አዲስ ነገር መረጃ
Открыть в Telegram
#አዲስ_ነገር_መረጃ #መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ Addis Ababa , Ethiopia Buy Ads : https://telega.io/?r=UbutLo2z #ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot
Больше2025 год в цифрах

103 594
Подписчики
-9224 часа
-3717 дней
+21730 день
Архив постов
Фото недоступноПоказать в Telegram
ይህ መረጃ በኢትዮጵያ የስነ-ከዋክብት ተመራማሪ በሆኑት በዶ/ር ሮዳስ ታደሰ የተሰጠ ሳይንሳዊ ትንበያ ሲሆን፣ ከሥነ-ፈለክ (Astronomy) አንጻር ሲታይ ፍጹም ትክክልና የሚከሰት ክስተት ነው።
የዕለቱ ዋና ዜና፡ የታህሳስ 11/12 ልዩ የሥነ-ፈለክ ክስተት
በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ታህሳስ 12 (በፈረንጆቹ December 21 ወይም 22) "Winter Solstice" ወይም የክረምት መለወጫ ተብሎ የሚጠራው ዕለት ነው። ዶ/ር ሮዳስ ያስተላለፉት መልዕክት የሚከተሉትን ነጥቦች ያጠቃልላል፦
* የቀኑ ርዝመት፡ ይህ ዕለት በሰሜናዊው የዓለም ክፍል (ኢትዮጵያን ጨምሮ) የዓመቱ አጭሩ ቀን ነው።
* የሌሊቱ ርዝመት፡ በአንጻሩ የዓመቱ ረጅሙ ሌሊት የሚመዘገብበት ወቅት ነው።
* ምክንያቱ፡ መሬት በዝንባሌዋ (Axial tilt) ምክንያት ከፀሐይ ርቃ የምትገኝበት የመጨረሻው ነጥብ ላይ በመድረሷ ነው።
ለምን እውነት ይሆናል? (ሳይንሳዊ ማብራሪያ)
ይሁን እንጂ ዶ/ር ሮዳስ ማህበረሰቡ ስለ ተፈጥሮ ክስተቶች ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግ የሚጠቀሙበት ሳይንሳዊ ሃቅ ነው።
* የፀሐይ ጉዞ፦ ፀሐይ በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ (Tropic of Capricorn) ላይ ቀጥታ ስለምታርፍ፣ ለእኛ ለሰሜናዊያኑ ብርሃኗ አጭር ሰዓት ብቻ ይቆያል።
* ቀጥታ ተፅዕኖ፦ ነገ እሁድ ፀሐይ ዘግይታ ትወጣለች፤ ቀድማም ትጠልቃለች። ይህም "ቶሎ ይመሻል" የተባለበትን ምክንያት ያረጋግጣል።
ማሳሰቢያ፦ ነገ እሁድ ታህሳስ 12 ቀን፣ ቀኑ አጭር በመሆኑ ለስራና ለጉዞ የምታቅዱ ሰዎች ጊዜያችሁን በአግባቡ እንድትጠቀሙ ይመከራል። ፀሐይ ቀድማ ስለምትጠልቅ የምሽቱ ጨለማ ረጅም ይሆናል።
በዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
@Addis_News
@Addis_News
❤ 75👍 13🤣 13👏 9🙏 3
04:30
Видео недоступноПоказать в Telegram
ጋይስ ይሄን እድል ተጠቀሙበት አዲሰ onlin ስራነዉ 100%ይከፍላል ስሙ buzzer app ይባላል በ 3 መንገድ ይከፍላል
1ኛ እንደ ቲክቶክ ስፖርታዊ አጫጭር ቪዲዩ በመልቀቅ ከቲክቶክ እያወረዳቹ በ 1k view ጀምሮ ይከፍላችሆል
2ኛ በኢንቫይት ሰው በመጋበዝ 0.15 ዶላር በናንተ ሊንክ ብቻ ስለከፈቱ ይከፍላችሆል
3ኛ ታስኮች አለ ቪዲዩ በማየት ላይክ በማድረግ ኮሜንት በመፃፍ ይከፍላል
🤑ልክ $10 ሲሞላ ማውጣት ትችላላችሁ
🧲አካውንት ለመክፈት ይህን step ተከተሉ
✔️ይህን ሊንክ ተጭናችሁ አፑን ከplaystore or appstore አውረዱ 👇
https://app.buzzerfan.com/referral-invite/rsdf3de6aff03447bab57010ece7626afe
በመቀጠል email ካላችሁ n emailላችሁ መግባት ትችላላችሁ ካልሆነ ግን create account ሚለውን ተጭናችሁ email እና የማረሱትን password አስገቡ ከዛ በemail የላከላችሁን ኮድ አስገቡ
✔️በመቀጠል username,first & last name አስገቡ ከዛ gender,age አስገቡ
✔️በመቀጠል referral code የሚል ሲመጣላችሁ bonus point ለማግኘት ይህን ኮድ አስገቡ 👉 6AF10E
✔️አሁን አካውንት ከፍታችኋል ከዚህ በኋላ ቪዲዮ እየጫናችሁ በ1k view ትከፈላላችሁ
በተጨማሪም 1ሰው ስጋብዙ $0.15 ታገኛላችሁ
✔️ከዚህ በኋላ መስራት ነው እድሉን ተጠቀሙ ሞክሩት ቪዲዮም ሙሉ ማብራሪያ ከፈለጋቹ አከፋፈቱን ከላይ የሰራነውን video ይመልከቱ
referral code 👉 6AF10E ይቺን ማስገባት
እንዳይረሳ አብረን ብዙ ስራዎችን ስለምንሰራ አዳዲስ መረጃም ካለ አሳዉቃለሁኝ
31.85 MB
❤ 10💯 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
ጥንቃቄ!! ከአጭበርባሪዎች ተጠበቁ!!!
