቲቮችን አዳክሟል ብለዋል።
አምባሳደሩ የሱዳን ወደ ህብረቱ አባልነት መመለስ የውጪ ጣልቃ ገብነትን እንደሚቀንስና ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ እንዲኖር እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
በኡጋንዳ የሱዳን አምባሳደሩ ዩዌሪ ሙሴቬኒ ሱዳን ወደ ህብረቱ እንድትመለስ ለማድረግ ውጤታማ ስራ እንደሚሰሩ እንጠብቃለን ብለዋል።
የአፍሪካ ህብረት በፈረንጆቹ ጥቅምት 2021 በኋላ ላይ እርስ በእርሳቸው ወደ ጦርነት የገቡት ጀነራሎች የወቅቱን የሲቪል አስተዳደር በኃይል ማንሳታቸውን ተከትሎ በሱዳን የሲቪል አስተዳደር እስኪመለስ ከአባልነት አግዷታል።
ዘገባው የTRT ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 18👍 1🤔 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ቴምርሪልስቴት፡ ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ 8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው።
ሳር ቤት ቫቲካን
🎯65/35 አከፍፈል
👉2መኝታ 106ካሬ ሙሉ ክፍያ 7.9ሚሊዮን
👉3መኝታ 139ካሬሙሉ ክፍያ 10.3ሚሊዮን
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 106ካሬ
20% ቅድመ ክፍያ 2.4ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 12.1ሚሊዮን
👉3መኝታ 139ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 3.1ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 15.9ሚሊዮን
አዋሬ
🎯65/35 አከፍፈል
👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉 1መኝታ 78ካሬ = 20%ቅድመ ክፍያ 1.7ሚሊዮን ፤ ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን
👉 3 መኝታ 117ካሬ = 20%ቅድመ ክፍያ 2.6 ሚሊዮን ፤ ሙሉ ክፍያ 12.9ሚሊዮን
👉 157 ካሬ = 20% ቅድመ ክፍያ 3.4ሚሊዮን ፤ ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን
ቀሪውን 80% በ 15ዙር ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት፤
* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇👇👇
0980782850
❤ 13
Фото недоступноПоказать в Telegram
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአምስት ተጨማሪ ሃገራት ላይ የሙሉ ለሙሉ የጉዞ እግድ ጥለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቡርኪናፋሶ፣ ማሊ፣ ኒጀር፣ ደቡብ ሱዳንና ሶሪያ ላይ ሙሉ በሙሉ የጉዞ እገዳ ጥለዋል።
በተጨማሪ በሌሎች 15 ሃገራት ላይ በከፊል እገዳውን ጥለዋል።ከነዚህ ሃገራት መካከል አሜሪካ አስተናጋጅ በሆነችበት በ2026 የአለም ዋንጫ አፍሪካን በመወከል የሚሳተፉት ሴኔጋልና አይቮሪኮስት ይገኙበታል።
በትራምፕ አስተዳደር ወደ አሜሪካ ሙሉ ለሙሉ እንዳይገቡ የተከለከሉት እነማን ናቸው?
-ኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ አፍጋኒስታን፣ ቡርኪናፋሶ፣ በርማ፣ ቻድ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ሃይቲ፣ ኢራን፣ ላኦስ፣ ሊቢያ፣ ማሊ፣ ኒጀር፣ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ፣ ሴራሊዮን፣ ሶሪያ፣ የመንና በፍልስጤም በሚሰጥ የጉዞ ሰነድ የሚጓዙ ግለሰቦች።
በከፊል እገዳው የተጣለባቸው ሃገራት
- ናይጄሪያ፣ አንጎላ፣ አንቲጉያና ባርቡዳ፣ ቤኒን፣ ቡሩንዲ፣ አይቮሪኮስት፣ ኩባ፣ ዶሚኒካ፤ ጋቦን፣ ጋምቢና፣ ማላዊ፣ ሞሪታኒያ፣ ሴኔጋል፣ ታንዛኒያ፣ ቶጎ፣ ቬኔዙዌላ፣ ዛምቢያና ዚምባቡዌ ናቸው።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 95🤔 33🤣 14🤬 7👎 6😢 5👍 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
#በእጆዎ
ለቤት ወይም አፖርትመንት
🏠 ገዢዎች፤
🏠 ሻጮች ፣
🏠 አሻሻጮች ፣
🏠 አብሮ አልሚዎች
ፍላጎታችሁን በአንድ ያጠቃለለውን አፕሊኬሽናችንን በማውረድ ህይወትዎን ያቅልሉ።
የሞባይል መተግበሪያውን ያውርዱና ይቀላቀሉን 👉https://beijoholding.com/
👍 8❤ 5🕊 1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና አኮያ ፕሮፐርቲስ ስምምነት ተፈራረሙ።
📌 አርቲስት እፀህይወት አበበ የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር ሆነች።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና አኮያ ፕሮፐርቲስ የደንበኞቻቸውን ተጠቃሚነት የሚያሳድግ የስትራቴጂካዊ አጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል።
ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በተከናወነው የፊርማ ስነ-ስርዓት፣ የአየር መንገዱን የሽልማት መርሃ-ግብር (ShebaMiles) ከሪል እስቴት ግብይት ጋር የሚያስተሳስር ስምምነት ተደርጓል።
በዚህ ስምምነት መሰረት በአኮያ ፕሮፐርቲስ እየተገነቡ ያሉ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን እና የንግድ ሱቆችን የሚገዙ ደንበኞች፣ የስታር አሊያንስ (Star Alliance) አባል ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይልስ የጎልድ አባልነት ሽልማት በክብር ያገኛሉ። ይህም ደንበኞች በኢንቨስትመንታቸው ልክ የአየር መንገዱን ጥቅማጥቅሞች እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።
ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና የሪል እስቴት ዘርፍ መካከል ያለውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑ ተመልክቷል።
በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ አኮያ ፕሮፐርቲስ በተለያዩ ፊልሞችና የጥበብ ስራዎቿ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈችውን አርቲስት እፀህይወት አበበን የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር አድርጎ በይፋ አስተዋውቋል። አርቲስቷ የድርጅቱን ገፅታ በመገንባትና የምርት ስሞቹን ለህዝብ በማስተዋወቅ ረገድ ግንባር ቀደም ስራዎችን እንደምትሰራ ተገልጿል።
ከ230 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረው አኮያ ግሩፕ፣ በውስጡ የተለያዩ ታላላቅ ድርጅቶችን አቅፎ የያዘ ግዙፍ ተቋም ነው። ከእነዚህም መካከል፦
📍አኮያ ፕሮፐርቲስ፦ በሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ ቤቶችን የሚያቀርብ፣
📍አኮያ ኮፊ፦ በቡና ምርትና ኤክስፖርት ላይ የተሰማራ፣
📍አኮያ ሞተርስ፦ በተሽከርካሪ ግብይት ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ ይገኙበታል።
❤ 37👎 6🔥 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን የሱዳንን ጦርነት ለማቆም ከትራምፕ ጋር ለመስራት ዝግጁ ነኝ ብለዋል።