📌ማንኛውንም በስልክ የሚመጣ ጥያቄ ባለመቀበል እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ!!!
''ባንካችን ብሔራዊ ባንክ ያወጣውን መመሪያ መሰረት በማድረግ ደንበኞቻችን በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ የባንክ ሒሳብ ቁጥራቸውን ከፋይዳ መታወቂያቸው ጋር እንዲያጣምሩ ያስተላለፈውን መልእክት እንደ አጋጣሚ በመጠቀም አጭበርባሪዎች ደንበኞቻችን ጋር እየደወሉ አገልግሎቱ በስልክ እንደሚሰጥ እንዲሁም የባንክ ሂሳብ በዚህ ምክንያት እንደሚዘጋ በማስመሰል ለማጭበርበር እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ ደርሰንበታል።
በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን ሒሳብን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር የማጣመሩ ሥራም ሆነ ሌሎች ከሞባይል ባንኪንግ ጋር የተያያዙ እና ማናቸውም አገልግሎቶች እርስዎ በአካል ወደ ቅርንጫፍ ካልሄዱ/ካልቀረቡ በስተቀር በስልክ ተደውሎ የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ በስልክ ለሚመጡ ጥያቄዎች ምላሽ ባለመስጠት እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች እንድትጠብቁ በአክብሮት እናሳውቃለን!''
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 17👍 8🤪 4
አሚጎስ በአንድ ጀምበር አምስት ቅርንጫፍ ቢሮዎችን ከፈተ
አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህ/ስ/ማህበር በሶስት ሳምንታት ግዜ ውስጥ ገንብቶ ያጠናቀቀውን አምስት ቅርንጫፍ ቢሮዎች በመርካቶ ፣ በልደታ፣ በደምበል፣ በቱሉዲምቱ እና በሰሚት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።
አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማኅበር የተቋቋመው በኢትዮጵያ የኅብረት ስራ ማህበር አዋጅ መሰረት በቁጥር 147/1998 ሲሆን ሕጋዊ ፍቃዱን ከአራዳ ክፍለ ከተማ የህብረት ስራ ማህበር ማደራጃ ቢሮ እና ከንግድ ሚኒስቴር በጥር 2005 ዓ.ም አግኝቷል።
በተጨማሪም በፌደራል ደረጃ ማለትም በኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ስር ማስተዳደር ከጀመረ ከአንድ አመት በላይ አስቆጥሯል። የአሚጎስ አላማ የአባላትን አቅም መሰረት ያደረገ መደበኛ ተቀማጭ በመሰብሰብ ለአባላት ተደራሽ፣ አዋጭ፣ ምቹ እና ቀልጣፋ የፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት አባላትን የተሻለ መተዳደሪያ እንዲኖራቸው ማገዝ ነው።
የአሚጎስ ራዕይ በ2030 በአለምአቀፍ ደረጃ ተመራጭ የፋይናስ ተቋም ሁኖ መገኘት ሲሆን አሚጎስ ያለበት የእድገት ደረጃ በአሁኑ ሰዓት የአባላቱን ቁጥር 13 ሺህ አድርሷል፤ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት አካብቷል እንዲሁም ከ6ሺ በላይ ለሚሆኑ አባላቶቹ ከ7 ቢሊየን ብር በላይ ብድር መስጠቱን ብስራት ሰምቷል።በተጨማሪም በቅርቡ የሚከፈቱትን ቅርንጫፍ ቢሮዎችን ጨምሮ በአዲስ አበባ 10 በክልል ከተሞች ደግሞ 7 ቅርንጫፍ ቢሮዎችን ከፍቷል።
ቅርብ በሚባሉ ግዜያት ውስጥ ደግሞ በአሶሳ፣ በሀዋሳ፣ በጅማ ቢሮዎቹን ለመክፈት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ አሚጎስ ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካ እና በዓለም ዓቀፍ ህብረት ስራ ጥምረት ተሳታፊ ለመሆን በቅቷል።
አለማቀፉ የህብረት ስራ ማህበር ኮንፌደሬሽ ኢንተርናሽል ኮፕሬቲቭ አልያንስ፣ አሚጎስ በተሳተፈባቸው ማህበራዊ ጉዳዮች አድናቆትን አግኝቷል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ህብረት ስራ ማህበራት መካከል በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እውቅናን አግኝቷል።
Dagu
@Addis_News
@Addis_News
❤ 14
01:08
Видео недоступноПоказать в Telegram
👉 ከ8 በላይ ሳይቶችን ገንብቶ ያስረከበው
ቴምር ፕሮፐርቲ
አሁንም በድጋሜ አዳዲስ ሳይቶችን
ለሽያጭ አቅርቧል ።
📍 ሳር ቤት
#በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ)
👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 5.7ሚ
👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚ
👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚ
👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 11.4ሚ
#በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን)
👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚ
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን)
👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚ
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን)
📍 አዋሬ
#በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ)
👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 145ካሬ = 10.3ሚሊዮን
#በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 78ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.7ሚሊዮን)
👉 135ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 14.8ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.9ሚሊዮን)
👉 157ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.4ሚሊዮን)
⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ ;- 0940464607
0994003949
25.16 MB
❤ 12
Фото недоступноПоказать в Telegram
ስልኮ መልክዎን እያበላሸው ይሆን
ቆዳችንን ከፀሐይ ጨረር ለመጠበቅ እንጠነቀቃለን፤ ነገር ግን በቀን ለሰዓታት ከምንመለከተው ስልክና ኮምፒውተር የሚወጣው "ሰማያዊ ብርሃን" (Blue Light) ተመሳሳይ ወይም የከፋ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ጥናቶች እያመለከቱ ነው።
እንደ "Journal of Investigative Dermatology" ያሉ የቆዳ ጤና ጥናት ተቋማት ላይ የወጡ ጥናቶች፤ ለረጅም ሰዓታት ለዲጂታል ስክሪኖች መጋለጥ የቆዳን ጥንካሬ በማዳከም ቆዳችን ያለዕድሜው እንዲሸበሸብ ያደርጋል ይላሉ።
ከስክሪን የሚወጣው ሰማያዊ ብርሃን ወደ ቆዳችን ጥልቅ ክፍል (Dermis) ዘልቆ በመግባት የቆዳን ወጣትነት የሚጠብቀውን ኮላጅን (Collagen) እና ኤላስቲን (Elastin) ይሰብራል። ይህም ቆዳ እንዲላላ፣ እንዲዝልና ጥቁር ነጠብጣቦች እንዲፈጠሩ ያደርጋል።
የቆዳ ሐኪሞች እንደሚመክሩት፤ በስልካችን ላይ "Blue Light Filter" ወይም "Night Mode" ማብራት የብርሃኑን ኃይል ለመቀነስ ይረዳል።
በተጨማሪም፣ የቆዳን መከላከያ አቅም የሚጨምሩ በ"አንቲ-ኦክሲዳንት" የበለጸጉ የቆዳ ቅባቶችን መጠቀምና ከስክሪን ራቅ ያለ ጊዜን ማዘውተር ለቆዳ ጤና ወሳኝ እንደሆነም ያስቀምጣሉ።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 16😢 3
የክልል መንግስታት ተግባራዊ እንዲያደርጉት የተዘጋጀው አዲሱ የንብረት ታክስ ሞዴል አዋጅ፣ በሕግ ከታክስ ነጻ የተደረጉ ንብረቶችና ተቋማት ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች ማካካሻ የሚሆን “በታክስ ምትክ የሚደረግ መዋጮ” እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ድንጋጌ ይፋ አደረገ።
ይህ ውሳኔ በከተሞች ውስጥ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በሁሉም ተጠቃሚዎች እንዲደገፉ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህ አዋጅ የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት ከቀጥተኛ የንብረት ታክስ ነጻ እንዲሆኑ ተደንግጓል። ሆኖም እነዚህ ተቋማት የሚገኙባቸው አካባቢዎች በከተማ አስተዳደሩ የሚከናወኑ እንደ መንገድ ጥገና፣ የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የጎዳና መብራት፣ የጽዳትና የደህንነት አገልግሎቶች ተጠቃሚ በመሆናቸው፣ ለእነዚህ አገልግሎቶች ማካካሻ የሚሆን መዋጮ እንዲከፍሉ ተደንግጓል።
እንደ ገንዘብ ሚኒስትር ማብራሪያ ከሆነ፤ የሃይማኖት ተቋማት ለአምልኮና ለመካነ መቃብር የሚጠቀሙባቸው ንብረቶች፣ ለህብረተሰቡ ነጻ ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ እንዲሁም የመንግሥት ቢሮዎችና ዲፕሎማቲክ ተቋማት የሚጠቀሙባቸው ንብረቶች ከታክስ ነጻ ቢሆኑም፣ እንደየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ “በታክስ ምትክ የሚደረግ መዋጮ” ሊጠየቁ ይችላሉ።
@Addis_News
@Addis_News
❤ 4🤣 2
በጥቁር ገበያውና በመደበኛው መካከል ያለው የዶላር ምንዛሬ ልዩነት በ4 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተገለጸ!