የሱዳን ጦር መሪው ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ከሰሞኑን በሳዑዲ አረቢያ የነበሩ ሲሆን ከጉብኝታቸው መጠናቀቅ በኋላ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትራቸው በኩል በወጣ መግለጫ ጦርነቱ እንዲያበቃና ሰላም እንዲመጣ ከፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ ከውጪ ጉዳይ ኃላፊው ማርክ ሩቢዮና ከትራምፕ የቀጣናው ልዩ መልዕክተኛ ማሳድ ቡሎስ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸው ገልፀዋል።
ሳዑዲ አረቢያ በሱዳን ሰላም ለማምጣት የተመሰረተው የግብፅ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና አሜሪካ ጥምረት አካል ስትሆን ጀነራሉ ወደ ሪያድ ያመሩት በልዑል አልጋ ወራሹ መሃመድ ቢን ሳልማን ግብዣ ነው ተብሏል።
ልዑል አልጋ ወራሹ በቅርቡ ወደ ዋሽንግተን አምርተው ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር ሲነጋገሩ የሱዳን ጦርነትን በተመለከተ መምከራቸው ይታወሳል።
አልቡርሃን ከዚህ ቀደም የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የተቀበለውንና በትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ማሳድ ቡሎስ የቀረበውን የሰላም እቅድ አንቀበልም በማለታቸው ውጊያው ቀጥሏል።
ዘገባው የሚድል ኢስት ሞኒተር ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 63🤣 5🤯 2👍 1
የሳህል ቀጣና ወርቅ
የሳህል ቀጣና 3860 ኪሎሜትር የሚሸፍን ከሰሃራ በረሃ በስተደቡብ የሚገኝና ከአፍሪካ ምዕራብ እስከ ምስራቅ የሚገኝ አካባቢ ነው።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በዚህ ቀጣና ካሉት እንደ ሱዳን፣ ሊቢያ፣ ማሊ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ኒጀር እና ቻድ እንደዚሁም በቀጣናው ካሉ ሌሎች ሃገራት ጋርም በወርቅ ላይ የተመሰረተ ግንኙነት መስርታለች።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በ2024 በአጠቃላይ 105 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ያለው 1400 ቶን ወርቅ ወደ ሃገሯ ስታስገባ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ከአፍሪካ የገባ ነው።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ወርቅ አምራች ባትሆንም 11 በመቶ የአለም ወርቅ ላኪ ነች። ሃገሪቷ በዘርፉ ያላትን ስፍራ ለማስቀጠልም ከኢ መደበኛ ምንጮች ወርቅ እንደምትገዛ ይነገራል።
40,000 የወርቅ ማውጫ ቦታዎችና ከ18ቱ ግዛቶቿ በ13ቱ ግዛቶች 60 የማጣሪያ ድርጅቶች ያሏት ሱዳን ወርቅ በማምረት ቀዳሚዋ የአረብ ሃገር ስትሆን በ2024 ብቻ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሱዳን 29 ቶን ወርቅ ገዝታለች። በዚሁ አመትም አሜሪካ መቀመጫቸውን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ያደረጉ 11 ድርጅቶቾ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን በወርቅ ይደግፋሉ በሚል ማዕቀብ ጥላለች።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሊቢያው የትጥቅ መሪ ካሊፋ ሃፍታርም በተለያዩ መንገዶች ወርቅ ትሸምታለች ሲባል ከ2020 ወዲህ ብቻ ሊቢያ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ዋጋው 3 ቢሊየን ዶላር የተጠጋ ከ50-55 ቶን ወርቅ አጥታለች።
በወርቁ ምትክም የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሃፍታር ለሚመሩት የሊቢያ አብዮታዊ ዘብ የመሳሪያና የሎጅስቲክስ ድጋፍ ታቀርባለች።