በ2018 በጀት አመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ውስጥ ይፋ በተደረገ ጥናት በጥቁር ገበያውና በመደበኛው መካከል ያለው የዶላር ምንዛሬ ልዩነት፤ ከ18 ነጥብ 4 በመቶ ወደ 13 ነጥብ 7 በመቶ በመውረድ ልዩነቱ ወደ 4 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ማለቱን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ለአሐዱ ሬዲዮ አስታውቋል።
ከማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ በኋላ የውጪ ምንዛሬ ሁኔታው ምን ላይ እንደሚገኝ እና የብርና የዶላር ምንዛሬ በገበያ ላይ ስላለው ሁኔታ ጥናት መደረጉን የገለፁት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ከፍተኛ ተመራማሪ ናስር የኑስ (ዶ/ር) ናቸው።
በጥናቱም በ2018 በጀት ዓመት ሩብ ዓመት ውስጥ ቀደም ሲል ከነበረው አንፃር የዶላር ምንዛሬ በመደበኛ እና በጥቁር ገበያው መካከል ያለው ልዩነት በአንፃራዊነት መጥበብ መቻሉን አንስተዋል።
ከተያዘው ሩብ ዓመት በፊት በመደበኛውና በጥቁር ገበያው መካከል ያለው የዶላር ምንዛሬ 18 ነጥብ 4 በመቶ ልዩነት የነበረው ሲሆን በዚህ ሩብ ዓመት ግን ወደ 13 ነጥብ 7 በመቶ መውረዱን ተናግረዋል።
ከዚህ ባሻገር እንደአጠቃላይ ያለው የብር ዋጋን በሚመለከት ግን አሁንም ድረስ የዶላርና የብር ምንዛሬ የተረጋጋ ሁኔታ ላይ አለመሆኑን ያነሱ ሲሆን፤ 2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ሩብ ዓመት ውስጥ ብር ከዶላር ጋር ያለው የምንዛሬ መጠን በ8 ነጥብ 1 መቀነሱን ተናግረዋል።
ይህም በ2017 የመጨረሻ በጀት ዓመት ሩብ አመት ጋር ከነበረው ከ4 በመቶ በላይ መጨመሩን ገልጸዋል።
ይህም አሁንም ድረስ ገበያው ትክክለኛ የሆነ መረጋጋት ላይ አለመሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፤ ብር ከዶላር አንፃር ያለው ዋጋ መቀነሱ በገበያው ላይ ጫና እንደሚፈጥር አንስተዋል።
ኢትዮጵያ በርካታ ምርቶችን ከውጪ የምታስገባ ከመሆኗ አንፃር የብር ዋጋ በቀነሰ ቁጥር ምርቶች እየተወደዱ እንደሚመጡ የገለጹት ከፍተኛ ተመራማሪው፤ ወደ ሀገር ውስጥ የራሳቸው የሆነ የዋጋ ግሽበትን በማምጣት የዋጋ መረጋጋት እንዳይኖር አስተዋጽኦ እንደሚያሳድሩ ተናግረዋል።
የዋጋ መረጋጋት ከሌለ ሰዎች በብር እርግጠኛ ስለማይሆኑ ያላቸውን ሀብት በዶላር ለመያዝና ወደሌላ ሀገር ለማሸሽ በሚሞክሩበት ወቅት ምጣኔ ሀብቱን እንደሚያዛባ አንስተዋል።
በመሆኑም ይህንን ለማስተካከል የሀገር ውስጥ አቅርቦትን መጨመርና የምጣኔ ሀብቱን መዋቅር ማስተካከል እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ በብዛት ወደውጭ የምትልከው የግብርና ምርቶችን መሆኑን የሚያነሱት ከፍተኛ ተመራማሪው እነዚህ ምርቶች ደግሞ ኢትዮጵያ የምትፈልገውን የውጪ ምንዛሬ በሚፈለገው መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንድታገኝ እያስቻሉ አይደለም ብለዋል።
ስለዚህ እነዚህ ችግሮች መቀረፍ፣ የውጪ ኢንቨስትመንትም ማደግና የሀገር ውስጥ ገቢው ከትይዩ ገበያ ወጥቶ ወደ ሕጋዊ መስመር መግባት እንደሚጠበቅበት በመግለጽ፤ ይህ ካልሆነ ግን ያለው አለመረጋጋት እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችል አሳስበዋል።
Via Ahadu
@Addis_News
@Addis_News
❤ 16🤣 5
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንቁራሪቶች ካንሰርን ድል ነሱ
በአምፊቢያን (የውሃና የየብስ እንስሳት) ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የካንሰር ሕዋስ ማጥፋት የሚችል ባክቴሪያ ተገኝቷል።
Ewingella americana የተባለው ባክቴሪያ የተገኘው በጃፓን የዛፍ እንቁራሪቶች አንጀት ውስጥ ነው። ይህ ባክቴሪያ በሰውነት ውስጥ በራሱ በመንቀሳቀስ የዕጢ ቦታዎችን በመፈለግ ያጠፋቸዋል፤ ካንሰሩም ተመልሶ እንዳይከሰት ያደርጋል።
በአይጦች ላይ የተደረገ ሙከራ አስገራሚ ውጤት አስገኝቷል፦ አንድ ጊዜ ብቻ የተሰጠ የዚህ ባክቴሪያ መርፌ በአይጦቹ ላይ የነበሩትን የካንሰር ዕጢዎች በ100% ስኬት አጥፍቷል።
ባክቴሪያው ሌሎች የሰውነት ክፍሎችን ስለማይጎዳ ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ ተገልጿል።
ዕጢዎቹ በሦስት ቀናት ውስጥ ጠፍተዋል።
እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ፣ ይህ ዘዴ ከኬሞቴራፒ እና ከኢሚውኖቴራፒ የበለጠ አስተማማኝ ነው።
ሳይንቲስቶች በአሁኑ ጊዜ በሰዎች ላይ ሙከራ ለማድረግ እየተዘጋጁ ነው። ይህ ሙከራ ከተሳካ በሕክምናው ዘርፍ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ግኝት ይሆናል።
@Addis_News
@Addis_News
❤ 62👏 13
የጨዋታ ቀን
በ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ስምንት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
ቼልሲ ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ አቅንቶ ኒውካስል ዩናይትድን የሚገጥምበት የዕለቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ቀን 9 ሰዓት ከ30 ይደረጋል፡፡
በሌላ ጨዋታ በሊጉ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በሜዳው ኢትሃድ ዌስትሃም ዩናይትድን ያስተናግዳል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ፤ አርሰናል እስኪጫወት ድረስ ሊጉን በ37 ነጥብ መምራት ይጀምራል፡፡
ወልቭስ ከብሬንትፎርድ፣ ብራይተን ከሰንደርላንድ እንዲሁም ቦርንማውዝ ከበርንሌይ በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡
ምሽት 2 ሰዓት ከ30 በሊጉ ወጥ ብቃት ማሳየት የተቸገሩትን ቶትንሃም ሆትስፐር እና ሊቨርፑል የሚያገናኘው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
የሊጉ መሪ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ተጉዞ መሪነቱን ለማጠናከር ምሽት 5 ሰዓት ላይ ኤቨርተንን የሚገጥምበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
መድፈኞቹ በሊጉ ከኤቨርተን ጋር ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ሦስቱን በማሸነፍ የበላይነት ያላቸው ሲሆን፥ በሁለቱ አቻ ተለያይተዋል፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ሊድስ ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
@Addis_News
@Addis_News
❤ 20
Фото недоступноПоказать в Telegram
አሜሪካ በጋዛ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍ ጠየቀች
በ'የደራው መጽሔት
#Ethiopia | የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ ከጦርነት በኋላ በጋዛ ሰርጥ ለሚቋቋመው ዓለም አቀፍ የፀጥታ ኃይል ኢትዮጵያ ወታደሮቿን እንድታበረክት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ።
ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ዲፕሎማቶች ለዘ ታይምስ ኦፍ ኢስራኤል እንደገለጹት፣ ጥያቄው የቀረበው በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ማርኮ ሩቢዮ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።
ዋሽንግተን ኢትዮጵያን የመረጠችበት ዋና ምክንያት፡-
* የዳበረ ልምድ፦ ኢትዮጵያ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት (እንደ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና አቢዬ) ባላት ስኬታማ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ የምትታወቅ መሆኑ።
* ገለልተኝነት፦ ከጦርነቱ ማብቂያ በኋላ አካባቢውን ለማረጋጋትና ለማስተዳደር የሚቋቋመው ኃይል ተቀባይነት ያለውና ገለልተኛ እንዲሆን ከመፈለጉ የተነሳ ነው።
📌የኢትዮጵያ ምላሽና አንድምታው
ምንም እንኳን ሲጂቲኤን አፍሪካ ጥያቄው መቅረቡን ቢያረጋግጥም፣ እስካሁን ድረስ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ የለም።
muktarovich
@Addis_News
@Addis_News
🤣 37👏 16❤ 11🤔 6
00:37
Видео недоступноПоказать в Telegram
🌟🌟ታላቅ የበዓል ቅናሽ በካሬ 78,000 ብር