በአፍሪካ ሁለተኛዋ ግዙፍ የወርቅ አምራች በሆነችው ማሊ 81 በመቶ የሚሆነው የወርቅ ማውጣት ስራን የሚያከናውኑት የኤምሬቶች ተቋማት ናቸው።
በ2024 ከሌላኛዋ ሃገር ቶጎ 4 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ያለው 52 ቶን ወርቅ ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሲላክ በዛው አመት 32 በመቶ የሚሆነው የቡርኪናፋሶ ወርቅም የተሸጠው ለኤምሬቶች ነው።
በጥር ወር 2024 1578 ኪሎግራም የሚመዝን የናይጄሪያ ወርቅ ያለ ዶክመንት ወደ ዱባይ ሲሄድ በአዲስ አበባም ተይዟል።
በ2022 ኒጀር ከ10 ሚሊየን ዩሮ በታች የሚያወጣ ወርቅ መላኳን ብትገልፅም በዱባይ የተደረጉ ምርመራዎች ኤምሬቶች ከኒጀር 457 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ወርቅ አስገብታለች።
በሁለቱ ቁጥሮች መካከል ያለውን ልዩነት ተከትሎም ኒጀር 82 የጉምሩክና የፖሊስ አባላቷ ላይ እርምጃ ወስዳለች።
ቻድ በ2024 ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች 2 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ወርቅ ስትልክ አይኤምኤፍ በ2023 ባወጣው መረጃ 3 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ያለው የወርቅ ሽያጭ በቻድ ይፋዊ ሰነድ አልተመዘገበም።
ከ2019-2020 ባለው ጊዜ ካሜሩን ለኤምሬቶች የላከችው ወርቅ 800,000 ዶላር ብቻ ነው ብትልም ኤምሬቶች ከካሜሩን ያስገባችው ወርቅ 340 ሚሊየን ዶላር እንደሚያወጣ ገልፃለች።
በ2020 ከ780 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ከወርቅ ባገኘችው ሞሪታኒያ 70 በመቶ የሚሆነው ህገወጥ የወርቅ ምርት መዳረሻው ዱባይ ነው።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በእነዚህ ሃገራት የተለያዩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችንና ስምምነቶችን ስትፈፅምም ከ2018-2023 ባለው ጊዜ ለኒጀር፣ ማሊ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ቻድና ሞሪታኒያ ከ700 ሚሊየን ዶላር በላይ እርዳታ አድርጋለች።
ጹሁፉ በ centre 4s ድህረገፅ የቀረበ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 57💔 13🤔 4😢 2👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ንብረቱ የአውሮፓ ሃገር የሆነ አውሮፕላን ከ35 ዓመታት በኋላ በባግዳድ አርፏል።
የኢራቅ የትራንስፖርት ሚኒስትር በግሪክ የሚተዳደር አውሮፕላን ከ35 ዓመታት በኋላ በባግዳድ ያረፈ የመጀመሪያው የአውሮፓ አውሮፕላን መሆኑን ገልጿል።
በ1990ዎቹ የወቅቱ የኢራቅ መሪ ሳዳም ሁሴን ኩዌትን መውረሩን ተከትሎ የአውሮፓ አየር መንገዶች ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ ወደ ባግዳድ በቀጥታ መብረር እንዳቆሙ ይታወሳል።
በ2003 አሜሪካ ኢራቅን ወራ ሳዳም ሁሴን ቢወርድም ሃገሪቱ ወደ እርስ በእርስ አመፅ ገብታ የሽብርተኞች መናኸሪያ ሆና ነበር።
ሃገሪቱ ከሁለት አስርት አመታት በኋላ አንፃራዊ መረጋጋት ስታሳይ የባግዳድ አቴንስ በረራም በሳምንት ሁለት ቀን መደረግ ይቀጥላል ተብሏል።
ዘገባው የአልአረቢያ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 47😢 4👍 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
📱ብድር ለመውሰድ ቀላል መንገድ ይፈልጋሉ?
Digaf MFI ብለው ከፕላይ ስቶር /playstore/ በማውረድ ብድር ማመልከት ይችላሉ፡፡
በስልክዎ ብቻ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ይመዝገቡ እና የብድር ሂደትዎን ቀላል አድርጉ!
👉 አሁን ይዉሰዱ | ቀላል | ፈጣን | ተደራሽ
📥 መተግበሪያውን አሁን ይጫኑ እና ብድር ሂደትዎን ቀላል አድርጉ!
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.digaf.digafselfapp
ለበለጠ መረጃ ደሞ 6575 ላይ ይደውሉ!
ድጋፍ አነስተኛ ብድር አቅራቢ አ/ማ
❤ 13
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ቴምርሪልስቴት፡ ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ 8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው።
ሳር ቤት ቫቲካን
🎯65/35 አከፍፈል
👉2መኝታ 106ካሬ ሙሉ ክፍያ 7.9ሚሊዮን
👉3መኝታ 139ካሬሙሉ ክፍያ 10.3ሚሊዮን
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 106ካሬ
20% ቅድመ ክፍያ 2.4ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 12.1ሚሊዮን
👉3መኝታ 139ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 3.1ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 15.9ሚሊዮን
አዋሬ
🎯65/35 አከፍፈል
👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉 1መኝታ 78ካሬ = 20%ቅድመ ክፍያ 1.7ሚሊዮን ፤ ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን
👉 3 መኝታ 117ካሬ = 20%ቅድመ ክፍያ 2.6 ሚሊዮን ፤ ሙሉ ክፍያ 12.9ሚሊዮን
👉 157 ካሬ = 20% ቅድመ ክፍያ 3.4ሚሊዮን ፤ ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን
ቀሪውን 80% በ 15ዙር ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት፤
* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇👇👇
0980782850
❤ 18👎 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
በመተት አስፈራርታ 3 መቶ ሺ ብር ከግል ተበዳይ ልትቀበል ያለች ተጠርጣሪ መያዙን ፖሊስ ገለጸ።
3መቶ ሺ ብር በባንክ ካላስገባህ በመተት በቤተሰብህ ላይ ጉዳት አደርሳለሁ እያለች ስታስፈራራ የነበረችን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
ግለሰቧ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ወሎ ሰፈር አካባቢ ከሚገኝ አንድ ፕላዛ ውስጥ በጽዳት ሰራተኝነት እና በአሳንሰር ተቆጣጣሪነት ተቀጥራ የምትሰራ ሲሆን የግል ተበዳይ በዚሁ ህንጻ ላይ ከሚገኝ የአንድ የግል ድርጅት የፋይናስ ኃላፊ ናቸው።
ተበዳይ ለፖሊስ በሰጡት ቃል የኔሰው የሚባል ግለሰብ ከአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ቢኮሎ ከሚባል አካባቢ እንደሚደውል ገልጸው 3መቶ ሺ ብር በባንክ ካላስገባህ ልጅህን የሰይጣን መሳቢያ አደርጋታለሁ የሚል የማስፈራሪያ መልዕክት በማያውቁት ስልክ ተደውሎ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።
ተጠርጣሪዋ የግል ተበዳይን በመከታተል ካጠናች በኋላ ማንነቷን በመደበቅ እና ድምጿን በመቀየር አስፈራርታ 25ሺ ብር በባንክ እንዲያስገቡላት ካደረገች በኋላ ቀሪ 275ሺ ብር ለማስላክ ስትሞክር የግል ተበዳይ ለፖሊስ በሰጡት መረጃና ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ልትያዝ ችላለች።
በተጨማሪም ፖሊስ ግለሰቧ ለግል ተበዳይ ለመላክ ያዘጋጀችው የማስፈራሪያ ጽሑፍ የእጅ ስልኳ ላይ መገኘቱን የገለጸ ሲሆን በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተጣራባት አስታውቋል።
😀 | @tikvahethmagazine
🤣 224❤ 86🤔 31👍 9👏 3😢 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
በቅርቡ ዛፍ በማቀፍ ጊነስ እውቅና የሰጣት ኬንያዊት በፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እውቅና ተሰጥቷታል።
ከቀናት በፊት የራሷን ሪከርድ ሰብራ ያለ ማቋረጥ ለ72 ሰዓታት ዛፍ ያቀፈችው ትሩፊና ሙቶኒ በፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለ15 ቢሊየን ዛፍ የመትከል ዘመቻ በአምባሳደርነት ተሹማለች።