✅እንዲሁም ሙሉ ክፍያ ለሚከፊል በካሬ 54,800
🔷 በ10 % ቅድመ ክፍያ
🔷 50 % የባንክ ብድር የተመቻቸለት
📍Location እንግሊዝ ኢንባሲ አጠገብ ውብ እይታ (Top View) ያላቸው ቤቶች በሽያጭ ላይ እንገኛለን
👉ከባለ 2 መኝታ- ባለ4 መኝታ
✅ ህንፃው ላይ ያሉ ተጨማሪ አገልግሎትች
👉5 ሰፋፊ ሊፍት /elevator
👉የቆሻሻ መጣያ/garbage chute
👉አውቶማቲክ ጀኔረተር/ automatic generator
👉ሰገነት/terrace
👉የመኪና ማቆምያ/car parking
👉 ጂም , እስፖ
👉 የዋና ገንዳ
👉 የልጆች መጫወታ
✨ባለ 2 መኝታ
138 ካሬ
157.3 ካሬ
163.6 ካሬ
✨ባለ 3 መኝታ
152.4 ካሬ
158.1 ካሬ
187.6 ካሬ
211.5 ካሬ
✨ባለ 4 መኝታ
240.7 ካሬ
258.4 ካሬ
📞 ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
0973559591
0919489575
Telegram -@Homef17
7.49 MB
❤ 3💯 2👍 1
በጋዛ በትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመ የእስራኤል ጥቃት 6 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ።
የቅርብ ጊዜውን የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ እስራኤል 6 ፍልስጤማውያን በጋዛ ወደ ትምህር ቤት በተቀየረ መጠለያ ላይ ባደረሰችው ጥቃት መግደሏ ተዘግቧል።
በጥቃቱ ህጻናትን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል።
ጥቃቱ የደረሰው በምስራቅ ጋዛ ከተማ ቱፋህ ሰፈር በሚገኘው ትምህርት ቤት ላይ ነው ተብሏል።
የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ፥ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ በሚቀጥለው ምዕራፍ ላይ ለመወያየት የኳታር፣ ግብፅ እና ቱርኪዬ ከፍተኛ ባለስልጣናትን በማያሚ፣ ፍሎሪዳ ያስተናግዳሉ።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፥ ሀማስን ትጥቅ ማስፈታት ይገባል ሲሉ ያሳሰቡ ሲሆን፥ አንድ የሃማስ ከፍተኛ ባለስልጣን በበኩላቸው ንግግሮቹ የእስራኤልን የተኩስ አቁም ጥሰቶች ለማስቆምም መሆን አለባቸው ማለታቸውን የዘገበው አልጀዚራ ነው።
@Addis_News
@Addis_News
❤ 11😢 9👏 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አለማችን ላይ 𝟔 𝐁𝐈𝐋𝐋𝐈𝐎𝐍 በላይ የሚሆነው ህዝብ አንዴም ቢሆን አውሮፕላን ውስጥ ገብቷ እያውቅም ( የዚን ቁጥር ከፍተኛ ድርሻ የሚወስዱት ሀገሮች 𝐈𝐍𝐃𝐈𝐀 እና 𝐂𝐇𝐈𝐍𝐀 ሲሆኑ ሀገራችን 𝐄𝐓𝐇𝐈𝐎𝐏𝐈𝐀 ደግሞ ከ 𝟏𝟏𝟓 𝐌𝐈𝐋𝐋𝐈𝐎𝐍 በላይ የሚሆነው ህዝቧ አውሮፕላን ውስጥ ከነ ጭራሹ ገብቷ አያውቅም !
@Addis_News
@Addis_News
🤣 80😢 10❤ 9🤪 6🫡 2
ሰው-ሰራሽ ክህሎት (AI)፤ የሰው ልጅ ረዳት ወይስ የወደፊት ስጋት?
ሰው-ሰራሽ ክህሎት (AI) በሦስት ዋና ዋና የዕድገት ደረጃዎች ይከፈላል፤ የመጀመሪያው ANI (Narrow Intelligence) የሚባለው ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት በስፋት በሥራ ላይ የሚገኝ የቴክኖሎጂ ደረጃ ነው። ይህ አይነቱ AI እንደ ቼዝ መጫወት ወይም ቋንቋ መተርጎም ያሉ የተወሰኑ ተግባራትን ብቻ እንዲያከናውን ተደርጎ የተሠራ በመሆኑ፣ ከተሰጠው ዓላማ ውጭ ሌላ ነገር ማከናወን የማይችል "ደካማ AI" ተብሎ ይታወቃል።
ሁለተኛው ደረጃ AGI (General Intelligence) ሲሆን፣ ይህም ማሽኖች እንደ ሰው ልጅ የማሰብ፣ የመረዳት እና ችግሮችን የመፍታት አቅም የሚኖራቸውበት ደረጃ ነው። በዚህ ደረጃ ላይ ያለ ማሽን አዳዲስ ነገሮችን በራሱ መማር፣ እቅዶችን ማውጣትና ውሳኔዎችን መስጠት የሚችል ቢሆንም፣ የሰውን አእምሮ ውስብስብነት በማሽኑ ውስጥ ለመቅረጽ ገና ረጅም ዓመታት የሚፈጅ ምርምርና ጥናት እንደሚያስፈልገው ይታመናል።
ሦስተኛውና የመጨረሻው ASI (Super Intelligence) ሲሆን፣ ይህም በሁሉም የዕውቀት ዘርፎች የሰውን ልጅ አእምሮ እጅግ በጣም የሚበልጥ የቴክኖሎጂ ደረጃ ነው። ይህ አይነቱ AI ከሳይንሳዊ ግኝቶች እስከ ማህበራዊ ግንኙነቶች ድረስ ካሉ ምርጥ የሰው ልጅ ጠቢባን በላይ ብቃት እንደሚኖረው የሚገመት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከሳይንስ ልብ-ወለድ ፊልሞች ባልዘለለ መልኩ በንድፈ-ሃሳብ ደረጃ ብቻ የሚገኝ ነው።