ከአምባሳደርነት በተጨማሪ ከኬንያ የዱር እንስሳት አስተዳደርና ከኬንያ ቱሪዝም ቦርድ ለእሷና አብረዋት ለነበሩት ቡድኖቿ ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ እንዲዝናኑ ሩቶ አዘዋል።
ሙቶኒ የ72 ሰዓት ዛፍ የማቀፍ ተግባሯን ባለፈው በተካሄደው የአየር ንብረት ጉባኤ ወቅት በብራዚል ለማድረግ ፈልጋ አስፈላጊው ድጋፍ አልተደረገልኝም ያለች ሲሆን ዊሊያም ሩቶ ሜዳሊያ ከሰጧት በኋላ ብራዚልን ሄዳ እንድትጎበኝ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
ዘገባው የኬንያንስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
🤣 124❤ 65👍 15🤔 6👏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የኢሎን መስክ የተጣራ ሃብት 600 ቢሊየን ዶላር መድረሱን ፎርብስ ይፋ አደረገ።
የኢሎን መስክ የተጣራ ሃብት የስፔስ ኤክስ ዋጋ 800 ቢሊየን ዶላር መገመቱንና ለህዘብ ድርሻው ይሸጣል መባሉን ተከትሎ 600 ቢሊየን ዶላር ደርሷል ተብሏል።
መስክ 500 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ሃብት ላይ የደረሰ የመጀመሪያው የምድራችን ሰው ባለፈው ጥቅምት ወር የሆነ ሲሆን 600 ቢሊየን ዶላር ላይም የደረሰ የመጀመሪያው ሰው ሆኗል።
መስክ የስፔስ ኤክስ የ42% ባለድርሻ ሲሆን የድርጅቱ ዋጋ ግምትና በቀጣይ አመት ለህዝብ ገበያ እንደሚቀርብ ከተነገረ በኋላ የኢሎን መስክ ሃብት በ168 ቢሊየን ዶላር ጨምሮ 677 ቢሊየን ዶላር ደርሷል።
ኢሎን መስክ ከስፔስ ኤክስ በተጨማሪ የቴስላ እና የኤክስ ኤአይ ተቋም ከፍተኛ ባለድርሻ ሲሆን እነዚህም ድርጅቶች የአክሲዮን ዋጋቸው እየጨመረ ይገኛል።
የኢሎን መስክን ሃብት መጨመር ተከትሎም የአለማችን 10 ሃብታም ግለሰቦች የያዙት የሃብት መጠን 2.5 ትሪሊየን ዶላር ተሻግሯል።
በዚህ አመት ብቻ የአለማችን አስሩ ሃብታሞች ሃብት በ558.9 ቢሊየን ዶላር ጨምሯል ሲባል ዘጠኙ ከአሜሪካ ሲሆኑ ከአስሩ ስምንቱ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ናቸው።
በዚህ አመት የኢሎን መስክ ሃብት በ205 ቢሊየን ዶላር ሲጨምር በሁለተኝነት የተቀመጠው የጎግሉ ላሪ ፔጅ ሃብት በዚህ አመት በ96.8 ቢሊየን ዶላር ጨምሮ 265 ቢሊየን ደርሷል።
በሶስተኝነት የጎግሉ ሌላኛው መስራች ሰርጂ ብሪን በ247 ቢሊየን ዶላር ሲቀመጥ የአራተኛ ስፍራውን የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ በ246 ቢሊየን ዶላር ይዞታል።
መስክን ከወራት በፊት በመብለጥ የአለማችን ቱጃሩ ተብሎ የነበረው ላሪ ኤሊሰን ሃብቱ በ46.1 ቢሊየን በመጨመር በ238 ቢሊየን ዶላር አምስተኛ ሆኗል።
ዘገባው የሮይተርስ እና አናዶሉ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 66👏 41🤣 19🤔 13🤯 12👎 4👍 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
❤ 15🤣 7👎 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
ኬንያ ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርዓቶች ከእስራኤል ተረከበች።
ኬንያ "SPYDER" እና "PYthon" የተሰኙ ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርዓቶችን ከእስራኤል ታጥቃለች።
ራፋኤል አድቫንስድ መከላከያ ስርዓት በተባለ ተቋም የሚመረተው ስርዓት የአውሮፕላን፣ ድሮን እና ሚሳኤሎችን ስጋት መቀልበስ ይችላል ተብሏል።
ኬንያ ስርዓቱን የታጠቀችው ከእስራኤል መንግስት በደገፈው የ26 ሚሊየን ዶላር ወይም 3.4 ሽልንግ ብድር ነው ተብሏል።
ኬንያ "SPYDER" የተሰኘውን የአየር መከላከያ ስርዓትም ከኢትዮጵያ እና ሞሮኮ ቀጥላ የታጠቀች ሶስተኛዋ የአፍሪካ ሃገር ሆናለች ተብሏል።
የኬንያ የአየር መከላከያ ስርዓት ግዢ በኬንያና እስራኤል መካከል ያለውን ትብብር ያሳየ ነው ሲባል እንደ ድሮን ያሉ መሳሪያዎች እየታጠቀ ካለው አልሸባብ ሊቃጣ የሚችልን ጥቃት ለመመከትም ይጠቅማል ተብሏል።
ዘገባው የኬንያንስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 55👍 30🤣 23👎 1