"የሰው ልጅ በራሱ ፈጠራ ሊገዛ ይችላልን?" የሚለው አሳሳቢ ጥያቄ የሚነሳውም በተለይ ይህ ASI ደረጃ ላይ ስንደርስ ሲሆን፣ ይህም ቴክኖሎጂው ከሰው ቁጥጥር ውጭ ሊሆን እንደሚችል ስጋት ይፈጥራል። በመሆኑም የሰው ልጅ ይህን ኃያል ቴክኖሎጂ ሲያለማ ከጥቅሙ ጎን ለጎን ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ለመከላከል ጥብቅ የሆኑ የሥነ-ምግባር እና የቁጥጥር ደንቦችን ቀድሞ ማዘጋጀት እንዳለበት በዘርፉ ያሉ ሊቃውንት ያስጠነቅቃሉ።
@Addis_News
@Addis_News
❤ 15😢 4
አባቱ አብዩድ ወይም ይሥሐቅ እናቱ ክሪስቲና ወይም ታውክልያ ይባላሉ።
ሚያዝያ 5 ቀን በ505 ዓ.ም በአክሱም ከተማ ተወለደ፡፡ በተወለደ በ7 ዓመቱ አባቱ ስለሞተ እናቱ የአክሱም ገበዝ የነበረው አጎቱ ጌዴዎን እንዲያስተምረው አደራ ሰጠችው፡፡
ቅዱስ ያሬድ ለሰባት ዓመት ተምሮ ፈቀቅ ባለማለቱ አንድ ቀን አጎቱ ተቆጥቶ ገርፈው፡፡ መታገስ ተስኖት ማይኪራህ ወደምትባል የቀዳማዊ ምኒልክ መቃብር ቦታ ሄዶ ተደበቀ፡፡ ቅዱስ ያሬድም በዛፍ ስር አርፎ እያለ አንዲት ትል ዛፉ ላይ ለመውጣት ስድስት ጊዜ ስትወጣና ስትወርድ ከቆየች በኃላ በሰባተኛው ዛፉ ላይ ወጥታ የዛፉን ፍሬ ስትበላ ተመለከተ፡፡ ቅዱስ ያሬድ ትሏ ከብዙ ድካምና ጥረት በኃላ ያሰበችውን ስታሳካ ተመልክቶ ራሱን በመውቀስ ወደ መምህሩ ተመልሶና ይቅርታ ጠይቆ ትምህርቱን ቀጠለ፡፡
ወደ አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን አዘውትሮ በመሔድም ጥበብና እውቀትን የሚገልጽ እግዚአብሔርን ይለምን ነበር፡፡ በጣም በአጭር ጊዜም 150 መዝሙረ ዳዊት፣ መኃልየ ነቢያት፣ መኃልየ ሰሎሞን ሌሎችንና ትርጓሜ መጻሕፍት ብሉያትና ሐዲሳትን አወቀ፡፡ ዜማ ባልነበረበት በዚያ ዘመን በስልት እያነበቡ ያመሰግኑ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ኅዳር 5 ቀን 527 ዓ.ም በኤዶም ገነት በሥላሴ አምሳል ሦስት አእዋፍን ወደ እርሱ ላከ፤ እነሱም በግዕዝ፣ ዕዝልና በአራራይ ዜማ ማዜምን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ለቅዱስ ያሬድ ዜማ ገልጹለት፡፡ ድምጹን ከፍ አድርጎም “ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን….” ብሎ በልሳነ ግዕዝ አዜመ፡፡
ሃሌ ሉያ ለአብ ምስጋና ይገባል፤ ለወልድም ምስጋና ይገባል፤ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፤ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ፤ ዳግመኛም ደብተራ ኦሪትን እንዴት አድርጎ መሥራት እንዳለበት ለሙሴ አሳየው” ማለት ነው፡፡ በ534 ዓ.ም ኅዳር 6 ቀን ወደ ሰማይ ተነጠቀ፤ በሰማይ ቅዱሳን መላእክት እግዚአብሔርን ልዩ በሆነ ጣዕመ ዝማሬ ሲያመሰግኑ ሰማ፡፡ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ አክሱም ጽዮን ውስጥ ወደ ምሥራቅ በኩል በመዞር ከሰማይ የሰማውን ዝማሬ ዘመረ፤ አርያም ብሎም ሰየመው፡፡ በዚሁም በ538 ዓ.ም ቅዱስ ያሬድ ማኅሌት ጀመረ፡፡ አሁን ድረስ የሚያገለግሉ ድጓ፣ ጾመድጓ፣ ዝማሬ፣ መዋሥዕትና ምዕራፍ የሚባሉ አምስት የዜማ መጻሕፍትም ደርሷል፡፡ ከሰማይ እንደተመለሰ ለመጀመሪያ ጊዜ ጣዕመ ዜማውን ያሰማበት ቦታ “ሙራደ ቃል” ይባላል፡፡
ይህችንም ዜማ “አርያም” አላት፡፡ ይህም ማለት ከመላእክት ወይም ከሰማይ የተገኘች ማለት ነው፡፡ ይህን ዜማ ከፍ አድርጎ ሲያዜም ሰው፣ እንስሳና አዕዋፍ ሁሉ እርሱ ወዳለበት ቦታ ተሰብስበው ልዩውን ሰማያዊን ዜማ ይሰማሉ፡፡ ቅዱስ ያሬድ የግእዝ ብሎም የኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ መሥራችም ነው፡፡ ከቅዱሳን መጻሕፍት የወሰዳቸዉን ርእሰ ጉዳዮች በፈርጅ በፈርጁ እየለየ በድርሰት ሥራዎቹ እንደ ፈርጥ ተጠቅሞባቸዋል፡፡ ብሉያትን ከሐዲሳት፣ ከሊቃዉንት እያጣቀሰ መንፈሳዊ ዜማዎችን ደርሷል፡፡ በመጨረሻ በተወለደ በ75 ዓመቱ በገዳማዊ ሕይወት በኖረበት በሰሜን ተራሮች ደብረ ሐዊ ገዳም ግንቦት 11 ቀን ተሠውሯል፡፡
ገዳማውያን እንኳን ዓለማዊ ደስታ ሊመኙ መንፈሳዊ ክብራቸውም በሰው ፊት እንዲገለጽ አይሹም፡፡ ለኛ ለደካሞቹ ግን ሁሌም ይጸልዩናል፡፡ እኛም ገዳማቸውን እየደግፍን በዓታቸውን እያጸናን ከበረከታቸው እንካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
❤ 48🥱 3
ስለ ማስተር አብነት!
በአሁኑ ወቅት ማስተር አብነት ከበደ በሀገራችን በሚገኝ አንድ ትልቅ ሆስፒታል ህክምናውን እየተከታተለ ይገኛል። በፈጣሪ እርዳታ አሁን ያለበት ሁኔታ ጥሩ የሚባል ነው። የሀኪሞችን ውሳኔ ተከትሎ በቀጣይ ከሀገር ውጪ አልያም በሀገር ውስጥ ህክምናውን ተከታትሎ በቅርቡ ወደ በጎ ስራው ይመለሳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። የሚኖረውን አዲስ ነገር የምናሳውቃቹ ይሆናል። አሁንም በፀሎት አስቡት። እናመሰግናለን።
NB:- በማስተር አብነት እውቅና ለመላው ኢትዮጽያውያን የተላለፈ መልዕክት።
Via brook news
@sheger_press
@sheger_press
🙏 93❤ 26
Фото недоступноПоказать в Telegram
አቶ ጌታቸው ረዳ የፕሪቶርያው የሠላም ሥምምነት እንደ ግዴታ ሊወሰድ ይገባል አሉ።
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትና የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነቱ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ የሚሆነው ሁለቱም ወገኖች ከሽኩቻ ወጥተው እንደ ግዴታ ሲወሥዱት ነው ብለዋል፡፡
ጌታቸው፣ ከስምምነቱ መፈረም በኋላ በትግራይ ፖለቲከኞች መካከል የተፈጠረው ችግር ስምምነቱ መኖር አለበት ወይስ የለበትም የሚል ሳይሆን፣ የትግራይን ሽግግርን ማን ይምራ የሚል እንደሆነ ጠቅሠዋል።
አክለውም ፕሪቶሪያ የፖለቲካ ኃይሎች አንድን ስምምነት "ለቡድናዊ ጥቅም" ሲያውሉት ሰላም ምን ያህል እንደሚሸረሸር በግልጽ አሳይቷልም ብለዋል።
የምዕራብ ትግራይ፣ ራያ እና የፌደራሉ ሠራዊት አወጣጥ ጉዳይ በፕሪቶሪያው ድርድር ያልተካተቱት፣ በእነዚህ ጉዳዮች ሳቢያ ድርድሩ ከከሸፈ በትግራይ ሕልውና ላይ የከፋ መዘዝ ይመጣል በሚል ስሌት መሆኑንም አውስተዋል።
የፌደራል መንግሥቱ ተደራዳሪ ልዑክ ወደፊት በትግራይ የሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር በምዕራብ ትግራይ እና ራያ ላይ "ቁጥጥር" እንዳይኖረው የሚከለክል አንቀጽ ለማስገባት ሞክሮ እንደነበር አቶ ጌታቸው የጠቀሱ ሲሆን፣ ሆኖም ያ አንቀጽ ቢገባ ድርድሩ ይከሽፍ ነበር ብለዋል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 35🤪 5💯 3👍 2😢 1🙏 1
በሱዳን ኮርዶፋን በአርኤስኤፍ የተኩስ ልውውጥ 16 ንፁሃን ዜጎች ተገደሉ
በሱዳን ኮርዶፋን ግዛት በተፈፀመ የመድፍ ጥቃት ቢያንስ 16 ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል። የሀገሪቱ አስከፊ የእርስ በርስ ጦርነት ወደ ሶስተኛ አመቱን ዘልቆ በመግባት የዜጎች ሞት እየጨመረ ይገኛል። የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች (አርኤስኤፍ) እና አጋሮቻቸው በሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጪ ንቅናቄ ውስጥ በደቡብ ኮርዶፋን የሚገኘውን የዲሊንግ የመኖሪያ አካባቢዎች ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ እስከ አርብ ድረስ ግጭቱ ቀጥሏል ሲል የሱዳን ዶክተሮች ኔትወርክ የህክምና ክትትል ቡድን ዘግቧል።
ቡድኑ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሆን ብሎ ከፈጸመው ጥቃት ከተገደሉት መካከል ሴቶች፣ አዛውንቶች እና ህጻናት ይገኙበታል። የሱዳን ጦርነት ከምእራብ ዳርፉር ክልል ወደ እስትራቴጂካዊው ማዕከላዊ ክፍል የተሸጋገረ ሲሆን በዲሊንግ የተፈፀመው ጥቃት ከታህሳስ መጀመሪያ አንስቶ በኮርዶፋን ዙሪያ ከ100 በላይ ንፁሀን ዜጎች የገደለው ጥቃት አካል ነው።
የሱዳን ዶክተሮች ኔትዎርክ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁለቱም የታጠቁ ሃይሎች በሲቪል አካባቢዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እና በግጭቱ የተስተጓገሉ ሰብአዊ አገልግሎት እንዲከፈት ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቋል።ከ50,000 የሚበልጡ ሰዎች በኮርዶፋን ሶስት ግዛቶች ሁከትን ሸሽተው ተሰደዋል።
Dagu
@Addis_News
@Addis_News
❤ 6😢 6
